ru
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Открыть в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
4 327
Подписчики
+2824 часа
+307 дней
-4230 дней
Архив постов
🚨🇮🇷🇺🇸 Trump ከኢራን ጋር የተደረገውን ስምምነት በተመለከተ ብዙ መግለጫዎች እየፃፈ ነው። ብዙ ንግግሮችንም እያደረገ ነው። ተስማምተናል፣ ኢራኖች ቃል ገብተዋል እያለ ያልተደረጉ ነገሮችን እየፈጠረ ነው። ለኢራን አደጋ ነው ይሄ ይዞ የሚመጣው። እንደ እውነቱ ከሆነ፣ በመሬት ላይ ያለው ነገር እሱ ከሚለው ጋር የተቃረነ ነው። እንዲህ የሚለው፣ በኋላ ላይ ኢራን ሁሉንም የስምምነቱን አዎንታዊ ደረጃዎችን እንደጣሰች እና ከፍተኛ ዋጋ መክፈል እንዳለባት ለማወጅ ነው። በድንገት በ Truth Social ላይ በመፃፍ የኃይል እርምጃ ያዛል። እስራኤልም ድንገተኛ ጥቃት በኢራን ላይ በሰዓታት ወይም በቀናት ውስጥ ልትሰነዝር እንደምትችል ግልጽ ነው።

🇱🇧 ከከፍታ የተነሳ ምስል በእስራኤል ድብደባ Ainata የተባለችውን የሊባኖስን መንደር ያሳያል። Ainata አብዛኛው ነዋሪዎቿ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ጥንታዊ የሮማ ከተማ ናት።
🇱🇧 ከከፍታ የተነሳ ምስል በእስራኤል ድብደባ Ainata የተባለችውን የሊባኖስን መንደር ያሳያል። Ainata አብዛኛው ነዋሪዎቿ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ጥንታዊ የሮማ ከተማ ናት።

🇺🇸⚡️🇮🇷 President Trump: "ኢራን ድጋሜ ባሕሩን መዝጋቷን ሰምቻለሁ። በዚህ ሊያስፈራሩን አይችሉም። አየር ሃይል የላቸው፣ ባሕር ሃይል የላቸው፣ መሪ የላቸው፣ ምንም የላቸውም።"

—❗️🇺🇸/🇮🇷 NEW: የአሜሪካ የጦር መርከብ ከኦማን ዳርቻዎች በቅርብ ርቀት በኢራን ሳይመታ አልቀረም– UKMTO መርከቡ እውን ከተመታ፣ በዛሬው ዕለት ከተመቱት ሦስተኛው ያደርገዋል። በሆርሙዝ
—❗️🇺🇸/🇮🇷 NEW: የአሜሪካ የጦር መርከብ ከኦማን ዳርቻዎች በቅርብ ርቀት በኢራን ሳይመታ አልቀረም– UKMTO መርከቡ እውን ከተመታ፣ በዛሬው ዕለት ከተመቱት ሦስተኛው ያደርገዋል። በሆርሙዝ ወሽመጥ ለማቋረጥ የሞከሩ ሁለት የሕንድ ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ዛሬ ጠዋት በኢራን ፈጣን የባሕር ላይ ጀልባዎች በተከፈተባቸው ተኩስ ተመትተው እንደቆሙ ታውቋል።

🇮🇷 የኢራን ጠቅላይ መሪ አያቶላህ ሙጅተባ ኻሚኒይ፡ "ባሕር ሃይላችን በጠላቶቹ ላይ መራር ሽንፈትን ሊያወርድ ዳግም ዝግጁ ነው።

🇮🇷 የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣን ለ FOX NEWS፡ የሆርሙዝ ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ በ IRGC ቁጥጥር ሥር ነው፣ አሁን ተዘግቷል።
🇮🇷 የአሜሪካ የደህንነት ባለስልጣን ለ FOX NEWS፡ የሆርሙዝ ወሽመጥ ሙሉ በሙሉ በ IRGC ቁጥጥር ሥር ነው፣ አሁን ተዘግቷል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 "አስጠንቅቀን ነበር፣ ነገር ግን አልተሰማንም። ይኸው፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ወደ ነበረበት በመመለሱ እንኳን ደስ ያላችሁ።" የኢራን ፖርላማ ፕሬዝዳንት
🇮🇷⚡️🇺🇸 "አስጠንቅቀን ነበር፣ ነገር ግን አልተሰማንም። ይኸው፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ ወደ ነበረበት በመመለሱ እንኳን ደስ ያላችሁ።" የኢራን ፖርላማ ፕሬዝዳንት

—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን ጦር ኃይሎች ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም ስለመዘጋቱ፣ ያወጣው ሙሉ መግለጫ፡ - እንደ አለመታደል ሆኖ፣ አሜሪካውያን የገቡትን ቃል በመጣስ ደጋግመው ሪከርዳቸ
—❗️🇺🇸/ 🇮🇷 የኢራን ጦር ኃይሎች ዋና መሥሪያ ቤት፣ ሆርሙዝ ወሽመጥ ዳግም ስለመዘጋቱ፣ ያወጣው ሙሉ መግለጫ፡ - እንደ አለመታደል ሆኖ፣ አሜሪካውያን የገቡትን ቃል በመጣስ ደጋግመው ሪከርዳቸውን እያሻሻሉ ቆይተዋል። ዛሬም ይህን የክህደት ሪከርዳቸውን አስቀጥለው፣ 'እገዳ' ብለው ባሉት ሽፋን በባሕር ላይ ውንብድና እና ዘረፋ ላይ መሳተፋቸውን ገፍተውበት ይገኛል። በመሆኑም፣ ዛሬ፣ ከዚህች ሰዓት ጀምሮ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ በኢራን ጦር ሠራዊት ዝግ ተደርጓል። የባህር ቁጥጥሩም ወደ ቀደመው ቦታው ተመልሷል፣ እናም ይህ ስልታዊ የውሃ መንገድ በጦር ኃይሎች ጥብቅ አስተዳደር እና ቁጥጥር ስር ይቆያል። አሜሪካ መርከቦች፣ ከኢራን ወደ መድረሻው፣ እና ከመድረሻው ወደ ኢራን፣ ሙሉ በሙሉ እንዲንቀሳቀሱ እስካልፈቀደች ድረስ፣ በሆርሙዝ ባህር ውስጥ ያለው ሁኔታ በጥብቅ ቁጥጥር ሥር እና እንደ ቀድሞው ሁሉ በነበረበት ሁኔታ እንዲቆይ ይደረጋል።

🇮🇷⚡️🇺🇸ሰበር፡ ኢራን የሆርሙዝን ወሽመጥ በድጋሜ ዘጋች። ይህን ያለችው ዛሬ ሁለት የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በአሜሪካ እንዳያልፉ መታገዳቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ኢራን "ሁሉም መርከቦች እን
🇮🇷⚡️🇺🇸ሰበር፡ ኢራን የሆርሙዝን ወሽመጥ በድጋሜ ዘጋች። ይህን ያለችው ዛሬ ሁለት የኢራን ነዳጅ ጫኝ መርከቦች በአሜሪካ እንዳያልፉ መታገዳቸው ከተሰማ በኋላ ነው። ኢራን "ሁሉም መርከቦች እንዲያልፉ ብለን ብንከፍትም፣ አሜሪካ የእኛን እያሳለፈች ባለመሆኑ፣ ሁርሙዝ ወደ ባለቤቱ ኢራን እንዲመለስ ተደርጓል" ብላለች በመግለጫዋ።

🇮🇷🇵🇰🇺🇸 ሌላ ዙር ድርድር፣ በመጪው ሰኞ በኢስላማባድ ፓኪስታን እንደሚደረግ CNN የኢራንን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።
🇮🇷🇵🇰🇺🇸 ሌላ ዙር ድርድር፣ በመጪው ሰኞ በኢስላማባድ ፓኪስታን እንደሚደረግ CNN የኢራንን ባለስልጣናት ጠቅሶ ዘግቧል።

🇮🇱⚡️ አዲሱ የኔታንያሁ የፕሬስ ቢሮ ዳይሬክተር Eli Hazan ሆን ብሎ የውሸት ዜናዎችን እንደ መገናኛ ዘዴ ለመጠቀም እንደሚፈበርክ ተናግሯል። "እውነት ከእንግዲህ አይሰራም። እውነት ከእንግዲህ ምንም ማለት አይደለም። ትራምፕን መሆን አለብን።"

🇮🇷⚡️🇺🇸 "የአሜሪካንን ጦር ሰራዊት ለቅቀው ለመውጣት ለሚያስቡ 'ህሊናዊ ተቃዋሚ' ወታደሮች የተዘጋጁት የስልክ መስመሮች፣ በሚደውሉ የሰራዊቱ አባላት ተጨናንቀዋል። ሁሉም ጥሪዎች ማለት ይቻላል
🇮🇷⚡️🇺🇸 "የአሜሪካንን ጦር ሰራዊት ለቅቀው ለመውጣት ለሚያስቡ 'ህሊናዊ  ተቃዋሚ' ወታደሮች የተዘጋጁት የስልክ መስመሮች፣ በሚደውሉ የሰራዊቱ አባላት ተጨናንቀዋል። ሁሉም ጥሪዎች ማለት ይቻላል፣ በኢራን የሴቶች ትምህርት ቤት ላይ 170 ህፃናት ልጆችን የገደለውን የቦምብ ጥቃት ይጠቅሳሉ።"

🇮🇱 🇺🇸 ትራምፕ ለእስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት 'አቁሚ' ማለቱ፣ ኔታንያሁን 'አፍዝዞታል፣ አስደንግጦታል።' የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶ
🇮🇱 🇺🇸 ትራምፕ ለእስራኤል በሊባኖስ ላይ የምታደርገውን ጥቃት 'አቁሚ' ማለቱ፣ ኔታንያሁን 'አፍዝዞታል፣ አስደንግጦታል።' የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፍ፣ በግል "ደንግጠዋል፣ ፈዘዋል" ሲል የእስራኤሉ Channel 14 ዘግቧል። ትራምፕ እስራኤልን ሳያማክር እንዲሁ ተነስቶ በድህረ ገፁ የእስራኤል መንግስት ሊባኖስን እንዳያጠቃ  "ተከልክሏል" ማለቱ፣ ኔታንያሁን እና መንግስቱን አስደንግጧል።

🇮🇷 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ፡ "ዩራኒየማችን እንደ ኢራን አፈር ውድ ነው! ለማንም በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ አሳልፈን አንሰጥም።

🇮🇷 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር: "ኢራን ዩራኒየሟን በፍፁም አሳልፋ አትሰጥም!"
🇮🇷 የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር: "ኢራን ዩራኒየሟን በፍፁም አሳልፋ አትሰጥም!"

🇺🇸⚡️🇮🇷 ኢራን የበለፀገውን 400kg ዩራኒየሟን በተለቀቀላት ገንዘብ ምትክ ለአሜሪካ ልታስረክብ ተስማምታለች፣ የሚል ወሬ ወጥቷል። በዚህም ምክኒያት ይመስላል፣ ትራምፕ በሁሉም ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ላይ ደርሰናል ያለው። ይሄ እውነት ከሆነ፣ ኢራን ተበላች ማለት ነው። 1. ሲጀመር 'ተለቀቀ' የተባለው $20 ቢሊዮን ዶላር የኢራን የራሷ ነው። የራሷን ገንዘብ ነው መልሳ ያገኘችው። አሜሪካ በልውውጡ 'የሰጠቻት' 0 ነው። 2. ይሄ አሃዝ ኢራን ከተያዘባት የገንዘብ መጠን ውስጥ ኢምንቱ ነው። ከጠቅላላው ፖለቲካዊ ሁነት ጋር ሲተያይም ምንም ማለት ነው። ቢያንስ ማዕቀቡን ማስነሳት ይገባቸው ነበር። 3. $20 ቢሊዮን የራስ ገንዘብ ተመልሶ ተሰጠኝ በሚል፣ ከ 10 ዓመት በላይ የለፉበትን ዩሬንየምና ሊያገኙት ጫፍ የደረሱበትን መመኪያ የኒውክሊየር ቦንባቸውን አሳልፎ ማስረከብ እብደት ነው፣ በምንም መስፈርት ልክ ሊሆን አይችልም። 4. $20 ቢሊዮን ነገ ይጠፋል፣ ለኢኮኖሚው የሚጨምረው የለም፣ ወደ ግል ሴክተሩ አይሄድም። ምናልባት መሳሪያ ይገዛበታል፣ እሱንም አሜሪካ ከፈቀደች የሚሆን ነው። ስለዚህ፣ በዚህ ሁኔታ ኢራን ዩራኒየሟን ልታስረክብ ተስማማች የሚባለው ከወሬ በዘለለ እውነት አይመስለኝም። አሜሪካ በጦርነቱ ያላሳካችውን የዩራኒየም ቅሚያ፣ በድርድር አሳካችው ለማለት ይከብዳል።

ሊያቋርጡ የነበሩ በርካታ መርከቦች ወደኋላ ተመልሰዋል። ሆርሙዝ ተከፈተ የተባለ ቢሆንም፣ ምናልባት ኢራን መርከቦቹ ከማለፋቸው በፊት ሂሳብ መክፈል፣ ከ IRGC ጋርም መቀናጀት ይሮርባቸዋል በማለቷ በተፈጠረ አለመግባባት ሊሆን ይችላል።

🇺🇸⚡️🇮🇷 — አዲስ: ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለCBS News፡ "ኢራን ሁሉንም ነገር ለማድረግ ተስማምታለች፣ የሚገርም ነው። ሁሉንም ለማድረግ ተስማማች። በጣም ደስ ይላል።"

🇺🇸⚡️🇮🇷 — አዲስ: ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለ CBS News፡ "ኢራን እንደ ሂዝቦላ እና ሀማስ ያሉ ቡድኖችን ካሁን በኋላ ላትረዳ ተስማምታለች።"

photo content