ru
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Открыть в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
4 295
Подписчики
Нет данных24 часа
-217 дней
-9130 дней
Архив постов
🇺🇸🇮🇷🇵🇰⚡- አስቸኳይ ዜና፦ ኢራን 'የመግባቢያ ስምምነት' (MoU) ላይ መድረሷን አረጋግጣለች፣ ይህም ኢስላማባድ ከዋሽንግተን ጋር ከተቀናጀች በኋላ በፓኪስታን ይፋ ይሆናል። ኢራን በMoU ውስጥ ከበፊት አቋማ ያላላቻቸው ስምምነቶችን እንዳደረገችም አረጋግጣለች።

እስራኤል ብቻዋን ኢራንን እንድትደበድባት በማድረግ፣ አሜሪካ በባሕረ-ሰላጤው የሚገኙ የአረብ ሀገሮችን በጦርነት እንዳይሳተፉ እና በኢራን እንዳይመቱ ዘዴ ልትቀይስ ትችላለች። በዚህም የተነሳ ኢራን ዒላማ እንዳታደርጋቸው ምክኒያት ታጣለች። ጦርነቱ "በኢራን እና በእስራኤል መካከል ብቻ" ስለሚሆን። ኢራን፣ አረቦቹ ለአሜሪካ የጦር ሰፈር ሰጥተው አስደበደቡኝ የምትልበት ground አይኖራትም። ስለዚህ፣ አረቦቹ ዳር ቆመው 'ኢራን ቶሎ በጠፋች' እያሉ ይመለከታሉ። ኢራን ታሳያቸዋለች? ይሄ ጨዋታ አይገባትም? አሜሪካም "አትገባበትም"፣ በእጅ አዙር ግን ከእስራኤል ጋር አብራ ትደበድባለች። አረቦቹም እስራኤልን ወደ ፊት ግፊ ይሏታል። ኢራን የሺዓ እምነት መስመር ስለምትከተል፣ የባሕረ ሰላጤው አረቦች አይወዷትም። የዘመናት ቁርሾ አለባቸው።

🇸🇦⚡- የሳውዲ ሜጋ ፕሮጀክት የሆነው NEOM The Line ግንባታ፣ እስከ 2030 እ.ኤ.አ ድረስ እንዲቆም ተደረገ። ምክኒያቱ፣ ለፕሮጀክቱ የሳዑዲ መንግሥት ገንዘብ የለውም የሚል ነው። የኢራን
🇸🇦⚡- የሳውዲ ሜጋ ፕሮጀክት የሆነው NEOM The Line ግንባታ፣ እስከ 2030 እ.ኤ.አ ድረስ እንዲቆም ተደረገ። ምክኒያቱ፣ ለፕሮጀክቱ የሳዑዲ መንግሥት ገንዘብ የለውም የሚል ነው። የኢራን ጦርነት በገልፍ ባሉ አረብ ሀገሮች ላይ ያመጣው ዋነኛ ጣጣ፣ የኪስ ድርቀት ነው። ለዚህም፣ አሜሪካ በጦርነቱ ዳግም እንዳታስገባቸው እየተማፀኑ ነው።

🇮🇷 በሺዎች የሚቆጠሩ የኢራን ዜጎች ለመንግሥት እና ለጦር ኃይሎቻቸው ጽኑ ድጋፋቸውን ለመግለጽ በቴህራን ኤንግሄላብ አደባባይ ተሰብስበዋል። አሜሪካ እና እስራኤል በማንኛውም ሰዓት ኢራንን ሊደበድቡ ይችላሉ የሚል ፍራቻ፣ በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቷል።

🇺🇸❌🇮🇷 ኢራን ጦር ሠራዊቷ በከፍተኛ የተጠንቀቅ ዝግጅት ላይ እንዲሆን አዛለች።

🇺🇸❌🇮🇷 — አስቸኳይ ሰበር ዜና፦ 'በሂደት ላይ ያሉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቢኖሩም፣ የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ለሚደረግ አዲስ የጥቃት ዙር እየተዘጋጀ ሲሆን፣ ወታደራዊ እርምጃ ሊታዘዝ ይች
🇺🇸❌🇮🇷 — አስቸኳይ ሰበር ዜና፦ 'በሂደት ላይ ያሉ የዲፕሎማሲ ጥረቶች ቢኖሩም፣ የትራምፕ አስተዳደር በኢራን ላይ ለሚደረግ አዲስ የጥቃት ዙር እየተዘጋጀ ሲሆን፣ ወታደራዊ እርምጃ ሊታዘዝ ይችላል የሚል ግምት በመኖሩ በርካታ የአሜሪካ ወታደራዊ እና የደኀንነት ባለሥልጣናት የሳምንታት መጨረሻ እቅዶቻቸውን ሰርዘዋል'-- CBS NEWS

🇷🇺 የሩሲያ ተማሪዎች በትምህርቶቻቸው ተጨማሪ ነጥቦችን ለማግኘት የድሮን አብራሪነት ስልጠና እየተሰጣቸው ነው - The Moscow Times
🇷🇺 የሩሲያ ተማሪዎች በትምህርቶቻቸው ተጨማሪ ነጥቦችን ለማግኘት የድሮን አብራሪነት ስልጠና እየተሰጣቸው ነው - The Moscow Times

🇺🇸🇨🇳🇪🇹🇪🇷 ትራምፕ ቤጂንግን ከጎበኘ በኋላ፣ የ14 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭን ለታይዋን ማገዱ ተረጋግጦ ነበር። ሆኖም፣ መሳሪያዎቹ ቀድሞውኑ ወደ ታይዋን ተጭነዋል። ነገሩ እንደዚያ ነው። ለዩክሬናውያን የሚደረገው ሽያጭ እንደቀጠለ ነው። ለሳዑዲ፣ ለኤሜሬትም እንደዚያው። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ በቀጥታ የመግዛት አቅም ባይኖራትም፣ አሮጌና የበሰበሱ የሩሲያ መሳሪያዎችን ከቀድሞ የሶቪየት ሕብረት ሀገራት ከአንዱ፣ ወይም የቻይና ዝቅተኛ ደረጃ ስሪት የሆኑ መሳሪያዎች በነፃነት ልትገዛ እንድትችል እገዳው ተነስቷል። በዚህ ሁሉ፣ አሜሪካ ከኢትዮጵያ ኮሚሽን አላት።

🇪🇷⚡️🇪🇹 አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላ የነበረውን የጦር መሳሪያ ግዢ ማዕቀብ ማንሳቷ ተሰምቷል፣ እንደ Business Insider ዘገባ። ይህ የተሰማው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረቱ
🇪🇷⚡️🇪🇹 አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጥላ የነበረውን የጦር መሳሪያ ግዢ ማዕቀብ ማንሳቷ ተሰምቷል፣ እንደ Business Insider ዘገባ። ይህ የተሰማው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ መካከል ውጥረቱ በተባባሰበት ነው። ** የአሜሪካ ጦር መሳሪያ አምራቾች ጦርነት አሽትተዋል መሰለኝ፣ መንግሥታቸውን ገፋፍተው እገዳውን እንዲያነሳ ያደረጉ ይመስላል። በአካባቢው ያሉ አመራሮች ጦርነት እና እልቂት ይጠምቃሉ፣ ለቢዝነስ ይመቻሉ።

🇮🇱🇺🇸⚡️🇮🇷 እንደ እስራኤል ቻናል 12 ዘገባ መሠረት፣ 'ትራምፕ በኢራን ምላሽ በጣም ተበሳጭቷል፣ በዚህ ሳምንት መጨረሻ የነበረውን የጎልፍ ክለብ ጉዞውን ሰርዟል እና ለወሳኝ እርምጃ አረንጓዴ መብራት ሊሰጥ ይችላል።'

🇺🇸🇮🇷⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር ወቅታዊ ሁኔታ ላይ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ እየተበሳጨ መምጣቱን እና የመጨረሻ ትልቅ ወታደራዊ ዘመቻ የማካሄድ ዕድል ሊኖር
🇺🇸🇮🇷⚡️— ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር በሚደረገው ድርድር ወቅታዊ ሁኔታ ላይ፣ ባለፉት ጥቂት ቀናት ውስጥ፣ እየተበሳጨ መምጣቱን እና የመጨረሻ ትልቅ ወታደራዊ ዘመቻ የማካሄድ ዕድል ሊኖር እንደሚችል አንስቷል፣ ከዚያ በኋላ ድል አድርጌያለሁ ብሎ ማወጅ እና ጦርነቱን ማቆም ይችላል፣ ሲል Axios ዘግቧል። በዲፕሎማሲያዊ ጥረቶቹ ላይ አጭር መግለጫ የሰጠ አንድ የአሜሪካ ባለሥልጣን፣ ድርድሮቹን “አሳሳቢ” ብሎ በመግለጽ፣ የረቂቅ ሐሳቦቹ “በየቀኑ ወደ ኋላ እና ወደፊት መጎተት” ፕሬዝዳንቱን አበሳጭተውታል፣ ይሄ ነው የሚባል ትርጉም ያለው ዕድገትም የለም፣ ሲል ተናግሯል።

🇪🇹⚡️🇪🇷 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዳግም ጦርነት ጫፍ ላይ ናቸው: Atlantic Council. የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣን የዛሬ ስምንት ዓመት ሲመጣ በሕዝቡ ዘንድ የነበረው ተስፋ
🇪🇹⚡️🇪🇷 ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዳግም ጦርነት ጫፍ ላይ ናቸው: Atlantic Council. የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሥልጣን የዛሬ ስምንት ዓመት ሲመጣ በሕዝቡ ዘንድ የነበረው ተስፋ፣ ባደረጋቸው ጦርነቶች እና የሕዝብ እልቂቶች ጨልሟል። በግምት 600 ሺ ኢትዮጵያዊያን ያለቁበት የትግራይ ጦርነት ለዚህ ተጠቃሽ ነው። ከኤርትራ ጋር ሰላም በፈጠረ ጊዜ ለዓለም ሕብረተሰብ ለአካባቢው በዘላቂነት ሰላም የሚያመጣ ሆኖ ታይቶ ነበር፣ በዚህም የኖቤል ሽልማት ተሸልሟል። ከዚያ ጊዜ በኋላ ግን "ተስፋዎችን ሁሉ" አጨልሟል። የሀገሩን ብቻ ሳይሆን የቀጠናውን ሕዝብ እና ደህንነት አደጋ ላይ ጥሏል። በአንድ ወቅት አጋር ከነበሩት የአማራ ብሔር ጋር የጀመረው አዲስ ጦርነት እና ከኤርትራ ጋር የሚያደርገው ሰጣ ገባ፣ አመራሩ በባሰ ሁኔታ የሕዝቡን አመኔታ እንዲያጣ አድርጎታል።

🇶🇦🇮🇷🇺🇸⚡ — ከኢራን ጋር የተነሳውን ጦርነት ለማቆም እና ያልተፈቱ ጉዳዮችን በመፍታት ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ፣ የኳታር ተደራዳሪ ቡድን ዛሬ ቴህራን ደርሷል፣ ሲ
🇶🇦🇮🇷🇺🇸⚡ — ከኢራን ጋር የተነሳውን ጦርነት ለማቆም እና ያልተፈቱ ጉዳዮችን በመፍታት ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ፣ የኳታር ተደራዳሪ ቡድን ዛሬ ቴህራን ደርሷል፣ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል። የፖኪስታኑ ዋና አደራዳሪ አሲም ሙኒር እንዲሁ፣ 35 ልዑካንን ይዞ ወደ ቴህራን አምርቷል። ኳታርና የቀጠናው ሀገሮች በሆርሙዝ ወሽመጥ ለማለፍ ለኢራን ክፍያ በመክፈል ምትክ፣ ኢራን ላይ የተጣለው ማዕቀብ እንዲነሳ አሜሪካ ላይ ግፊት እያደረጉ ናቸው ተብሏል። ይህን ሐሳብ ኢራን እንደምትደግፍ ተስፋ አላቸው።

🇦🇪🇸🇦🇶🇦🇮🇷🇺🇸⚡️— አክሲዮስ እንደዘገበው፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከኢራን ጋር የተካሄደውን ጦርነት ለማቆም በቅርብ ቀናት ውስጥ ጥረቶችን አጠናክራለች፣ ከሳዑዲ አረቢያ እና ከኳ
🇦🇪🇸🇦🇶🇦🇮🇷🇺🇸⚡️— አክሲዮስ እንደዘገበው፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከኢራን ጋር የተካሄደውን ጦርነት ለማቆም በቅርብ ቀናት ውስጥ ጥረቶችን አጠናክራለች፣ ከሳዑዲ አረቢያ እና ከኳታር ጋር በመቀላቀልም ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርድሩን እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። ➡ የባህረ ሰላጤው መሪዎች፣ በተለይ ዩናይትድ አረብ ኤሜሬት እና ሳዑዲ ዓረቢያ ጦርነቱ እና የኢራን የበቀል እርምጃዎች የቀጠናውን ኢኮኖሚዎች እንዳናጉ እና ሰፊ መረበሽ እንደፈጠሩባቸው ለትራምፕ በመንገር ወደ ጦርነት እንዳይመለስ አስጠንቅቀዋል። ➡ ዩናይትድ አረብ ኢሚሬትስ፣ ሳዑዲ አረቢያ እና ኳታር ዋሽንግተን ከኢራን ጋር ምን ዓይነት ስምምነት መፈጸም አለባት በሚለው ላይ ቢለያዩም፣ ሁሉም ጦርነቱ እንዲያበቃ ይፈልጋሉ።

🇮🇷⚡- ኢራን 35 መርከቦች ክፍያውን እንደከፈሉ እና ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ የሆርሙዝ ወሽመጥን በደህና እንዳቋረጡ ተናግራለች። በወሽመጡ ማለፊያ ክፍያ፣ በመርከብ $2 ሚሊዮን ዶላር እንደሆነ ይገመታል።

— 🇮🇷/🇦🇪/🇶🇦/🇸🇦/🇰🇼/🇧🇭 ባህሬን፣ ኩዌት፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በጋራ ባወጡት መግለጫ አማካኝነት፣ ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ አለኝ የምትለውን የባለቤትነት ቁጥጥር አውግዘው፣ መርከቦች፣ በፋርስ ባሕር ላይ ኢራን ያቋቋመችውን አዲሱን አስተዳደር እንዳያነጋግሩ አስጠንቅቀዋል። ኢራን ከትናንት በስቲያ በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ ያላትን የባለቤትነት ድንበር በአዲስ መልክ ቀርጻ ማውጣቷ እና የዛሬ ሁለት ሳምንት በወሽመጡ አስተዳደራዊ ባለስልጣን በማቋቋም ወደ ሥራ መግባቷ ይታወሳል። በውስን ቁጥርም ቢሆን መርከቦች በባሕሩ እየከፈሉ ማለፍ እንደጀመሩ ታውቋል። ይሄ እየሆነ ያለው፣ በሌላ መንገድ እዚያው ባሕሩ ላይ አሜሪካ መርከቦች እንዳያልፉ እገዳ ጥያለሁ በምትልበት ነው።

🇷🇺🇺🇦⚡️— የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን የተነሳውን ጦርነት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ማቆም ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ሞስኮ እንደ አሸናፊ ልትታይ በምትችልበት ሁኔታ ብቻ ነው፣ ሲ
🇷🇺🇺🇦⚡️— የሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን የተነሳውን ጦርነት እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ማቆም ይፈልጋሉ፣ ነገር ግን ሞስኮ እንደ አሸናፊ ልትታይ በምትችልበት ሁኔታ ብቻ ነው፣ ሲል ብሉምበርግ ዘግቧል። ➡ ለዚህ የሩሲያ ቅድመ ሁኔታዎች፣ በዶንባስ ላይ ሙሉ ቁጥጥርን እና አውሮፖ በዩክሬን ውስጥ የሩሲያን የግዛት ባለቤትነት በተግባር እውቅና የሚሰጡ ሰፊ የደህንነት ዋስትናዎችን ማግኘት ያካትታሉ። ** ችግሩ አውሮፓና ዩክሬን ጦርነቱን ማቆም አይፈልጉም፣ በሂደት ቀስ በቀስ ሩሲያን አድምተን እንጨርሳታለን የሚል ሕልም አዳብረዋል። በአጭሩ፣ ጦርነቱ ጥሟቸዋል።

🇺🇸🇮🇷⚡— እንደ FOX NEWS ዘገባ መሠረት፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረጉ ውይይቶች አሁንም በመካሄድ ላይ ናቸው፣ ሁለቱም ወገኖች በመጨረሻ ስምምነት ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ጥቂት
🇺🇸🇮🇷⚡— እንደ FOX NEWS ዘገባ መሠረት፣ በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረጉ ውይይቶች አሁንም በመካሄድ ላይ ናቸው፣ ሁለቱም ወገኖች በመጨረሻ ስምምነት ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ ጥቂት ቢሆንም የተስፋ ምልክቶች አሉ።

+2
🇦🇪🇸🇩🇪🇹❗️በሱዳን እጅግ አስከፊ ጦርነት በቅጽል ስሙ አቡ ሉሉ በመባል የሚታወቀው ወይም እውነተኛ ስሙ፣ አልፋቴህ አብዱላ እድሪስ የሆነው፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዘይድ እና በኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ በከፍተኛ ደረጃ የሚደገፈው፣ የፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) አዛዥ፣ ዛሬም በሱዳን የጦር ሜዳዎች እንዳለ የሚያሳይ አዲስ ቪዲዮ ወጥቷል። በሱዳን ጦርነት 'ከሁሉ የከፋ ወንጀል በሲቪሊያን ላይ የፈጸመ ነው' የሚባለው አቡ ሉሉ፣ ከጥቂት ወራት መጥፋት በኋላ ዳግም ብቅ ብሎ በውጊያ ሜዳ ላይ መታየቱን ሮይተርስ ዘግቧል። አቡ ሉሉ ሴቶችን፣ ህፃናት እና አረጋዊያንን ጨምሮ ባልታጠቁ ንፁሐን ዜጎች ላይ፣ ራሱን በፊልም እየቀረፀ እና እየሳቀ በመረሸን እና በመጨፍጨፍ የሚታወቅ ሲሆን፣ ከዓለም አቀፍ ውግዘት እና ትችት በኋላ ከጦር ሜዳ ጠፍቶ ነበር። ሮይተርስ ደርሼበታለሁ ባለበት የምርመራ ሪፖርቱ፣ አቡ ሉሉ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በቪዲዮ ወጥቶ ታይቷል።

🇺🇸⚡️ — የአሜሪካ የጦር ኃይሎች ሚኒስትር ፒት ሄግሴት፣ ዛሬ በተለቀቀ የጦሩ የመረጃ ቪዲዮ ላይ 'አትችሉንም ይቅርባችሁ' የሚል ይመስላል።
በፕሬዝዳንት ትራምፕ $1.5 ትሪሊዮን ዶላር ወታደራዊ በጀት፣ የተኛውን ግዙፍ አካል እያነቃቃን እና የአሜሪካን የነፃነት መሳሪያ እየገነባን ነው — ይህንን ስናደርግ በፍፁም ኃላፊነት ነው።