Christ-centered
رفتن به کانال در Telegram
ጤናማ አስተምህሮ ለበሰለ ህይወት መሰረት ነው። እውነት ለአእምሮ፣ ጸጋም ለልብ ብርሃን ነው።
نمایش بیشتر1 767
مشترکین
+524 ساعت
+127 روز
+9930 روز
آرشیو پست ها
1 767
"የታደሰች ቤተክርስቲያን ሁልጊዜም በቃሉ መታደስ አለባት!"(Ecclesia reformata, semper reformanda)
የሰዎች ፋሽን ይቀየራል፣ የዘመኑ ፍልስፍናዎች ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ የባህል ማዕበሎችም ቤተክርስቲያንን ከዚህና ከዚያ ሊያወዛውዟት ይሞክራሉ። ነገር ግን የቤተክርስቲያን ራስ የሆነው ክርስቶስ ያስቀመጠው መሠረት ግን ፈጽሞ አይነድም።
የ16ኛው ክፍለ ዘመን የተሃድሶ ዘመን ታላቅ መፈክር የሆነው "Ecclesia reformata, semper reformanda" የዛሬዋም ቤተክርስቲያን የልብ ትርታ ሊሆን ይገባል!
Ecclesia reformata (የታደሰች ቤተክርስቲያን): ቤተክርስቲያን በታሪክ ውስጥ ከእግዚአብሔር ቃል ውጭ በነበሩ የሰዎች ሥርዓትና ውድቀቶች ውስጥ አልፋ፣ በጸጋውና በቃሉ ብርሃን እንደገና የታደሰች ናት።
Semper reformanda (ሁልጊዜም የምትታደስ): ተሃድሶ በአንድ ወቅት ተጠናቆ የሚቀመጥ ታሪካዊ መዘክር አይደለም። ቤተክርስቲያን በየዕለቱ፣ በየዘመኑ፣ ከራሷ ድክመትና ከዘመኑ እርኩሰት እየነጻች በእግዚአብሔር ቃል ማስተዋል የምትመላለስ ሕያው አካልናት።
ዛሬ ቤተክርስቲያን ከፊቷ ትልልቅ ፈተናዎች ተደቅነዉባታል፤ የሰዎችን ጆሮ ደስ የሚያሰኝ፣ ጊዜያዊ ሞገስ ያለው ትምህርት ከእውነተኛው ወንጌል ጋር ሊቀላቀል ይፈልጋል። የዘመኑ ባህልና ፍልስፍና እንዲህ ኑሩ ብሎ የራሱን መመሪያ ሊጭን ይተጋል።
ነገር ግን መፍትሔው አንድና ብቸኛ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛን! ቤተክርስቲያን ማዕበሉን የምትቋቋመው የሰዎችን አስተሳሰብ በመከተል ሳይሆን፣ ሁልጊዜ ትምህርቷንም ሆነ አኗኗሯን በጽኑ የቃሉ መለኪያ ላይ በመመዘን ነው።
ቤተክርስቲያን የዓለም ብርሃን እንጂ የዓለም መስተዋት አይደለችም። ዛሬም ማሕበረሰባችንንና ራሳችንን መለወጥ የሚችለው የሰዎች ብልሃት ሳይሆን፣ የማያልፈውና ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው።
ቅዱሳን ቃሉን እንመርምር፤ በቃሉ ሐይልም ሁልጊዜ እንታደስ!
@christcentered7
1 767
እግዚአብሔር አብ አስቀድሞ ካወቃቸው፣ ኢየሱስ ክርስቶስን ለመታዘዝ በደሙ ለተረጩትና በመንፈስ አማካይነት ለተቀደሱት፤ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
ስምዖን በረ ዮና🥰
1 767
ይህ ከወ/ዊ ያሬድ አዲሱ መጽሐፍ መግቢያ ላይ የተወሰደው “መጽሐፍ ቅዱስ የመለኮት እስትንፋስ ያለበት” የሚለው ሐረግ ትልቅ ጥንቃቄን የሚጠይቅ ነው። እንዲህ ዓይነቱ አገላለጽ ትክክለኛውን የነገረ መጽሐፍ ቅዱስ መስመር ስቶ፣ ለአላስፈላጊ የተሳሳተ ትርጉም ተጋላጭ የሚያደርግ አደገኛ አሰራር ነው። እርግጥ የወንጌላዊ ያሬድ ጥላሁን ዋና ትኩረት መጽሐፍ ቅዱስ ሰብአዊ ምንጭ ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ አምላካዊ ስልጣንና ምንነት ያለው መሆኑን ማሳየት እንደሆነ ግልጽ ነው። ነገር ግን የተወሰኑ አገላለጾች አውዳቸው ካልተጠበቀ ወይም ቃላቱ በጥንቃቄ ካልተመረጡ ለተሳሳተ ግንዛቤ (Misinterpretation) በር ሊከፍቱ ይችላሉ።
ማወቅ ያለብን "መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሰ መለኮት ያለበት ሳይሆን በራሱ እስትንፋሰ መለኮት መሆኑን ነው"
ልዩነቱ
👉 እስትንፋሰ መለኮት ያለበት» ሲባል (Inspiration as an addition/attribute): መጽሐፉ በራሱ ተራ ሰብአዊ ጽሁፍ ሆኖ፣ የሆነ ቦታ ወይም የተወሰኑ ክፍሎች ላይ ብቻ የመለኮት እስትንፋስ ወይም መንፈስ ተጨምሮበታል እንደማለት ነው። ይህ አመለካከት መጽሐፉ ሙሉ በሙሉ የመለኮት ቃል አይደለም፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል አለበት ወደሚል የተሳሳተ ድምዳሜ ሊወስድ ይችላል።
👉"መጽሐፉ በራሱ እስትንፋሰ መለኮት ነው" ሲባል (Inspiration as the nature/essence): መጽሐፍ ቅዱስ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ሙሉ በሙሉ የተጻፈው በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነትና እስትንፋስ መሆኑን ያመለክታል። እስትንፋሰ መለኮትነቱ የውጭ ተጨማሪ ባህሪ ሳይሆን የመጽሐፉ መሠረታዊ ማንነትና ምንነት (Essence) ነው።
ለምን ይህን ልዩነት ማጉላት አስፈላጊ ሆነ?
👉 የቃሉን ሙሉ ስልጣን (Authority of Scripture) ለማሳየት፡
መጽሐፉ "እስትንፋሰ መለኮት አለበት" ከተባለ፣ ሰዎች የትኛው ክፍል ነው እስትንፋሰ መለኮት ያለው? የትኛውስ የሰው ሐሳብ ነው? እያሉ መጽሐፉን ለመከፋፈልና ስልጣኑን ለማዳከም መንገድ ይከፍታል። "መጽሐፉ በራሱ እስትንፋሰ መለኮት ነው" ሲባል ግን ሙሉው ጽሁፍ የእግዚአብሔር ቃል መሆኑን ያረጋግጣል።
👉 የቃሉን ህያውነት ለማሳየት፡
የእግዚአብሔር እስትንፋስ ያለበት ነገር ህይወት አለው (እግዚአብሔር በሰው አፍንጫ የሕይወት እስትንፋስ እንደተነፈሰና ሰው ህያው ነፍስ እንደሆነ ሁሉ)። መጽሐፍ ቅዱስም በራሱ ህያውና የሚሰራ፣ ሰዎችን የሚለውጥ፣ የሚያንጽና የሚያስመልጥ የእግዚአብሔር ህያው ህልውና የተገለጠበት ቃል ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔር ቃል የተቀላቀለበት ወይም የተጨመረበት ሳይሆን፣ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው የእግዚአብሔር ህያው እስትንፋስ የወጣበት፣ ሙሉ በሙሉ አምላካዊ ስልጣን ያለውና ህይወትን የመለወጥ ኃይል ያለው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
1 767
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ የቅዱሳን አጽም፣ የክርስቶስ መስቀል ስብርባሪ፣ ወይም የቅዱሳን ልብስ ተብለው የሚሸጡና የሚሳለሙባቸውን ነገሮች (Relics) በተመለከተ ካልቪን በ1543 Treatise on Relics በተሰኘው መጽሐፉ ያቀረበው ሂስ እጅግ የሚያዝናና ነበር........
"በየአብያተ ክርስቲያናቱ ያሉትን የክርስቶስ እውነተኛ መስቀል ስብርባሪዎች ብንሰበስባቸው፡ አንድ ትልቅ የመርከብ ጭነት ይወጣቸዋል😁...መጽሐፍ ቅዱስ ግን መስቀሉን አንድ ሰው (ስምዖን የቀሬናው) ብቻ ሊሸከመው እንደቻለ ይነግረናል።"
እንዲሁም ስለ ሌሎች ቅዱሳን አጽሞች ሲናገር፦
"በየካቶሊክ ቤተክርስቲያኑ የተቀመጡትን የመጥምቁ ዮሐንስ ራሶች ብንቆጥራቸው፡ መጥምቁ ዮሐንስ አራት ወይም አምስት ራሶች የነበሩት ይመስላል"😁
1 767
አሁን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያመንን፤ ከእርሱ ጋር ሞተናል፣ ከእርሱም ጋር ተንስተናል፣ ከእርሱም ጋር በሰማያዊ ስፍራ ተቀምጠናል፤ ያመንነው በከንቱ ካልሆነ በቀር በእምነታችን ጸንተን ከክርስቶስ ጋር እንነግሣለን በዚህም የሚመጣውን ዓለም ከክርስቶስ ጋር አብረን እንወርሳለን፤ ይህ ታላቅ ተስፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ አማካኝነት ከእግዚአብሔር ተሰጥቶናልና አጥብቀን እንያዝ፤ ዓይናችንን ከተስፋው የሚያነሱ በዘመኑ መንፈስ የሚመሩ ነገሮችን ሁሉ ወደኋላ እየተውን፤ መከራን፣ ችግርን፣ ክፋትን፣ ስቃይን ሁሉ......ደግሞ እየታገስን፤ በተስፋ ደስተኞች እንሁን።
ከክርስቶስ ጋር አብረን የእግዚአብሔር ወራሾች ነንና!
1 767
"እግዚአብሔር ሆይ፤ የምትኖርበትን ቤት፣ የክብርህን ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።" እንዲል ቃልህ፤ የቅዱሳን ጉባኤ የእግዚአብሔር መንፈስና ልዩ ክብሩ (Shekinah Glory) የሚገለጥበት የጸጋ ማዕከል በመሆኗ፣ ወደ ቤቱ ስንሄድ በእግዚአብሔር ግርማዊ ፊት እንቆማለን። ክርስትና የሕብረት ጉዞ በመሆኑም፣ የዛሬው የአምልኮ ስብሰባችን በሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም የምናደርገውን ዘላለማዊ አንድነት አስቀድሞ የሚያሳይ (Eschatological Foretaste) ሕያው ምስል ነው፤ እንዲሁም የጌታችንን ትንሣኤና በክርስቶስ ያገኘነውን መንፈሳዊ እረፍት የምናድስበት ዕለት ነው።
ስለሆነም የዚህን ዓለም ጫጫታና ሩጫ ወደ ጎን ብለን፣ ነፍሳችን እውነተኛ ዕረፍቷን ወደምታገኝበት ወደ እግዚአብሔር ቤት እንገስግስ፤ በምስጋና ፊቱ እንቁም፣ ሕያው ቃሉንም እንስማ።
መልካም የጌታ ቀን!
1 767
በሰው እውቀትና ጥበብ የሚፈቱ አያሌ ችግሮች ቢኖሩም፣ በጸሎት እንጂ በሰው ጥረት በፍጹም የማይፈቱ ውስብስብ ቋጠሮዎችም አሉ። በራስ ጥረት ከመደከም ይልቅ በመስቀሉ ስር መውደቅና በጸሎት መበርታት ከብዙ ከንቱ ድካም ያድናል!
በጸሎት እንበርታ 🙌
1 767
ሰው በገዛ ጥረቱ፣ በበጎ ምግባሩ ወይም በጥበቡ ወደ እግዚአብሔር ለመድረስ የሚያደርገው ጉዞ ጨለማን በሻማ ለመብራት እንደመሞከር ነው፤ ድካም እንጂ ብርሃን አይገኝበትም። ከእግዚአብሔር ጸጋ ክልል ውጭ ያለ ማንኛውም ሰው መንፈሳዊ አቅም ያጣ፣ የራሱ አቅምና ጥረት ወደ አምላካዊ ቅድስና ሊያደርሰው የማይችል ደካማ ፍጡር ነው።
መንፈሳዊ ህይወት በሰው ፈቃድና ጥረት የሚጀምር ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ቀዳሚ ፍቅርና ጸጋ የሚገለጥ አምላካዊ ስጦታ ነው።
ሰው ወደ አምላክ አይወጣም፤ ይልቁንም አምላክ ወደ ሰው ወረደ።
ሰው በገዛ እጁ አምላክን አይዝም፤ ይልቁንም እግዚአብሔር በወደደው ልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ ታች ዘንበል ብሎ ሰውን ያቅፈዋል።
እኛ ወደ እሱ ለመቅረብ ጥረት ስናደርግ ሳይሆን፣ እሱ በጸጋው ድካማችንን አይቶ ሲቀበለን ህይወታችን ይለወጣል። ኢየሱስን መቀበል እንኳ የራሳችን ብቃት ሳይሆን፣ የፈሰሰልን አምላካዊ ጸጋ ያበቃን ታላቅ እድል ነው።
አዳኝነቱ የጥንካሬአችን ውጤት ሳይሆን፣ የጸጋው ጥልቀትና ወሰን የሌለው ፍቅር ውጤት ነው!
1 767
ጸጋ ሲባል ብዙ ጊዜ ተራ መልካምነት ወይም ይቅርታ ብቻ ተደርጎ ይወሰዳል፤ ነገር ግን በነገረ-መለኮታዊ ጥልቀቱ ሲታይ "ያልተገባ፣ በዋጋ የማይገዛ እና ሙሉ በሙሉ በሰጪው ልግስና ላይ የተመሠረተ አምላካዊ ፍቅርና ስጦታ" ማለት ነው።
በክርስቲያናዊ አስተምህሮ ውስጥ የጸጋን ምንነት ከሶስት መሠረታዊ ነገሮች አንጻር እንረዳዋለን፦
👉Unmerited Favor (ያልተገባ ሞገስ)፦ ሰው ሊሰራበት፣ ሊደክምበት ወይም በራሱ ብቃት ሊያገኘው የማይችለው አምላካዊ ስጦታ ነው።
👉De-merited Favor (ጥፋተኛ እያለን የተሰጠ ሞገስ)፦ ጸጋ ባዶ እጃችንን ብቻ ሳይሆን፣ በእግዚአብሔር ላይ አምጸንና ጥፋተኞች ሆነን ሳለን የተሰጠ ፍቅር ነው።
👉God's Riches at Christ's Expense (በክርስቶስ መስዋዕትነት የተገኘ የአምላክ ሀብት)፦ የጸጋው ዋጋ ለእናንተ ነፃ ቢሆንም፣ ለእግዚአብሔር ግን የአንድያ ልጁን ሕይወት ያስከፈለ ውድ ስጦታ ነው።
1 767
መለኮታዊ መገለጥ (Divine Revelation) እና የክርስቶስ ታሪካዊ ህልውና
የሰው ልጅ በራሱ የምክንያታዊነት (Rationalism)፣ የፍልስፍና ጥበብ እና የቁሳዊ ምርምር አቅም እግዚአብሔርን በሙላት ማወቅ አለመቻሉ የምስጢረ መለኮት መታወር (Epistemic limitation of human reason) ውጤት ነው። ሰው በፍጡርነቱ እና በውድቀቱ ምክንያት ገደብ የለሹንና እውነተኛውን አምላክ በገዛ ጥረቱ ሊደርስበት አይችልም።
ይህንን የሰው ልጅ ውስንነት ለመሻገር እግዚአብሔር ራሱን ይፋ ያደረገበት መንገድ ሥጋዌ (Incarnation) ነው።
የራሱ የሥጋዌ መለኮታዊ መገለጥ (Self-Revelation through Incarnation)፦
እግዚአብሔር ረቂቅና በሰው አእምሮ የማይታሰብ ህልውና ሆኖ አልቀረም። ይልቁንም በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ወደ ታሪክና ወደ ፍጥረት ግዛት ገባ። ክርስቶስ የማይታየው አምላክ ፍጹም ምስል (eikon) እና የመለኮቱ ፍጹም መገለጫ በመሆኑ፡
👉 የፈጣሪን መኖር በረቂቅ ንድፈ-ሐሳብ ሳይሆን በግልጽ ታሪካዊ ህልውና አስመስክሯል።
👉 እግዚአብሔር ማን እንደሆነ፤ ቅድስናው፣ ጽድቁ እና ፍጹም አጋፔ (Agape) ፍቅሩ፤ በክርስቶስ ህይወት፣ ትምህርት እና ህልውና ውስጥ ፍጹም ሆኖ ታይቷል።
"እግዚአብሔር አለ ወይስ የለም?" ለሚለው የሰው ልጅ ትልቅ ጥያቄ ክርስቲያናዊ ስነ-መለኮት የሚሰጠው ምላሽ ፍልስፍናዊ መላምት ሳይሆን የመስቀሉን እና የትንሣኤውን ታሪካዊ እውነት ነው።
👉የመስቀሉ ምስጢር (Theologia Crucis)፦ መስቀል እግዚአብሔር በሰው ልጅ ስቃይ፣ ኃጢአት እና ውድቀት ውስጥ አብሮ የተካፈለበት፣ ጽድቁንና ፍቅሩን በተግባር ያረጋገጠበት ታሪካዊ ኩነት ነው።
👉የትንሣኤው ድል (The Reality of the Resurrection)፦ ትንሣኤ የእግዚአብሔርን ህልውና እና በሞት ላይ ያለውን ስልጣን በይፋ ያወጀ፣ በታሪክ ውስጥ የተፈጸመ ተጨባጭ እውነት ነው። ሞትን ያሸነፈ አካል በታሪክ መታየቱ የእግዚአብሔር አለመኖርን የሚሞግቱ ፍልስፍናዎችን ሁሉ የሚሽር ታላቅ ማስረጃ ነው።
እግዚአብሔርን ማወቅ በሰው ልጅ የምርምር አቅም ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር ራሱን ዝቅ አድርጎ በክርስቶስ በኩል በገለፀው መለኮታዊ መገለጥ (Divine condescension) ላይ የተመሰረተ ነው። በመሆኑም የመስቀሉ እና የትንሣኤው ታሪክ የክርስቲያናዊ እምነት መሰረት ብቻ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር ህልውና እና ማንነት ለዓለም የተረጋገጠበት ትልቁ የስነ-መለኮትና የታሪክ ምላሽ ነው።ይህ መለኮታዊ መገለጥ በጽሑፍ ሰፍሮ በቃሉ (በመጽሐፍ ቅዱስ) በኩል ለእኛ ደርሷል።
1 767
አምላኬ ሆይ፤ በዚች ምድር ላይ በምንመላለስበት ጊዜ ሁሉ፦
➙እንደ ጽድቅህ ቅድስናህ በእኛ ውስጥ ይገለጥ፤
➙ እንደ ቸርነትህ ፍቅርህ ከእኛ ዘንድ ይፍሰስ፤
➙ እንደ እውነተኛነትህ ማንነትህ በንግግራችንና በተግባራችን ይታይ። አሜን🙏🙌
1 767
“አውጤኪስ የሚሉትም አንድ ጎበዝ በመስኮት ተቀምጦ ታላቅ እንቅልፍ አንቀላፍቶ ነበር፤ ጳውሎስም ነገርን ባስረዘመ ጊዜ እንቅልፍ ከብዶት ከሦስተኛው ደርብ ወደ ታች ወደቀ፥ ሞቶም አነሡት።”
— ሐዋርያት 20፥9
ስብከት ሲረዝም መተኛት የዛሬ ሰዎች ብቻ ልማድ አይደለም፤ ገና በሐዋርያት ዘመን የተጀመረ ጥንታዊ ውርስ ነው😁......ልዩነቱ አውጤኪስ ፎቅ ላይ ተቀምጦ ስለነበር ተከሰከሰ (በኋላ ጳውሎስ በጸሎት አስነስቶታል)።
እናንተ ግን በየወንበሩ ላይ የምታሸልቡ ወዳጆቼ...ጥንቃቄ አድርጉ! አሁን ባለንበት ዘመን(ነብያት ነን ባዮችን አትመኗቻው) እንደ ጳውሎስ አይነት ፈጣን ድገስ ያለው የለምና ከወንበር እንዳትፈጠፈጡ😁
ያው በቅዱሳን ጉባኤ በእንቅልፍ አትመሰጡ ለማለት ነው።
መልካም የጌታ ቀን!
1 767
የሰባኪያኑ አለቃ Charles Spurgeon በምሳሌ 18፥12 ስብከቱ ላይ፤ ኩራት የስኦል የበኩር ልጅ ነው...ዙፋኑም የአማኝ ልብ ነው ይለናል።
እውነት ነው....ዲያብሎስ ብዙ ልጆች አሉ፡ ምቀኝነት፣ ሀሜት፣ ስስትን የመሳሰሉ… ነገር ግን በSpurgeon ገለፃ ኩራት የቤት አበጋዝ፣ የበኩር ልጅ ነው። የአባቱ አጋንንት ሁሉ የሚወረስ ነው። ለምን ቢባል? ሌሎቹ ኃጢአቶች ቢያንስ ጥቂት የአቅም ማነስ ወይም ምኞት አለባቸው። ኩራት ግን ሙሉ በሙሉ ዲያብሎሳዊ ኮንፊደንስ ነው ያለው! ራሱን ከፈጣሪ ጋር አኩል ለማድረግ ሲሞክር ከሰማይ የወደቀውን የዲያብሎስን መልክ በትክክል የሚወርሰው ኩራት ነው።
ኩራት ዙፋኑን አድርጎ የሚቀመጠው ያልተማረ፣ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሰው ልብ ውስጥ ብቻ ቢሆን ጥሩ ነበር። ነገር ግን ኩራት በጣም “የከበረ” ቦታ ይወዳል፡ የሚፈልገውም የአማኝን ልብ ነው!
አማኝ ሰው ጾመ፣ ጸለየ፣ መጽሐፍ ቅዱስ አጠና፣ በቤተክርስቲያን አገልግሎት በረታ… ኩራት ከጀርባ መጥቶ በትዕቢት ይሞላዋል። ሳይጣን በኃጢአት ሊጥለን ሲያቅተው፣ በሚገርም ሁኔታ በበጎ ሥራችን እና በቅድስናችን ምክንያት ኩራትን አፋፍቶ ሊጥለን ይሞክራል!
ኩራት ወደ ልባችን ገብቶ ዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ፣ እኛ ትልቅ የሆንን ይመስለናል። ነገር ግን እውነታው ኩራት የውድቀታችን መጀመሪያ መሆኑ ነው።
ስለዚህ፣ ኩራት በልባችን ዙፋን ላይ የተቀመጠ እንግዳ ከሆነ፣ እሱን አክብሮ ማስተናገድ ሳይሆን በንስሐና በትህትና አውርዶ ማስወጣት ያስፈልጋል። Spurgeon እንዳለው፤ ትህትና የጸጋ መሸሸጊያ ስትሆን፣ ኩራት ግን የውድቀት ትልቅ ምንጣፍ ናት።
"ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።" ምሳ 18፥12(NASV)
1 767
ነፍሴ የእርሱ የእጆቹ ሥራ ናት፤ ወደ እርሱም ልትመለስ የተፈጠረች የአምላክ እስትንፋስ ናት። ሞት ሊያጠፋት የማይችልን የዘላለም ሕይወት የሰጣት ኢየሱስ፣ በኃጢአትና በጥፋት ውስጥ ወድቃ በነበረችበት ጊዜ በጥበቡና በበጎነቱ ፍለጋ ወጣ። ነፍሴን ከዘላለም ሞት አድኖ በኪዳኑ ደም አተማት፤ የማትጠፋውንና የማትበሰብሰውን እርሱን እንድትመስል ሕያው ተስፋን አደላት።
በዚህ በምድር ጉዞዋ ውስጥ የሚታየውና የሚያልፈው ነገር ሁሉ ሊያረካት አልቻለም፤ ምክንያቱም የተፈጠረችው ለአላፊ ነገር ሳይሆን ለዘላለም ማንነት ነውና። እውነተኛው የነፍሴ መጠጊያ፣ የውኃ ምንጭና የሕይወት እንጀራ እርሱ ኢየሱስ ብቻ ነው። ጥማቷ የሚቆረጠው፣ ሕይወቷም ትርጉም የሚያገኘው በእርሱ ፍቅር ውስጥ ስትሰጥም ብቻ ነው።
ስለዚህ ነፍሴ ሆይ፣ በዓለም ውጣ ውረድና ፈተና አትናወጪ፤ እረኛሽና ጠባቂሽ የፍቅር አምላክ ነውና። በመስቀል ላይ የተቀበለሽ፣ በየቀኑ የሚያስብሽና የሚመራሽ እርሱ ዘላለማዊ ነው። አሁንም በዓይነ ሥጋ የማታይውንና በልብሽ የምትወጂውን ያንን አምላክሽን እያሰበሽ ዘወትር አመስግኚው፤ ቅዱስ ስሙንም አክብሪ። በክብሩ ተገልጦ በሙሉ እውቀትና በፍጹም አካል የምታይበት፣ ከሕይወት ምንጭም ሙሉ በሙሉ የምትጠጪበት ያ የደስታ ቀን እስኪመጣ ድረስ በተስፋና በፍቅር ተከተዪው። ነፍሴ ሆይ፣ ለእርሱ ብቻ ስገጂለት፣ ዘምሪለት፣ ታመኚለት፣ ተገዥለት🥰
