ru
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Открыть в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
4 311
Подписчики
-524 часа
-227 дней
-8430 дней
Архив постов
🇩🇪 "ሩሲያ አታሸንፍም" መርዝ የጀርመኑ ቻንስለር፣ ፑቲን በግንባር ቀደምትነት የሚደረገውን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በያዘው አፍራሽ ሚና የሚቀጥል ከሆነ፣ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና
🇩🇪 "ሩሲያ አታሸንፍም" መርዝ የጀርመኑ ቻንስለር፣ ፑቲን በግንባር ቀደምትነት የሚደረገውን ጦርነት እንዲያቆም ጥሪ አቅርቧል። ፑቲን በያዘው አፍራሽ ሚና የሚቀጥል ከሆነ፣ በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና እንደሚጨምር አስፈራርቷል። "ለሩሲያ ግልጽ ምልክት እየላክን ነው፣ ድርድር ለመጀመር፣ የፊት መስመሩን (የግንባር ጦርነቱን) ለማቀዝቀዝ እና ግድያውን ለማስቆም ጊዜው ደርሷል" ብሏል። አያይዞም፣ "ሩሲያ በዚህ ጦርነት አታሸንፍም! አውሮፓ ለዩክሬን የሚያደርገው ድጋፍ አሁንም የማይናወጥ ነው። በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ጫና ለመጨመር ዝግጁ ነን" ሲል መርዝ ተናግሯል። ይህን ያለው፣ የአውሮፓ ሕብረት ለዩክሬን ተጨማሪ $90 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ፣ በመጪው የአንካራ የኔቶ ስብሰባ ላይ ለማወጅ እንደተዘጋጀ በገለፀበት መግለጫው ነው።

🇷🇺⚡️🇺🇦 የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ባለፉት አምስት ወራቶች ከ39,000 በላይ የዩክሬን ድሮኖችን በሩሲያ እና በሩሲያ ቁጥጥር ሥር ባለው ዩክሬን ግዛቶች ላይ ጥለዋል። - ይህም
🇷🇺⚡️🇺🇦 የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር እንደገለጸው፣ ባለፉት አምስት ወራቶች ከ39,000 በላይ የዩክሬን ድሮኖችን በሩሲያ እና በሩሲያ ቁጥጥር ሥር ባለው ዩክሬን ግዛቶች ላይ ጥለዋል። - ይህም በአማካይ በወር 6,000 እና በቀን 223 ድሮኖች ማለት ነው። የሁለቱም ወገኖች ኦፊሴላዊ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ዩክሬን፣ በመጋቢት፣ ግንቦት እና ሰኔ 2026, ከሩሲያ የበለጠ መካከለኛ እና የረዥም ርቀት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ማስወንጨፍ ችላለች። ሩሲያ በበኩሏ፣ እንደ ፈረንጆች ከሐምሌ 2024 ጀምሮ እስከ መጋቢት 2026 ባሉት ወራት ሁሉ፣ ከዩክሬን የበለጠ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን መጠቀም ችላለች።

⚡️🇻🇪 ከታች ያለው ካርታ ከሰኔ 25 ጀምሮ በቅርቡ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ለቬንዙዌላ ሰብዓዊ ዕርዳታ ወይም ድጋፍ ያወጁ ሀገሮችን ያሳያል። ተጨማሪ ሀገሮች በሚቀጥሉት ቀናት የእር
⚡️🇻🇪 ከታች ያለው ካርታ ከሰኔ 25 ጀምሮ በቅርቡ የተከሰተውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ለቬንዙዌላ ሰብዓዊ ዕርዳታ ወይም ድጋፍ ያወጁ ሀገሮችን ያሳያል። ተጨማሪ ሀገሮች በሚቀጥሉት ቀናት የእርዳታ ፓኬጆችን እና የእርዳታ ጥረቶችን ያሳውቃሉ ተብሎ ይጠበቃል። *-*-*-* ምን አስተዋላችሁ? 3ኛው ዓለም የሚባለው፣ 'ጨለማው' በሚል ቅጥያ ስምም የሚታወቀው፣ እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የደሃ ደሃ ሀገሮች የታጨቁበት፣ አህጉረ- አፍሪካ ጭብጥ እጅ መሆኑን አያችሁ? 'ስጥ ይሰጠሃል'፣ የሚለው የመጠሃፉ ቃል 'ጨለማው' ጋር አይሰራም። ይሄን አይቶ እንልካለን ብሎ ያውጅ ይሆን የኖቤሉ ጉብል?

🇮🇱⚡️IDF እንደዘገበው ጋዛ ውስጥ ሕንፃዎችን ለማፍረስ ሲረዳ የነበረ የጦሩ ኮንትራክተር "በኦፕሬሽን ክስተት" መገደሉን ዘግቧል። ያልተረጋገጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ኤክስካቫተሩ መስጊድ እ
🇮🇱⚡️IDF እንደዘገበው ጋዛ ውስጥ ሕንፃዎችን ለማፍረስ ሲረዳ የነበረ የጦሩ ኮንትራክተር "በኦፕሬሽን ክስተት" መገደሉን ዘግቧል። ያልተረጋገጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት፣ ኤክስካቫተሩ መስጊድ እያፈረሰ ነበር እና የሕንፃው ሚናር በኦፕሬተሩ ላይ ወድቆ ሊገድለው ችሏል።

—❗️🇮🇷/🇴🇲 ኦማን፣ ና በኔ በኩል እለፍ፣ አለሁልህ፣ ብላ ነው መርከቡን ያስመታችው። ኦማንን ተማምኖ ውጭ ያደረ የበግ ላት

—❗️🇮🇷/🇴🇲 ሰበር ዜና: የIRGC ባሕር ኃይል ከኦማን 7.5 Miles ርቀት ላይ፣ መርከብ መምታቱን አስታወቀ። መርከቡ፣ በኢራን ባልፀደቀው የሆርሙዝ መስመር ውስጥ ለማለፍ ሲሞክር እንደተመታ
—❗️🇮🇷/🇴🇲 ሰበር ዜና: የIRGC ባሕር ኃይል ከኦማን 7.5 Miles ርቀት ላይ፣ መርከብ መምታቱን አስታወቀ። መርከቡ፣ በኢራን ባልፀደቀው የሆርሙዝ መስመር ውስጥ ለማለፍ ሲሞክር እንደተመታ ነው IRGC የገለጸው። መርከቡ ከመመታቱ በፊት፣ በሃሎ ሃሎ 'ኧረ አንተ ሰው… ' ተብሎ ብዙ ማስጠንቀቂያዎች ተሰጥተው ነበር። 'በምን ታመጣላችሁ' ስሜት ግን፣ ጭራሽ ፍጥነቱን ጨምሮ ተጉዞ ነበር፣ ተብሏል።

🇺🇸🇴🇲🇧🇭 - ማስታወሻ፣ ኦማን ዓለም አቀፉ የባሕር ኃይል ድርጅት ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት የሆርሙዝ ባሕርን በመጠቀም በትራፊክ ላይ ምንም አይነት ክፍያ እንዳይጣል አረጋግጣለው ያለችው እና በዚህ ጉዳይ ከኢራን በተፃራሪ ያፈነገጠችው ዛሬ በባሕሬን በተካሄደው የባሕረ ሰላጤው የትብብር ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ በተገኘበት ነው።

🇮🇷🇴🇲⚡ - ኢራን ኦማን ያለ ቴህራን ተሳትፎ ለሆርሙዝ ባህር የመርከብ መስመሮችን በማውጣቷ ተችታለች። የ IRGC ባሕር ኃይል በሰጠው መግለጫ "አንዳንድ ባለስልጣናት" - ኦማንን በቀጥታ ሳይጠ
+1
🇮🇷🇴🇲⚡ - ኢራን ኦማን ያለ ቴህራን ተሳትፎ ለሆርሙዝ ባህር የመርከብ መስመሮችን በማውጣቷ ተችታለች። የ IRGC ባሕር ኃይል በሰጠው መግለጫ "አንዳንድ ባለስልጣናት" - ኦማንን በቀጥታ ሳይጠቅስ - ከኢራን ጋር ሳይቀናጁ በባሕር ዳርቻው በኩል "አዲስ የመርከብ ትራፊክ መንገድ" አስተዋውቀዋል ብሏል። አክሎም፣ "የተፈቀደላቸው የትራፊክ መስመሮች" በቴህራን የተሰጡ ናቸው፣ ሌሎች ማንኛቸውም "በጣም አደገኛ" መሆናቸውን አስጠንቅቋል። አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን፣ "ይህ የኦማን እርምጃ በደም የተገኘውን የኢራንን ድል ለማጨናገፍ የተወጠነ" ብሎታል። አስተያየቱ የመጣው ኦማን ከዓለም አቀፉ የባሕር ኃይል ድርጅት ጋር በመቀናጀት በሆርሙዝ ባህር ውስጥ "ጊዜያዊ የባህር ኮሪደር" ካወጀች በኋላ ነው። ባለፈው ሳምንት፣ ኦማን፣ ሆርሙዝን በጋራ ከኢራን ጋር ለማስተዳደር እና የይለፍ ቀረጥ ለመቅረጥ ስምምነት ላይ እንደደረሰች ተናግራ ነበር። ምን ተገኝቶ፣ ከነበራት አቋም 360 ዲግሪ እንደዞረች አልታወቀም። *-*-*- ድሮን ለብለብ? ሚሳዬል ስፔሻል? አልበላችም እኮ ኦማን።

🇩🇰⚡️ - ዴንማርክ የእስልምና የጸሎት ጥሪን (አዛን) የሚያሰራጩ መስጊዶች ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እገዳ ለመጣል እያሰበች ሲሆን የኢሚግሬሽን ሚኒስትሩ ሞርተን ቦድስኮቭ ድርጊቱ "በዴንማርክ ውስ
🇩🇰⚡️ - ዴንማርክ የእስልምና የጸሎት ጥሪን (አዛን) የሚያሰራጩ መስጊዶች ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ እገዳ ለመጣል እያሰበች ሲሆን የኢሚግሬሽን ሚኒስትሩ ሞርተን ቦድስኮቭ ድርጊቱ "በዴንማርክ ውስጥ ቦታ የለውም" ሲል ተናግሯ። ➡️ ቦድስኮቭ እስልምና በሕዝብ ህይወት ውስጥ በጣም እየታየ መጥቷል፣ "በዴንማርክ ዙሪያ ስትዞር በእስላማባድ ከተማ ዳርቻ ላይ እንደደረስክ ምንም ጥርጣሬ ውስጥ መሆን የለብህም" ብሏል።

🇷🇺🇺🇦⚡️ — ሩሲያ ምሽቱን በግዛቷ ውስጥ እና በጥቁር ባሕር አቅራቢያ፣ 269 የዩክሬን ድሮኖችን መትቼ ጥያለሁ አለች። RIA Novosti

🇷🇺⚡️🇺🇦 የሩሲያ ጦር ሠራዊት ቁልፍ ከተማ ወደ ሆነችው፣ የሰሜን ምሥራቅ ዩክሬንዋ ሱሚ፣ የተጠጉ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የከተማዋን በር እያንኳኩ ናቸው ተብሏል። የዩክሬን ኃይሎች እስከ አሁን
+2
🇷🇺⚡️🇺🇦 የሩሲያ ጦር ሠራዊት ቁልፍ ከተማ ወደ ሆነችው፣ የሰሜን ምሥራቅ ዩክሬንዋ ሱሚ፣ የተጠጉ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት የከተማዋን በር እያንኳኩ ናቸው ተብሏል። የዩክሬን ኃይሎች እስከ አሁን ድረስም ከተማዋን ነቅለው አለመሸሻቸው፣ ምናልባት እስከመጨረሻው ለመዋጋት ፍላጎት እንዳላቸው ጠቋሚ ነው። ሱሚ፣ የሱሚ ክፍለ ሀገር (Oblast) ዋና ከተማ ናት። ባለፉት አራት ዓመታትም የሩሲያ ጦር ሠራዊት ሲጠጋት ቆይቷል። ሱሚን፣ ጋሸና፣ ወልዲያ፣ ደብረዘቢጥ፣ ደሴ በሏት። ወሳኝ ከተማ ናት።  በሌላ በኩል የሩሲያ ኃይሎች ወደ ሌሎቹ የዩክሬን ከተሞች፣ ለመን፣ ኩብያነስክ እና ካርኪቭ፣ እየተጠጉ መሆኑ ተነግሯል። ዩክሬን በበኩሏ፣ ሩሲያ ጥልቅ ድረስ ዘልቃ በመግባት፣ በድሮን እና በክሩዝ ሚሳዬል 'ወታደራዊ ዒላማ' ያለቻቸውን ስትመታ አንግታለች።

🇺🇸🇻🇪 አሜሪካ ቬኔዝዌላውን በሚያስፈልጋት ለመርዳት፣ ፅኑ ፍላጎቷን ታሳያለች። ዝግጁ ነን … ሁሉም የመንግሥት አካላት ቬኔዝዌላን በመርዳት ላይ በቻሉት እንዲንቀሳቀሱ ትእዛዝ አውርጃለሁ።
🇺🇸🇻🇪 አሜሪካ ቬኔዝዌላውን በሚያስፈልጋት ለመርዳት፣ ፅኑ ፍላጎቷን ታሳያለች። ዝግጁ ነን … ሁሉም የመንግሥት አካላት ቬኔዝዌላን በመርዳት ላይ በቻሉት እንዲንቀሳቀሱ ትእዛዝ አውርጃለሁ።

🇺🇸🇻🇪 አሜሪካ ቬኔዝዌላውን በሚያስፈልጋት ለመርዳት፣ ፅኑ ፍላጎቷን ታሳያለች። ዝግጁ ነን።
🇺🇸🇻🇪 አሜሪካ ቬኔዝዌላውን በሚያስፈልጋት ለመርዳት፣ ፅኑ ፍላጎቷን ታሳያለች። ዝግጁ ነን።

🇻🇪⚡️የቬኒዝዌላ ፕሬዝዳንት፣ ዶልሲ ሮድሪገዝ፣ አስቸኳይ State of Emergency አውጃለች። ቬኔዝዌላ በአሁኑ ሰዓት አስደንጋጭ ሁኔታ ውስጥ ያለች ሲሆን፣ የአየር ክልሏን፣ የአይሮፕላን ማረፊያዎች፣ በተለይ በዋና ከተማው ካራካስ፣ ክፉኛ የተጎዱ በመሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ ዝግ ማድረጓን ገልፃለች። አሜሪካ በመቶዎች የሚቆጠሩ የአደጋ ጊዜ ሠራተኞችን፣ የሕክምና ቁሳቁሶችን፣ ሄሊኮፕተሮችን እና አስፈላጊውን እርዳታ ሁሉ ለማንቀሳቀስ ዝግጅቷን እንዳጠናቀቀች፣  በሁሉም ነገር ከቬኔዝዌላ ሕዝብ ጎን እንደሆነች አስታውቃለች። እንዲሁ የኢልሳልቫዶሩ ፕሬዝዳንት ሀገሩ ቬኔዝዌላን በሚቻለው ለማገዝ ዝግጁ እንደሆነች በመግለፅ፣ በመርከብ የሚያስፈልገው ቁሳቁስ ለመላክ ተዘጋጅተናል ብሏል። ኢኳዶር እና ቦሊቪያም እንዲሁ ከቬኔዝዌላ ጎን እንደሆኑ ተናግረዋል።

🚨 በርካታ ሀገሮች ከባድ በሚባል የመሬት መንቀጥቀጥ ዛሬ ተመትተዋል - M5.6 ካሊፎርኒያ, USA 🇺🇸 - M7.1 ቬኔዝዌላ 🇻🇪 - M7.5 ቬኔዝዌላ 🇻🇪 - M6.9 ጃፓን  🇯🇵

🇻🇪 USGS የቬኔዝዌላን የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክታል ስኬል 7.5 አድርሶታል። መጠኑ፣ በደቡብ አሜሪካ ከፍተኛ ሆነው ከተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጦች ተርታ ሆኗል።
+3
🇻🇪 USGS የቬኔዝዌላን የመሬት መንቀጥቀጥ በሬክታል ስኬል 7.5 አድርሶታል። መጠኑ፣ በደቡብ አሜሪካ ከፍተኛ ሆነው ከተመዘገቡ የመሬት መንቀጥቀጦች ተርታ ሆኗል።

+4
🇻🇪 ሰበር ዜና፡ ቬኔዝዌላ በሬክታል ስኬል በተመዘገበ 7.1 ማግኒቲውድ የመሬት መንቀጥቀጥ ተመታለች። በዋና ከተማው ካራካስ ጨምሮ፣ በበርካታ የሀገሩ ሥፍራዎች፣ ሕንፃዎች ተደርምሰዋል፣ ከፍተኛ ውድመትም እንደደረሰ ታውቋል። የሟቾች ቁጥር ከፍተኛ ይሆናል ተብሎ ተሰግቷል። *-*-*- አይ አሜሪካ …

🇺🇸🇺🇦 ጋዜጠኛ: ዘለንስኪ አሁን ላይ ጦርነቱን እያሸነፈ ነው ብለህ ታስባለህ? ትራምፕ: ከገመትኩት በላይ ጥሩ እየሰራ ይመስለኛል፣ በየትም በኩል እየው፣ ጥሩ እየሠራ ነው በጣም። ቢያንስ የቆመበትን መጠበቅ ችሏል፣ ጦርነቱን መጠበቅ ችሏል። ከሁለቱም ወገን በጣም ብዙ ሕይወት እየጠፋ ነው፣ ግን ጥሩ ይዟል።

🇷🇺 ሩሲያ የተፈጠረባትን የጋዛ እጥረት ለማሟላት፣ ካዛኪስታን ጋዝ እንድትሰጣት ጠይቃለች።
🇷🇺 ሩሲያ የተፈጠረባትን የጋዛ እጥረት ለማሟላት፣ ካዛኪስታን ጋዝ እንድትሰጣት ጠይቃለች።

🇷🇺 የሩሲያን መርከብ ካገኛችሁ አግቱ፣ ዝረፉ፣ ገንዘቡን ውሰዱ፣ ሆኗል ሕጉ፣ ነጣ ገንዘብ። እንግሊዝ ባለፈው ወር 'ማዕቀብ ጥሷል' በሚል የያዘችውን የሩሲያን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ ነዳጁን ሸጣ ገን
🇷🇺 የሩሲያን መርከብ ካገኛችሁ አግቱ፣ ዝረፉ፣ ገንዘቡን ውሰዱ፣ ሆኗል ሕጉ፣ ነጣ ገንዘብ። እንግሊዝ ባለፈው ወር 'ማዕቀብ ጥሷል' በሚል የያዘችውን የሩሲያን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ ነዳጁን ሸጣ ገንዘቡን ለዩክሬን ጦርነት ማስኬጃ ልትሰጥ እንደሆነ አስታወቀች። ከኡራል ሩሲያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረው መርከብ በእንግሊዝ ቻናል ሲያልፍ ነበር በቁጥጥር ሥር የዋለው። የሩሲያን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ከዚህ በፊት ፊንላንድ፣ ፈረንሳይ፣ አሜሪካ፣ ስኮትላንድ፣ እንግሊዝ፣ ዩክሬን ይዘው ገንዘቡን ወደ ኪሳቸው ከተዋል። ሩሲያ፣ የተነፈሰችው የለም። *-*-*-*- እነዚህ ሀገሮች፣ አንዳቸውም፣ የኢራንን መርከብ ይዘው መሸጥ አይደለም፣ ይዘው ሳምንት ለማሳደር እንኳ አይደፍሩም። ድንገት እንኳ ከያዙ፣ አንዲት ነገር ሳትጫር ይመልሳሉ። ያን ያህል ነው፣ የፑቲን ሩሲያ በፑቲን አመራር ሥር ዛሬ የተናቀችው። ምንምም እንደማያመጡ እንግሊዝ በልታቻቸዋች።