ru
Feedback
ምክር ለወጣቶች

ምክር ለወጣቶች

Открыть в Telegram

"አላማችን ወጣቱ ያለበትን የዲን ክፍተት እንዲስተካከል ማድረግ ነው"

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
7 265
Подписчики
+124 часа
+1937 дней
+81630 дней
Архив постов
*ፈጅር ሶላት የአሏህን* ትእዛዝ ለመተግበር የቀን ውሎህን በደስታ የምትጀምርበት ትልቅ ፀጋ ነው። *ሰላት ሳይሰግዱ የህይወትን* ጥፍጥና መቅመስ የማይታሰብ ነው ። الصلاة خير من النوم 🍇
*ፈጅር ሶላት የአሏህን* ትእዛዝ ለመተግበር የቀን ውሎህን በደስታ የምትጀምርበት ትልቅ ፀጋ ነው። *ሰላት ሳይሰግዱ የህይወትን* ጥፍጥና መቅመስ የማይታሰብ ነው ። الصلاة خير من النوم 🍇  የፈጅር ሶላት የመልካም ስራዎች ሁሉ መጀመሪያ ነው ዒብኑል ቀይም ረሂመሁሏህ ሶላተል ፈጅር👉🏻⏰ https://t.me/nejashi_nejashi

በአለባበስሽ የዝሙት አምባሳደር አትሁኚ
በአለባበስሽ የዝሙት አምባሳደር አትሁኚ

"ወጣት ሸባብ አላህን ፍራ" 🎙በሸይኽ አብዱልሃሚድ🎙 #ሼር #ሼር #ሼር #ሼር #ሼር #ሼር @Abu_Umer1 @Abu_Umer1

🚫  የቲክ – ቶክ አደጋ ♻️ ቲክ – ቶክ ማለት በአሁኑ ጊዜ በጣም ብዙ ሰዎች የተፈተኑበትና ከስነ-ምግባርና ግብረ–ገብነት ያፈነገጠ ትውልድን የሚያጠፋ መርዘኛ ሚዲያ ነው።     🔎 በጣም የሚገርመው ቲክ – ቶክን ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች በፓርላማዎቻቸው አማካይነት እንዲታገድ እያደረጉ ነው። ምክንያታቸው ደግሞ እምነትና መልካም ባህልን የሚያጠፋ ነው የሚል ነው። ምክንያቱ ይለያይ እንጂ ብዙ የምእራብ ሀገሮችም እንዲታገድ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።   ➲ በርግጥ እነርሱ እንደአፍሪካዊያን እምነትና ባህልን ይጎዳል በሚል አይደለም የሚጠሉት ይልቁንም ምክንያታቸው ፖለቲካዊ ነው።    ➪ ከማንም በፊት ኢስላም የሰዎችን ዲን፣ ጤና፣ ንብረትና ክብር የሚጎዳን ነገር ይከለክላል። የኢስላም ሸሪዓ ትኩረት ሰጥቶ ከሚጠብቃቸው ነገሮች ዋናውና ትልቁ ዲን ነው። ዲንን የሚጎዳ ማንኛውም ነገር በኢስላም ክልክል ነው።    ➧ ታዲያ እንኳን በመለኮታዊ የህይወት መመሪያ የሚመራ የኢስላም አስተምሮ ይቅርና ጤነኛ አእምሮ ያላቸው ከሀዲያን እንኳን የልጆችን ስነምግባር ያበላሻል የሰዎችን እምነትና መልካም ልማድ አደጋ ላይ ይጥላል ብለው የሚያወግዙትን ቲክ – ቶክ የሱና ሰዎች ነን ከአቋማችን አልተንሸራተትንም እያሉ የሚሞግቱ አካላት ወጣቱን ወደ ቲክ – ቶክ ሲጣሩ ምን ይባላል ‼?       ↪️ አላህ ሐቅን አውቀን የምንከተለውና ባጢልን አውቀን የምንርቀው ያድርገን።     የአደጋው አድማስ በተለይ በሙስሊሞች ላይ እየሰፋ እየሄደ ስለሆነ በድጋሚ የተለቀቀ ። https://t.me/bahruteka

ሀያዕ (አይናፋርነት) ያለው ሰው፡ በፍፁም ተሳዳቢና ዘላፊ ሊሆን አይችልም እንደውም በማይመለከተው ጉዳይ ላይ ዝምታን ያበዛል። ሼኽ ሙቅቢል አል ዋዲዒ https://t.me/NasihaLishebab

👆 አንብቡት እስኪ ያጀማዓ
👆 አንብቡት እስኪ ያጀማዓ

አፍወን ዛሬ ጥያቄና መልስ አይኖረንም ❗️ ሀጃ ገጥሞኝ ነው

እየለመንከው ካለህ በአላህ ላይ ምን ትጠረጥራለህ?

አላህዋ ልቤ ተሰብሮ ወደ አንተ መጣሁ። ሰዎች የማይሰሙትን ድምፅ፣ በአፌ የማልናገረውን ሀዘን፣ በልቤ ውስጥ ተደብቆ ያለውን ሁሉ አንተ ታውቃለህ። እኔ ዝም ብዬ ብቀመጥም አንተ የልቤን ሁኔታ ታውቃለህ
አላህዋ ልቤ ተሰብሮ ወደ አንተ መጣሁ። ሰዎች የማይሰሙትን ድምፅ፣ በአፌ የማልናገረውን ሀዘን፣ በልቤ ውስጥ ተደብቆ ያለውን ሁሉ አንተ ታውቃለህ። እኔ ዝም ብዬ ብቀመጥም አንተ የልቤን ሁኔታ ታውቃለህ። አላህዬ፣ ልቤ በሰዎች እንዳይሰበር ከሰዎች ጋር አታስረው፤ ከአንተ ጋር አገናኘው። የሚያልፈውን ነገር እንደ ዘላቂ ሀዘን እንዳላየው አስተምረኝ። የጠፋብኝን ነገር በምትኩ ከአንተ የሚመጣ የተሻለ ነገር እንዳገኝ አድርገኝ። አላህዬ፣ እንባዬን ወደ ደስታ፣ ሀዘኔን ወደ ሰላም፣ ፍርሃቴን ወደ እምነት ቀይረው። ልቤ የተደከመበትን ነገር አንተ አቅልልኝ። ያለፈውን ለመተው ጥንካሬ፣ የሚመጣውን በተስፋ ለመጠበቅ ትዕግስት ስጠኝ። አላህዬ፣ ከአንተ ጋር ያለውን ልቤን በማንም እንዳልተካ፣ ከአንተ የራቀ ነገር እንዳይጎዳኝ፣ በውሳኔህም ላይ ልቤን እንዲረጋ አድርገኝ። ምናልባት ዛሬ ምክንያቱን አልገባኝም፤ ግን አንተ ጥበበኛ ነህ። ምናልባት ዛሬ እያለቀስኩ ነው፤ ግን አንተ ከእንባዬ በኋላ ፈገግታ እንዳለ ታውቃለህ። ስለዚህ የኔ አላህ፣ በልቤ ላይ የማይጠፋ ሰላምህን አውርድ። አንተ እንደሚበቃኝ አስተምረኝ። ሰዎች ቢተዉኝም አንተ እንደማትተወኝ ልቤ እንዲያምን አድርገው። የተሰበረውን ልቤን አንተ አድነው፤ የደከመውን ነፍሴን አንተ አጽናናት። አላህዬ… የምትወደውን እንድወድ፣ የማትወደውን እንድርቅ፣ በሁሉም ሁኔታ አንተን እንዳመሰግን አድርገኝ። ልቤን ከሀዘን አውጥተህ በኢማን፣ በሱኩን እና በተስፋ ሙላው። አላህዬ፣ ከአንተ በላይ መጠጊያ የለኝም። ወደ አንተ እመለሳለሁ፣ በአንተም እታመናለሁ። ዛሬ ልቤ ቢያለቅስም፣ ነገ በአንተ ፈቃድ ይህን ቀን ተመልክቼ “አልሐምዱሊላህ፣ አላህ የተሻለውን መርጦልኝ ነበር” እንድል አድርገኝ። 🤲🏻🤍

የኔ አላህ… 🤍 ሁሉም ነገር ሲተወኝ አንተ አትተወኝም። ልቤ ሲደክም አንተ ታበረታኛለህ፤ እንባዬን ማንም ሳያየው አንተ ታያለህ። የኔ አላህ፣ ስለሰጠኸኝ ኒዕማ ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ስለማላውቀው ጥበቃ
የኔ አላህ… 🤍 ሁሉም ነገር ሲተወኝ አንተ አትተወኝም። ልቤ ሲደክም አንተ ታበረታኛለህ፤ እንባዬን ማንም ሳያየው አንተ ታያለህ። የኔ አላህ፣ ስለሰጠኸኝ ኒዕማ ሁሉ አመሰግንሃለሁ። ስለማላውቀው ጥበቃህ፣ ስለማላየው እዝነትህ፣ ስለዘጋህልኝ በሮች እና ስለከፈትህልኝ የማላስበው በሮች ሁሉ አመሰግንሃለሁ። የኔ አላህ፣ እኔ ደካማ ብሆንም አንተ ጠንካራ ነህ፤ እኔ ስሳሳት አንተ መንገዴን ታሳየኛለህ። ከሰዎች ይልቅ በአንተ እንድታመን አስተምረኝ፣ ልቤንም በዝክርህ አሳርፈው። አልሐምዱሊላህ ለኒዕማዎችህ፣ አልሐምዱሊላህ ለፈተናዎችህ፣ አልሐምዱሊላህ ለሰጠኸኝ እና ለከለከልከኝ ነገር። ምክንያቱም አንተ የምታውቀውን እኔ አላውቅም። የኔ አላህ፣ ከአንተ ውጭ የምታምንበት ማንም የለኝም። በዱንያም ሆነ በአኺራ ልቤን በአንተ አጽና። በኢማን አኑረኝ፣ በኢማንም አሳልፈኝ። ለአንተ በምስጋና የሚኖር፣ በተውሒድ የሚጸና ባሪያህ አድርገኝ። አልሐምዱሊላሂ ዐላ ኩሊ ሓል።🫶🏻🤌🏻

የመጨረሻው ስንብታችን መች እንደሆነ አለማወቃችን ሳያንሰን !ከራሳችን አልፈን.. የሰዎች ሂወትን ለማበላሸት የምንሮጥ.. ከጥፋተኛ የምንተባበር.. በሀሰት የምንመሰክር.. ለክፋት የምንተጋገዝ አስገራሚ
የመጨረሻው ስንብታችን መች እንደሆነ አለማወቃችን ሳያንሰን !ከራሳችን አልፈን.. የሰዎች ሂወትን ለማበላሸት የምንሮጥ.. ከጥፋተኛ የምንተባበር.. በሀሰት የምንመሰክር.. ለክፋት የምንተጋገዝ አስገራሚ ፍጥረቶች መሆናችን አይደንቅም?!።   Join     and    share https://t.me/nejashi_nejashi

የዛሬው መልዕክት ይለያል🫶🏻 ኧረ ተንቀሳቀሱ
የዛሬው መልዕክት ይለያል🫶🏻 ኧረ ተንቀሳቀሱ

ምስጋና በጠቅላላ ለአላህ ለአለማቱ ጌታ ይገባው። የአላህ ውዳሴና ሰላም በነቢያችን ሙሐመድ፣ በተከታዮቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ ሁሉ ይሁን። ከዚህ በመቀጠል፦ እኔ አቡ ሙዓዝ፥ ከወሎ ደሴ ከተማ ወደ ሲዳማ ክልል ሐዋሳ ከተማ ተዛውሬያለሁ። ከሱና ሰዎች ጋር ለመቀራረብ ፣ ከሰለፊዮች ጋር አብሮ ለመሆን እና በዚች ቦታ ላይ የሰለፊያ ደዕዋን ለመደገፍና ለመርዳት በማሰብ እዚያው ሐዋሳ ውስጥ ከሰለፊይ ወንድሞች ጋር ለመኖር ወስኛለሁ። እነሱንም—አላህ ይውፈቃቸውና—ከመላው የስሜት ባለቤቶች፤ ወሰን ካለፉና ካላለፉ ሱፊዮች፣ ከዘመነኞቹ የፖለቲካ ኢኽዋኖች፣ እንዲሁም የሰለፊያን ስም ከሚያበላሹ መርሆቻቸውን ካላሉ (ሙመዪዓዎች) ሁሉ ተለይተው አግኝቻቸዋለሁ።  ጥራት የተገባውና የበላይ የሆነው አሏህ ከእስልምናና ከሙስሊሞች (በመርዳታቸው) መልካሙን ምንዳ ይክፈላቸው። ከወንዶች፣ ከሴቶች፣ ከትላልቆችና ከትናንሾች የሆኑ ተማሪዎችን የሚያስተምሩባቸው መድረሳዎች አሏቸው። የጌታቸውን መጽሐፍ (ቁርኣንን) እና የነቢያቸውን ﷺ ሱና ያስተምሯቸዋል፤ እንዲሁም በሰለፎች መንገድ ላይ በዐቂዳ (በእምነት)፣ በዒባዳ (በአምልኮ)፣ በአኽላቅ (በሥነ-ምግባር) እና በአካሄድም ጭምር ያንጿቸዋል። ነገር ግን ወንድሞች ሆይ!👉 ልብን የሚሰብረውና የሚያስደነግጠው ነገር ቢኖር፥ እነዚህ የሰለፊያ ጀመዓዎች የራሳቸው የሆኑ (የባለቤትነት መብት ያላቸው) መስጂዶችም ሆኑ ማእከላት (መርከዞች) የሏቸውም። ይልቁንም እነሱ ያሉት በተከራዩባቸው ቤቶችና ማእከላት ውስጥ ሲሆን፥ የኪራዩን ጫና፣ የሁኔታዎችን መዋዠቅ እንዲሁም ቦታውን የመልቀቅ ስጋትን እየተሸከሙ ይገኛሉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ የደዕዋቸውን ቀጣይነት አደጋ ላይ የሚጥል፣ እንቅስቃሴያቸውን የሚገድብና በማኅበረሰቡ ውስጥ ያላቸውን ተፅዕኖ የሚያዳክም ነው። በመሆኑም በየትኛውም ቦታ በሚገኙ ሰለፊዮች ሁሉ ላይ—መሪዎችም ሆኑ ተመሪዎች፣ ሀብታሞችም ሆኑ ድሆች፣ ዑለማኦችም ሆኑ የዕውቀት ፈላጊዎች—በሐዋሳ የሚገኙ ወንድሞቻቸውን በቻሉት ነገር ሁሉ መርዳት ግዴታ ይሆንባቸዋል። በገንዘብ፣ በዱዓእ፣ በምክር፣ በማስተዋወቅ፣ በመካከለኛነት (በማገናኘት)፣ መሬት በመግዛት፣ መስጂድ ወይም የደዕዋ ማእከል ወይም ሸሪዓዊ ትምህርት ቤት በመገንባት ሊረዷቸው ይገባል። ይህም ከትልልቅ የመርዳት ዓይነቶችና ላቅ ካሉ የእስልምና መልካም እሴቶች መካከል የሚመደብ ነው። የላቀው አሏህ እንዲህ ብሏል፦ {አማኞች ወንድማማቾች ናቸው} [አል-ሁጁራት፡ 10]። ነቢያችንም ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው፤ አይበድለውም፣ አሳልፎም አይሰጠውም» [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል]። ወደ አላህ የሚጣራን (ዳዒን) የረዳ ሰው ሃይማኖቱን ሁሉ እንደረዳ ይቆጠራል። በደዕዋ መንገድ ላይ አንዲትን እርምጃ ያቀና ሰው በየቦታው ላይ መስጂድን እንደገነባ ይቆጠራል። ከሙስሊም ላይ ከአለማዊ ጭንቀቶች አንዲትን ጭንቀት ያስወገደ ሰው አላህ በዱንያም በኣኺራም ከጭንቀቶቹ ያስወግድለታል። የመልካም ነገር ባለቤቶችና የሱና ሰዎች ሆይ! በሐዋሳ የሚገኙ ወንድሞቻችሁን ለመርዳት ፍጠኑ፣ ለእነሱም ረዳትና ደጋፊ ሁኑ። አላህ ባሪያው ወንድሙን በመርዳት ላይ ባለ ቁጥር እሱን በመርዳት ላይ ነው፤ አላህም የመልካም ሠሪዎችን ምንዳ አያባክንም። አላህም ትክክለኛን መንገድ የመግጠም ባለቤት ነው። አቡ ሙዓዝ፥ ሐዋሳ ከተማ፣ ሲዳማ፣ ኢትዮጵያ
€-በግርድፉ ከቃላት ይልቅ ፅንሰ-ሀሳብ ላይ ያተኮረ ትርጉም ነው። ስህተት ካለ የተርጓሚው ብቻ ነው።

እህቶች ዝናብ🌧 ሲዘንብ እንሸኛችሁ ብለው የሚመጡ ባጃጆችም ሆነ ማንኛውንም ነገር እንዳታምኑ❤️‍🩹 በተለይ በማታ ❗️

እቺን ነገር አስተውሉልኝ እሺ❤️‍🩹

ቆይ ያልተኛችሁ እስኪ ምክንያት አስቀምጡ

ጥያቄ አልቋል ተኙ በቃ

የመልስ ሰዐት ደርሷል 1 C🏆 2 B🏆 3 A🏆 4 B🏆 5 A🏆 6 A🏆 7 B🏆 8 A🏆 9 B🏆 10 A🏆 11 B🏆 12 C🏆 13 C🏆 14 B🏆 15 B🏆 16 ከነዐን ነው🏆 17 ተውራት ነው🏆 18 ኢስራኢል ነው🏆 19 ኢንጂል ነው🏆 20.عَنْ عُمَرَ بْنِ الْخَطَّابِ رضي الله عنه قَالَ: بَيْنَمَا نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ رَسُولِ اللهِ ﷺ ذَاتَ يَوْمٍ، إِذْ طَلَعَ عَلَيْنَا رَجُلٌ شَدِيدُ بَيَاضِ الثِّيَابِ، شَدِيدُ سَوَادِ الشَّعَرِ، لَا يُرَى عَلَيْهِ أَثَرُ السَّفَرِ، وَلَا يَعْرِفُهُ مِنَّا أَحَدٌ، حَتَّى جَلَسَ إِلَى النَّبِيِّ ﷺ، فَأَسْنَدَ رُكْبَتَيْهِ إِلَى رُكْبَتَيْهِ، وَوَضَعَ كَفَّيْهِ عَلَى فَخِذَيْهِ، وَقَالَ: يَا مُحَمَّدُ، أَخْبِرْنِي عَنِ الْإِسْلَامِ. فَقَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ: «الإِسْلَامُ أَنْ تَشْهَدَ أَنْ لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ، وَأَنَّ مُحَمَّدًا رَسُولُ اللهِ، وَتُقِيمَ الصَّلَاةَ، وَتُؤْتِيَ الزَّكَاةَ، وَتَصُومَ رَمَضَانَ، وَتَحُجَّ الْبَيْتَ إِنِ اسْتَطَعْتَ إِلَيْهِ سَبِيلًا». قَالَ: صَدَقْتَ. فَعَجِبْنَا لَهُ يَسْأَلُهُ وَيُصَدِّقُهُ. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِيمَانِ. قَالَ: «أَنْ تُؤْمِنَ بِاللهِ، وَمَلَائِكَتِهِ، وَكُتُبِهِ، وَرُسُلِهِ، وَالْيَوْمِ الآخِرِ، وَتُؤْمِنَ بِالْقَدَرِ خَيْرِهِ وَشَرِّهِ». قَالَ: صَدَقْتَ. قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ الإِحْسَانِ. قَالَ: «أَنْ تَعْبُدَ اللهَ كَأَنَّكَ تَرَاهُ، فَإِنْ لَمْ تَكُنْ تَرَاهُ فَإِنَّهُ يَرَاكَ». قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنِ السَّاعَةِ. قَالَ: «مَا الْمَسْؤُولُ عَنْهَا بِأَعْلَمَ مِنَ السَّائِلِ». قَالَ: فَأَخْبِرْنِي عَنْ أَمَارَاتِهَا. قَالَ: «أَنْ تَلِدَ الأَمَةُ رَبَّتَهَا، وَأَنْ تَرَى الْحُفَاةَ الْعُرَاةَ الْعَالَةَ رِعَاءَ الشَّاءِ يَتَطَاوَلُونَ فِي الْبُنْيَانِ». ثُمَّ انْطَلَقَ، فَلَبِثْتُ مَلِيًّا، ثُمَّ قَالَ لِي: «يَا عُمَرُ، أَتَدْرِي مَنِ السَّائِلُ؟» قُلْتُ: اللهُ وَرَسُولُهُ أَعْلَمُ. قَالَ: «فَإِنَّهُ جِبْرِيلُ، أَتَاكُمْ يُعَلِّمُكُمْ دِينَكُمْ🏆 ጥያቄና መልሱ ላይ የነበራችሁ በሙሉ አላህ እኛ በጠየቅነው እናንተ በመለሳችሁት ተጠቃሚዎች ያድርገን ነገ ሀሙስ ነው እየፆምን በተለይ ላጤያንስ አስታወስኳችሁ አይደል ዱዐ አድርጉልኝ አህባብ መልካም ለይል🤌🏻 ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ🤚

አዎ ሙሉውን

20.የመጨረሻ ጥያቄ የጂብሪል አለይሂ ሰላም ታዋቂውን ሀዲስ አስቀምጡ🫴