fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች

አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች

رفتن به کانال در Telegram

መጅሊስ፣ ምንጣፍ፣ ድጋፍ፣ መጋረጃ፣ ትራስ ልብስ፣ ሁሉንም የሲንጀር ውጤቶችን የተሟሉ ረኮበት ሴቶችንና የተለያዩ ኳሊቲ የቤት እቃዎችን እንዲሁም አስቤዛዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ በታማኝነት ያሉበት ሀገር እንልካለን!

نمایش بیشتر
أثيوبيا2 805دسته بندی مشخص نشده است

📈 تحلیل کانال تلگرام አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች

کانال አቡ ፈህድ ዘመናዊ ዐረቢያን መጅሊስና ኳሊቲ የቤት እቃዎች (@abu_fehd_online_market) بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 12 583 مشترک است و جایگاه را در دسته متفرقه و رتبه 2 805 را در منطقه أثيوبيا دارد.

📊 شاخص‌های مخاطب و پویایی

از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 12 583 مشترک جذب کرده است.

بر اساس آخرین داده‌ها در تاریخ 29 اکتبر, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر -560 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر -21 بوده و همچنان دسترسی گسترده‌ای حفظ شده است.

  • وضعیت تأیید: تأیید نشده
  • نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 1.61% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً 0.89% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب می‌کند.
  • دسترسی پست‌ها: هر پست به طور میانگین 202 بازدید دریافت می‌کند. در اولین روز معمولاً 112 بازدید جمع‌آوری می‌شود.
  • واکنش‌ها و تعامل: مخاطبان به‌طور فعال حمایت می‌کنند؛ میانگین واکنش به هر پست 1 است.

📝 توضیح و سیاست محتوایی

نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاه‌های شخصی توصیف می‌کند:
“መጅሊስ፣ ምንጣፍ፣ ድጋፍ፣ መጋረጃ፣ ትራስ ልብስ፣ ሁሉንም የሲንጀር ውጤቶችን የተሟሉ ረኮበት ሴቶችንና የተለያዩ ኳሊቲ የቤት እቃዎችን እንዲሁም አስቤዛዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እኛ ጋር ያገኛሉ በታማኝነት ያሉበት ሀገር እንልካለን!”

به لطف به‌روزرسانی‌های پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 30 اکتبر, 2026)، کانال همواره به‌روز و دارای دسترسی بالاست. تحلیل‌ها نشان می‌دهد مخاطبان به‌طور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته متفرقه تبدیل کرده‌اند.

12 583
مشترکین
-2124 ساعت
-1177 روز
-56030 روز
آرشیو پست ها
#ሂክማ ክፍል ስምንት : ከሰዓት ቢደክመኝም ከነ አባቢ ጋር ወደ አያቶቻችን ቤት ሄድን። አያቴ ቤት ስንደርስ ዘመድ አዝማዱ ሁሉ ተሰብስበው እየተጫወቱ ደረስን። ምሳ ሰዓት ትንሽ ቢረፍድም የኛን መምጣት እየተጠባበቁ ስለነበር አልበሉም። እንደደረስን ምሳ ቀረበና በላን። እሁድ እሁድ ሁሌም ምሳ ከአያቶቼ ቤት ነው ምንበላው። ሪ የሰራችው ወጥ ለራት ነበር። ያው አምሽተን ስለምንመለስ ከዛ በኋላ ለማዘጋጀት ስለሚመሽ። ማሚ ዘመደ ብዙ ናት። ሁለት ታላቅ ወንድሞች፣ ሁለት ታላቅ እህቶችና አንድ ታናሽ እህት አሏት። ከማሚ ታናሽ እህት በቀር ሁሉም አግብተው ወልደዋል። በአጠቃላይ ወደ 10 የምንሆን የልጅ ልጆች ቤቱን ሞልተነዋል። ነብሷን ይማራትና አያቴ ባትሞት ኖሮ ከዚህም በላይ ደመቅ ይል ነበር። ቡና ከተጠጣ በኋላ አያታችን ሁሌ እንደሚያደርገው እኛን የልጅ ልጆቹን ሰብስቦ መምከር ጀመረ። እስከዛሬ ካንገት በላይ ቢሆንም የማዳምጠው ዛሬ ግን ሙሉ ህዋሳቶቼን አንቅቼ እንደ ቴፕ ሪከርደር መቅዳት ጀመርኩ። ማን ያውቃል ለሂክማ የምልክላት ምክሮችን ባገኝስ? በማለት። አያቴ ስለተንኮል መጥፎነት ከመከረን በኋላ መቼም ልረሳው የማልችለውን ገጠመኙን እንዲህ ሲል ነገረን፦ "ድሮ ልጅ እያለን ከማል የሚባል አንድ የሰፈራችን ልጅ ነበር። ይህ ልጅ ሰፈራችን ውስጥ የሚታወቀው በተንኮሉ ነበር። ህፃናቶችን ማስለቀስና ገንዘብ ካላመጣችሁ እያለ ማስቸገር ያበዛ ነበር። ከማል ሁሌም ከእጁ የማትጠፋ ወንጭፍ ነበረችው። በዚህች ወንጭፉ ከትንሽ  እስከ ትልቁ  ብዙ ሰው ፈንክቶባታል። በተለይ ደግሞ ወፎችንና ጫጬቶችን ካገኘ አይምርም። ኢላማውንም አይስትም ነበር። በዚህ ድርጊቱ ያልተማረረበትና ያልረገመው ሰው የለም። የሚገርመው ደግሞ ዕድሜው ገና 16 ዓመት ቢሆንም ከተንኮለኛነቱ የተነሳ የማይፈራው ሰው አልነበረም ነበር። ሌላው ቀርቶ የሰፈሩ ለማኝ እንኳን ሳይቀር ተመፅውቶ ሲመርቅ "ከልጅ እንከፍ፤ ከከማል ወንጭፍ ይሰውራችሁ!" ብሎ ነበር መፅዋቹን የሚመርቀው። አንድ ቀን እማማ ኪሮስ የሚባሉ ደሃ ባልቴት ብቸኛ ንብረታቸው የሆነችው ዶሯቸው የሚያማምሩ ስድስት ጫጩቶችን ፈለፈለችላቸው። አቤት የዛኔ ደስታቸውን ብታዩ! የሳቸውን ደስታ ያየ የሰፈራችን ሰው ሁሉ ከልቡ ደስታቸውን ተጋራቸው። ግና ምን ያደርጋል ከማል ተብዬ እርጉም ሰው በቤታቸው አጥር ተደብቆ በወንጭፉ አንድም ሳያስቀር አረገፋቸው። ያ አልበቃ ብሎት ጫጩቶቹን ቀጭን ክር ላይ እግራቸውን አስሮ በራቸው ላይ እንደ ቋንጣ አንጠለጠላቸው። እማማ ኪሮስ አገር አማን ብለው በራቸውን ሲከፍቱ ስድስቱም ጫጩቶች እንደ ዲምላይት አንፖል በአንድ ቀጭን ገመድ ላይ ተንጠልጥለው አገኟቸው። እኔና ጓደኞቼ በአጥሩ በኩል ሁነን የሚሆነውን እያየን ነበር። እማማ ኪሮስ አይናቸው እንደ ፈጠጠ ብዙ ቆሙ። ከድንጋጤያቸው ሲነቁ እዬዬውን አስነኩት። የሰፈሩ ሰው ሁሉ ቤታቸውን ሞሉት። ሁሉም ሰው ለእማማ ኪሮስ ከልቡ አዘነ። ትዝ ይለኛል እኔ እራሱ ከሁለቱ አይኖቼ በኩል የእንባ ዘለላ ኮለል ብሎ ወጥቶብኛል። ማን ሊያደርገው እንደሚችል ሳይታለም የተፈታ ነውና እማማ ኪሮስ ከማል ላይ የእርግማን ናዳ ያዘንቡበት ጀመር። "አንድዬ ይፋረድህ! እጅህ ሽባ ይሁን! ልጅ አይውጣልህ! ዘላለም አለምህን ባይተዋር ያድርግህ! ጧሪ ቀባሪ ይንሳህ..." እያሉ እረገሙት። የሰፈሩ ሰው "ኧረ እማማ ይተው! ይቅር ይበሉት።" ቢሏቸውም አልሰማ አሉ። በመጨረሻም አረጋግተውና ገንዘብ አዋጥተው ሰጧቸውና ሰው ተበተነ። ይሄን የታዘበ አንድ አዝማሪ፦ "ጎልያድን አየሁ፤ በጁ ወንጭፍ ይዞ እራሱን ሲመታ፤ ራሱ ላይ ወርውሮ" ሲል ተቀኘ። ጎልያድ ማለት በቁርዓን ውስጥ ጃሉት በመባል የሚታወቅ በነብዩላህ ዳውድ ጊዜ የነበረ አመፀኛ ንጉስ ሲሆን፤ ነብዩላህ ዳውድ በወንጭፍ መትተው ገድለውታል። አዝማሪው ማለት የፈለገው ከማል በወንጭፉ ምክንያት እማማ ኪሮስ ስለረገሙት ወንጭፉ ዙሮ እራሱ ላይ ያርፍበታል ለማለት ነው። እርግማን ከወንጭፍ በላይ ስለሆነ። ይህ ሁሉ ሲሆን ከማል ተደብቆ እያየና እየሳቀ ነበር። ታዲያ ይሄ ልጅ ከአመታት በኋላ ውትድርና ሄደ። እዛም ሂዶ በተንኮሉና በጭካኔው ወታደሩን ያሸብር ነበር። ተሰሚነት ስላለውም ከማዕረግ ወደ ማዕረግ እያደገ የጦር መኮንን እስከመሆን በቃ። አንዲት ካፊርም አግብቶ ሁለት መንታ ወንድ ልጆች ወለደ። ይህን ባየሁ ጊዜ "የእማማ ኪሮስ እርግማን መና ቀረ።" ስል አሰብኩ። ጭራሽ ከሁለት አመት በኋላ ሌላ ሁለት መንትያ ሴት ልጆችን ጨመረ። በኑሮው ደስተኛ ይመስላል። ምስቱንም ልጆቹንም በጣም ይወዳቸው ነበር። ከጥቂት አመታት በኋላ በገዛ መኪናው ሙሉ ቤተሰቦቹን ይዞ ለመዝናናት ወደ ናዝሬት ሲጓዝ ከአንድ የጭነት መኪና ጋር ተጋጨ። በአደጋውም ሁሉም ቤተሰቦቹ እንዳልነበሩ ሆኑ። እሱን ግን ለተዓምር አተረፈው። ነገር ግን በደረሰበት አደጋ የተነሳ ሙሉ አካሉ ፓራላይዝድ(ሽባ) ሆነ። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሆስፒታል ውስጥ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ያለጧሪ በጥሮታ ደሞዝ ሲተዳደር ቆየና ሞተ። በእርግጥም የእማማ ኪሮስ እርግማን ልክ እንደ ከማል ወንጭፍ ኢላማዋን አልሳተችም ነበርና እያንዳንዷ እርግማን በከማል ላይ ተፈፀመች። አያችሁ ልጆቼ! ተንኮል ሰዎች ዘንድ እንድትጠሉ ያደርጋችኋል። በናንተ የተማረረ ሰው የረገማችሁ እንደሆነ፤ ልክ እንደ ከማል ፍፃሜያችሁ አስከፊ ይሆናል። ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) የተበዳይ ዱዓ ተቀባይ እንደሆነ ይነግሩናል። የተበደለው አካል ሴትም ይሁን ወንድ፣ ህፃንም ይሁን ትልቅ፣ ሙስሊምም ይሁን ካፊር እስከ ተበደለ ድረስ ዱዓው ተቀባይ ነው። ስለሆነም ማንንም ቢሆን አትበድሉ። በተለይ ደግሞ የወላጆቻችሁን እርግማን ተጠንቀቁ። በተቻላችሁ መጠን እነሱን ላለማስከፋት ሞክሩ። የሚያዙትን ፈፅሙ።" ሲል መከረን አያታችን። እንደ ዛሬ ምክሩን ከልቤ አዳምጬ አላውቅም። ዛሬ ሁላችንም በጥሞና ነው የአያታችንን ምክር ያደመጥነው። በተለይ ደግሞ የተንኮለኛውን ከማል ታሪክ። ሪሃና ታሪኩን ስትሰማ ጉንጮቿ በእንባ ርሰው ነበር። "ሳሊሜ ሶላት ጀመርክ?" ሲል ጠየቀኝ። ሁሌም በየ ሳምንቱ ስገድ እያለ እንደ ጨቀጨቀኝ ነው። "ኢንሻ አላህ እሰግዳለሁ።" ስል መለስኩ በደፈናው። "ያንተ ኢንሻ አላህ¡ ለማንኛውም ያሁኑን አመት ግማሽ ሴሚስተር ረፍት እኔ ጋር ነው ምታሳልፈው። የዛኔ ወደህ ሳይሆን በግድህ ትሰግዳለህ!" አለኝ። ከሁሉም የልጅ ልጆቹ ታላቅ እኔ ስለሆንኩ ትኩረት ያደርግብኛል። ትንሽ ከእኔ ጋ በእድሜ የሚቀራረበው የአጎቴ ልጅ በክሪ ነው። እሱ ደግሞ በዲኑ ጠንካራ ነው። "ኧረ አያያ እኔኮ ጅማ ለመሄድ ነበር ያሰብኩት።" ስል ተሟገትኩ። ጅማ የአባቢ ቤተሰቦች አሉ። እነሱጋ ለማሳለፍ ነበር እቅዴ። "እንግዲህ ወስኛለሁ ወስኛለሁ! ከፈለክ ክረምቱን እነሱጋ ማሳለፍ ትችላለህ።" አለኝ። አያቴን በጣም ነው ምፈራው። ከመስማማት በቀር ሌላ አማራጭ እንደሌለኝ አወቅኩ። መቼ በደረሰ ስል የነበረውን የእረፍት ቀን ምነው ባልደረሰ ስል ተመኘሁ። 15 ቀን ሙሉ እየተመከርኩ እንዴት እደምቆይ ጨነቀኝ። "15 እሁዶች ኤጭ!" አልኩኝ በውስጤ። የአያቴን ቤት ቆይታ ጨርሰን ስንወጣ ከቤቱ ፊት ለፊት ወደ ነበረችው ሱቅ ተመለከትኩ። የነ አባቢ ፍቅር የተጠነሰሰባት ሱቅ ቦታዋ ላይ የለችም። በሷ ቦታ ባለ ሦስት ፎቅ ቪላ ቤት በኩራት ተገትሯል። "ምናለ መንግስት ለቅርስነት እንኳን ቢያስቀምጥልን!" አልኩ በውስጤ።

#ሂክማ ክፍል ሰባት ይሄኔ ቀልድ አልያም የዘፈን ግጥም ብትለኝ ኖሮ እስኪበቃት አጎርፍላት ነበር። ምን ይሻላል? ትንሽ እንዳሰብኩ አንድ ሃሳብ ብልጭ አለልኝ። አዎ ለይላ ትዝ አለችኝ። ለይላ ከኔ ጋር መዋል ከጀመረች በኋላ አቋሟ ወረደ እንጅ የመስጅድ ጀመዓ ውስጥ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ናት። ብዙ ኪታቦችንም ቀርታለች። ስለሆነም እሷን የተወሰኑ ምክሮችን ለማስላክ አሰብኩ። ከሂክማ አካውንት ስወጣ ለይላ ሦስት መልዕክቶችን ልካልኝ አገኘሁ። 1- "ኔትዎርክ? ምነው ሰፈር ቀየራችሁ እንዴ? እስከዛሬ ለምን አላስቸገረህም?" 2- "እሽ ለማንኛውም ደህና ነሃ? ዛሬ ስላላገኘሁህ እንዴት እንደደበረኝ ባየህ። ነገ አንገናኝም?" 3- "አንተን እኮነው ማናግረው። አሁንም በኔትወርክ ልታሳብብ ባልሆነ። ጥንቅር በል ከፈለክ እሽ ያበዛሃው አልመሰለህም?" የሚሉ መልዕክቶችን አከታትላ ልካለች። "ምን አስቸኮለሽ ትንሽ ታገሽ እኔ እራሴ ጥንቅር አድርጌ እተውሽ የለ።" አልኩ በውስጤ። ለአሁኑ አስተባብዬ የፈለኩትን ነገር ማግኘት ስላለብኝ፦ "ሊዬ ለምን አንደማታምኚኝ አይገባኝም። ሰሞኑን ከስልኬ ነው መሰል ኔቱ በግድ ነው የሚሰራልኝ። ያው ካልፈለግሽኝ ግን እንደፈለግሽ አላስገድድሽም" ስል መለስኩላት። "ሳሊሜ እንደዛ ማለቴ እኮ አይደለም። በቃ እሽ ይቅርታ አድርግልኝ" ስትል መለሰችልኝ። ሲጀመርም ምላሿ ይሄ እንደሚሆን እርግጠኛ ነበርኩ። "ይቅርታ እንዳደርግልሽ ከፈለግሽ መቀጣት አለብሽ!" "እሽ ደስ ያለህን ቅጣኝ።" "አንድ ሶስት ምክሮችን ላኪልኝ!" "ኪኪኪኪኪ ትቀልዳለሃ? የምን ምክር ነው ደግሞ? በል መቀለድህን ትተህ ቅጣቴን ንገረኝ። ፎቶ ልላክልህ፣ በቴሌግራም እየዘፈንኩ ድምፄን ልላክልህ ወይስ ነገ ተገናኝተን ምሳ ልጋብዝህ?" "የምሬን ነው። ምክር እንድትልኪልኝ እፈልጋለሁ።" "አንተ ልጅ ግን ዛሬ ጤነኛ ነህ? እሽ ካልክ ምን አገባኝ እመክርሃለው። 1ኛ አትዋሽ። 2ኛ መልዕክት ስልክልህ ቶሎ ምላሽ ስጥ። 3ኛ ሁሌም ከጎኔ አትጥፋ።" ብላ ላከችልኝ። በምላሿ ቅጥል አልኩ። "ባክሽ አትዘላብጅብኝ! እኔ ያልኩሽ ከቁርዓን፣ ከሀዲስ ወይም ከዑለማዎች ምክር ውስጥ ነው።" "ዛሬ ምን ተገኘ? እሽ በቃ ጠብቀኝ!" "እሽ ቶሎ በይ!" ብዙም ሳትቆይ ወደ አምስት የሚደርሱ ምክሮችን ላከችልኝ። ይቅርታ እንዳደረኩላት ነግሬያት ቶሎ ወደ ሂክማ ሄድኩ። አንዳንዴ የራሴ ነገር ግርም ይለኛል። አዲስ ነገርና አልፊ ነገር ደስ ይለኛል። ለዛም ነው ለይላን ችላ ብዬ ወደ አዲሷ ታዳኜ ቱኩረት ያደረኩት። አፍለኛ የሚለው ቃል ይገልፀኝ ይሆን? "ስለዘገየሁብሽ ይቅርታ! ምክር አንድ : ሰዎች ላንች እንዲያደርጉልሽ ምትመኝውን ነገር አንች ቀድመሽ አድርጊላቸው። የሰው ልጅ መልካም ለዋለለት መልካም መዋሉ አይቀሬ ነውና፤ ካደረግሽላቸው በላይ ላንች ለማድረግ ሲጥሩ ታያቸዋለሽ! ነገር ግን በጎን ነገር ስትውይ አፀፋውን ፈልገሽ አይሁን። ሰዎች አመሰገኑሽም አላመሰገኑሽም መልካምን ነገር ከማድረግ ወደኋላ አትበይ። ይህንን ሁሉ ስታደርጊ ግን ከሰዎች ጋር አብሮ በመኗኗር የሚገኘውን አጅር ከአላህ ፈልገሽ ይሁን!" "ማሻ አላህ አሪፍ ምክር ነው። እሽ ምክር ሁለት : ቆንጆዎች ቁንጅናቸው ሁሉን የሚተካ እየመሰላቸው ከእውቀትና ከትህትና ይርቃሉ። ሁሉንም ሰው በመልካቸው የሚማርኩት ስለሚመስላቸው ኩሩና ተንኮለኞች ይሆናሉ። የላይ ነገር ከንቱና አላፊ ነውና በሚፈርስ አካል፣ ኑሮ በሚለውጠው መልክ አትደለል።" ይህ መልዕክቷ ሆን ብላ እኔን ለመንካት እንደሆነ አላጣሁትም። ያው ለመመከር ልቤ ክፍት ስላልነበር ከምክሩ ይልቅ ከምክሩ በስተጀርባ ያለውን ተንኮል ወይም ሴራ ብቻ ነው የሚታዬኝ። እንዲህ እንዲህ እያልን በየተራ ስንመካከር ለይላ የላከችልኝ አምስት ምክሮች አለቁብኝ። ምን ይዋጠኝ። ለይላን እንደሆን ድጋሚ መጠየቅ አልችልም። ምክንያቱም ሳያጠፉ ቅጣት የለምና! ግራ ገብቶኝ እንዳለ አንድ ነገር ትዝ አለኝ። ትዝ ያለኝ ከለይላ የተዋወቅን ሰሞን ከአንድ የቴሌግራም ቻናል ፎርዋርድ ያደረገችልኝ ምክር ነበር። ምናልባትም የቻናሉ ሊንክ ካለ የምክር ሀይቅ ወስጥ ተነከርኩ ማለት ነው። ስቻኮል ቴሌግራሜን ከፍቼ መፈለግ ጀመርኩ። ከመልዕክቱ በኋላ ብዙ ነገሮችን አውርተን ስለነበር በቶሎ ላገኘው አልቻልኩም ከብዙ ፍለጋ በኋላ አገኘሁት። ወደ ቻናሉም ገብቼ የተወሰኑ መልዕክቶችን መርጬ የስልኬ ማስታዎሻ ላይ አሰፈርኩ። ከነዚህ ምክሮችም በተራዬ እየላኩ የሷን ምክሮችን አነበብኩ። ምክሮቿ በጣም ገራሚዎች ነበሩ። ሆነ ብላ ለኔ ያዘጋጀቻቸው እስኪመስል ድረስ ሁሉም የሚመለከቱኝ ናቸው። ለነገሩ እኔን የማይመለከት ምክር ይኖራል ብላችሁ ነው? ጥቂቶቹ እነዚህ ነበሩ፦ "የምትለካው ነገር  በመለኪያህ ልክ ልኬቱ ይለያያል። ወርቅን በእህል ሚዛን ብትለካው ልክ አይመጣም፤ ጤፍን በሊትር ልትለካው አትችልም፤ ብርንም ቆጥረህ እንጅ መዝነህ ብዛቱን ማውቅ አትችልም፤ ጥጥን በኪሎ እንጅ በመዳበሪያ ልትገምተው አይቻልህም። ስለሆነም ራስህን የምትለካበትን ሚዛን ለይ። ራስህን ከእብዶች አንፃር ከለካህ ጤነኛ መሆንህ ብቻ ስኬት ነው! እንደዚሁም ራስህን በተራ ሰዎች ሚዛን ከመዘንክ ጥቂት የተሻልክ መሆንህ ብቻ ትልቅነት ነው። ይልቁንስ ራስህን የሁሉም ነገር መለኪያ እስኬል በሆኑት ታላላቅ ሰዎች ለካ የዛኔ ትክክለኛ ደረጃህን ታውቃለህ።" "ለሰው ልጅ ክብር ስጥ፣ ታላላቆችህን አክብር፣ ለታናሾችህ እዘን። ወንድን ከሴት፣ ሰውን ከሰው አታበላልጥ። ከሰዎች ጋር በምትኗኗረው ልክ ሰዎች አንተን ይኗኗሩሃል፣ ለሰዎች በምታሳየው እዝነት ልክ አላህ ያዝንልሃል።" "የጌታህን ውለታ አትዘንጋ። የጌታህን ፀጋ ቆጥረህም ሆነ ከፍለህ ባትዘልቅም ክልክላቱን በመከልከል፣ ትዛዛቱን በመፈፀም የተቻለህን ለመወጣት ጣር።" ምክሮቿ የተጠኑ ከመምሰላቸው የተነሳ "ይህች ልጅ ወይ ሳይኮሎጂስት አልያም የምታውቀኝ ሰው መሆን አለባት።" ስል አሰብኩ። በዚህ መልኩ ስንመካከር ከቆየን በኋላ ተሰናብታኝ ወጣች። ለይላን በመሃል እያዋራኋት ስለነበር ብዙም አልተከፋችም። ከሷም ጋር ጥቂት ካዋራን በኋላ ተሰናብቻት ከፌስቡክ ወጣሁና ተኛሁ። ጠዋት ለቁርስ ተቀስቅሼ ተነሳሁና ከቤተሰቦቼ ጋር ደስ የሚል የቁርስ ጊዜ አሳለፍን። አባቢ አንድ ሰው ኢንተርቪው ሊያደርግ ሊሄድ እንደሆነ ነገረንና የሱን ድርሻ እኔ እንድሸፍን ነግሮኝ ሄደ። እሁድ እሁድ ሁላችንም የስራ ድርሻ አለን። እኔና አባቢ ቤት የማፅዳት፣ ግቢ የመጥረግ፣ አበባዎችን የመኮትኮት፣ የሚስተካከል ነገር ካለም የማስተካከሉን ድርሻ ስንወስድ፤ ማሚና ሪ ደግሞ ምሳ የማዘጋጀት፣ እንጀራ የመጋገርና ልብስ የማጠቡን ሃላፊነት በጋራ ይወጣሉ። "ዛሬ የኛ ቡድን ነው የሚያሸንፈው።" አለች ሪ በኩራት። "እኔ ሳሊም ነኝ በናንተ የምሸነፈው?" ስል መለስኩላት። "አይ ሪሃናዬ ሳሊሜንማ ማሸነፍ ዘበት ነው። ባንለፋ ይሻላል።" አለች ማሚ "ማሚዬ አፌ ቁርጥ ይበልልሽ! እስኪ ምናለ ልጅሸም እንዳንች ሀቀኛ ብትሆን?" አልኩ። "እንዴ ማሚ ምን ነክቶሻል? ልጅሽ ጉረኛ መሆኑን እያወቅሽ እንዲህ ትያለሽ?" አለች እየተሞጣሞጠች። "በሉ ተነሱ እዚሁ ተጎልተን ሁላችንም ጊዜ በሚባለው ባላንጣችን እንዳንሸነፍ! 'ጊዜ እንደሰይፍ ነው ቀድመህ ካልቆረጥከው ራሱ ይቆርጥሃል።' አሉ አረቦች።" አለች ማሚ። "አቤት ማሚ እኮ ስትናገር! ሴት ሆነች እንጅ የመስጂድ ኢማም ነበር ምትሆነው። በቃ እውቀት እሷጋ ቀረ።" አልኩ በውስጤ። መልሼ ደግሞ "ቆይ ግን በየትኛው መለኪያ ነው የለካኋት? ይቀጥላል.....

#ሂክማ ክፍል ስድስት "እንዳልኳችሁ እናታችሁ ቅሬታዋን በግጥም መልክ ገለፀችልኝ። ቅሬታዋ እጠረጥር የነበረውን የስነ-ፅሁፍ ፍቅሯን አረጋገጠልኝ። ለዛውም ገጣሚ መሆኗንም ጭምር። በማግስቱ ፓስታ ልትገዛኝ ስትመጣ ፓስታውን ለቅሬታዋ ምላሽ በፃፍኩበት ልሙጥ ወረቀት ጠቅልዬ ሰጠኋት።" "ምላሹ ምን የሚል ነበር?" ስትል ጠየቀችው ሪ። "ካንች ጋር አይሄድም፣ ሳይሰሩ መብላት፤ መክፈል ግድ ይልሻል፣ ፅሁፍ ለማግኘት፤ እቃን ልትገዥ፣ ወደ ሱቅ ስትመጪ፤ ግጥም መያዝሽን፣ ቀድመሽ አረጋግጪ" ብዬ ነበር የፃፍኩላት። ከዛ በኋላ ለተወሰኑ ቀናት ወደ  ሱቅ ስትላክ ግጥም እየፃፈች ታመጣልኛለች። እኔም በአፃፋው እራሴ ከፃፍኳቸው መጣጥፎች፣ ታሪኮችና ወጎች እየፃፍኩ እሰጣታለሁ።  ከጊዜ በኋላ ግን እቃ ልትገዛ ባይሆንም እንኳን እሮጥ ብላ መጥታ ትወስድ ጀመር። እንዲሁ እኔ ሱቅ ስትመላለስ ያየው ወሬኛው የሱቅ ጎረቤቴ "ቆይ ምን ብታስነካት ነው በሆነው ባልሆነው አንተጋ እድትመላለስ ያደረካት?" ሲል ጠየቀኝ። "በመጣች ቁጥር የተጨማደደ ፊቷን በካወያ ተኩሼ እየላኳት ነዋ¡" ስል አሾፍኩበት።" የአባቢ ቀልድ ሁላችንንም አሳቀን። ተመስጠን እያዳመጥን ስለነበር ይህ ምቀኛ ሰዓት በጣም መግፋቱን አላስተዋልንም። ድንገት ስልኬን ሳበራ ሰዓቱ 4:15 ሆኗል። በውስጤ 'አባቢ ሰዓቱን ሳያይ በቀጠለ።' ብዬ ሳልጨርስ፤ "በሉ ልጆች ሰዓቱ ሂዷል ሳምንት እቀጥልላችኋለው። አሁን ተኙ!" አለን። ሪ "እንዴዴዴ አባቢ ገና እስከ ዛሬ ሳምንት ልንጠብቅ? ትላንትን እራሱ እንዴት እንዳደርኩ እኔ ነው ማውቀው" ስትል ቅሬታዋን አቀረበች። "እሽ ጠዋት ቀጥልልና!" ስል ተማፀንኩኝ። "ጠዋትማ ከቁርስ በኋላ ኢንተርቪው ከማደርገው ሰው ጋር ቀጠሮ አለብኝ። እናንተም እናታችሁን ልብስ በማጠብ ትረዷታላችሁ። ከሰዓት ደግሞ እንደተለመደው አያታችሁን ለመዘየር እንሄዳለን።" አለን። የኛ ቤት ፕሮግራም እንዲሁ ነው። ከጁሙዓ ምሽት እና ከቅዳሜ በቀር ቴሌቭዢን ማየትም ሆነ እየተጫወትን ማምሸት አይፈቀድልንም። ከነ ዮኒ ጋር ከት/ቤት ውጭ በሰፊው የምንገናኘው ቅዳሜ ቀን ብቻ ነው። እሁድ የቤተሰብ ጥየቃ ቀን ነው። ማታ ከራት በኋላ ደግሞ የጥናት ሰዓት። በትምህርት ላይ የሚከታተሉንን ያህል በዲን ላይ ቢከታተሉን ኖሮ ይሄኔ ጥምጣም ለብሼ ኹጥባ እያደረኩላችሁ ነበር።ሃሃሃሃ ከነ አባቢ እንደ ተለየሁ ሂክማ ትዝ አለችኝ። ቀኑን ሙሉ ሳስታውሳትና እሷን እንዴት ማንበርከክ እንዳለብኝ ሳውጠነጥን ብውልም ማምሻውን ግን የነአባቢ ታሪክ አስረስቶኝ ነበር። መኝታ ክፍሌ ገብቼ ፌስቡኬን ከፈትኩ። ከሁሉም በፊት የሂክማን አካውንት ነበር ከፍቼ ያየሁት። ኦን ላይን ላይ የለችም። እስከምትገባ ድረስ ከሌሎች የተላኩልኝን መልዕክቶች መመለስ ጀመርኩ። ከላኪዎች ውስጥ ለይላ አንዷ ነበረች። ለይላ በቅርብ ጊዜ የተዋወቅኳት የት/ቤታችን ተማሪ ናት፡፡ በቃኝ ብዬ እስክተዋት ድረስ ተረኛዋ እሷ ናት። ከትላንት ጀምሬ ቀዝቀዝ ስላልኩባት እየተነጫነጨች ነው። "እኔ እኮ የተሻለህ ስለመሰለኝ ነው የቀረብኩህ። እንዳመልህ ልትርቀኝ ፈልገህ ነዋ ችላ ማለት የጀመርከው?" ብላ ላከችልኝ። "ኧረ ሊ እንደዛ አይደለም። ኔቶርክ እያስቸገረኝ ስለሆነ ነው።" ብዬ መለስኩላት። ልክ ይሄን ፅፌ ወደ ሂክማ አካውንት ስገባ ኦንላይን ላይ አገኘኋት። "ሃይ! እንዴት ነሽ?" ብዬ ላኩላት። "አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ!" ብላ መለሰችልኝ። እንግዲህ ወግ ማጥበቋን መጀመሯ ነው። "ያሰቡት ለመድረስ ትዕግስት ያስፈልጋል። ታራራም ቢያስወጣ ልትወጣ ግድ ይላል።" ስል ለራሴ ገጠምኩ በውስጤ። "ወአለይኩሙሰላም።" ብዬ መለስኩላት። "አላህ (ሱ.ወ) ሰላምታ በቀረበላችሁ ግዜ ከሷ በተሻለ፤ አልያም ቢጤዋን መልሱ ብሏል!" አለችኝ። ኦፏ! አሁንስ አበዛችው። እንዴ ፌስቡክ ነው ወይስ መስጂድ የገባሁት? "እሽ! ወአለይኩሙሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ! ቤት ባይተኙ ኖሮ ድምጼንም ከፍ አድርጌ እመልስልሽ ነበር!" አልኳት በንዴት። እንኳንም ፊት ለፊቴ አልኖረች። ይሄኔ ፊቴን አይታ ደንግጣ ነበር። "አይደል?" ስትል ባጭሩ መለሰች። "አዎ! እንዴት ነሽ ብየሽ ነበር። ነው ወይስ ደህና አይደለሽም?" "አልሐምዱሊላህ! ምን እሆናለሁ ብለህ ነው?" "የኔ ነገር ምን ይታወቃል። ባንድ ቀን በናፍቆት ሰላም ነስቼሽ ከሆነ ብዬ ነዋ! ሃሃሃ" "ተው ባክህህህ! አንተ የናፈቅከኝ ቀን ድል ያለ ሰደቃ አወጣለሁ።" "አሳይሽ የለ! ሰደቃሽን የሰርጋችን ድግስ ካላደረኩት ሳሊም አይደለሁም።" "የአቡበክር ኢማን፣ የዑመር ጀግንነት፣ የሰላሃዲን አል አዩቢ ወኔ ካለህ እንደሚሳካልህ እርግጠኛ ነኝ።" አለች። ስለጠራቻቸው ሰዎች የጠለቀ ዕውቀት ባይኖረኝም ታላላቅ ሰዎች እንደሚሆኑ እርግጠኛ ነኝ። የዚህን ያህል እራሷን መስቀሏ አናደደኝ። "ተይ ግን በኋላ አወዳደቅሽ አያምርም!" ልላት አሰብኩና ሃሳቤን ቀይሬ፤ "እራስሽን እንዴት ነው ምታይው ባክሽ?" ስል ጠየቅኳት። "መስታውት ፊት ቁሜ ነዋ!" ስትል መለሰች። ኧረ መቀለድ! ይሄኔ የአባቢ ጨጓራ ቢኖርብኝ ኖሮ ተቃጥዬ ነበር። "ቀልዱንም ትችይበታለሽ¡" አልኳት። "አንዳንዴ እሞክራለሁ። ይበልጥ ግን ቁም ነገር ያስደሰደተኛል። ለምን እንዲህ አናረግም?" ስትል ጠየቀችኝ። ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቼ "እንዴት? ምን?" ስል ጠየቅኳት። ምን እንዲህ ልቤን እንደሰቀለው አላውቅም። ብቻ ለማመን ባልፈልግም ውስጤ ውስጥ ግን አንዳች ለውጥ እየተካሄደ እንዳለ ይታወቀኛል። "ለምን አንመካከርም ማለቴ እኔ አንድ ምክር ስልክልህ አንተም አንድ ምክር ትልክልኛለህ።" አለችኝ። እኔ የጠበቅኩት ሌላ ነገር ስለነበር ይህን ስትለኝ ትንሽ ተናደድኩ። ቢሆንም አደን ላይ ስለሆንኩ እንዳረገችኝ መሆን እንዳለብኝ ራሴን ነገርኩት እና፦ "እሽ እንዳልሽ" አልኳት ቸልተኝነቴን በሚገልጽ መልኩ። "እሽ ሃሳቡን ያመጣሁት እኔ ስለሆንኩ እኔ ልጀምር።" "እሽ ይቻላል።" "ምክር አንድ : ልጅነት የለሰለሰ መሬት፣ ወጣትነት ያዝመራ ዘመን፣ ሽምግልና ደግሞ ያጨዳ ጊዜ መሆኑን አስተውል። በሽምግልናህ የምታጭደው በወጣትነትህ የዘራሃውን ነውና ዛሬ ለምትዘራው ጥንቃቄ አድርግ።"  የላከችው መልዕክት አያቴን አስታወሰኝ። የማሚ አባት በየሳምንቱ እሁድ እሁድ ልንዘይረው በሄድን ቁጥር ሰብስቦ ይመክረናል። እኔ ደግሞ ምክር አላርጅኬ ነው። ለዛም ነው ከማሚ እናት (ከአያቴ) ሞት በኋላ ለዚያራ ወደ አያቶቼ መሄድ የምጠላው። ነብሷን ይማራትና  አያቴ እያለች የራሷን፣ የቤተሰቦቻችንን እና ሌሎች አዝናኝ ታሪኮችን ስለምትነግረን እሁድ እስክትደርስ ትናፍቀን ነበር። አሁን ግን የወንዱ አያቴ ምክር እንደሚጠብቀኝ ስለማውቅ እሁድ ሲደርስ ይጨንቀኛል። ያ አልበቃ ብሎ ይህች ሂክማ ተብዬ የቅዳሜ ምሽቴን እሁድ ካላደረኩ ትል ይዛለች። እንግዲህ ተረኛው እኔ መሆኔ ነው። በሰዓቱ አዕምሮዬ ውስጥ ምንም አይነት ምክር አልመጣልህ አለኝ። ለነገሩ መች ተመከርኩና ሰው እመክራለሁ። አያቴ እስከዛሬ የመከረንን ምክሮች ከልቤ አዳምጥ እንዳልነበር አሁን ተገለፀልኝ። ይሄኔ ሪ ብትሆን ኑሮ እንደ ሀምሌ ጎርፍ ባዥጎደጎደችው ነበር። ግራ ተጋብቼ እንዳለሁ፤ "እ ምነው ዝም አልክ ተረኛው አንተ እኮነህ አንድ ምክር ላክልኛ!" አለችኝ። "እሽ ትንሽ ጠብቂኝ እያሰብኩ ነው።" ስል መለስኩላትና ባዶውን ጭንቅላቴን መበርበር ጀመርኩኝ... ይቀጥላል!

🧕ሂክማ🧕 ክፍል አምስት ✍ ኢብኑ ኢብራሂም "አንተ በቃ ጎርምሰህ ቀረህ አይደል?" አለኝ አባቢ ሁሉንም ሰላም ብዬ ቁጭ እንዳልኩ። ምንም ምላሽ ሳልሰጥ ዝም አልኩ። ብዙ ጊዜ እንዲህ ሲለኝ ዝም ነው የምለው። "ሶላቱንም አልሰግድም አልክ!" አለኝ አሁንም። "አባቢ አንድ ቀን እሰግዳለሁ አልኩህ አይደል? ለምን ትጨቀጭቀኛለህ? ባይሆን የትላንቱን ታሪክ ቀጥልልን!" አልኩት ለማረሳሳት። "መጀመሪያ እራት ይበላ!" አለኝ። በቃ አባቢ ሁሌም እንዲሁ ነው። መቆጣት ይፈልጋል። ነገር ግን ስለሚወደኝ ይተወዋል። ሳረሳሳውም የረሳ መስሎ ነገሩን ያበርደዋል። ማሚም ተስፋ ስለቆረጠች እርግፍ አርጋ ትታኛለች። "አዎ እኔ እራሴ እስከሚመሽ በጣም ነው ስጓጓ የዋልኩት። ቶሎ እንብላና ትነግረናለህ።" አለች የኔንና ያባቢን ምልልስ ዝም ብላ ስታዳምጥ የቆየችው ሪ። ራት ከበላን በኋላ ትኩስ ሻይ እየጠጣን አባቢ ታሪኩን ቀጠለልን። "...እንዳልኳችሁ እናታችሁን ለመጀመሪያ ጊዜ ካየኋት ጀምሮ ልቤ ውስጥ ገባች። በቀጣዮ ቀን ምናለ እቃ ልትገዛ በመጣች እያልኩ ሳለ አጅሪት ከተፍ አለች። እንደተኮሳተረችም፦ 'አጃክስ ስጠኝ!' አለችኝ።" ሪ አባቢን አቋርጣ "ብቻ ፓስታ ሰጠኋት እንዳትለኝ!" ብላ መሳቅ ጀመረች። "እስኪ ዝም በይ ቃጭል!" አልኳት ተናድጄ። ማሚም ተናዳባት ኑራ፤ "ቆይ እንዴታባቷ ነው የሚቆላት?" ስትል ተናገረቻት። "እንዴ ማሚ ከኛ በላይ ተመሰጥሽ እኮ! ታሪኩ ያንች አይደለም እንዴ? ነው ወይስ ካንች በፊት ሌላ አግብቶ ነበር?" አለቻት አሁንም እየሳቀች። "ሂጅ የልጅ ቡዳ!" ብላ ጀርባዋ ላይ አቀመሰቻት። ማሚ በሪ ንግግር አፍራ ቀያይ ጉንጮቿ ፍም መሰሉ። ሁሌም የማሚ አይናፋርነት ይገርመኛል። ሌላው ቀርቶ እኛ ልጆቿን እንኳን ታፍራለች። ለዛም ነው የነ አባቢን የፍቅር ታሪክ በጉጉት የምሰማው። አይን አፋር ከመሆኗ ጋ አባቢ እንዴት አድርጎ በፍቅር ሊረታት እንደቻለ ለማዎቅ። አባቢ "አንች ልጅ በስርዓት ማታዳምጭ ከሆነ ማውራቴን አቆማለሁ!" ሲል አስጠነቀቃት። "እሽ በቃ አላወራም ይሄው!" ብላ አፏን በመዳፏ ያዘች። አባቢም ትረካውን ቀጠለ። "እንዳልኳችሁ ኮስተር እንዳለች  'አጃክስ ስጠኝ!' አለችኝ። መደርደሪያው ላይ የነበረው አጃክስ አልቆ ስለነበር ከውስጥ ላወጣ ወደ ጓዳ ገባሁ። ከውስጥ አንድ ካርቶን አምጥቼ እየፈታሁ እያለ እናታችሁ ለዕቃ መጠቅለያነት የገዛሁት ጋዜጣ ላይ አፍጥጣ ስታነብ አየኋት። በውስጤም "አሃ ግጥም ትወዳለች ማለት ነው!" አልኩኝ። መፅሔቱ ላይ ያለው ፅሁፍ ከታዳሚያን አምድ ውስጥ ያለን አንድ የጋዜጣው ተከታታይ ደንበኛ የላከው ግጥም ነበር። እንደወደደችው ስላወቅኩ በዛው ጋዜጣ ጠቅልዬ ሰጠኋት። ፍላጎቷን ስለተረዳሁ ደስ አላት። አቤት ደስሲላት ደስ ስትል! የዛኔ ውበቷ እንዳሁኑ እንዳይመስላችሁ። በቃ ስትኮሳተርም ስትስቅም ያምርባታል። አሁንማ እድሜ ለእናንተ አስረጃችኋት።" አለ አባቢ ወደ ማሚ በፍቅር እየተመለከተ። እኛም ስናፈጥባት ማሚ "እንዴ ምን ሆናችኋል? ልትበሉኝ ነው እንዴ?" አለችን። እውነትም ግን ቆንጆ ነበረች። ቀይና ክብ ፊቷ ከስስ ቅንድቦቿ፣ ከትላልቅ አይኖቿ እና ከአይኗ ጀምሮ እስከ ከንፈሯ ድረስ ቀጥ ብሎ ከወረደው አፍንጫዋ ጋር ተዳምረው አይንን ታፈዛለች። "በወጣትነቷ እንዴት ልታምር ነው?" ስል አሰብኩ። "ልክ እኔን ነበር አይደል ምትመስለው?" አለች ሪ። እስካሁን ምንም አልተናገረችም ነበር። ሪ እውነቷን ነው። በሁሉ ነገሯ ማሚን ነው የምትመስለው። እኔ ከቅላትና ከአንዳንድ ነገሮች ውጭ ወደ አባቢ ነው የማደላው። አባቢ የጠይም ቆንጆ ነገር ነው። "አዎ አንችን ነበር ምትመስለው። ግን አንች እንደሷ አታምሪም!" አላት አባቢ እየሳቀ። ሪ እንደማኩረፍ አለች። "ስቀልድሽ ነው የኔ ቆንጆ ቁርጥ አንችን ነው የምትመስለው።" አለና ትረካውን ቀጠለ። "እናም በዚህ መልኩ እኔና እናታችሁ ደህና ደንበኛ ሆንን። መፀሐፍ ከእጇ ተለይቶ ስለማያውቅ ማንበብ እንደምትወድ ተረዳሁ። እኔ አሪፍ አሪፍ ፅሑፍ ያለበትን መፅሔት እና ጋዜጣ መርጬ አስቀምጥላትና እቃ ልትገዛኝ ስትመጣ በዛው ጠቅልዬ እሰጣታለሁ። እሷም ደስ ብሏት ትሄዳለች። አንድ ቀን እጣን ልትገዛኝ ስትመጣ አውቄ በልሙጥ ወረቀት ጠቅልዬ ሰጠኋት። በጣም ቅር እንደተሰኘች ከፊቷ ላይ መረዳት ቻልኩ። እንደምታውቁት የእናታችሁ ፊት እንደ መስታዎት የውስጡን መደበቅ አይችልም። እኔም ለማናደድ ፈልጌ ስለነበር በመናደዷ ደስ ተሰኘሁ። ምንም ሳትናገር እቃውን ይዛ ሄደች። በነገራችን ላይ እስካሁን ምንም ተነጋግረን አናውቅም። ሂዳ ትንሽ እንደቆየች የሰጠኋትን እጣን መልሳ ይዛ መጣች። 'ምነው ምን ሆነ?' ስል ጠየቅኳት። 'አይ እሩብ ኪሎ ስኳር ነው የተባልኩት።' አለች። እሽ ብዬ እጣኑን ተቀበልኳትና ስኳሩን በፌስታል ልመዝንላት ስል፤ 'አይ በጋዜጣ ይሁንልኝ!' አለችኝ። አነጋገሯ ትዕዛዝ ይመስል ነበር። 'ከፈለግሽ እሽ!' ብዬ በጋዜጣ ጠቅልዬ ሰጠኋትና ሄደች። የመለሰችውን እጣን ወደ ነበረበት ልመልስ ወረቀቱን ስፈታ ውስጡ ፅሁፍ አገኘሁበት። ስሰጣት ምንም ፅሁፍ እንዳልነበረው እርግጠኛ ስለነበርኩ እሷ እንደ ፃፈችው አረጋገጥኩ። ተቻኩዬም አነበብኩት። 'ላታስጨርስ ነገር አጉል አስለምደህ ምን ይሉት ነገር ነው የዛሬን መንፈግህ'...የሚል ግጥም ነበር የፃፈችልኝ። በፅሁፍም ቢሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ስላናገረችኝ ደስ ተሰኘሁ።" "ማሚ ግን የምር ስኳር ነበር እንድትገዢ የተላክሽው?" ስል ጠየቅኳት። "አይ አይደለም። ግዥ የተባልኩትማ እጣን ነበር። ነገር ግን በባዶ ወረቀት ሲጠቀልልልኝ ተናደድኩና ሳያዩኝ ጓሮ ገብቼ እጣኑን ወደ እቃ ገለበጥኩትና ወረቀቱ ላይ ግጥሙን ፅፌ እንደገና ጠቅልዬ መለስኩለት።" "ማሚዬ ስኳሩን ይዘሽ ስትሄጅ ቤት ምን አሉሽ?" ስትል ጠየቀቻት ሪሃና። "እነሱ እጣን መስሏቸው ሲከፍቱት ስኳር ሆኖ አገኙትና እናቴ 'አንች ልጅ እጣን እኮ ነው አምጭ የተባልሽው?' አለችኝ።  'እጣን ነበር እንዴ ያላችሁኝ?' አልኳቸው አውቄ። 'ቆይ ከመች ጀምሮ ነው ሩብ ኪሎ ስኳር ለዚህ ቤት ተገዝቶ የሚያውቀው?' ሲል ጠየቀኝ አባቢ። 'በቃ እንደዛ ያላችሁ መሰለኛ!' አልኳቸው። 'አንች ልጅ ፍቅር ይዞሽ እንዳይሆን?' አለችኝ እናቴ።" እኔና ሪ በአንድ ድምፅ "እና ምን አልሻት?" ስንል ጠየቅናት። "ምን እላታለሁ አልያዘኝም ነዋ!" አለችን። "የምር ግን አልያዘሽም ነበር?" አለቻት ሪ "ይዞኛል!" አለች። በማሚ ንግግር ተገርመን ሁላችንም አፈጠጥንባት። "ምን ታፈጡብኛላችሁ? አዎ ፍቅር ይዞኝ ነበር። የያዘኝ ግን ካባታችሁ ሳይሆን ከስነ ፅሁፍ ነው!" አለች፡፡ አባቢን ጨምሮ ሁላችንም ሳቅንባት። "ኧረባክሽ ከስነ-ፅሁፍ ቢሆን ኖሮ ጋዜጣውን ገዝተሽ አታነቢም ነበር። ምን አስሬ አመላለሰሽ?" አልኳት። "ሂድ! ባለጌ!" አለችኝና ለአባቢ "አንተ ነህ ከልጅ ፊት የማይወራ ወሬ እያወራህ ምታዋርደኝ።" አለችው። "ልጆች ስለ ወላጆቻቸው ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባቸው። ዝም በሏት እኔ እቀጥልላችኋለሁ።" አለና ታሪኩን ይተርክልን ጀመር . . ይቀጥላል...

#ሂክማ ክፍል አራት እኔ ከዚያን ቀን ወዲህ ስለፍቅር አንስቼባት አላውቅም። ከኔ በኩል ሳይነሳ ሲቀር ራሷው ጠየቀችኝ። "ፌሩ መጀመሪያም እኮ እንቢ ስላልሽኝ እንጅ እኔ ደስታዬ ነው።" አልኳት። ከዚህ በኋላ እሷ ፍቅሩን እኔ ማስመሰሉን አደራነው። ጓደኞቼ ምንም እንደማይሳነኝ አረጋገጡልኝ። መጀመሪያውንም ለሷ ፍቅር አልነበረኝምና ከጥቂት ወራቶች በኋላ እርግፍ አድርጌ ተውኳት። እሷ ግን ችላ ስላት ባሰባት። በዛኑ አመት ውጤቷ ቀነሰ። በሷ ቦታ እኔ ሆንኩ፡፡ በኔ ቦታ ደግሞ ሌላ ሰው። እሷ ወደ ሶስተኛ ደረጃ ዝቅ አለች። የሚገርመው ግን አሁንም ድረስ ተስፋ አልቆረጠችም። ከግጥሞቹ በላይ ከሰፈሩት አስተያየቶች ውስጥ የመጨረሻው አስተያየት የሷ ነበር። የሂክማ ተብየዋም እጣ ከሷ እንደ ማይለይ "ሴቶችን አትፈትን" ከሚለው ንግግሯ መረዳት ችያለሁ። "ላታመልጭኝ አታሩጭኝ!" አለ ያገሬ ሰው። አልኩኝ ለራሴ። "ከመከርሽኝ አይቀርማ በደንብ ምከሪኛ¡" አልኳት በማሾፍ አይነት። "እኔ የመምከር ደረጃ ላይ አልደረስኩም።" "ቢያንስ ከኔ ትሻያለሽ።" አልኳት ቃላቶቹ እንደ ኮሶ ቢመሩኝም በባዶ ወጥመድ አይጥ አይጠመድምና ትንሽ ሙገሳ ነገር ጣል ማድረግ አለብኝ። ከተናገርኩት በኋላ ግን አንገሸገሸኝ። ሴት ልጅን ከመናቄ የተነሳ በምንም መልኩ እንድትበልጠኝ አልፈልግም። መቼም ሴትን ስጠላ ያየ ከዘር ማንዘሬ ውስጥ ሴት መኖሩን መጠራጠሩ አይቀርም። የሴት ልጅ ጥላቻዬ የሚመነጨው ሴትን ልጅ ከፆታዊ ግንኙነት በዘለለ ስለማላስባቸው ይመስለኛል። በፆታዊ ግንኙነት ደግሞ ለኔ ቀላሎች ስለሆኑ እንቃቸዋለሁ። "ማን ከማን እንደሚሻል የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው። ለማንኛውም ያወቅኩትን ያህል ላለመደበቅ እሞክራለሁ!" "ተባረኪ እንኳንም እበልጥሃለው አላልሽ" አልኩ ለራሴ። "ለማንኛውም ለሱቢህ መነሳት እንዳይከብደኝ ልተኛ! አላህ ካለ ነገ እናወራለን!" አለችኝ። "እሽ! ይቻላል።" አልኳት። "ምክሩን ከዚሁ ልጀምራ "እሺ" ሳይሆን "ኢንሻ አላህ!" ነው ሚባለው። በቃ ደህና እደር ወሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላህ" ብላኝ ወጣች። "ወአለይኩሙሰላም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ" ብዬ መለስኩላትና ከሷ ጋር ሳወራ የዘነጋኋቸውን ሌሎች ሜሴጆችን ለማየት ገባሁ። ብዙ መልዕክቶች ደርሰውኝ ነበረ። ሁሉም ሳልመልስላቸው ስቀር ተቀይመውኛል። ከመልዕክት ላኪዎች ውስጥ ዮኒ ነበረበት። "ስማ አንተ! ብለህ ብለህ ደግሞ እኛም ላይ ልትኮራ አሰብክ?" አለኝ። "ምን ባክህ አንዲት ጥሬን አበስላለሁ ብዬ ስሰቃይ ቆይቼ እኮ ነው።" "ይሄኔ ልክ ልክህን ከነገረችህ ልጅ ጋር እልህ ተያይዘህ ይሆናል። ሃሃሃ" "አንተ ቡዳ በምን አወቅክ?" "አተን መች አጣሁህና! ምን ላይ ደረሳችሁ ታዲ?" "እሱን ነገ ስንገናኝ እነግርሃለሁ። አሁን ሌሎቹ እየተንጫጩ ነው ላሽ በል።" አልኩትና ለሌሎቹ ሴቶች ምላሽ መስጠት ጀመርኩ። ስጨርስ ሁሉንም ተሰናብቼ ተኛሁ። * ዛሬ ቅዳሜ እንደመሆኑ አርፍጄ ወደ 4:00 አካባቢ ነው ከእንቅልፌ የተነሳሁት። ተጣጥቤ ቁርሴን በላሁና እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ እያጠናሁ ቆየሁ። ምሳዬን ከማሚና ከሪሃና ጋር በልቼ ወደ ዮኒ እና ሀማድ ዘንድ አቀናሁ። ዩሀንስ እና ሃማድ በጣም የምወዳቸው የት/ቤት ጓደኞቼ ናቸው። ሦስታችንም የራሳችን የሆነ ባህሪ ነው ያለን።  የኔ ባህሪ እንደ ነገርኳችሁ ነው። ዮኒ ደግሞ በጣም ምላሰኛ ነው። ሲናገር ያየው ሁሉ "ምላሱ ጤፍ ይቆላ የለም እንዴ?" ማለቱ አይቀርም። በተለይ ሴቶችን እንዴት መጥበስ እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቅበታል። ሴቶችም ጨዋታውና ቀልዱ ስለሚማርካቸው በፍቅር ይወድቁለታል። ሃሚ (ሃማድ) ደግሞ እጅግ ሲበዛ አይን አፋር ነው። አባቱ የመስጅድ ሸይኽ ስለሆኑ አስተዳደጉ ላይ ተፅዕኖ ሳያሳድሩበት አልቀሩም። በተለይ ሴቶችን በጣም ነው የሚፈራቸው። እንደዛም ሆኖ ሴቶች ያሳድዱታል። ለጓደኞቹ ግን ሟች ነው። ለኛ ሲል የማያደርገው ነገር የለም። አንዳንዴ እንዲያውም ከኛ ጋር መሆኑ የማይመጥነው መስሎ ይታየኛል። በቃ እሱ ከእኛ ጋር መጃጃል ያለበት ሰው አልነበረም። ቢሆንም ግን ስለምንዋደድ እንዲርቀን አንፈልግም። ለእሱም ቢሆን ከኛ መለየት ሞቱ ነው። እንዲህ የተለያዬ ባህሪ ቢኖረንም ሰዎች ዘንድ ያለን ተፈላጊነት አንድ ያደርገናል። ወንዶች የኛ ቡድን ውስጥ ቢቀላቀሉ ሰርጋቸው ነው። ሴቶች ደግሞ ከእኛ ውስጥ አንዳችንን የግላቸው ማድረግ ቢችሉ ሰርግና ምላሻቸው ነው። እኔን በኩራቴ፣ ዮኒን በጨዋታው፣ ሀሚን ደግሞ በአይን አፋርነቱ። ዮኒ እና ሃሚ ሁሌም የምንገናኝባት ካፌ ውስጥ ቀድመውኝ አገኘኋቸው። ዮኒ ለሃሚ ስለ ማታዋ ልጅ ነግሮት ስለነበር መጥቼ እስክነግራቸው ጓጉቶ ነበር። ሃሚ ሴትን መቅረብ ቢፈራም እኛ ስለ ሴቶች የገጠመንን ስንናገር መስማት ግን ነብሱ ነው። ገና ሰላም ብዬ ሳልቀመጥ፤ "ሳሊሜ ቁጥር ሁለት ፌሩዛ እንዴት ናት?" ሲል ጠየቀኝ። "ተዋት ባክህ መያዟ ላይቀር ካላሯሯጥኩህ እያለች ነው።" አልኩት። "እስኪ ያወራችሁትን አንብብልን!" አለኝ ዮኒ። ስልኬን ከፍቼ አንድም ሳላስቀር አነበብኩላቸው። "ሳሊሜ እች ከበድ ሳትልህ አትቀርም። ሸኪ ነገር ነች መሰል።" አለ ሃሚ። "ሳሊሜን አታውቀውም ማለት ነው። የፈለገውን እስኪያገኝ ሸኪ ከመሆን  አይመለስም።" አለ ዮኒ። ሁላችንንም አሳቀን። "አንተ ብቻ ጠንከር በል እኔ ከአባቴ ኪታብ ሰርቄም ቢሆን አመጣልሃለው።" አለ ሃሚ። በሱም ንግግር ከልብ ሳቅን። ዛሬ ሲኒማ ለማየት ነው ያሰብነው። ስለሆነም ተያይዘን ወደ ሲኒማ ቤት ሄድን። ከነ ዮኒጋ ወደ ምሽት አካባቢ ተለያየሁና ወደ ቤቴ ሄድኩ። ቤት ስገባ አባቢ ከኢሻ መልስ ቤት ገብቶ አገኘሁት። . . . ይቀጥላል!

💜 የእርጅና ጊዜ ላይኖረን ይችላልና ወጣትነታችንን በደጋግ ነገራቶች እንሙላው ።

🧕ሂክማ🧕 ክፍል ሦስት አሁን ላይ የ18 ዓመት ልጅ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነኝ። የተወለድኩት መካከለኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች ቢሆንም ለሚያየኝ ግን የባለ ሃብት ልጅ ነው የምመስለው። ከኔ ማማርና መዋብ ጀርባ ግን የወላጆቼ መጎሳቆልና መስዋትነት ነበር። በትምህርቴም ጎበዝ ከሚባሉት ተርታ ነኝ። በዲን በኩል ግን ማሚ በግድ እየተቆጣች ካስቀራችኝ ቁርዓን ውጭ ምንም የማውቀው ተአምር የለም። ሶላት እንኳን ምሰግደው በአመት ሁለቴ ብቻ ነው። እሱም የኢድና የአረፋ በዓል ጊዜ። ወላጆቼ እንድስተካከል ብዙ ቢጥሩም ሊያሸንፉኝ አልተቻላቸውም። የሚገርማችሁ ደግሞ ት/ቤት ውስጥም ልክ እንደ ቤቴ ተወዳጅ መሆኔ ነው። በተለይ ደግሞ ሴቶች ዘንድ። ከማሚ ከወረስኩት ቁንጅና ላይ ቤተሰቦቼ  ከሚያሳዩኝ ከልክ ያለፈ አክብሮት የመነጨው ኩራቴ ታክሎበት ሴቶች የሚያሳድዱኝ  ሰው ሆኛለሁ። እኔ ሴትን ልጅ ስለምንቅ ለጊዜ ማሳለፊያነት እንጅ ለፍቅር ቀርቤያቸው አላውቅም። በኔ አይን የትኛዋም ሴት አትመጥነኝም። እንደዚያም ሆኖ ግን በአመት ውስጥ ሦስትና አራት ሴቶችን አቀያይራለሁ። ከሁሉም የሚገርመኝ ደግሞ ሴቶች ይህን ዓመሌን እያወቁ እንኳን "ምናልባት የኔ አደርገዋለሁ!" በሚል ተስፋ እኔን ለማግኘት መፎካከራቸው ነው። ሌላው ቀርቶ ቀርቤ የራቅኳቸው ሴቶች እንኳን ሳይቀሩ "የዛሬን አያርገውና እኔም ፍቅረኛው ነበርኩ።" እያሉ ይፎክራሉ። ራሴን ያካበድኩባችሁ እንደ ሚመስላችሁ እርግጠኛ ነኝ። እውነታው ግን እንደ ነገርኳችሁ ነው። ለነገሩ ሴት ልጅ በተፈጥሮዋ ኮራ የሚልባትንና ችላ የሚላትን ወንድ እንደምትወድ የሚያውቅ የተናገርኩት እውነት መሆኑን ለማመን አይቸገርም። ታዲያ እኔም ቢሆን ሴቶች ሲያዳንቁኝ፣ ወንዶች ሲቀኑብኝ በጣም ነው ደስ የሚለኝ። ለዛም ነው በየ ጊዜው ፌስቡክ ላይ ፎቶዬን የምለጥፈው። ዛሬ የነ ማሚን ታሪክ ስንሰማ አምሽተን መኝታ ክፍሌ ከገባሁ በኋላ ፌስቡኬን ከፍቼ ያገኘሁትን ላይክ መቁጠር፣ የተሰጠኝን ኮመንት ማንበብ ጀመርኩ። ዛሬም እንደተለመደው ብዙ ላይክ እና ኮመንቶች ደርሰውኛል። "መላዕክት ልጅ መውለድ ጀመሩ እንዴ?" "እኔ ምለው እየሱስ ነው ዮሱፍ ድጋሚ ይመጣል የተባለው? በዕውነቱ የነብዩ ዩሱፍ መልክ ነው የተሰጠህ!" "እርግጠኛ ነኝ ወላጆችህ አንተን የወለዱ ዕለት በደስታ ራሳቸውን ስተዋል።" እነዚህ ከተሰጡኝ አስተያየቶች ውስጥ ጥቂቶቹ ሲሆኑ፤ በግጥም መልክም ያወደሱኝም ነበሩ። "ውበትህ ቢካፈል፤ ለዓለም ህዝብ ሁሉ፣ ይትረፈረፍ ነበር፤ ተዳርሶ ለሁሉ!" "ጌታዬን ተማፀንኩ፤ ቢያድለኝ ውበትክን፣ ሙሉው እንኳን ቢቀር፤ አፍንጫና አይንህን!" "ውይ ሴቶች!" አልኩኝ ስራዬ ብለው ለኔ ስንኝ መቋጠራቸው አስደንቆኝ። ቆይ አሁን እንዲህ ቅዱስ ሲያርጉኝ እያየሁ ብኮራ ይፈረድብኝ ይሆን? አስተያየቶችን ማንበቤን ቀጥያለሁ። ከክላስ ሴት ጓደኞቼ አስተያየት ያልሰጠ የለም ማለት ይቻላል። ነብሴ በሀሴትና በኩራት ተወጥራ እያነበብኩ ሳለ አንድ አስደንጋጭ አስተያየት አነበብኩና ኩምሽሽ አልኩ። የተሰማኝን ስሜት ግለፀው ብትሉኝ ንፍሮ እየበላችሁ እያለ ጠጠር ወይም ጥሬ እህል ሲገጥማችሁ በሚሰማው ስሜት እገልፀዋለሁ። በቃ ይሄ አስተያየት ጭቃ ውስጥ እንዳለ እሾህ ተሰንቅሮ ሳገኘው አመመኝ። ራሴን ከሰቀልኩበት ማማ አምዘግዝጎ ጣለኝ። መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነበር፦ "ውስጥህ ልክ እንደ ውጭህ በኢማን ያሸበረቀ ካልሆነ ውበትህ ልክ መሬት ላይ እንደ ፈሰሰ ቀለም ነው። 'አላህ ወደ ልቦቻችሁ እንጅ፤ ወደ ተክለ ቁመናችሁ አልያም ወደ መልካችሁ አይመለከትም።' ይሉናል ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)" ሀዲሱን ሳነበው ረሱል ከብዙ ዘመናት በፊት የተናገሩት ሳይሆን ልጅቷ እኔን ለማናደድ የፈጠረችው ንግግር መሰለኝ። ወይም ደግሞ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከዘመናት በፊት እኔን አይተው ተናግረውት ይሆን እንዴ? ስል አሰብኩ። ኮመንቱን የሰጠችኝን ልጅ ፕሮፋይል መበርበር ያዝኩ። ስሟ ሂክማ ይላል። የሆነች ሀይማኖተኛ ነኝ የምትል ሳትሆን አትቀርም። የምትፓስታቸው ፖስቶች ሁሉ ወይ የነብዩ አልያም የታላላቅ ሊቃውንት ጥበብ አዘል ንግግሮች ነበሩ። እስኪበቃኝ ከበረበርኩ በኋላ፤ መልዕክት መፃፊያው ጋ ገብቼ፤ "ብዙ ከማውራትሽ በፊት በእነዚህ ፎቶዎች ተዝናኝ!" ብዬ ወደ አምስት የሚሆኑ ፎቶዎቼን መርጬ ላኩላት። በሰዓቱ ኦን ላይን አልነበረችም ነበር። ገብታ እስክታዬው ድረስ የተላኩልኝን መልዕክቶች መመለስ ያዝኩ። ከ10 ደቂቃ በኋላ ፌስቡኬ ከልጅቷ መልዕክት እንደተላከልኝ አበሰረኝ። ተቻኩየም ከፈትኩት። ልጅቷ ከኔ የባሰች ኩራተኛ ነገር ሳትሆን አትቀርም። ለላኩላት መልዕክት እንዲህ ስትል ነበር የመለሰችልኝ፦ "ከላክልኝ ፎቶዎች ውስጥ የውስጥህን ውበት የሚገልፀው ፎቶ የትኛው እንደሆነ መለየት አልቻልኩም።" "የውስጥ ውበት ማለት አበዛሽሳ መልከ ጥፉ ሳትሆኝ አትቀሪም! ሃሃሃ" ብዬ ላኩላት። "ምናለ መልኬ ከአለም አንደኛ መልከ ጥፉ በሆነና ልቤ በኢማን ባሸበረቀ!" ስትል መለሰችልኝ። ልጅቷ ትንሽ ከበድ ሳትል እንደማትቀር ገመትኩ። ቢሆንም ግን እጅ መስጠት አልፈለኩም። በነገራችን ላይ በጣም እልህኛ ነኝ። የፈለግኩትን እስከማገኝ ድረስ አላርፍም። "እስኪ ንገሪኝ ውስጤ መጥፎ መሆኑን እንዴት ልታውቂ ትችያለሽ?" "የውስጥህ ማንነት ከተግባርህና  ከፊትህ ላይ መንፀባረቁ አይቀርም። ለማንኛውም እኔ መጥፎ ነህ የሚል ቃል አልወጣኝም። አንድ ነገር ግን ልመክርህ እፈልጋለሁ። ፎቶዎችህን እየፓሰትክ ለሴቶች ፈተና አትሁን! አላህን ፍራ!" አለችኝ። መቼም አላህ አንዴ ልባችሁን አይዝጋባችሁ። ከለገሰችኝ ምክር ውስጥ "ሴቶችን የሚፈትን ውበት አለህ!" የሚል አድናቆትን ነበረ የተረዳሁት። "መቼም ፈተና ባልሆንባት ኖሮ ሴቶችን አትፈትን። አትለኝም ነበር።" አልኩ በውስጤ። "በቅርቡ ሳሊሜ ሳሊሜ አስብልሽ አይደል!" ስል ፎከርኩ። እልኻም ነኝ አላልኳችሁም? እኔ ማንም ሴት እንቢ እንድትለኝና ሳታደንቀኝ እድታልፍ አልፈልግም። እስካሁንም ከአንዲት ሴት በቀር እምቢ ብላኝ አታውቅም። እሷም ፌሩዛ ትባላለች። የት/ቤታችን ጎበዝ ተማሪና ለማንም ፊት የማትሰጥ ልጅ ነበረች። ታዲያ አንድ ቀን ጓደኞቼ እሷን መጥበስ ከባድ መሆኑን ሲያወሩ ሰማሁና "በኔ ጣሉት አሁን ሳንበረክካት ታዩ የለ።" ብያቸው ወደሷው ሄድኩ። "ፌሩዬ አንድ ነገር ልነግርሽ ፈልጌ ነበር።" አልኳት። የኔን ዝና ታውቅ ስለነበር ብዙም ታስቸግረኛለች ብዬ አላሰብኩም ነበር። በዚያ ላይ በትምህርትም ተፎካካሪዋ ነኝ። "ምን ነበር?" አለችኝ። እንደ ምወዳት እና ለፍቅር እንደ ምመኛት ገለፅኩላት። "ሳሊሜ በዚህ ሰዓት ለኔም ላንተም የሚበጀን ትምህርታችን ላይ ማተኮር ነው። እኔ ደግሞ ዓላማ ያለኝ ሰው ነኝ። በፍቅር ምክኒያት ከዓላማዬ መሰናከል አልፈልግም!" ብላ አሳፍራ ሰደደችኝ። ጓደኞቼ፦ "አላልንህም?" እያሉ ተሳለቁብኝ። እኔ ግን እሷን ሳላንበረክክ ማረፍ እንደሌለብኝ ራሴን አሳመንኩ። በማግስቱም "ያልሽኝን አስበቤት ልክ እንደሆንሽ አምኘበታለሁ። እና ለምን አብረን አናጠናም?" ስል ጠየቅኳት። ሳታንገራግር በየዋህነት ጥያቄዬን ተቀበለችኝ። ከዚያ ቀን በኋላ እየተደዋወልን ላይብረሪ መሄድ፣ ማጥናትና አሳይመንት መስራት ጀመርን። ቀስበቀስ እየወደደችኝ መጣች። እኔ ከዚያን ቀን ወዲህ ስለፍቅር አንስቼባት አላውቅም። ከኔ በኩል ሳይነሳ ሲቀር ራሷው ጠየቀችኝ። . . . ይቀጥላል

🧕ሂክማ🧕 ክፍል ሁለት : "ከአ.አ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት ሙያ ተመርቄ እንደ ወጣሁ ስራ አጥቼ ስራ ፈት ሆኜ ነበር። ብዙ መስሪያ ቤቶችን ባንኳኳም ሙስሊም በመሆኔ ነው መሰለኝ ማንም ሊቀጥረኝ ፍቃደኛ አልሆነም። ስራ ፈትቼ ስጨናነቅ ያስተዋለኝ አጎቴ እዚሁ አ.አ እናታችሁ የምትኖርበት ሰፈር ውስጥ ከነበረችው ትንሽዬ የሸቀጥ  ሱቁ ውስጥ እንድሰራ አደረገኝ። ለጊዜውም ቢሆን ስራ እስካገኝ ድረስ ህሊናዬን የማሳርፍበት ስራ በማግኘቴ ደስ ተሰኘሁ። እናታችሁ የምትኖረው ከአጎቴ ሸቀጥ ሱቅ ፊት ለፊት ካለው መኖሪያ ቤት ነበር። ታዲያ አንድ ቀን ፓስታ ልትገዛ ወደ ሸቀጧ ሱቅ መጣች። ስራውን ከጀመርኩ ሦስት ቀን ቢያልፈኝም ከዛሬ ውጭ አላየኋትም ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ ሳያት ልቤ ቀጥ አለች። ፓስታ ስጠኝ ብትለኝም ደንግጬ ስለነበር ፊት ለፊቴ ያገኘሁትን አጃክስ ሳሙና  አንስቼ ሰጠኋት።..." አባዬ ይሄንን ሲነግረን ሪሃና የተቀመጠችበት መፈረሻ ላይ እየተንፈራፈረች ትስቅ ጀመር። እማዬም ልክ ዛሬ የተፈጠረ ያህል እያስታወሰች በመሳቅ ላይ ናት። እኔም ምንም እንኳን ከዚህ የባሰ  ነገር ሲደረግ ያየሁ ቢሆንም በአባቢ ደርሶ ስላየሁ ከነሱ ባላነሰ መልኩ  እየሳቅኩ ነው። እኔ ታሪኩን ለመስማት ጓጉቻለሁ።  ነገር ግን ሪ አንዴ መሳቅ ከጀመረች ቶሎ ስለማታቆም እስክታበቃ መጠበቅ ግድ ሆነብን። ስትጨርስ አባቢ ታሪኩን ቀጠለልን። "አጃክሱን ስሰጣት ሳቅ እያፈናትም ቢሆን ኮስተር ብላ "ለኔ ነው?" አለች ወደ አጃክሱ እያመላከተችኝ። ልቤን ስገዛ ፓስታ እንዳለችኝ አስታወስኩና ደንገጥ ብዬ ፓስታ አውጥቼ ሰጠኋትና አስር ብር ሰጥታኝ መልስ ሳትቀበለኝ ሄደች። ፓስታ የዛኔ ሦስት ብር ነበር፡፡ ለካስ እኔ ብቻ አልነበርኩም የደነገጥኩት። አጅሪትም ስታዬኝ ደንግጣ ነበር።" አለ አባቢ ወደ ባለ ቤቱ እየተመለከት። "ዝም በሉት ይሄን ቀጣፊ!" አለች ማሚ እንደ ማፈር እያለች። ሪ አሁንም መሳቋን ቀጥላለች። በዚህ አይነትማ ሌሊቱን ሙሉ ቢተርክልን የሚያልቅ አይሆንም። "ይህች ሙጢ! ምናለ በተኛች!" እያልኩ ሳለ አባቢ እስክታቆም ሳይጠብቅ ታሪኩን ቀጠለልን። ሪም ሳቋን አቁማ ታዳምጥ ያዘች። "...ትንሽ ቆይታ መጣችና 'መልስ አልሰጠኸኝም!' ብላ መልሷን ይዛ ሄደች። ከአጎቴ ሱቅ ቀጥሎ ያለው ሱቅ ውስጥ የሚሰራውን አህመድ የሚባል ልጅ ስሟ ማን እንደሆነ ጠየቅኩት። 'ስሟ ሰሚራ ይባላል። ግን አትልፋ ልታገኛት አትችልም!' አለኝ። መጀመሪያ እንደወደድኳት ስላወቀብኝ አፈር አልኩ። ግን ደግሞ ለምን አታገኛትም እንዳለኝ ለማወቅ ስለጓጓሁ፤ 'እንዴት እንደዛ ልትል ቻልክ?' ስል ጠየቅኩት። 'ሲጀመር ፊት ስትሰጥህ አይደል? ያን የመሰለ ውብ ፊት ሳታኮሳትር መች ትመጣና! ዝም ብዬ ሳስበው ከሁሉ ነገሯ በፊት ፊቷ ቀድሞ የሚያረጅ ይመስለኛል። ሁሌም ስለምትኮሳተርበት። ሃሃሃሃ' ብሎ ሳቀ። ስላሾፈባት በጣም ተናደድኩ። ቢሆንም ግን ንዴቴን ዋጥ አደረኩት። ሰውስ ገና ዛሬ ስላየኋት ሴት ስናደድ ቢያይ ምን ይለኛል? 'እና ስልኳ የለህም?' ስል ጠየቅኩት ደፈር ብዬ። ምን እንዳስነካችኝ አላውቅም አይን አፋር የነበርኩትን ልጅ በአንዴ አይን አውጣ አድርጋኛለች። 'ሃሃሃሃ ስልክ ነው ያልከው? ሃሃሃሃ' እያለ ሳቀብኝ። ሲስቅ ሳየው እንደማፈርም እንደ መደንገጥም አልኩ። 'ስለማታውቃት ይሄን ብትጠይቅ አልፈርድብህም። ወንድሜ! እንኳን ስልኳን ስሟን እራሱ በቅርቡ እናቷ ስትጠራት ነው  የሰማሁት። ልጅቷ እኮ ስሪየስ ነገር ናት!' አለኝ። እሷን ማግኘት ዘበት እንደሆነ በነገረኝ ቁጥር ይበልጥ እየወደድኳትና እያከበርኳት መጣሁ። 'ቆይ ግን ምን አስበህ ነው? ስለሷ ጥናት ልትሰራ ነው ወይስ ፍቅሯ ገባልሽ?' አለኝ። ምንም መልስ አልሰጠሁትም። ልጁ የሆነ ወሬኛ ነገር ነው። አንድ ጠይቀኸው ሁለት ሦስት ነው የሚመልስልህ። ዝም ስለው ግዜ፤ 'ብቻ ፎንቃ እንዳይዝህ ተጠንቀቅ! ካልሆነ በቅርቡ 'የማትበላ ወፍ ተይዛ በጭራ...' እያልክ መዝፈንህ አይቀርም።' አለኝ። በውስጤ 'አሳይህ አይደለ!' አልኩና ጥየው ወደ ሱቄ ገባሁ።" አባቢ ሲተርክልን ሁላችንም ፈዘን እያዳመጥን ነው። ሌላው ቀርቶ ገና አንድ ገፅ የተረት መፅሐፍ ሲነበብላት እንቅልፍ የሚወስዳት ሪሃና ጆሮዋን አቁማ እያዳመጠች ነው። ከሁሉም የገረመኝ ደግሞ የማሚ ነው። የሌላ ሰው ታሪክ የምታዳምጥ ነው ምትመስለው። አንዴ እንደማፈር፣ አንዴ እንደመሳቅ እያለች ከእኛ ጋር እኩል ታዳምጥ ይዛለች። አባቢ ወደ ግድግዳ ሰዓታችን ተመለከተና፤ "በሉ ልጆች መሽቷል ተኙ! ነገ ቅዳሜ ስለሆነ ማታ እጨርስላችኋለሁ።" አለ። እውነትም ሰዓቱ ከምሽቱ 4:15 ሆኖ ነበር። ሪሃና እየተነጫነጨች "ነገ አረሳሳለሁ በልና አልለቅህም!" አለችው። "ችግር የለውም የኔ ቆንጆ እጨርስላችኋለሁ።" አላት። "ቆይ ግን እሬቴ ከመች ወዲህ ነው እንዲህ ወሬኛ የሆንሽው?" አልኳት። "ሂድ ወደዛ!" ብላ እስከ መኝታ ቤቴ ድረስ አሯሩጣኝ ተመለሰች። ሪሃና እሬቴ ስላት አትወድም። እሬቴ የምላት በአረበኛ ሪሃና ማለት አሪቲ የተሰኘ ለሽቶ መስሪያነት የሚያገለግል ጥሩ ማዓዛ ያለው ተክል ነው። ላናዳት ስፈልግ አሪቲ የሚለውን እሬቴ ብዬ በማንሻፈፍ እጠራታለሁ። መኝታ ክፍሌ ገብቼ ልብሴን አወላልቄ አልጋዬ ላይ ጋደም አልኩና ቀን ላይ የፖሰትኩት ፎቶዬ ላይ የተሰጠኝን አስተያየት እና ላይክ ለማየት ፌስቡኬን ከፈትኩ። . . ይቀጥላል!

#ሂክማ ክፍል አንድ . . . "አባቢ ዛሬ አልፋታህም! ማሚን እንዴት እንዳገባሃት ካልነገርከን አኮርፍሃለው!" አለች በአራት አመት የምታንሰኝ እህቴ። "አዎ ሪ ያለችው እውነትዋን ነው። ዛሬ ካልነገርከን እኔም አኮርፋለሁ!" ስል የእህቴን ሪሃና ሃሳብ ተጋራሁ። አባቴ የኔን ሃሳብ በጣም ነው የሚያከብረው። በተለይ ደግሞ እንደ ኩርፊያዬ በዚህች ምድር ላይ የሚጠላው ነገር እንደሌለ እራሱ በገዛ አንደበቱ  ለአጎቴ ሲናገር ሰምቻለሁ። ትንሽ እንደ መቆጣት ቢያደርጋትም እናቴም እንደዛው ናት። ባጭሩ የቤቱ ተወዳጅም ተሰሚም ሰው ነኝ። ይህን ክብር ያጎናፀፈኝ የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ በመሆኔ እንደሆነ ቤተሰባችንን በቅርብ የሚያውቅ ሁሉ ያውቀዋል። በእርግጥ በዚህ ብቻ አይደለም ለመወደድ የበቃሁት። የስለት ልጅ በመሆኔም ጭምር እንጅ። ማሚና አባቢ ለብዙ ዓመታት መውለድ አልቻሉም ነበር። በዚህም የተነሳ ትዳራቸው ከመዋደዳቸው ጋር ለመፍረስ ቋፍ ላይ ደርሶ እንደ ነበር ነብሷን ይማራትና አያቴ ነግራኛለች። አንድ ቀን ታዲያ ማሚ ለአባቢ እንዲህ አለችው:- "ይሄን ዓመት አይተን የማንወልድ ከሆነ እንድንፋታ እፈልጋለሁ!" ስትል በመሃላ ጭምር አስረግጣ ውሳኔዋን አሳወቀችው። ማሚ አባቢ እንዲጠላትና እሷን ፈትቶ ሌላ እንዲያገባ የማታደርገው ጥረት አልነበረም። ይሄን የምታደርገው ክፉ ስለሆነች ሳይሆን ችግሩ ያለው ከእሷ እንደሆነ በማመኗና በሷ ምክንያት ዘር አልባ ሆኖ እንዲቀር ስለማትፈልግ ነው። "ታዲያ ለምን ሁለተኛ እንዲያገባ አትፈቅድለትም?" ትሉ ይሆናል። ማሚ ግን በዚህ ሃሳብ ፍፁም አትስማማም። እንዲያውም ባይገርማችሁ እናቷ (አያቴ) ይሄንን ሃሳብ አቅርባላት ለብዙ ወራቶች አኩርፋታለች። ምክንያቱም አባቢን በጣም ስለምትወደውና ስለምትቀናበት። አባቢ ግን የሚስቱ ፀባይ እየተቀያየረ ቢቸገርም በፅናትና በጥበብ ከማለፍ አልቦዘነም ነበር። በእርግጥ ከሚባለው በላይ ልጅ መውለድ ይፈልጋል። ሆኖም ግን መውለድ ካለበት ከእናቴ እንጅ ከሌላ እንደማይሆን ራሱን አሳምኗል። የዛሬው የእናቴ አቋም ግን የምር መሆኑን ሲረዳ ከቤቱ ወጥቶ ወደ መስጂድ ነበር ያቀናው። ሰዓቱ ረፋድ ላይ ስለነበር ውዱዕ አድርጎ ዱሃ ሶላት (ረፋድ ላይ የሚሰገድ ሱና ሶላት ነው።) ሰግዶ ተንሰቅስቆ አላህን ይማፀን ያዘ። ማሚም በተመሳሳይ ሰዓት መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ፈጣሪዋን በመማፀን ላይ ነበረች። አላህ ሁለት ባሪያዎቹ በተመሳሳይ ሰዓት በሁለት አቅጣጫ ስለ ተመሳሳይ ጉዳይ የሚጠይቁትን ጥያቄ እንቢ ብሎ ማለፍ የፈለገ አይመስልም። ስለሆነም ዱዓቸውን ተቀበላቸው። ዱዓ ባደረጉ በሁለተኛው ወር ማሚ ነብሰ ጡር መሆኗን አወቀች። በዚህም ሰበብ አንድ ሀሙስ ብቻ  ቀርቶት የነበረው የወላጆቼ ትዳር ዳግም አንሰራርቶ በፍቅር ይደምቅ ያዘ። "ልጅ የትዳር ቀለም ነው! ፍቅር ሊያረጅ ሲል ድምቀት ሰጥቶ የሚያስውብ! ልጅ የትዳር ማሰሪያ ልጓም ነው! በትንሽ በትልቁ ከመፈርጠጥ  የሚያቅብ!" ትል ነበር አያቴ። ማሚ ከፀነሰች በኃላ ግን ጤናዋ ይታወክ ያዘ። ይባስ ብሎም ፅንሱ እየገፋ በሄደ ቁጥር ከፅንሱ ጋር  የማሚም ህመም አብሮ እየበረታ መጣ። የተጀመረ ሁሉ ማለቁ፣ የተፀነሰ ሁሉ መወለዱ አይቀርምና  እንደ ምንም የማሚ መውለጃ ጊዜ ደረሰ። ሆስፒታል ገብታም ማማጥ ጀመረች። ከረጅም ምጥ በኃላም ማሚ የፀነሰችውን ፅንስ ለመገላገል በቃች። ነገር ግን  ማሚ ከፅንሷ በተገላገለችበት ሰዓት የተወለደውም ልጅ ይህችን ውጥንቅጥ ዓለም በሞት  ተገላግሏት ነበር። ከማዋለጃው ክፍል ውጭ ሆኖ የትዳሩን መሰረት ያፀናለትን የአዲስ ልጁን ለቅሶ ሲጠባበቅ የነበረው አባቢ በህፃኑ ለቅሶ ምትክ የአማቹን (የአያቴን) ኡኡታ ነበር የሰማው። መጀመሪያ ላይ ማሚ የሆነ ነገር የሆነች መስሎት ራሱን ስቶ ወደቀ። ራሱን መግዛት ሲችልና እሱ ከተኛበት የሆስፒታል አልጋ ጎን ማሚን ሲመለከት "አልሐምዱ ሊላህ!" የሚል ቃል ከአፉ ወጣ። ማሚ በልጇ ሞቶ መወለድ መጀመሪያ ላይ በጣም ያዘነች ቢሆንም የአላህን ውሳኔ ለመውደድ ግን ብዙ ግዜ አልፈጀባትም። አባቢም ቢሆን ራሱን የሳተው የሚወዳት ሚስቱ የሞተችበት ስለመሰለው እንጅ፤ በሞተው ልጁ በኩል ከማሚ የተለዬ አቋም ኖሮት አልነበረም። እንደ ወላድነታቸውና ለልጅ እንዳላቸው ጉጉት አሳዛኝ ክስተት ቢሆንም፤ ለእነሱ ግን መውለድ መቻላቸውን ማወቃቸው ብቻ ትልቅ ተስፋና መፅናኛ ሆኗቸዋል። ምስጋና ከአላህ በታች ሞቶ ለተወለደው ወንድሜ ይግባውና መፀነስ መቻላቸውን ካረጋገጡ በኋላ ትዳራቸው በፍቅር እንደ ደመቀ ነው። ከወራቶች  በኋላ ማሚ ድጋሚ ፀነሰች። የአሁኑ ፅንሷ እንደ መጀመሪያው ከባድ አልነበረም። ሌላው ቀርቶ ሴቶች ሲያረግዙ እንደ ሚያምራቸው አላማራትም ነበር። የመውለጃ ቀኗ ሲቃረብ የአሁኑ ልጃቸው በሰላም እንዲወለድ የአላህን በር ማንኳኳት ያዙ። በየፊናቸውም ለአላህ ስለት ገቡ። አምላካቸው አሁንም አላሳፈራቸውም። ማሚ ወንድ ልጅ ተገላገለች። ስሙንም ሳሊም (ሰላም) ሲሉ ሰየሙት። በልጁ ምክንያት ትዳራቸው፣ ልጃቸውና እናቴ ሰላም ስለሆኑ። ሳሊም ማለት እንግዲህ እኔ ነኝ 😊። ወላጆቼም ዘንድ ተወዳጅና ተሰሚ የሆንኩትም በዚህ ምክንያት ነው። ምንም እንኳን አብዛኛዎቹ የመጀመሪያ ልጆች ተወዳጅ የሚሆኑት ታናሽ እስኪወለድባቸው ድረስ ቢሆንም፤ እኔ ግን ከአራት ዓመታት በኋላ እህቴ ሪሃና ብትወለድም መወለዷ ተወዳጅና ተሰሚ ከመሆን  አላገደኝም ነበር። እንግዲህ እስካሁን የነገርኳችሁን የቤተሰቤን ታሪክ የነገረችኝ አያቴ ናት። የነ ማሚና አባቢ የፍቅር ታሪክና ግንኙነት ከታሪኩ ባለቤቶች በቀር ማንም ሊነግረን አይችልምና ይሄን ታሪክ ዛሬ እንዲነግሩን አስገደድናቸው። ከዚህ በፊት ብዙ ጊዜ እንዲነግሩን የጎተጎትናቸው ቢሆንም ሌላ ቀን ምናምን እያሉ ያረሳሱን ነበር። ምናልባት ከልጆች ፊት የፍቅር ታሪክን ማውራቱ ጥሩ እንደማይሆን አስበው ሳይሆን አይቀርም። ዛሬ ግን ትንሽ ጥያቄያችንን ጠንከር አድርገንባቸዋል። ስለሆነም አማራጭ ያጣው አባቢ ከብዙ አመታት የጋዜጠኛነት ልምዱ ባካበተው መሳጭ አተራረኩ እንዲህ ሲል ይተርክልን ያዘ... . . . ክፍል ሁለት ይቀጥላል!

ወደ ዋናው ቻናላችን ይቀላቀሉ!