6 328
مشترکین
-124 ساعت
-67 روز
+2030 روز
آرشیو پست ها
6 328
"ስር ነቀል ለውጥ" (The term used most of the time) ከቃል ወደ ተግባር ለመቀየር ዘርፈ ብዙ የጤና ባለሞያዎች ጥያቄ በግልጽና ቅደም ተከተል መፍትሔ ሊያገኝ ይገባል።
በኢትዮጵያ ስር ነቀል የጤና ለውጥ ለማምጣትና የሕዝቡን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በተግባር ለመመለስ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባው የባለሙያዎችን ጥያቄ ነው።
የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ የአንድ የሞያ ሴክተር የጥቅም ጥያቄ ብቻ ሳይሆን የሀገር ልማትና የሕዝብን የኑሮ ጥራት በቀጥታ ይሁን በተዘዋዋሪ የሚነካ መሠረታዊ ጥያቄ ነው።
ባለሙያው ተገቢው መብቱና ጥቅሙ ተጠብቆ ካልሠራ ጠንካራ ተቋምና የበለፀገች ሀገር መገንባት አይቻልም።
የጤና ባለሙያዎች ጥያቄ መፍታት የሀገር ዕድገት መነሻ ነው። ለሕዝብ የሚቆረቆር የመንግስት አካል መጀመሪያ ለሕዝቡ የሚያገለግሉትን ባለሙያዎች መብት ማስከበር እንዲሁም የሚገባቸው ጥቅማ ጥቅሞች ግዜውና የኑሮ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ማሻሻያ ማድረግ አለበት።
ዶ/ር ንጉስ አበበ: Internist
6 328
⬆ የጤና ባለሙያዎች ትርፍ ሰዓት መመሪያ
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የጤና ተቋማት ሠራተኞች ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጭ ለሚሰጡት አገልግሎት የሚፈጸመውን የክፍያ አፈጻጸም ረቂቅ መመሪያ ካቢኔው አጽድቆ በሥራ ላይ እንዲውል አድርጓል።
6 328
የአማራ ህክምና ማህበር ለተለያዩ ተቋማት/ለክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ለክልሉ ጤና ቢሮ፣ለሲቭል ሰርቪስና የሰው ሀብት ኮሚሽን፤ለክልሉ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ፤ለኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም(ባህርዳር ቅርንጫፍ)፣ለክልሉ ፍትሕ ቢሮ፣ለአማራ ሚዲያ ኮርፐሬሽን/ስለ ጤና ባለሙያዎች የ2018 ዓ.ም ያልተከፈለ ዱቲና ስለ አዲሱ የሰው ሀይል ስምሪት ይፋው ደብዳቤ ፅፏል።
6 328
Call for Participation – Peaceful Advocacy for Clear Answers
Dear Colleagues,
The EHPM Team is planning to initiate a peaceful advocacy effort to seek tangible and appropriate responses to our 12 clearly defined questions. To support the EHPM Board in this process, we intend to form a small but strong working group.
We invite health professionals who are currently General Practitioners (GPs), residents, senior physicians, or other expert health professionals to contact us. Together, we will proceed accordingly. @HPs0005
This is a completely peaceful struggle aimed at obtaining legal, concrete answers to survival-related questions that we have clearly outlined.
United we stand, divided we fall!
6 328
Heart attack
ወይም Acute Myocardial Infarction ይባላል
የሚከሰተው ወደ ልብ የሚሄደው የደም ስር ድንገት በደም መርጋት (thrombus) ምክንያት ሲደፈን እና ለልብ ጡንቻዎች በቂ ኦክስጅን ሳያገኙ ቀርተው የልብ ህዋሳት (cells) ሲሞቱ ነው።
መንስኤዎች እና ለአደጋ የሚያጋልጡ ሁኔታዎች
ለውጥ ልናደርግባቸው የማንችላቸው
[ ] እድሜ መጨመር
[ ] ወንድ መሆን
[ ] በቤተሰብ ውስጥ የልብ ህመም ታሪክ መኖር
በተገቢው እንክብካቤ እና ህክምና መቀየር የሚቻሉ
[ ] ሲጋራ ማጨስ
[ ] የደም ግፊት ህመም
[ ] የስኳር ህመም
[ ] በደም ውስጥ የኮሌስትሮል መጠን መጨመር (High LDL)
[ ] ከባድ የሰውነት ክብደት (ወፍራምነት)
[ ] እንቅስቃሴ አለማድረግ
[ ] ጤናማ ያልሆነ አመጋገብ
[ ] የዘለቀ የኩላሊት ህመም (Chronic kidney disease)
[ ] የነርቭ እና የአእምሮ ውጥረት (Stress)
ምልክቶች
[ ] በደረት መካከለኛ ክፍል ላይ ከ20 ደቂቃ በላይ የሚቆይ ከባድ የማቃጠል ወይም የመጫን ስሜት
[ ] ወደ ግራ እጅ፣ መንጋጋ፣ አንገት ወይም ጀርባ የሚሰራጭ ህመም
[ ] ከፍተኛ ላብ ማውጣ
[ ] ትየትንፋሽ እጥረት
[ ] ማቅለሽለሽ ወይም ማስታወክ
[ ] ራስን ማዞር ወይም ራስን ስቶ መውደቅ
ምርመራ
ECG (የልብ ምት ምርመራ): ታካሚው እንደደረሰ በ10 ደቂቃ ውስጥ የሚደረግ
High-sensitivity cardiac troponin: የልብ ጉዳትን ለማወቅ የሚደረግ የደም ምርመራ
Echocardiography (የልብ አልትራሳውንድ)Coronary
angiography: የተዘጋውን የልብ ደም ስር ለመለየት የሚደረግ ምርመራ
ህክምናው (ESC 2023 guideline)
በመጀመሪያ ደረጃ የሚደረግ (ፈጣን እርምጃ)
በአስቸኳይ የአደጋ ጊዜ ህክምና (አምቡላንስ) መጥራት
Aspirin 150–300 mg ማኘክ
የኦክስጅን መጠን ከ 90% በታች ከሆነ ኦክስጅን መስጠት
ለከባድ ህመም ማስታገሻ የሚሆን መድኃኒት (ለምሳሌ Morphine) መስጠት
የተዘጋውን ደም ስር የመክፈት ህክምና (Reperfusion)
Primary PCI (በካቴተር ደም ስር መክፈት)ተመራጭ እና በተቻለ ፍጥነት መደረግ ያለበት ህክምና ነው።PCI በቅርብ ማግኘት ካልተቻለ፣ ደም የሚያቅልጡ መድኃኒቶችን (Fibrinolysis) መስጠት እና ወዲያውኑ ወደ PCI ማዕከል ማዛወር።
በመድኃኒት ህክምና (secondary prevention )
Dual antiplatelet therapy
የኮሌስትሮል መድኃኒት (High-intensity statin)
Beta-blocker እና ACE inhibitor/ARB እንደ አስፈላጊነቱ
መከላከል
🚭 ሲጋራ ማጨስን ማቆም
🩺 የደም ግፊትን ቁጥጥር ስር ማድረግ
🍳 የኮሌስትሮል መጠንን መቀነስ
🏃♂️ ዘወትር አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ (በሳምንት ቢያንስ 150 ደቂቃ)
🥗 ጤናማ አመጋገብ መከተል
⚖️ ትክክለኛ የሰውነት ክብደትን መጠበቅ
🍷 የአልኮል መጠጥ መቀነስ እና ከአደንዛዥ ዕፆች መራቅ
💊 የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መውሰድ
🏥 ከህክምና በኋላ የልብ ማገገሚያ (Cardiac rehabilitation) ፕሮግራሞችን መከታተል
በቀጣይ ምን ይዘንላቹ እንምጣ ? comment ፃፉልን
ይህ ና መሰል ሕክምና የምታገኙበት ቦታ እንጠቁማቸዋለን DM አርጉልን
6 328
አንድ ሃኪም ለሁሉም ሃኪም፣ ሁሉም ሃኪም ለአንድ ሃኪም። We leave Noone behind!
በአንድነት በመስራት እንጂ በመቃቃር የሚመጣ ለውጥ የለም።
ይህን ሃኪም እንደሌሎቻችሁ ከሶሻል ሚዲያ ውጪ አንተዋወቅም፣ ነገር ግን በተለያዩ ሃኪሞች ጡጫ ሲዘነዘርበት አይቼ ምን አጥፍቶ ይሆን ብዬ ተመለከትኩ። ከዚህ በፊት በኮሮና ጊዜ፣ የሬዚደንት ሃኪሞች በደል ጊዜ እንዲሁም የህክምና ጥራትና የህክምና ባለሞያ የጥቅማጥቅም እንዲከበር ስንሞግት ሁላችንም በቻልነው መጠን አንድ ላይ ድምፅ ሆነናል። አሁን ይህን ሃኪም በተመለከተ በምትዘነዝሩት ቡጢ ግን ፈፅሞ ከጎናችሁ ልንቆም አንችልም። ምክንያቱም እሱም ወንማችን ሃኪም ነው።
ከዚህ ቀደም ሃኪም እንዲከበር፣ እንዲደመጥ፣ ተገቢውን የህዝብ ትኩረት እንዲያገኝ ብሎም ደግሞ ተፅእኖ ፈጣሪ እንዲሆን ስንሞግት ከርመናል። ይሄም ልጅ በገባው መንገድ ዘመኑን ዋጅቶ ሶሻል ሚዲያን ሰንጥቆ በመግባት ከመንግስት ሆስፒታል ጀምሮ ቀጥሎም የግሉን ተቋም በማቋቋም በስፔሻሊቲው መንገድ ተፅእኖ ለመፍጠር ሞክሮየቻለውን ያህል ተሳክቶለታል። ታዲያ አብዛኛው የኛ ቡጢ ሰንዛሪ ሃኪም ያልገባው ነገር ወደድንም ጠላንም ዘመኑ የሶሻል ሚዲያ እንደሆነና ሶሻል ሚዲያው ደግሞ የሚፈልገው የራሱ የሆነ አካሄድ አለው። ለምሳሌ ይሄ ዶክተር ከህፃናት ጋር ቢጨፍር እንዲሁም የመሳሰሉትን በህክምናው አለም ያልተለመዱ ተግባራትንና እራስን አጉልቶ ማሳየትን ቢጠቀም፤ ይህ ሶሻል ሚዲያውን ጠርምሶ ለመግባትና በዚህ ዘመን ተፅእኖ ለመፍጠር የግድ አስፈላጊ ስለሆነ ነው።
ይሄ ሃኪም የራሱን ስራ ከመስራትና ፕሮሞት ከማድረግ ውጪ ማንኛችሁንም ሲተች አላየሁትም። እንደሆነም ሀ እና ለ ን ሳይለዩ ሶሻል ሚዲያውን የተቆጣጠሩትን ግለሰቦች ተጋፍቶ ትንሽ መውጣት የቻለ ብቸኛ የሞያ አጋራችንና ወንድማችን ነው። አስቸጋሪ የሆነውን የህክምና ትምህርት ተቃጥሎ ከነስፔሻሊቲው ያጠናቀቀ ባለሞያም ነው። እውነት እንነጋገር ከተባለ ደግሞ በተመደበበትም ቦታ በትጋት አገልግሎ የጨረሰም ነው። ታዲያ ይሄ ሁሉ ቡጡ እሱ ላይ ለምን?
ይህ ሃኪም እዚህ የደረሰው በወሬ ብቻ ቢሆን ኖሮ እኮ ሁሉም ያን ባደረገ ነበር። በህክምና ትምህርቱም በሶሻል ሚዲያውም ጠንክሮ ዘመኑን በመዋጀት ስለሰራ ስኬታማ መሆን ችሏል። ጥሎብን ደግሞ ብዙ ሃበሻዎች የሰው ስኬት አይናችንን ያቀላዋል ትችትና ነቀፌታ ይቀድመናል። ግን እስከመቼ?
በህክምናው ዘርፍ ተገቢው ለውጥ ያልመጣው እርስ በእርስ አንድ ሆኖ ከመቀጠል ይልቅ አንዱ አንዱ ላይ ጣቱን መጠቆምና መመቀኛኘት ስለሚበዛ ነው። ሁላችሁም እዛው ተቀብራችሁ ከምትቀሩ አንድ በአንድም ቢሆን በየተራ መውጣቱ አይሻልም?
ይሄ ሃኪም እኮ ባገኘው እውቅና ከፍ ከፍ ብሎ ትልቅ የህክምና ማእከል ቢገነባ ቀጥሮ የሚያሰራው እኮ ኢትዮጵያዊ ሃኪሞችን ነው። ያ ደግሞ ለህክምናው ዘርፍ እድገት ነው። ይህ ሃኪም የሚሰራው ሰርጀሪም ሆነ ሁሉም ህክምና ቢከፈልበት ገንዘብ ቢያገኝበት ሲያንሰው እንጂ አይበዛበትም። የምበላው አጣው፣ ቤቴ ኑሮዩ ተቦሳቆለ ብሎ የሚጮህ ሃኪም ወንድሙ ከፍ ሊል ሲሞክር ወደታች ካልጣልኩት ካለ ነገ እሱስ በየት በኩል ይወጣል። ይሄ አንዱ ከፍ ሊል ሲል ተባብሮ የመቅበር መንገድ ሁሉንም እታች ያስቀራል እንጂ የትም አያደርስም። እኛንም ከዚያች ሃገር ያራቀ ይኸው ምቀኝነት ነው። በቅርቡም ከአሜሪካ ሃገር ድረስ ብዙ ሪሶርስ ይዞ እየመጣ የልብ ቀዶ ጥገና ዘመቻ የሚያስተባብር ሃኪም በዚህ ምቀኝነትና እኔ ካልሆንኩ ሌላው አይስራ አይከናወንለት ብለው በሚስቡ ሰዎች ተማሮ በገዛ ፌስ ቡክ ገፁ ላይ የተናገረውን ተመልክቻለሁ። ይብቃችሁ፣ ይሄን ከመተባበር ይልቅ የመቀናቀን እርግማን ከላያችሁ አውልቃችሁ ጣሉ። ለመከበር ማክበርን፣ ለመደነቅ ማድነቅን፣ ለመባረክ መባረክን ተማሩ። ዘሪ የዘራውን ያጭዳል ጨለምተኝነትና ትችትን ብቻ የሚዘራ በጨለማና በትችት ውስጥ ይኖራል።
እንደኔ እይታ ዶር አብይ ታደሰ ለህክምና እና ሃኪም ቦታ በሌላት ሃገርና ሲስተም ውስጥ በገባው መጠን ተፍጨርጭሮ የህዝብን ቀልብ መሳብ የቻለ ሊበረታታ የሚገባው ሃኪም ነው። ስንት ጋጠወጦች በሚሰሙበትና በሚከበሩበት ሶሻል ሚዲያ እሱ ለምን ተንቀሳቀሰ ተብሎ ስቀለው ስቀለው መባል የለበትም። ይልቁንስ ከቻላችሁ ሌሎቻችሁም እንደሱ ዘመኑን ዋጅታችሁ ተንቀሳቀሱ። One Hakim for all, all hakim for one ለዶክተር አብይ ታደሰም ይሰራል። በእውነቱ ደግሞ ልጁ የራሱን ስራ ከመስራት ውጪ ማንንም ሲተችና ሲነቅፍ አላየሁትም። እራስን መሸት ጥፋት ለሚመስላችሁ ወንድሞቻችን ደግሞ በዚህ ዘመን እራስን መሸጥ self promotion ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው።
እና ምን ለማለት ነው፣ ኔጌቲቪቲ ትተን በነገር ሁሉ ፖዘቲቭ እንሁንና ተያይዘን የኢትዮጵያ ሃኪምንና የህክምና ዘርፍን ከፍ ከፍ እናርግ። የመበላላትና የመጠላለፍ መንገድ ለማንም አይበጅም።በሱ ስኬት የሃኪምን ስኬት ተመልከቱ እንጂ፣ የሱ እውቅና ከናንተ የሚቀንሰው ነገር የለም። በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ ደግሞ የሞያ ባልደረባን እንጥል አውራጅ፣ ጉሮሮ ቧጣጭ ምናምን እያሉ ለማሸማቀቅ መሞከር እጅግ የወረደ ቦታ የሚያሰጥ ነው። አንድ ጠጠር ሳያነሱ በራሱ ገንዘብና አቅም ብዙ ህፃናትን የነፃ ህክምና ዘመቻ ሰራሁ ያለን ሰው መሳደብ የሞራል እንዲሁም የስነልቦና ውድቀት ምልክት ነው። እናንተ ስንት የነፃ ዘመቻ በራሳችሁ ቁስ አደረጋችሁ። የሌላውን ትታችሁ የራሳችሁ ስኬትን ለምን አትነግሩንም። እውነቱን ለመናገር ሁላችሁም እንደሱ ታዋቂና ብዙ ተከታይ ያላችሁ መሆን ትፈልጋላችሁ። እድሉንም ብታገኙ ወደኋላ አትሉም። በሌላው ነገር አብረን ድምፅ እንደሆነው ወንድማችሁን ለመቅበር ስትታገሉ ግን አብረናችሁ አንቆምም። ይልቁንስ ከዚህ የሚደብርና አሳፋሪ ተግባር ተመለሱ እንላችኋለን። ምክንያቱም አንድ ሃኪም ለሀሉም ሃኪም ሁሉም ሃኪም ለአንድ ሃኪም ተባብለናል። ሁላችንም ለአንዱ ሃኪም ዶር አብይ እንቆምለት ይገባል። Remember , We will not leave anyone behind
እኔ ግን እልሃለሁ ከዚህ የበለጠ በርታ፣ ጠንክር ፣ወደፊትም ገስግስ። ከሰው ስህተት አይጠፋምና ስተትህን ለመማሪያነት ብቻ ተጠቀመው እንጂ በትንሽ ስህተት ሊቀብሩህ የሚሞክሩትት ጆሮ ሳትሰጥ ወደፊት ገስግስ። በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለምም ተፅእኖ የሚፈጥር ትልቅ ማዕከል ለመገንባት አልም፣ አሁን እንደጀመርከው ከመቶዎች አልፈህ ለሺ ህፃናት ድረስ።
ዶር አብርሃም ታሪኩ
6 328
"በ 2 ቀናት የጤና ሚኒስተር ስብሰባ ወቅት ጥያቄዎቻችንን በድጋሚ አቅርበናል ግን አጥጋቢ ምላሽ አሁንም አልተሰጠንም።"
ከተሰብሳቢዎች
6 328
Call for Participation – Peaceful Advocacy for Clear Answers
Dear Colleagues,
The EHPM Team is planning to initiate a peaceful advocacy effort to seek tangible and appropriate responses to our 12 clearly defined questions. To support the EHPM Board in this process, we intend to form a small but strong working group.
We invite health professionals who are currently General Practitioners (GPs), residents, senior physicians, or other expert health professionals to contact us. Together, we will proceed accordingly.at telegram👉 @HPs0005
This is a completely peaceful struggle aimed at obtaining legal, concrete answers to survival-related questions that we have clearly outlined.
United we stand, divided we fall!
6 328
#የታገቱ_ባለሙያዎች_እንዲለቀቁ ተጠየቀ
የደባት የመጀመሪያ ሆስፒታል ጤና ባለሞያዎች ና ተገልጋይ ህዝብ የታገቱ ባለሙያዎች እንዲለቀቁ በሆስፒታሉ በመገኘት ጠየቀ።
6 328
+1
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ለተመጣጣኝ ክፍያ አገር አቀፍ ንቅናቄ ና ስራ ማቆም አድማ በዝግጅት ላይ
የሀገሪቱ የጤና ሥርዓት የጀርባ አጥንት የሆኑት የኢትዮጵያ ሐኪሞች፣ ነርሶች እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች በተባበረ ጥምረት፤ ያልተፈቱ ቅሬታዎችን እና የሥራ ሁኔታዎችን እንዲሁም በጤና ባለሙያዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ችግር ለመፍታት ግንቦት 5 ቀን 2018 ዓ.ም በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ ታላቅ ንቅናቄ ለማድረግ ተዘጋጅቷል ። ይህ እርምጃ ለረጅም ጊዜ ለቆዩ እና ምላሽ ላልተገኘላቸው የሥራ ሁኔታ እና የኑሮ ውድነት ጥያቄዎች የተሰጠ ቀጥተኛ ምላሽ ባለመኖሩ ነው
ዋነኛ ጥያቄዎች
የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር እና የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ለሚከተሉት ወሳኝ ጉዳዮች አፋጣኝ እና ተጨባጭ መፍትሄዎችን እንዲሰጡ እንጠይቃለን
ፍትሃዊ እና ወቅታዊ Duty ክፍያ፡
ሥር የሰደደ የክፍያ መዘግየት እንዲቆም እና ለትርፍ ሰዓት እንዲሁም ለፈረቃ ሥራዎች ደረጃውን የጠበቀ እና ፍትሃዊ የሆነ የክፍያ ሥርዓት እንዲተገበር።
የተጋላጭነት አበል እና የቤት አበል፡ ከሥራው አስቸጋሪነት ጋር የሚመጣጠን የሙያ ስጋት አበል እና ወቅታዊውን የኑሮ ውድነት ያገናዘበ የቤት አበል እንዲተገበር።
አስተማማኝ የሥራ አካባቢ፡
ሁሉም የጤና ተቋማት የባለሙያዎችን እና የሕመምተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስፈልጉ ግብዓቶች እንዲሟሉላቸው ማድረግ።
የ"ቶፕ አፕ" (Top-Up) ማስተካከያ፡ የሁሉንም የጤና ባለሙያዎች የደመወዝ ስኬል እና የ"ቶፕ አፕ" ጥቅማጥቅሞች ክለሳ እንዲደረግ።
6 328
የመጋቢት ማለቂያ ፀሐይ የሆስፒታሉን ኮሪደር አቋርጣ ፊቴ ላይ ታርፋለች። እኔ ግን ብርሃኑ ሳይሆን የሚሰማኝ የውስጤ ጨለማ ነው። ስሜ ዶክተር X ይባላል—ወይም ደግሞ በሽተኞቹ እንደሚጠሩኝ "ጋሽ ሐኪም"። አራት ልጆች፣ አንዲት ሚስት እና ሰባ ሁለት ካሬ ሜትር የማትሞላ የጭቃ ክራይ ቤት ባለቤት ነኝ። በዓል ደርሷል። ለሰዎች በዓል ማለት ደስታና ጭብጨባ ነው፤ ለኔ ግን በዓል ማለት የጭንቀት ጋሬጣ፣ የልጆች አይን ማየት የሚያስፈራበት የምፃት ቀን ነው።
ትላንት ማታ ታናሽ ልጄ እግሬ ስር ተጠምጥሞ "አባዬ ለፋሲካ ያቺን መብራት የምታበራ ጫማ ትገዛልኛለህ?" ሲለኝ፣ ምላሴ ተሳሰረ። "እግዚአብሔር ካለው እገዛልሃለሁ" አልኩት። "እግዚአብሔርማ አለው አባዬ፣ አንተ ነህ የሌለህ" አለኝ በህፃን አንደበቱ። ልቡን ሳይሆን የኔን ማንነት ነበር የሰበረው።
ኪሴን ዳሰስኩት። ባዶ ነው። የሰባት ወር የduty (ተረኛ) ክፍያዬ በሆስፒታሉ ፋይናንስ ክፍል ወረቀት ላይ ሰፍሮ ቀርቷል። ሰባት ወር! ሰባት ወር ሙሉ ሌሊቱን ስገተር አድሬ፣ የሰውን ህይወት ስታገል ቆይቼ፣ የራሴን ልጆች ህይወት ግን መምራት አቅቶኛል።
ሆስፒታሉ ውስጥ ያለው ሽታ የኬሚካልና የቆሸሸ ፋሻ ብቻ አይደለም፤ የተስፋ መቁረጥ ሽታም ጭምር ነው። ወደ አስተዳደሩ ቢሮ ሄድኩ። ስራ አስኪያጁ በለሰለሰ ወንበራቸው ላይ ተደላድለው ስልክ ያወራሉ። ስለ በዓል በግ ግዥና ስለ ቤተሰብ ሽርሽር ያወራሉ።
የሰባት ወር ክፍያችንስ? ስል ጠየቅኩ። ቀና ብለው በንቀት አዩኝ። "ዶክተር፣ አገር ያለችበት ሁኔታ ይታወቃል። በጀት አልመጣልንም። ለምን ትንሽ ትዕግስት አይኖርህም? ደግሞም አንተኮ የሰው ህይወት የምታድን ባለሙያ ነህ፣ ስለ ገንዘብ ብቻ ማሰብ አይገባህም" አሉኝ።
ይህች ናት መደበቂያቸው! "ሰብአዊነት" የሚባለውን ቃል እንደ ሰንሰለት ይጠቀሙበታል። እኔ ሰብአዊነት ካለኝ ልጆቼ ለምን ይራባሉ? እኔ ሰብአዊነት ካለኝ ለምን በዓልን በለቅሶ አሳልፋለሁ? አስተዳደሩ ይሳለቅብናል፤ የጤና ቢሮው ደግሞ "ጥያቄያችሁ ተገቢ ነው፣ ወደ ላይ አሳውቀናል" የሚል ያረጀ ቴፕ ይከፍትብናል።
ስልኬን ከፈትኩ። የጤና ሚኒስቴር ገፅ ላይ የሚኒስትሯ ፎቶ ይታያል። አዲስ ሆስፒታል ሲመረቅ፣ በፈገግታ የታጀበ ሪባን ሲቆረጥ። "የባለሙያዎችን ጥቅም እያስከበርን ነው" የሚል መፈክር ከስር ተፅፏል። ውስጤ በቁጭት ተቃጠለ። እኛ እዚህ በረሃብ አለንጋ እየተገረፍን፣ እነሱ አዲስ አበባ ላይ የፎቶ ፖለቲካ ይሰራሉ።
በአሁኑ ሰዓት ስለ ህክምና ሳይንስ (Science) ማውራት አቁመናል። ድሮ በጠዋት ሪፖርት ላይ ስለ አዳዲስ የህክምና ግኝቶች፣ ስለ ታካሚዎች የጤና ሁኔታ እንከራከር ነበር። ዛሬ ግን የምንከራከረው ስለ ሽንኩርት ዋጋ፣ ስለ ቤት ኪራይ ጭማሪ እና "ዛሬ ማንን ብድር ልጠይቅ?" በሚል ጭንቀት ነው።
ሳይንሱ ሞቷል። ባለሙያው በኑሮ ውድነት ናላው ዙሯል። አንድ የቀዶ ጥገና ሀኪም ሆዱ እየጮኸ እንዴት ብሎ ጭንቅላት ይበጥሳል? አንድ ሲስተር የልጆቿ ደብተር መግዣ አጥታ እንዴት ሆና ለታካሚ ፈገግታ ትለግሳለች? መንግስት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ ብሏል። ምንም የተፈጠረ አይመስለውም። ለእነሱ እኛ ቁጥር እንጂ ነፍስ ያለን ሰዎች አይደለንም።
ዛሬም ማታ ተረኛ ነኝ። ለማይከፈል ክፍያ፣ ለውርደት፣ ለድካም። ሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ ቆሜ ወደ ሰማይ አየሁ። ወደ ገጠር ቤተሰቦቼ ደወልኩ። እናቴ "ልጄ፣ በዓል ደርሷል የዘንድሮውን በግ አንተ ትልካለህ ብለን እየጠበቅን ነው" አለችኝ። ድምፄ ተንቀጠቀጠ። "እሺ እማዬ... ይላካል" አልኩ። ውሸት! የነጭ ጋውን ለባሹ ውሸታም ሆኗል።
ቤት ስመለስ ልጆቼ ተኝተዋል። ሚስቴ አይኖቿ ቀልተዋል። "ከየት አመጣዋለሁ?" የሚለው ጥያቄ በቤቱ ግድግዳ ላይ ተፅፎ ይታየኛል። የጤና ባለሙያ መሆን መርገም የሚመስልበት አገር! ህይወት እየሰጠን ህይወታችን የሚቀማበት ሙያ!
አሁን ቁጭቱ ወደ ቁጣ ተቀይሯል። ዝምታችን እንደ ፍርሃት ተቆጥሯል። ነገር ግን የታፈነ እሳተ ገሞራ መፈንዳቱ አይቀርም። ምክንያቱም እኛን የገደለን በሽታ ሳይሆን፣ የአስተዳደሩ ግድየለሽነትና የመንግስት ንቀት ነው።
6 328
ጤና ባለሞያዎች ለDesigners ና Logo makers ሼር አድርጉላቸው
ለ Digital Hakim የሚሆን Logo እንድተሰሩልን በትሕትና እንጠይቃለን🙏
በውስጥ ላኩልን
6 328
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ወቅታዊ ሁኔታ
----------------------------------------------------------
"ለቁርጠኝነት ተጠያቂነት፣ ለታማኝነት ክብር፣ እንዲሁም ለአገልግሎት ፍትህ ሊሰጥ ይገባል።"
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል። ለዓመታት የተበላሸው የጤና ሥርዓት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል ፣ ከፍተኛ የግል እና የሙያ መስዋዕትነት እየከፈልን ሸክሙን ተሸክመናል። በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ዜጎች አስፈላጊውን እንክብካቤ በመስጠት—በቀንም ሆነ በሌሊት፣ ከአቅማቸውን በላይ በሆኑ የጤና ተቋማት ውስጥ እና በከፍተኛ ጫና ውስጥ—ሳይሰለቸን ደክመናል። ሆኖም ለከፈልነው መስዋዕትነት ሁሉ ቸልተኝነት፣ በቂ ያልሆነ ክፍያ እና ተገቢው እውቅና አጥተናል ።
ከእኛ የሚጠበቀው የ24/7 አገልግሎት ቢሆንም፣ ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል ድጋፍ፣ ጥበቃ ወይም ጥቅማጥቅም የለም። ይህ ሁኔታ ዘላቂ ሊሆን አይችልም። ማንኛውም የሰው ኃይል ፍትሃዊ አያያዝ፣ ተገቢ ማበረታቻ እና ክብር ያለው የሥራ አካባቢ ሳይኖር እንዲህ ያለውን ጫና ለዘላለም ሊንቋቋም አንችልም።
በቅን ልቦና እና ገንቢ በሆነ መንገድ ለመነጋገር በማሰብ፣ 12 ግልጽ እና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ጥያቄዎችን ለመንግስት አቅርበን ነበር። እነዚህ ጥያቄዎች የእኛን የባለሙያዎችን ፍላጎት ብቻ ሳይሆን፣ ውጤታማ እና ጠንካራ የጤና ሥርዓት እንዲኖር የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ጉዳዮችንም ያካተቱ ናቸው። ጥያቄዎቹ የፍትሃዊ ክፍያ፣ የሥራ አካባቢ ደህንነት፣ ጥቅማጥቅሞች ፣ የሙያ እድገት እና ለምንጫወተው ወሳኝ ማህበራዊ ሚና የሚገባውን ክብር የሚመለከቱ ናቸው።
ሆኖም ግን፣ እስከ ዛሬ ድረስ ምንም አይነት አጥጋቢ ምላሽ አልተሰጠም።
ለፍትሃዊ ጥያቄዎች ምላሽ ሳይሰጡ ዝም ማለት ገለልተኝነት ሳይሆን ቸልተኝነት ነው። እርምጃ አለመውሰዱ መፍትሄዎችን ከማዘግየቱም በላይ የጤና ባለሙያዎች የሚገኙበት ሁኔታ ይበልጥ እንዲባባስ አድርጓል። ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ ሌሎች የመንግስት ሰራተኞች የሚያገኟቸው ጥቅማጥቅሞች እና ማሻሻያዎች እኛን እንደማይመለከቱ ተደርጎ መታሰቡ በመንግስት አገልግሎት ዘርፍ ውስጥ ያለውን ኢ-ፍትሃዊነት እና ቅሬታ ይበልጥ አጉልቶታል ።
ከቀረቡት 12 ጥያቄዎች መካከል አንዳቸውም ቢሆኑ እስካሁን ተገቢውን ምላሽ አላገኙም።
ይህ የባለሙያዎች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን አገራዊ አሳሳቢ ጉዳይ ነው። የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ ሲያጡ፣ አጠቃላይ የጤና ሥርዓቱ አደጋ ላይ ይወድቃል። የሥራ Burnout፣ የሰው ኃይል ፍሰት (መልቀቅ) እና የተነሳሽነት ማጣት የህክምና አገልግሎቱን ጥራት ይቀንሳሉ፤ የህዝቡን ጤና እና ደህንነትም አደጋ ላይ ይጥላሉ።
እኛ ልዩ መብትን አልጠየቅንም፤ የጠየቅነው ፍትህን ነው።
መንግስት የሚከተሉትን እርምጃዎች እንዲወስድ እንጠይቃለን፦
-እውነተኛ እና አፋጣኝ ውይይት እንዲጀመር፤
ለጥያቄዎቻችን ግልጽ እና ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ፤
-ለጤና ባለሙያዎች የሚሰጠውን ዋጋ የሚያንፀባርቁ ተጨባጭ እርምጃዎች እንዲጀመር
የኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ህዝብን ለማገልገል ያላቸው ቁርጠኝነት እንደጸና ነው።
tiktok: tiktok.com/@digitalhakim2
6 328
ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጀመረው የዱዩቲ አከፋፈል ስርዓት ውጪ 12ቱ ጥያቄዎቻችን በሁሉም የሀገሪቱ ክፍል አልተመለሱም ።
6 328
የዛሬ ዓመት መሬት አንቀጥቅጥ strike ያደረጉ ሬዚደንቶች አሁን ሲኒየር ሆኖአል ፣ ኢንተርኖች ጠቅላላ ሐኪም ሆኖአል ። ያ ወኔያቸው አሁንም አለ ። ቀጣይ Strike ሲኔየሮች ናቸው የሚመሩት ።
