AAU FM 99.4_Radio Official channel
رفتن به کانال در Telegram
AAU FM 99.4 Brodcast time every day from Morning 6:00Am - Evenning 10፡00PM.ከማለዳ 12:00_ምሽት4፡00አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን የተመለከተ ፈጣን የመረጃ ምንጭ! ➮ዩኒቨርሲቲ ተኮር መረጃዎች ➮የሃገር ቤት ትኩስ መረጃዎች ➮የአፍሪካ እና አለምን የተመለከቱ መረጃዎች ➮የዩኒቨርሲቲዉ ምሁራን ቃለ-መጠይቆች... ለበለጠ መረጃ 011-1-26-67-54/41ይደዉሉ
نمایش بیشتر899
مشترکین
-124 ساعت
-17 روز
+930 روز
در حال بارگذاری دادهها
کانالهای مشابه
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسبها
هیچ دادهای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26اکتبر '26
اکتبر '26
+13
در 0 کانالها
سپتامبر '26
+21
در 0 کانالها
Get PRO
اوت '26
+18
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئیه '26
+19
در 0 کانالها
Get PRO
ژوئن '26
+37
در 3 کانالها
Get PRO
مه '26
+251
در 6 کانالها
Get PRO
آوریل '26
+10
در 1 کانالها
Get PRO
مارس '26
+33
در 0 کانالها
Get PRO
فوریه '26
+13
در 1 کانالها
Get PRO
ژانویه '26
+29
در 2 کانالها
Get PRO
دسامبر '25
+204
در 4 کانالها
Get PRO
نوامبر '25
+158
در 6 کانالها
Get PRO
اکتبر '25
+332
در 0 کانالها
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 19 اکتبر | +1 | |||
| 18 اکتبر | 0 | |||
| 17 اکتبر | 0 | |||
| 16 اکتبر | 0 | |||
| 15 اکتبر | +3 | |||
| 14 اکتبر | +1 | |||
| 13 اکتبر | 0 | |||
| 12 اکتبر | +2 | |||
| 11 اکتبر | +2 | |||
| 10 اکتبر | +2 | |||
| 09 اکتبر | 0 | |||
| 08 اکتبر | 0 | |||
| 07 اکتبر | 0 | |||
| 06 اکتبر | 0 | |||
| 05 اکتبر | +2 | |||
| 04 اکتبر | 0 | |||
| 03 اکتبر | 0 | |||
| 02 اکتبر | 0 | |||
| 01 اکتبر | 0 |
پستهای کانال
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚከናወኑ የማህበረሰብ አገልግሎቶች የእውቀት ሽግግርንና ችግር ፈቺ ተግባራትን መሰረት አድርገው ሊከናወኑ እንደሚገባ ተመላከተ።
ጥቅምት 09፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮና ኮምፒውቲሽናል ሳይንስ ኮሌጅ ምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ዲን ዶክተር ዘወትር አበበ እንደገለጹት፣ ኮሌጁ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ኮሌጁ ከምርምር ስራዎች መካከል የዝባድ ምርትን (Modernization of Civet Musk) ማዘመን ላይ ያተኮረው ፕሮጀክት አንዱ ሲሆን፣ በዚህም ዘርፍ የተሰማሩ ባለሙያዎችን በማሰልጠን የምርት ጥራቱና መጠኑ እንዲጨምር እየተደረገ ይገኛል ሲሉ አብራርተዋል። ።
በኮሌጁ ማንኛውም የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክት ከመቀረጹ በፊት የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት እንደሚደረግና የህብረተሰቡ ተጨባጭ ችግሮች ከተለዩ በኋላ መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ እቅዶች ተይዘው ወደ ስራ እንደሚገባ አስረድተዋል።
አብዛኛዎቹ ፕሮጀክቶች በኮሌጁ ባለሙያዎች ብቻ የሚከናወኑ እንደሆኑ ዶክተር ዘወትር አስታውሰው፣ በቀጣይ ግን በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ከሚገኙ ሌሎች ኮሌጆች እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት እቅድ መኖሩን ሀላፊዋ አስታውቀዋል።
የአንድ ዩኒቨርሲቲ ዋና አላማ ማስተማር፣ ምርምር ማካሄድ እና ማህበረሰባዊ አገልግሎት መስጠት መሆኑን የተናገሩት ሀላፊዋ፣ ብዙ ጊዜ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ተዘንግቶ የሚቆይበት ሁኔታ እንደሚስተዋል ገልጸው በመሆኑም ምርምሮችን በወረቀት ላይ ብቻ አስቀምጦ ከመተው ይልቅ፣ ወደ ህብረተሰቡ ወርደው ተጨባጭ ችግሮችን መፍታት እንዲችሉ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአንተነህ ጌታቸው
| 2 | ANETNH GETACHEW TENA NEWS 06 02 19 (1).mp3 | 150 |
| 3 | ስለ ውስብስቡ የአእምሮ ጤና ሙያዊ ማብራሪያ!
ናርሲስስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር (NPD) የተጋነነ በራስ የመተማመን ስሜት፣ ከመጠን ያለፈ ትኩረት እና አድናቆት፣ የተቸገረ ግንኙነት እና ለሌሎች ያለ ርህራሄ ማጣት የሚታወቅ ውስብስብ የአእምሮ ጤና ሁኔታ ነው።
ናርሲስስቲክ ፐርሰናሊቲ ዲስኦርደር (NPD)ከተለያዩ የአእምሮ የህመሞች ዓይነቶች መካከል አንዱ ነው።
የናርሲሲስቲክ ስብዕና መዛባት ምልክቶች ብዙውን ጊዜ የሚጀምሩት ገና በለጋ ዕድሜ ላይ ሲሆን በክብደት ሊለያዩ ይችላሉ።
የጠባይ መታወክ በሽታ ይህ ሁኔታ ግለሰቦች ስለራሳቸው አስፈላጊነት የተጋነኑ ፣ የአድናቆት ጥልቅ ፍላጎት እና ለሌሎች ርኅራኄ የሌላቸው ሰዎች ያሉበት ሁኔታ እንደሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በዛሬው የጤና መረጃችን ከዚሁ ርዕሰ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ዶ/ር ብርክተአብ ሙሉጌታ የሰጡትን ማብራሪያ እንዲያደምጡ እንጋብዛለን።
አዘጋጅ ፦ አንተነህ ጌታቸው | 145 |
| 4 | ANETNH GETACHEW TENA NEWS 06 02 19.mp3 | 1 |
| 5 | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢ_ለርኒግ እና ተከታታይ ትምህርት ቢሮ ከ ዩኔስኮ ኢቼ ጋር በመተባበር "በዲጂታል ሊትረሲ እና ትራንስፎርሜሽን ሴቶች ማብቃት" በሚል ርዕስ አውደ ጥናት ከሰሞኑ አካሂዷል።
የአውደ ጥናቱ አላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማብቃት እና ተወዳዳሪ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
በአውደ ጥናቱ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዬች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጄይሉ ዑመር ፤ በሀገራችን እየተከናወነ ባለው ሁለንተናዊ የዲጂታል ለውጥ ሂደት ውስጥ የሴቶችን አቅም ማጎልበት የነገን ዕድገት ለመወሰን ወሳኝ ነው ብለዋል።
የዩኔስኮ (UNESCO) የዓለም አቀፍ አጋርነት እና ፕሮግራም ቢሮ ከፍተኛ የፕሮግራም ኦፊሰር የሆኑት ዩዋን ዢን ፤ በኢትዮጵያ ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሴቶች ተሳትፎን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል። | 149 |
| 6 | 📣 CALLING CREATIVE MINDS
Join Bruh Creative!
Are you passionate about storytelling, radio, and creating content for children? We're looking for creative and motivated Addis Ababa University students to join our team.
Who Can Apply?
Current AAU students
Interested in radio, storytelling, or children's content
Creative, reliable, and eager to learn
Able to commit 10-15 hours per week
Strong teamwork and communication skills
What You'll Gain
Hands-on experience in content production
Skills in storytelling and audio production
Opportunities to collaborate on real projects
Valuable experience for media and communication careers
How to Apply
Apply by email: Send your CV and a brief motivation letter to bruhaddiscreative@gmail.com
Subject: Creative Collaborator Application – [Full Name]
Or apply online: Complete the Google Form linked in this announcement. https://forms.gle/BVyjertJ18eyHnRB8
📅 Deadline: October 30, 2026
Build your skills, share your ideas, and help create inspiring stories for children ✨ | 187 |
| 7 | በዲጂታል ቴክኖሎጂ እውቀት የሴቶችን አቅም ማጎልበት ይገባል ተባለ።
ጥቅምት 05፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢ_ለርኒግ እና ተከታታይ ትምህርት ቢሮ ከ ዩኔስኮ ኢቼ ጋር በመተባበር "በዲጂታል ሊትረሲ እና ትራንስፎርሜሽን ሴቶች ማብቃት" በሚል ርዕስ አውደ ጥናት አካሂዷል።
የአውደ ጥናቱ አላማ በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ የሚገኙ ሴቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማብቃት እና ተወዳዳሪ ማድረግ መሆኑ ተገልጿል።
በአውደ ጥናቱ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚ ጉዳዬች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጄይሉ ዑመር ፤ በሀገራችን እየተከናወነ ባለው ሁለንተናዊ የዲጂታል ለውጥ ሂደት ውስጥ የሴቶችን አቅም ማጎልበት የነገን ዕድገት ለመወሰን ወሳኝ ነው ብለዋል።
በተለይም በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ የሚታየውን ክፍተት በማጥበብ አንዲሁም የሴቶችን ተሳትፎ በመሳደግ ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን
ጠቁመዋል።
የዩኔስኮ (UNESCO) የዓለም አቀፍ አጋርነት እና ፕሮግራም ቢሮ ከፍተኛ የፕሮግራም ኦፊሰር የሆኑት ዩዋን ዢን ፤ በኢትዮጵያ ባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሴቶች ተሳትፎን የተመለከተ ንግግር አድርገዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኢ_ለርኒ ዩኒትአስተባባሪ ዶ/ር ተምትም አሰፋ በበኩላቸው፤ቢሮው ለአካዳሚክ ሴቶች የተለያዩ የዲጂታል ስልጠናዎችን መስጠቱን በማንሳት ይህ መድረክ ያለውን ክፍተት በመለየት ለፓሊሲ ቀረፃ ግብአት እንደሚውል አንስተዋል።
አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ወደ ዲጂታላይዜሽን የሚያደርገውን ጉዞ ለማስቀጠል አሁንም ሴቶችን ይበልጥ በዲጂታል ቴክኖሎጂ ማብቃቱን እንደሚቀጥል አመላክተዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተካሄደው ይህ መድረክ የሴቶችን የዲጂታል እውቀት በማሳደግ ሀገራዊ የትራንስፎርሜሽን ጉዞውን ማፋጠን ረገድ ታላቅ ምዕራፍ ነው ተብሏል።
በብዙአየሁ ወንድሜነህ | 165 |
| 8 | بدون متن... | 1 |
| 9 | በማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል የፖሊሲ ማዕቀፍ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ፡፡
ጥቅምት 05፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም የፖሊሲ ትኩረት አስፈላጊነት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የግምገማ የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ማህበራዊ ሚዲያ ሁለት ስለት ያለው በመሆኑ በአግባቡ ከተጠቀምንበት ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ እድገታችንን በማፋጠን የጋራ ትርክታችንን ለማሳካት ይጠቅማል ሲሉ በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጶያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ጸጋ ጠቅሰዋል።
የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ከአገራዊ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገት እንዲሁም ከጋራ አብሮነት አንፃር ትልቅ ተጽዕኖ መፍጠር የሚችል ቢሆንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ ግን ከፍተኛ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል ተገልጿል።
ዳይሬክተሩ አክለውም የሚስተዋሉ የአጠቃቀም ክፍተቶችን ለማስተካከል የግንዘቤ ማስጨበጥ ስራዎችን እንዲሁም ጠንካራ ቁጥጥር እና ተጠያቂነትን በማስፈን ጉዳቱን መቀነስ እንደሚቻል ተናግረዋል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነትና ስነ-ተግባቦት ትምህርት መምህር እና በመድረኩ ላይ ጥናታዊ ጽሁፋቸውን ያቀረቡት ዶ/ር አዱላዚዝ ዲኖ የሚስተዋሉ ስጋቾችን እና ክፍቶችን ለማስተካከል የፖሊሲ ማዕቀፎች እንደሚያስፈልጉ ገልጸዋል።
በፍጥነት እየተለወጠ ካለው የቴክኖሎጂ አሰራር ጋር አብሮ ለመጓዝ እና ህገወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል የህግ ማዕቀፎችን ማጠናከር፣ ማሻሻል እንዲሁም አዳዲስ ህጎችን ማውጣት አስፈላጊ መሆኑም ጠቁሟል።
በነጻነት መረተ | 154 |
| 10 | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የመልካም አስተዳደር እና አካታችነት ፖሊሲ ሊተገብር ነው፡፡
ጥቅምት 04-2019(AAU RADIO FM 99.4)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ስርዓቱ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን የሚቀርፍ የመልካም አስተዳደር እና አካታችነት ፖሊሲ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር ሊገባ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ያረቀቀውን የመልካምአስተዳደር እና አካታችነት ፖሊሲ ለሴኔት አመራሩ ለውይይት አቅርቧል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በወቅቱ እንደገለጹት፤ አዲሱ ፖሊሲ ከዚህ ቀደም በትምህርት አሰጣጥ ምዘና ላይ የነበሩ የአፈጻጸም ውስንነቶች ለመቅረፍና ጠንካራ ጎኖችን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል።
ፕሬዘዳንቱ አክለውም ባለፉት ሦስት ዓመታት የተመዘገቡ ለውጦች እና ያልተፈቱ ቁልፍ ችግሮችን በመተንተን አሁን የተዘጋጀው ፖሊሲ ወጥ በሆነ አሰራር አፈፃፀሞችን መገምገም እንደሚያስችል ገልፀዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ዘመኑን የሚመጥን የትምህርት ስርዓት እንዲኖረው የመምህራን የአፈፃፀም ልኬት እና የኮርሶች መልሶ ግምገማ እንደሚያስፈልግም ተነስቷል፡፡
ፖሊሲው በአሁኑ ወቅት በሴኔት አባላት ውይይት እየተደረገበትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተጨማሪ ግብዓቶች እየተሰበሰቡ ይገኛል፡፡
በቀጣይ ከሴኔቱ የተሰበሰቡ ግብዓቶችን በመውሰድ ቦርዱ ፖሊሲው አፅድቆ ወደ ተግባር እንደሚገባ ተመለክቷል፡፡
አዲስዓለም አየሁ | 205 |
| 11 | በኢትዮጵያ የክሊኒካል ሙከራዎችን ለማሳደግ የሰው ኃይልና የምርምር መሠረተ ልማትን ማጠናከር ያስፈልጋል ተባለ።
ጥቅምት 03፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲዲቲ አፍሪካ "በኢትዮጵያ የክሊኒካል ሙከራዎችን ሥነ - ምህዳር ለማሳደግ ምን መደረግ አለበት " በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት ተደርጓል ።
በሲዲቲ አፍሪካ ማዕከል ምክትል ሃላፊ ፕሮፌሰር እያሱ መኮንን አንደገለፁት፤ በኢትዮጵያ የክሊኒካል ሙከራዎች ዘርፍ የተለያዩ ጅምሮች ቢኖሩም ዘርፉን ለማሳደግ የሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በቂ በጀትና ተስማሚ የምርምር ስራዎችን ማሟላት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።
ክሊኒካል ሙከራዎች የመድኃኒቶችን፣ የሕክምና ዘዴዎችንና ሌሎች የጤና አገልግሎቶችን ደህንነትና ውጤታማነት ለመገምገም የሚካሄዱ ምርምሮች ሲሆኑ፣ ለዘርፉ የተለየ ክህሎት፣ በቂ የገንዘብ ድጋፍ፣ የምርምር መሣሪያዎች ያስፈልጋሉ ሲሉ ፕሮፌሰር እያሱ ተናግረዋል ።
በዘርፉ የተሰማሩ ተቋማት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ሥልጠናዎችንና የማስተርስ ፕሮግራሞችን እያከናወኑ መሆናቸውም ተጠቁሟል።
በተጨማሪም በጀት ለማሟላት ከውጭ ለጋሾችና ከምርምር ድጋፍ ሰጪ ተቋማት ጋር መተባበር አስፈላጊ መሆኑ አንስተዋል ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶክተር ራሔል አርጋው በበኩላቸው ፤ በኢትዮጵያ የክሊኒካል ሙከራዎችን ሥነ-ምህዳር ለማሳደግ የምርምር ተቋማትን አቅም ማጠናከር፣ የሰለጠነ የሰው ኃይል ማፍራትና የምርምር መሠረተ ልማትን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል ።
የዘርፉን አቅም ለማሳደግም የጤና ተቋማት፣ የምርምር ማዕከላትና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አመላክተዋል ።
በሰዎች ላይ የሚካሄዱ የክሊኒካል ሙከራዎች የተሳታፊዎችን መብትና ደህንነት በሚጠብቁ ጥብቅ የሥነ ምግባር መርሆዎችና ሕጋዊ ሥርዓቶች መመራት እንዳለባቸውም ተገልጿል።
በቀጣይ የመንግሥት ተቋማት፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የጤና ተቋማትና የምርምር አጋሮች በቅንጅት ከሠሩ በኢትዮጵያ የክሊኒካል ሙከራዎችን ማሳደግና ለሀገሪቱ የጤና ምርምር ዘርፍ የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ተመላክቷል።
በአዲሱ አለማየሁ | 239 |
| 12 | የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ14ኛውን ዙር የምርምር አስተዳደር መድረክ አካሄደ።
ጥቅምት 03፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የምርምር አስተዳደር ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት፤ የ14ኛው ዙር የምርምር አስተዳደር የመግቢያ ፕሮግራም መድረክ ተካሂዷል።
መድረኩ የምርምር ሥራዎችን ጥራትና ውጤታማነት ለማሳደግ፣ እንዲሁም በአስተዳደራዊና የፋይናንስ አጠቃቀም ዙሪያ ግልጽ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ የ14ኛው ዙር የቴማቲክ ሪሰርች አሸናፊ ዋና ተመራማሪዎች፣ የኦፕሬሽን ዳይሬክተሮች እና የፋይናንስ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪሰርች አድሚኒስትሬሽን ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ፍቃዱ ጋሻው እንደገለጹት፤ በርካታ የምርምር ፕሮፖዛሎች ቀርበው በተለያዩ መስፈርቶች ተመዝነው ተመርጠዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ለሶስት ዓመታት የሚቆዩት እነዚህ የምርምር ፕሮጀክቶች እውቀት ከመፍጠር ባሻገር በህብረተሰቡ ላይ አዎንታዊ ለውጥ የሚያመጡ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል፤ የዩኒቨርሲቲው የበጀት እና ፋይናንስ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሮሀ ወንድሜነህ፣ ዩኒቨርሲቲው ለምርምር ሥራዎች የሚመድበውን በጀት ከአመት ወደ አመት እያሳደገ መምጣቱን ተናግረዋል።
በተለይም በ14ኛው ዙር የተመደበው በጀትና ለአሸናፊዎች የሚሰጠው የገንዘብ ጣራ ከፍ እንዲል መደረጉን ጠቁመዋል።
ኦፊሰሩ አክለውም፣ በፋይናንስ በኩል የሚታዩ መዘገየቶችን ለማስወገድ ዘመናዊ አሰራር ሥራ ላይ መዋሉን ገልጸው፤ በዚህም ተመራማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው በባንክ ሂሳባቸው ክፍያዎችን በፍጥነት ማግኘት እንደሚችሉ አስረድተዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከአገር ውስጥ በተጨማሪ ከ68 በላይ ዓለም አቀፍ ትስስር ያላቸው የምርምር ስራዎችን እንደሚያከናውን የተገለጸ ሲሆን፣ ወደፊትም የምርምር ስራዎችን ይበልጥ ለማቀላጠፍና ዘመናዊ አሰራርን ለመዘርጋት ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተመልክቷል።
በብዙአየሁ ወንድሜነህ | 182 |
| 13 | በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የካንሰር ህክምና አገልግሎት በዘመናዊ መንገድ ለማስፈፋት የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑ ተጠቆመ።
ጥቅምት 02፤2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የበላይ ልቀት ማዕከል የካንሰር ህክምናን በዘመናዊና በተሟላ መንገድ ለመስጠት የሚያስችሉ የህክምና ዘርፎች ተደራሽ እየተደረጉ መሆኑ ተገልጿል።
ማዕከሉ አገራዊ የህክምና ፍላጎትን ከመሸፈን ባሻገር፣ አገሪቱን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችን ዘርግቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።
በማዕከሉ ውስጥ ከሚሰጡ አበይት የህክምና አገልግሎቶች መካከል የካንሰር ህክምና ዋናው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ዘርፎች አገልግሎት እየተሰጠ እንደሚገኝ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ብርሀኑ ሰንደቅ ተናግረዋል።
በማዕከሉ ከሚሰጡት አበይት አገልግሎቶች መካከል የካንሰር ህክምና ዋነኛው ሲሆን፤ ከፍተኛ ደረጃ ያላቸውና ውስብስብ የሆኑ የቀዶ ህክምና፣ በመድኃኒቶች አማካኝነት የሚከናወን የኬሞቴራፒ፣ በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች የሚሰጥ የጨረራ ህክምና እንዲሁም የካንሰር ሴሎችን ብቻ ነጥለው ማጥፋት የሚችሉ የኣንቲቦዲ (የዒላማ) ህክምና አገልግሎቶች በስፋት እየተሰጡ ይገኛሉ ሲሉ ዶክተሩ አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም እንደ የአጥንት መቅኔ ውህደት (Bone Marrow Transplant) ያሉ ህክምናዎችን በማካተት የህክምና አቅሙን ያሳደገ ሲሆን፣ ይህም የሀገር ውስጥ ህሙማንን ከመደገፍ ባሻገር የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ሀገር ውስጥ መጥተው ህክምና የሚያገኙበትን የህክምና ቱሪዝም ለማስፋፋት ያለመ ስራዎችን እየተሰራ መሆኑ ተጠቅሷል።
በአንተነህ ጌታቸው | 216 |
| 14 | 📢 CALL FOR ALL ADDIS ABABA UNIVERSITY STUDENTS!
AAU FM 99.4 CLUB IS BEING ESTABLISHED!
https://t.me/AAUFM99point4
Do you want to make your voice heard?
Are you interested in public speaking, interviewing, research, scriptwriting, media production, and current affairs?
Do you want to learn how to identify, verify, and communicate reliable information?
If yes, this club is for you!
The Addis Ababa University AAU FM 99.4 CLUB is a student-led club being established in collaboration with AAU Community Radio FM 99.4.
The club aims to create opportunities for students from different academic backgrounds to develop practical communication and media skills while actively participating in public communication activities.
✅ What Will You Gain?
• Opportunity to host a radio programs
• Certificate of media expriance and training
• Training in program production, scriptwriting, interviewing, and presentation
• Public speaking and communication skills
• Media and digital literacy
• Workshops on identifying and verifying misinformation
• Knowledge of media law and professional ethics
• Practical experience and Certificates that can strengthen your CV
• Leadership and teamwork opportunities
• Opportunities to build friendships and professional networks
• Opportunities to participate in student communication and media-related activities
👥 Who Can Join?
All Addis Ababa University student, from any department and any year of study, are welcome to join.
No previous media or communication experience is required.
All you need is interest, commitment, and a willingness to learn.
⚠️ LIMITED SLOTS AVAILABLE!
Only a limited number of students will be accepted. Register early to secure your place.
🔗 Registration: https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLScB-ODKRNHbfJcW22ZEibpAQ1lhBfdv9o2RVMmNv-rhaMf0hg/viewform?usp=dialog
📅 Registration Deadline: Oct 13, 2026 G.C.
Make Your Voice Heard. Build Your Skills. Join AAU FM 99.4 CLUB!!! | 381 |
| 15 | የገነተ ልዑል ቤተመንግስት እድሳትን በይፋ ለማስጀመር የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
መስከረም 29፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሰቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ማዕከል የሆነውን የገነተ ልዑል ቤተመንግስት ሕንፃን ለማደስ ዩኒቨሲቲው ከጣሊያን መንግስት ጋር ያደረገውን ስምምነት ተከትሎ ከቅድመ ዝግጅት ወደ ተግባር ለመሸጋገር የሚያስችል የውይይት መድረክ ተካሄደ፡፡
ይኸው መድረክም ሁለት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ሲሆን፤ የመጀመሪያው የቤተመንግስቱን ሕንፃ የማደስ ስራ ነው፡፡
ለዚህም ቅድመ ዝግጅት በህንፃው የታችኛው ወለል ውስጥ የነበሩ ከ15 ሺህ በላይ ቅርሶችን ሳይንሳዊ ሂደቱን በጠበቀ መልኩ ወደ ሌላ ማቆያ ስፍራ እንዲዛወሩ መደረጋቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሐንስ አድገህ ተናግረዋል።
ሕንፃውን ለማደስም በቅርቡ ጨረታ እንደሚወጣ እና ከታህሳስ ወር አጋማሽ ጀምሮ የመልሶ ግንባታ ሥራው በይፋ ይጀመራል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም በጣሊያን የልማት ትብብር ሚኒስቴር በሚደረግ ድጋፍ ባለፈው አንድ አመት ውስጥ በቅርሶች ላይ ሲደረግ የነበረው ጥናት የደረሰበት ሁኔታ ግምገማ እንደሚካሄድም ጠቅሰዋል።
እድሳቱ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ እንደሚጠበቅና በእድሳቱ ወቅትም የሙዚየሙ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደማይቋረጥም ገልጸዋል፡፡
ነጻነት መረተ | 249 |
| 16 | የመድረክ ግብዣ!
"አንድ ጤና ለውስብስብ ስጋቶች መፍትሔ ሊሆን ይችላል" በሚል ርዕስ ፕሮፌሰር ሚርግሳ ካባ ጥናታዊ ፅሑፍ ነገ ሐሙስ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አዳራሽ ያቀርባሉ።
በዕለቱ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬዲዮ የማህበረሰቡ ድምፅ። Tune: AAU FM Radio 99.4
Phone: 011_1-26-67-41/54
Telegram: https://t.me/AAUFM99point4
Email: aaufm.radio@aau.edu.et youtube:- https://www.youtube.com/watch?v=mKpD-jTMR3o | 283 |
| 17 | ሎሚ ዴሊቨሪ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ዴሊቨሪ አገልግሎት ጀመረ።
መስከረም 27፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሚያጋጥማቸውን የጊዜና የምግብ አገልግሎት ተደራሽነት ችግር ለመፍታት ያለመ ሎሚ ዴሊቨሪ አገልግሎቱን በይፋ ጀምሯል ።
ሎሚ ዴሊቨሪ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስታርትአፕ ሴንተር የሚሰራ ሲሆን፣ ከዩኒቨርሲቲው ስታርትአፕ ሴንተር እና "ጂ አይ ካ" ትብብር የመጀመሪያ ኮሆርት አካል ሆኖ መቋቋሙ ተገልጿል።
የሎሚ ዴሊቨሪ መስራቾች ከተለያዩ ካምፓሶች የተውጣጡ ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ከመስራቾቹ መካከል ተማሪ ሃይማኖት ገበየሁ እንደገለፀችው ፣ ሀሳቡ የመጣው ተማሪዎች ምግብ ለመግዛት ሲሄዱ ከሚያጋጥማቸው ረጅም ሰልፍ፣ የጊዜ እጥረትና የዋጋ ጫና በመነሳት ነው።
ችግሩን በቴክኖሎጂ ለመፍታትም ተማሪዎች ከሚገኙበት ቦታ ሆነው በስልካቸው ምግብ እንዲያዙና በአጭር ጊዜ እንዲደርሳቸው አገልግሎቱ መጀመሩን ቡድኑ አስታውቋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት ሃላፊ ፕሮፌሰር ማቲዎስ እንሰርሙ በበኩላቸው ፣አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱ ምርምሮችን ፣ እውቀቶችንና ግኝቶችን ወደ ተግባራዊና የንግድ ስራዎች በመቀየር የራሱን ገቢ ለማመንጨት እየሰራ መሆኑን በማንሳት ዩኒቨርሲቲው ፣ ለሀገር፣ ለአፍሪካና ለዓለም ያሉ ችግሮች መፍትሄ እንዲሆኑ የሚያስችሉ እንደሆኑ ገልፀዋል።
አዳዲስ የስታርትአፕ ሀሳቦች ወደ ውጤታማ ንግድ እንዲቀየሩም ልምድና እውቀት ያላቸው ስራ አስኪያጆችና ስራ ፈጻሚዎች እንዲሳተፉ እየተደረገ ሲሆን፣ የዚህ ጥረት የመጀመሪያ ውጤቶችም መታየት መጀመራቸውን ተናግረዋል ።
አገልግሎቱ ከካፌዎችና ሬስቶራንቶች ጋር በመተባበር የሚሰጥ ሲሆን፣ የሎሚ ዴሊቨሪ ትዕዛዞች ቅድሚያ እንዲሰጣቸውና ምግቦች በፍጥነት እንዲዘጋጁ ከአጋር ተቋማት ጋር ስምምነት መደረጉን ተማሪ ሃይማኖት ገበየሁ ገልፃለች ።
በተጨማሪም ሎሚ ዴሊቨሪ ሌሎች ተማሪዎች ከትምህርት ጊዜያቸው ውጭ እንደ ራይደር በትርፍ ሰአት በመስራት ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙ ዕድል መፍጠሩን አስታውቋል።
አገልግሎቱ ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በመጀመር በቀጣይ ወደ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰቦች ለማስፋፋት ዕቅድ እንዳለው ተገልጿል ።
አዲሱ አለማየሁ | 243 |
| 18 | አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 4ተኛውን የፋይናንስ እና የኢንዱስትሪ ፎረም የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ አካሄደ።
መስከረም 26፤ 2019 ዓ.ም (AAU FM RADIO 99.4)
የአካዳሚ ትምህርቶችን ከኢንዱስትሪና ከፋይናንስ ዘርፍ ጋር በማጣመር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማጠናከር ያለመው 4ኛው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፋይናንስ፣ የኢንዱስትሪ ፎረም እና የቴክኖሎጂ አውደ ርዕይ በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ተካሂዷል።
በዚህ መድረክ ላይ የፋይናንስ ተቋማት፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ ተመራማሪዎች እና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ተገኝተዋል።
የፎረሙ ዋና ዓላማ በዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩ ምርምሮችና የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች በቀጥታ ወደ ኢንዱስትሪው እና ፋይናንስ ዘርፉ ገብተው ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ማስቻል ነው ተብሏል።
በመርሀ ግብሩ ንግግር ያደረጉት የአአዩ የምርምር እና ፈጠራ ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ወራሽ ጌታነህ ኢንድስትሪውን እና ዩኒቨርስቲውን በማስተሳሰር የምርምር ስራዎችን ወደ ገበያው ማድረስ የሚያስችል መንገድ ለመፍጠር እንዲህ አይነቱ መድረክ ድርሻው የጎላ እንደሆነ ተናግረዋል።
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእውቀት፣የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ማዕከል ከመሆን ባለፈ የምርምር ስራዎችን ወደ ገበያ ማውጣት ላይ በትኩረት አየሰራ መሆኑን ያነሱት ፕሮፈሰር ወራሽ ፤ይህን ለማጎልበት ዩኒቨርሲቲ ፣ኢንድስትሪ ፋይናንስ ትስስር መፍጠር ወሳኝ ነው ብለዋል።
ፕሮፌሰሩ አያይዘውም ዩኒቨርሲቲው ለያዘው አላማም የፋይናንስ ተቋማት ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዬጱያ ንግድ ባንክ ማርኬቲግ ዳይሬክተር አቶ ተስፋ ተክሌ በበኩላቸው፤ባንኩ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በአጋርነት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመው፤አሁንም ዩኒቨርሲቲው ለያዘው አላማ እንደ ፋይናንስ ተቋም የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ገልፀዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረበ ሲሆን፤ በዩኒቨርሲቲው ተመራማሪዎች የተሰሩ የተለያዩ የምርምር ውጤቶች ለእይታ ቀርበዋል።
በብዙአየሁ ወንድሜነህ | 299 |
| 19 | ዓይነ ስውርነትን ጨምሮ ለዓይን ህመም የሚያጋልጡ ችግሮችን የሚለይ ሐገር አቀፍ ጥናት ሊካሔድ እንደሆነ ተገለጸ
መስከረም 26፤2019 ዓ.ም
በሀገር አቀፍ ደረጃ ለዓይነ ስውርነት የተዳረጉ ሰዎችን እና ለዓይን በሽታ የሚያጋልጡ ችግሮችን የሚዳስስ ሳይንሳዊ ጥናት ሊካሄድ እንደሆነ የኢትዮጵያ የዓይን ህክምና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ማንደፍሮ ስንታየሁ ተናግረዋል።
ጥናቱ በገጠር እና በከተማ ከጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም. ጀምሮ እንደሚካሔድ የተገለጸ ሲሆን፤ ጥናቱ በዋናነት በጤና ሚኒስቴር መሪነት ሌሎች ባለድርሻ አካላትን አካቶ ይከናወናል ተብሏል።
ሀገር አቀፍ ጥናቱን ማካሔድ ያስፈለገው በኢትዮጵያ ለዓይነ ስውርነት ስርጭት በመጨመሩ እና አጠቃላይ ያለውን ችግር የሚያሳይ ሀገር አቀፍ ጥናት ባለመኖሩ እንደሆነ ተገልጿል።
ለጥናቱ የተደረገው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁን ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል። | 259 |
| 20 | ቻይንኛ ቋንቋ መማር ለምትፈልጉ!
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት የቻይንኛ ቋንቋ ስልጠና ፈላጊዎች (Chinese Language Certificate Program) ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል።
የምዝገባ ጊዜ፦
እስከ ጥቅምት 02/2019 ዓ.ም (ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ3:00-5:00 ሰዓት)
ስልጠናው ከጥቅምት 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለአስር ተከታታይ ሳምንታት፣ ቅዳሜ ከሰዓት ከ7:00-9:00 ሰዓት ይሰጣል፡፡
የስልጠና ደረጃ፦ Level 1
የምዝገባ ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ፎረም ህንፃ፣ 8ኛ ወለል፣ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ (ያሉ ቦታዎች ውስን ስለሆኑ ቀድመው ይመዝገቡ ተብለዋል። | 258 |
