cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም ቤ/ክ መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት

ይህ በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ (አዲስ አበባ) የሚገኘው የገነተ ኢየሱስ ገነተ ማርያም አብያተ ክርስቲያናት መሠረተ ሃይማኖት ሰ/ት/ቤት ይፋዊ የቴሌግራም ገፅ ነው። እንኳን በደኅና መጡ!

Больше
Рекламные посты
1 328
Подписчики
+424 часа
+107 дней
+2730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰላም እንደምን አደራችሁ የማኅበራዊ ሚዲያ ተከታታዩቻችን እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ ዛሬ ጠዋት ከቀኑ 4:00 ሰዓት ይጠብቁን 🙏
Показать все...
፫- ሁለቱንም ጌታ ስማቸውን ለውጦታል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አስቀድሞ የዮና ልጅ ስምዖን ተብሎ ይጠራ ነበር። (ዮሐ. ፳፩፡፲፭) ጌታም ጴጥሮስ ብሎ ስያሜ አወጣለት። የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ። እኔም እልሃለሁ፥ አንተ ጴጥሮስ ነህ፥ በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም። (ማቴ. ፲፮፡፲፯-፲፰) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አስቀድሞ ለአገልግሎት ሲጠራ ስሙ ሳውል ተብሎ ይጠራ ነበር። በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። (ሐዋ. ፱፡፬) በአገልግሎቱ ጽናት ጳውሎስ የሚል ስያሜ ተሰጠው። ፬- ሁለቱም ድንቅና ተአምራትን አድርገዋል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስላደረገው ድንቅ እንዲህ ተብሎ በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፏል፦ ጴጥሮስም በየስፍራው ሁሉ ሲዞር በልዳ ወደሚኖሩ ቅዱሳን ደግሞ ወረደ። በዚያም ከስምንት ዓመት ጀምሮ በአልጋ ላይ ተኝቶ የነበረውን ኤንያ የሚሉትን አንድ ሰው አገኘ፤ እርሱም ሽባ ነበረ። ጴጥሮስም። ኤንያ ሆይ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈውስሃል፤ ተነሣ ለራስህም አንጥፍ አለው። ወዲያውም ተነሣ። በልዳና በሰሮናም የሚኖሩ ሁሉ አይተውት ወደ ጌታ ዘወር አሉ። (ሐዋ.፱፡፴፪-፴፭) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ታላላቅ ተአምራቶችና ድንቅ ስለማድረጉ፦ እግዚአብሔርም በጳውሎስ እጅ የሚያስገርም ተአምራት ያደርግ ነበር፤ ስለዚህም ከአካሉ ጨርቅ ወይም ልብስ ወደ ድውዮች ይወስዱ ነበር፥ ደዌያቸውም ይለቃቸው ነበር ክፉዎች መናፍስትም ይወጡ ነበር። (ሐዋ. ፲፱፡፲፩-፲፪) ፭- ሁለቱም ሙታንን አሥነስተዋል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ጣቢታ የተባለችውን ብላቴና ስለማሥነሳቱ፦ በኢዮጴም ጣቢታ የሚሉአት አንዲት ደቀ መዝሙር ነበረች፥ ትርጓሜውም ዶርቃ ማለት ነው፤ እርስዋም መልካም ነገር የሞላባት ምጽዋትም የምታደርግ ነበረች። በዚያም ወራት ታመመችና ሞተች፤ ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች። እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት። (ሐዋ. ፱፡፴፮-፵፩) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አውጤኪስን ከሞት ስለማሥነሳቱ፦ አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት። ጳውሎስም ወርዶ በላዩ ወደቀ፥ አቅፎም። ነፍሱ አለችበትና አትንጫጩ አላቸው። ወጥቶም እንጀራ ቆርሶም በላ፤ ብዙ ጊዜም እስኪነጋ ድረስ ተነጋገረ እንዲህም ሄደ። ብላቴናውንም ደኅና ሆኖ ወሰዱት እጅግም ተጽናኑ። (ሐዋ. ፳፡፯-፲፪) ፮- ሁለቱም የሰማዕትነት አክሊል አግኝተዋል፦ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በስልሣ ሰባት ዓ.ም. በኔሮን ቄሣር እጅ ቁልቁል ተሰቅሎ ሕይወቱን አጥቷል (ሰማዕትነትን ተቀብሏል)። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በስልሣ ሰባት ዓ.ም. በኔሮን ቄሣር እጅ አንገቱን ተቆርጦ ሕይወቱን አጥቷል (ሰማዕትነትን ተቀብሏል)   የቅዱሳኑ በረከት ዘወትር ከእኛ ጋር ይሁን ወስብሐት ለእግዚአብሔር !! ምንጭ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ጥሩ ምንጭ (ኅሩይ ወልደ ሥላሴ) ፲፱፻፺፭ SAINT PETER AND PAUL  (POPE SHENOUDA )
Показать все...
Фото недоступноПоказать в Telegram
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በየዓመቱ ሐምሌ ፭ ቀን ጴጥሮስ ወጳውሎስ በማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እና ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልካሙን የክርስትና ገድል ተጋድለው ሰማዕትነት የተቀበሉበትን ቀን በታላቅና በተለየ ሁኔታ ታከብራለች ። ክርስትናን በማስፋፋት ከፍተኛውን ሚና የተጫወቱት እነዚህ ቅዱሳን አባቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መልእክታትን ጽፈዋል ። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ስምንት ምዕራፎችን የያዘ ሁለት መልእክታትን ሲጽፍ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ አንድ መቶ ምዕራፎችን የያዘ አሥራ-አራት መልእክታትን ጽፏል። ለአግልግሎት የጠራቸውም የክብር ባለቤት የሆነው አምላካችን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ዓሣ በማጥመድ ሥራ ላይ ሳለ ለዚህ ታላቅ አገልግሎት ሲጠራ (ማቴ ፬፦፲፰) ሐዋርያው ተከተሉት። (ማቴ. ፬፡ ፲፰-፳) ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጌታ የተጠራው ወደ ደማስቆ ይጓዝ በነበረበት ጊዜ ነው። ሳውል ግን የጌታን ደቀ መዛሙርት እንዲገድላቸው ገና እየዛተ ወደ ሊቀ ካህናት ሄደ ፥ በዚህ መንገድ ያሉትንም ሰዎች ወንዶችንም ሴቶችንም ቢያገኝ ፥ እያሰረ ወደ ኢየሩሳሌም ያመጣቸው ዘንድ በደማስቆ ላሉት ምኵራቦች ደብዳቤ ከእርሱ ለመነ። ሲሄድም ወደ ደማስቆ በቀረበ ጊዜ ድንገት በእርሱ ዙሪያ ከሰማይ ብርሃን አንጸባረቀ፤ በምድርም ላይ ወድቆ ሳለ። ሳውል ሳውል፥ ስለ ምን ታሳድደኛለህ? የሚለውን ድምፅ ሰማ። ጌታ ሆይ፥ ማን ነህ? አለው። እርሱም። አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ፤ የመውጊያውን ብረት ብትቃወም ለአንተ ይብስብሃል አለው። (ሐዋ. ፱፡፩-፭)
Показать все...
ፓትርያርክ በጨለማ አፍኖ ወስዶ በኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት በዙፋን አዳራሽ ሥር የሚገኝ የወይን ጠጅ ማቀዝቀዣ ክፍል አስገብቶ ለብቻቸው ካሰራቸው በኋላ ‹‹ሲጠበቅ የቆየው ፍርድ›› በሚል ርእስ መግለጫ አወጣባቸው ሐምሌ 7 ቀን 1971 ዓ.ም በልዑል ራስ ዐሥራተ ካሳ ግቢ ውስጥ በሰዋራ ስፍራ የተደበቁ ሥልጡን ኮማንዶዎች በገመድ አንቀው ከገደሏቸው በኋላ በዘግናኝ ኹኔታ ከተገደሉ ሌሎች እስረኞች ጋራ በአጥሩ ካባ ሥር በእርድ መልክ በተቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ ጥለው አፈር አለበሷቸው የቅዱስነታቸውን መቃብርና አሠቃቂ አሟሟት ያውቁ የነበሩ በሰጡት ጥቆማ መሠረት ነበር ቦታው ከ17 ዓመታት የታወቀው መቃብሩ ጥልቀት ስለነበረው ቁፋሮው ከሚያዝያ 20 – 22ቀን 1984 ዓ.ም ቆይቷል አፅማቸው ሚያዝያ 23 ቀን ሣጥኑ በወርቀ ዘቦ የተጌጠ መጎናጸፊያ ተላብሶ በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ትክሻ ተይዞ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ለጊዜው እንዲያርፍ ተደርጓል ። ሐምሌ 3 ቀን ደግሞ ዐፅማቸው ወደ መንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተወስዶ ጸሎተ ፍትሐት ሲደረስበት አድሯል በማግሥቱ ሐምሌ 4 ቀን ከውጭ አገር ለበዓሉ በመጡ የአብያተ ክርስቲያን ልኡካን የልዩ ልዩ እምነት ማኅበሮች መሪዎችና ካህናት በርካታ ምእመናን በተገኙበት በዐውደ ምሕረቱ ልዩ ሥነ ሥርዓተ ተደረገ የቅዱስነታቸው ትሩፋትና ገድል በወቅቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዐቃቤ መንበር ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ባደረጉት ንግግር ከተገለጸ በኋላ የሚከተለውን የቅድስና ሥያሜ ዐዋጅ አሰሙ፡- ‹‹ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ከዛሬ ጀምሮ ‹ቴዎፍሎስ ቅዱስ ሰማዕት› ተብለው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል›› በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት ኹሉ ‹‹ይደልዎ›› በማለት መንፈሳዊ ዐዋጁን እንደተቀበሉት በወቅቱ ተዘግቧል የቅዱስነታቸው አፅም ዕለቱኑ ተወስዶ በክብር ያረፈው ራሳቸው ባሠሩት በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል ነው በቅፅሩም በቅዱስነታቸው ስም የተሰየመ ቤተ መዘክር ይገኛል በረከታቸው ይደርብን ።
Показать все...
👍 3
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሁለተኛው (ከ1951 እስከ 1971 ዓም) ፓትርያርክ የነበሩና በአጠቃላይ በዘመናቸው ቤተክርስትያኗን በልዩ ልዩ ቦታዎች ለ20 ዓመታት አገልግለዋል አባታችን ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ራስን መቻል መንፈሳዊና ዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጋራ ለመቀራረብ ለክርስቲያናዊ ተግባርና ልማት ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ጽናት ይጥሩ የነበሩትን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስን ደርግ የካቲት 9 ቀን1968 ዓ.ም ከመንበረ
Показать все...
" እነሆ የሃይማኖት ፍሬ " ቅዱስ ድዮስቆሮስ ከሁሉ አስቀድመን በነገሮች ሁሉ ያገዛችሁ የረዳችሁን እግዚአብሔርን እያመሰገንን  ከተለያዩ ዮንቨርሲቲ ከተመረቁ የሃይማኖት ፍሬ ከሆኑት መካከል :- 👉 መ/ር ኤርምያስ ክብረአብ በዶክትሬት ከአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ 👉 መ/ር ዮሐንስ ብርሃኑ ከቅድስት ሥላሴ ዮንቨርስቲ በነገረ መለኮት በድግሪ 👉 ኢ/ር ሜላት ከበደ ከደብረ ማርቆስ ዮንቨርሲቲ በኢንጅነሪግ የተመረቁ 👉 ዲ/ን አዲሱ ተ/አብ ከአዲስ አበባ ዮንቨርሲቲ በማኔጅመንት የተመረቁ 👉 መምህርት ኢየሩሳሌም ምሕረት ከደብረ ብርሃን ዮንቨርሲቲ በመምህርትነት ስለተመረቃችሁ ገነተኢየሱስንና እናቱ ወይብላ ማርያምን እያመሰገንን ለዚህ ክብር በመብቃታችሁ የተሰማንን ደስታ እየገለጽን ሁሉን ያደረገን እግዚአብሔርን ስለእናንተ እናመሠግናለን እንኳን ደስ አላቹ ። “ ለአምላካችንና ለአባታችንም እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን ፤ አሜን ። ” ፊልጵስዩስ ፬ ፥ ፳ ከመሰረተ ሃይማኖት ሰንበት ትምህርት ቤት
Показать все...
👏 7👍 2
Фото недоступноПоказать в Telegram
በጸሎትና በልመናም ሁሉ ዘወትር በመንፈስ ጸልዩ፤ በዚህም አሳብ ስለ ቅዱሳን ሁሉ እየለመናችሁ በመጽናት ሁሉ ትጉ፤”   — ኤፌሶን 6፥18 ከቅዱሳን ኅብረት ጋር ኑ አብረን እናስቀድስ ቀዳሚት ሰንበትን እና ዕለተ ሰንበተ ክርስቲያንን የአገልግሎት ልብስ በመልበስ የቅዳሴ አገልግሎት በመፈጸም የሰዓት አስራታችንን ለእግዚአብሔር እንገብር ።   ማስታወሻ የአገልግሎት ልብስ ሌሊት 10:00 ሰዓት ላይ የሚሰጥ መሆኑን በመገንዘብ በዓለ ጰራቅሊጦስ ቅዳሴ በማስቀደስ እንድናገለግል ይኹን ።      እግዚአብሔር አገልግሎታችንን ይባርክ
Показать все...
🙏 5
Фото недоступноПоказать в Telegram
ሰላም እንደምን አረፈዳችሁ ውድ አባላት ዛሬ በቀን 29/10/2016 ዓ.ም መዝጊያ ወርኃዊ መርኃግብራችን “ ሁሉ ይፈልጉሃል ” ማርቆስ 1፥37 በሚል ርዕስ በመምህር ብሩክ ይሰጣል በመርኃግብሩ ላይ በመገኘት አብዝታችሁ ታተርፉ ዘንድ ጋበዝኖ ። “በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ፤” — ዘዳግም 30፥19
Показать все...
🙏 1
Фото недоступноПоказать в Telegram
አንጋፋው የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት ከ270 በላይ ደቀ መዛሙርትን ያስመርቃል። ሰኔ ፳፰/፳፻፲፮ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አንጋፋ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በነገው ዕለት ቅዳሜ ሰኔ ፳፱ ቀን ፳፻፲፮ ዓ/ም ከ270 በላይ ደቀ መዛሙርትን ያስመርቃል። ዩኒቨርሲቲው የሚያስመርቃቸው ደቀመዛሙርት በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በድግሪ በቀንና በማታ እንዲሁም ርቀት በማስተርስ በመደበኛ ትምህርታቸውን የተከታተሉ እንደሆነም ተገልጿል። በ2016 ዓ/ም ለትምህርት ትጥራት ትግበራ ከፍተኛ ትኩረት በመሰጠቱ ምክንያት የተመራቂዎች ቁጥር ከሌሎች ዓመታት አነስተኛ ሆኗልም ተብሏል። የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲት 1935 ዓ/ም ጀምሮ የተለያዩ ደረጃዎችን እያለፈ የመጣ ከፓትርያርክ እስከ ሰባክያነ ወንጌል የወጡበት የቤተ ክርስቲያናችን ባለውለታ ተቋም ነው። ++++++++++++++++++++++++++++++++++++ #ቅድስት በምትሆን በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደ የአብ በረከት የወልድ ፍቅር የመንፈስ ቅዱስ አንድነት በሁላችን ላይ ይውረድ ዕፅፍ ድርብ ይሁን" ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ.፻፴፮
Показать все...
👍 3
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.