cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

Dr wedajeneh mahrene ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ

ዶ/ር ወዳጀረነህ ማህረነ ነኝ ማማከር ምፈልጉት ካለ ከታች ባለ አካዉንት አዉሩኝ አመሰግናለሁ ። @wedajrnehmahrenebot የስልጠና እና ማማከር ሳምንታዊ እና ወርሀዊ ፓኬጅ ምትፈልጉ አናግሩኝ።

Больше
Рекламные посты
2 376
Подписчики
Нет данных24 часа
+187 дней
+2830 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

5.መዉቀስ እና መካድ ምን ማለት ነዉ ? ላጠፋሀዉ ጥፋት ተወቃሽ ላለመሆን ሌሎችን የመዉቀስ ልምድ ፡፡ለምትናገረዉ እና ለምታረገዉ ተግባር ሀላፊነትን መካድ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ በመጨረሻም ባጠፋነዉ ነገሮች ምክንያት እንድንጎዳ እና ለጭንቀት እንድንዳረግ ያደርገናል ፡፡ስለዚህ ሌሎችን መዉቀስ እና ለጥፋትህ ሀላፊነትን መዉሰድ ይገባሀል ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ ወደ ስራ ቦታህ ሁልጊዜ በእንቅልፍህ ምክንያት እያረፈድክ እየሄድክ ለምን አንደምታረፍድ ለራስህ ሚስትህ ሰበብ እንደሆነች ስታስብ አሷን ተወቃሽ ስታደርግ ፡፡ በእንቅልፍ ምክንያት አርፋጅ መሆንህን በመካድ ሚስትህ ለማርፈድህ ምክንያት ናት ብለህ ስታስብ ፡፡ 6.ቀጥታ መወሰን ምን ማለት ነዉ ? ያለምንም መረጃ እና ሙከራ ሳታደርግ ነገራቶችን በግምት ቀጥታ መወሰን ፡፡ ሁለት አይነት ቀጥታ ዉሳኔ አሉ ፡፡ አንደኛ ወደፊቱን በማሰብ መጥፎ ነገር ብቻ እንደሚገጥምህ ማሰብ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ ነዉ ፡፡ ሰዎች ጋር ስትገኛኝ ስላንተ መጥፎ ሀሳብ እንዳላቸዉ ያለምንም ማስረጃ ማሰብ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ከሰዉ ጋር ያለንን ግንኙነት በማበላሸት ለ ድብርት ይዳርገናል፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ ፍቅረኛህ ሜሴጅ ልከህላት ለ ሁለት ሰዐት ያህል ስላልመለሰችልህ ግንኙነታችሁ እንዳበቃለት ማሰብህ ፡፡ አንድ ሰው መንገድ ላይ አፍጥጦ ስላየህ ይጠላኛል ብለህ ማሰብህ ፡፡ 7.አሉታዊ ጎን ብቻ ማሰብ ምን ማለት ነዉ ? በምታረጋቸዉ ድርጊቶች ላይ ሚከሰቱትን አሉታዊ ጎኖች ብቻ ትኩረት ሰጥቶ ማሰብ፡፡ ሚከሰቱ አወንታዊ ዉጠቶችን በማንጎለል አሉታዊዉ ላይ ትኩረትን በመስጠት በስራችን ደስተኛ እንዳንሆን ሚያደርግ አስተሳሰብ ነዉ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ደስተኛ እንዳንሆን ስለሚያረግ ከአዕምሮአችን ማፅዳት አለብን ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ የቅርብ አለቃህ በሰጠህ ወርሀዊ የስራ ግምገማ ላይ ብዙ አወንታዊ እና ጠንካራ ጎን ቢኖሩህም ትንሽ የተሰጠህ አሉታዊ ወይም ደከም ያልክበት ጎንም ጠሰጥቶሀል ፡፡ በዚህ ግምገማ ላይ የተሰጠህን ጥሩ አስተያየት በመተዉ የተሰጠህን ደካማ ጎን በማጋነን ማሰብ እና ሙሉ ቀን ያንን አስተያየት እያሰብክ ለድብርት መዳረግ ፡፡ 8. ወደራስህ ማዞር ምን ማለት ነዉ ? ነገሮችን ወደራስ ማዞር ምንም ካንተ ጋር ሚያገናኘዉ ነገር ባይኖርም ፡፡ አስተያት ወይም ጥቆማ ሲነገር ይህ ነገር እኔን ለማለት ተፈልጎ ነዉ ብለህ ወደራስህ ማድረግ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ምንም በሌለ ነገር ላይ ሀሳብ ማምጣት ስለሆነ ከ አዕምሯችን ማፅዳት አለብን ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ የፍቅር ጎደኛሽ ባንቺ ላይ ሲማግጥብሽ ችግሩ ከሱ የመጣ ሁኖ ሳለ ችግሩ ባንቺ ምክንያት እንደሆነ ምታስቢ ከሆነ ፡፡ መስሪያ ቤት ዉስጥ ለተፈጠሩ ችግሮች አንተን ማይመለከቱ ቢሆኑም የችግሩ መንስኤ እኔ ነኝ ብለህ ማሰብህ ፡፡ 9. የተፈጠረ ችግር ከመጠን በላይ ማጋነን ምን ማለት ነዉ? የሚፈጠሩ ችግሮች ከመጠን በላይ አጉልቶ አበቃልኝ በቃ ብሎ ማሰብ ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን፡ ምሳሌ ትንሽ ጡትሽ አካባቢ ዉጋት ነገር አመም ቢያረግሽ በቃ አለቀልኝ የጡት ካንሰር ታማሚ ሆንኩ ብለሽ ልክ በሽታዉ እንደደረሰብሽ አድረገሽ ራስሽን መሸበር 10.ፅንፈኛ አስተሳሰብ ምን ማለት ነዉ? በነገራቶች ወይም አስተሳሰብ ላይ በአንድ ፅንፍ በመያዝ ሌሎች አስተሳሰቦችን ዉድቅ ማድረግ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ እኔ የያዝኩት ሀሳብ ብቻ ትክክል ነዉ ሌሎች አስተሳሰቦች ምንም ጥቅም የላቸዉም ብልህ ስታስብ ነዉ፡፡ ምን ማለት ነዉ? ባለህ የፖለቲካ አስተሳሰብ ላይ እኔ ብቻ ልክ ነኝ ብለህ ማሰብህ ሌሎች አስተሳሰቦችን መረዳት ሆነ ማዳመጥ አለመፈለግ ፡፡
Показать все...
👍 8👏 1
10 አዕምሮን የሚጎዱ አስተሳሰቦች 1.ነገሮችን ማካበድ ወይም ነገሮችን ማቅለል ምን ማለት ነዉ ? ነገሮችን ማክበድ ማለት አዕምሮህ ስህተት ስትሰራ ወይም ችግር ሲገጥምህ ነገሮችን በማክበድ ስሜታዊ የመሆን ችግር ነዉ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ትንሽም ችግር ቢገጥመዉ ነገሩን በማክበድ መጨናነቅ ሰላምን ማጣት ነዉ በተቃራኒዉ ነገሮችን ማቅለል ማለት ነገሮችን ሰኬትን እና ሰራን ከሚገባዉ በታች አቅልሎ ትኩረት አለመስጠት ነዉ ፡፡ ፡፡እነዚህ አስተሳሰቦች በጣም ጎጂ ስለሆኑ ከአዕምሮችን ማፅዳት ወይም ማስወገድ አለብን ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ በመስራቤትህ ለምታቀርበዉ የግምገማ ንግግር ምክንያት ከመስራቤተህ እንደምትባረር ማሰብ በተቃራኒዉ ነገሮችን ማቅለል ያደረከዉ የስበሰባ ንግግር ጥሩ ቢሆንም መጥፎ ንግግር እንዳደረክ እና ራስህን ንግግር ማይችል ሰዉ አርገህ ማሰብ፡፡ 2.ግዴታ መሆን አለበት ብቻ ብለህ ማሰብ ምን ማለት ነዉ ? ይሄማለት የምትሰራዉ ስራ ምን እንደሚሆን ዉጤቱ እየታወቀ ነገር ግን የራስህን የተለየ ዉጤት ብቻ አስበህ ያዉጤት ግዴታ መገኘት አለብህ ብለህ ማሰብ ፡፡ ይህም አስተሳሰብ መጥፎ እና ለ አዕምሮ ጭንቀት እና ድብርት የሚያጋልጥ ስለሆነ ማስወገድ አለብን፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ ግዴታ ከዩኒቨርስቲ የተመረቀ ተማሪ ሁላ ወዳዉ ስራ ይይዛል ብለህ ማሰብህ ነገር ግን ተመርቀህ አንተ እና ጎደኞችህ ስራ ስታጡ ድብርት ወይም ጭንቀት ዉስጥ መግባት ፡፡ 3.ዉስጣዊ ስሜትን(Emotion) መከተል ምን ማለት ነዉ ? ሎጂክን ወይም እዉነታን ከመከተል ይልቅ በዉስጣዊ ስሜትህ የተሰማህን ነገሮችን ያለምንም ማስረጃ መከተል ማለት ነዉ ፡፡ ይህ ማለት አንድን ነገር በዉስጣዊ ስሜትህ ስላሰብከዉ ብቻ እዉነት ነዉ ብለህ ማሰብ ነዉ ፡፡ይህ አስተሳሰብ በሎጂክ እንዳናምን በማረግ ኋላ ቀር እንድንሆን እና ለድብርት ተጋላጭ ስለሚያረገን መወገድ ያለበት አስተሳሰብ ነዉ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡- ድንገት የብቸንነት ስሜት ስለተሰማህ በዚህ የተነሳ ሁሌም ብቸኛ ሰዉ መሆን ነዉ ያለብኝ ብለህ መወሰን ፡፡ ነገር ግን የተሰማህ የብቸኝነት ሰሜት ጊዜያዊ ነዉ ግን ራስህን ብቸኛ አድርገህ ራስህን ትጎዳለህ ፡፡ 4.በአንድ ማጠቃለል ምን ማለት ነዉ ? ነገራቶች ላይ አጠቃላይ ድምዳሜ ላይ መድረስ በአንድ የተከሰተ ጉዳይ ላይ ብቻ ተመርኩዞ ፡፡ አዕምሮህን በአንድ ሙከራ ዉጤት ላይ ብቻ በመገደብ በዛይ ላይ በሚከሰተዉ ዉጤት ሙሉ ድምዳሜ ላይ መድረስ ፡፡ ይህ አስተሳሰብ ለጭፍን ድምዳሜ እና ለጭንቀት ስለሚዳርገን መወገድ ያለበት አስተሳሰብ ነዉ፡፡ ምሳሌ ከህይወታችን ፡ የመጀመርያ ፍቅረኛህ ስለበደለችህ ብቻ ሁሉም ሴቶች መጥፎ ናቸዉ ብለህ ማሰብህ ፡፡ በአንድ ሴት የደረሰብህን መጠፎ ነገር ለሁሉም ሴቶች መገለጫ አርገህ መስጠትህ በአንድ ማጠቃለል ነዉ ፡፡ @drwedajenehmahrene
Показать все...
👍 22
ከመሬት ተነስቶ ድብር ጭንቅ ይሎታል ይህ ነገር ዝም ብሎ ሚመጣ ነገር አደለም ከአስተሳሰብ መጣመም እንጅ!! ጭንቀት ድብርት ፍራቻን ለማጥፋት ሚረዳ ስልጠና ምፈልጉ ይህን ሰው አናግሩ @Doctor_Abuki
Показать все...
👍 18
የእራስህ ይሻልሃል! ታዋቂው ካናዳዊ ፀሃፊና መምህር ቦብ ፖሮክተር በአንድ ቃለ መጠየቅ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር። "95% የአለማችን ህዝብ የሚኖረው የማይፈልገውን ህይወት ነው። 5% ብቻ የሚፈልገውን ህይወት በመረጠው ሁኔታ ይኖራል። ለዚህም ዋነኛውና ትልቁ ምክንያት ሰዎች የእራሳቸውን ንፁ አቅም ከማውጣት ይልቅ ሰዎች ያደረጉትን ተግባር በመደጋገም ስለተጠመዱ ነው።" የእራሴ የምትለው መለያ፣ ያንተ ብቻ የሆነ መታወቂያ ከሌለህ ህይወትህ አሰልቺና አድካሚ አዙሪት የማይሆንበት ምክንያት የለም። እድሜ ልኩን የሰዎችን ስራ እየደጋገመ የሚኖር ሰው እውነተኛውን ውስጣዊ ደስታና የመኖር ጉጉት ሊያገኝ የሚችልበት እድል ጠባብ ነው። የተደረገን ተግባር እየደጋገሙ መኖር ምናልባት ገቢ ሊያስገኝልህና ለመኖር ሊጠቅምህ ይችላል ነገር ግን አንተን አንተ አያደርግህም፤ የተለየውን ማንነትህን አያወጣውም፤ ተፅዕኖ ፈጣሪነትህን አያጎላውም። አዎ! ጀግናዬ..! የእራስህ ይሻልሃል! በማንም ስራ ለመክበር ከመሞከርህ በፊት ጥረትህን ሁሉ የእራስህን ነገር ማውጣት ላይ አውለው፤ እራስህ ላይ invest አድርግ፤ እራስህን አጎልብት። የተሟላና ስኬታማ ህይወት ለመኖር የእራስህ ልዩ አፈጣጠር፣ አንተነትህና ውስጣዊ ማንነትህ እጅግ በጣም በቂ ነው። ህይወትህ ሙሉ የሚሆነው ከሰዎች በተገለበጠና ምንም አይነት አዲስ ስሜት ባልታከለበት ተግባር ሳይሆን ቢያንስም በእራስህ በሆነ፣ በሚገልፅህ፣ በሚወክልህ ልዩ የእራስህ መገለጫ ተግባር መሆኑን አስተውል። ልዩነት ውስጥ የስሜት ውበት አለ፤ የጠዓም ማራኪነት አለ፤ የሙላት ደስታ አለ። እርካታን ፍለጋ ማስመሰል ውስጥ መግባት አይጠበቅብህም። መስለህ ሳይሆን እራስህን ሆነህ በእራስህ አለም መደሰት ትችላለህ። አዎ! ምንም ነገር ከእራስህ ንፁ ወንዝ ከተቀዳው ውሃ በላይ አያረካህም። የህይወትህ ጠዓም ከእራስህ ምንጭ የሚቀዳ ነው። መድከምህ ካልቀረ የእራስህን መንግስት ለመገንባት ድከም፤ መልፋትህ ካልቀረ እራስህን በእራስህ መልክ ለማበልፀግ ልፋ። እየገለበጥክ፣ የተሰራውን እየደገምክ፣ እየኮረጅክ ከሆነ የፈጠራ አቅምህን እየገደልክ እንደሆነ አስታውስ። ያንተ የሆነ፣ ባንተ ላይ ብቻ የሚያምር፣ መገለጫህ የሆነ አንድ ተግባር እንደሚኖር እመን። አንዴ ፍለጋውን ስትጀምር ምቾትን ብታጣም የኋላ ኋላ የተለየውን ብቾትና ደስታ የሚሰጥህ እርሱ እንደሆነ አስታውስ። ከሌላው በመገልበጥ፣ በቀጂነትና በአስመሳይነት ከመጓዝ እራስን መሆን፣ በእራስ ቀለም መድመቅ፣ በገዛ ማንነት መኩራት እጅጉን የተሻለ ነውና እራስህን ሁን፤ እንደራስህ ኑር፤ እንደራስህ ተጓዝ። ግሩም ድንቅ ቀን ይሁንልን!
Показать все...
👍 11👏 1
እያለህ አጊጥበት! ዘላለም አብሮን የሚቆይ ነገር የለም፤ የእኔ የምንለው የገዛ አካላችን እንኳን አንድ ቀን ይከዳናል፤ ያረጃል፤ ያልፋል፤ ይጠፋል፤ እንዳልነበርም ይሆናል። የሆነው ሆኖ፣ የሆነው ላይቀየር፣ ያልሆንከውን ላትሆነው "እንደዚህ ቢሆን፣ እንደዛ ቢሆን ይሻለኝ ነበር" በማለት ማማረጥህንና ያለህን ማማረርህን አቁም። እንዳለህ ማመስገን ትችላለህ፤ ያለህን መውደድ፣ ማድነቅ፣ ማሞገስ፣ በእርሱም መኩራት ትችላለህ። ተጨማሪ ነገር እየፈለክ ያለህ እስኪወሰድ አትጠብቅ። አዎ! ጀግኒት..! ተፈጥሮ አስውቦሽ፣ ዋናውን ነገር ሰቶሽ ሳለ በሰው ሰራሽ በጊዜያዊ ቁስ ለማጌጥ አትሽቀዳደሚ። ተጨመሪ ቁስ የሚያስፈልግሽ ጊዜ እስኪደርስ ባለሽ ማማርን፣ በተሰጠሽ መዘነጥን ተለማመጂ። ዛሬ ያለሽ ሁሉ ጊዜው ያልፋል፤ ያረጃል፤ በጊዜው ግን በነፃነት ተጠቀሚበት፤ ውደጂው፣ ተቀበይው፣ ተደሰቺበት። አሁን ሁሉ ነገርሽ ሙሉ ነው፣ ውብ ነው ከጊዜ ቦሃላ ግን ላይሆን ይችላል። ሙሉና ውብ ሆነሽ ሳለ የጎደለሽና ያነሰሽ ነገር እንዳለ ተጨማሪ ነገር ከማሳደድ ብትቆጠቢ በእራስሽ እንድትኮሪ ያደርግሻል። አዎ! ጀግናዬ..! ከሌለ የለም፤ ካለፈም አለፈ፤ ከቀረም ይቀራልና እያለህ አጊጥበት፤ ድመቅበት፤ ታይበት። ዛሬ ሰውነትህን እንደፈለክ ማዘዝ ትችላለህ፤ ተነስ ስትለው የሚነሳ፤ ተቀመጥ ስትለው የሚቀመጥ፣ የፈለከውን የሚፈፅምልህ ብርቱና ጠንካራ ሰውነት አለህ። አንድ ቀን ግን ላትቆጣጠረው ትችላለህና በእጅህ እያለ ተጠቀምበት፤ ያሰብከውን ሁሉ በጊዜ ከውንበት። የሚያደምቅህን ተጨማሪ ጊዜያዊ ነገር ከምትፈልግ ባለህና በተፈጥሮዓዊ ነገር ደምቀህ ለመታየት ሞክር። ያለህን፣ የተሰጠህን፣ ያንተ ብቻ የሆነውን እያንዳንዱን ስጦታህን ተጠቀም፤ ኩራበት፤ አጊጥበት። የቀረብህን ጥቂት ነገር ፍለጋ ያለህን፣ የተሰጠህን ውድ ሰጦታም ዋጋ አታሳጣው። ውብ ምሽት ይሁንልን!
Показать все...
👍 10
Фото недоступноПоказать в Telegram
👍 2
#ሰላም_ውድ_ቤተሰቦች * ያለህን ጊዜ አጣጥመው! * የማይጠቅምህን ነገር ያለማቋረጥ ማድረግህን ተው! ለአንተ አስፈለጊ የሆኑ ነገሮች ለማድረግ ጊዜ አትውሰድ! እናም ያለህን ጊዜ አጣጥመው። ህይወት አጭር ስትሆን ማድረግ የምትችለው እንደዚያ ነው! —Paul Graham በዚህ ምድር ላይ ለመኖር በተሰጠህ አጭር እድሜህ የማይጠቅምህን በማድረግ ጊዜህን አታባክን። ይልቁንም ያለችህን ጊዜ ለአንተ እና ለሌሎች የሚጠቅም ነገር ብቻ በማድረግ ለአንተ ደስታን ለሌሎች ሃሴትን ፍጠር። መልካም የስኬት ቀን ተመኘን!!! (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣የስኬት ስነልቦና ለመገንባት የሚያስችሉ ነገሮችን ለማግኘት  ቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።) Telegram- 👇👇👇 @drwedajenehmahrene
Показать все...
👍 15
ልዮ የስነልቦና ስልጠና መሰልጠን ምፈልጉ በኔ ጎበዝ ተማራዎች ስልጠና ጀምረዋል ምፈልጉ አናግሩኝ ።
Показать все...
👍 8
Фото недоступноПоказать в Telegram
#ሰላም_ውድ_ቤተሰቦች በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ። : " በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። : ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" አንድ ነገር ልንገራችሁ! : በህይወትሁ ማንንም አትውቀሱ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃችሀል መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችሀል ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችሀል ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችሀል። (ጋሽ ስብሃት ገብረእግዚአብሄር) (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣የስኬት ስነልቦና ለመገንባት የሚያስችሉ ነገሮችን ለማግኘት  ቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።) Telegram- 👇👇👇 t.me/gondgroup T.me/gondgroup T.me/gondgroup
Показать все...
👍 5
** #በዓለም_ትልቁ_ሀብት_አመለካከት_ነው። -#ፈጣሪን አመስጋኝ ብንሆን ህይወታችን ብሩህ ይሆናል። መፍትሄ ፈላጊዎች እንጂ እንከን አሳሾች አንሆንም። -#ብሩህ አመለካከት ብንይዝ  ቀናችንም... ህይወታችንም ይስተካከል። -#ተነጫናጭና ብሶተኛ ከሆንን የሚያጋጥመንም እንደዛው ነው። ጥሩ አመለካከት ካለን ጥሩ እንሆናለን። መጥፎ አመለካከት ካለን መጥፎ ነገሮች ውስጥ እንገኛለን! -ሁልጊዜም በውስጣችን ስለምንገነባው አመለካከት ጥንቃቄ እናድርግ! 👍ውስጣችን በገነባነው ልክ ነው መልስ የሚሰጠን። (በየቀኑ አነቃቂ መልእክቶችን፣የስኬት ስነልቦና ለመገንባት የሚያስችሉ ነገሮችን ለማግኘት  ቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ።) Telegram- 👇👇👇 @drwedajenehmahrene
Показать все...
👏 13👍 1
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.