ru
Feedback

Не попадитесь на канал ботавода! Telemetrio находит и помечает такие каналы 👉 Хотите видеть метку — оформите подписку

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

✍የራያ እና አካባቢው የሰለፍዮች ቻናል

Открыть в Telegram

ዋና አላማችን ትክክለኛውን ኢስላማዊ አስተምህሮት 👉 ከቁርዓን እና ከሐዲሥ፣ [በሰለፎች አረዳድ]፣ 👉 ከታማኝ የሱና ዑለማዎች፣ኡስታዞች፣ዳዒዎች፣ወንድሞች ፣ የተለያዩ ጠቃሚ መረጃዎች፣ ምክሮች፣ሙሀደራዎች ፣ 👉ማህበረሰባችንን የሚመለከቱ ጥቆማዎች እና ወቅታዊ መረጃዎችን በአማርኛ ቋንቋ የምናደርስበት የመረጃ አውታር ነው። https://t.me/Rayaselefi

Больше
Страна не указанаКатегория не указана
195
Подписчики
Нет данных24 часа
-37 дней
-730 дней
Архив постов
የጠ/ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ የሙስሊም ጥላቻ እስከዚህ ድረስ ነበር፦ «እኔ ፕሬዝዳንት እንድሆን በተጠየኩበት ወቅት በእውቀት ከኔ የሚበልጥ አንድ ሙስሊም ሰው ነበር። እሱ ከኔ የተሻለ ስለሆነ ፕሬዝዳንት እሱ ይሁን ብዬ ለ አቶ መለስ ዜናዊ ሀሳብ አቀረብኩኝ። እሱም አይ ሀገራችን ለሙስሊም መሪ ዝግጁ አይደለችም ብሎ መለሰለኝ። እኔም እንዲህ አይነት አስተሳሰብ መኖሩን በሰሟህ ጊዜ እጅጉን ተገርሜ ነበር።» ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ በሙስሊምነታቸው ምክንያት የኢትዮጵያ ፕረዝዳንት እንዳይሆኑ የተደረጉት ዶ/ር ጀማል ዓብዱልቃድር ናቸው ።

Repost from Dr. Seid Musa
👌 ሸይኽ ሙሐመድ አወል ሰዒድ - አላህ ይጠብቃቸውና - እንዲህ አሉ:- "ከስንፍና ጋር የመጣ ድህነት ከምቀኝነት ጋር የመጣ ጥላቻ ከርጅና ጋር የመጣ በሽታ መድሃኒት የለውም።" = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/AbulbukhariSeid

👉 ሽርክ የመጭው አለም ህይወት (አኼራችንን) ብቻ ሳይሆን በዱኒያም ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ያደርሳል።ከዚህም በመነሳት አንድ ግለሰብ የደረሰበትን  ጉዳት  እንዲህ ሲል እወቁልኝ ብሏል። ኑሮ  ላይ ላስመትት ጠንቋይ ቤት ዘልቄ፣ እርሱ የሌለውን ብዙ ሀብት ጠይቄ፣ በቀጠሮ ብዛት ዶሮ ሳመላልስ፣ ሽሮ እየበላሁኝ ቀን በቀን ስለግስ፣ ፈረሰኛ በልቶ በድሎት ሲያገሳ፣ ያለኝን ሰጥቼ ሰውነቴም ከሳ፣ አወይ ሞኝነቴ እንዴው ከንቱነቴ፣ ዶሮን እየሰጠሁ ሽሮ እንኳን ማጣቴ፣ ላስመትት ገብቼ ተሰርቶብኝ መጣሁ፣ ጠንቋይን አምኜ ገንዘቤን ተበላሁ ለእርሱ የወሰድኩት በሒሳብ ቢደመር፣ ለእኔ ዶሮ እርባታ ያስጀምረኝ ነበር ።

የቤት አያያዝ አደቦች፦ 1. ፎቶን ማስወገድ 2. ውሻን ማስወጣት 3. ከመጠን በላይ አለማስዋብ 4. በጣም ውድ እቃ አለማስገባት 5. ግድግዳን አለመለጠፍ 6. ለልጆች አደብ ማስያዣ አለንጋ ማንጠልጠል 7. ሲተኙ እሳትን ማጥፋት 8. መጝሪብ ላይ ህፃናትን መሰተር 9. በሮችን መዝጋት 10. እቃዎችን መግጠም /መሸፈን 11. ቁርአን መቅራት በተለይ ሱረተል በቀራን 12. ትርፍ ሶላቶችን ከቤት መስገድ = [ኢርሻዱል አናም፣ (260 - 264)] (ሸይኽ ኡሳማ ብኑ ዘይድ አልኹኺ)

👉 ሽርክ የመጭው አለም ህየወት(አኼራችንን) ብቻ ሳይሆን በዱኒያም ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ያደርሳል።ከዚህም በመነሳት አንድ ግለሰብ የደረሰበትን ጉዳት እንዲህ ሲል እወቁልኝ እያለ ነው። ኑሮ ላይ
👉 ሽርክ የመጭው አለም ህየወት(አኼራችንን) ብቻ ሳይሆን በዱኒያም ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶችን ያደርሳል።ከዚህም በመነሳት አንድ ግለሰብ የደረሰበትን ጉዳት እንዲህ ሲል እወቁልኝ እያለ ነው። ኑሮ ላይ ላስመትት ጠንቋይ ቤት ዘልቄ፣ እርሱ የሌለውን ብዙ ሀብት ጠይቄ፣ በቀጠሮ ብዛት ዶሮ ሳመላልስ፣ ሽሮ እየበላሁኝ ቀን በቀን ስለግስ፣ ፈረሰኛ በልቶ በድሎት ሲያገሳ፣ ያለኝን ሰጥቼ ሰውነቴም ከሳ፣ አወይ ሞኝነቴ እንዴው ከንቱነቴ፣ ዶሮን እየሰጠሁ ሽሮ እንኳን ማጣቴ፣ ላስመትት ገብቼ ተሰርቶብኝ መጣሁ፣ ጠንቋይን አምኜ ገንዘቤን ተበላሁ ለእርሱ የወሰድኩት በሒሳብ ቢደመር፣ ለእኔ ዶሮ እርባታ ያስጀምረኝ ነበር ።

​⭕ ገንዘብህንና እድሜህን በጫት አታባክን ​🍁🥀🍁🥀🍁🥀 ​በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ፣ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። የአላህ ሰላትና ሰላም በመልእክተኛው፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸውና ቅኑን መንገድ በተከተሉት ሁሉ ላይ ይሁን። ከዚህ በመቀጠል፦ ​ወንድሜ ሆይ! የጫት ተክል ይጎዳሃል ሃይማኖታዊ ቅጣት ያለው ወንጀል ከመሆኑም በላይ በአእምሮህ፣ በአካልህ፣ በዱንያህና በአኼራህ ላይ ጉዳት አለው። ​አላህ ሀብትን የሰጠህ ሰው ሆይ! ስለ እሱ እንደምትጠየቅ እወቅ። ልእለ ሀያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በውስጡ መሸጥ፣ ወዳጅነትም፣ ምልጃም የሌለበት ቀን ሳይመጣ ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ...﴾ [ልቡቃራ፡ 254] አላማህ ሰዕዲ በተፍሲራቸው ላይ እንዲህ ብለዋል፦ "ይህ አላህ ለባሮቹ ካለው እዝነት የተነሳ ነው፤ ሰራተኞች የአንዲት ብጥስጣሽ ፍሬ ያህል መልካም ስራ በሚያስፈልጋቸው ቀን ለእነሱ መያዣና ሙሉ ምንዳ ይሆን ዘንድ አላህ ከሰጣቸው ሲሳይ ግዴታና ተወደጅ የሆኑ ምጽዋቶችን እንዲሰጡ አዟቸዋል።" ​የአላህ ባሪያ ሆይ! ገንዘብ ፈተና እንደሆነ እወቅ፣ ታግሰህ በሃላል ታወጣዋለህ፣ ወይም በጸጋው ክደህ በሃራም ታባክነዋለህ። ስንት የሚረዳቸው የሚፈልጉ የቲሞች፣ ስንት ባል የሞተባቸው ሴቶች፣ ስንት ደሃዎችና ምስኪኖች፣ ስንት ገንዘብ የሚፈልጉ ችግረኞች አሉ! አንተ ግን በገንዘብህ 🌿 ጫት ትገዛበታለህ። አላህ የሰጠህ እንድትሰጥና በዙሪያህ ያሉትን ሙስሊሞች እንድትረዳ ነው፤ ስትሰጥ ደግሞ የልብ እረፍትና ደስታ እንደሚሰማህ ሙሉ በሙሉ እርግጠኛ ሁን። ​ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፦ ﴿...ማንኛውንም ነገር ብትሰጡ እሱ ይተካዋል፤ እሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ የበላይ ነው﴾ [ሰባእ፡ 39]፤ ስለዚህ ምጽዋት (ሶደቃ) ገንዘብን አያጎድልም፤ ይልቁንም ይጨምረዋል። ​እውነተኛ ጥረትና ደስታ ሁልጊዜም በአላህ መንገድና አላህን በሚያስደስት ሃላል ነገር ውስጥ ነው። በሃራም ነገሮች ላይ በማደር ጊዜውን የሚያባክን፣ መብቶችና ግዴታዎችን የሚተው ሰው እንዴት ይሆናል? በጫት ምክንያት በባለቤቱ፣ በልጆቹና በወላጆቹ ላይ እንኳ ወጪ አያደርግም። ጫት ጉልበትህንና ገንዘብህን በመቃም የሚያጠፋ ተክል ነው፤ ጊዜህና እድሜህ ከጫትና ከከፋ ጓደኞችህ ጋር ያልቃል፤ ከዚያም በ ትንሳኤ ቀን በትንሽ ትልቁ ትጠየቅበታለህ! ​የአማኝ ሁኔታ አላህ ባዘዘውና በከለከለው ነገር ላይ ታዛዥና እጅ የሰጠ መሆን አለበት። የልዑል አላህን ቃል ተመልከት፦ ("እናንተ ሰዎች ሆይ! በምድር ላይ ካለው የተፈቀደውንና መልካሙን ብሉ፤ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ፤ እሱ ለእናንተ ግልጽ ጠላት ነውና" [ልቡቃራ፡ 168] አንቀጹ ግልጽ ነው። የአላህ ባሪያ ሆይ! አላህ ከሰጠህ የተፈቀደና ጠቃሚ ነገር ብላ፤ አንተ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ አረንጓዴ መርዝ የሆነውን ጫት ወስደህ ሰውነትህን ትመግባለህ። ​ስጋን፣ ፍራፍሬዎችንና አትክልቶችን ለምን ትተዋለህ... ​ይህ ንግግር ለአርሷደሩም ጭምር ነው፤ ሰዎችን የሚጎዳ ነገር ትዘራለህ፣ ወይም በየቀኑ በሚረጩት መርዞች ምክንያት ሰውነትህ ይጎዳል። እንዲሁም የሚገርመው ነገር ሰውነትህን በመጉዳት ለተከለከሉና በኮንትሮባንድ ለሚገቡ መርዞች ሻ ጮች መተባበርህ ነው፤ ይህ አእምሮ የሚቀበለው ነውን? በፍጹም አይደለም፣ አላህንም አያስደስትም። ​ውድ ወንድሜ ሆይ! ሰውነትህ ባንተ ላይ መብት እንዳለው እወቅ። እያንዳንዱ የሰውነትህ ክፍል ባንተ ላይ ይመሰክራል። የአርሹ ባለቤት የአላህን ቃል ተመልከት፦ ﴿ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ይሠሩት በነበረው ነገር በእነሱ ላይ በሚመሰክሩበት ቀን﴾ [አል-ኑር፡ 24] አንተ ምስኪን ቃሚ ሆይ! እጆችህ መርዛማውን የጫት ቅጠል እየቆረጡ ወደ አፍህ ሲከቱ፣ እግሮችህ ደግሞ መስጊድና የተፈቀዱ ቦታዎች ከመሄድ ይልቅ ወደ ጫት ገበያና ወደ ከንቱ ጨዋታ ቦታዎች በመሄዳቸው ይመሰክሩብሃል። ​ጫት የምትቅም ሰው ሆይ አልደከመህም? ጫትን በብዙ ሺህ የምትገዛ ሰው ሆይ አልደከመህም? ከእንቅልፍህ የምትነቃበት ጊዜ አልደረሰም? ​🌹 አንተ የአላህ ባሪያ ነህ፤ ታዲያ ለምን በጫት ራስህን ታሰቃያለህ? ስለዚህ ጫትን ሙሉ በሙሉ መተው፣ መራቅና ወደ አላህ ተውበት ማድረግ ያስፈልጋል። ​ከአርሽ በላይ ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦ "አላህንም የሚፈራ ሰው ለእሱ መውጫን ያደርግለታል፤ ካላሰበውም በኩል ይሰጠዋል" [አል-ጠላቅ፡ 2-3]፤ እንዲሁም እንዲህ ይላል፦ "አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ለእሱ እፎይታን ያደርግለታል" [አል-ጠላቅ፡ 4] ​ምክርንና ማስታወስን ብንተው በእኛ ውስጥ ምንም መልካም ነገር የለም፤ ፈተናዎችና ጥርጣሬዎች በበዙበት በዚህ ዘመን ይህ በእኛ ላይ ግዴታ ነው። ​አላህ ከሚወደው ነገር ጋር ይግጠመን የመጨረሻ ጥሪያችንም ምስጋና ለአለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን። ​

የተፈጥሮ ሱናዎች 1. መገረዝ፦ ለወንዶች ዋጂብ ሲሆን ለሴቶች ግን ሙስተሐብ የሆነ ተግባር ነው። 2. ኢስቲሕዳድ፦ በወንድም ሆነ በሴት የሽንት መሽኒያ አካባቢ የሚበቅልን ፀጉር መላጨት። 3. የብብትን ፀጉር መንጨት፦ መንጨት ያልቻለ መላጨት ይችላል። 4. ጥፍርን መቁረጥ፦ ጥፍርን ማሳደግ ጎጂ እና ኋላቀር መጥፎ ባህሪ ነው። ከአውሬዎች እና ከካፊር ሴቶች ጋርም መመሳሰል ነው። 5. ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር፦ ከወንድ የላይኛው ከንፈር ላይ የሚበቅል ፀጉር ነው። ይህን ማሳጠር። እነዚህ አምስቶቹ በየሳምንቱ መሆን አለባቸው። ከአርባ ቀን በላይ መቆየት የለበትም። 6. የመገጣጠሚያ አካላትን መፈተግ፦ የጀሮ መታጠፊያዎች እና አፍንጫ አካባቢ። የእጅ እና የእግር መገጣጠሚያ አካላት። 7. ፂምን ማሳደግ፦ ሙሉ በሙሉ መላጫት ከባድ ወንጀል ነው። 8. የራስ ፀጉርን መንከባከብ፦ የሚያሳድገው ከሆነ ቅባት መቀባት እና በየሁለት ቀኑ ማበጠር። አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ግማሹን ተላጭቶ ግማሹን መተው ክልክል ነው። የአይሁዶች እና የሌሎች ካፊሮች ስራ ስለሆነ በዚህ ከመመሳሰል መጠንቀቅ ይገባል። 9. ኩል መክኳል፦ አይንን ያጠራል። ፀጉርን ያበቅላል። 10. የፀጉር ሽበትን አለመንቀል፦ ፂም ላይም ሆነ እራስ ፀጉር ላይ ሴት ላይም ሆነ ወንድ ላይ አይነቀልም። ሽበት የሙስሊም ኑር ነው። ደረጃን ከፍ ያደርጋል። ወንጀልን ያስሰርዛል። 11. ሽበትን ማቅለም፦ በሒናእ፣ በቀይ ወይም በቢጫ ቀለም ማቅለም። ለሴት ልጅ ሒናእን ለእጇ እና ለእግሯ መጠቀም ትችላለች። 12. ሽቶ መጠቀም፦ ሚስክም ሆነ ሌላ ነፍስን የሚያስደስት፣ ልብን የሚያረካ፣ መንፈስን የሚያድስ፣ አካልን የሚያበረታ ሽቶ መጠቀም ጥሩ ነው። ለሴት ልጅ ባዳ ወንዶች ባሉበት አካባቢ ተቀብቶ ማለፍ የተከለከለ ነው። 13. ሲዋክ መጠቀም፦ አፍን ያፀዳል። አላህን ያስወድዳል። ሲዋክ መጠቀም በሚከተሉዋቸው ሁኔታዎች ላይ ይበልጥ ይወደዳሉ፦ 1. ለሶላት ሲቆሙ 2. ውዱእ ሲያደርጉ 3. ከእንቅልፍ ሲነቁ 4. ከቤት ሲገቡ 5. ቁርአን ሲቀሩ 6. የጁሙዐ ቀን

የሸሪአ ትምህርት ለምትማሩ ተማሪዎች 1. የምንቀራውን ኪታብ ቃላት ልቅም አድርጎ መያዝ። ከኪታቡ ውስጥ የማናውቀው ቃል ላይኖር። 2. የኪታቡ መልእክት ላይ ትኩረት ማድረግ። መልእክቱን በትክክል መረዳት። ቃላት ለቀማ #ብቻ እንዳይሆን። 3. ማስረጃ ሲጠቀስ ከርእሱ ጋር ያላቸውን ተዛምዶ መለየት። مَحَلَّ الشَّاهِد እና وَجْهُ الاِستِدلال 4. ከደርስ በፊት እና ከደርስ በኋላ ሙራጀዓ ማድረግ። ከጓደኛ ጋር ወይም ለብቻ ሁኖ። • ባጭሩ = የተማርነውን ኪታብ ለሌሎች ማስተላለፍ በሚያስችል አቅም መያዝ ያሰፈልጋል። ~ ከኢብኑ ሙነወር ደርሶች ላይ የተወሰደ።

ለሕፃናት ልጅ ቢሆን እንኳ ቃል ገብቶ አለመፈጸም ትልቅ ውሸት ነው። ​📚 የነቢዩ (ﷺ) ሐዲሥ ​ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተወራው የዓላህ መልእክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡
​«ለሕፃን ልጅ "ና ይህንን እንካ" ብሎ ከዚያ ሳይሰጠው የቀረ ሰው እርሷ (ያቺ ንግግር) ውሸት ሆና ትጻፍበታለች።»
​📚 ምንጭ፡ አሕመድ የዘገቡት፤ አልባኒ በ«ሶሒሕ አት-ተርጊብ» (2942) ላይ ሶሒሕ ብለውታል። ​📝​ይህ ሐዲሥ የሚያስተላልፋቸው ዋና ዋና ትምህርቶች ​የመልካም ሥነ-ምግባር ጥሪ፡ እስልምና ከመጥፎ ባህሪያት እንድንርቅና በመልካም ሥነ-ምግባር እንድንጌጥ ያዛል። ከምእመናን መካከል እምነቱ ሙሉ የሚሆነው መልካም ሥነ-ምግባር ያለው ሰው ነው። ​የውሸት አደገኛነት፡ መጥፎ ባህሪያት ደረጃ ቢኖራቸውም ውሸት ግን ከባህሪያት ሁሉ እጅግ የከፋው ነው። ውሸት ወደ ወንጀልና አመጸኝነት አመጸኝነት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል። ​በቀልድም ቢሆን ውሸት አይፈቀድም፡ ውሸት በቁም ነገርም ሆነ በቀልድ መዋሸት በፍጹም አይቻልም። ​ከሕፃናት ጋር በሚኖር ግንኙነት፡ ለምሳሌ ያህል አንዲት እናት እጇን ጨብጣ ለልጇ "ና ልስጥህ" ብላ ብትጠራውና እጇ ባዶ ከሆነ ይህ ውሸት ተብሎ ይመዘገብባታል። ለሕፃናት ቃል ገብቶ አለመፈጸም የውሸት አንዱ አካል ነው። ​🌴 የዓብደላህ ኢብን መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ንግግር ​ዓብደላህ ኢብን መስዑድ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ብለዋል፡
​«ውሸት በቁም ነገርም ሆነ በቀልድ አይበጅም (አይፈቀድም) እንዲሁም ማንኛውም ሰው ለልጁ አንድን ነገር ቃል ገብቶለት ከዚያ ሳይፈጽምለት መቅረት የለበትም።»
​📚 ምንጭ፡ አልባኒ በ«አል-አደብ አል-ሙፍረድ» (299) ላይ ሶሒሕ ብለውታል።

❤❤❤የትዳር ሕይወት ውብ፣ የማረፊያ፣ የመዋደድና የርህራሄ ምንጭ እንዲሁም በዱንያም በዲንም በረከት ያለው ነው። 👉​ነገር ግን በሴቷ በኩል የሚከተሉት ነገሮች ያበላሹታል፦ ١. እልህና ክርክር ٢. ኩራትና ትዕቢት ٣. ማህበራዊ ሚዲያ (የመገናኛ ዘዴዎች) ٤. ጭቅጭቅና የባህሪ መለዋወጥ (ሙድኝነት) ٦. አፈራራሽና አበላሽ አካባቢ (እናት፣ የቅርብ ዘመዶች፣ ጓደኞች) ٦. ትክክለኛ መንገድ የማያሳዩ ቤተሰቦች ٧. የሴቷ እፍረት ማጣትና ዓይኗን አለመጠበቅ ٨. ውሸት 👉​በወንዱ በኩል ደግሞ፦ ١. ስግብግብነት (ብስጭት/ቁጣኝነት) ٢. እርም (ህገ-ወጥ) የሆኑ ግንኙነቶች ٣. የብልግና ምስሎችንና ቪዲዮዎችን ማየት ٤. ድዩስነት (በቤተሰቡ ላይ ቅናት ማጣት/ቀናት አለመሆን) ٥. የትዳር ግንኙነትን ችላ ማለት ٦. ሚስትንና ልጆችን አለመከታተል ٧. ውሸት ٨. ሀጢአትን በግልጽ መስራት ​አላህን በባለቤቱ ላይ የፈራ እሷም አላህን በባለቤቷ ላይ የፈራች ጥቂት ችግሮችና ቀጣናዎች ቢገጥሟቸውም እንኳን ደስተኛና ሰላማዊ ህይወትን ይኖራሉ።

​⭕ የጫት ሥነ-ልቦናዊ ጉዳቶች ​ ​1. የሱስ በሽታ (Dependency Syndrome) ​ሱስ ማለት አንድን ነገር አካላዊ፣ ሥነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ጉዳት እንደሚያስከትል እያወቁ አዘውትሮና በቋሚነት መጠቀም ነው። የሱስ ምልክቶች የሚከተሉት ናቸው፡ ​ነገሩን በከፍተኛ መጠን፣ በቋሚነትና ያለማቋረጥ መጠቀም። ​የመጠቀም ከፍተኛ ፍላጎትና ማቆም ወይም መተው አለመቻል። ​ሰውነት ከጫት ተጽዕኖዎች ጋር መላመድ (ተፅዕኖው እንዲሰማ መጠን መጨመር)። ​ሲያቆሙ ወይም መጠኑን ሲቀንሱ የሱሱ መተው (Withdrawal) ምልክቶች መታየት። ​ጫቱን ለማግኘት፣ ለመቃም ወይም ከደስታው ስሜት በኋላ ለማገገም ብዙ ጊዜ ማባከን። ​አጠቃቀሙ በቤተሰብ፣ በማህበራዊና በሥራ ሀላፊነት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደር። ​አካላዊና ሥነ-ልቦናዊ ችግሮችን እንደሚያስከትል ወይም እንደሚያባብስ እያወቁ መጠቀምን መቀጠል። ​ጫት በሚቃምበት ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች፡ ​የደስታና የዕረፍት ስሜት። ​የንቃት መጨመር፣ የድካምና የእስትንፋስ ቁርጠት አለመሰማት። ​የማተኮርና የመጠበቅ ብቃት መጨመር። ​የልብ ምት፣ የደም ግፊትና የሰውነት ሙቀት መጨመር። ​ስሜት መነቃቃት፣ ድፍረት ማግኘትና የመናገር ፍላጎት መጨመር። ​የእንቅልፍ፣ የምግብና የወሲብ ፍላጎት መዛባት። ​በአንዳንድ ሁኔታዎች፡ ​እጅግ በጣም ብዙ መናገር፣ በፍጥነት መበሳጨትና ስሜታዊ መሆን። ​የደም ግፊት፣ የልብ ምትና የሰውነት ሙቀት ከፍተኛ ደረጃ መድረስ። ​በአስተሳሰብና በባህሪ ላይ ለውጥ መምጣት፣ የሌሉ ነገሮችን ማየትና መስማት (Hallucinations)። ​በሰውነት ላይ በተለይም በመንጋጋ አካባቢ ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ እንቅስቃሴዎች መከሰት። ​የማቆም (የማቋረጥ) ምልክቶች፡ ​እንደ አጠቃቀም ጊዜውና መጠኑ ከሰው ሰው ይለያያሉ። ​አብዛኛውን ጊዜ ሥነ-ልቦናዊ ስሜቶች ሲሆኑ ከአካላዊ ምልክቶች ጋር ከ1 እስከ 2 ሳምንታት ይቆያሉ። ​የድብርትና የጭንቀት ስሜት። ​ከፍተኛ ድካም (መዛል) እና ሥራ የመስራት ብቃት ማጣት። ​የምግብ ፍላጎት መጨመር። ​እንቅልፍ መብዛትና አስፈሪ ሕልሞችን (ቅዥት) ማየት። ​የማተኮርና የመረዳት አቅም መቀነስ። ​ጫት የመቃም ከፍተኛ ፍላጎት። ​2. የጭንቀት በሽታዎች (Anxiety Disorders) ​ጫት መቃም የኖራድሬናሊን (Noradrenaline) ሆርሞን ምርትን በመጨመር የሲምፓቴቲክ አእምሮ ሥርዓትን ያነቃቃል። ​ይህም በፍርሃት፣ ባለመረጋጋት፣ በልብ ምት መጨመር፣ በሙቀት፣ በሰውነት መንቀጥቀጥ፣ በእስትንፋስ መፍጠን፣ እጅና እግር ቅዝቃዜና መደንዘዝ ያሉ የጭንቀት ምልክቶችን ያስከትላል። ​አስቀድሞ የጭንቀት ህመም ባላቸው ሰዎች ላይ ምልክቶቹን ያባብሳል፣ የጭንቀት መድኃኒቶችን ውጤታማነት ይቀንሳል፣ እንዲሁም ድንገተኛ የፍርሃት ጥቃቶችን (Panic attacks) ወይም የእስረኛ-አእምሮ (OCD) ህመምን ሊያበሳጭ ይችላል። ​3. የድብርት በሽታ (Depression) ​ጫት ሲያቆሙ፣ መጠኑን ሲቀንሱ ወይም መቃም በሚገባቸው ሰዓት ሲያረፍዱ ይከሰታል። ​የድብርትና የጭንቀት ስሜት። ​በሥራ ላይ ያለውን ፍላጎት ማጣት ወይም በሕይወት አለመደሰት። ​የእንቅልፍ፣ የምግብና የወሲብ ፍላጎት መዛባት። ​የድካምና የመዛል ስሜት። ​የተስፋ መቁረጥ ስሜት እና አንዳንድ ጊዜ ስለ ሞት ማሰብ። ​እነዚህ ምልክቶች ለአጭር ጊዜ ሊቆዩ ወይም ለበርካታ ወራት ሊዘልቁ ይችላሉ። ​4. የባይፖላር ህመም - ከመጠን ያለፈ ደስታና ብስጭት (Bipolar Disorder) ​ከተለመደው በላይ የደስታና የሐሴት ስሜት ወይም በፍጥነት መበሳጨትና መቆጣት። ​ከመጠን ያለፈ እንቅስቃሴና የእንቅልፍ ፍላጎት መቀነስ። ​የንግግር ብዛትና ፍጥነት፣ አንዳንድ ጊዜ ሀሳብ ከሀሳብ በመዝለሉ ምክንያት የንግግር አለመያያዝ። ​ስለራስ ከፍተኛ ግምት መስጠት (ልዩና ልዩ ተሰጥኦ እንዳለው ማሰብ)። ​ችኩልነት፣ ድርጊቶችን መቆጣጠር አለመቻልና አላስፈላጊ ባህሪያትን ማሳየት። ​5. የስኪዞፍሬኒያ / አእምሮ መታወክ ህመም (Schizophrenia) ​በአእምሮ ውስጥ የዶፓሚን (Dopamine) መጠን መጨመር በአስተሳሰብ፣ በእስትንፋስና በባህሪ ላይ መዛባትን ያመጣል። ​በሌሎች ሰዎች በተለይም በቅርብ ሰዎች ላይ መጠራጠር (ሰዎች ስለ እሱ እንደሚያወሩ፣ እንደሚከታተሉት ማሰብ፣ አላስፈላጊ ቅናት ወዘተ)። ​በስሜት ህዋሳት ላይ ለውጥ መምጣት (አጠገቡ የሌሉ ሰዎች ድምፅ መስማት፣ አስፈሪ ምስሎችን ማየት ወዘተ)። ​ጠበኛ ወይም አላስፈላጊ ባህሪን ወይም እንቅስቃሴ አልባ መሆንን ሊያስከትል ይችላል። ​6. የእንቅልፍ መዛባት (Sleep Disorders) ​የእንቅልፍ ማነስ፣ እንቅልፍ ለመተኛት መቸገር ወይም በእንቅልፍ ወቅት ተደጋግሞ መንቃት ይከሰታል፤ ይህም ጠዋት ላይ ድካምና መዛልን ያመጣል። ​ጫት በሚተውበት ጊዜ ደግሞ እንቅልፍና ድካም ይበዛል፣ አስፈሪ ቅዥቶችም ያጋጥማሉ። ​7. የወሲብ መዛባት (Sexual Disorders) ​የወሲብ ፍላጎት መዛባት። ​የስሜት ህዋሳት ደካማ መሆንና በፍጥነት ፈሳሽ ማፍሰስ (Erectile dysfunction and premature ejaculation)። ​በብልት አካባቢ መቆጣትና የዘር ፈሳሽ ያለ ፍላጎት መውጣት። ​በወሲብ ሆርሞኖች መጠን ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደር። ​8. ሌሎች ተጽዕኖዎች ​ታካሚው የሚወስዳቸውን ሌሎች መድኃኒቶች አሠራር በመጋፋት የህክምና ውጤታማነታቸውን ይቀንሳል። ​የበሽታውን ማገገም ያዘገያል፣ ይህም የሕክምና ጊዜን ያራዝማል። ​ህመሙ ካገገመ በኋላ ተመልሶ እንዲያሸራተት (Relapse) ምክንያት ይሆናል። ​ጫትን ከሌሎች አነቃቂ ነገሮች ጋር አብሮ መጠቀም የነገሮቹን ጉዳትና በሰውነት ላይ ያላቸውን ተጽዕኖ በጥፍ ያባብሰዋል። ​* 👉 አንተ ሙስሊም ወንድሜ ሆይ!!! እራስህን ከዚህ አደገኛ ዕጽ ጠብቅ!!!! ወንድማችሁ ሙሃመድ ሰኢድ (የማህበራዊ እና ስነ ልቦና ዲጋፍ ስፔሻሊስት ) ራያ ቆቦ

አንዳንዱ ሰው እንደት መዠለጥ እንዳለበት ያውቃል። ለማንኛውም የሁሉም ሴቶች እድሜ ከ 25 አመት በታች ነው እያሉህ ነው። ዝም ብለህ አግባ መስፈርቴ እድሜዋ ከ 25 በታች ነው መሆን ያለበት አትበል
አንዳንዱ ሰው እንደት መዠለጥ እንዳለበት ያውቃል። ለማንኛውም የሁሉም ሴቶች እድሜ ከ 25 አመት በታች ነው እያሉህ ነው። ዝም ብለህ አግባ መስፈርቴ እድሜዋ ከ 25 በታች ነው መሆን ያለበት አትበል ። ምክንያቱም ያላገቡት በሙሉ እድሜያቸው ከ 25 በታች ነው

የጦርነት ዝግጅቱ እየተጧጧፈ እንደሆነ የሚገልፁ ዘገባዎችን እያየን ነው። ብዙዎቹን ፈተናዎች ማስቀረት ባይቻልም ለሁሉም ሁኔታ እራስን ማዘጋጀት አይከፋም። በተለይም ጦርነቱ ሊደርስባቸው ይችላሉ ተብለው በቀዳሚነት በሚገመቱ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች የባንክ አገልግሎት፣ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ኢንተርኔት፣ መብራት፣ ... ቢቋረጡ የሚከሰተውን ሁሉ ቀድሞ ማሰብ ችግሩን ባያስቀር እንኳ ከፈተናው ጋር ህይወትን እንዴት መግፋት እንደሚቻል አእምሮን ማዘጋጀቱ አይከፋም። በተረፈ ከባለፈው ጦርነት ብዙ ነገር መማር እንደሚቻል ማሰብ ጥሩ ነው። ተለዋዋጭ ነገሮች ቢገጥሙ እንኳ ኋላ የቂመኞች ሰለባ መሆን እንዳይመጣ አጉል መንቀዥቀዥ አያስፈልግም። አላህ ክፉውን ይያዝልን። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ግን አንድ ምክር በግሌ ልመክራችሁ ወደድኩ በየ ሰአቱ ልዩነት ቡናን ከምትጋቱ ለውዝ ብትጠቀሙ ብዙ ጥቅም ታገኙበታላችሁ!!!በተለይ ወጣቶች ቡናን ባትጠቀሙ ጥሩ ነው። በተለይ ደግሞ ከቤት ውጭ የሚሰራ ቡና ከብዙ ባእድ ነገራቶች ጋር ተዘጋጅቶ ነው የሚሰራው፦ 👉ትንባሆ(አንጋዳ) 👉የጫት ቅጠልና ግንድ 👉ሌሎች አነቃቂ እጾችም አብረው ይጨመራሉ። ነገር ግን በተቃራኒው የዘውዝን(ኦቾሎኒ) ሻይን ብንጠቀም ብዙ ጥቅሞችን እናገኛለን። ከእነዚህም ውስጥ በከፊል፦ ​❶. ለወሲባዊ ጤንነት እና ብቃት ➥​የደም ፍሰትን ይጨምራል፦ በውስጡ በሚገኘው ኤል-አርጂኒን (L-Arginine) አሚኖ አሲድ በሚባል አማካኝነት በሰውነት ውስጥ የናይትሪክ ኦክሳይድ ምርትን በመጨመር ወደ ብልት አካባቢ የሚሄደውን የደም ፍሰት ያሳድጋል። ➥​ሆርሞንን ያመጣጥናል፦ እንደ ዚንክ እና ማግኒዚየም ያሉ ማዕድናት የወንዶችን ዋና የፆታ ሆርሞን (ቴስቶስቴሮን) ማመጣጠን ላይ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። ➥​ጉልበትና ጽናት ይሰጣል፦ በከፍተኛ ፕሮቲንና በጥሩ ስብ የበለፀገ በመሆኑ ለስጋዊ ግንኙነት ዘላቂ ጉልበት ይሰጣል። ➥​ስነ-ልቦናዊ ጭንቀትን ይቀንሳል፦ በውስጡ ባለው ትሪፕቶፋን በሚባል አእምሮን በማረጋጋት ለስንፈተ-ወሲብ ምክንያት የሚሆነውን ጭንቀት ይቀንሳል፤ አንቲኦክሲዳንቶች ደግሞ የደም ስሮችን ጤንነት ይጠብቃሉ። ​❷. ለጡንቻ ግንባታ እና ለአካላዊ ብርታት ➥​የጡንቻ እድገት፦ ከፍተኛ የዕፅዋት ፕሮቲን (Plant-based Protein) ስላለው የሰውነት ሴሎችን ለመገንባት፣ የጎዱ ቲሹዎችን ለማደስ እና የጡንቻን ጥንካሬ ለመጠበቅ ይረዳል። ➥​ፈጣን ኃይል፦ በካሎሪና በጥሩ ስብ የበለፀገ በመሆኑ በተለይ ጠዋት ሲጠጣ ወይም ከስራ ድካም በኋላ ፈጣን ጉልበት (Energy) ይሰጣል። ​➌. ለልብ ጤንነት ➥​በውስጡ ያልበለፀጉ በጥሩ ጎን የሚነሱ ቅባቶችን (Unsaturated Fats) እና ኦሜጋ-6ን ይይዛል። እነዚህም በደም ውስጥ የሚገኘውን መጥፎ ኮሌስትሮል (LDL) በመቀነስ የልብ ሕመም ስጋትን ይቀንሳሉ። ​❹. የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል ➥​በውስጡ ባለው ከፍተኛ የፋይበር (Fiber) መጠን የምግብ መፈጨት ሥርዓትን ያሳልጣል፣ የሆድ ድርቀትን ለመከላከል ይረዳል። ​❺. የአንጎል እና የነርቭ ሥርዓትን ያጠናክራል ➥​ቫይታሚን ኢ (Vitamin E) እና ናያሲንን (Vitamin B3) በከፍተኛ መጠን ይይዛል። እነዚህ ንጥረ ነገሮች የአንጎልን ሥራ የሚያነቃቁ፣ የትኩረት ብቃትን የሚያሳድጉ እና የማስታወስ ችሎታን የሚያጠናክሩ ናቸው። ​❻. የሰውነት በሽታ መከላከል አቅምን ያሳድጋል ​በውስጡ የሚገኙት አንቲኦክሲዳንቶች እና እንደ ዚንክ፣ ማግኒዚየም ያሉ ማዕድናት ሰውነትን ከተለያዩ ኢንፌክሽኖችና በሽታዎች ይከላከላሉ። ​❼. የደም ስኳር መጠንን ለመቆጣጠር ➥​ዝቅተኛ Glycemic Index ስላለው እና በጥሩ ስብና ፕሮቲን የበለፀገ በመሆኑ በደም ውስጥ ያለው የስኳር መጠን ድንገት ከፍ እንዳይል ያደርጋል (ያለ ብዙ ስኳር ከተዘጋጀ)። ​❽. ለቆዳ እና ለፀጉር ጤንነት ➥​ቫይታሚን ኢ፦ ቆዳ እንዲያንጸባርቅ፣ ከፀሐይ ጨረር ጉዳት እንዲጠበቅ እና የቆዳ የመለጠጥ አቅም እንዳይቀንስ ይረዳል። ➥​ባዮቲን (Biotin)፦ የፀጉርን ጥንካሬ ይጨምራል፣ መሰባበርን ይከላከላል። ​❾. የአጥንትና የጥርስ ጥንካሬ ➥​እንደ ፎስፈረስ፣ ማግኒዚየም እና ካልሲየም ያሉ ማዕድናት የአጥንትና የጥርስን ጥንካሬ ለመጠበቅ እና የመሰበር አደጋን ለመቀነስ አስፈላጊ ናቸው። ​❿. ጭንቀትን ለማስታገስ እና ደስተኛ ስሜት ለመፍጠር ➥​በውስጡ ያለው ትሪፕቶፋን (Tryptophan) የሚባለው በሰውነታችን ውስጥ ወደ ሰሮቶኒን (Serotonin / የደስታ ሆርሞን) ስለሚቀየር አእምሮ እንዲረጋጋ፣ ጭንቀት እንዲቀንስ እና ጥሩ እንቅልፍ እንድናገኝ ይረዳል። ​⓫. የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ➥​በውስጡ ያለው ፖታሺየም (Potassium) በሰውነት ውስጥ ያለውን የሶዲየም (የጨው) መጠን በማመጣጠን የደም ሥሮች እንዳይጠቡ እና የደም ግፊት እንዲስተካከል ያደርጋል። ​⓬. የሐሞት ጠጠር (Gallstones) ስጋትን ይቀንሳል ➥​የለውዝ ምርቶችን አዘውትሮ መውሰድ በሐሞት ከረጢት ውስጥ የሚፈጠርን የኮሌስትሮል ጠጠር (Cholesterol Gallstones) የመፈጠር እድልን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሳል። ​⓭. የሕዋሳት እብጠትን (Inflammation) ይቀንሳል ➥​በውስጡ ባሉት ፖሊፊኖል (Polyphenols) እና አንቲኦክሲዳንቶች አማካኝነት በሰውነት ውስጥ የሚፈጠሩ የተለያዩ የሕዋሳት እብጠቶችን የመከላከል አቅም አለው። ​⓮. የደም ማነስን (Anemia) ለመከላከል ➥​ብረት (Iron) እና ፎሊክ አሲድ (Folate) የያዘ በመሆኑ ቀይ የደም ሴሎች (Red Blood Cells) ምርትን ያፋጥናል፤ ይህም የደም ማነስ ችግር እንዳይከሰት ይረዳል። ​⓯. ለነፍሰ ጡር እናቶች እና ለፅንስ እድገት ➥​በፅንሱ የአንጎል እና የአከርካሪ አጥንት እድገት (Neural Tube Defects) ላይ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመከላከል ወሳኝ የሆነውን ፎሊክ አሲድን ይይዛል። ​⓰. የሰውነት ክብደትን ለመቆጣጠር ➥​በውስጡ ያለው ከፍተኛ የፕሮቲን እና የፋይበር መጠን የመርካት/የመጥገብ ስሜት በመፍጠር የረሀብ ስሜትን ይቀንሳል፤ ይህም አላስፈላጊ ምግቦችን በመቀነስ ክብደት ለመቀነስ ይረዳል። ​⓱. የሆርሞን መዛባትን ያመጣጥናል ➥​ዚንክ እና ማግኒዚየም በሰውነት ውስጥ የሆርሞኖች ምርት እና ስርጭት የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳሉ። ​⓲. የእርጅና ምልክቶችን ይከላከላል ➥​ሬስቬራትሮል (Resveratrol) የተባለ ኃይለኛ አንቲኦክሲዳንት ስላለው የሕዋሳትን እድሜ በማራዘም እና የቆዳ መጨማደድን በመቀነስ የእርጅና ሂደትን ያዘገያል። ​⓳. ከስፖርት በኋላ ለሰውነት ማገገሚያ (Post-Workout Recovery) ➥​የፕሮቲን፣ ካርቦሃይድሬት እና ኤሌክትሮላይቶች ጥምረት ከባድ ስራ ወይም ስፖርት ከሰራን በኋላ የተጎዱ ጡንቻዎችን በፍጥነት ለማደስ እጅግ ተስማሚ ነው። ​⓴. የታይሮይድ (Thyroid) እጢን ሥራ ያመጣጥናል ➥​ሴሊኒየም (Selenium) እና ኮፐር (Copper) የታይሮይድ እጢ በትክክል ሆርሞኖችን እንዲያመነጭ እና የሰውነት ህዋሳት ምግብን ወደ ጉልበት የመቀየር ሂደታቸውን (Metabolism) እንዲያፋጥን ይረዳል። ​❷❶. የዓይን ጤንነትን መጠበቅ ➥​ቫይታሚን ኢ እና ዚንክ የዓይን ብርሃን እንዳይቀንስ እና በእድሜ መገፋት ምክንያት የሚመጡ የዓይን ሕመሞችን (እንደ Macular Degeneration ያሉ) ለመከላከል ይረዳሉ። ​❷❷. የጉበትን ጤንነት ይጠብቃል (Fatty Liver Protection) ➥​ከፍተኛ የቫይታሚን ኢ እና የፀረ-ኦክሲዳንት መጠን በጉበት ውስጥ አላስፈላጊ ስብ እንዳይከማች በማድረግ የጉበትን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል። ​NB: ➾ እነዚህን የጤና ጥቅሞች በተሻለ ሁኔታ ለማግኘት የለውዝ ሻይን ስናዘጋጅ የስኳር መጠን ቀንሰን (ወይም በትንሽ ማር ተክተን) እና እንደ ቀረፋ ወይም ቅርንፉድ ያሉ ቅመሞችን ጨምረን ብንጠጣው ይመረጣል። ➾​ጥንቃቄ፦ የለውዝ ሻይ ከፍተኛ የካሎሪ መጠን ስላለው እና ለውዝ #ለአንዳንድ ሰዎች የአለርጂ (Allergy) ስሜት ሊፈጥር ስለሚችል በልክ መውሰድ ተስማሚ ነው።

ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰ
ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰበር፣ የአዛውንቶች ያለ ጧሪ ቀባሪ መቅረት፣ የሃገር መቆርቆዝ የማያስደነግጠው ልብ ከጠላት በላይ ጨካኝ ነው። ሰው ሌሎች ላይ ከደረሰው፣ ከጎረቤቱ ይማራል። እሱ ቢቀር እንዴት በራስ ላይ ከደረሰው መማር ያቅታል?! ለማንኛውም ወጣት ሆይ! ለራስህ እወቅበት። በስምህ የሚምለው ሁሉ ተቆርቁሮልህ እንዳይመስልህ። ጀግና ጀግና የሚልህ ጀግና ስለሆንክ አይደለም። እየሸነገለህ ነው። ራሱንም ቤተሰቡንም ከእሳቱ አርቆ ነው አንተን የሚማግደው። ካንተ ሞት በኋላ ልጅህን፣ እናትህን ዞሮ አያይም። ግፋ ቢል ነገ ካንተ ሞት በኋላ የሰማእታት ሀውልት ብሎ የድንጋይ ክምር ቢያቆምልህ ነው። ይሄ ላንተም ለቤተሰብህም የሚጠቅመው ነገር የለም። ህዝብ ማደንዘዣ፣ ሌላ እልቂት ማቀጣጠያ እንጂ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ኡስታዝ ሙሃመድ አህመድ ሙነወር (ኢብኑ ሙነወር) አንገብጋቢ እና ወቅታዊ አጀንዳ የተዳሠሠበት በወሎ ኮምቦልቻ

ዘመኸሸሪ ማነው??? እምነቱስ??