ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

Afar Communication Bureau

Afar Communication Bureau

Открыть в Telegram

Rakaakayak Doolat Angaarawih Biiro

Больше
818
Подписчики
Нет данных24 часа
+17 дней
+1130 дней
Архив постов

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተፈጥሮ ጋዝ የሚሰሩ አውቶብሶች ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ያስተላለፉት መልዕክት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኬንያ የማሹጃ ቀን አከባበር ላይ ያደረጉት ንግግር ​#PmAbiyAhmed #KenyaEthiopia #MashujaaDay #Ethiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በትግርኛ ቋንቋ ያደረጉት ቆይታ #PMAbiyAhmed #EBC #Ethiopia #Tigray #FailedTPLF #Sha'ebia #PMOEthiopia

ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥና ለሀገራዊ ብልጽግና እያበረከተ ይገኛ
+3
ቀደም ሲል ችላ የተባለው የማዕድን ዘርፍ፣ ዛሬ የዕድገት ስትራቴጂካዊ ሞተር ሆኗል! በ#መደመርመንግሥት አማካኝነት የማዕድን ዘርፉ አቅሙን በማላቅ ለኢኮኖሚ ለውጥና ለሀገራዊ ብልጽግና እያበረከተ ይገኛል። 🇪🇹 #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers

"ኢትዮጵያ የምትታወቀው ነፃነቷን እና ሉዓላዊነቷን በጽኑ እና በተባበረ ክንዷ ከወራሪ በመጠበቅ ነው። የዚህም ምስጢሩ ሕዝቦቿ ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸው ጥልቅ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት ነው። ይህ አርማች
+2
"ኢትዮጵያ የምትታወቀው ነፃነቷን እና ሉዓላዊነቷን በጽኑ እና በተባበረ ክንዷ ከወራሪ በመጠበቅ ነው። የዚህም ምስጢሩ ሕዝቦቿ ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸው ጥልቅ ፍቅርና ብሔራዊ ስሜት ነው። ይህ አርማችን፣ በመላው ጥቁር ሕዝብ ዘንድ የነፃነት፣ እኩልነትና የፅናት ተምሳሌት በመሆኑ በርካታ ሀገራት ቀለማቱን የሰንደቃቸው አካል አድርገው ወስደውታል ለዚህም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው።" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ #የመደመርመንግሥት #Ethiopia #EBC #Medemer #MedemerGovernment #NationalFlagDay

የኢትዮጵያ ሕዝብ መዝሙር #Ethiopia #FlagDay #NationalAnthem

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት --------------------------------------------- 19ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን ‎ ‎“ሠንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን” ‎ ‎ብሔራዊ አንድነት ለኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ መሠረት ነው። ሠንደቅ ዓላማችንም የጋራ ታሪካችንን፣ ሉዓላዊነታችንና በልዩነቶቻችን መካከል በጋራ የመቆም አቅማችንን የሚያስታውስ የብሔራዊ አንድነታችን ምልክት ነው። ‎ ‎በዓድዋ የሀገሪቱ ሕዝቦች ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው በጋራ በመቆማቸው፣ በታላቅ ገድላቸው የዓለምን ትኩረት መሳብ ችለዋል። አባቶቻችን በፈተናዎች ከመከፋፈል ይልቅ አንድነታቸውን አሳይተዋል። ይህ በጋራ የመቆም ጥሪ መቼም ቢሆን ተቋርጦ አያውቅም፤ እያንዳንዱም ትውልድ ለዚህ ጥሪ እንዴት ምላሽ መስጠት እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። ‎ ‎መደመር ሁላችንንም አንድ ቀላል ጥያቄ ይጠይቀናል፤ እኛ የሀገራችንን እጣ ፈንታ ከዳር ቆመን የምንታዘብ ተመልካቾች ነን? ወይንስ “ይህች ሀገሬ ናት፤ የወደፊት ዕጣ ፈንታዋም ያሳስበኛል” ማለት የምንችል ባለቤቶች? ‎ ‎ቋንቋዎቻችን፣ ሃይማኖቶቻችን እና ማንነቶቻችን ለዘመናት በጋራ በምናልፍበት ታሪካዊ ጉዞ ውስጥ አብረው ተሰናስለው የተሸመኑ የአንድ ሸማ ክሮች ናቸው። ለሀገር መቆም ከትንንሽ የድፍረት እርምጃዎች ይጀምራል፤ ከራስ አልፎ ሰፊ ርዕይ ይዞ መሥራትንም ይጠይቃል። ያለፉት ትውልዶች ሀገሪቱን እንድንረከብ መስዋዕትነት ከፍለዋል፤ ዛሬ በጋራ የምናጸናትን ሀገር ነው ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈው። ‎ ‎ስለሆነም ዛሬ ራስዎን ይጠይቁ፤ ለሀገርዎ አንድነትና ብልጽግና ምን አበረክታለሁ?

photo content
+1

«Ni Simbil Ne Hinnay Ni Gaali Yaxige» Sultaan Qali Mirac Canfaxe
«Ni Simbil Ne Hinnay Ni Gaali Yaxige» Sultaan Qali Mirac Canfaxe

የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ : የኢትዮጵያውያን የሉዓላዊነትና የአንድነት ጽናት ----------------------------------------------- የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን የሀገራችን የኢትዮጵያውያን የማንነት መገለጫና የታሪካችን ታላቅ አርማ የሆነውን ሰንደቅ ዓላማችንን ክብር፣ መስዋዕትነትና ጥልቅ ትርጓሜ በድምቀት የምናስታውስበት ልዩ ታሪካዊ ዕለት ነው። የሀገርን ዳር ድንበርና ክብሯን ለማስጠበቅ ሲሉ የቀደሙ አባቶቻችንና እናቶቻችን ደምና ላባቸውን አፍስሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ያስከበሩትን ሰንደቅ ዓላማ በጋራ ማክበር የማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሊወጣው የሚገባ ታላቅ የዜግነት ኃላፊነትና የሞራል ግዴታ ነው። ሰንደቅ ዓላማችን በዋናነት ለብሔራዊ መግባባትና ለሀገራዊ አንድነታችን የጸና ምሰሶ፣ የህብረ ብሔራዊነታችንና የአብሮነታችን ውብ ማሳያ እንዲሁም የነፃነታችን እና የሉዓላዊነታችን ህያው ምስክር ሆኖ ይኖራል። ኢትዮጵያዊነት በደም እና በአጥንት የተሳሰረ፣ በትውልዶች መተካካት ውስጥ ሳይበገር የጸና የማይበጠስ ጠንካራ የታሪክና የባህል ገመድ ነው። ሀገራችን በታሪኳ አጋጣሚዎች ሁሉ በውጭ እና በውስጥ ጠላቶች የተደቀኑባትን አደጋዎችና ፈተናዎች የተሻገረችው በዚሁ ጽኑ ኢትዮጵያዊ ህብረትና ሀገራዊ ፍቅር ነው። የታሪካችን ዳግማዊ አድዋ የሚያረጋግጠው እውነት ቢኖር ለኢትዮጵያ ሀገራችን የመጣ ማንኛውም አደጋና ፈተና እኛን ሳያገኝና ሳይነካ እንደማያልፍ፣ እያንዳንዱ ዜጋም ሀገሩን ለመጠበቅ ጋሻና መከታ ለመሆን ዝግጁ መሆኑን ነው። በዚህ ታሪካዊ የሀገር ፍቅር ገድል ውስጥ የአፋር ህዝብ ለሀገርና ለሰንደቅ ዓላማ ያለው ታማኝነትና ቁርጠኝነት ምትክ የሌለው ልዩ ቦታ ይዟል። አንጋፋውና የተከበሩት የአፋር ሱልጣን አሊ ሚራህ ሀንፈሬ (ረሂመሁላህ) የአፋር ህዝብ ከሀገሩ ሰንደቅ ዓላማ ጋር ያለው ጥልቅና የማይበጠስ ትስስር ሲገልጹ "እንኳን እኛ ግመሎቻችን እንኳን ያውቁታል" በማለት የተናገሩት ታዋቂ ንግግር፣ ህዝቡ ከሰንደቅ ዓላማውና ከሀገሩ ሉዓላዊነት ጋር ያለውን ተፈጥሯዊና ጥበቃ የታከለበት ጥልቅ ፍቅር ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የዘንድሮው የብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በዓል ሲከበር ዜጎች በሙሉ በሰንደቅ ዓላማችን ፊት በኩራት ቆመው ቃለ መሃላ በመፈጸም ለአገራቸውና ለሰንደቅ ዓላማቸው ያላቸውን ጥልቅ ክብርና ፍቅር ዳግም የሚገልጹበት፣ እንዲሁም የሀገራቸውን አንድነትና ሉዓላዊነት አጽንተው ለማስጠበቅ ቃላቸውን የሚያድሱበት ታላቅ ዕለት ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ለሰንደቅ ዓላማችን የሚገባውን ክብር በመስጠት፣ የጋራ እሴቶቻችንን አበልጽጎ በማጠናከር እና ህብረ ብሔራዊ ወንድማማችነታችንን በጽናት በማጠናከር ሊሆን ይገባል። የአፋር ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ

photo content
+8

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል። Prime Min
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ አቶ ጌታቸው ረዳን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አድርገው በድጋሚ ሾመዋል። Prime Minister Abiy Ahmed reappoints Getachew Reda as East Africa Affairs Advisor to the Prime Minister with a rank of Minister. #PMOEthiopia

የመደመር መንግሥት ምስረታ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦ 1. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት
የመደመር መንግሥት ምስረታ እንደቀጠለ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚከተሉትን ሹመቶች ሰጥተዋል፦ 1. ዲያቆን ዳንኤል ክብረት - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የዴሊቨሪ ክትትል ዘርፍ ኃላፊ 2. አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በሚኒስትር ማዕረግ - የENFI ክትትል ዘርፍ ኃላፊ 3. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ 4. አቶ ፍሰሃ ደሳለኝ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ 5. ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ 6. አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ 7. አቶ ሀብታሙ ሲሳይ - በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ አስተባባሪ #መደመርመንግሥት #PMOEthiopia

"በጋራ ሀገር እንገነባለን!" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) #የመደመርመንግሥት #PMOEthiopia

የአንደኛና የሁለተኛ ዘመን አብቅቷል

ተጨባጭ ማስረጃ ካገኘን በ24 ሰዓት እንቀይራለን

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡለትን የሚኒስትሮች ሹመት አጽድቋል

photo content
+9

photo content