cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Rehoboth Media

Spiritual Media Ministry to Equip the generation with the word of GOD

Больше
Рекламные посты
1 126
Подписчики
Нет данных24 часа
-67 дней
-3330 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

🔵 ወንድም ሄኖክ በተደጋጋሚ ጊዜ አንተ ባለህበት ብዙ አይነት ስህተቶች መድረክ ላይ ሲታዩና ለዩቲዩብ ሰራተኞች የገቢ ትርፋቸዉ ሲሆን አይተናል። ከድመቷ ፈዉስ ጀምሮ፣ በነ ጌድዮን አስቻለዉ የሱዳን ዘፈንና ልቅ የሆነ የጭፈራ ግርግር በጣም የበዙ ስህተቶች እያየን ነዉ። ብዙም ጊዜ ስህተቶች ሲፈጠሩና ሲሰሩ ይቅርታ ብሎ ከማረም ይልቅ ስህተትን እንደ ትክክለኛ ማንነት በመቁጠር ስታልፍ አስተዉያለዉ። እኔ የማስተምረዉ የህይወት ቃል አገልግሎታችሁ ለሰዉ አእምሮ የሚመች ይሁን፥ ለራስህና ለምታስተምረዉ ትምህርት ተጠንቀቅ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህ ይላል። ታድያ የምናገለግለዉ አገልግሎት በእምነት ያልጠነከሩትን ማሰናከያ፤ በማያምኑት አህዛብ ዘንድ መሳለቅያ ከሚያደርገን ነገር ሁሉ መጠንቀቅ ይገባናል። የምንሰብከዉ፣ የምንዘምረዉ ብቻ ሳይሆን የምንኖረዉም ክርስትና ነዉ የተሰጠን። በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ፥ ዛሬ በፎቶዉ ላይ ያስቀመጥኩትን የአንተንና አብረዉክ የተነሱትን ሰዎች መጠየቅ እፈልጋለሁ። 🔵 አንተ የለበስከዉ ጋዉን ከድግሪና ከማስተርስ በኃላ በብዙ ድካም በእግዚአብሔር እርዳታ የሚገኝ የዶክትሬት ማዕረግ እንደሆነ አዉቃለሁ። በዚሁ መሠረት አንተ የኮሌጅ ትምህርት እንኳን እንዳልተከታተልክ አዉቃለሁ፤ ታድያ የዲፕሎማ ዉጤት ሳይኖረን የዶክትሬት ጋዉን መልበስ ተገቢ ነዉ❓ 🔵 ክርስቶስ ከሞት ሲነሳ ለቤተክርስቲያን ስጦታ ይሆን ዘንድ አንዱ የተሰጠዉ የነቢያት አገልግሎት ሲሆን ይህን ፀጋ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠዉና በፍሬ የሚገለጥ ስጦታ እንጂ እየተነሳን የነቢያት ትምህርት ቤት እያልን እኛ የምንሾመዉ ፀጋ ነዉ❓ቤተክርስቲያን ፀጋዉ በፍሬና በተግባር ስትመለከት የምትሾመዉ እንጂ ጉባኤዉን ሁሉ አስተምረን የምናፀድቀዉ የፀጋ ስጦታ ነዉ እንዴ❓ 🔵 የነቢያት አገልግሎት ጥሪ እንጂ እኛ ፈልገን የምንሾመዉ ስራ ነዉ❓ወይስ እንደፈለግን እየተነሳን ነቢይ፥ ኃዋርያ እየተባባልን እንጀራ የምንበላበት ስራ ነዉ እንዴ❓ 🔵 ዛሬ 127 ነቢያትን አስተምረን አስመረቅን አልከን፤ በነቢይነት ተምሮ የተመረቀና የተቀጠረ አገልጋይ ከመፅሐፍ ቅዱስ ብትጠቅስልን❓ወይስ ሰዎችን ሰብስበህ አሜን ስለሚሉህ ህዝቡን አንተ በፈለከዉ መንገድ እየነዳከዉ ነዉ❓አገልግሎት ሹመት ብቻ ሳይሆን መከራና ስደት እንዳለበትስ ነግረሀቸዋል❓ለማገልገል ብቻ ሳይሆን ለወንጌል መሞትም እንዳለባቸዉ ነግረካቸዋል❓ 🔵 መልካም ለሊት። ሰኔ 26/10/2015 ዓ.ም፤ “የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን።” — 2ኛ ቆሮ 13፥14 #የእግዚአብሔር_አገልጋይ_ማስረሻ_በላይ
Показать все...
Показать все...
የኬፋ ሚደቅሳ ገራሚ መዝሙር | Kefa Mideksa | Ethiopian song

በዚህ ቻናል የተለያዩ አዳዲስና የቆዩ መንፈሳዊ ፊልሞችና ምስክርነቶች ይቀርቡበታል እርሶዎም ሰብስክራይብ በማድረግ ለወዳጅዎ ያጋሩ

ከቄስ ዶ/ር ገለታ ሰሚሶ ኢሬቻን አስመልክቶ ለክርስቲያኖች የተላለፈ መልዕክት ከሰሞኑ በየስፍራው ከሚነሱት የመወያያ ጉዳዮች ውስጥ አንዱና ምናልባትም ዋነኛው የእሬቻ በዓል ምንነት ነው፡፡ አንዳንዶች እሬቻን ፍጹም ባህላዊ እንደሆነና ምንም ዓይነት ኃይማኖታዊ ንክኪ እንደሌለው ይሞግታሉ፤ ከዚህም በመነሳት የማንኛውም ዕምነት ተከታይ የሆነ ሰው የእሬቻ ሥርዓትን ቢሳተፍ ምንም ችግር የለበትም የሚል ሀሳብ አላቸው፡፡ ሌሎች የዚሁ ሥርዓት ደጋፊዎች ደግሞ እሬቻ ለአምላክ "ዋቃ" ስላለፈው የክረምት/የዝናብ ወቅት ምስጋና እንዲሁም ለመጪው አዲስ ዓመት ደግሞ ጥበቃው እንዳየቋረጥ ልመና የሚቀርብበት ሥነ ሥርዓት እንደሆነ አስረግጠው ነገር ግን ምንም ዓይነት ባዕድ አምልኮን እንደማይቀይጥ ከዚህም የተነሳ ከክርስትና ጋር ግጭት እንደሌለው አበክረው ይሞግታሉ፡፡ ማንም ሰው የፈለገውን ማምለክና መከተል ወደፈለገው አምላክም ምስጋናውንም ሆነ ጸሎቱን ማድረስ ሰብዓዊ ብሎም ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ከዚህ አስተሳሰብ በመነሳትም የእሬቻም ሆነ የሌሎች ሥርዓት አስፈጻሚዎች የወደዱትን የማድረግ መብት እንዳለቸው አልክድም፡፡ በዚሁ አስተሳሰብ ላይ ቆሜ እንደ አንድ የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋይና የሥነ መለኮት መምህር ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች የሚከተሉትን ወሳኝ ናቸው ያልኳቸውን ነጥቦች ማስቀመጥ እፈልጋለሁ፡፡ 1ኛ. በስነ መለኮት ትምህርት ውስጥ በእንግሊዝኛ ቋንቋ “Natural revelation” ተብሎ የሚገለጽ አስተሳሰብ አለ፡፡ ይህ ማለት በጣም በአጭሩ ለማስቀመጥ እግዚአብሔርን ከሚታየው ተፈጥሮ በመነሳት ማወቅ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ እሬቻን በዚህ ዘርፍ ውስጥ እናገኘዋለን፡፡ በርካታ የሥነ መለኮት ምሁራን እንደሚስማሙበት ምንም እንኳን በተፈጥሮ ውስጥ የፈጣሪውን ችሎታና አዋቂነት ማየት ቢቻልም ፈጣሪውን ግን ማየት አይቻልም፡፡ ስለዚህ ሰዎች እግዚአብሔርን ለማወቅና ከርሱ ጋር የግል ትውውቅ ወይም ግንኙነት ለማድረግ ከተፈጥሯዊው መገለጥ የሚበልጥና የተሻለ መንገድ ያስፈልጋቸዋል፡፡ 2ኛ. በብዙ ባህላዊ ዕምነቶች ዘንድ የተለመደው የምስጋናና የምልጃ ሥርዓት በእኛ ሀገር ባህላዊ ዕምነቶችም እሬቻንም ጨምሮ ውስጥም ይንጸባረቃል፡፡ የእነዚህ ባህላዊ ዕምነቶች ወይም ሥርዓቶች ተከታዮችም ምስጋናችንን ለፍጡር ሳይሆን ለፈጣሪ የምናቀርብበት ሥርዓት ነው ብለው ይሞግታሉ፡፡ ይህ የእነርሱ መረዳት ሊሆን ይችላል፡፡ ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ማንም ሰው የፈለገውን መርጦ ማምለክም ሆነ ማመስገን ይችላል፡፡ ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች ግን ይህ በምንም መለኪያ ትክክለኛ አካሔድ ሊሆን አይችልም፡፡ ምክኒያቱም በክርስትና አስተምህሮ መሠረት ማንም ሰው ከክርስቶስ ኢየሱስ ውጪ ወደ እግዚአብሔር ለምስጋናም ሆነ ለልመና መቅረብ አይችልም፡፡ ቀጥሎ ያሉት ሁለት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ይህን የክርስቶስን ማዕከላዊነትና አስፈላጊነት የሚያሳዩ ናቸው "አንድ እግዚአብሔር አለና በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንደ አለ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፡፡" 1 ጢሞ 2፡5 "ኢየሱስም እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም፡፡" ዮሐ. 14፡6 3ኛ. ከነዚህ መሠረታዊና ቀላል ምልከታዎች በመነሳት በክርስቶስ ኢየሱሰ ላመኑ ክርስቲያኖች በእሬቻ አምልኮ ላይ መሳተፍ ትክክል አይሆንም፡፡ ምክኒያቱም ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ከተፈጥሮ ባለፈ በክርስቶስ ኢየሱስ ራሱን እንደገለጸላቸውና በርሱም ሥራ ወደ መንግሥቱ እንደጠራቸው የሚቀበሉ አማኞች ናቸው፡፡ ስለዚህ በክርስቶስ ሞትና ትንሣዔ በኩል እግዚአብሔር ራሱን ገልጦልኛል ብሎ ለሚያምን አንደ ክርስቲያን ክርስቶስ መካከለኛ ባልሆነበትና ፈጽሞ በማይታይበት አምልኮ ውስጥ መሳተፍ የክርስቶስን ሥራ ማቃለል ይሆናል፡፡ ተፈጥሮ የፈጣሪዋን ችሎታ ልትገልጥልን ብትችልም ወደ እርሱ የምንደርስበትን መንገድ አታሳየንም፡፡ በአንጻሩ ክርስቶስ ኢየሱስ ግን የእግዚአብሔርን ችሎታ ብቻ ሳይሆን አባትነቱን የገለጠልንና በሞቱና ትንሣዔው በማመን ወደ እግዚአብሔር እንድንደርስ የመግቢያ በር የሆነን ፍጹም ሰው ደግሞም ፍጹም መለኮት የሆነ ጌታችን ነው፡፡ 4ኛ. ስለዚህ ማንኛውም ክርስቲያን ብሔሩን ወይም ዘሩን ለማሳየት በግድ በባህላዊ/ኃይማኖታዊ ሥርዓቶች ውስጥ መሳተፍ ላይኖርበት ይችላል፡፡ ሲጀመር ከዚህኛው ወይም ከዚያኛው ብሔር እንድንወለድ ያደረገው እግዚአብሔር እንደሆነ ሁሌም ማስታወስ ጠቃሚ ነው፡፡ በመቀጠል የዚህ ወይም የዚያ ብሔር አባለት መሆናችንን ለማሳየት ብዙም መንፈራገጥ አይጠበቅብንም ምክኒያቱም በሰዎች ፈቃድ ያልተሰጠንንነ ማንነት በሰዎች ፈቃድ ልንነጠቅ አንችልምና፡፡ ከሁሉ በላይ ደግሞ ክርስቲያኖች በክርስቶስ ኢየሱስ በማመናችን በምድር ካለን ብሔርም ሆነ ዘር የሰፋና የበለጠ ማንነት እንደተጎናጸፍን መርሳት የለብንም፡፡ ከባህል፣ ከቋንቋ፣ ከዘር ወይም ከዜግነት ባለፈ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል የተሰጠን የእግዚአብሔር ልጅነት ወቅት ሳንጠብቅ፣ ተራራ ሳንወጣ ሸለቆም ሳንወርድ ሁል ጊዜ በየዕለቱ እግዚአብሔርን ልናመሰግንበት የሚገባ ምክኒያት አለን፡፡ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአልና በአማኞች ዘንድ ሁሌም በዓል ሁሌም ምስጋና ሊሆን ይገባል፡፡ Geleta Simesso (Dt)
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
Показать все...
አደረገልኝ ድንቅ ዝማሬ በዘማሪ አበነዘር ጴጥሮስ Aderegelign Singer Abenezer Petros #worshipzone

CONTACT US FACEBOOK =

https://www.facebook.com/Worship-Zone

... TELEGRAM =

https://t.me/worshipz

በየጊዜው የሚለቀቁ ቪዲዮዎች በፍጥነት እንዲደርስዎት ሰብስክራይብ እንዲሁም የደወል ምልክቱን በመጫን አብረውን ጌታን ያገልግሉ © All rights reserved to Binyam Mekonnen official #worship zone# No part of this publication may be reproduced, distributed, or transmitted in any form or by any means without the prior written permission of the publisher.

ሰሞኑን ኢየሱስ አማላጅ ነው በሚል ጽሁፌ በሉቃ 19 ላይ ኢየሱስ ሊፈርድ እንዳልመጣ በደምን ጠቅሼዋለው። ኢየሱስ ለፍርድ እንዳልመጣ እና ከፍርድ ቀን በፊት ማንም መፍረድ እንደሌለበት ተናግሯል። ስለዚህ አንድ ሰው ተግሳፅ በተናገረ ቁጥር አትፍረድ ከማለት ይልቅ የቃሉን ፍቺና ትርጉም ማወቅ ያስፈልጋል። ሌሌው ደግሞ አሁን ቤተክርስቲያን ምትገኝበት ዘመን የፀጋ እንጂ የህግ ዘመን አይደለችም ስለሆነውም ፈራጁ እስኪመጣ ማንም መፍረድ( ቅጣት ሊሰጥ) አይችልም። ስለዚህ ኢየሱስ ያወራው አትፍረድ ያለው አውድ በሙሴ አይን ለአይን ጥርስ ከጥርስ ህግ መሰረት ቅጣት(ፍርድ) መሰጠት እንደሌለበት በሚል አውድ እንጂ የሳተውን ተው ተመለስ የሚለው ሀሳብ ጋር ፈጽሞ ገይገናኝም።ምክንያቱም ማንም ለሰራው በደል ቅጣትም ሆነ ለሰራው በጎ ነገር ፍርድ ሚቀበለው በመጨረሻ ከክርስቶስ ዳግም ምጻት በኋላ ነው። ሲጠቃለለ በአሁኑ ዘመን ማንም የመፍረድ Mandate ሆነ ስልጣን የለውም ምክንያቱም ክርስቶስ ብቻ ነው ፈራጅ ሆኖ በመጨረሻ ሚመጣው።ስለዚህ አትፍረድ ብሎ ከመናገር በፊት ፍርድ ምንድነው አንድ ሰው ምን ሲያረግ ነው ፍርድ ሚባለው ብሎ የእግዚአብሔር ቃል ማንበብ እና መረዳት ጥሩ ነው። መልካም ንባብ ✍️🙏 ከጽሁፉ ከተማሩበት ለሚወዱት አንድ ሰው ሼር ያድርጉ ። ከትልቅ አክብሮት ጋር! ........................... ⭕️ Join us⭕️ @RehobothMedia @RehobothMedia @RehobothMedia
Показать все...
#አትፍረድ ===== ይህ ቃል ብዙ ጊዜ ትክክል ባልሆነ መልኩ ጥቅም ላይ ሲውልን ይስተዋላል። ቃሉ ደግሞ ብዙ ጊዜ ጥቅም ላይ ሚውለው አንዳንድ ሰዎች ትክክል ያልሆነ ተግባር ሲፈፅሙ ለዚያ ድርጊታቸው ሲተቹ፣ ሲነቀፉ ያ ድርጊታቸው ልክ እንዳልሆኑ ሲነቀፉ ለድርጊታቸው ማምለጫ ወይም እነሱን ሚደግፉ ሰዎች እንደማገዝ መስሏቸው ያንን ድርጊት መሸፈኛ አትፍረድ፣ አንተን ማን ፈራጅ አረገህ ይላሉ። ለመሆኑ ፍርድ ምንድነው? የቃሉ ታሪካዊ አመጣጥስ ምንድነው? ፍርድ የሚለው ቃል ከህግ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው ቃል ነው። ፍርድ ለመፍረድ ህግ ያስፈልጋል ሚፈረደውም ህጉን መሰረት ተደርጎ እንጂ ያለ ህግ አንድ አካል ላይ መፍረድ አይቻልም ። ምክንያቱም ፍርድ የአንድ ህግ የመጨረሻኛው ውሳኔ ነውና። አንድ ሰው ከመሬት ተነስቶ ፍርድ በራሱ ሊፈርድ አይችልም። ፍርድ ለአንድ ነገር የመጨረሻ ውሳኔ የሚሰጥ ውሳኔ እንጂ ትችት መሰንዘር አይደለምና። አሁን በ21ኛው ክፍለ ዘመን ያለውን ለጊዜው እንተውና ወደ መፅሀፍ ቅዱስ ጎራ ብለን ትክክለኛውን ትርጉምና አጠቃቀም ትንሽ እንይ እስቲ ምክንያቱም ብዙ ጊዜ ይህንን ቃል ሚጠቀሙ ሰዎች አትፍረድ የሚለውን መሰረት ሚያደርጉት መፅሀፍ ቅዱስን ስለሆነ ። እግዚአብሔር አምላክ ለህዝበ እስራኤል ህግ በሙሴ አማካኝነት የሰጠው ህግ ነው( ዘፀአት 20፣ ዘዳግም 6) እግዚአብሔር ለሙሴ ከሰጠው ህግ ሲሆን አስርቱ ትዕዛዛት በመባል ይታወቃል። ከዚህም በተጨማሪ ከዘፍጥረት እስከ ዘዳግም ያሉት አምስቱ መፅሀፍ የህግ መፅሀፍት(Pentateuch ወይም Tora)በመባል ይታወቃሉ። ከዚህ መነሻ ተነስተን እግዚአብሄር ለሙሴ ህግን ሲሰጥ ለህጉ ተገዢ የሆኑትን ሲያመሰግን ህጉን ለሚጥሱት ምን ቅጣት እንደሚያስከትል በእነዚህ አምስቱ የህግ መፅሀፍት በግልፅ ሰፍሯል። በእነዚህ ህግ መፅሀፍት ላይ ህጉን ለሚተላለፉ ሙሴ እንዲፈርድ ፍርዱም ምን እንደሆነ በግልፅ ተፅፏል። ለዚህ ነው በፅሁፌ መጀመሪያ ላይ ፍርድ የህግ የመጨራሻኛው ውሳኔ እንደሆነ የገለፅኩት።ስለሆነም በዚያ ህግ መሰረት አንድ ሰው ህጉን ቢጥስ በህጉ መሰረት ፍርድ ይሰጠዋል። ለምሳሌ ===== 1.“ሰው በሬ ወይም በግ ቢሰርቅ፥ ቢያርደው ወይም ቢሸጠው፥ በበሬው ፋንታ አምስት በሬዎች፥ በበጉም ፋንታ አራት በጎች ይክፈል።” ዘጸአት 22፥1 👉ህግ:- አትስረቅ ፍርድ:- አራት ወይም አምስት እጥፍ መመለስ 2. ሄዶም ሌሎች አማልክትን ያመለከ፥ እኔ ላላዘዝኋቸው ለፀሐይና ለጨረቃ ለሰማይም ሠራዊት ሁሉ የሰገደ ቢገኝ፥ ⁴ ቢያወሩልህም ብትሰማም፥ ያንን ፈጽመህ መርምር፤ እነሆም፥ እውነት ቢሆን፥ በእስራኤልም መካከል እንዲህ ያለ ርኵሰት እንደ ተሠራ እርግጥ ሆኖ ቢገኝ፥ ⁵ ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ። ቢያመነዝር በድንጋይ ተወግሮ ይሞታል" ዘዳግም 17 👉ህግ:-ሌሎች አማልክት አታምልክ ፍርድ:- በድንጋይ ወግሮ መግደል ስለዚህም ነው በኢየሱስ ዘመን በዮሐ 8:10 ላይ ስታመነዝር የተያዘችውን ሴት ሊወግሩ ፍርድ ሊሰጡ ተሰብስበው ሊወግሩ(ሊፈርዱ) ፈልገው። ህጉ ወግረን እንድንገድል (የሞት ፍርድ እንድንፈርድ)ያዝዛል አንተ ምን ትላለህ ያሉት። እነዚህንና ሌሎች የመፅሀፍ ቅዲስ ክፍሎች ስንመለከት ፍርድ ተብሎ የተፃፈው ወይም ሰዎች ሲፈርዱ የነበረው በህጉ መሰረት የመጨረሻ ቅጣት በመስጠት ማለትም በመስቀል፣ በመውገር ወዘተ እንጂ በአፍ በመናገር አይደለም አይደለም።በሌላ አባባል ፍርድ ድርጊት የሚከናወን ስርዓት ነው። ታዲያ በዚህ ዘመን አንዳንድ ሰዎች ኢ-መፅሀፍ ቅዱሳዊ ልምምድ ሲያደርጉ ቃሉ ያልፈቀደውን ሲያደርጉ ወይም ትክክል አይደለህም ተብለው ሲተቹ ቶሎ ብለው አትፍረድ ይላሉ። ታዲያ ይህ በታሪክም በቅዱስ ቃሉም ስንመዝን ምንም መሰረት የለለው እና ትክክልም ያልሆነ አባባል ነው። አንድ ሰው ትክክል ያልሆነ ነገር ሲያደርግ ትክክል አይደለህም ማለት ፍርድ ተብሎ አይጠራም ፍርድም አይደለም። መፍረድማ ቢሆን ያ ሰው አመንዝሮ ከሆነ በድንጋይ ወግሮ መግደል ነው። ሰርቆ ከሆነ አራት ወይም አምስት እጥፍ ማስከፈል ነው። ታዲያ አንድ ሰው ሀጢያት ሲሰራ ሰርተሃል፣ ተሳስተሃል ማለት መፍረድ አይደለም? አወ መፍረድ አይደለም መገሰፅ ይባላል። ብዙ ሰዎች ተግሳፅን እና መፍረድን ቀላቅለውታል። የእግዚአብሔር ቃል ሲናገር ለጢሞቴዎስ ዝለፍና ገስፅ ይለናል። “ቃሉን ስበክ፥ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና፥ ፈጽመህ እየታገሥህና እያስተማርህ፥ #ዝለፍና #ገሥጽ ምከርም።” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥2 በሌላም ክፍል ጢሞቴዎስን እንዲህ ይላል። “ይህን በሙሉ ሥልጣን #ተናገርና ምከር #ገሥጽም፤ ማንም አይናቅህ።” — ቲቶ 2፥15 ታዲያ አንድ ሰው በስህተት ስራ ወይም ትክክል ባልሆነ ነገር ሲገኝ መንቀፍ፣ ትክክል አለመሆኑን መናገር መገስፅ ቃሉ የሚደግፍ ትክክለኛ መፅሀፉ የሚያዝ ተግባር እንጂ ፍርድ ነው የሚል ድምዳሜ ከየት የመጣ ትርጉም ነው? ኢየሱስ በአዲስ ኪዳን አትፍረድ ይፈረድብሃል ያለው ዘመነ ኦሪት ሰዎች በህጉ መሰረት የሚፈርዱትን ፍርድ ማብቃቱን እና ፍርድ መጨረሻ እሱ ዳግም መምጣቱን ለማሳየት እንጂ ፍርድ የሚለው አውድ ዛሬ ብዙዎች በሚጠቅሱት አውድ አይደለም። ዛሬ ብዙዎች ፍርድ ብለው የሚጠሩትን ኢየሱስ በብዙ መልኩ ገስጿል። ለምሳሌ ማቴ 23:13 “እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ መንግሥተ ሰማያትን በሰው ፊት ስለምትዘጉ፥ ወዮላችሁ እናንተ አትገቡም የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።” በዚህ ክፍል መንግስተ ሰማይ አትገቡም ይላል ይህ ፍርድ ነው ማለት ነው? እናንተ ግብዞች ይላል ፍርድ ነው ማለት ነው? ይህ ፍርድ አይደለም እነዚህ ሰዎች ከስህተታቸው ተመልሰው ትክክለኛውን መንገድ እንዲመለሱ እየገሰጻቸው እንጂ እየፈረደ አይደለም። ፍርድማ ቢሆን ወዲያው መንግስተ ሰማይ እንዳይገቡ ከልክሎ ወደ ገሃነመ እሳት መላክ ነበረበት። ከላይ በአጽኖት እንደጻፍኩት ፍርድ የመጨረሻ ውሳኔ ነው አንድ ሰው ከተፈረደ ቀጣዩ እርምጃ መተግበር ብቻ እንጂ ሌላ እድል የለውም። በዘመነ ህግ የነበረው አሰራርም ይህ ነበር። ስለዚህ አንድን ነገር ያለ አውዱ ያለ ቦታው መጠቀም አላጎሪ ነው። ኢየሱስ ብቻ ሳይሆን ሌሎችም የአዲስ ኪዳን አገልጋዮች ሲያገለግሉ በተመሳሳይ መልኩ ሰዎችን ሲገስጹ ነበር ለምሳሌ 3.እናንተ #የእፉኝት ልጆች (ዮሃንስ ማቴ 3:7)) 4. #ውሾች ፊሊ 3:2 (ሀዋሪያው ጳውሎስ) እነዚህ ሁሉ ለእግዚ/ር የተመረጡ አገልጋዮች በአንዳንሶች ስሌት ፈርደዋል ወይም እየፈረዱ ነው ማለት ነው። እነዚህ አገልጋዮች ፍርድ ምን እንደሆነ ኦሪቱንም ሀዲሱንም ጠንቅቀው ያውቃሉ። ማወቅ ብቻ አይደለም ይህ ድርጊት ተግሳጽ ስለሆነ ቃሉም ገስጹ ብሎ ስላዘዛቸው በመገሰጻቸው አክሊል እንደሚያገኙ ጠንቅቀው አውቀው ነው ሚገስጹት እንጂ ፍርድ እንዳልሆነ የፍርድ ቀን ደግሞ ከክርስቶስ ዳግም ምጽዓት በኋላ እንደሆነ ጠንቅቀው ሚያውቁ ሚያስተምሩም ጭምር ናቸው። የተሰሎንቄን መጽሀፍ የጻፈው ስለ መነጠቅ ያብራራው በእጅ ስላልተሰራችው በሰማይ ስላለችው መኖሪያ የጻፈው ይህንን ሁሉ የተግሳጽ ቃል ሲያዘንብ ፍርድ መሆኑን ተምታቶበት አይደለም።
Показать все...
#ኢየሱስ_አማላጅ_እንጂ_ፈራጅ_አይደለም። ******************************** ይህ ርእስ ብዙ ጊዜ አጨቃጫቂ ሲሆን ብዙ ጊዜ እንመለከታለን ለምን ቢባል ብዙዎቹ የሚነሱበት መሰረት (ground) ከሚያምኑበት ቤተእምነት ዶክትሪን እንጂ ከመፅሀፍ ቅዱስ ስላልሆነ ነው። ኢየሱስ ወደ ምድር ሲመጣ ለሰው ልጆች ሀጢያት ዋጋ ከፍሎ ሰውንና እግዚአብሔርን ሊያስታርቅ (ሊማልድ) እንጂ ሊፈርድ አይደለም የመጣው ። ለዚህም እራሱ ሲናገት እንዲህ ብሏል። “ዓለምን ላድን እንጂ በዓለም ልፈርድ አልመጣሁምና ቃሌን ሰምቶ የማይጠብቀው ቢኖር የምፈርድበት እኔ አይደለሁም።” ዮሐንስ 12፥47" ከዚህ ከኢየሱስ ክርስቶስ ከራሱ ንግግር ምንማረው ወደ ምድርም የመጣው የሰውን ልጅ ሊያድን እንጂ ሊፈርድ እንዳልመጣ ነው። ሌላኛው ክፍል ሉቃስ 19:10 ላይ " የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና "ይለናል። ክርስቶስ ወደ ምድር የመጣበትን ዓላማ ፍንትው አድርጎ ይነግረናል።ብዙ ሰዎች የኢየሱስን የምልጃ ሚረዱት በተሳሳተ መንገድ ነው።ኢየሱስ ሲያማልድ ሰዎች ሲጣሉ አንተም ተው አንተም ተው ብለው ሰዎች ጎረቤቶቻቸው፣ ጓደኞቻቸው ወዘተ እንደሚያስታርቁት ልክ ኢየሱስም በዚያ መንገድ ያማለደ( ያስራረቀ) አድርገው ያስባሉ። ልመና ሚለምንም ሚመስላቸው ሰዎች አሉ ለዚያም ነው ብዙዎች የሰዎችን፣ የመልአክትን ምልጃ ከኢየሱስ ምልጃ ጋር አንድ አድርገው ሚያነፃፅሩት። ኢየሱስ ሰውንና እግዚአብሔርን በዚህ መንገድ አይደለም ያማለደውም ያስታረቀውም። በሮሜ 6:23 ላይ ሲናገር “ የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነውና” ይለናል። በዚህ ክፍል በተፃፈው መሰረት እና በዘፍ 3 ላይ የሰው ልጅ በሰራው ሀጢያት በሞት መቀጣት እንዳለበት እግዚአብሔር ደንግጎ ነበር ። እግዚአብሔር ሀጢያትን በሰራችሁ ቀን ሞትን ትሞታላችሁ ባለው መሰረት ያ ህገ የአምላክ ትዕዛዝ ስለሆነ መፈፀሙ ግድ ነው። ስለዚህ ያ የሰው ልጅ የሰራው የሀጢያት ክፍያ በሆነ አካል ካልተከፈለ በስተቀር ከቅጣት ማምለጥ አይቻልም። ኢየሱስ በአማላጅነት ስራው የሰራው ያንን ነው። የሰው ልጅ የሰራውን የሀጢያት እዳ የራሱን ደም መስዋዕት አድርጎ ከፍሎ ነው ያስታረቀው እንጂ ከላይ እንደጠቀስኩት ብዙዎች ቅዱሳን ማራቸው ተውላቸው እንደሚሉት በዚያ መልክ አይደለም። ስለዚህ የኢየሱስን ምልጃ በምድር ማንም አልማለደምም ሊማልድም አይችልም የእሱ ምልጃ የራሱን ደም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለሰው ልጅ ሁሉ ከፍሏልና። ለዚህ ጉዳይ የዕብራውያን መልእክት እንዲህ ተፅፏል “የዘላለምን ቤዛነት አግኝቶ አንድ ጊዜ ፈጽሞ ወደ ቅድስት በገዛ ደሙ ገባ እንጂ በፍየሎችና በጥጆች ደም አይደለም።” ዕብራውያን 9፥12 “እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል።”ዕብራውያን 7፥25 ታዲያ ብዙዎች ስለ ክርስቶስ አማላጅነት ያላቸው ግንዛቤ ልክ ከላይ እንደጠቀስኩት አንተም ተው አንተም ተው አይነት ስለሆነ ጉዳዩንም በዚህ መንገድ ስለተረዱትም ኢየሱስ አማለደ ሲባል ያዋረዱትን ሚሰማቸው። አንድ ሰው ነገሩን በዚም መንገድ ከተረዳ ለዚህ አይነት ድምዳሜ ቢደርስ አይፈረድበትም ምክንያቱም የማማለድ ስራ የሰው አይነት ከሆነ የኢየሱስ መሞት አስፈላጊ አይደለምና። ስለዚህ ነገሩን ፈራጅ እንጂ አማላጅ አይደለም ወደሚል ድምዳሜ አመጡት። ነገር ግን ኢየሱስ ያማለደውን ምልጃ ቅዱሳን፣ መላእክት ማንም ፍጥረት ሊማልድ በሚችለው መልኩ ሳይሆን የገዛ ስጋውንና ደሙን አፍስሶ ለእግዚአብሔር በመሰዋት የሀጢያት ክፍያ አድርጎ በማቅረብ ነው። ኢየሱስ የሰውን ልጅ ሀጢያት ለመክፈል ነው የመስቀል ላይ መሰቀል የነበረበት እንጂ ለሌላ ጉዳይ አይደለም። የኢየሱስ ምልጃ የተከናወነው በዚህ መንገድ ነው። እስከ ዛሬ ለሰው ልጅ ሀጢያት በዚህ መንገድ የገዛ ደሙን ከፍሎ በመስቀል ላይ ሞቶ ዋጋ የከፈለ ያማለደ ቅዱስ ወይም መልዓክ የለም። ክርስቶስ ኢየሱስ ግን ኣራሱ መስዋእት ሆኖ የሰውን ልጅ ሀጢያት ከፍሎ ነው ሰውንና እግዚአብሔርን ያስታረቀው ያ በመስቀል ላይ የተሰራው ስራ ነው ማማለድ(ማስታረቅ) የተባለው እንጂ ዛሬ እኛ እንደምናስበው ቅሱዳን፣ ማርያም ልጇን ተውላቸው ትላለች በሚል መልኩ አይደለም። የገዛ ደሙን ይዞ ዕብ ስለዚህ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣል በገዛ ደሙ የሰውን ልጅ ሀጢያት ከፍሎ ሊያስታርቅ(ሊማልድ) እንጂ ሊፈርድ አይደለም። ታዲያ ኢየሱስ ዳግመኛ ሲመጣ አማላጅ ነው ወይስ ፈራጅ? ይህ በማያሻማ መልኩ ቁርእርንም ሳይቀር ሊፈርድ እንደሚመጣ ግልፅ ነው። ኢየሱስ ዳግም እስኪመጣ ድረስ አሁን በአብ ቀኝ ሳይቀር ያኔ በመስቀል የከፈለው ዋጋ እስከ ዳግም ምፅአት ወይም እስከ ፍርድ ቀን ድረስ ለሰው ልጅ ሀጢያት ያስተሰርያል። ያ የስርዬት ስራ ማማለድ ይባላል። ስለዚህ ኢየሱስ አሁን ፈራጅ ሳይሆን አማላጅ ነው። ዳግም ሲመጣ ግን ፈራጅ ሆኖ ሊፈርድ ነው ሚመጣው። AsAb Engr ነኝ! መልካም ንባብ
Показать все...