ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Открыть в Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
195
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-730 дней
Архив постов
የሩቅ ምስጢር (1).pdf6.06 KB

አንተ ወንጀልህን እንደ ጀብድ የምትናገረው ወንድም ሆይ! ጥንቃቄ አድርግ! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿كُلُّ أُمَّتِي مُعَافًى إِلَّا الْمُجَاهِرِينَ ، وَإِنَّ مِنَ الْمَجَانَةِ أَنْ يَعْمَلَ الرَّجُلُ بِاللَّيْلِ عَمَلًا، ثُمَّ يُصْبِحَ وَقَدْ سَتَرَهُ اللَّهُ، فَيَقُولَ : يَا فُلَانُ، عَمِلْتُ الْبَارِحَةَ كَذَا وَكَذَا. وَقَدْ بَاتَ يَسْتُرُهُ رَبُّهُ، وَيُصْبِحُ يَكْشِفُ سِتْرَ اللَّهِ عَنْهُ﴾ “የሁሉም ህዝቦቼ ወንጀላቸው ይማርላቸዋል በግልፅ አውጥተው የሚናገሩት ሲቀሩ። ሰውዬው በለሊት ማንም ሳያየው ወንጀል ይፈፅምና አላህ ደብቆሎት ሳለ ከዛ ንጋት ላይ እንዲህ ይላል፦ እከሌ ሆይ! እኔ እኮ ትላንት ማታ ይህን ይህን ሰርቼያለሁ ጌታው የምሽት ስራውን ደብቆለት ሳለ እሱ ግን ንጋት አላህ ከሱ ላይ የደበቀለትን (የሸፈነለትን) ወንጀል ይገልፃል (ይረጫል)።” አላህ ሰትሮናል እና ወደ እርሱ ተመልሰን ተዉበት እናድርግ። 📚 ቡኻሪ (6069) ሙስሊም (2990) ዘግበውታል            

"ከአላህ ሌላ የሆነን አካል እየተጣራ የሞተ ሰው በእርግጥ እሳት ገባ" ብለዋል መልዕክተኛው ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም። ስለዚህ ተውሒዳችንን እናስተካክል።

4_5945205443222573303 (1).mp44.58 MB

ነጃሳው የበዛበት የቲክ ቶክ ግቢ ውስጥ የረባ ያልረባውን የምትሰሙና የምትመለከቱ ወንድሞችና እህቶች አሏህን ፍሩ ! ሁሉም ነገር አልፎ የቀብርን አፈር መንተራስ ይመጣል ፣ ይሄ ሁሉ አክትሞለት አሏህ ፊት መቆም ይከሰታል ! ✍️አሏህ ነገራችንን ሁሉ ተመልካች ነው ! እዚህ መንደር እውነተኛን ደስታ ማግኘት የሚታሰብ አይደለም ። የረከሱ እርኩሳንን መመልከትና መከታተል ከአማኞች ክብር ጋር የማይሄድ ምግባር ነው ።  ነፍስን የሚያረክስ ጎጂ ልማድ ነው ! እናንተ አማኞች ሆይ ፣ የተከበራችሁ ናችሁና የረከሰውን ለሚገባው ተውት ! ወደ እምነታችን ፣ ወደ ክብራችን እንመለስ !❗️            

በአንድ ረከአ ብቶን የለሊት ሰላት አደራ!! ✍የአላህ መልእክተኛ ሰለሏህ አለይሂ ወሰለም እንድህ አሉ። የመጨረሻ ሶላታችሁን በለሊት ዊትር አድርጉ 📚(ቡኻሪ ሙስሊም ዘግበውታል)            

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ሴቶች በዩኒቨርሲቲው እየደረሰባቸው ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፅ ይሆኗቸው ዘንድ በEBC እና ፋና ዋና ፅ/ቤት በመገኘት አቤቱታ አቀረቡ ! ! ! --------
+4
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ሴቶች በዩኒቨርሲቲው እየደረሰባቸው ስላለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ድምፅ ይሆኗቸው ዘንድ በEBC እና ፋና ዋና ፅ/ቤት በመገኘት አቤቱታ አቀረቡ ! ! ! -------------------------------------------- መጋቢት 22 / 2018 ዓ.ል --------------------------------------------   ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ከሆኑ ቡሃላ የሙስሊም ተማሪዎችን ሒጃብ (ኒቃብ) የመልበስ ሰብዓዊ መብት የሚከለክል ኢ- ሕገመንግስታዊ መመሪያ ወጥቶ ተማሪዎች ለመጠነ ሰፊ እንግልት መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው። ይህንንም ተከትሎ ላለፉት 18 ወራት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች የተደረገ ሲሆን ባለፉት ሳምንታት ውስጥ በማህበራዊ ሚዲያ በተደረገ ዘመቻ የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ሐብት የሆኑት እነ EBC: FANA እና ሌሎች ሚዲያዎች የተማሪውን ድምፅ እንዲያስተጋቡ፤ ዩኒቨርሲቲውን እና አመራሩንም ተጠያቂ እንዲያደርጉ ሲጠየቅ ነበር።   ሆኖም ምላሽ ባለመገኘቱ በዛሬው እለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሚዲያዎቹ ጽ/ቤት በመገኘት ሚዲያዎቹ ሚዛናዊ እና ፍትሐዊ ዜናዎችን በመስራት እና ዘገባዎችን በማውጣት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት ድምፅ ሆነው ሀላፊነታቸውን ይወጡ ዘንድ ጠይቀዋል።    በአላህ ፈቃድ መሠል እንቅስቃሴዎች በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ግፍ እስኪቆም ድረስ የሚቀጥል ይሆናል። በቀጣይ የሚኖሩ እንቅስቃሴዎችን እና ውጤቶችንም የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ጥያቄ አለን: ዛሬም ነገም! ጥያቄ አለን: ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ!! ጥያቄ አለን: ቢሮ ውስጥም በአደባባይም!

ለወንድማችን ሙሐመድ አህመድ አል-ጃዊ ላፕቶፕ ለመግዛት ይደረግ የነበረው የገቢ ማሰባሰብ ስራ ተጠናቋል! በድምሩ 72,840 ብር የተሰበሰበ ሲሆን፣ በዚህ ገንዘብ አሪፍ የሚባል ላፕቶፕ ተገዝቶ ለወንድማችን የሚረከብ ይሆናል። የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ያደረጋችሁ ሁሉ አላህ ይዘንላችሁ፤ መልካሙን ሁሉ ይወፍቃችሁ። የገቢ ማሰባሰቡ ፋይል በዚህ ተዘግቷል። ጀዛኩሙላህ ኸይር!

⭕ ማሳሰቢያ 🚥🚥🚥🚥🚥 አብዛኞቹ እህቶች የፈተዋ ጥያቄ ለመጠየቅ ብለው እየገቡ ባለማወቅ እየተሸወዱ ነው!! 🚫 ይህ ቻናል የሀጁሪዎች ቻናል እንጂ የሰለፊያዎች ቻናል አይደለም ሰለፊያ ስለተመሳ
⭕  ማሳሰቢያ 🚥🚥🚥🚥🚥 አብዛኞቹ እህቶች  የፈተዋ ጥያቄ ለመጠየቅ ብለው እየገቡ  ባለማወቅ እየተሸወዱ ነው!! 🚫 ይህ ቻናል የሀጁሪዎች ቻናል እንጂ የሰለፊያዎች ቻናል አይደለም ሰለፊያ ስለተመሳሰሉ አትሸወዱ ሰለፊ ነን ስላሉ ብቻ ሰለፊ ናቸው ማለት አይደለም አብዛኞቹ እህቶች  የፈተዋ ጥያቄ ለመጠየቅ ብለው እየገቡ  ባለማወቅ እዛው እየተመሳሰሉ ነው ያሉት በሰለፊዎች ዘንዳ በቂ የሆነ የፈትዋ ጥያቄ የሚጠየቅበት መንገድ  ባለመመቻቸቱ የተነሳ እህቶቻችን ወደዛ እንዲጎርፉ እያደረጋቸው ነው  በመጀመሪያ ደረጃ እውቀት ከማን ከማን መውሰድ እንዳለብን ጠንቅቀን እንወቅ ጥያቄ እኮ ጃሂልም ይመልሳል ግን መልሱ የተሳሳተ ነው ሊሆን የሚችለው ጥያቄ ለመጠየቅ የሚመልስልን ሳይሆን ትክክለኛ እውቀት ያለው ሰው ነው የሚያስፈልገው ©°py

ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና የተባለ ታላቅ ሊቅ እንዲህ ይላል :- "በምድር ላይ አንድም የቢዳዓ ባለቤት የለም የሚሸፍነው ውርደት የሚያገኝ ቢሆን እንጂ እሱም በቁርአን ላይ ነው የት ቦታ ላይ ነው ብለው ጠየቁት እንዲህ የሚለው የአላህን ቃል  አልሰማችሁም እንዴ አላቸው "እነዚያ ወይፈንን ጣኦት አድርገው የያዙ ሰዎች ከጌታቸው ዘንድ የሆነ ቁጣና ውርደት በቅርቢቱ ዓለም ያገኛቸዋል " የሙሀመድ አባት ሆይ ይህ እኮ ወይፈን ያመለኩት ብቻ የሚመለከት ነው አሉት በፍፁም ቀጥሎ ያለውን አንብቡት "እንደዚሁ ቀጣፊን ሁሉ እንመነዳለን " ከዚያም ይህ አንቀፅ ሁሉንም ቀጣፊና ሙብተዲዕን እስከ ቂያማ ይመለከታል አላቸው " حلية الاولياء (٢٨٠/٧)

"ከእኛ ዘንድ ዳዕዋ ከወንበር (ከስልጣን) ትበልጣለች" ሸይኽ ሙቅቢል ረሒመሁሏህ

ነቢያት በጌታቸው ያላቸው መተማመን ~ 1⃣- ኑሕ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی لَغَفُورࣱ رَّحِیمࣱ} {ጌታዬ በእርግጥ መሓሪ አዛኝ ነው።} [ሁድ፡ 41] 2⃣- ሁድ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءٍ حَفِیظࣱ} {ጌታዬ በነገሩ ሁሉ ላይ ጠባቂ ነው።} [ሁድ፡ 57] 3⃣- ሷሊሕ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی قَرِیبࣱ مُّجِیبࣱ} {ጌታዬ ቅርብ (ልመናን) ተቀባይ ነው።} [ሁድ፡ 61] 4⃣- ኢብራሂም ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی لَسَمِیعُ ٱلدُّعَاۤءِ} {ጌታዬ በእርግጥ ልመናን ሰሚ ነው።} [ኢብራሂም፡ 39] 5⃣- ሹዐይብ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی رَحِیمࣱ وَدُودࣱ} {ጌታዬ አዛኝ ወዳድ ነው።} [ሁድ፡ 90] 6⃣- ዩሱፍ ﷺ :- {إِنَّ رَبِّی لَطِیفࣱ لِّمَا یَشَاۤءُۚ} {ጌታዬ ለሚሻው ነገር እዝነቱ ረቂቅ ነው።} [ዩሱፍ፡ 100] 7⃣- ሙሳ ﷺ :- {إِنَّ مَعِیَ رَبِّی سَیَهۡدِینِ} {ጌታዬ ከእኔ ጋር ነው። በእርግጥ ይመራኛል።} [ሹዐራእ፡ 62] 8⃣- ሱለይማን ﷺ :- {فَإِنَّ رَبِّی غَنِیࣱّ كَرِیمࣱ} {ጌታዬ ተብቃቂ ቸር ነው።} [ነምል፡ 40] 📚 ምንጭ፦ [ፈራኢድ ወፈዋኢድ ሚነል ቁርኣኒል ከሪም] = IbnuMunewor

ጓደኝነታችሁ አርተፊሺያል ጓደኝነት አታድርጉት ! 🎙 በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ሀፊዘሁላህ https://t.me/Darutewhide

እንዲህ አድርጉ
እንዲህ አድርጉ

ከቤትህ ወይም ከቤትሽ ውስጥ መጥፋት የሌለባቸው ኪታቦች...... 🎙በኡስታዝ አቡ ሙስሊም ሀፊዘሁላህ https://t.me/Darutewhide

ወዓለይኩም ሰላም ወራህመቱሏሂ ወበረካቱህ

አሠላሙአለይኩም ወረህመቱሏህ

ለወላጆች ማዘን.mp32.47 MB

ለቤተሰብ ማዘን.mp31.47 MB