cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Ethyo fikre Entertainment🇪🇹

Рекламные посты
4 377
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
Нет данных30 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Watch "አስቴር አወቀ ምኞት" on YouTube https://youtu.be/peYWHh1raxA
Показать все...
አስቴር አወቀ ምኞት

Watch "የናፍቆትህ ደብዳቤ ደርሶኝ 😑" on YouTube https://youtu.be/AhqbnONKJPg
Показать все...
የናፍቆትህ ደብዳቤ ደርሶኝ 😑

Показать все...
የስኬት መንደር

ይህ ትልቁ የስኬት መንደር ነው የራሳችንን አሻራ የምናሳርፍበት ሰዎች ያላቸውን ልምድ አዎንታዊ ሃሳብ የሚያካፍሉበት ነፃ አሳታፊ የቴሌ ግራም የውይይት ቻናል ነው። *እውቀት ይለግሱበታል *ልምድ ያካፍሉበታል *ልምምዶች እናካሂዳለን *የቤተሰቡን ጥያቄ ሰብስበን ባለሙያ ጋብዘን ምላሽ እንዲያገኝ እናደርጋለን *እንግዶችን እንጋብዛለን እውቀት ልምድ ተሞክሮ እናገኛለን ሁሉም ነገር ከሃሳብ ነው ሚጀምረው!!!

Показать все...
ፍቅር ሰማይ ምድር (አሁንም አይደል ወደ ማታ ከሚለው መፅሀፍ ላይ የተወሰደ 🍎

Watch "ትዝታህ" on YouTube https://youtu.be/9V8cVbo86mE
Показать все...
ትዝታህ

ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር . ያሳለፍነዉ ሁሉ አሁን ትዝታ እንጂ ዉስጡ ህይወት የለም እያልሽ ላገሩ... ታወሪያለሽ አሉ . . (እኔ ግን ልንገርሽ) የሁለታችን ፍቅር ምን እንደሚመስል. . . እንዴት እንደነበር በሶስት ምስክር 1 አሁን በቀደም ለት የሆነ ቦታ ላይ ድምጻችን ከፍ አርገን የሳቅንበት ቦታ ፒያሳ አደባባይ ድንገት በቀደም ለት በዛ ቦታ ስሄድ ከሰባት ወር በፊት ስቀሽ የነበረዉ ያንቺ ሳቅ ተሰማኝ መራመድ አቃተኝ የሚገርምሽ ነገር ያለፈ ነዉ ያልሺዉ ትዝታ ነዉ ያልሽዉ ፍቅርሽና ሳቅሽ ከሰባት ወር ኋላ እንደ ወንዝ ፍሳሽ ይሰማል ልንገርሽ . (ታዲያ ለምንድን ነዉ) የወንዝ ዉሀ ሳቅሽ ያለፈ ትዝታ ምናምን ነዉ ብሎ ማንም ተራ ዘፋኝ የሚሸነግልሽ (ይልቅ እኔን ስሚኝ) . ወደየትም ሳይሆን ወዴትም ተመለሽ የትም ሳትደርሺ ጊዜን እንዳቆምነዉ እንኳን ጊዜ ቀርቶ ሰዓት እንዳልሄደ ደቂቃ እንዳልሄደ አስረጂ ሊሆንሽ ምስክር ሊሆንሽ ከምንም አቅጣጫ. . . የትም ሳትመለሽ አደባባይ መሀል ከቡና ጠረን ጋር እንደወንዝ የሚፈስ ሳቅሽን ትሰሚያለሽ . 2 ትዝ ይልሽ እንደሆን ካንቺ መኖሪያ ቤት (የመጣሁኝ ጊዜ) የመራራቅ ናፍቆት አስክሮን ቸኩለን ሰማያት ለመዝለቅ ከመሬት ላይ ወድቀን ፍቅር ስንሰራ ፍቅር ስንሰራ ፍቅር ስንሰራ ከሴት ወዝሽ ጋራ የጡትሽ ስር ሽቶ ሸሚዜ ላይ ቀርቶ ሸሚዜ ላይ ቀርቶ ምወደዉን ሸሚዝ ለመልበስ እርም አልኩኝ ለብሼዉ እንዳልሄድ ከበደኝ ጨነቀኝ ያንቺን ጠረን ማጠብ. . . ነፍስ የማጥፋት ያህል ሀጥያት መስሎ ታየኝ (የሚገርምሽ ነገር) እስከ ዛሬ ድረስ በመስኮቱ ዘልቆ. . .በበሬ የሚወጣዉ የማለዳዉ ነፋስ በሽቶሽ ጠረን ነዉ መንደሩን የሚብስ . 3 ታስታዉሽ እንደሆን የሆነ ቅዳሜ የሆነ ዉብ ሆቴል ደግሞም አትረሺዉም. . .ፍጻሜ ምሳ ነዉ ይኼ እንኳን ትዝ ይላል እና. . . እኔና አንቺ ብቻ የተቀመጥንበት ወንበር ጠረጴዛዉ ከዘጠኝ ወር ኋላ. . . እዛዉ ቤት ዳግመኛ ተመልሼ ባየዉ የሚገርምሽ ነገር ጻፊዉን ባላዉቅም # ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር የሚል ጽሁፍ ሰቅለዉ ከዘጠኝ ወር ኋላ አንድ ለብቻዬ ካንድ አንቺ ናፍቆት ጋር ነበር ለምትይዉ ለሁለታችን ፍቅር (ምስክር ሊሆኑን) ያኔ ሁለታችን የጠጣነዉ ወይን ከወይንም. . . Two Ocean እኔ የጨለጥኩት አንቺ ያጋመስሽዉ እኛ ያስተረፍነዉ እስከዛሬ ድረስ ያተረፍነዉ ማዕድ. . . ጠርሙስና ጽዋዉ በክብር ተቀምጧል ማንም ሳያነሳዉ. . .ያኔ እንደነበረዉ (ታዲያ ምን ማለት ነዉ) . . . ፒያሳ አደባባይ የወንዝ ዉሃ ሳቅሽ ከቡና ጠረን ጋ ከኔ መኖሪያ ቤት. . . የምወደዉ ሸሚዝ ላይ የሽቶ መአዛሽ ከሴት ላቦትሽ ጋር ደግሞም እዚያ ዉብ ሆቴል ስር ያስተረፍነዉ . . . ማዕድ ጠርሙስና ጽዋ አንጀት ከሚበላ ከቆንጆ ጥቅስ ጋር ‘’#ፍቅር_እዚህ_ቦታ_ፈገግ_ብሎ_ነበር::’’ . ነበርን እስካሁን በመሆን እያየሽ ሳቅሽ ፈሶ ሳያልቅ ከምወደዉ ሸሚዝ የሽቶ መዓዛሽ ዉብ ጠረኑ ሳይለቅ ማዕድ ሳይነሳ ጽዋዉ ሳይታጠብ ሦሥቱን ምስክሮች በዓይንሽ ፊት እያየሽ (ታዲያ ለምንድን ነዉ) ያሳለፍነዉ ሁሉ # አሁን_ትዝታ_እንጂ ..... # ዉስጡ_ህይወት_የለም ብለሽ ለመንደሩ ላገሩ ማዉራትሽ እዉነት ለምንድን ነዉ? . . . . . ©ኤፍሬም ስዩም096 303 9962
Показать все...