cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ልዕልት አንድሮሜዳ🌍

ይህ ቻናል የተከፈተው ስነ ፈለግን ለሚወዱና ለሚመረምሩ ብቻ ነው። በዚህ ቻናል ላይ ስለ ህዋ መጤ ፍጡራን(ALIEN)👽፣ስለ ሁለንታ(UNIVERSE)፣ስለ ህብረ ኮከብ(constellation)🌌፣ስለ ጨረቃ🌑 ፣ስለ አነጋጋሪው ቤርሙዳ፣ስለ አስደናቂ ተፈጥሮ ስላለው back hole....እናወጋበታለን። ይህን ቻናል ለሚዷቸው ለወዳጅ ዘመድ ሼር በማድረግ እውቀትን ያስተላልፉ ።

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
495
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
------------ይገምቱ ይሸለሙ---------- አርሰናል VS ማን ዩናይትድ 👉 ህጋችን የሚሆነው ቀድሞ ገሞቶ ግምቱ ለተሳካ አንድ ተከታያችን የሚሆን ሲሆን ጨዋታው የሚጀምረው 12:30 ሲሆን እርሶ እስከ 12:30 መገት ይችላሉ:: 👉 ያስታውሱ ግምታችሁን የምታደርሱን በ @sport4_3_4 ሲሆን ጥያቄውም የሚሆነው ማን ያሸንፋል, ስንት ለስንት, ጎልቹን ማን ያገባል, በስንተኛው ደቂቃ ያገባሉ የሚለው ነው:: 👉ማሳሰቢያ ግምቶዎን እስከ 12:30 ለገመቱ ሰዎች ብቻ ነው የምንሸልመው በተጨማሪም @bisirat_sport12 ይህን ቻናል ካልተቀላቀሉ ግምቶዎ ተቀባይነት የለውም:: ⚡️ሽልማቱ🏆 ሽልማቱ የሚሆነው ግምቱ ለተሳካ አንድ ሰው የሚደግፈውን ክለብ አዲሱን ማሊያ ይሸለማል:: ቻናላችንን ይቀላቀሉ @bisirat_sport12 ከዛም በዚህ👉 @sport4_3_4 ግምቶዎን አስቀምጡልን:: መልካም እድል: ብስራት ስፖርት @bisirat_sport12 @bisirat_sport12 @bisirat_sport12
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🔥 ትምህርት ሚኒስቴር ከ ኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እስከ መስከረም 5 ድረስ የሚቆይ በየቀኑ የሚጠቀሙት ያልተገደበ የኢንተርኔት ፓኬጅ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ‼️ ✅ አላማውም በዚህ ክረምት በሁሉም ደረጃዎች የሚገኙ ተማሪዎች እንዲውም ማህበረሰቡ ለካርድ የሚያወጡትን ገንዘብ በመቀነስ በኦንላይን አጋዥ መማሪዎችን በመጠቀም ንቃተ ህሊናውን እንዲያሻሽል የታለመ ነው:: 📶 የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን ከስር ያለውን ቦት በማስጀመር ለ 30 እና ከዚያ በላይ ለሚሆኑ ወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት ከ 15GB እስከ Unlimited Premium Package መጠቀም ይችላሉ ቦቱን ለማስጀመር ከስር ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ 👇👇 https://t.me/MoE_OfficialBot?start=r00420544540 https://t.me/MoE_OfficialBot?start=r00420544540
Показать все...
Repost from Ethio Fx Trading
Фото недоступноПоказать в Telegram
--------ይገምቱ ይሸልሙ------- 12:30 ቼልሲ ከ ቶተንሃም ጥያቄ የሚሆነው ቼልሲ ከቶተንሃም ማን ያሸንፋል ስንት ለስንት ነው የሚያልቀው ሲሆን መልሱን 👇👇👇👇👇 @sport4_3_3 ነውየምታደርሱን ማሳሰቢያ! መልሱን እስከ 12:20 የመለሱ ሰወች ነው በተጨማሪም ቀድመው የመለሱ 3 ሰዎች ነው አሸናፊ ነው የሚሆኑት::
Показать все...
🌑ግንቦት 8/2014 ዓ.ም. ሙሉ ጨረቃ በኢትዮጵያ በሌሎች ሃገራት ደግሞ የደም ጨረቃ ግርዶሽ ይከሰታል🌒 ✍️ በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ 💥 እንደሚታወቀው ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ የሚከሰተው ጨረቃ ሙሉ ለሙሉ በመሬት ጥላ ውስጥ ስታልፍ ነው፡፡ ሙሉ ለሙሉ በተጋረደችባቸው ሰዓታትም ቀይ ሆና የደም ጨረቃ (ብለድ ሙን) የሚባለውን ቀለም ታሳያለች፡፡ በጨረቃ ግርዶሽ ጊዜ ሰማያዊ ብርሃን በመሬት ከባቢ አየር ሲበተን ቀዩ ብርሃን ብቻ ጨረቃ ላይ ይደርሳል። 💥 የደም ሙሉ ጨረቃ ደም ግርዶሽ Super Blood Moon total lunar eclipse በሃይማኖት፣ በሳይንስ እጅግ ብዙ ምሳሌዎችና ትርጉሞች ያሉት ሲኾን በማዛሮት መጽሐፌ ላይ በስፋት ስለተተነተነ አንባብያን መጽሐፉን አንብበው እንዲረዱት በመጋበዝ በዚህ ላይ ግን ክስተቱን ብቻ ጠቅሼዋለሁ። 💥 ይህ የደም ጨረቃ ግርዶሽ (Super Blood Moon) በምሥራቅ ፓስፊክ፣ በአሜሪካ፣ አንታርክቲካ፣ በአውሮፓ በደንብ ይታያል። በአህጉራችን አፍሪካ ቢታይም በኢትዮጵያ ግን አይታይም ምክንያቱም በኢትዮጵያ ማታ 12:02 ላይ ስለምትጋረድ በዚህ ሰዓት ደግሞ ጨረቃ ከአድማስ በታች በመኾና ለማየት አዳጋች ስለሚኾን ነው። 💥 ቢሆንም ግን በሀገራችን ሰኞ ግንቦት 8 ሙሉ ጨረቃ በመሆኗ ወደ መሬትም በጣም በመጠጋቷና መጠኗና ብርሃኗም ከወትሮው ስለሚጨምር “ሱፐርሙን” (ታላቋ ጨረቃ) super moon ተብላ የምትታወቅበት ወቅት ላይ መሆኗ ነው፡፡ 💥 በተለይ ጨረቃን ፎቶ ማንሣት እንደኔ ለሚወዱ ውብ የሆነ የሙሉ ጨረቃን ፎቶ ለማንሣት ይህ የሙሉ ጨረቃ (ፉል ሙን ፌዝ) እና ሱፐር ሙን ወቅት ከሁሉም ጊዜ በተለየ በጣም ተመራጭ ጊዜ ነው፡፡ 💥 ፀሐይ እንደጠለቀች ምሽት ላይ ጀምሮ እስኪነጋ ድረስም ደምቃ አብርታ ጎልታ ስለምትታይ ለአድናቂዎችና ለተመልካቾች ጥሩ ጊዜ ይሆናልና ፎቶ እያነሣችሁ መደሰት ትችላላችሁ፡፡ 💥 ግርዶሹ በሚታይባቸው በምሥራቅ ፓስፊክ፣ በአሜሪካ፣ አንታርክቲካ፣ በአውሮፓ ሀገራት ያላችሁ ደግሞ ደመና ከሌለ በስተቀር ግርዶሹ በምሽት ስለሚታይ የሚታይበትን Space.com በመጠቀም ያላችሁበትን ከተማ በመሙላት ማታ እያያችሁ መደሰት ትችላላችሁ።
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
🕌EID MUBAREK 📿 اد مبرك ☪ ለሁሉም ሙስሊም ወንድም እህቶቼ እንኳን ለተከበረው ለ1443ኛ ኢድ አል ፈጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን , በዓሉ የሰላም፤የፍቅር፤የመተሳሰብ ይሁንልን!!
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
ዛሬ ምሽት “ቬነስ እና ጁፒተር ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠጋግተው እንደሚታዩ” የህዋ ሳይንቲስቶች አስታወቁ! የህዋ ሳይንቲስት እና ሶሳይቲ ፎር ፖፑላር አስትሮኖሚ ውስጥ ዋና የከዋክብት ተመልካች ፕ/ር ሉሲ ግሪን ፣ ክስተቱ ለከዋክብት አጥኚዎች ብቻ ሳይሆን ለተቀረው ማኅበረሰብም አስደናቂ ብለዋል፡፡ሁለቱ ደማቅ ፕላኔቶች ዛሬ ምሽት ለመነካካት ጥቂት እስከሚቀራቸው ድረስ ነው የሚቀራረቡት።ፕላኔቶቹ በየዓመቱ የሚቀራረቡ ቢሆንም፤ ዘንድሮ ግን ከመቼውም በበለጠ የሚጠጋጉበት ነው ተብለዋል፡፡ ይህንን አይነት ክስተት እስከ ፈረንጆቹ 2039 ድረስ በድጋሚ እንደማያጋጥምም ነው የተገለጸው። ክስተቱን ዛሬ ምሽት በዐይን ወይም በአጉሊ መነጽር መመልከት እንዳሚቻልም ነው የህዋ ሳይንቲስቶች መረጃ የሚያመለክተው፡፡
Показать все...
ኤለን መስክ፤ ስታርሊንክ የተሰኘው የበይነ መረብ ፕሮጀክቱ ሳተላይቶች ሕዋን እያጣበቡ ነው መባሉን አስተባብሏል። በምድር ምህዋር "በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ" ሳተላይቶች መንቀሳቀስ ይችላሉ ሲል ለፋይናንሻል ታይምስ ጋዜጣ ተናግሯል። ኤለን ይህን አስተያየት የሰጠው የዓለም አቀፉ ሕዋ ምርምር ጣቢያ ኃላፊ "መስክ የሕዋ ኢንዱስትሪ ሕግ ራሳቸው ናቸው የሚያወጡት" ካሉ በኋላ ነው። በያዝነው ሳምንት ቻይና ሳተላይቶቼ ከስታርሊንክ ሳተላይቶች ጋር ሊጋጩ ነበር ስትል ቅሬታ አቅርባለች። "ሕዋ ማለት እጅግ ሰፊ ሥፍራ ነው፤ ሳተላይቶች ደግሞ ከዚህ አንፃር በጣም ኢምንት( ትንሽ ) ናቸው" ብሏል መስክ። የስፔስኤክስ ባለቤቱ ኤለን መስክ የእሱ ድርጅት ሳተላይቶች ሌሎች ድርጅቶችን ከገበያው እያስወጡ ነው ስለመባሉም ማስተባበያ ሰጥቷል። "ይህ ሌሎች እንዳይንቀሳቀሱ የምናደርግበት ዘርፍ አይደለም። እኛ ማንም ሥራውን ከመሥራት ወደ ኋላ እንዲል አላደረግንም። እንድናደርግም አይጠበቅም።" "በጥቂት ሺዎች የሚቆጠሩ ሳተላይቶች ምንም ማለት አይደሉም። ምድር ላይ ጥቂት ሺህ መኪናዎች አሉ እንደማለት ነው" ሲል ለጋዜጣው ተናግሯል። የአውሮፓ ሕዋ ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ጆሴፍ አስክባቸር ስታርሊንክ የሚያስወነጭፋቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የኮሚዩኒኬሽን ሳተላይቶች ለተወዳዳሪዎች አስጊ ናቸው ሲሉ በቅርቡ ተናግረው ነበር። ሌሎቹ ባለሙያዎች ደግሞ በሳተላይቶች መካከል የሚኖር ግጭትን ለማስቀረት ርቀታቸውን ጠብቀው ነው መንሳፈፍ ያለባቸው ይላሉ። ሳይንቲስቶች ከዚህ በፊት በሕዋ ላይ የሳተላይቶች ግጭት እንዲቀንስ የዓለም መንግሥታት መረጃ እንዲያጋሩ ጠይቀው ነበር። ሳይንቲስቶቹ፤ መንግሥታት በግምት ሕዋን እየዞሩ ነው ስለሚባሉት 30 ሺህ ሳተላይቶች እንዲሁም ስብርባሪዎች መረጃ ማቅረብ አለባቸው ይላሉ። ቻይና የስታርሊንክ ሳተላይቶች የእኔን ሳተላይቶች ሊገጩ ለጥቂት ነው የተረፉት ካለች በኋላ ኤለን መስክ የመገናኛ ብዙሃንና የማኅበራዊ ድር አምባው መነጋገሪያ ሆኖ ነበር። ቻይና፤ ሁለት ጊዜ ሳተላይቶቿ ከስታርሊንክ ሳተላይቶች ጋር ከመጋጨት መትረፋቸውን ገልጣለች። ቻይና ለተባበሩት መንግሥታት የሕዋ ጉዳዮች ቢሮ ባስገባችው ደብዳቤ ላይ እንዳሰፈረችው ሁኔታው የተፈጠረው ባለፈው ዓመት ሐምሌ ነው። "የቻይና ሕዋ ጣቢያ ለደኅንነት በማለት የግጭት ማስወገድ መንገዶችን ተጠቅሟል" ሲል የጣቢያው ድረ-ገፅ አስነብቧል። ቻይና በኤለን መስክ ላይ ያቀረበችው ጥያቄ እስካሁን በገለልተኛ አካል አልተጣራም። ቻይና፤ ዩናይትድ ስቴትስ የሕዋ ሕግጋትን በመጣስ የጠፈርተኞችን ሕይወት አደጋ ላይ እየጣለች ነው ስትልም ወቅሳለች። የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባዩ ዣዎ ሊጂያን አሜሪካ ኃላፊነት እንዲሰማት ሃገራቸው ጥሪ እንደምታቀርብ ገልጠዋል። ስፔክስ የተባለው የኤለን መስክ ድርጅት እስካሁን 1900 ሳተላይቶችን በስታርሊንክ ኔትዎርክ ስም አምጥቋል። https://t.me/jAndromeda
Показать все...
ልዕልት አንድሮሜዳ🌍

ይህ ቻናል የተከፈተው ስነ ፈለግን ለሚወዱና ለሚመረምሩ ብቻ ነው። በዚህ ቻናል ላይ ስለ ህዋ መጤ ፍጡራን(ALIEN)👽፣ስለ ሁለንታ(UNIVERSE)፣ስለ ህብረ ኮከብ(constellation)🌌፣ስለ ጨረቃ🌑 ፣ስለ አነጋጋሪው ቤርሙዳ፣ስለ አስደናቂ ተፈጥሮ ስላለው back hole....እናወጋበታለን። ይህን ቻናል ለሚዷቸው ለወዳጅ ዘመድ ሼር በማድረግ እውቀትን ያስተላልፉ ።

ሰሞኑን ስላልፖሰትን ይቅርታ እንጠይቃለን ከነገ ጀምሮ በአዲስ መልክ ወደ ስራ እንገባለን https://t.me/jAndromeda
Показать все...
ልዕልት አንድሮሜዳ🌍

ይህ ቻናል የተከፈተው ስነ ፈለግን ለሚወዱና ለሚመረምሩ ብቻ ነው። በዚህ ቻናል ላይ ስለ ህዋ መጤ ፍጡራን(ALIEN)👽፣ስለ ሁለንታ(UNIVERSE)፣ስለ ህብረ ኮከብ(constellation)🌌፣ስለ ጨረቃ🌑 ፣ስለ አነጋጋሪው ቤርሙዳ፣ስለ አስደናቂ ተፈጥሮ ስላለው back hole....እናወጋበታለን። ይህን ቻናል ለሚዷቸው ለወዳጅ ዘመድ ሼር በማድረግ እውቀትን ያስተላልፉ ።

ኤለን መስክ ያስወነጨፋት ሮኬት ከጨረቃ ጋር ልትጋጭ ነው የኤለን መስክ ሕዋ ምርምር ተቋም ያስወነጨፋት አንዲት ሮኬት ከጨረቃ ጋር ተጋጭታ ልትፈነዳ እንደምትችል ተሰምቷል። ፋልከን 9 የተሰኘችው ሮኬት ወደ ሕዋ የተወነጨፈችው በፈረንጆቹ 2015 ሲሆን ነገር ግን የያዘችው ነዳጅ በመገባደዱ ምክንያት ተልዕኮዋን ጨርሳ ወደ ምድር ከመመለስ ይልቅ ሕዋ ላይ ስትዋልል ነበር። ጠፈርተኛው ጆናታን ማክዶዌል፤ ከጨረቃ ጋር የተጋጨች የመጀመሪያዋ ከቁጥጥር ውጭ የሆነች ሮኬት ትሆናለች ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር መጋጨቷ ያለው ፋይዳ ይህን ያህል የሚባል አይደለም። ከሰባት ዓመታት በፊት ሥራዋን ጨርሳ ሕዋ ላይ የተረሳችው ሮኬት ከ1.6 ኪሎ ሜትር በላይ ርቀት አዳርሳለች። ስፔስኤክስ የተባለው የኤለን መስክ የሕዋ ምርምር ተቋም ወደፊት ሰዎች በሌሎች ፕላኔቶች ላይ እንዲኖሩ ማመቻቸት የሚል ዓላማ አለው። ሮኬቷ ከ2015 ጀምሮ በተለያዩ የምድር፣ የጨረቃና የፀሐይ የስበት ኅይሎች አቅጣጫዋን እየቀያየረች ቆይታለች ይላሉ ጠፈርተኛው። "የስበት ሕግን ተከትላ ከጥቅም ውጭ ሆና ነበር ማለት ይቻላል።" ይህች ሮኬት ብቻ ሳትሆን ለተልዕኮ ተስወንጭፈው ዕቅዳቸውን ያሳኩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሮኬቶች ሕዋ ላይ እየዋለሉ ይገኘሉ። "ባለፈው አስር ዓመት ከቁጥጥራችን ውጭ የሆኑ ቢያንስ 50 ትላልቅ ሮኬቶች አሉ። ከዚህ በፊትም ሳናውቀው ተፈጥሮ ሊሆን ይችላል። ይሄኛው የመጀመሪያው የታወቀ ክስተት ይሆናል ማለት ነው" ይላሉ ማክዶዌል። የፋልከን 9 ወደ ጨረቃ መገስገስ ሊታወቅ የቻለው ጋዜጠኛ ኤሪክ በርገርና የዳታ ተንታኙ ቢል ጌሪ ባደረጉት ክትትል ነው። ሮኬቷ፤ በሚቀጥለው የፈረንጆቹ ወርሃ መጋቢት አራት ከጨረቃ ጋር እንደምትጋጭ ተገምቷል። "4 ቶን የምትመዝን ከኋላ ሞተር ያዘለች ብረት ማለት ናት። ይህን ያህል ክብደት ይዛ በሰዓት ከ8 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር በላይ እየተጓዘች ስትጋጭ የሚፈጠረው ነገር አስደሳች አይሆንም" ሲሉ ያክላሉ። ሮኬቷ ከተጋጨች በኋላ የጨረቃ መልክዓ ምድር ላይ አነስ ያለ ሰው ሰራሽ ጉደጓድ ትፈጥራለች። ሶፍትዌር ተጠቅሞ ለምድር የቀረቡ ሕዋ ላይ ያሉ ቁሶችን የሚከታተለው ቢል ጌሪ ሮኬት መጋቢት 4 ከጨረቃ እንደምትጋጭ ገምቷል። በፈረንጆቹ 2009 ፕሮፌሰር ማክዶዌልና ሌሎች ጠፈርተኞች መሰል ነገር ቢፈጠር ምን ሊከሰት ይችላል የሚለውን ሐሳብ በቤተ ሙከራ አዳብረውታል። ይህ ማለት ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር ስትጋጭ ሳይንቲስቶች ብዙም የሚማሩት አዲስ ነገር የለም ማለት ነው ይላሉ ፕሮፌሰሩ። አክለው አሁን ምንም እንኳ ሕዋ ላይ እየዋለሉ ያሉ ቁሶች እየሄዱ ሲጋጩ ችግር ባይፈጥሩም ወደፊት ግን አደጋ ሊሆኑ ይችላሉ ይላሉ። ሮኬቷ ከጨረቃ ጋር እስክትጋጭ ባለው ጊዜ የስበት ህግን ተከትላ ሕዋ ላይ ትንሳፈፋለች።
Показать все...