ru
Feedback
G-Tutorialclass

G-Tutorialclass

Открыть в Telegram

Impossible is possible with learning & reading.

Больше
904
Подписчики
Нет данных24 часа
-57 дней
-1530 дней
Архив постов
የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት 29/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ተባለ። ፈተናው መቼ
የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት 29/2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ተባለ። ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ ገና #አለመወሰኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል። የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን አሁንም ገና እንዳልተወሰነ ገልፀዋል። ኤጀንሲው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ሲደረስ በይፋ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።(tikvahuniversity) @ethio_mereja_university @ethio_mereja_university

#Wolkite በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ "ሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ ህዝብ " በሚል መሪ ቃል በወልቂጤ ከተማ አዘጋጅነት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ መነሻ አደርጎ የ15 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር
#Wolkite በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ "ሰላም እና አንድነት ለኢትዮጵያ ህዝብ " በሚል መሪ ቃል በወልቂጤ ከተማ አዘጋጅነት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ መነሻ አደርጎ የ15 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር በመካሔድ ላይ ይገኛል። ውድድሩን አትሌት ሻለቃ ዶ/ር ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚደንት አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ እንዲሁም የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ፋሪስ ደሊል የመክፈቻ ንግግር በማድረግ አስጀምረውታል። Via የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት @ethio_mereja_university @ethio_mereja_university

በመኖሪያ ቤቱ የተገደለው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር! ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ደምቢዶሎ ከተማ በራሱ ቤት የተገደለው የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ ቀጄላ ታሲሳ ጉዳይ እያወዛገበ ነው፡፡ መምህር ቀጄላ ታሲሳ ትምህርታቸውን ከሚከታተሉበት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ደምቢዶሎ ያቀኑት ባለፈው ቅዳሜ መሆኑንና እሁድ ማታ በገዛ ቤታቸው በፀጥታ ኃይሎች መገደላቸውን ቤተሰቦቻቸው ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ የመመህሩ ወላጅ እናት ወ/ሮ አጊቱ ቡልቻ እንዳሉት ልጃቸው የዘጠኝ ወር እርጉዝ የሆነችውን ባለቤቱን ለመጠየቅና በዓልን አብሯት ለማሳለፍ ከሚማርበት አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ እለት መምጣቱን ይናገራሉ፡፡ እሁድ ማምሻውን 1 ሰዓት ከ 30 ገደማ “ቁጥራቸው በርከት ያለ ነው” ባሉት የመንግስት የጸጥታ ኃይል ልብስ የለበሱ የመኖሪያ ቤት አጥሩን ከበው ግድያ መፈጸማቸውንም ተናግረዋል፡፡ ይህንኑን ድርጊት ለመንግስት አሳውቃችኋል ወይ? ከዚህ በፊትስ መምህር ቀጄላ በፀጥታ ኃይሎቹ ተፈልገው ያውቃሉን? ሲል ዶይቼ ቬሌ ለወ/ሮ አጊቱ ቡልቻ ላቀረበው ጥያቄ ግድያውን ለማንም አለማመልከታቸውንና መምህሩ ከዚህ ቀደም ለሦስት ዓመታት ሲያስተምርበት የነበረው ደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲን የፀጥታ አካላት የት እንዳለ መጠየቃቸውን ብቻ በጭምጭምታ መስማታቸውን ተናግረዋል፡፡ መምህር ቀጄላ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት ዕድል በማግኘት ከሚያስተምርበት ደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ስፍራው ያቀናው ባለፈው መስከረም ነበር፡፡ ስለጉዳዩ የተጠየቁት የቄለም ወለጋ ዞን የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተሰማ ዋሪዮ ጉዳዩ እንደሚባለው አይደለም ይላሉ፡፡ በጫካ የሚንቀሳቀስ ሸማቂ ቡድን “አባቶርቤ” በሚል የመለመላቸው ግድያውን ሳይፈጽሙት እንዳልቀረም ተናግረዋል፡፡ ከመመህር ቀጄላ ታሲሳ በተጨማሪ ሰሞኑን ብቻ በአከባቢው አራት ሰዎች ላይ ተመሳሳይ ጥቃት መፈጸሙንም በመግለጽ፤ ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ሁለቱ የመንግስት የጸጥታ አባላት ናቸው ብለዋል፡፡ የቄለም ወለጋ ዞን የጸጥታ አስተዳዳሪው በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች ታጣቂዎች እንደሚንቀሳቀሱና ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ በመቶዎች የሚቆጠሩ ግድያ መፈጸማቸውንም አብራርተዋል፡፡ ግድያውን ይፈጽማሉ ያሏቸው ታጣቂዎች የመንግስት የፀጥታ ልብስ ጭምር እንደሚጠቀሙም አክለዋል፡፡ ©ጀርመን ድምፅ @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news

ሰበር መረጃ ከአጣዬ‼️ማቆምያ ያጣው የአጣዬ ረብሻ አሁንም ሰዎች እየተገደሉ አየቆሰሉ ነው ዝርዝሩን ያድምጡ👇 https://youtu.be/M6vYJKZdMlE https://youtu.be/M6vYJKZdMlE

📚 ዩኒቨርስቲዎች የሚሰጡትን filed የያዛ ዶክሜንት ..! 💾Excel file @Free_Education_Ethiopia Stay safe 😷

❗️አዲሱ የዩንቨርስቲ ምርጫን በተመለከተ 📚 የሳይንስ እና የከፍተኛ ትምህርተ ሚኒስተር የሆነው ዌብሳይት ላይ Www.moshe.gov.et አዲስ መረጃ ወጥቷል ።መረጃውም ምደባ እንደቀድሞ እንዳልሆነ ተነግሯል ተጨማሪ 4 ዮኒቨርስቲዎች መጨመራቸው እና የዮኒቨርስቲ ምርጫችሁን በፊልድ ምርጫቹሁ መሰረት ነው የምትሞሉት...ማለትም ለምሳሌ አንድ ተማሪ አርክቴክት መማር ቢፈልግ አርክቴክት የሚሰጡ ግቢዎች የመጀመርያው ምርጫው ያደርገል ....ከዛም ሁለተኛው ምርጫው mechanical enegernig ቢሆን በምርጫው መሰረት ይህ ፊልድ የሚሰጡ ግቢዎች አስከትሎ ይሞላል ...እስከ ሮብ የዮኒቨርስቲ ምርጫችሁን እንደ አዲስ መሙላት እንዳለባችሁ አሳስበዋል ። ዮኒቨርስቲዎች ምን ፊልድ እንደሚሰጡ በምን እናውቃለን ❓ 📚 እንደድሮ ሁሉም ካንፓሶች አንድ አይነት ፊልድ አይሰጡም ዮኒቨርስቲዎች በ4 ምድብ ተከፋፍለዋል ... ከታች በለቀቅንላችሁ pdf የትኛው ግቢ የትኛውን ፊልድ እንደሚሰጥ ማየት ትችላላችሁ ....ከፊልዶቹ ፊትለፊት ካሉ ዮኒቨርስቲዎች የ * ምልክት ካለ ፊልዱ ይሰጣል ማለት ነው ባዶ ከሆነ ፊልዱ አይሰጥም .... ስለዚህ ምርጫችሁ የሆነው ፊልድ የሚሰጥባቸውን ግቢዎች ብቻ የመጀመርያ ምርጫችሁ ታረጋላችሁ ማለት ነው....። 📚 በpdfኡ መጨረሻ ላይ የምትፈልጉት ፊልድ የሚሰጡ ካንፓሶች (ዮኒቨርስቲዎች ) ብዛት ይናገራል ለምሳሌ ለ software engenerig የሚሰጡ ዮኒቨርስቲዎች ብዛት 14 ነው ስለሆነም የእናንተ የመደመርያ ፊልድ ምርጫ ሶፍትዌር ኢንጂነሪግ ከሆነ በዛ መሰረት 14 ቱን አስቀድማተችሀ ትመርጣላችሁ ( ከ14ቱ ደሞ እናንተ እንዲደርሳችሁ በፈለጋችሁ ቅደም ተከተል መሰረት ትሞላላችሁ ..) ...ከዛም ቀጣዮን የፊልድ ምርጫችሁን የሚሰጡትን ዮኒቨርስቲዎች ትሞላላችሁ ማለት ነው ። @Free_Education_Ethiopia Stay safe 😷

በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች ተደመሰሱ - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች መደምሰሳቸውን የኢፌዴሪ ሀገር
በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች ተደመሰሱ - ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ በትግራይ ስምንት አካባቢዎች የነበሩ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች መደምሰሳቸውን የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሠራዊት ግንባታ ዘርፍ ዋና አስተባባሪ ሌ/ጄ ባጫ ደበሌ አስታውቀዋል፡፡ የጁንታው ቡድን ወታደሮች እና ጠባቂዎች በትግራይ ሲያደርግ የነበረው የሽፍታ እንቅሰቃሴ በመከላከያ ሠራዊቱ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ውጊያ በማድረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ህገ ወጥ ቡድኑ ወደ መቐለ እርዳታ እና ሌሎች ነገሮችን ለማጓጓዝ የሚያስችሉ ወሳኝ ቦታዎችን በመያዝ ሲዋጋ የነበረ ቢሆንም በመከላከያ ሰራዊቱ ተደምስሷል ነው የተባለው፡፡ አሁን ላይ የጁንታው ወታደሮች እና ጠባቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እየሰጡ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች መያዙን የጎንደር ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ለፋና ብሮድካስቲን
በጎንደር ከተማ 168 ህገወጥ ቱርክ ሰራሽ  ሽጉጦች መያዙን የጎንደር ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ ህገወጥ የጦር መሳሪያው የተገኘው በተለምዶ ህዳሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግለሰብ ቤት በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ነው፡፡ የመኖሪያ ቤቱ  ባለቤት ለጊዜው የተሰወሩ ሲሆን ግለሰቧን ለመያዝና የህገወጥ የጦርመሳሪያውን  ምንጭ ለማወቅ ፖሊስ እየሰራ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተር እየሩስ አስማረ  ገልጸዋል። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news

"...ግብፅ 2ኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት" - ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም [አል ዓይን ኒውስ] የግብፅ ባለሥልጣናት በመጪው የክረምት ወቅት ሊሞላ ለታ
"...ግብፅ 2ኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ ናት" - ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም [አል ዓይን ኒውስ] የግብፅ ባለሥልጣናት በመጪው የክረምት ወቅት ሊሞላ ለታቀደው ሁለተኛ ዙር የሕዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ሀገሪቱ በመዘጋጀት ላይ እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡ የግብፅ መስኖ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢንጂነር ሞሐመድ ጋኔም ትላንት ለ “አል-አረቢያ” ቴሌቪዥን በሰጡት መግለጫ ፥ ግብፅ ሁለተኛው ዙር የሕዳሴ ግድብ ሙሌት ሊያስከትል የሚችለውን ተጽዕኖ ለመጋፈጥ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡ ቃል አቀባዩ የግድቡን 2ኛ ዙር የውሃ ሙሌት ተጽዕኖ ለመቀነስ በመስኖ መስክ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ መግባታቸውን አንስተዋል፡፡ “ይሁን እና በዓባይ ውሃ ላይ ያለንን ታሪካዊ መብት እንዳልተውን እናረጋግጣለን” በማለት በውሃ ክፍፍል ረገድ ግብፅ ያላት አቋም የጸና መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ቃል አቀባዩ አክለውም ፥ “በሕዳሴ ግድብ ጉዳይ የሁሉም ወገኖች ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ የምንጥር በመሆኑ ኢትዮጵያ ከግብፅና ከሱዳን ጋር ስምምነት ላይ ለመድረስ የተወሰነ የአቋም ለውጥ ማሳየት አለባት” ብለዋል፡፡ “መረጃ ከመለዋወጥ በፊት በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ እንፈልጋለን” ሲሉም ነው ኢንጂነር ሞሐመድ የሀገራቸውን አቋም የገለጹት፡፡ @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news

አሳዛኝ ዜና ከነቀምት በቦንብ ፍንዳታ ሰዎች ሞቱ ቆሰሉ | የኢትዮ ሱዳን ድንበር ጉዳይ አይሏል ዝርዝር መረጃ ይዘናል ያድምጡ 👇 https://youtu.be/lRwysfYzhL4 https://youtu.be/lRwysfYzhL4

🔝 ምርጥ 11 ተማሪዋች (2012) 👏👏👏 1️⃣ 669 ➖ BROOK BALKACHEW NIGATU ST.JOSEPH A-A(R) ➖ 361757 2️⃣ 665 ➖ NAOL BELETE ADUGNA EXCEL(R
🔝 ምርጥ 11 ተማሪዋች (2012) 👏👏👏 1️⃣ 669 ➖ BROOK BALKACHEW NIGATU ST.JOSEPH A-A(R) ➖ 361757 2️⃣ 665 ➖ NAOL BELETE ADUGNA EXCEL(R) ➖342175 3️⃣ 657 ➖ AEMIRO DEMEMEW YILAKU QUARIT(R) ➖ 40895 3️⃣ 657 ➖ BILEN MEHALEK DANA WOLAYTA LIQA(R) ➖350501 5️⃣ 656 ➖ ABENEZER TADESSE AMANUEL SCHOOL OF TOMORROW(YE)(R) ➖ 369782 6️⃣ 655 ➖ BINIYAM GETACHW MENA WOLAYTA LIQA(R) ➖ 350502 6️⃣ 655 ➖ TADIWOS YEHUALASHET KEBEDE KIDUS RAGUEL(R) ➖353940 8️⃣ 653 ➖ LEUL WUJIRA BERHE ETHIO BIHERAWI(R) ➖354931 8️⃣ 653 ➖ NAOL SAMUEL EREGA ODA-SPECIAL BOARDING(R) ➖342015 🔟 652 ➖ MILLION TOLESSA SEDI WOMBERA(R) ➖277313 🔟 652 ➖ ISRAEL WOLDEGIORGIS WANGORE WACHAMO(R) ➖292519 #SHARE

ባለፈው ወር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን እና በኦሮሞ ብሄረሰብ ልዩ ዞን በተቀሰቀሰው ግጭት ከ300 በላይ ሰዎች እንደሞቱ እና 369 ደሞ እንደቆሰሉ የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር እንዳለ ኃይሌ መናገራቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል። የኦሮሞ አስተዳደር ዞን አንድ ሃላፊ ደሞ በዞኑ ብቻ 68 ሰዎች እንደተገደሉ እና 114 እንደቆሰሉ ተናግረዋል። ለግጭቱ መንግሥት የሰጠው ምላሽ የዘገየ እንደነበር የጠቀሱት የፌደራሉ እንባ ጠባቂ፣ አሁንም ፌደራል መንግሥቱ ችግሩን ለመፍታት ጣልቃ እንዲገባ መጠየቃቸውን ዘገባው አመልክታል። ዋዜማ - ራዲዮ @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news

#ማስተካከያ‼️ ትላንት ይፋ በተደረገው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመቁረጫ ነጥብ ላይ የተደረገ ማስተካከያ (መስማት ለተሳናቸው እና ለአይነስውራን) እንደሚከተለው ቀርቧል። ተፈጥሮ ሳይንስ ፦ - መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 275 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ - መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ ማህበራዊ ሳይንስ ፦ - መስማት ለተሳናቸው ወንድ ተማሪዎች 270 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ - መስማት ለተሳናቸው ሴት ተማሪዎች 265 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ - ለአይነስውራን ወንድ ተማሪዎች 240 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ - ለአይነስውራን ሴት ተማሪዎች 235 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ መረጀውን ያገኘነው ከMoSHE ነው። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news

ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል። በመዲናዋ ትናንት ሌሊት በአራት የተለያዩ አካባቢዎች በደረሰ የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወደመ! የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ ለኢዜአ እንደገለጹት የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው መልካ ሸኔ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12:50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል። በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች መሞታቸውን ተናግረዋል፡፡ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል። በተጨማሪም በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል። በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል። እንደ አቶ ጉልላት ገለፃ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከ ወረዳ 8 የተከሰተው አደጋ መንስኤው አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል። @ethio_mereja_news @ethio_mereja_news

#Update የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦ - በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። - በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ
+2
#Update የግል ተፈታኞችን በተመለከተ የመቁረጫ ነጥብ ፦ - በተፈጥሮ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። - በማህበራዊ ሳይንስ በግል የተፈተኑ ተማሪዎች (በሁሉም ፆታዎች) 385 እና ከዚያ በላይ ያስመዘገቡ። ከኢፌድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (@MinistryoSHE) የመቁረጫ ነጥብን በተመለከተ የተላከልንን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ያንብቡ ፤ ለሌሎችም ያጋሩ። @Free_Education_Ethiopia Stay Safe!

61.jpg1.30 MB

51.jpg1.76 MB

41.jpg1.61 MB

51.jpg1.76 MB