KebronHill Microfinance Official Telegram Channel
Открыть в Telegram
Больше
Страна не указанаКатегория не указана
369
Подписчики
Нет данных24 часа
Нет данных7 дней
+630 дней
Архив постов
መልካም የሥራ ሳምንት!
👉በፍጥነት የሚስተናገዱ አጭር እና አስቸኳይ ጊዜ ብድር አማራጮችን እንዲሁም አነስተኛ እና መካከለኛ ብድሮችን በተቀላጠፈ ሁኔታ ያገኛሉ!
👉ብልህ ከሆኑ ቀላልና ትርፋማ የሚያደርግዎ ኢንቨስትመንት ከእኛ ጋር ይገኛል!
ይህም ጊዜዎን የማይሻማ እና የኪሳራ ስጋት የሌለበት : የዉስጥ ሆነ የዉጪ ተፅዕኖ የማይጎዳው ምቹ ኢንቨስትመንት ነው::
የከብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ #የጊዜ #ገደብ #ተቀማጭ ቁጠባ.
ከ5,000 ጀምሮ ስቆጥቡ እስከ 20% እና ከዛ በላይ የወለድ ትርፍ የሚያስገኝ ምርጥ ዕድል ነው ይጠቀሙ
ለ6, 12, 18, 24 እና 36 ወር እንደፍላጎትዎ እኛ ጋር የጊዜ ገደብ ተቀማጭ ቁጠባ ስቆጥቡ እጅግ የተሻለ ትርፍ ያገኛሉ::
እንደየገንዘቡና እና እንደቆይታ ጊዜ መጠን 20 ⁺ ሲሆን ለተጨማሪ ድርድር ተቋሙ ዝግጁ ነው::
ብራችሁን በተሻለ ዋጋ እንገዛዋለን!
ኬብርንሂል በአብሮነት ወደ ልህቀት!
ለበለጠ መረጃ:-
የስልክ ቁጥር :-
+251113693794 አየርጤና ቅርንጫፍ
+25111 557 1234 ሜክስኮ ቅርንጫፍ
+251115300195 ካዛንቺስ ቅርንጫፍ
+251222381216 አሰላ ቅርንጫፍ
+251226654543 ሮቤ ቅርንጫፍ
+25133 312 7446 ደሴ ቅርንጫፍ
+251981827772 ሳሪስ ቅርንጫፍ ይደዉሉ
ጠቃሚ ሊንኮች :
👉KebronHill Telegram :-
https://t.me/+quucyPHlQFhlZGFk
https://t.me/KHMFI_2025
👉Facebook:-
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082971387221
👉Website:-
www.kebronmfi.com
👉Whatsaap
https://chat.whatsapp.com/LRBLZ53ylVeLI2Jq1yjNGN?mode=ems_copy_t
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@..khmfi?_r=1&_t=ZM-911zunkbQa0
👉Linkden
https://www.linkedin.com/company/kebronhill-microfinance-institution-share-company/
Everybody Join our Social media links for updates and new informations
#ማሳሰቢያ!
ውድ ደንበኛችን
ያስተውሉ! ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አጭበርባሪዎች የቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ፣ኢሜይል አድራሻ … ወዘተ በመጥለፍ እና ከቅርብ ሰው እንደተላከ በማስመሰል“ችግር ላይ ነኝ”፣ “አስቸኳይ ክፍያ አለብኝ” በማለት ገንዘብ እንዲላክላቸው የሐሰት መልዕክቶችን እየላኩ ይገኛሉ።
በመሆኑም ብሔራዊ ባንክም የማህበረሰቡን ደህንነት ለመጠበቅ በዚህ ጉዳይ ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ የሚገኝ ሲሆን እንዲህ አይነት የማጭበርበር መልዕክቶች ሲደርሱዎት፣ በቅድሚያ መልዕክቱን ልኮታል ወደተባለው ሰው በቀጥታ በመደወል እውነተኛ መሆኑን ሳያረጋግጡ በፍጹም ገንዘብ እንዳይልኩ ተቋማችን ኬብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ አ.ማ ያሳስባል።
ጥንቃቄ በማድረግ ራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ!
ኬብሮንሂል በአብሮነት ወደ ልህቀት!
ለተከበራችሁ የኬብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች፣ ደንበኞች እና ሰራተኞች በሙሉ፤ እንኳን ለጌታችን እና ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ይህ የትንሳኤ በዓል በአማርኛ ፋሲካ ፣ በዕብራይስጥ Pesach፣ በግሪክ Pascha እንዲሁም በእንግሊዝኛ Passover የሚል ትርጉም ያለው ሲሆን፣ የአሮጌ ነገሮች ሁሉ መጨረሻ እና የአዲስ ነገር ጀማሬን ያሳየናል። በዚህም ውስጥ የትላንት ድክመቶች፣ ውድቀቶችና ትውስታዎች ሁሉ ማለፋቸውን፣ አሮጌው ሁሉ ማለፉን፣ ሁሉ በጌታ በኢየሱስ የመስቀል ገድል አዲስ መሆኑን እንረዳለን።
ለተቋማችን ሰራተኞች ያለኝ መልእክት በክርስቶስ ኢየሱስ ሞት ውስጥ ራስን ስለሌሎች አሳልፎ መስጠትን፣ ፍጹም የሆነ መታዘዝን እንደ ምሳሌ በመውሰድከትናንት ይልቅ ዛሬ ዛሬም ላይ ቆመን አሁን በአገልጋይነት ስሜት በቅንነት በታማኝነትና በትጋት እንበርታ እያልኩ ዛሬም ይህንን የትንሳኤ በዓል ስናከብር፣ ትንሳኤው ከሞት በኋላ የመጣ ክብር ነውና፣ ለተቋማችን ዕድገትና ከፍታ የሚያስፈልገውን ሁሉ ለመክፈልና፣ የተቋሙን ባለቤቶች ባለ አክሲዮኖችን እንዲሁም ደንበኞቻችንን በፍጹም ፍቅርና መታዘዝ ለማገልገል ቁርጠኛ ትሆኑ ዘንድ አሳስባለሁ።
ክቡራን ደንበኞቻችን አያይዤም፣ እናንተን ለማገዝ ባለን ቁርጠኝነት አዳዲስ እና በናንተ ፍላጎት ላይ ያተኮሩ የብድር አገልግሎቶችን ይዘን መቅረባችንን እየገለጽኩ ፣ ለዚህም ማሳያ በዚህ ሳምንት የጀመርነውን የስድስት ወር የአስቸኳይ ጊዜ የብድር አገልግሎትን ሳበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው።። ይህንንም ፈጣን አገልግሎት ዋናውን መስሪያቤታችንን ጨምሮ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን በመቅረብ አገልግሎቱን ማግኘት እንደምትችሉ አሳውቃለሁ።
በድጋሚ በአሉ የሰላም የጤናና የስኬት ይሁንላችሁ።
አቶ ሸዋፈራው ደሳለኝ
የኬብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ አ.ማ የዲያሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ
ሚያዝያ 2018 ዓ.ም
ታላቅ የምስራች ለአስመጪዎች ላኪዎች :ለትራንዚት ጅርጅቶች እና ድንበር ተሻጋሪ ተሽከርካሪ ማህበራት እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!
#Short-term( #Emergency) #Loan Solution for our Logistics sector Clients!
ለሎጂስትክሱ አጭርና አስቸኳይ ጊዜ ብድር አማራጮችን እንደ መፍትሄን ይዘን መጥተናል::
👉ከዉጪ ሀገር ወደ ሀገር ዉስጥ ዕቃ #በማስገባት እና ወደ ዉጪ ሀገር #በመላክ ሂደት ላይ ከመነሻ ወደብ እስከ መጨረሻ መዳረሻ ቦታ ድረስ ባሉ ሂደቶች ላይ #ከሎጅስቲክስ እና #ጉምሩክ #ክሊራንስ ጋር ተያይዞ ደንበኞቻችንን ሊያጋጥሟቸው የሚችሏቸው ችግሮችን ታሳቢ ያደረገ መፍትሄ እነሆ!
👉ከወደብ ክሊራንስ ጋር ተያይዞ የወደብ #ዲሜሬጅ እና የተለያዩ #የቅጣት ወጪዎችን ክፍያ ለመሸፈን
👉 የዕቃ #ማጓጓዣ ወጪዎች ለመሸፈን
👉እቃዎች ወደ ጉምሩክ መዳረሻ ከደረሱ በኃላ በአየር መንገድ በካርጎ ከሆነ #በ10 ቀናት እንዲሁም በሌሎች ቅርንጫፎች ከሆነ ደግሞ #በ15 ቀናት የሚጠበቅባቸዉን #የጉምሩክ #ታክስ ከፍለው ክሊራንስ ሂደቱን ማጠናቀቅ እንዳለባቸው የተቀመጠውን አሰራርን በትክክል ፈፅመው እቃዎትን በሰላም ለማዉጣት የሚረዳ #ለጉምሩክ #ታክስ ክፊያ የሚሆኑ #አስቸኳይና #መጠነኛ ብድሮችን #በዝቅተኛ ወለድ በኬብሮንሂል ማይክሮ ፋይናንስ በኩል ተመቻችቶለዎታል ::
👉በድጋሚ እንኳን ደስ አለዎ እያልን ኬብርንሂል ማይክሮ ፋይናንስ በቀጣይም በሎጂስትክሱ ዘርፉ ያሉ ደንበኞቻችንን ሊያጋጥሟቸው የሚችሉ ወቅታዊ ችግሮችን በዘላቅነትና በትኩረት ለመፍታት ተግቶ ይሠራል::
#ማስታወሻ:- ከእኛ ጋር #ሲሰሩ:-
👉 ለዲመሬጅ ቅጣት : ለጉምሩክ መጋዘን ቆይታ ጊዜ ቅጣት እና ለተለያዩ ቅጣቶች አይዳረጉም :: ይህ ብቻ አይደለም የመጋዘን ቆይታ ጊዜ አልፏል ተብለው #እቃዎት #አይወረስም ምክንያቱም በሚንሰጠው #አስቸኳይ ጊዜ የብድር አገልግሎት ፈጣን ምላሽ ስለሚያገኙ
"#ኬብሮንሂል #በአብሮነት ወደ #ልህቀት"!!
ለበለጠ መረጃ:-
የስልክ ቁጥር :-
+251113693794 አየርጤና ቅርንጫፍ
+25111 557 1234 ሜክስኮ ቅርንጫፍ
+251115300195 ካዛንቺስ ቅርንጫፍ
+251222381216 አሰላ ቅርንጫፍ
+251226654543 ሮቤ ቅርንጫፍ
+25133 312 7446 ደሴ ቅርንጫፍ
+251981827772 ሳሪስ ቅርንጫፍ ይደዉሉ
ጠቃሚ ሊንኮች :
👉KebronHill Telegram :-
https://t.me/+quucyPHlQFhlZGFk
https://t.me/KHMFI_2025
👉Facebook:-
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082971387221
👉Website:-
www.kebronmfi.com
👉Whatsaap
https://chat.whatsapp.com/LRBLZ53ylVeLI2Jq1yjNGN?mode=ems_copy_t
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@..khmfi?_r=1&_t=ZM-911zunkbQa0
👉Linkden
https://www.linkedin.com/company/kebronhill-microfinance-institution-share-company/
Everybody Join our Social media links for updates and new informations
#ከብሮንሂል ማይክሮፋይናንስ አ.ማ
👉14 ብድር እና 6 የቁጠባ አማራጮችን ይዞ ቀርቦላችኃል:: በተለይም በዝቅተኛ እና መካከለኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ለሚገኙ ለማህበረሰባችን ክፍሎች የሥራ ማስጀመሪያ እና ማስፋፊያ(Working Capital) ብድሮችን በስፋት እያቀረብን እንገኛለን::
በተጨማሪም
👉ዉድ ጊዜዎትን የማይጠይቅ : የማታቃጥሉበትን
👉ሰራተኛ ደመወዝ ወጪ ብለው የማያስቡበትን:
👉 ቢዝነስ ለማስጀመር ብላችሁ ዉስብስብ የቢሮክራሲ ሂደቶችን ማለፍን የማይጠይቅ
👉የሥራ ቦታ ኪራይ እና ሌሎች አላስፈላጊ ወጪዎችን የማታወጡበት
👉ይከስርብኛል ከሚል ስጋት ነፃ የሚያደጋችሁን
ከ5,000 ጀምሮ ለ6 ወር : ለ12 ወር : ለ18 ወር : ለ24 ወር : ለ36 ወር እና ከዛም በላይ በጊዜ ገደብ ቁጠባ መልክ ገንዘባችሁን እኛ ጋር በማስቀመጥ ብቻ ከ9.5% እስከ 20% የሚደርስ አጓጊ የወለድ ትርፍን የሚያስገኝ ቀላል እና ብልህ ኢንቨስትመንት ላይ ይሳተፉ! ይህ ግሩም ዕድል ነው::
ስለሆነም :- ኑ ተበደሩ ጅምር ስራዎቻችሁን አስፋፉ!
ገንዘባችሁን እኛ ጋር በማስቀመጥ #በቀላሉ #ትርፋማ የሚያደርጋችሁን የብልሆችን ኢንቨስትመንት ይቀላቀሉ!
N. B:- ከተቀማጭ ወለድ የሚገኘዉን ትርፍ በየወሩ እንደደመወዝ ቀድመው መዉሰድ ይችላሉ ወይም ደግሞ በስምምነትዎ መሰረት በየወሩ ወደ ባንክ ህሳብዎ ትራንስፈር እናደርግለዎታለን::
ከፍ ያለ እና ረዘም ያለ ጊዜ ተቀማጭ መጠን bonus ይኖረዋል!
እኛን ምርጫዎ ስላደረጉ ከልቤ እናመሰግናለን
ኬብሮንሂል በአብሮነት ወደ ልህቀት!!!
👉ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎ የሚገኝ የተቋማችን ቅርንጫፍ ሰራተኞችን ያናግሩ
የስልክ ቁጥር :-
+251113693794 አየርጤና ቅርንጫፍ
+25111 557 1234 ሜክስኮ ቅርንጫፍ
+251115300195 ካዛንቺስ ቅርንጫፍ
+251222381216 አሰላ ቅርንጫፍ
+251226654543 ሮቤ ቅርንጫፍ
+25133 312 7446 ደሴ ቅርንጫፍ
+251981827772 ሳሪስ ቅርንጫፍ ይደዉሉ
ጠቃሚ ሊንኮች :
👉KebronHill Telegram :-
https://t.me/+quucyPHlQFhlZGFk
https://t.me/KHMFI_2025
👉Facebook:-
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082971387221
👉Website:-
www.kebronmfi.com
👉Whatsaap
https://chat.whatsapp.com/LRBLZ53ylVeLI2Jq1yjNGN?mode=ems_copy_t
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@..khmfi?_r=1&_t=ZM-911zunkbQa0
👉Linkden
https://www.linkedin.com/company/kebronhill-microfinance-institution-share-company/
Everybody Join our Social media links for updates and new informations
ከመጋቢት 14 ጀምሮ የባንክ የገንዘብ ማስተላለፊያ ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 እንዲሆን ተወሰነ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በሀገሪቱ ያለውን የዲጂታል ክፍያ ሥርዓት ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግና የገንዘብ ዝውውርን ለማሳለጥ፣ የሪል ታይም ግሮስ ሴትልመንት (RTGS) የሥራ ሰዓት ላይ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።
ባንኩ ለሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ባስተላለፈው መመሪያ መሠረት፣ ቀደም ሲል በቀን ለ9 ሰዓታት ብቻ ይሰጥ የነበረው የገንዘብ ማስተላለፊያ አገልግሎት በሁለት ሰዓታት እንዲራዘም ተወስኗል።
በዚህም መሠረት አገልግሎቱ በየሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1:00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል።
ይህ አዲስ የሥራ ሰዓት ማሻሻያ ከመጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናልም ተብሏል።
ብሔራዊ ባንኩ ውሳኔውን ያስተላለፈው በገበያው ውስጥ ያለውን ገንዘብ ዝውውር ፍላጎት ለማሟላትና የክፍያ ሥርዓቱን ዘመናዊነት ለማገዝ መሆኑን አመልክቷል።
ሁሉም የፋይናንስ ተቋማት ለተራዘመው የሥራ ሰዓት የሚመጥን የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ ዝግጅት እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ይህ መመሪያ በባንኮች መካከል የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮች ያለምንም መስተጓጎል እንዲከናወኑ ለማስቻል ያግዛል ተብሎ ይጠበቃል።
Repost from THIKVAH-ETHIOPIA ᴘᴀɪᴅ.ᴠᴇʀsɪᴏɴ
+1
" የኛ የብድር ወለድ መጠን ከባንኮች ከፍ ያለ የሆነው የብድር ካፒታላችን 20 በመቶ ከባንክ ስለሆነ ነው " - የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ማህበር
የኢትዮጵያ አነስተኛ ብድር እና ቁጠባ ተቋማት ማህበር ከሚሰጣቸው የብድር አገልግሎቶች የሚቀበለው የብድር ወለድ መጠን ከባንኮች ከፍ ያለ የሆነው 20 በመቶ የሚሆነውን የብድር ካፒታሉን የሚያገኘው ከባንክ ስለሆነ መሆኑን ገለጸ።
ማህበሩ ይህን የገለጸው ከመጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ( UNECA ) አዳራሽ የሚካሄደውን ዓለም አቀፍ የማይክሮ ፋይናንስ ኮንፈረንስ አስመልክቶ ትላንት ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጠበት ወቅት ነው።
የማህበሩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተሾመ ከበደ ከማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የብድር አቅርቦት ጋር በተገናኘ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?
" የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ብድር አይሰጡም፣ ቃላቸውን አያከብሩም የሚሉ ቅሬታዎች በተደጋጋሚ ከደንበኞቻችን ይነሳሉ። ይህ ችግር የመነጨው የለብድር የሚውል የገንዘብ መጠን (ካፒታል) በማነሱ ነው።
ተቋማቱ ብድር ሚሰጡት ከደንበኞች ከሚሰበሰብ ቁጠባ ሲሆን፣ ይህም በየጊዜው ከሚወጡ የፖሊሲ ለውጦች ጋር ተዳምሮ የአቅርቦት እጥረት እየፈጠረ ነው።
ለደንበኞቻቸው የተሰጡ ብድሮች በተቀመጠው ውል መሠረት በጊዜ ካልተመለሱ፣ ተቋሙ ለቀጣዩ ተበዳሪ የሚሰጠው ገንዘብ አይኖረውም። ይህም በብድር አቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ መስተጓጎል ፈጥራል።
ሌላው ደግሞ ተበዳሪው የዋስትና መስፈርቶችንና ሌሎች ከመሥሪያ ቦታ ጋር የተያያዙ ቅድመ ሁኔታዎችን በወቅቱ ካላሟላ የብድር ሂደቱ እንዲዘገይ ምክንያት ይሆናል።
የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የገንዘብ ምንጭ ከ75 እስከ 80 በመቶ የሚሆነው ከቁጠባ የሚገኝ ነው። ይሁን እንጂ ከአነስተኛ የህብረተሰብ ክፍል የሚሰበሰበው ቁጠባ በጣም አነስተኛ በመሆኑ ይህን አጠራቅሞ ለአንድ ተበዳሪ ለማቅረብ ረጅም ጊዜ ይፈጃል።
በሀገራችን የፋይናንስ አካታችነት (Financial Inclusion) ከ60 በመቶ አይበልጥም፤ ይህም ማለት 40 በመቶ የሚሆነው ህዝብ አሁንም አገልግሎቱን እየጠበቀ ነው።
ችግሩን ለመቅረፍ የብድር አቅርቦቱን በዲጂታል መንገድ ማድረስ ካልተቻለ አሁን ባለው ፍጥነት የህዝቡን ፍላጎት ለማሟላት ረጅም ዓመታት ይፈጅብናል። ግን ችግሩን ለመቅረፍ እየሰራን ነው።
አነስተኛ የብድር እና ቁጠባ ተቋማት የሚሰጡት የብድር ወለድ መጠን ከባንኮች ከፍ ያለ ቢሆንም ከጎረቤት ሀገሮች አንጻር ሲታይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት በጣም አነስተኛ ወለድ ነው የሚያስከፍሉት።
በአማራና በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ችግር ምክንያት የፋይናንስ አገልግሎቶቹ የተቋረጡባቸው ቅርንጫፎች አሉ። ነገር ግን በዚህ ምክንያት የከሰረ ማይክሮ ፋይናንስ እስካሁን የለም።
በፀጥታ ችግር ምክንያት ቅርንጫፎቹ በሚፈለገው ልክ አገልግሎት መስጠት በማቆማቸው ያልተመለሱ ውዝፍ ብድሮች አሉ። ነገር ግን የጸጥታ ሁኔታው መሻሻል በሚያሳይበት ጊዜ ተበዳሪዎቹ ያለባቸውን ውዝፍ ገንዘብ መጥተው እየከፈሉ ነው " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መጋቢት 3 ቀን 2018 ዓ/ም
@thikvahethiopia
ውድ ደንበኞቻችን፤
ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በተጻፈ ደብዳቤ ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሚፈጸሙ ግብይቶች በደንብ ቁጥር 576/2018 ዓ.ም ላይ በተጠቀሰው የማስከፈያ ስሌት መሰረት ከደንበኞች ላይ ክፍያዎችን በመሰብሰብ በብሔራዊ ባንከ በተያዘው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ሂሳብ ገቢ እንዲያደርጉ ለሁሉም ማይክሮፋይናንሶችና ባንኮች ማሳሰቢያ ሰጥቷል፡፡
በመሆኑም ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ተቋማችን ከሚሰጠው ማንኛውም አይነት መደበኛ ብድር ላይ የሚሰጠውን የብድር መጠን 1% (አንድ በመቶ)፣ እየተጨመረ የሚሰበስብ መሆኑን በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ለበለጠ መረጃ አቅራቢያዎ የሚገኝ የተቋማችን ቅርንጫፍ ሰራተኞችን ያናግሩ
የስልክ ቁጥር :-
+251113693794 አየርጤና ቅርንጫፍ
+25111 557 1234 ሜክስኮ ቅርንጫፍ
+251115300195 ካዛንቺስ ቅርንጫፍ
+251222381216 አሰላ ቅርንጫፍ
+251226654543 ሮቤ ቅርንጫፍ
+25133 312 7446 ደሴ ቅርንጫፍ
+251978742927 ሳሪስ ቅርንጫፍ ይደዉሉ
ኬብሮንሂል
በአብሮነት ወደ ልህቀት
ጠቃሚ ሊንኮች :
👉KebronHill Telegram :-
https://t.me/+quucyPHlQFhlZGFk
https://t.me/KHMFI_2025
👉Facebook:-
https://www.facebook.com/profile.php?id=100082971387221
👉Website:-
https://www.kebronmfi.com/
👉Whatsaap
https://chat.whatsapp.com/LRBLZ53ylVeLI2Jq1yjNGN?mode=ems_copy_t
👉Tiktok
https://www.tiktok.com/@..khmfi?_r=1&_t=ZM-911zunkbQa0
👉Linkden
https://www.linkedin.com/company/kebronhill-microfinance-institution-share-company/
Everybody Join our Social media links for updates and new informations
