cookie

Мы используем файлы cookie для улучшения сервиса. Нажав кнопку «Принять все», вы соглашаетесь с использованием cookies.

avatar

ምስለ ፍቁር ወልዳ

[ ጽዮን እናቴ ሆይ ከጎኔ አትሽሺ ] [ማነው የሚያፈቅረው እስከሞት ድረስ?] " እርስ በርሳችሁ ከመዋደድ በቀር ለማንም ዕዳ አይኑርባችሁ፥ ሌላውን የሚወድ ሕግን ፈጽሞታልና።" (ወደ ሮሜ ሰዎች 13:8) [የእግዚአብሔርን ቃል በማጋራት ግዴታዎን ይወጡ።] ሀሳብ አስተያየቶን ይላኩ @Mesle_Fikur_Welda_Bot

Больше
Рекламные посты
1 336
Подписчики
-224 часа
+1047 дней
+6730 дней

Загрузка данных...

Прирост подписчиков

Загрузка данных...

Фото недоступноПоказать в Telegram
Фото недоступноПоказать в Telegram
=>+"+ እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም #ሥላሴ እና ለቅዱሳን አበው #አብርሃም: #አባ_ሲኖዳ እና #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋሥጫ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ +"+ +"+ #ሥሉስ_ቅዱስ +"+ =>በአንድነቱ ምንታዌ (ሁለትነት): በሦስትነቱ ርባዔ (አራትነት) የሌለበት የዘለዓለም አምላክ: የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር ነው:: #አብ : #ወልድ : #መንፈስ_ቅዱስ በስም: በአካል: በግብር ሦስትነት: በባሕርይ: በሕልውናና በፈቃድ አንድነት የጸኑ ናቸው:: በዚህ ጊዜ ተገኙ: በዚህ ጊዜ ያልፋሉ አይባሉም:: መጀመሪያም መጨረሻም እነርሱ ናቸውና:: +ርሕሩሐን ናቸውና በእናት ሥርዓት " #ቅድስት_ሥላሴ " እንላቸዋለን:: የሚጠላቸው (የማያምንባቸውን) አይጠሉም:: የሚወዳቸውን ግን እጽፍ ድርብ ይወዱታል:: በቤቱም መጥተው ያድራሉ:: +ከፍጥረታት ወገን ከእመቤታችን ቀጥሎ የአብርሃምን ያህል በሥላሴ ዘንድ የተወደደ ፍጡር የለም:: አባታችን #ቅዱስ_አብርሃም የደግነት ሁሉ አባት ነውና በኬብሮን በመምሬ ዛፍ ሥር ሥላሴን ተቀብሎ አስተናግዷል:: ሥላሴ አኀዜ ዓለም (ዓለምን በእጁ የያዘ) ነው:: ነገር ግን በፍቅር ለሚሻው በፍቅር ይመጣል:: +አባታችን አብርሃም በ99 ዓመቱ: እናታችን ሣራ በ89 ዓመቷ ሥላሴን በድንኩዋናቸው አስተናገዱ:: አብርሃም እግራቸውን አጠበ:: (ወይ መታደል!) በጀርባውም አዘላቸው:: (ድንቅ አባት!) ምሳቸውንም አቀረበላቸው:: እንደሚበሉ ሆኑለት:: በዚያው ዕለትም የይስሐቅን መወለድ አበሠሩት:: #ቅድስት_ሣራ ሳቀች:: እንደ ዘንድሮ ወገኖቻችን የማሾፍ አይደለም:: ደስታና ጉጉት የፈጠረው እንጂ:: ሥላሴ "ምንት አስሐቃ ለሣራ በባሕቲታ" ብለው ነበርና በዚህም ምክንያት ነው " #ይስሐቅ" የተባለው:: +ሥላሴን ያስተናገደች ድንኩዋን (ሐይመት) የድንግል እመቤታችን ማርያም ምሳሌ ናት:: በድንግል ላይ #አብ ለአጽንኦ: #መንፈስ_ቅዱስ ለአንጽሖ: #ወልድ በተለየ አካሉ ለሥጋዌ በእርሷ ላይ አርፈዋል / አድረዋልና:: +"+ #ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+ =>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:- ¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ ¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ ¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት ¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት ¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ ¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ ¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ ¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው:: +ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን (መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ ¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ ¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ ¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ ¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ ጋር የተነጋገረ ¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና ¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ አባት ነው:: +በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ #አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: ) +ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር:: +በዚህች ዕለት በ120 ዓመቱ ጌታችን ወርዶ ሲያሳርገው #አቡነ_ኪሮስ "ታላቅ ምሰሶ (ታላቅ ዛፍ) ወደቀ" ብለው አልቅሰዋል:: #ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው:: +"+ #አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ ( #GIYORGIS_OF_SEGLA ) +"+ =>ታላቁ ኢትዮዽያዊ ሊቅና ጻድቅ የተወለደው ወሎ #ጋስጫ ውስጥ በ1358 ዓ/ም ነው:: ከልጅነቱ ትምሕርት አልገባሕ ቢለውም በልቡናው ግን ቅን እና ታዛዥ ነበር:: መምሕሩ "ትምሕርት አይገባውምና ውሰዱት" ቢላቸው "የእግዚአብሔር ነውና ያገልግላችሁ" ብለው መለሱት:: መገፋቱን የተመለከተ #አባ_ጊዮርጊስ #እመቤታታችንን ከልቡ ይወዳት ነበረና ይማጸናት ገባ:: +ቀን ቀን ገዳሙን ሲረዳ: እሕል ሲፈጭና ሲያቦካ: ላቡንም ሲያፈስ ውሎ ሌሊት ደግሞ ሲጸልይ ያነጋ ነበር:: ድንግል እመቤታችን ጸሎቱን ሰምታለችና #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ መጣችለት:: በንጹሐት እጆቿ ባርካው ምሥጢርንም ነገረችው:: "ወነገረቶ ሐምስተ ቃላተ" እንዲል:: ጽዋዐ ልቡናን አጠጥታው ተሠወረችው:: +ከዚህች ሰዓት ጀምሮ አባ ጊዮርጊስ ፍጹም ተለወጠ:: በጽድቁ ላይ የሊቅነትን ካባ ደረበ:: ቅዱሳት መጻሕፍትን ይተነትናቸው: መናፍቃንንም ምላሽ ያሳጣቸው ገባ:: የተረጐማቸውና ያተታቸውን ሳይጨምር 41 ድርሰቶችን ደረሰ:: (መጽሐፈ ሰዓታት: መጽሐፈ ምሥጢር: አርጋኖን: ኆኅተ ብርሃን: ውዳሴ መስቀል: ወዘተ የእርሱ ድርሰቶች ነበሩ) +ስለ ሃይማኖትም ጠበቃ ነበር:: ስለ ቅድስናውና ውለታው የኢ/ ኦ/ተ/ቤ እንዲህ ትጠራዋለች:- 1. #ሊቀ_ሊቃውንት 2. #በላዔ_መጻሕፍት 3. #ዓምደ_ሃይማኖት 4. #ዳግማዊ_ቄርሎስ 5. #ጠቢብ_ወማዕምር +ጻድቁ ሊቅ በተወለደ በ60 ዓመቱ በ1418 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል:: አባ ጊዮርጊስ የተወለደውም ያረፈውም ሐምሌ 7 ቀን ነው:: =>የሥላሴ ቸርነት: የአብርሃም ደግነት: የአበው አባ ጊዮርጊስና አባ ሲኖዳ በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን:: =>ሐምሌ 7 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት= 1.ቅዱሳን አብርሃምና ሣራ (ሥላሴን ያስተናገዱ) 2.ብሥራተ ልደተ ይስሐቅ 3.ታላቁ አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን ሁሉ አለቃ) 4.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ሊቀ ሊቃውንት: ኢትዮዽያዊ የሃይማኖት ምሰሶ) 5.ቅዱስ አግናጥዮስ ዘአንጾኪያ (ምጥው ለአንበሳ) 6.አባ መቃቢስ 7.አባ አግራጥስ   =>ወርሐዊ በዓላት 1.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት 2.አባ ባውላ ገዳማዊ 3.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ    =>+ እግዚአብሔርም ለአብርሃም ተስፋ          በሰጠው ጊዜ:- 'በእውነት እየባረክሁ እባርክሃለሁ:: እያበዛሁም አበዛሃለሁ' ብሎ ከእርሱ በሚበልጥ በማንም ሊምል ስላልቻለ በራሱ ማለ:: እንዲሁም እርሱ ከታገሠ በሁዋላ ተስፋውን አገኘ:: (ዕብ 6:13)   =>+ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ሕብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን:: አሜን:: (ቆሮ 13:14)   ✝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝
Показать все...
††† ✝እንኳን ለሐዋርያው ቅዱስ መርቄሎስ እና ለነቢዩ ቅዱስ ዕዝራ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✝††† †††✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✝††† ††† ✝ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ ✝††† ††† ቅዱሱ በነገድ እሥራኤላዊ የሆነ የመጀመሪያው መቶ ክ/ዘመን ሰው ነው:: ጌታችን በመዋዕለ ስብከቱ ሲያስተምር በምሥጢሩና በተአምራቱ ተማርኮ ተከትሎታል:: ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስም ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ይሆን ዘንድ አድሎታል:: ከጌታችን ሕማማትና ስቅለት በፊትም ድውያንን መፈወስና አጋንንትን ማስወጣት ከቻሉ አርድእትም አንዱ ነው:: ቅዱስ መርቄሎስ በበዓለ ሃምሳ ጸጋ መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ ለወንጌል አገልግሎት ተሰማርቷል:: በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ለሰላሳ አራት ዓመታት በማገልገሉ ሐዋርያት ስሙን "ጳውሎስ" ብለውታል:: ጳውሎስ ማለት ብርሃን ማለት ነውና:: ልክ ሳውል "ጳውሎስ" እንደተባለው ማለት ነው:: ስሙ የግብር (በሥራ የሚገኝ) ስም ነው:: በዚህም ምክንያት ዛሬም ድረስ ቤተ ክርስቲያን የምትጠራው "ጳውሎስ የተባለው መርቄሎስ" እያለች ነው:: ቅዱስ መርቄሎስ በ60ዎቹ ዓ/ም አካባቢ ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በሮም ይሰብክ ነበር:: ኔሮን ቄሳር ሊቀ ሐዋርያትን ዘቅዝቆ ሲሰቅለው የተመለከተና ይህንኑ የጻፈ እርሱ ነበር:: ወታደሮቹ ቅዱስ ጴጥሮስን ገድለውት ሲሔዱ ቅዱስ መርቄሎስ እያነባ ቀርቦ: ችንካሮችንም ነቅሎ: ሊቀ ሐዋርያትን ከተሰቀለበት አወረደው:: በፍጥነት ዋጋው ውድ የሆነ ሽቱ አምጥቶ በቅዱስ ጴጥሮስ ሥጋ ላይ አፈሰሰና በፍቅርና በክብር ሊገንዘው ጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሊቀ ሐዋርያት አይኑን ግልጥ አድርጎ መርቄሎስን ተመለከተውና አለው:- "ልጄ! ምነው ለእኔ ይህንን ያሕል ሽቱ አባከንክ?" አለውና ተምልሶ ዐረፈ:: ቅዱስ መርቄሎስም እግዚአብሔርን እያመሰገነ በንጹሕ በፍታ ገንዞ እርሱ በሚያውቀው ቦታ ሠወረው:: ሊቀ ሐዋርያትን በመገነዙ የክብር ክብር ተሰጥቶታል:: ቅዱሱ አሁንም ስብከተ ወንጌልን ቀጠለ:: ከጥቂት ጊዜ በኋላ ግን እርሱም ተይዞ በኔሮን ፊት ቀረበ:: ኔሮን ቄሳር ቅዱስ መርቄሎስን ጠየቀው:: "እንዴት ባለ አሟሟት ልግደልህ? እንደ መምህርሕ ጴጥሮስ ወይስ ሌላ የምትፈልገው ዓይነት አሟሟት አለህ?" ቅዱስ መርቄሎስ መለሰለት:- "የትኛውም ዓይነት ሞት እኔን አያስፈራኝም:: የምፈልገው ወደ ጌታዬ ቶሎ መሔድ ብቻ ነው::" አለው:: ንጉሡ ኔሮንም ዘቅዝቃችሁ ስቀሉት አላቸው:: ወታደሮቹም በዚህች ዕለት እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘቅዝቀው ሰቅለው ገድለውታል:: †††✝ ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ✝ ††† ከክርስቶስ ልደት በፊት በ500 ዓመት አካባቢ የነበረ ¤እሥራኤል ከምርኮ ከተመለሱ በኋላ መጻሕፍት ተቃጥለው ጠፍተው ነበርና ስለ እነሱ አብዝቶ የለመነ ¤ጥበብን ሽቷልና እግዚአብሔር ቅዱስ ዑራኤልን የላከለት ¤በሊቀ መላእክት እጅም ጽዋዐ ልቡናን የጠጣ ¤ብዙ ምሥጢራት የተገለጡለት ¤ለአርባ ቀናት ምግብ ሳይበላ አገልጋዮቹ የጠፉ መጻሕፍትን እየነገራቸው የጻፉለት ¤መጽሐፈ ዕዝራ የተሰኘ መጽሐፍን ያዘጋጀና ¤በብሉይ ኪዳን ከነበሩ ዐበይት ነቢያተ ጽድቅ አንዱ የሆነ ታላቅ የእግዚአብሔር ሰው ነው:: ††† ስለ ቅድስናውም ሞትን አልቀመሰም:: በዚህች ዕለት ቅዱሳን መላእክት ብሔረ ሕያዋን ውስጥ አስገብተውታል:: ††† እግዚአብሔር ከሐዋርያውና ከነቢዩ በረከትን አይንሳን:: ††† ሐምሌ 6 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ መርቄሎስ ሐዋርያ (ከሰባ ሁለቱ አርድእት) 2.ቅዱስ ዕዝራ ነቢይ 3.ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ 4.ቅድስት ቴዎዳስያ ሰማዕት 5.ቅድስት ንስተሮኒን ዘኢየሩሳሌም ††† ወርኀዊ በዓላት 1.ቅድስት ደብረ ቁስቋም 2.አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን 3.አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል 4.ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ 5.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 6.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ 7.ቅድስት ሰሎሜ 8.አባ አርከ ሥሉስ 9.አባ ጽጌ ድንግል 10.ቅድስት አርሴማ ድንግል ††† "እግዚአብሔርም በቤተ ክርስቲያን አንዳንዶቹን አስቀድሞ ሐዋርያትን: ሁለተኛም ነቢያትን: ሦስተኛም አስተማሪዎችን: ቀጥሎም ተአምራት ማድረግን: ቀጥሎም የመፈወስን ስጦታ: እርዳታንም: አገዛዝንም: የልዩ ልዩ ዓይነት ልሳኖችንም አድርጓል:: ሁሉ ሐዋርያት ናቸውን? ሁሉስ ነቢያት ናቸውን? ሁሉስ አስተማሪዎች ናቸውን? . . . ነገር ግን የሚበልጠውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ::" ††† (፩ቆሮ. ፲፪፥፳፰) ††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Показать все...
Показать все...
ቅድስና | ክርስቲያናዊ የሕይወት ለውጥ ለማምጣት | መምህር ዘበነ ለማ

ቸነከሩአቸው። ሁለተኛም እስከ አንገት የሚደርስ በትከሻ አምሳል ሠሩ በፊትና በኋላም ቸነከሩአቸው ደግሞም መላ አካላቸውን የሚከብና ከአካላቸው ምንም እንዳይታይ የሚሸፍን የብረት ሠሌዳ ሠሩ ከወገቦቻቸውም ጋራ ቸነከሩት ችንካሮችም ተረከዛቸውን ነድለው ወደ ጭኖቻቸው እስከሚደርሱና እስከ አቈሳሏቸው ድረስ የብረት ጫማ ሠርተው እግሮቻቸውን ቸነከሩ። ደግሞ በመሸፈኛ አምሳል የብረት ሰናፉል ሠሩ ቀማሚዋችም መጡ አንድ መክሊት የሚመዝን እርሳስንም አመጡ ታላቅ የብረት ጋንንም ሰባት ልጥር የሰሊጥ ቅባትን አመጡ ሰቡንና አድሮ ማሩን የእሳቱንም ኋይል አብዝቶ የሚያነደውን ቅመሙን ከሙጫውና ከድኙ ጋር ቀላቀሉ ከዋርካና ከቁልቋል ከቅንጭብም ደም ሰባት ልጥር አንድ የወይን አረግንና ቅባት ያላቸውን ዕንጨቶች ሁሉ አመጡ። በጋን ውስጥ ያበሰሉትንና ያሟሙትንም ልዩ ልዩ ቅመማ ቅመም አምጥተው ከስጋቸው ጋር እስከሚጣበቅ በቅዱሳን ሐዋሪያት ሥጋ ላይ ባሉት ሠሌዳዎች ውስጥ ጨመሩት በእግራቸው እስከ ራሳቸውም ከፍ ከፍ እስከሚል ድረስ በእሳት ያቀለጡትን ያንን እርሳስ ጨመሩ ርዝመቱ ዐሥራ አምስት ክንድ በሆነ ወፍራም የጥድ ምሰሶ ላይም አቆሟቸውና ከበታቻቸው ፍሬ በሌለው በወይን ሐረግና በተልባ እሳቱን አቀጣጠሉ አንዳንዱ የእሳቱ ነበልባል ከሥጋቸው በላይ ከፍ ከፍ አለ ሐዋርያት ግን ወደ #እግዚአብሔር ይፀልዩ ነበር። ከመኳንንቱም በአንድ ልብ ርኅራኄን አሳደረና እንዲፈቷቸው አዘዘ ፈቷቸው በፈቷቸውና ሠሌዳውን ከስጋቸው ላይ በአስወገዱ ጊዜ ቆዳቸው ተገፈፈና ከብረቱ ሰሌዳዋች ጋር ወጣ ብዙ ደምም ከስጋቸው ፈሰሰ። ሰይጣንም በከተማው ሰዎች ልብ አደረና ሐዋርያትን ወደ እሳት ውስጥ መለሱአቸው ያን ጊዜ #ጌታችን ወርዶ የእሳቱን ነበልባል አጠፋው ዝናምን የተመላች ብርህት ደመናም መጥታ ቅዱሳን ሐዋርያትን ከበበቻቸው ከዚያችም አገር አንድ ጊዜ በደንጊያ በመወገር አንድ ጊዜም በፍላጸ በመንደፍ ብዙ ተሠቃዩ ከዚህም በሗላ ሙታንን በአነሡ ጊዜ የከተማው ሰዎች ሁሉ አመኑ አጠመቋቸውም ቤተ ክርስቲያንንም ሰሩላቸው ካህናትንም ሾሙላቸው በቀናች ሐይማኖትም እስቲጸኑ አስተማሩአቸው ከዚያም ወጥተው #ጌታችን ወደ አዘዛቸው ወደ ሌላ አገር ሔዱ። ክብር ይግባውና #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ለጳውሎስ ተገለጸለትና የመረጥኩህ ጳውሎስ ሆይ ሰላም ለአንተ ይሁን። መታሰቢያህ የሚያደርገውን በውስጧ የሚጸልየውን ስለትንና መባንም የሚሰጠውን በመታሰቢያህም ቀን ለድኇች የሚመጸውተውን ሁሉ ከአንተ ጋራ በመንግሥተ ሰማያት አኖራቸዋለሁ አለው። በስምህ የታነፁትንም አብያተ ክርስቲያናት መላእክቶቼን እንዲጠብቋቸው አደርጋቸዋለሁ ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጠው በመለኮታዊ አፉ አፉን ሳመውና ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማያት በክብር ዐረገ። ከዚህም በሗላ እልዋሪቆስ ወደምትባል ታላቅ ሀገር እስከ ሚደርስ በብዙ አገሮች ውስጥ ተመላለሰ በዚያም የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል #ማርያም ተገልጻለት አረጋጋችው ረዳችውም በመጋቢት ሃያ ዘጠኝ እንደጻፍነው የአገሩን ሰዎች እንዲአጠምቃቸውና እንዲአስተምራቸው አዘዘችው። ከዚህም በሗላ ወደ ሮሜ ከተማ ገብቶ በውስጧ ሰበከ ከበስብከቱም ብዙዎች ሰዎች አምነው የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃቸው በመጻሕፍትነት የታወቁ ዐሥራ አራት መልእክቱም ለሮሜ የተጻፈችው ናት። መልካም ሩጫውንም ከፈጸመ በሗላ ንጉሥ ኔሮን ይዞ ድኑ ሥቃይን አሠቃየው እራሱንም በሰይፍ እድቆርጢት ለሰያፊ ሰጠው ከሰያፊውም ጋራ አልፎ ሲሔድ ከንጉሥ ኔሮን ዘመዶች የሆነች አንዲት ብላቴና አገኘችው እርሷም ክብር ይግባውና በጌታችን ያመነች ነበረች ስለርሱም አለቀሰች። እርሱ ግን መጎናጸፊያሽን ስጨኝ እኔም ዛሬ እመልስልሻለሁ አላት እርሷም መጎናጸፊያዋን ሰጠችውና ራስ ወደ ሚቆርጡበት ቦታ ሔደ ለሰያፊውም ራሱን በአዘነበለ ጊዜ በመጎናጸፊያዋ ፊቱን ሸፈነ ሰያፊውም የቅዱስ ጳውሎስን ራስ ቆርጦ በዚያች ብላቴና መጎናጸፊያ እንደገደለው ለንጉሥ ሊነግረው በተመለሰ ጊዜ ያቺ ብላቴና አገኘችው ያ ጳውሎስ ወዴት አለ አለችው ራስ የሚቆረጥበት ቦታ ወድቋል ራሱም በመጎናጸፊያሽ ተሸፍኗል አላት። እርሷም እንዲህ ብላ መለሰችለት ዋሽተሃል እነሆ ጴጥኖስና ጳውሎስ በእኔ ዘንድ አልፈው ሔዱ እነርሱም የመንግሥት ልብሶችን ለብሰዋል በራሳቸውም ላይ በዕንቁ የተጌጡ ዐይንን የሚበዘብዙ አክሊላትን አድርገዋል መጎናጸፊያዬንም ሰጡኝ እርሷም እነሗት ተመልከታት ብላ ለዚያ ሰያፊ አሳየችው ከርሱ ጋራ ለነበሩትም አሳየቻቸው አይተውም አደነቁ ስለዚህም ክብር ይግባውና በ #ጌታችን_በኢየሱስ_ክርስቶስ አመኑ። የዚህም ሐዋርያ ጳውሎስ ተአምራቶቹ ቁጥር የሌላቸው እጅግ የበዙ ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳት ሐዋርያት ጸሎት ይማረን በረከታቸው የቅዱሳት ሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን። (#ስንክሳር_ዘወርኀ_ሐምሌ_5)
Показать все...
Выберите другой тариф

Ваш текущий тарифный план позволяет посмотреть аналитику только 5 каналов. Чтобы получить больше, выберите другой план.