fa
Feedback
ቃሉን እንማር📖

ቃሉን እንማር📖

رفتن به کانال در Telegram

📖 ቃሉን እንማር 📅 የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ በ05/01/2019 ዓ.ም ተጀመረ። 📖 ከዘፍጥረት እስከ ራእይ መጽሐፍ ቅዱስን ምዕራፍ በምዕራፍ እናነባለን፣ እናጠናለን። 💡 ቀላል ግልጽ እና በመጽሐፍ ቅዱስ የተመሠረተ ማብራሪያ 📅 በየቀኑ አዲስ ምዕራፍ 🎯 ዓላማችን፦ ቃሉን ማወቅ፣ መረዳት እና በሕይወት መተግበር። 📩 Questions & Suggestions: @mr_dani10 🕊️ EST 2018e.c

نمایش بیشتر
أثيوبيا7 712دسته بندی مشخص نشده است
2 800
مشترکین
+3024 ساعت
+1367 روز
+86230 روز

در حال بارگیری داده...

کانال‌های مشابه
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
ابر برچسب‌ها
هیچ داده‌ای
مشکلی وجود دارد؟ لطفاً صفحه را تازه کنید یا با مدیر پشتیبانی ما تماس بگیرید.
اشارات ورودی و خروجی
---
---
---
---
---
---
جذب مشترکین
اکتبر '26
اکتبر '26
+78
در 0 کانال‌ها
سپتامبر '26
+927
در 65 کانال‌ها
Get PRO
اوت '26
+1 042
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئیه '26
+704
در 1 کانال‌ها
Get PRO
ژوئن '260
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مه '26
+9
در 0 کانال‌ها
Get PRO
آوریل '26
+19
در 0 کانال‌ها
Get PRO
مارس '26
+4
در 0 کانال‌ها
Get PRO
فوریه '26
+5
در 0 کانال‌ها
Get PRO
ژانویه '26
+8
در 0 کانال‌ها
Get PRO
دسامبر '25
+13
در 0 کانال‌ها
Get PRO
نوامبر '25
+18
در 0 کانال‌ها
Get PRO
اکتبر '25
+244
در 3 کانال‌ها
تاریخ
رشد مشترکین
اشارات
کانال‌ها
03 اکتبر+30
02 اکتبر+32
01 اکتبر+16
پست‌های کانال
Repost from Natina Graphics
📲በቀላሉ በስልካችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን በማንኛውም ሰዓት የሚያደርሱን 💁🏻‍♀የቴሌግራም ቻናሎችን ልጦቁማቹ የምትፈልጉትን አገልግሎት መርጣቹ ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇

2
🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ አሁን በዳምጣው የምትሉትን መርጣው "Join" ያድርጉ 🙏🙏
6
3
🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ አሁን በዳምጣው የምትሉትን መርጣው "Join" ያድርጉ 🙏🙏
33
4
⚠️ለአንተ❓ወይም ለአንቺ❔ ምርጡ አገልጋይ ማነው በትምህርቶቹ እና በስብከቶቹ ይበልጥ የተባረካቹበትን አገልጋይ ምረጡ የሚመጣላቹሁን ቻናል ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1 666
5
ሰላም ሰላም የተወደዳቹ የአባቴ ልጆች እንደምን አላቹ እያልኩ በምን ዓይነት መልኩ መባረክ ትፈልጋላችሁ??? Free Wave @My_comfort_God
23
6
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ መቀላቀል ያለበት ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻነል 👇👇👇👇👇 🈴JOIN🈴 ያድርጉ Wave @seer_lewi
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ መቀላቀል ያለበት  ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻነል 👇👇👇👇👇 🈴JOIN🈴 ያድርጉ Wave @seer_lewi
24
7
📖 ዘፍጥረት 10 — የኖኅ ልጆች ትውልድ ዘፍጥረት 10 ከጥፋት ውኃ በኋላ የኖኅ ልጆች ትውልድ እንዴት እንደተስፋፋ ያሳየናል። ምዕራፉ በተለይ ከሴም፣ ከካም እና ከያፌት የተወለዱ ልጆችንና ከእነርሱ የተነሱትን ሕዝቦች ይዘረዝራል። 🌍 1. የያፌት ዘር መጀመሪያ የያፌት ልጆች ይጠቀሳሉ። ከእነርሱም የተነሱ ትውልዶች በየምድራቸውና በየቋንቋቸው ተስፋፉ። ምዕራፉ የኖኅ ልጆች ዘር በምድር ላይ መበተኑን ያሳየናል። 🌍 2. የካም ዘር ቀጥሎ የካም ልጆች ይጠቀሳሉ፦ ኩሽ፣ ምጽራይም፣ ፉጥ እና ከነዓን። ከእነዚህ የተነሱ ብዙ ትውልዶችና ሕዝቦች በምድር ላይ ተስፋፉ። 👑 3. ናምሩድ በዚህ ክፍል ምዕራፉ ልዩ ትኩረት የሚሰጠውን ሰው ያስተዋውቀናል፦ ናምሩድ። እርሱ በምድር ላይ ኃያል ሰው መሆኑን እና “በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ” መሆኑን ጽሑፉ ይገልጻል። መንግሥቱም በባቢሎን፣ በኤሬክ፣ በአካድና በካልኔ እንደጀመረ ይጠቀሳል። ከዚያም ወደ አሦር ሄዶ ነነዌንና ሌሎች ከተሞችን እንደሠራ ይነገራል። 🧭 4. የከነዓን ዘር ከዚያ የከነዓን ዘር በየምድራቸው ይዘረዘራሉ። የከነዓን ወገኖች እስከ ጋዛና ሰዶም፣ ገሞራ፣ አድማና ጽቦይም አካባቢ ድረስ ተዘርግተው እንደነበር ምዕራፉ ያሳያል። 🌿 5. የሴም ዘር በመጨረሻ የሴም ዘር ይዘረዘራል። ከሴም የተወለዱት ትውልዶችም በየምድራቸውና በየቋንቋቸው ተስፋፉ። ምዕራፉ የሴምን ዘር በመጥቀስ ይደመደማል። 💡 ዋናው ትምህርት ዘፍጥረት 10 ከጥፋት ውኃ በኋላ የኖኅ ልጆች ዘር እንዴት ተስፋፍቶ ብዙ ሕዝቦችና አገሮች እንደተፈጠሩ ያሳየናል። ምዕራፉ የተለያዩ ሕዝቦችን ቢዘረዝርም፣ መነሻቸው ከኖኅ ልጆች እንደሆነ ያሳያል። እንዲሁም ምዕራፉ በቀጣዩ ምዕራፍ ለምናነበው የባቢሎን ግንብ ታሪክ መሠረት ያዘጋጃል። 🙏 የማሰላሰያ ጥያቄ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የሰጠውን የመባዛትና በምድር ላይ የመስፋፋት ታሪክ ስመለከት፣ እኔ የምኖርበትን ሕይወት ለእግዚአብሔር ዓላማ እንዴት እየተጠቀምኩ ነው? 📖 የዛሬ ንባብ፦ ዘፍጥረት 10 📖 ቃሉን እንማር በየቀኑ አንድ እርምጃ ወደ እግዚአብሔር 🙏
210
8
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ — 400+ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርጫ ጥያቄዎችና መልሶች ይህ መጽሐፍ ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል (ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን) በመሸፈን ከ 400 በላይ የተመረጡ የምርጫ
ከዘፍጥረት እስከ ራእይ — 400+ የመጽሐፍ ቅዱስ የምርጫ ጥያቄዎችና መልሶች ይህ መጽሐፍ ሙሉውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል (ከብሉይ ኪዳን እስከ ሐዲስ ኪዳን) በመሸፈን ከ 400 በላይ የተመረጡ የምርጫ ጥያቄዎችን ከትክክለኛ መልሶቻቸው ጋር አካቶ የያዘ አጠቃላይ የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀት መፈተሻ ነው እያንዳንዱ ጥያቄ ትክክለኛ መልሱን የያዘ ሲሆን፣ ለበለጠ ማብራሪያና ማስታወሻ የሚሆን ክፍት ቦታም አለው ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን በቀላሉ መጽሐፉን ያውርዱ👇👇👇👇 https://ye-buna.com/samiyy?ref=product_detail&product=6ab4104676ce2_samiyy
1
9
🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ አሁን በዳምጣው የምትሉትን መርጣው "Join" ያድርጉ 🙏🙏
18
10
+3
بدون متن...
189
11
📖🌿 የሳምንቱ መደምደሚያ 📚 ዘፍጥረት 5–9 ውድ የ📖 ቃሉን እንማር ቤተሰቦች፣ ይህንን ሳምንት ከዘፍጥረት 5 እስከ 9 በመጓዝ አጠናቀናል። አሁን ደግሞ የተማርነውን በአጭሩ እንመልስ። 📖 🌿 1. ዘፍጥረት 5 — ትውልድና የሰው ሕይወት ዘፍጥረት 5 ከአዳም ጀምሮ የሰዎችን ትውልድ ያሳየናል። በዚህ የትውልድ ዝርዝር መካከል አንድ ነገር በተደጋጋሚ እናያለን፦ “ሞተ”። ይህም በኃጢአት ምክንያት ሞት ወደ ሰው ልጅ የገባበትን እውነታ ያስታውሰናል። ነገር ግን በዚህ ምዕራፍ ሄኖክንም እናያለን። ሄኖክ “ከእግዚአብሔር ጋር ሄደ” ተብሎ ተገልጿል። 🌊 2. ዘፍጥረት 6 — የሰው ኃጢአትና የኖኅ ጽድቅ የሰው ኃጢአት በምድር ላይ በጣም በዛ። እግዚአብሔርም የሰውን ክፋት አየ። ነገር ግን ኖኅ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን አገኘ። እግዚአብሔርም ኖኅን አዳነው እና መርከብ እንዲሠራ አዘዘው። 🛶 3. ዘፍጥረት 7 — የጥፋት ውኃ ኖኅ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ። የጥፋት ውኃም መጣ። ኖኅ፣ ቤተሰቡና በመርከቡ የነበሩት ፍጥረታት ተጠበቁ። ይህ ክፍል የእግዚአብሔርን ፍርድ እና በእርሱ የሚታመኑትን የማዳን ኃይሉን ያሳየናል። 🌿 4. ዘፍጥረት 8 — ውኃው ቀነሰ እግዚአብሔር ኖኅን አስታወሰ። ውኃውም መቀነስ ጀመረ። በመጨረሻም ኖኅና ቤተሰቡ ከመርከቡ ወጡ። ኖኅ ከዚያ በኋላ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠርቶ መሥዋዕት አቀረበ። ይህ እግዚአብሔር በመከራ ጊዜ የሚያስበንን እና ከመዳን በኋላ እርሱን ማመስገን እንዳለብን ያስታውሰናል። 🌈 5. ዘፍጥረት 9 — ኪዳንና አዲስ ጅማሬ እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባረከ። ከኖኅና ከሚመጡት ትውልዶች ጋርም ኪዳን አደረገ። 🌈 ቀስተ ደመናንም የኪዳኑ ምልክት አደረገ። ምዕራፉም በኖኅ የመጨረሻ ዘመናት ይዘጋል፤ ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ፣ በ950 ዓመቱም ሞተ። 💡 የሳምንቱ ዋና ትምህርት ከዘፍጥረት 5–9 ያለውን ጉዞ ስንመለከት፣ የሰውን ኃጢአት፣ የእግዚአብሔርን ፍርድ፣ የኖኅን እምነት፣ የእግዚአብሔርን ማዳን እና በመጨረሻም ኪዳኑን እናያለን። ይህ ጉዞ አንድ ነገር በግልጽ ያስተምረናል፦ 📖 እግዚአብሔር ቅዱስ ነው። 🙏 እርሱ የሚናገረውን ይፈጽማል። ❤️ በእርሱ የሚታመኑትን ያድናል። 🌈 ኪዳኑንም ይጠብቃል። ❓ የሳምንቱ የማሰላሰያ ጥያቄ በእነዚህ አምስት ምዕራፎች ውስጥ ከተማርኩት ነገር ዛሬ በሕይወቴ መተግበር የምፈልገው አንዱ ነገር ምንድነው? 🙏 በዚህ ሳምንት ከእኛ ጋር ዘፍጥረት 5–9ን የተማራችሁ ሁላችሁ እናመሰግናለን። ነገ ደግሞ አዲስ ምዕራፍ ይዘን ጉዟችንን እንቀጥላለን። 📖❤️ 📖 ቃሉን እንማር በየቀኑ አንድ እርምጃ ወደ እግዚአብሔር 🙏
192
12
📖 ዘፍጥረት 9 — እግዚአብሔር ከኖኅ ጋር ያደረገው ኪዳን 🌿 1. እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው ከጥፋት ውኃ በኋላ እግዚአብሔር ኖኅንና ልጆቹን ባርኮ ብዙ እንዲበዙና ምድርን እንዲሞሉ ነገራቸው። ይህ ለኖኅና ለቤተሰቡ አዲስ ጅማሬ ነበር። 🍖 2. ስለ ምግብና ደም እግዚአብሔር እንስሳትን ለምግብ እንደሰጣቸው ነገራቸው። ነገር ግን ሥጋን ከደሙ ጋር እንዳይበሉ አዘዛቸው። ደም ሕይወትን ስለሚወክል በልዩ ሁኔታ እንዲከበር ተነገረ። ❤️ 3. የሰው ሕይወት ዋጋ እግዚአብሔር የሰውን ደም ስለሚያፈስ ተጠያቂነት እንዳለ ነገረ። ምክንያቱም ሰው በእግዚአብሔር ምሳሌ ተፈጥሯል። ስለዚህ በዚህ ምዕራፍ የሰው ሕይወት በእግዚአብሔር ፊት ያለውን ታላቅ ዋጋ እናያለን። 🌈 4. የእግዚአብሔር ኪዳን ከዚያም እግዚአብሔር ከኖኅ፣ ከልጆቹና ከሚመጡት ትውልዶች ጋር ኪዳን አደረገ። እንደገና በጥፋት ውኃ ሁሉንም ሥጋ እንደማያጠፋ ተናገረ። 🌈 ቀስተ ደመናንም የኪዳኑ ምልክት አደረገ። ቀስተ ደመናው በደመና ውስጥ በታየ ጊዜ እግዚአብሔር ኪዳኑን እንደሚያስታውስ ተናገረ። 🍇 5. ኖኅ እና የወይን እርሻ ኖኅ አርሶ ወይን ተከለ። ከዚያም ወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰከረና በድንኳኑ ውስጥ ተራቁቶ ተኛ። ልጁ ካም የአባቱን እርቃን አይቶ ወደ ውጭ ወጥቶ ለወንድሞቹ ነገራቸው። ሴምና ያፌት ግን ልብስ ወስደው በትከሻቸው ላይ አድርገው ወደኋላ እየተመለሱ አባታቸውን ሸፈኑ። እንዳይመለከቱትም ፊታቸውን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዞሩ። 📌 እዚህ ላይ የምናየው፣ የሌላን ሰው ድክመት ማየት ብቻ ሳይሆን ለዚያ ድክመት የምንሰጠው ምላሽም አስፈላጊ መሆኑን ነው። ⚖️ 6. የኖኅ ቃል ኖኅ ከሰከረበት ሁኔታ ከነቃ በኋላ ታናሹ ልጁ ያደረገውን አወቀ። ከዚያም ስለ ካናን፣ ስለ ሴምና ስለ ያፌት ተናገረ። እዚህ ላይ ጠቃሚ ነገር አለ፦ መጽሐፉ በግልጽ የሚናገረው ኖኅ የተናገረው እርግማን በተለይ ለካናን እንደሆነ ነው። ካም የካናን አባት ነበር። 📖 7. የኖኅ የመጨረሻ ዘመናት ምዕራፉ በኖኅ ሕይወት የመጨረሻ መረጃ ይዘጋል። ኖኅ ከጥፋት ውኃ በኋላ 350 ዓመት ኖረ። የኖኅም ዕድሜ በአጠቃላይ 950 ዓመት ሆኖ ከዚያ ሞተ። 💡 ዋናው ትምህርት ዘፍጥረት 9 ከጥፋት ውኃ በኋላ የተጀመረውን አዲስ የሰው ልጅ ጉዞ፣ እግዚአብሔር ያደረገውን ኪዳን፣ የሰው ሕይወትን ክብር እና የኖኅን የመጨረሻ ዘመናት ያሳየናል። እንዲሁም የኖኅ እና የልጆቹ ታሪክ የሰውን ድክመት ስናይ በክብርና በጥበብ መመላለስ እንዳለብን ያስተምረናል። 🙏 የማሰላሰያ ጥያቄ እግዚአብሔር የሰጠኝን አዲስ እድል እንዴት እየተጠቀምኩበት ነው? እና የሌሎችን ድክመት ስመለከት በክብር እና በፍቅር እመላለሳለሁ? 📖 የዛሬ ንባብ፦ ዘፍጥረት 9 📖 ቃሉን እንማር በየቀኑ አንድ እርምጃ ወደ እግዚአብሔር 🙏
208
13
የዕለቱ የንባብ ክፍል ኦራት ዘፍጥረት - ምዕራፍ ዘጠኝ (ሙሉውን አንብቡት ምሽት ላይ ማብራሪያ እንወስዳለን)❤️+3
የዕለቱ የንባብ ክፍል ኦራት ዘፍጥረት - ምዕራፍ ዘጠኝ (ሙሉውን አንብቡት ምሽት ላይ ማብራሪያ እንወስዳለን)❤️
190
14
kingdom sound የዝማሬ ህብረት የተዘመሩ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ዝማሬዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን button ተጭነው ይቀላቀሉ
kingdom sound የዝማሬ ህብረት የተዘመሩ አዳዲስ እና ቆየት ያሉ ዝማሬዎችን ለማግኘት ከታች ያለውን button ተጭነው ይቀላቀሉ
6
15
🎧📖 የድምፅ ጥናት በቅርቡ ይጀምራል! ውድ የ📖 ቃሉን እንማር ቤተሰቦች፣ ቀደም ሲል ከእኛ ጋር በተገናኘው ጥያቄ መሠረት፣ የጀመርነውን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለሁሉም ተደራሽ ለማድረግ የድምፅ ጥናት እንደምንጀምር ገልጸን ነበር። አሁን ደግሞ ይህንን ቃል ወደ ተግባር እያስገባን ነው። 🙏 📅 ከሚመጣው ሳምንት ጀምሮ የጥናታችንን ይዘት በድምፅ መልክም ማቅረብ እንጀምራለን። 🎧 📖 የጽሑፍ ጥናታችን ግን እንደቀድሞው ይቀጥላል። የምዕራፍ ማብራሪያዎችን በጽሑፍ እያጋራን እንቀጥላለን፤ ከዚህ በተጨማሪም ተመሳሳዩን ይዘት በድምፅ ለመስማት የሚፈልጉ አማራጭ ያገኛሉ። 🎧 የድምፅ ጥናቱም ከዘፍጥረት 1 ጀምሮ ያለፉትን ምዕራፎች በማካተት ይዘጋጃል፣ እና ከአሁን በኋላ ከሚቀጥሉት ምዕራፎች ጋርም አብሮ ይጓዛል። ዓላማችን ቃሉን ማንበብ፣ መስማት፣ መረዳት እና በሕይወት መተግበር ለሚፈልግ ሁሉ ይህንን ጉዞ ተደራሽ ማድረግ ነው። 📖❤️ 🔔 STAY TUNED! ከሚመጣው ሳምንት ጀምሮ ቃሉን በሁለት መንገድ አብረን እንከተላለን፦ 📖 በጽሑፍ — እናነባለንና እናጠናለን። 🎧 በድምፅ — እንሰማለንና እንማራለን። አንድ ቃል፣ አንድ ጉዞ፣ ለሁሉም ተደራሽ። ❤️ 📖 ቃሉን እንማር በየቀኑ አንድ እርምጃ ወደ እግዚአብሔር 🙏
162
16
📢 የስም ለውጥ እና የመርሃ ግብሩ ማስታወቂያ ውድ የቃሉ ቤተሰቦች፣ የቻናላችንን ስም ከ“ቃሉን አነባለሁ” ወደ “📖 ቃሉን እንማር” መቀየራችንን አስመልክቶ አስፈላጊውን ማብራሪያ ልንሰጣችሁ ወደድን። የቀድሞው ስም ከሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተክርስቲያን ጋር በተያያዘ በሚካሄደው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ መርሃ ግብር ጋር ተመሳሳይ ስለነበር፣ በሁለቱ መርሃ ግብሮች መካከል ግራ መጋባት እየተፈጠረ ነበር። በተለይም የቻናሉን ዓላማ፣ አስተዳደር እና የመርሃ ግብሩን ምንነት በግልጽ ለመለየት የተለየ ስም መጠቀም አስፈላጊ ሆኗል። በመሆኑም “📖 ቃሉን እንማር” የሚለውን አዲስ ስም መርጠናል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📖 ምን ተቀየረ? የተቀየረው የቻናሉ ስም ብቻ ነው። የጀመርነው የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብና ጥናት መርሃ ግብር አልተቀየረም። ከዘፍጥረት እስከ ራእይ ቃሉን በተከታታይ ለማንበብ፣ ለመማር፣ ለመረዳትና በሕይወታችን ለመተግበር የጀመርነው ጉዞ በቀጣይነት ይቀጥላል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🎯 የመርሃ ግብሩ ዓላማ 📖 መጽሐፍ ቅዱስን በተከታታይ ማንበብ 🔎 የምናነበውን ቃል በቀላሉ መረዳት 💡 ከየምዕራፉ ዋና ትምህርቶችን መለየት ❤️ የተማርነውን በዕለት ተዕለት ሕይወታችን መተግበር 🤝 አብረን በእግዚአብሔር ቃል ማደግ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚 የምንጓዝበት መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን መጻሕፍት በተከታታይ እየተጓዝን ከዘፍጥረት → ራእይ እንደርሳለን። በየምዕራፉም የምናነበውን ቃል በመመርመር ዋና ሐሳቦችን፣ ትምህርቶችን እና ከሕይወታችን ጋር የሚያገናኙንን ነጥቦች እንመለከታለን። 👥 ለማን ነው? ይህ ጉዞ ለወጣቶች ብቻ ወይም ለአዋቂዎች ብቻ አይደለም። 👦 ለታዳጊዎች 👩‍🎓 ለወጣቶች 👨‍👩‍👧‍👦 ለቤተሰቦች 🙏 ለአማኞች 📖 እና የእግዚአብሔርን ቃል በቁም ነገር ማወቅ ለሚፈልግ ሁሉ ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🔔 STAY TUNED | ይከታተሉን በቀጣይ የምንማራቸውን ምዕራፎች፣ የምዕራፍ ማብራሪያዎችን እና ተጨማሪ የቃሉ ጥናቶችን እናጋራለን። 📌 ቻናሉን ይቀላቀሉ፣ ሌሎችንም ይጋብዙ፤ ይህንን ጉዞ አብረን እንጓዝ። 🔗 የቻናሉ ሊንክ: https://t.me/kalun_anebalew ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📖 ቃሉን እንማር “ቃልህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴም ብርሃን ነው።” — መዝሙር 119፥105 በየቀኑ አንድ እርምጃ ወደ እግዚአብሔር 🙏 #ቃሉንእንማር #BibleStudy #BibleReading #የመጽሐፍቅዱስጥናት #የእግዚአብሔርቃል #ChristianLife #BibleJourney
155
17
📖 ዘፍጥረት 8 — ውኃው ቀነሰ ኖኅም ከመርከቡ ወጣ ዘፍጥረት 7 ላይ የጥፋት ውኃ ምድርን ሸፍኖ ነበር። በዘፍጥረት 8 ግን ውኃው መቀነስ ይጀምራል፣ ኖኅና ቤተሰቡም ከመርከቡ የሚወጡበት ጊዜ ይደርሳል። 🌿 1. እግዚአብሔር ኖኅን አስታወሰ “እግዚአብሔርም ኖኅን አሰበው” ይላል። ይህ ማለት እግዚአብሔር ኖኅን ረስቶት ነበር ማለት አይደለም። ይልቁንም ኖኅንና በመርከቡ ውስጥ ያሉትን ሁሉ እየጠበቀ እንደነበር ያሳያል። እግዚአብሔርም ነፋስ አሳለፈ፤ ውኃውም መቀነስ ጀመረ። 🌊 2. ውኃው ቀነሰ የጥልቁ ውኃ ምንጮችና የሰማይ መስኮቶች ተዘጉ። ዝናቡም ቆመ። ውኃው ቀስ በቀስ እየቀነሰ ሄደ። መርከቡም በአራራት ተራሮች ላይ ቆመ። 🕊️ 3. ኖኅ ወፎችን ላከ ኖኅ ምድር ደርቃ እንደሆነች ለማወቅ መጀመሪያ ቁራ ላከ። ከዚያም ርግብን ላከ። ርግቡ የምታርፍበት ቦታ ስላላገኘች ወደ ኖኅ ተመለሰች። ከሰባት ቀን በኋላ እንደገና ላካት። በዚህ ጊዜ በአፏ የወይራ ቅጠል ይዛ ተመለሰች። 🌿 ይህም ውኃው ከምድር ላይ እየቀነሰ መሆኑን ኖኅ እንዲያውቅ ረዳው። እንደገና ሌላ ሰባት ቀን ጠበቀ፣ ርግቡንም ላከ። በዚህ ጊዜ ግን ወደ እርሱ አልተመለሰችም። 🚪 4. እግዚአብሔር ኖኅን ከመርከቡ እንዲወጣ አዘዘው በመጨረሻ ምድር ደረቀች። እግዚአብሔርም ኖኅን፣ ሚስቱን፣ ልጆቹንና የልጆቹን ሚስቶች ከመርከቡ እንዲወጡ ነገራቸው። እንስሳቱም ሁሉ ከመርከቡ ወጡ። ኖኅ ግን በራሱ ውሳኔ ቀድሞ አልወጣም። እግዚአብሔር እስኪነግረው ድረስ ጠበቀ። 🙏 5. የኖኅ የመጀመሪያ ሥራ ከመርከቡ ከወጣ በኋላ ኖኅ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ። ከንጹሕ እንስሳትና ከንጹሕ ወፎች ወስዶ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት አቀረበ። ይህ ኖኅ ከታላቁ መዳን በኋላ ያደረገው ነገር ምስጋናና አምልኮ መሆኑን ያሳየናል። 🌈 6. እግዚአብሔር የሚቀጥለውን ተስፋ አሳየ እግዚአብሔር ምድርን እንደገና በጥፋት ውኃ እንደማይመታት ወሰነ። እንዲሁም ምድር እስካለች ድረስ ዘርና መከር፣ ብርድና ሙቀት፣ በጋና ክረምት፣ ቀንና ሌሊት እንደማይቋረጡ ተናገረ። 💡 ዋናው ትምህርት ዘፍጥረት 8 ከእኛ ጋር ብዙ ነገር ያካፍላል፦ • በረዥም መጠበቅ ውስጥም እግዚአብሔር አይረሳንም። • እግዚአብሔር የሚያዘገየው ሁሉ ትቶን ስለሄደ አይደለም፤ ጊዜውን ያውቃል። • ኖኅ ከመርከቡ ለመውጣት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠበቀ። • ከመዳን በኋላ የመጀመሪያው ምላሽ ምስጋናና አምልኮ ነበር። ❤️ አንዳንድ ጊዜ በሕይወታችን ውስጥ እንደ ኖኅ በመርከብ ውስጥ እንዳለን ሊሰማን ይችላል። መውጫውን አናይም፣ መቼ እንደሚያበቃም አናውቅም። ዘፍጥረት 8 ግን ያስታውሰናል፤ እግዚአብሔር ኖኅን እንዳልረሳው እኛንም አይረሳንም። 🙏 የማሰላሰያ ጥያቄ በሕይወቴ ውስጥ እየጠበቅሁት ያለ ነገር ቢኖር፣ እግዚአብሔር ጊዜውን እስኪያመጣ በትዕግሥት መጠበቅ እችላለሁን? 📖 የዛሬ ንባብ፦ ዘፍጥረት 8 @kalun_anebalew
155
18
+3
بدون متن...
192
19
🙏❤️ ውድ የቃሉን አነባለሁ ቤተሰቦች፣ ዛሬ በተለያዩ ሥራዎችና በብዙ የተጠመድንባቸው ነገሮች ምክንያት የዕለቱን የቃል ጉዞ በተያዘለት ጊዜ ማቅረብ ስላልቻልን ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን። 🙏 ይህ ጉዞ የእኛ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ነው። 📖❤️ እያንዳንዱ ምዕራፍ እንድናነበው፣ እንድንማርበትና ቃሉን ወደ ሕይወታችን እንድናመጣው ነው የጀመርነው። 🌿 እና አሁን አንድ ነገር ከእናንተ ጋር ማካፈል እንፈልጋለን። በልባችሁ የእግዚአብሔር ቃል ያለ፣ ለጌታ ማገልገል የምትፈልጉ እና ከእኛ ጋር ይህን የቃሉን ጉዞ ለማገዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ ወንድሞችና እህቶች ካላችሁ፣ እንፈልጋችኋለን። ❤️🙏 አገልግሎት ማለት ትልቅ መድረክ ላይ መቆም ብቻ አይደለም። አንድ ሰው ቃሉን እንዲሰማ፣ እንዲያነብ፣ እንዲረዳ ማገዝም አገልግሎት ነው። 🎧 በተለይም የቃሉን ጥናት በድምፅ ለማቅረብ፣ ይዘት ለማዘጋጀት፣ ለማስተካከል ወይም በሌላ መንገድ ለማገልገል ፍላጎትና ልብ ያላችሁ ከሆነ፣ እንድትገናኙን እንጋብዛችኋለን። ቃሉን ከእኛ ጋር አድሚን ሆኖ ለማስጠናት ከስር ባለው አድራሻ ያግኙኝ 👇 📩 @mr_dani10 “ለእግዚአብሔር ማገልገል በልባችሁ ካለ፣ ለምን ከእኛ ጋር አትጀምሩም?” 🙏 እግዚአብሔር ይባርካችሁ። 📖 ቃሉን አብረን እንማር፣ አብረንም እናገልግል። ❤️
188
20
🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ አሁን በዳምጣው የምትሉትን መርጣው "Join" ያድርጉ 🙏🙏
23