ወደ ኢየሱስ ደረት
Открыть в Telegram
Romans 8÷1 There is therefore now no condemnation to them which are in Christ Jesus, who walk not after the flesh, but after the Spirit.
БольшеСтрана не указанаКатегория не указана
276
Подписчики
Нет данных24 часа
-17 дней
-630 дней
Архив постов
276
ወገኖቼ ምንም ብንሆን ከኢየሱስ አናፈግፍግ🥹 ዳዊት እግ/ርን ምንም ያህል ቢበድል ወደ እግ/ር ነበር የሚሸሸው።ስለዚህ የኛ መሸሸጊያችን ኢየሱስ ጋር
እኛን እኮ ከሰው ቀድሞ የተቀበለን እሱ ነው እድፋችን ደምቆብን ሰው ሁሉ ሲያግፋፋን ኢየሱስ ነው ከነ ቆሻሻችን ያቀፈን🥺 የተቀበለን አትጠራጠሩ በእርሱ ካማረብን ብዋላ ነው የሰውን ፍቅር ያየነው ማን ነው ኢየሱስ ጋር መቶ የተጎዳ/የተጨነቀ/ያለቀሰ ....ከቶ የለም ይህ በእርሱ ዘንድ፤ወንድሞቼ ምንም ብንበድለው ከቶ ከሱ አናፈግፍግ🧎♀🧎🙌❤️❤️
276
Repost from እውነተኛ ክብር
ሰሞኑን አንድ የተወደደ ወንድም ስያወራ ሰምቼ በጣም በልቤ ላይ የከበደውን ነገር ላካፍላችሁ…
የበረከት ተስፋዬ መዝሙርን ታስታውሱታላችሁ አይደል
(ሰው ሁሉ ንጹህ ሆኖ እኔ ግን ብቆሽሽ በምድር ላይ እኔ ብቻ በኀጢአት ብበላሽ መሞት የሚገባኝ እኔ ብቻ ብሆን ኢየሱስ ለብቻዬ ይመጣልኝ ነበር )የምለውን መዝሙር ብዙ ጊዜ ዘምረን ይሆናል ግን እስኪ ቆም ብለን እናስብ የምር ግን በምድር ያሉ ሰዎች በሙሉ ንጹህ ሆኖ እኔ ብቻ ብቆሽሽ እና ሀጥአተኛ ብሆን ኢየሱስ ለኔ ብቻ ይመጣልኝ ነበር? መልሱ በጣም አስደናቂ ነው አዎ ይመጣልኝ ነበር የማቴዎስ ወንጌል 18:11 የሰው ልጅ የጠፋውን ለማዳን መጥቶአልና። ምን ይመስላችኋል? ለአንድ ሰው መቶ በጎች ቢኖሩት ከእነርሱም አንዱ ቢባዝን፥ ዘጠና ዘጠኙን በተራራ ትቶ ሄዶም የባዘነውን አይፈልግምን? ቢያገኘውም፥ እውነት እላችኋለሁ፥ ካልባዘኑቱ ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል። ኢየሱስ አይሁዶችን ለማዳን በመጣበት እግረ መንገዱን አደለም ያዳነን ለእያንዳንዳችን ብሎ ነው የመጣው ለራሳቹ ዋጋ ስጡ… Blessed😇
276
ትኩረት_ወይስ_ትዝታ
👉 ትዝታ የምታስታውሱት ያለፈ ነገር ስሆን፤
👉 ትኩረት ግን አሁን ሃሳባችሁን የያዘ/ የተቆጣጠረ ነገር ነው።
👉 ክርስቶስ ለአንዳንዶች ትዝታ ነው።
ለአንዳንዶች ደግሞ ትኩረታቸው ነው፤
👉 ክርስቶስ ትኩረታችሁ ስሆንና ትዝታችሁ ስሆን የህይወታችሁ #ቃና ይለያል።
👉 ክርስቶስ የኑሮአችን ተጨማሪ ህይወት ሳይሆን የመኖራችሁ ምክንያት ይሁን።
👉 ክርስቶስ የሆነ ግዜ ብቻ ትዝ የምላችሁ ከሆነ ትኩረታችሁን የዚህ ዓለም ጉዳይ ሰርቆታል: ልንነቃ ይገባል።
➽ እርሱ በትዝታ የምመለክ አምላክ ሳይሆን #በትኩረት የምትከተሉት የዘላለም ክብራችሁ ነው።
👉 አብዘኞቻችን ብዙ ዕድሜ ሳናስቆጥር ትዝታ ሕይወት መኖር ጀምረናል፤
➽ ኢየሱስ ትኩረታችን እንጂ ትዝታችን አይሁን!!
(tesfa s)
276
please yihenin mezmur simu
👇👇👇👇👇👇👇
▶ዘማር ደረጀ ማሴቦ◀
⏩ፀጋ ይብዛልኝ ⏪
አንተ ምራኝ (2*) አንተ
ልከተልህ (2*) አንተን
እንዴት ማገልገል እንዳለብኝ
ኧረ እንዴት መራመድ(መጨረስ) እንዳለብኝ
ቅርፍቱ ይነሳ ከአይኔ አጥርቼ እንዳይ ዘመኔን
አገልግዬ የተጣልኩ እንዳልሆን
በአንተ ፊት መራራ ሰው እንዳልሆን
አገልግዬ ተጥዬ እንዳልቀር
ከዘላለም ለዘላለም እንድኖር
⏩ጌታ ሆይ አግዘኝ
ጌታ ሆይ ደግፈኝ
ጌታ ሆይ ምከረኝ( ምህረትህ)
ጌታ....... ሆይ( ፀጋ... ይብዛልኝ)⏪
በእኔ ዘንድ መልካሙን ስራ
እንዳልባክን በሁሉ ስፍራ
ምሳሌ አርገኝ ለአንተ መኖር
ፍጥረት ሁሉ አንተን እንዲያከብር
⏩ታማኝ አርገህ ቆጥረህ
ታላቅ እድል ሰጥተህ
በቤትህ ስትሾመኝ
ደርሶ እንዳይቀልብኝ⏪
በእንባ ሽቶ ቢፈልገው ሊያገኘው እንዳልቻለው
አቃልዬ ጥየው እንዳልል ወየው ወየው (2*)
ከእውርነቴ አለም አውጣኝ መድሀኒአለም
ያንተን ፈለግ አሳየኝ ወደ ሃሳብህ አስጠጋኝ
ጌታ ሆይ አግዘኝ
ጌታ ሆይ ደግፈኝ
ጌታ ሆይ ምከረኝ( ምህረትህ)
ጌታ....... ሆይ( ፀጋ... ይብዛልኝ)
276
እንጠጋ ወደ እርሱ
ሰው ልቡ ሲደክም፣ ሐሳቡ ሲተላለፍ፣ መንገዱም ሲያስጨንቀው የሚፈልገው ትክክለኛ መጠጊያ የኢየሱስ ፍቅር ነው። እርሱ ሲቀበለን ስህተታችንን አይቈጥርም፤ የሚመለከተን ልባችንን ነው፣ እና ወደ እርሱ ስንቀርብ የምናገኘው እረፍት ዓለም ሊሰጥ የማይችለው ነው።
ወደ እርሱ መጠጋት ማለት በጸሎት ልባችንን መክፈት፣ በቃሉ መመራት፣ በፍቅሩም መታመን ነው። በዚህ ቅርብነት ውስጥ ፍርሃት ይቀንሳል፣ ጭንቀት አይኖርም፣ ልብም አዲስ ኃይል ይቀበላል። ኢየሱስ የሚሰጠው እረፍት ከሰዎች ወይም ከነገሮች አይመጣም፤ ከእርሱ ጋር ባለ ግንኙነት ብቻ ይገኛል።
ስለዚህ ወገኔ፣ ልብህ ቢደክም ወይም መንገድህ ቢጨልም፣ ወደ ኢየሱስ ደረት ተጠጋ፤ በዚያ የማይቀንስ ፍቅር፣ የማይለወጥ ሰላም እና አዲስ ተስፋ ታገኛለህ።✊
276
መንፈስ ቅዱስን የሚያርቁ 5 አደገኛ ልማዶች
እነዚህ ልማዶች በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ያለውን ግንኙነት የሚጋርዱ ናቸው፡
1. ንስሐ ያልተገባበት ስውር ኃጢአት (Hidden sin with no repentance) ሰው የማያየው ነገር ግን እግዚአብሔር የሚያውቀው ፣ ተደብቆ የሚሰራ እና ንስሐ ያልተገባበት ኃጢአት። ይህ ልብን ያጠነክራል ፤ የመንፈስ ቅዱስንም ህልውና ያጠፋል።
2. ምሬት እና ይቅር አለማለት (Bitterness and unforgiveness) በልብ ውስጥ ቂምን መያዝ ፣ የቀድሞ ጉዳትን እያሰቡ መመረር እና ይቅር ለማለት ፈቃደኛ አለመሆን። ይህ ልብን ለእግዚአብሔር ፀጋ ዝግ ያደርገዋል።
3. ትዕቢት እና ግትርነት (Pride and stubbornness) እርማትን አለመቀበል ፣ "እኔ አውቃለሁ" ማለት እና ለሰውም ሆነ ለእግዚአብሔር ቃል ልብን ማደንደን። እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል ፤ ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል።
4. ከዓለማዊ ተጽዕኖዎች ጋር ዘወትር መስማማት (Constant compromise with worldly influences) የእግዚአብሔርን መመዘኛዎች ዝቅ በማድረግ ከዓለም ጋር ለመምሰል መሞከር። ቅድስናን ወደ ጎን በመተው ከኃጢአት ጋር መደራደር መንፈሳዊ ህይወትን ይገድላል።
5. እግዚአብሔር አስቀድሞ ለተናገረን ነገር አለመታዘዝ (Disobedience to what God already told you) እግዚአብሔር እንድታደርገው ወይም እንዳታደርገው በግልፅ የነገረህን ነገር ሆን ብሎ መጣስ። ይህ "የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ ማጥፋት" ነው።
🤔 ዛሬ ምን ማድረግ ይኖርብናል?
🧐 ከእነዚህ ልማዶች ለመውጣት የዛሬው ምላሻችን ይህ መሆን አለበት?
▫️ራስን መመርመር (Examine)፦ ከላይ ከተጠቀሱት አምስት ነጥቦች ውስጥ በህይወቴ ያለው የትኛው ነው? ብሎ በታማኝነት ራስን መጠየቅ።
▫️በግልፅ መናዘዝ (Confess)፦ ኃጢአቱን ወይም ድክመቱን ለእግዚአብሔር በግልፅ መናገር (መዝሙር 32፡5)። "እግዚአብሔር ሆይ ይቅር በለኝ" ብቻ ሳይሆን፣ በትክክለኛው ስሙ ጠርቶ ንስሐ መግባት።
▫️በአፋጣኝ መታዘዝ (Obey Immediately)፦ እግዚአብሔር እንድታስተካክል የነገረህን ነገር አሁኑኑ ማድረግ። ይቅርታ መጠየቅ ካለብህ ጠይቅ፤ መተው ያለብህ ነገር ካለ ዛሬውኑ ቁረጥ።
▫️የመንፈስ ቅዱስን መሞላት መፈለግ (Ask for Filling)፦ ባዶውን ቤት ርኩስ መንፈስ እንዳይሞላው፣ በምትኩ መንፈስ ቅዱስ እንዲሞላህና እንዲቆጣጠርህ መጸለይ።
✨የኛ መለወጥ እንጂ የነገሮች መለወጥ ለውጥን አያመጣም ስለዚህ እኛ በአዕምሮ እንታደስ እንደግ የቦታን ለውጥ ሳይሆን የአዕምሮ ለውጥን እንፈልግ እራሱ የተሰራ ህይወት ነገሮችን ይሰራል
✨እኛ ወደ ለውጥ እንሄዳለን እንጂ ለውጥ ወደ እኛ አይመጣም ቢመጣም እንኳን አረምነ ይዞ ይመጣል እኛ ስንሄድ ወደ መልካሙ ነው።
276
" አላውቃችሁም"❗✋
ማቴ 25÷1-13
↔አላውቃችሁም በመባል ውስጥ ያለው ስሜት እንዴት ከባድ ይሁን !
↔እነዚህ ሙሹራዎች ሙሽራቸውን ሊቀበሉት በሰመመን ሲጠባበቁ ትልቅ ነገር ሆነ......
↔በአይሁድ ህግ ሙሽራው ሙሽሪትን ወደ ቤቱ ለመውሰድ ሲመጣ በፈለገበት ሰአት ነው። ቀንም ሆነ ማታ ሊመጣ ይችላል የሙሽሪት ተግባር ምንድ ነው መምጫው ስለማይታወቅ በዬትኛውም ሰአት ሌሊት ሆነ ቀን ውብ ሆና አጊጣ ተዘጋጅታ ቤቱዋን አዘጋጅታ መጠበቅ
አለባት።አሊያም ጥሎዋት ይሄዳል።
↔እነኚ ሙሽራዎች ይህ ዕጣ ፈንታ ደረሳቸው ከሰርጉ ከእራቱ ሳይሆኑ ቀሩ።😔
➡የክርስቲያኖች ሙሽራ የሆነ ኢየሱስ ሊመጣ እነሆ በደጅ ነው።
➡ሙሽራው የሚወደውን ነገር እያደረግን ቤታችንን ጉዋዳችችንን አሰናድተን እየጠበቅን ይሁን፤ ዛሬ ቢመጣ እንኳን ከእርሱ ጋር ለመሄድ ተዘጋጅተን ይሁን?
➡ዛሬ ወገኖቼ ለምን እንደ ምንኖር ለማንስ እንደምንኖር ዘንግተን በዘፈቀደን እየኖርን ነው።የሙሽራችን ጉዳይ እጅግ ሊያሳስበን እና ልንዘጋጅበት የሚያስፈልገን ጉዳይ ነው።
➡ ማቴ 24÷42
"ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።"
ይህ ጌታችን በምን ሰአት ሊመጣ እንዳለ አናውቅም፤ አሁን እያነበባችሁም ሊመጣ ይችላል ስለዚህ ነቅተን ሳንዘነጋ መጠበቅ።
➡ሉቃ12÷35-36
"ወገባችሁ የታጠቀ መብራታችሁም የበራ ይሁን፤
እናንተም ጌታቸው መጥቶ ደጁን ሲያንኳኳ ወዲያው እንዲከፍቱለት ከሰርግ እስኪመለስ ድረስ የሚጠብቁ ሰዎችን ምሰሉ።"
➡የእኛስ እጣፈንታ አላውቃችሁም የመባል እንዳይሆን
➡ስለዚህ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነቅተን ሙሽራችን መጠበቅ፤እንደሚወደው እና ሲያየን እንዳያፍርብን አለምን ከውስጣችን አውጥተን ለእርሱ እየተጋን በፅናት እንጠብቅ።
✍️በፅናት
276
ምን ይሁን መታወቂያችን ❓
📌ምን ይሁን መታወቂያችን ሰዎች ሲያዩን ሲሰሙን በስራ ቦታችን፤ እንደ አገልጋይ ስንመላለስ
ሰዎች እንዴት ቢያውቁን ደስ ይለናል ?ከዝማሬያችን ከስብከታችን፣ ከፅሁፎቻችን፣ ከጉብዝናችን ባለፈ እንዴት ቢያውቁን ደስ ይለናል??
➡#2ነገ 2÷15# በዚህ ክፍል በኤልሳዕ እና በኤልያስ መሀከል ብዙ ነገር ከሆነ ብዋላ ኤልሳዕም ሳይናገር መታወቂያው እንዲ ሆነ፦
ከኢያሪኮም መጥተው በአንጻሩ የነበሩት የነቢያት ልጆች ባዩት ጊዜ፡— የኤልያስ መንፈስ በኤልሳዕ ላይ ዐርፎአል፡ አሉ። ሊገናኙትም መጥተው በፊቱ ወደ ምድር ተደፉ።ኤልሳዕ የኤሊያስ መንፈስ አለብኝ አረፈብኝ ሳይል ባዩት ጊዜ አወቁት!!
➡#ማቴ 26÷73# በዚህ ክፍል ጴጥሮስ ምን እንደ ተባለ እናስታውሳለን
ጴጥሮስ ከኢየሱስ ጋር መቆየቱ እንዲታወቅ ሳይፈልግ ግን ከኢየሱስ ጋር እንደቆየ መታወቂያ ሆነ።ሳይፈልግ እዩኝ እዩኝ ሳይል እንዲ ነኝ ሳይል ሰው በፍሬው አወቀ።
📍የእኛስ መታወቂያችን ዛሬ ላይ ምንድነው?ሰባኪ ነው ሳይባል ህይወታችን እየሰበከ ነው? ?
📍ዘማሪ ነው ሲባል አንደበት ብቻ ወይስ ህይወትም እየዘመረ ነው??
🔺ሳንናገር ግን ህይወታችን ላይ የሚንፀባረቀው ምን ይሁን??
📍ይልቁንስ ከንግዲ መታወቂያችን በፍሬያችን የሚያሳብቅ ይሁን
💫በኢየሱስ ስም እኔ ኢየሱስን መስላለው ሳንል ሰዎች ከሩቅ ሲያዩን ንግግራችንን ሲሰሙ ከእኛ ጋር ሲቆዩ በአገልግሎታችን ጊዜ ኢየሱስን ተመስላለህ/ትመስያለሽ ይበሉን🙌
✍.Betsinat
✅https://t.me/wedeysusedert✅
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ
276
Repost from እንዘምር ለጌታ🎤🎸🎹🎧🎤
መዋቅረ ፀሎት!!
1. ስምህ ይቀደስ
2. መንግስትህ ትምጣ
3. ፈቃድህ ትሁን!!
እንዴት እንድንፀልይ አስተምረን ተብሎ ለቀረበለት ጥያቄ ጌታችን ኢየሱስ እንዲህ ፀልዮ ብሎ ባስተማረበት የፀሎት መዋቅሩ ላይ በቀዳሚነት የጠቀሳቸው አንኳርና ቀዳሚ ጉዳዮች እኒህ ነበሩ:: እነዚህ ከዕለት እንጀራና ከሌሎች ፍላጎቶቻችን ሁሉ ይቀድማሉ::
በእነዚህ ጉዳዮች ባለጠጋ መሆን
👉 የማያረጅ ባለጠግነት ነው
👉 በሰማያት መዝገብ መሰብሰብ ነው::
👉 የዘላቂ ደስታና የእውነተኛ እርካታ ምንጭ ነው::
የፀሎት መዋቅራችን እና የመሻት ዓለማችን ላይ እነዚህ ፊተኛና ቀዳሚ ይሁኑልን::
1. ስምህ በእኔነቴ ላይ ይቀደስ!
2. መንግስትህ በዕድሜዬና በዘመኔ ላይ ትምጣ!
3. ፈቃድህ በህይወቴ ትፈፀም!!
አሜን::
✍️ Dr. Lealem Tilahun
sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ
እንዘምር ለጌታ https://t.me/beka_tm
✅ ▷ https://t.me/inzemirlegeta ◁✅
🔺ይ🀄️ላ🀄️ሉ
276
ያለስብራት መጠንከር የለም እግዚአብሔር ለብዙዎች ስብራት መዳኒት ሊያረግክ ካሰበ ቀድሞ አንተን ሰብሮ መጠገንን ያስተምርሃል(ኢዮብ 5:18) ኢየሱስ እንዲ አለ አብ ሲያረግ ያየውትን ነው የማደርገው ያ ማለት በጓዳ አብ ያላሳየክን በብርሃን ለመግለፅ ይዳግታል ተባረኩ 🙌
276
Repost from እውነተኛ ክብር
"ድምፅህን አላምደኝ"
የትላንት ማንነቴን አስረስተህ
በድምፅ ሹክሹክታ ከልብህ መክረ
ስትመልስ ነብሴን በኮበለለች ጊዜ
በውብ ድምፅህ አባብለህ ተስፋን ስትሰጥ ለልቤ
ይኸው ዛሬም የውዴን ሽኩሽክታ ልሰማ ጓግቼ
ያቺ ጊዜ ትመለስ ይሁን እያልኩ በሀሳብ ተክዤ
እጠብቅሀለው እድትደግመው ያንን ድምፅ ለልቤ
ያቺ ቀን ግን እኔ እና አንተ የተገናኘንበት
ከአለም እና ከስጋ ሀሳብ የተለያየሁበት
እራሴን ክጄ አንተን ልመስል የወሰኩበት
በፍቅርህ እሳት የተቃጠልኩበት
ነብስ መንፈሴን ዘልቀህ ያጠነከርክበት
ያቺ አጋጣሚ ትዝ ትለኛለች የተቃቀፍንበት
ከቶ የማልረሳት ከውስጤ የማትጠፋ
ያቺ ቅዝበት ናት በፈቃድህ የተገናኘንባት
አባ እወዳታለው ከልብ ልብ ያወራንባት
ውዴ እጠብቅሀለው ያኔ መተ እንዳዋራኸኝ
ዛሬም ናና ድምፅህን አላምደኝ
እየሱስ....
276
እጅግ ወሳኝና የሆነ የጊዜ መልዕክት ነው በተለይ አገልጋይ የሆናችሁ ሳታነቡ እንዳታልፉ
ቤተክርስቲያን ውስጥ ስብከት ላይ ወጣቶችን ቴክስት መደራረግን የማያስቆም መልእክት ከሌለኝ፣ ቴክስት መደራረግ ይቀጥሉ። መልዕክታችን እየተሰበከ እንኳን ኢንተርቴይመንት ሊያምረን፣ ሰዓት ጠብቀን የምንወስደውን መድኃኒት የሚያስረሳ መሆን አለበት። አሁን እኮ ስብከታችን ይዘት የለውም፤ እኛም የምናወራው ዝም ብሎ ተደጋጋሚ ቃላት ብቻ ነው። ወላጆች ወጣት ልጆቻቸውን አስገድደው ቸርች እንዲመጡ ያደርጓቸዋል። ልጆቻቸው ወይ ግቢ ውስጥ ይጫወታሉ ወይ በግድ ይቀመጣሉ። ዛሬ ማስተካከል ካልቻልን ከስረናል ማለት ነው። ለትውልዱ መልእክት አጥተናል ማለት ነው። ይዘት ያለው መልዕክት ይፈልጋሉ። ካልተዘጋጀን ትውልዱ በጣም ያመልጠናል። ፍጥነቱ በጣም ከፍተኛ ነው። እኛ ካልሰጠነው ዓለም የምሰጠው በጣም ብዙ አለ።
እኔ መልእክቴን ስዘጋጅ የሚያስጨንቀኝ አንዱ ነገር ይሄ ነው። እኔ ካልሰጠሁት፣ እኔ ካላጎረስኩት፣ ይህ ትውልድ አየር ላይ ተንጠልጥሎ አይኖርም። የሚያጎርሰው አለ። መንገዱ አማራጭ በአማራጭ ነው። ኢንተርኔት ላይ ቢገባ፣ ጎግል ቢያደርግ ብዙ የሚጠቅም ነገር ያገኛል። የኔን የማይጠቅም ነገር ለመስማት ለምን ቁጭ ይላል? ድሮ አማራጭ ስለሌለ ነው። ዛሬ ምንም የሚዘገይ ነገር የለም፤ ድሮ ጋዜጣ እንኳን በደንብ በሌለበት አገር ነበር። አሁን መዓት ነገር አለ። ሁሉን የሚያስጥል! እኛ የፈለግነውን ነገር እያደረግን ወጣቱ በጠብታ እያለቀቀው ነው። አሁን ቸርች ውስጥ ረሃብ በጣም አለ። በጣም! አንዳንድ ወጣቶች ያስታውቃሉ። ዓለም ነች የምትመግባቸው። እኛ ስላልመገብናቸው ረሃብ ዝም ብሎ አይኖርም። እውነተኛ ምግብ ካላገኘህ ቆሻሻ ያስበላሃል። መንፈሳዊ ረሃብ በጣም ስላላቸው በዚህ ይሞክሩታል፣ በዚያ ይሞክሩታል። እና ዓለም የምትሰጣቸው ጃንክ ሆኖባቸዋል፣ ሰልችቷቸዋል፤ ቸርች ደግሞ የምትሰጣቸው ብዙ ሚረባ ነገር የለም። ስለዚህ ምን ይሁኑ? እጆቼን ሳስብ በጣም እጨነቃለሁ። የልጅ ልጆቻችንን ስናስብ በጣም ሊጨንቀን ይገባል።
276
#ቀን:4 ምሕረትና ሰላም ፍቅርም ይብዛላችሁ።
“ኢየሱስ ክርስቶስ ካልተሰበከ ጨርሶ ወንጌል አልተሰበከም፤ሞቱና ትንሣኤው ማዕከላዊ ካልተደረጉም እውነተኛው ክርስቶስ አልታወጀም።”
#ለ50 ተከታታይ ቀናት #ወንጌልን በድፍረት #በሥራ ቦታ፣ #በትምህርት ቤቶች፣ #በታክሲ ስፍራ፣ #በቤተሰብ መካከል፣ #በባልንጀሮቻችን ፊት እና #በማህበራዊ ሚድያ ገጾች መመስከር
#Share በማድረግ #ለሌሎችም በማድረስ በዚህ የወንጌል ሥራ አብረውን #ሠራተኞች እንዲሆኑ እናድርግ።
#በርቱ #ፀጋ ይብዛላችሁ ! 🙏
