🥀ሶልያና🇪🇹
•┈•❈••✦✾✦••❈•┈• 👉ምርጥ ምርጥ ግጥሞች ከእውቅ ገጣሚያን በድምፅና🎧 በፅሁፍ📃 👉አዝናኝ፣ አስተማሪና መረጃ ነክ ፅሁፎች👌 😇 😁 •┈•❈••✦✾✦••❈•┈•
БольшеСтрана не указанаЯзык не указанКатегория не указана
568
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней
- Подписчики
- Просмотры постов
- ER - коэффициент вовлеченности
Загрузка данных...
Прирост подписчиков
Загрузка данных...
🥀ሶልያና🇪🇹
ይሄ ነው ጎጆችን
ፍቅር ሳያንሰን ባህር የከፈለው
መፈላለጋችን እመነት ያራራቀው
የኔ ፀባይ ሰናይ አመልህ የሰራው
ጣራ ግርጊዳውን ድምፅህ ያሳመረው
አጥብቆ ያቆመው ንፁ ማንነትህ
ብለያይም እንኳ እመነቴና እመነትህ
ይሄ ነው ቤታች በንፁ ህሊና ፍቅር የገነባው
መሞጋገስ እንጂ መወቀሳ የሌለው
አየህ የኔ ትውት !!!❣️
ለቤቴ ድምቀት ነው ፀባህ እና አመልህ
ተስፋ እሰነቀ ሁሌ ምያባብልህ
የሄ ነው ጎጆችን ባህር የከፈልው
አንድ ነገር ብቻ ስሩን ያራራቀው
በነፃነት ቡዙና
@Soliana9
@Soliana9
የውበት ጀርባው
(በእውቀቱ ስዩም)
ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ
ያበባ ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ
ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ ስትበሳ
የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ
የዋጠችው ህመም፤ ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ?
ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ
ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ
ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ስእል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ
ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ።
@Soliana9
@Soliana9
እንደምትወዳት ንገራት!
[በእውቀቱ ስዩም]
ህይወት -የብድር በሬ፤ መቼ ሁሌ ይጠመዳል?
ለጊዜው ብቻ የመጣ ፤ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ፀጋ ሁሉ፤ ደሞ ካንተ ይወሰዳል፤
ቀለበት ፤ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ፤ ሁል ጊዜ የሉም-
-ቀናት ፤ሳምንታት፤ ወራት
ዛሬውኑ ፤ አሁንኑ ፤ እንደምትወዳት ንገራት ፡፡
.
አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምኡዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያፀድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ ፤ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ህይወት- የላምባ መብራት
አሁንኑ ዛሬውኑ፤ እንደምትወዳት ንገራት::
.
ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደ ጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደ እማትቀባው አመድ
ወደ እማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንተም አንደበት ሳለህ ፤ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት!!
.
@Soliana9
@Soliana9