cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ቢደአ ሁሉ ጥመት ነው!

Больше
Страна не указанаЯзык не указанКатегория не указана
Рекламные посты
182
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

ለኡማው አሳቢዎቹ ብልጦቹ የሳውዲ ኡለማዎች፡፡ ============================== የሳኡዲ ኡለሞዎች አልሐምዱሊላህ ብልጦች ናቸው ማንም አላዋቂ ያለውን ቢላቸው የሰይጣንንም ሆነ የአሜሪካን ህልም አያስፈፅሙም፡፡ አላዋቂዎች እና ስሜት የሚጋልባቸው ሰዎች አንድን ሰው “ኡለማ ደፋርና የማይፈራ” የሚሉት ደም የሚያፋስ፣ ሙስሊሞችን ለችግር የሚዳርግ፣ ሙስሊም አገራትን ለጠላት በር ለመክፈት ሰበብ የሚሆንን ግለሰብ ነው፡፡ ሳውዲ እና ኡለማዎቿ አላዋቂዎች እንደሚሉት የአሜሪካ ወዳጆች አይደሉም፡፡ አላዋቂዎች የአሜሪካ ምኞት ምን እንደሆነ ቢያውቁ ለዚህች ውድ የተውሒድ አገር ጥብቅና ይቆሙ ነበር፡፡ ነገር ግን አለማወቅ ከባድ በሽታ ነው፡፡ አለማወቃቸውን አለማወቅ ሲደረብበት ደግሞ የበሽታም በሽታ ነው፡፡ አሜሪካ ሳውዲን አራት ቦታ እንድትከፋፈል እና ልፍስፍስ አገር እንድትሆን ትመኛለች፡፡ ከመመኘትም አልፎ ሙከራዎችን አድርገዋል፡፡ ሌሎች አገራት ላይ ሰልፍ እንደሚቀሰቀሰው ሳውዲም ላይ ሰልፍ ተብሎ ተቀስቅሶ ይህች የተቀደሰች አገር ወደ ብጥብጥ ገብታ እንድትፈራርስ ይፈልጋሉ፡፡ የነብያት ወራሾች፣ ለዲናቸው ታማኝ የሆኑት እነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎች ህዝባቸውን ባለው የሙስሊም መሪ ላይ አምፀው እንዳይወጡ፣ ህዝቡ መሪው ላይ ለሚያየው ስህተት ዱኣ እንዲያደርግ እና እንዲታገስ በማድረግ ይሀው አገሪቷ ከአላህ በታች በነዚህ ብርቅዬ ኡለማዎች ሙስሊሞች ደማቸው ሳይፈስ ጠላትም አይኑ እንዳፈጠጠ ቀረ፡፡ አላህ ሳውዲንም ይሁን ሌሎች የሙስሊም አገራትን ከውስጥም ከውጭም ጠላት ይጠብቃቸው፡፡ አስገራሚው ደፋር ተብዬዎቹ የፈተና ቀስቃሾች በሰላም ካሉበት ተቀምጠው ሙስሊም አገራትን እና ህዝባቸውን አሁን ላሉበት አደጋ ዳርገዋል፡፡ የጠላትንም አላማ አሳክተዋል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለሙስሊሞች መሪን አስመልክቶ የመከሩት ይህን ነበር፡፡ - “የሀበሻ ባሪያም ቢሾምባችሁ ስሙት ታዘዙት”፣ - “እጅህን ጠምዝዞ አንገትህን ይዞ ገንዘብህን ቢቀማህ ሰላትን እስካቋቋሙ ድረስ ……. ስሙ ታዘዙ”፣ - ሰሃባዎች የአላህ መልክተኛን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ሲሉ ጠየቁ “የእሱን ሀቅ የሚጠይቀን የእኛን ሀቅ የማይሞላልን መሪ ካጋጠመን ምን እናድርግ” የአላህ መልክተኛም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ስሙት ታዘዙት” ሲል ይግባኝ የሌለውን ፍርዳቸውን ሰጡ፡፡ እናም ሌሎች ትምህርቶችንም ሰጥተዋል፡፡ አሳዛኙ ዛሬ የነ አሜሪካ ጠላት ነን እያሉ የነ አሜሪካን ህልም የሚያስፈፅሙ በኢስላም ስም የሚንቀሳቀሱ መኖራቸው ነው፡፡ አገራችንም ላይ ይሁን ከአገራችን ውጭ የሳውዲ ለሙስሊሙ መልካም አሳቢ የሆኑትን ኡለሞች የሚያከፍሩና የሚወርፉትን ተመልከቷቸው በኩፍር እና ሺርክ የተሞሉትን ሺአ ራፊዳዎች ምንም ሲሉ አትሰሟቸውም፡፡ ምክንያቱም እነሱ ዘንድ ለአላህ ብሎ መውደድ እና ለአላህ ብሎ መጥላት የለም፡፡ ስልጣን ፍለጋ ማድረግ ያለባቸውን ሁሉ ያደርጋሉ፡፡ እንዲያውም የግብፁ ኢኽዋን መሪ ሙሐመድ ሙርሲ ስልጣን ሲይዝ ሰሃባዎችን የሚያከፍሩ፣ በኩፍር የተጨማለቁ፣ ቀን እና ለሊት ሰሃባዎችን የሚራገሙትን የኢራን ሺአዎች ግብፅ ላይ በሩን ከፈተላቸው አላህ እሳት ለቀቀበት፡፡ ሰው የዘራውን ያጭዳል፡፡ አሜሪካን ተመልከቱ ኢራንን ላይ ላዩን አሸባሪ ትላታላች ግን የሱንዬችን አገር ኢራቅ ወራ ስልጣኑን ለኢራን አስረክባ ነው የወጣችው፡፡ አረ የአእምሮ ባለቤቶች እንንቃ፡፡ ሳውዲ እና የሳውዲ መሪዎች ልንከላከልላቸው ይገባል ስንል ከስህተት የፀዱ ናቸው እያልኩ አይደለም፡፡ ነገር ግን ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሙስሊም መሪ ሲያጠፋ ለብቻው ዞር ተደርጎ እንደሚመከር ስለነገሩን እኛም የሙስሊም መሪዎችን ስህተት አደባባይ ላይ አይለቀቅም የምንለው፡፡ ተወደደም ተጠላም አለም ላይ ተውሒድ እና ሱና የበላይ የሆነባት ሺርክና ቢድኣ የተዋረደባት አገር እንደ ሳዉዲ የለም፡፡ አላህ ሳውዲንም አሁን ካለችበት የተሻለ ያድርጋት፣ ሌሎች ሙስሊም አገሮችንም አላህ ወደሚፈልገው መልካም ይምራቸው፡፡ የሳውዲ እንቁዎች ግን ሰው ያለውን ቢላቸው ሰይጣንን እና መሰሎቹን እየተቃረኑ ኢስላም የሚለውን በግልፅ ያስተምራሉ፡፡ ኡለማ ያልሆኑ በዲን ስም የሚንቀሳቀሱት ደግሞ ሰይጣን እየጋለባቸው የጠላትን አጀንዳ እያስፈፀሙ ሙስሊሞችን እና ሙስሊም አገራትን ለመከራ ይዳርጋሉ፡፡ በነገራችን ላይ አገራችንም ላይ ይሁን ሌሎች ቦታዎች ላይ ስሜታቸውን አምላኪዎች የሳውዲ ኡለሞችን “የንጉሳዊያን ስልጣን ጠባቂዎች”፣ “የአምባገነኖች ምርኩዞች”፣ “የቤተሰመንግስት ፍርፋሪ ለቃቃሚዎች” እንዳሏቸው ሁሉ ነብዩ ሙሐመድን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን ሊሏቸው ነው? ምክንያቱም የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) “ከእኔ በኋላ የማያዝኑላችሁ መሪዎች ይመጣሉ… ስሟቸው ታዘዟቸው” ብለዋልና ? ? ? ? ? ? እኮ መልስ ይስጡና ??? የነዚህ ሰዎች ምሳሌ አላህ ቁርኣን ላይ እንዲህ ሲል እንደገለፃቸው ነው وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡ እነሱ አሳማሪ ነን የሙስሊሙ መብት ያስጨንቀናል ቢሉም አላህ እንዲህ ሲል መልስ ሰጣቸው أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡ አላህ ሆይ! በዲን ስም ዲን ከመናድ በአንተው እንጠበቃለን፡፡ ሀቁን መንገድ ምራን በጠላቶቻችን ላይ ድልን አጎናፅፈን፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት ሁሉ መደምረሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡
Показать все...
ፆመን ውለን ስናበቃ ያለ አጅር ባዶዋችን እንዳንገባ እንጠንቀቅ!!! ⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁽⁾⁼ በዚህን ጊዜ አላህ ያዘነለት ሰው ሲቀር የብዙ ሰዎችን ተግባርና ምላስ ስናይ ፆም ማለት:- በቃ ከምግብና ከሚጠጡ ነገሮች መታቀብ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ከባድ የሆነ አደጋ ነው!። አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:- عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ :- " مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ وَالْجَهْلَ، فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ". صحيح البخاري وغيره “የውሸት ንግግርን በእርሱም መስራትን እና ሞኛ ሞኝነትን (መጃጃልን) ያልተወ ሰው ምግቡን እና መጠጡን ቢተውም አሏህ ጉዳዩ አይደለም” ቡኻሪና ሌሎችም ዘግበውታል። ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:- «ፆመኛ ማለት አካሎቹ ከሀጢአት የጸዱ፤ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤ ሆዱን ከምግብ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነውፆመኛ ከተናገረ፣ ፆሙን በማይጎዳ መልኩ ይናገራል፣ ስራ ከሰራ ፆሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል። ፆመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው። ከፆመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች ከቅጥፈት፣ ውሸት፣ ከጥመት እና በደል ሁሉ ሰላም ይሆናል። ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ፆም ማለት፣ ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ፆም አይባልም። ፆም ማለት አካላትን ከሀጢአት እና ሆድን ከምግብና ከሚጠጣ ነገር በመታቀብ መፆም ነው። ምግብና የሚጠጣ ነገር ፆምን እንደሚያበላሽ ሁሉ ሀጢአትም የፆምን ምንዳ ያበላሻል፣ ውጤቱን ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ፆም እንዳልፆመ ተደርጎ ይታሰባል።» [አልዋቢሉ አስ-ሶይብ 31-32] ✍🏻 ኢብን ሽፋ: ረመዷን 3/1441 ዓ.ሂ https://t.me/joinchat/Sn62xstw8Nvq1swV
Показать все...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ረመዷንን ፆመው ከሚጠቀሙት ያድርገን!!! ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

✍️Sadat Kemal Abu Nuh የእምነት መሰረቶችን ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ማስገንዘብ (ማስታወስ):: አላህ ይባርካችሁ አሉ በሚባሉ ሚድያዎች ለከተማም ለገጠሩም፤ አገር ውስጥም ላለው ውጭ ተቀማጭ ሼር ያርድጉት፡፡ ሃይማኖታዊ እውቀት በወንድም በሴትም ላይ ግዴታ ነው፡፡ تلقين أصول العقيدة العامة የእምነት መሰረቶችን ለአጠቃላይ ሙስሊም ማህበረሰብ ማስገንዘብ (ማስታወስ) بسم الله الرحمن الرحيم እጅግ በጣም ሩህሩህ እና እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው አላህ ስም እጀምራለሁ፡፡ إذا قيل لك: من ربك؟ ጌታህ ማን ነው? ከተባል فقل: ربي الله ጌታዬ አላህ ነው በል፡፡ فإذا قيل لك: ما معنى الرب؟ ረብ የሚለው የአረብኛ ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው? ከተባልክ فقل: المعبود المالك المتصرف. የሚመለክ (ተመላኪ)፤ ገዢ (ንጉስ)፤ አስተናባሪ ማለት ነው በል፡፡ فإذا قيل لك: ما أكبر ما ترى من مخلوقاته؟ ትልቁ ከምታያቸው አላህ ከፈጠራቸው ፍጡራን ምንድን ነው? ከተባል فقل: السموات والأرض. ሰማያት እና ምድር ናቸው በል፡፡ فإذا قيل لك: بماذا تعرف ربك؟ (ጌታህን) በምንድን ነው የምታውቀው? ከተባልክ فقل: أعرفه بآياته ومخلوقاته. በበርካታ ፍጡራኖቹ እና በበርካታ ተአምራቶቹ (በአንቀፆቹ) አቀዋለሁ፡፡ وإذا قيل لك: ما أعظم ما ترى من آياته؟ ከበርካታ ተአምራቶቹ (ምልከቶቹ) በጣም ትልቁ ምንድን ነው? ከተባልክ فقل: الليل والنهار، ለሊት እና ቀን ናቸው በል፡፡ والدليل على ذلك قوله تعالى: የዚህም ማስረጃችን የላቀ ከፍ ያለው የአላህ ቃል ነው {إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ اسْتَوَى عَلَى الْعَرْشِ يُغْشِي اللَّيْلَ النَّهَارَ يَطْلُبُهُ حَثِيثاً وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ وَالنُّجُومَ مُسَخَّرَاتٍ بِأَمْرِهِ أَلا لَهُ الْخَلْقُ وَالأَمْرُ تَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ} ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ከአርሽ በላይ ሆነ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡ فإذا قيل لك: ما معنى الله؟ አላህ የሚለው ቃል ትርጉሙ ምንድን ነው? ከተባልክ فقل: معناه ذو الألوهية والعبودية على خلقه أجمعين. የአምላክነት ባለቤት እና ከፍጡራኑ ሁሉ የተመላኪነት ባለቤት የሆነው ነው በል፡፡ فإذا قيل لك: لأي شيء الله خلقك؟ አላህ ለምንድን ነው የፈጠረህ? ከተባልክ فقل: لعبادته. እሱን ለማምለክ (ለመገዛት) ነው በል فإذا قيل لك: أي شيء عبادته؟ እሱን ማምለክ ማለት ምን ማለት (ምንድን) ነው? ብትባል : فقل توحيده وطاعته. እሱን በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ እና በጥቅሉ የእሱን ትዕዛዝ ማክበር ነው በል፡፡ فإذا قيل لك: ما هؤ الدليل على ذلك؟ በዚህ ላይ ማስረጃው ምንድን ነው? ከተባልክ فقل: قوله تعالى "وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالأِنْسَ إِلاَّ لِيَعْبُدُونِ" ‹‹አጋንንትንም ይሁን የሰው ዘርን አልፈጠርኩም እኔን በብቸኝነት ሊያመልኩኝ እንጂ›› የሚለው የላቀው ከፍ ያለው የአላህ ቃል ነው በል፡፡ وإذا قيل لك: أي شيء أول ما فرض الله عليك؟ የመጀመሪያ አላህ ባንተ ላይ ግዴታ ያደረገው ነገር ምንድን ነው? ብትባል فقل: كفر بالطاغوت وإيمان بالله، በጣዖት መካድ እና በአላህ ማመን ነው በል፡፡ والدليل على ذلك قوله تعالى ለዚህም ማስረጃው ከፍ ያለው የላቀው አላህ ቃል ነው :{لا إِكْرَاهَ فِي الدِّينِ قَدْ تَبَيَّنَ الرُّشْدُ مِنَ الْغَيِّ فَمَنْ يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِنْ بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَى لا انْفِصَامَ لَهَا وَاللَّهُ سَمِيعٌ عَلِيمٌ}. በሃይማኖት ማስገደድ የለም፡፡ ቅኑ መንገድ ከጠማማው በእርግጥ ተገለጠ፡፡ በጣዖትም የሚክድና በአላህ የሚያምን ሰው ለርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ዘለበት በእርግጥ ጨበጠ፡፡ አላህም ሰሚ ዐዋቂ ነው፡፡ فإذا قيل: ما هؤ العروة الوثقى؟ ጠንካራዋ ዘለበት ማለት ምን ማለት ናት? ብትባል فقل: لا إله إلا الله. ላኢላሃኢለላህ (ከአላህ በስተቀር በሃቅ የሚመለክ የለም) (የተውሂድ ቃል) ናት በል፡፡ ومعنى "لا إله" نفي و " إلا الله " إثبات. ‹‹ላኢላሃ›› የሚለው ትርጉም አምልኮ የሚገባው እንደሌለ ፡፡ ‹‹ኢለላህ›› የሚለው ቃል ደግሞ እውነተኛ አምልኮ ለአላህ ብቻ እንደሆነ ማረጋገጥ ነው፡፡ فإذا قيل لك: ما هؤ أنت نافي، وما هؤ أنت مثبت؟ አንተ ውድቅ የምታደርገው ምንድን ነው? የምታረጋግጠውስ ምንድን ነው? ብትባል فقل: نافي جميع ما يعبد من دون الله، ومثبت العبادة لله وحده لا شريك له. ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ነገሮችን ባጠቃላይ ውድቅ አደርጋለሁ፡፡ አጋር ለሌለው እና ብቸኛ ለሆነው አላህ አምልኮን አፀድቃለሁ፡፡ فإذا قيل لك: مالدليل على ذلك؟ በዚህ ላይ ማስረጃው ምንድን ነው? ብትባል فقل: قوله تعالى ከፍ ያለው የአላህ ቃል ነው በል :{وَإِذْ قَالَ إِبْرَاهِيمُ لأَبِيهِ وَقَوْمِهِ إِنَّنِي بَرَاءٌ مِمَّا تَعْبُدُونَ} (ሙሐመድሆይ!) ኢብራሂም ለአባቱ እና ለህዝቦቹ ያለውን አውሳላቸው፤ እኔ እኮ ከምታመልኩት ነገር ሁሉ የጠራሁኝ ነኝ፡፡ هذا دليل النفي، ይሄ ውድቅ የማድረግ ማስረጃ ነው ودليل الإثبات {إِلاَّ الَّذِي فَطَرَنِي}. (አምልኮን ለአላህ ብቻ) የማፅደቅ ማስረጃው ያ የፈጠረኝ ጌታ ሲቀር (ብቸኛው ፈጣሪ ብቸኛው ተመላኪ ነው) فإذا قيل لك: ما هؤ الفرق بين توحيد الربوبية وتوحيد الألوهية؟ (አላህን) በጌትነቱ ብቸኛ ማድረግ እና በአምላክነቱ ብቸኛ ማድረግ ልዩነቱ ምንድን ነው? ብትባል فقل: توحيد الربوبية إفراد الله بأفعاله، مثل الخلق والرزق، والإحياء، والإماتة، وإنزال المطر وإنبات النبات، وتدبير الأمور... ይቀጥላል t.me/sadatkemalman
Показать все...
ሳዳት ከማል ማነው

ሳዳት ከማል ማነው? እውን ሳዳት ከማል ተሳዳቢ ነው ? አንድ አውዲዮ ሳይሰሙ ሰው በጭፍን አይናገሩ የራሱን አውዲዮዎች አድምጠው ይፍረዱ ፍትሃዊነት ማለት ይህ ነው አደራ ሳያዳምጡ ሳይሰሙ አያውሩ አድል ለራስ ነው አላህ ሆይ ሀቅን በሀቅነቱ አሳየን የምንከተለውም አድርገን ባጢልን በባጢልነቱ አሳየን የምንረቀውም አድርገን

303123270621812.m4a15.70 MB
⭕ ዲናችን ከናንተ ስሜት የጠራ ነው ሱዑዲያን ለመወረፍ በተንሻፈፈ ሚዛን አትለኩ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ የተውሒድ ስንፀ ሐሳብን በቅጡ ካልተረዳን ፣ የላኢላሃ ኢለላህ ትስስርን በአግባቡ ካልተገነዘብን ፣ የኢስላምን መርሕና መመሪያ በተገቢው መልኩ ማወቅ ከተሳነን ,,,,, ለሌሎች ያለን ውዴታና ጥላቻ በግል ጥቅማችንንና ጉዳት ላይ የተመሰረተ ይሆናል።በዚህ ግዜ ለሌሎች የምንሰጠው ቦታ የውዴታና ወንድምነት ቅብ ቢኖረውም ሐቂቃው ግን ሌላ ነው።ካልገባን ሲገባን ይገባናል ,,,, ለዚህ ነው በርካታ ሰወች ትስስራቸውና ቅርርባቸው በንፁህ የተውሒድ ገመድ ላይ ሳይመሰረት ይቀርና ከግዜያት በአንዱ ቀን በራሳቸው አጀንዳ ተባልተው ሆድና ጀርባ ሆነው ሚቀሩት።ይህ አጉል ልማድ ሲያድግ ወደ ሙስሊም አገሮች ሕዝቦችና መሪዎቻቸውንም ያለ ተገቢ መንገድ መጎንተል ይወስደናል። እንደምናስታውሰው "በፊት በሱዑዲያ ያለው ስርኣት ባህል እንጂ ሸሪዓ አይደለም።ሴቶች መሸፋፈናቸው ተገቢ አይደለም ,,,, " እያሉ ጆሮኣችንን ያደነቁሩ እንዳልነበር ፤ ዛሬ ደግሞ ክፍተት አለ ብለው ሲያምኑ " ሸሪዓውን ጣሉት ፣ መሸፋፈን ቀነሰ ፣ በዚህ ገባ በዚያ ወጣ ,,, " እያሉ የአዞ እንባ ያጎርፋሉ።ደብል ስታንዳርዶች ሆይ ለማያቅሽ ታጠኝ ,,,,,, ጥቅምና ኪሳራችንን እያሰላን ፣ በኢስላም አጥር ስር ተወሽቀን የእርግማንና የስድብ ናዳ ማውረድ ተገቢ አይደለም።ቢያንስ ይህን ክፉ ባህሪያችንን ከኢስላም ነጥለን ራሳችንን ችለን እንውረግረግ።አስተውሉ ሙስሊም መሪዎች ላይ በይፋ ምላሳቸውን ሚያረዝሙ ብዙ ሰወች በዲን ዕውቀትም ሆነ ተግባር በርካታ ክፍተት ያለባቸው ናቸው በስነምግባርም እንደዛው።አስገራሚ ጥፋቶችና ወንጀሎች ላይ ተዘፍቀዋል።አንዳንዶቹ መሰረታዊ የእስልምናን መመሪያ በሚጥስ መስመር ውስጥ ይጓዛሉ።እራሳቸውን ለማስተካከል ችግራቸውንም ለመቅረፍ የማይታይባቸው ትግል ሙስሊም አገራትንና መሪዎችን ለመዘርጠጥ ግን ግንባር ተሰላፊ ናቸው። ወንድሞቼ ሆይ እንደ እምነታችን አስተምህሮ የትኛውም አገርም ሆነ ሙስሊም መሪ ከስህተት አይፀዳም።ደረጃው ቢለያይም በታሪክ የተለያዩ ወንጀልና ስህተት ላይ የተዘፈቁ ሙስሊም መሪዎች ነበሩ።ግና ይህን አስመልክቶ የኛ ግብረ መልስና አቋም ምን መምሰል እንዳለበት ኢስላም በግልፅ አስቀምጦልናል።ከኛ ሚጠበቀው ይህን እንደ ማለዳ ፀሐይ ፍንትው ያለ አስተምህሮ ከንፁህ ምንጩ ተንበርክከን መማር ነው። ስለዚህ ያለ ዕውቀትና ግንዛቤ የሚዘረጋ ምላስና ስሜት የሞላው ተቆርቋሪነት የጥፋት መንገድ ስለሆነ እንቆጠብ። ሙስሊም ሁሌም የአላህ መመሪያ ሲጣስ ከማንም በላይ ያንገበግበዋል።ምላሽና አቋሙ ግን እንደሁኔታው የኢስላምን መርሕ በተከተሉ መልኩ ይሆናል።ይህም ሊላህ ብቻ ሲል የሚያደርገው ነው። አላህ ሆይ በጥፋት ጎዳና ያሉ ሙስሊም መሪዎችን አቅናልን።የአንተን ፍራቻ በልቦናቸው አስርፅ።ሕዝቡና ተመሪውንም ልቦና ስጠው።ወደአንተ መንገድም መልሳቸው። وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم 🖊 በኡስታዝ ዐብዱል ሐኪም( አቡ ማሪያ 🌐 https://t.me/Alfaruuq
Показать все...
الفاروق - Al Faruuq

ተከታታይ ቋሚ ኪታቦች የሚቀሩበት ቻናል።

👉 እውነት ወደ ጀነት ይመራል عن ابن مسعود  عن النبي ﷺ قال : " إن الصدق يهدي إلى البر، وإن البر يهدي إلى الجنة، وإن الرجل ليصدق حتى يكتب عند الله صديقا. وإن الكذب يهدي إلى الفجور، وإن الفجور يهدي إلى النار، وإن الرجل ليكذب حتى يكتب عند الله كذابا " متفق عليه " እውነት ወደ መልካም ነገር ይመራል :: መልካም ነገር ወደ ጀነት ይመራል :: አንድ ሰው እውነት ይናገራል አላህ ዘንድ እወነተኛ ተብሎ እኪመዘገብ ድረስ :: ውሸት ወደ ጥመት ይመራል :: ጥመት ወደ ጀሀነም ይመራል :: አንድ ሰው ይዋሻል አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስኪመዘገብ ድረስ :: ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል ➡️ አላህ እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ አላህን ፍሩ ከእውነተኞችም ሁኑ ይለናል :: ከላይ ያየነው ሐዲስ አንድ ሰው ውሸት ከጀመረ እየቀለለው ይሄድና ውሸት ባህሪው ሆኖ አላህ ዘንድ ውሸታም እስኪባል ድረስ ውሸትን እንደሚላበስ ነው :: ይህ ደግሞ የጀሀነም ሰዎች ስነ ምግባር ነው :: እራሳችንን እንፈትሽ ውሸት እየከበደን ነው ? ወይስ እየቀለለን ? ዛሬ ዛሬማ ወደ ዲን እጣራለሁ የሚለውም ዳዒ ወይም ኡስታዝ በዚህ ክፉ ደዌ የመለከፉ እድል ሰፉ ሆኗል :: በዲን ስም በውሸት ዝንባሌን ማርካት የሙጥኝ ተብሎ ይታያል :: በሌላ በኩል ከአየር ላይ የተገኘ ወሬን ወንፊት ውስጥ ሳያስገቡ በቀጥታ እንደሰሙት ፖስት የሚያደርጉ ይህ ውሸት የማይመስላቸው እየበዙ ነው :: የአላህ መልእክተኛ - ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም - ለአንድ ሰው የሰማውን ሁሉ መናገር ለወንጀል ይበቃዋል ይላሉ :: ሌላ ደሞ አለ ላዩ የምክር ሽቶ ነስንሶ ውስጡ እሱ ለሚፈልገው ዓላማ ተቀምሞ የተከሸነ የውሸት መርዝ እየረጨ ስንት ወንድሞችን የሚያለያይ ይህ ተዋናይ የተደበቁ ነገሮች ለሚወጡበት ቀን ምን እንዳዘጋጀ አላህ ይወቀው :: ሌላው በውሸት በዲን የሚነግድ እርሶም ይሞክሩት የግሩፕ ኪዮክስ ከፍቶ የቁርኣንና ሐዲስ ማአት በመደርደር ወደርሱ ኪዮክስ ያልመጣን ሙናፊቅ የሆነ የሚያስመስል ሞልቷል :: በጣም የተንሰራፋውና እንደ ማእበል እያናወጠ ያለው በውሸት ወሬ ማቀባበል እገሌ እንዲህ ብሎ እገሊት እንዲህ ብላ !!!! የሚለው ነው :: ውድ ወንድምና እህቶች ይህ ወረርሽኝ በጣም እየተስፋፋ ስለሆነ አላህን ፈርተን አኼራችንን እንጠብቅ ከእውነተኞችም ለመሆን እንሞክር :: አላህ ከእውነተኞች ያደርገን : : http://t.me/bahruteka
Показать все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

➲ሀቅ ከሁሉም ሰው ዘንድ ተወዳጅ አይደለም፡ ሀቅ የሚወደደው ከአስተዋዮችና አላህ ከመረጣቸው ሰወች ዘንድ ብቻ ነው። ሸይኽ ሙሀመድ አማን አል ጃሚ ምንጭ፦ ሸርህ ቁረት ዑዩን አል-ሙወሒዲን (6)
Показать все...
ታዋቂ ግን ደካማ ሐዲሦች እና ታሪኮች (ክፍል ሁለት) ~~~ ያለንበት ወር የረጀብ ወር ነው። ከዚህ ወር ጋር የሚያያዙ እጅግ በርካታ መሰረተ ቢስ ቅጥፈቶችና ደካማ ሐዲሦች አሉ። ወሩን ጠብቀው ብዙ ሰዎች ሲያሰራጯቸው ያጋጥማል። ይህንን የረጀብ አስመልክቶ ከተላለፉ መሰረተ ቢስ ዘገባዎች እና ደካማ ሐዲሦች ውስጥ ከፊሉን እንይ፡- [1ኛ]፡- رجب شهر الله وشعبان شهري ورمضان شهر أمتي “ረጀብ የአላህ ወር ነው። ሸዕባን የኔ ወር ነው። ረመዷን ደግሞ የህዝቦቼ ወር ነው።” ሸይኹል አልባኒ - ረሒመሁላህ - “ዶዒፍ” (ደካማ) እንደሆነ ገልፀዋል። [አዶዒፋህ፡ 4400] [2ኛ]፡- ረጀብ ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር፡- اللهم بارك لنا في رجب وشعبان، وبلغنا رمضان “አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን አድርሰን።” ነወዊይ በ“አዝካር”፣ ዘሀቢይ በ“ሚዛን” ደካማ እንደሆነ ብይን የሰጡ ሲሆን አልባኒም “ደካማ ነው” ብለዋል። [ዶዒፉል ጃሚዒ ሶጊር፡ 4395] [3ኛ]፡- فضل شهر رجب على الشهور كفضل القرآن على سائر الكلام “የረጀብ ወር በሌሎች ወራት ላይ ያለው ብልጫ ቁርኣን በሌሎች ንግግሮች ላይ እንዳለው ብልጫ ነው።” ኢብኑ ሐጀር “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት ነው ብለዋል። [4ኛ]፡- خمس ليال لا ترد فيهن الدعوة أول ليلة من رجب، وليلة النصف من شعبان، وليلة الجمعة، وليلة الفطر، وليلة النحر “አምስት ሌሊቶች በነሱ ውስጥ የተደረገ ዱዓእ አይመለስም። የመጀመሪያው የረጀብ ሌሊት፣ የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት፣ የዒደል ፊጥር ሌሊት እና የዒደል አድሓ ሌሊት ናቸው።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 1452] [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 2852] [5ኛ]፡- رجب شهر عظيم يضاعف الله فيه الحسنات، فمن صام يوما من رجب، فكأنما صام سنة، ومن صام منه سبعة أيام، غلقت عنه سبعة أبواب جهنم، ومن صام منه ثمانية أيام، فتحت له ثمانية أبواب الجنة، ومن صام منه عشرة أيام، لم يسأل الله شيئا إلا أعطاه إياه، … “ረጀብ አላህ መልካም ምንዳዎችን የሚያነባብርበት ታላቅ ወር ነው። ከረጀብ አንድ ወር የፆመ ሰው አመት እንደፆመ ነው። ከሱ ሰባት ቀናትን የፆመ ሰባቱ የጀሀነም በሮች ይዘጉለታል። ከሱ ስምንት ቀናትን የፆመ ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል። ከሱ አስር ቀናትን የፆመ አላህን የሆነ ነገር አይጠይቅም፣ እሱኑ የሰጠው ቢሆን እንጂ፣ …” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 5413] [6ኛ]፡- إن في الجنة نهرا يقال له رجب ماؤه أشد بياضا من اللبن وأحلى من العسل من صام يوما من رجب سقاه الله من ذلك النهر “በጀነት ውስጥ ረጀብ የሚባል ወንዝ አለ። ውሃው ከወተት የነጣ፣ ከማር የጣፈጠ ነው። ከረጀብ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ ከዚያ ወንዝ ያጠጣዋል።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት” ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 1902] [7ኛ]፡- صوم أول يوم من رجب كفارة ثلاث سنين، والثاني كفارة سنتين، والثالث كفارة سنة، ثم كل يوم شهرا “የረጀብን የመጀመሪያ ቀን መፆም የሶስት አመት ወንጀል ያብሳል። ሁለተኛው የሁለት አመት ያብሳል። ሶስተኛው ደግሞ የአመት ያብሳል። ከዚያም እያንዳንዱ ቀን የወር ነው።” አልባኒ ደካማ ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 3500፣ 5649] [8ኛ]፡- لا تغفلوا عن أول جمعة من رجب فإنها ليلة تسميها الملائكة الرغائب “ከረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐ አትዘናጉ። እርሷ መላእክት ‘አረጋኢብ’ ብለው የሚጠሯት ሌሊት ነች።” ‘ሶላተ ረጋኢብን’ በተመለከተ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡- “እርሷን የፈጠረን ሰው አላህ ይርገመው! እርሷ አስቀያሚ ቢድዐ ነች!” [ሸርሑ ሙስሊም] በተጨማሪም እሷንና የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ሶላትን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፡- “… ቢድዐ እና አስቀያሚ ፈጠራዎች ናቸው። በ‘ቁቱል ቁሉብ’፣ ‘ኢሕያእ ዑለሚዲን’ ኪታብ ውስጥ ስለተጠቀሱ ማንም እንዳይሸወድ። እነሱን በሚጠቁመው ሐዲሥም እንዲሁ (እንዳይሸወድ)። ምክንያቱም ሁሉም ውድቅ ነውና።…” [አልመጅሙዕ፡ 3/548] [9ኛ]፡- أن رسول الله -صلى الله عليه وسلم- لم يصم بعد رمضان إلا رجبًا وشعبان “የአላህ መልእክተኛ ከረመዷን በኋላ ረጀብንና ሸዕባንን እንጂ አልፆሙም።” ኢብኑ ሐጀር በጣም ደካማ ነው ብለውታል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 12] [10ኛ]፡- من صلى المغرب في أول ليلة من رجب ثم صلى بعدها عشرين ركعة يقرأ في كل ركعة بفاتحة الكتاب، وقل هو الله أحد مرة، ويسلم فيهن عشر تسليمات، أتدرون ما ثوابه؟ قال: حفظه الله في نفسه وأهله وماله وولده، وأجير من عذاب القبر، وجاز الصراط كالبرق بغير حساب ولا عذاب ". “በረጀብ የመጀመሪያ ሌሊት መግሪብን ሰግዶ ከዚያም በእያዳንዷ ረከዐ ፋቲሐንና ቁል ሁላሁ አሐድን አንድ ጊዜ እየቀራ፣ በአስር ተስሊማት እያሰላመተ ሃያ ረከዐ የሰገደ ሰው ምንዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አላህ በነፍሱም፣ በቤተሰቡም፣ በገንዘቡም፣ በልጁም ይጠብቀዋል። ከቀብር ቅጣትም ይጠበቃል። ሲራጥንም ያለ ሂሳብና ያለ ቅጣት እንደ ብልጭታ ያቋርጧል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/123] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 20] [11ኛ]፡- من صام من رجب وصلى فيه أربع ركعات ... لم يمت حتى يرى مقعده من الجنة أو يُرى له “ከረጀብ ፁሞ፣ በሱ ውስጥ አራት ረከዓዎችን የሰገደ ሰው … በጀነት ውስጥ መቀመጫውን ሳያይ ወይም ሳይታይለት አይሞትም።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/124] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 21] [12ኛ]፡- إن شهر رجب شهر عظيم، من صام منه يومًا كتب الله له صوم ألف سنة ... ". “የረጀብ ወር ታላቅ ወር ነው። ከሱ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺ አመት ፆም ይመዘግብለታል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/206-207] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 26] ከረጀብ ጋር የሚያያዙት ዘገባዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም። እነዚህን ለምሳሌ ያክል ይዘን ሌሎቹንም ጭምር በሚመዝን የዓሊሞች ንግግር ልቋጭ:— 1/ አልሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር - ረሒመሁላህ - እንዲህ ብለዋል፡- “የረጀብን ወር ልዩ ብልጫም፣ መፆሙን ወይም ከፊሉን በተለየ እንዲፆም፣ ወይም ከሱ ውስጥ የተገደበን ሌሊት በሶላት ማሳለፍን፣… የሚጠቁም ለማስረጃነት የሚበጅ ትክክለኛ ሐዲሥ አልተላለፈም።" [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 6 እና 8] 2/ አልሓፊዝ አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ በክር አዲመሽቂይ (691 ሂ.) ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዱ የረጀብን ፆም እና ከፊል ሌሊቶቹን መስገድን የሚጠቁም ሐዲሥ ውሸት፣ ቅጥፈት ነው።” [አልመናሩል ሙኒፍ፡ 1/96]
Показать все...
💦ፊትናው በዛ ሀያእ ጠፍቶ💦 ወጣ ስንል በመንደሩ ሴትም ወንድም በመኖሩ እሷም በወንዱ ስታፈጥ ወንዱም አይቷት ሲያገጥ ከንፈሯ መስሎ ወጥ በወጥ ይዟት ሲዞር ጎጥ ለጎጥ እጁን ትከሻዋ ላይ ማኖሩ ሲያቅፋት አለማፈሩ ሳትሆን ለሱ ባለቤቱ ወይ አይደለች ውድ እህቱ አልወለዳት ልጁ አይደለች ያልተፈቀደችለት አጅ ነብይ ነች እሷም ስቴድ አለማፈሯ ፊቷን አስመስላው አቧሯ ቀሚሷን ማሳጠሯ ብጣሽ ሻርፕ አርጋ ለፀጉሯ ብቅ ስትል በመንደሩ የሽቶዋ ሽታ በሰፈሩ ወንዶትን ሁሉ መጥራቱ ወደ ሀራም መጎተቱ ሀያእ አጥታ ልጅቱ ፈሳድ ሞላው ከቤቱ ጉዱ ተወርቶ አለማለቁ የሴት ከወንድ ድብልቁ በየቦታው መማቀቁ በየ ሚዲያው መሳሳቁ ሀያእ ቢጠፋ ከመንደር ወንጀል ቢበዛ በሀገር የፀሀዪ እንዲ ማቃጠል የብርዱ እንዲህ መቆምጠል በሌላ አይደለም አታማር ቻለው ምንም ቢመር ያንተው የኔም ወንጀል ሲበዛ ይከረፋል ለመስማትም ይቀፋል ሲያዩትም ያስከፋል ከኛአልፎ ለንፁሀኑም ይተርፋል ተውባ አድራጊ ጠፍቶ ፈሳድ ባለሙ ተስፋፍቶ ዛሬ ብትጮህ በደረቁ ህዝብ እንዲህ ማለቁ እሬሳ አይቶ መሳቀቁ ጉድኮ ነው መብዛቱ የወንጀላችን ማስጠላቱ ዳኢ ተብዬ ያ ወንዱ ዘፈን ሙዚቃ በመፍቀዱ ኢስላማዊ ፊልም ማለቱ ቢድአውን ማስፋፋቱ በዲኑ ላይ መጫወቱ ተውሂድ ሱናን በመርሳቱ አቤት ምድር ማስጠላቱ በዚህ ፈሳድ መሞላቱ ሲያንሰን ነው ፀሀይ ብርዱ ጠፍቷል ሁሉ መዋደዱ በዑለሞቻችን ማሾፍ በዝቶ ቢደአን ስንወድ ሱናን ጠልቶ እርስበርስ እዝነት ጠፍቶ ወሬያችን እንቶ ፈንቶ አይናፋርነት ተጠልቶ ፊትናው በዛ ሀያእ ጠፍቶ አይናፋርነት ተጠልቶ ስቃይ በዛ እዝነት ጠፍቶ። ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺃﻫﺪﻱ ﺑﻨﺎﺗﻨﺎ ﻭﻧﺴﺎﺋﻨﺎ ﻭﺍﻟﻤﺴﻠﻤﻴﻦ ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺭﺯﻗﻬﻢ ﺍﻟﻌﻔﺔ ﻭﺍﻟﺘﻘﻮﻯ ﻭﺃﺑﻌﺪ ﻋﻨﻬﻢ ﺷﺮ ﻛﻞ ﺫﻱ ﺷﺮ ﻳﺎ ﺃﻣﺎﻥ ﺍﻟﺨﺎﺋﻔﻴﻦ ﻭﻳﺎ ﺟﺎﺭ ﺍﻟﻤﺴﺘﺠﻴﺮﻳﻦ ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺃﺻﻠﺢ ﺷﺒﺎﺑﻨﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺃﺻﻠﺢ ﺷﺒﺎﺑﻨﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺣﻔﻆ ﺷﺒﺎﺑﻨﺎ ﻣﻦ ﺍﻟﻔﺘﻦ ﻣﺎ ﻇﻬﺮ ﻣﻨﻬﺎ ﻭﻣﺎ ﺑﻄﻦ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺳﺘﺮ ﻧﺴﺎﺀﻧﺎ ﻭﺑﻨﺎﺗﻨﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺳﺘﺮ ﻧﺴﺎﺀﻧﺎ ﻭﺑﻨﺎﺗﻨﺎ ﺑﺮﺣﻤﺘﻚ ﻳﺎ ﺃﺭﺣﻢ ﺍﻟﺮﺍﺣﻤﻴﻦ ! ــــــــــــــــــــــــــــــــ #انشرها_واكسب_الأجر_والثواب -----❀------ @Qidmeia_le_tewhid @Qidmeia_le_tewhid
Показать все...
በአምስት ነገሮች ካልሆነ በቀር ችኮላ ከሼይጧን ነው። 1⃣ እንግዳን ማብላት, 2⃣ የሞተን ሰው መሸኘት, 3⃣ ልጃገረድን መዳር, 4⃣ እዳን መክፈልና, 5⃣ ተውበት ማድረግ። ምንጭ 【አልሂልየቱ ሊአቢ ኑኤይም 8/82】
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.