ሙሓጂሪን መድረሳ مدرسة المهاجرين Muhajirin medresa
Открыть в Telegram
1 177
Подписчики
+1624 часа
+547 дней
+10030 дней
Архив постов
🛑ቀጥታ ስርጭት
╰┈➢ ተ
╰┈➢ ጀ
╰┈➢ም
╰┈➢ ሯ
╰┈➢ል
📒 رياض الصالحين من كلام سيد المرسلين
📒ሪያዱ አስ-ሳሊሂን
🎙በኡስታዝ አቡ ኢልሀም ሙሀመድ ኑር
(حفظه الله)
https://t.me/sunah123
🕌በአልሙሐጂሪን መድረሳ🕌
https://t.me/sunah123
https://t.me/sunah123
القواعد المثلى-١٠.mp34.40 MB
القواعد المثلى-٩.mp32.91 MB
القواعد المثلى-٨.mp31.99 MB
القواعد المثلى-٧.mp31.47 MB
القواعد المثلى-٦.mp31.97 MB
القواعد المثلى-٥.mp32.89 MB
القواعد المثلى-٤.mp32.43 MB
القواعد المثلى-٣.mp33.29 MB
القواعد الأربع-٤.mp31.25 MB
القواعد المثلى-٢ (1).mp32.43 MB
القواعد المثلى-١.mp33.88 MB
القواعد_المثلى_في_صفات_الله_تعالى_وأسمائه_الحسنى_ابن_عثيمين.pdf2.20 MB
📀 صوتية :
📌إبطال قاعدة المعذرة والتعاون للعلامة محمد أمان الجامي
💧مُسْتَلَّة من الأسئلة الموجّهة للشيخ رحمه الله ضمن شرحه على القواعد المثلى لابن عثيمين {الشريط الثاني }
https://t.me/sunah123
🔴 የእረፍት ማጥፊያ፦
ልጆችን በመድረሳ እንዳይማሩ ማሳነፍ ያለው ስውር አደጋ፦
✅ በየዓመቱ የክረምት ወራት ሲቃረብ በብዙ ወላጆች ዘንድ የሚደጋገም አንድ የተለመደ ፈሊጥ(አባባል) አለ። ልጆች ዓመቱን ሙሉ ሲማሩ ደክሞቸዋል፣ አሁንማ እረፍት ያድርጉ፣ መጨናነቅ የለባቸውም የሚል ይህ አባባል ለአይንና ለጆሮ እጅግ አራሪና ለልጆች ተቆርቋሪ ይመስላል። ነገር ግን ከጀርባው የልጆችን አእምሮአዊ፣ ስነ-ምግባራዊና መንፈሳዊ ህንጻ የሚንድ ትልቅ የማሳነፍ አደጋ ደቅኖ ይገኛል።
ልጆች በክረምት ወራት መድረሳ ሄደው ዲናቸውንና ቁርኣናቸውን እንዳይማሩ ማድረጉ የሚያስከትላቸውን ዋና ዋና አደጋዎች እንመልከት፦
1. ባዶነትና የጊዜ መባከን (የዲጂታል ሱሰኝነት)
አእምሮ ባዶ ከሆነ ክፉ ነገር ይሞላበታል ። ልጆችን ከመድረሳና ከትምህርት አርቀን ይረፉ ስንላቸው የሚያረፉት በተፈጥሮአዊ ጨዋታ ሳይሆን አብዛኛውን ጊዜ በስልክ፣ በቲቪና በቪዲዮ ጌሞች ፊት ተገትረው ነው። ይህ ደግሞ እረፍት ሳይሆን የአእምሮ መደንዘዝን፣ ብቸኝነትንና አላስፈላጊ ለሆኑ የእይታ ብክለቶች መጋለጥን ይፈጥራል። መድረሳ ግን ጊዜያቸውን በበረካና በትርጉም ያለው ስራ እንዲያሳልፉ ያደርጋል።
2. የዲን (የሃይማኖት) መሰረት መላላት
የክረምት ወራት ልጆች ከዓለማዊ ትምህርት ጫና ነፃ የሚሆኑበትና ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ በቁርኣን ንባብ፣በዓቂዳ፣ በተውሂድ፣ በፊቅህና በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ታሪክ፣በመንሀጅ ትምህርቶች ላይ የሚያሳልፉበት ወርቃማ እድል ነው። ይህንን እድል መከልከል ማለት ልጁ ስለ ዲኑ ያለው እውቀት ደካማ እንዲሆንና ለተለያዩ የተሳሳቱ የአስተሳሰብ ሞገዶች በቀላሉ እንዲሸነፍ በር መክፈት ነው።
3. የስነ-ምግባር (አደብ) መበላሸት
መድረሳ የድን እውቀት ብቻ የሚቀሰምበት ሳይሆን አደብ፣ ታዛዥነት፣ ወላጅ አክባሪነት፣ታማኝነትና አብሮነት የሚለመድበት ማህበራዊ ተቋም ነው። ልጆች በዚህ እድሜያቸው ያለ ቁጥጥርና ያለ መድረሳ ስነ-ስርዓት በየመንደሩ ሲዋልሉ፣ከወላጅ፣ ከትልቅ ሰዎች ጋር የመግባባትና ራሳቸውን የመግዛት ክህሎታቸው አብሮ ይሸረሸራል።
4. የትምህርት መዘንጋትና ስንፍና ፦
ልጆች ለረጅም ወራት ከአእምሮ ስራና ከንባብ ሲርቁ፣ ቀደም ሲል የተማሩትን የመያዝ ብቃታቸው ይቀንሳል። በክረምት መድረሳ እየሄዱ ቁርኣን የቀሩ፣ የአረብኛ ፊደላትን ና የተለያዩ ድናዊ ትምህርትን ያጠኑ ልጆች በመስከረም ወር ወደ መደበኛ ትምህርት ቤት ሲመለሱ ንቁ፣ ተቀባይና ትጉህ ይሆናሉ። በተቃራኒው ክረምቱን ሙሉ በሙሉ በዝምታና በጨዋታ ያሳለፉ ልጆች ትምህርት ሲጀምሩ ለመልመድ ይቸገራሉ፣ የመስነፍ አዝማሚያም ይታይባቸዋል።
🔴 ሚዛናዊው መፍትሔ ምንድን ነው?
እረፍት ያስፈልጋል፤ ነገር ግን እረፍት ማለት የእውቀት መቋረጥ ማለት አይደለም። እውነተኛ እረፍት ማለት ተግባርን መለወጥ ነው። ዓመቱን ሙሉ አስቸጋሪ የነበረውን የሒሳብና የሳይንስ ጭንቀት አስቀምጦ፣ ነፍስን በሚያክመው የቁርኣን ትምህርትና በድናዊ እውቀት አእምሮን ማደስ እራሱ ትልቅ እረፍት ነው።
📌ለወላጆች መልእክት፦
ልጆቻችሁን ከመጠን በላይ አታጨናንቋቸው፣ ነገር ግን አታሳንፏቸውም። የክረምት ወራት የልጆቻችሁን የቀጣይ ዘመን ማንነት የምትቀርጹበት እንጂ፣ ጊዜያቸውን ለባዶነት የምትሰጡበት መሆን የለበትም።
ያስታውሱ፦ ዛሬ በክረምት ይረፉ ብለን ያሳነፍናቸው ልጆች፣ ነገ በህይወታቸው ስኬታማ እንዳይሆኑ መሰረት እየናድንባቸው ሊሆን ይችላል። ልጆቻችንን በእውቀትና በዲን አናንጻቸው!አላህ ያግዘን። https://t.me/almuhajrinmedresa
Repost from قناة الشيخ الدكتور حسين بن محمد
تخريج حديث عتبة بن عمرو السلمي، قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم: ((الخلافة في قريش، والحكم في الأنصار، والدعوة في الحبشة، والجهاد والهجرة في المسلمين والمهاجرين بعد)) تقديم أبي إلحام شيخ مدرسة المهاجرين وأبي معاذ وزيني السانكري رفع الله قدرهم وزادهم علما . السياق لأبي معاذ مع تصرف يسير.
✅التخريج
✅أخرجه الطبراني في المعجم الكبير(٢٩٨) من طريق محمد بن أبي زرعة الدمشقي عن هشام بن عمار ح وأيضا من طريق إسماعيل بن قيراط الدمشقي عن سليمان بن عبد الرحمان
✅والبخاري في الكبير(٣٠٤٨)من طرق عبد الوهاب بن ضحاك
✅وأحمد في المسند(١٧٦٠٤) من طريق الحكم بن نافع،
✅وابن أبي عاصم في السنة من طريق من طريق الحوطي وهشام بن عمار
خمستهم(هشام بن عمار وسليمان بن عبد الرحمان وعبد الوهاب والحكم بن نافع والحطي) عن إسماعيل بن عياش عن ضمضم بن زرعة عن شريح بن عبيد عن كثير بن مرة عن عتبة به، إلا أن في إسناد البخاري وأحمد وابن أبي عاصم قال عن عتبة بن عبد وأيضا ليس عند أحمد لفظ "والجهاد"، وأخرج ابن أبي عاصم الفقرة الأولى فقط.
✅وأخرجه أيضا أبو العباس جمح بن القاسم في " جزء من حديثه " (٥٧ / ٢) وعلي بن طاهر السلمي في " كتاب الجهاد " (٢ / ١ / ٢) وأبو الحسن البزار بن مخلد في "الأمالي" وابن عساكر في تاريخ دمشق (٨ / ٢٤١ / ١) من طريق أحمد.[قاله الألباني في الصحيحة 4/ 467]
✅درجة الحديث
① ضمضم بن زرعة بن ثُوب الحضرمي الحمصي[٦]
وثقه ابن معين وابن حبان وغيرهما وضعفه أبو حاتم كما في التهذيب(2/ 571).
قال في الميزان(2/ 331): روى عنه جماعة
② إسماعيل بن عياش العنسي أبو عتبة الحمصي [٨] (تـ ١٨١ أو ١٨٢)
قال أحمد: في روايته عن أهل العراق وأهل الحجاز بعض الشئ وروايته عن أهل الشام كأنه أثبت وأصح. [الجرح والتعديل 2/ 192]لابن أبي حاتم
✅الحكم الإسناد
«إسماعيل بن عياش- ثقة في روايته عن الشاميين- وهذه منها ، وضمضم بن زرعة وثقه ابن معين وضعفه أبو حاتم .»
قال الألباني في الصحيحة(4/ 467):وهذا إسناد شامي حسن وفي بعضهم كلام لا يضر.
ثم قال:« وقال الهيثمي في " المجمع " (٤ / ١٩٢) : " رواه أحمد والطبراني ورجاله ثقات ". وقال شيخه الحافظ العراقي في " محجة القرب إلى محبة العرب " (ق ١٩ / ٢) بعد أن رواه من طريق أحمد: " حديث صحيح، ورجال إسناده ثقات وإسماعيل بن عياش روايته عن الشاميين صحيحة، دون روايته عن الحجازيين ".»انتهى
✅الخلاصة: الحديث حسن كما قال الألباني والجرح في ضمضم غير مفسر وقد وثقه ابن معين فأقل أحواله أن يكون صدوقا. ولبعض فقرات الحديث شواهد معروفة تطلب من مظانها وقد أشار إليها محققوا مسند أحمد.
هذا ما تيسر والله أعلم
Repost from የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
🔷ሰዎች አይቀበሉትም በሚል ሰበብ ኡለሞች እውነቱን እዳያብራሩ ማድረግ አይፈቀድም!
ሸይኽ ኢብን ዑሰይሚን - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል ፡
“ግን ጉዳዩ ይኸውልህ ፣ አንዳንድ ሰዎች አሊሞቹ እውነቱን እንዳያብራሩ ያበረታታሉ፡፡ 'ሰዎች ተጠቃሚ ላይሆኑ ለምን ግልጽ ታደርጋላችሁ?!' ይላሉ፡፡ ይህ የተከለከለ ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ንግግር ሰዎች ከእውነት ተስፋ እንዲቆርጡ ስለሚያደርግ ተቀባይነት የለውም፡፡ ኡለሞች እውነቱን ካብራሩ ፣ ጠቀመም አልጠቀመም ሌላው ቀርቶ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ ላይ መሆናቸውን ማወቃቸው (እንደቀላል መታየት የለበትም፡፡)
ምክንያቱም ኡለሞች ሰዎች ከእውነት ጋር የሚቃረን ተግባር እየፈጸሙ እየተመለከቱ ዝም ካሉ ፣ ሰዎች ምን ያስባሉ ፣ ተግባራቸው ትክክለኛ እውነት እንደሆነ ያስባሉ፡፡ ስለዚህ በዚያ ተግባር ላይ ይቀጥላሉ እና ይለምዳሉ ፡፡ ነገር ግን ውግዘቱን ካዩ ትክክል እንዳልሆኑ ያውቃሉ፡፡ እናም ከዚህ ሌላ ጥቅም ባይኖር ኖሮ በቂ ይሆን ነበር፡፡ ስለዚህ እውነቱን የማብራራት አስፈላጊነትን ፈጽሞ አቅልለህ አትመልከተው፡፡”
فتح ذي الجلال والإكرام بشرح بلوغ المرام
(2\437)
https://t.me/alateriqilhaq
كن على بصيرة
