fa
Feedback

فریب کلاهبرداران را نخورید! تل‌متریو این کانال‌ها را شناسایی و برچسب‌گذاری می‌کند 👉 برای مشاهده برچسب، اشتراک تهیه کنید

ሐሳቦቻችን

ሐሳቦቻችን

رفتن به کانال در Telegram

በዚ ቻናል ላይ የተለያዩ ሀሳቦቻችንን ፣ ምልከታዎቻችንን ፣ ትዝብታችንን ፣ ከተለያዩ መልኮች እያነሳን እንወያያለን! ሀሳብና አስተያየት ካላቹ @haileabb

نمایش بیشتر
أثيوبيا13 780دسته بندی مشخص نشده است
980
مشترکین
-224 ساعت
-17 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
photo content

ይሄ ሁሉ መቆንጀት ፡ ይሄ ሁሉ ማማር ግማሹ ቁም ነገር ፡ ቢሆን ምን ነበር አስናቀች ወርቁ @ourrthought

‎"ነጮቹ መጀመሪያ ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መፅሐፍ ቅዱስ እኛ መሬት ነበረን። መፅሐፍ ቅዱስ ሰጡንና አይናችንን ጨፍነን መፀለይ አስተማሩን። አይናችንን ስንገልጥ ግን እነሱ መሬት እኛ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነበረን።" ‎ ‎ቄስ ዴዝሞን ቱቱ ‎ @ourrthought

Repost from ሐሳቦቻችን
‎"ነጮቹ መጀመሪያ ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መፅሐፍ ቅዱስ እኛ መሬት ነበረን። መፅሐፍ ቅዱስ ሰጡንና አይናችንን ጨፍነን መፀለይ አስተማሩን። አይናችንን ስንገልጥ ግን እነሱ መሬት እኛ መፅሐፍ ቅዱስ
‎"ነጮቹ መጀመሪያ ወደ አፍሪካ ሲመጡ እነሱ መፅሐፍ ቅዱስ እኛ መሬት ነበረን። መፅሐፍ ቅዱስ ሰጡንና አይናችንን ጨፍነን መፀለይ አስተማሩን። አይናችንን ስንገልጥ ግን እነሱ መሬት እኛ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነበረን።"
‎
‎ቄስ ዴዝሞን ቱቱ
‎ @ourrthought

አሁን አሁን እንደ ፋሽን እየመጣ ያለ ነገር ቢኖር የሚወለዱ ልጆችን ስም ከመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ እያወጡ በ 1250 የነበሩ አይሁዶች የቀበሌ ስም (Torah ላይ ራሱ የጠፉ) እያወጡ አይሁዶች ራሱ የማይጠሩበትን ስም ያወጣሉ። ትርጉሙ ምንድነው ሲባሉ ላባና ያዕቆብ የታረቁበት ቦታ ትኖር የነበረች ድንቢጥ ናት ምናምን ይላሉ። ፅድቅ በስም ቢሆን ይሁዳ (የስሙ ትርጉም ታማኝ ነው) ነበር ቅዱስ። በዚህ ልክ ከማንነታችን መራቅም ያስተዛዝባል። @ourrthought

ከጠዋት እስከማታ social media እየተጠቀማቹህ ጤነኛ የሆናቹህ ሰዎች እንኳን Disorder ቀርቶ Cancer ራሱ አይገላቹሁም። ሰማያዊ እገዛ አላቹህ በውነቱ። በጌታ ስም አለ ያሬድ ነጉ ቀኑን ሙሉ social media ተጠቅሞ መሆን አለበት። ስካር በስንት ጣዕሙ። @ourrthought

ሲሲፈስ እድለኛ ነበር። የሚገፋው አንድ ቋጥኝ ብቻ ነበር። በዛ ላይ የመግፊያው አቅምም ነበረው። እዚህ ዘመን ላይ ቢሆን ኖሮ አማልክቱ ቅጣቱን አዘምነው የሚቀጡት ቀኑን ሙሉ Tik tok ፣ Facebook ፣ IG ፣ TG ፣ X scroll እንዲያደርግ ነበር የሚቀጡት። @ourrthought

ማርጀትህን የምታውቀው የሆነ ቀን ታኪሲ ላይ በ አሮጌ ብር እና በ አዲስ ብር ስትጨቃጨቅ ስታይ ነው። እድሜ ይጋልባል። @ourrthought

Ethiopia-by-GIGI.m4a5.72 MB

photo content

photo content

አንድ አንዴ ውስጤ ያለሁ ሀሳብ ልክ እንደ ማዕበል ይንጠኛል። ሲብስበት ደግሞ ልክ እንደ ወተት ገንፍዬ ካሎጣው ይለኛል። ዝም ካልኩት በዛው ይጠፋል እና ከመጥፋቱ በፊት ብዕሬን አንስቼ እሞነጫጭረዋለሁ ካልሆነ ሰላም አይሰጠኝም። የሆነ ጊዜ አለማየሁ ገላጋይ የማከብረው ደራሲ የሰጠው ቃለ መጠይቅ ላይ እንዲህ ሲል ሰምቼዋለሁ፤ "እኔ ብዙ ጊዜ መፅሀፍ ከመፃፌ በፊት በ አእምሮዬ ታሪኩን ጀምሬ እጨርሰዋለሁ ከዛን በኋላ ነው በወረቀት የማሰፍር ፣ እስከዛሬ አንድ ሶስት የሚሆኑ ሙሉ ያለቁ ልብወለድ መፅሀፍ አእምሮዬ ውስጥ ጠፍቶብኛል" ያለውን አልረሳውም፣ እኔም ሀሳቤ እንደንጋት ጤዛ ከመጥፋቱ በፊት ልፅፈው ብዕሬን አንስቼ መሞነጫጨር ጀመርኩ። "ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እነሆ ለሀገራችን ክብር ብለው ህይወታቸውን አሳልፈው ከሰጡ 86 ዓመታትን አስቆጠሩ።" እያለ ሬድዮኑ ይለፈልፋል። እኔም በዛው በሀሳብ ባህር ጭልጥ ብዬ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም የሽምጥ የኋሊት ጋለብኩና በምናቤ አቡነ ጴጥሮስ ጋር ተሰየምኩ። ወቅቱ ዳግም ጣሊያን ወረራ ላይ ነበር። ቂጡን በሳንጃ ተወግቶ ከተባረረ በኋላ አርባ አመታትን ቆይቶ ዳግም ለበቀል የመጣበት ወቅት ነበር። ታዲያ የዛን ጊዜ ህዝቡ ሁሉ በአንድነት የሚሰማቸው፣ የሚያከብራቸው እና የሚወዳቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስን ነበር። ታዲያ ይሄን የተገነዘበው ግራዚያኒ አቡነ ጴጥሮስ ዘንድ ሄዶ ህዝቡን ከጣሊያን ጎን ሆኖ እንዲያስገዙት ህዝቡ እንዲታዘዝ እሳቸውም የተሻለ ነገር እንደሚያገኙ ነገራቸው። እሳቸውም " ጣሊያንን ተቀበሉ ብዬ አልሰብክም፣ እንኳን ህዝቡ መሬቱ እንዳይታዘዝ ብዬ አውግዤዋለሁ" አሉ። ግራዚያኒም ህዝብ በተሰበሰበበት አስረሽኖ ገደላቸው። እንኳንም ዛሬ ላይ አልሆነ ብዬ ፈጣሪን አመሰገንኩት። ለምን አትሉም!? አሁን ዘመን ላይ ቢሆን ደግሞ ግራዚያኒ ሳይሆን ህዝቡ ነበር 'ሚረሽናቸው። የስልጣኔ ፀር፣ እኛ እንዳናድግ እንቅፋት ሊሆኑብን ነው፣ የድሮ ናፊቂ! ብሎ ሲያበሻቅጣቸው ሳልኩትና ዘገነነኝ፣ እንኳንም የዛኔ ሆነ ሆሆሆ። ግራዚያኒ ህዝቡን "ጠላታችን ስለሞተ አጨብጭቡ።" አላቸው። ህዝቡም በጭብጨባ አቀለጠው አሉ ይሄ አጨብጫቢ ህዝብ! ለገዳዩም ላስገዳዩም እንዳጨበጨበ ይሄው እስከአሁን አለ። የእነሱ ልጆች ዛሬም ድረስ በየስብሰባው በየፓርላማው እንዳጨበጨቡ ነው አሉ። አይ አንቺ ሀገር ስንት ጠባቂ ልጆችሽን በጭብጨባ ሸኘሽ!፣ መች ይሁን ማጨብጨቡ የሚበቃሽ!? መዳፍሽ ለጠላቶችሽ ማጨብጨቡን ትቶ ሰይፍ የሚጨብጠው! መች ይሆን ልጆችሽን መገበር የሚበቃሽ? እንጃልሽ!። በአንድ ወቅት የሆነ ፍልስፍና ፀጣፍ ላይ የቃረምኩት ትዝ አለኝ። " በአንድ ወቅት ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ እስራኤል ከተማ ሲመጣ በመንገድ ያገኙት ሰዎች እየሱስን እየሰደቡ እየተፉበት እርሱ ግን በመካከላቸው ምንም ሳይናገር በዝምታ ያልፋል። ታዲያ በዚህ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ነገሩን ሲከታተሉ ቆይተው ኖሮ ለምን ዝም እንዳለ ጠየቁት። በዚህ ጊዜ እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው " ሰው ከቅርጫቱ ውስጥ የሚያወጣው ቅርጫቱ ውስጥ ያለውን ነው። እነዚህም ሰዎች ከስድብና ጥላቻ ውጪ ሌላ ነገር አያውቁም አትፍረዱባቸው" ብሎ ነገራቸው። አቤት! የዚህ ዘመን ቅርጫት ሲከፈት ውስጡን አሰብኩት። ዘረኝነት፣ እርኩሰት፣ ሴሰኝነት፣ ጥላቻ፣ ተንኮል ወዘተ ተጭቀውበት ታየኝ። ስንት ዘመን ከዚህ ቅርጫት እንደምንኖር እንጃ! ስንት ዘመን አዳኞቻችን ታዳጊዎቻችንን ከዚህ ቅርጫ እንደምንወረውርባቸው እንጃ! ማን ያውቃል!? ብቻ ተስፋ አልቆርጥም። 22/11/2014 ዓ.ም የተከተበ @ourrthought

​ለዚህ Evidential Problem of Evil እሳቤ አማንያን እና የሃይማኖት ፈላስፎች መከራከሪያ ሚሆኑ ሶስት ዋና ዋና ምላሾችን ይሰጣሉ፦ ​አንደኛ Skeptical Theism (የሰው ልጅ እውቀት ውስንነት) ሲሆን :ሀሳቡ፦ እኛ የሰው ልጆች የፈጣሪን ሙሉ እቅድ እና ትልቅ ምስል (Big Picture) የማየት አቅም የለንም::ለምሳሌ፦ አንድ ትንሽ ልጅ ሀኪም መርፌ ሲወጋው ሀኪሙ ያለ ምክንያት የሚያሰቃየው ይመስለዋል::ምክንያቱም መርፌው ከከፋ በሽታ እንደሚጠብቀው የመረዳት አቅም ስለሌለው ነው:: እኛም አንድ መከራ 'ከንቱ ነው' ብለን ስንደመድም ከጀርባው ያለውን አጠቃላይ ምክንያት የማወቅ ውስንነት ስላለን ሊሆን ይችላል:: ​ሁለተኛ Greater Good Defense (ታላቁ መልካም ነገር) ​ፈጣሪ አንዳንድ አሰቃቂ መከራዎችን የሚፈቅደው: ከእነዚያ መከራዎች በስተጀርባ የበለጠ ታላቅ መልካም ነገር (Greater Good) ስለሚወጣ ወይም ከእዚያ የከፋ ነገር ስለሚከለክል ነው የሚል መከራከሪያ ነው:: ሌላኛውና ሶስተኛው Theistic Evidence (የፈጣሪ ህልውና ሌሎች ማስረጃዎች) ሲሆን: የመከራ ጥያቄ ብቻውን አይቆምም:: የዓለም መፈጠር: የፊዚክስ ህግጋት ውስብስብነት (Fine-tuning): የሞራል ህጎች መኖር እና የህይወት አመጣጥ ፈጣሪ የመኖሩን እድል እጅግ በጣም ከፍተኛ ያደርጉታል:: ​ስለዚህ ሌሎች ሚዛኖች ፈጣሪ እንዳለ የሚያሳዩ ከሆነ: የመከራን ምክንያት ሙሉ በሙሉ ባናውቀውም ፈጣሪ የለም ወደሚል መደምደሚያ አንደርስም:: 16/11/2018 ዓ.ም By ሀኑ-ን @ourrthought

The Logical Problem of Evil (የሎጂክ የመከራ ጥያቄ) በጄ.ኤል. ማኪ (J.L. Mackie) እና በአልቪን ፕላንቲንጋ (Alvin Plantinga) መካከል የተደረገ በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከተካሄዱት ታላላቅ የሃይማኖት ፍልስፍና (Philosophy of Religion) ክርክሮች አንዱ ነው:: አውስትራሊያዊው ኤቲስት ፈላስፋ ማኪ 'Evil and Omnipotence' በተሰኘው ታዋቂ ጽሁፉ የሚከተለውን ጥንካሬ ያለው የሎጂክ አጣብቂኝ አቀረበ፦ ​- እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው (Omnipotent): ​- እግዚአብሔር ፍጹም ደግ/ርህሩህ ነው (Wholly Good): ​- መከራ/ክፋት በዓለም ላይ አለ (Evil exists) ​ማኪ እንደተናገረው እኚህ ሶስት ሀሳቦች በአንድ ላይ ሲቀመጡ በሎጂክ እርስ በእርሳቸው ይጋጫሉ (Logical Contradiction):: ​የማኪ ዋና ጥያቄ፦ 'አንድ ፍጹም ደግ የሆነ አካል በተቻለው መጠን ክፋትን ያጠፋል::ሁሉን ቻይ የሆነ አካል ደግሞ ማድረግ የማይችለው ነገር የለም::ስለዚህ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ደግ ከሆነ ክፋት በፍጹም ሊኖር አይችልም ነበር::ነገር ግን ክፋት አለ: ስለዚህ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ደግ የሆነ ፈጣሪ በሎጂክ ደረጃ ሊኖር አይችልም::' ማኪ የነፃ ፈቃድን (Free Will) ሀሳብ ውድቅ ሲያደርግም፦ 'ሁሉን ቻይ ፈጣሪ ሰዎችን በነፃ ፈቃዳቸው ሁልጊዜ መልካም ነገርን ብቻ የሚያደርጉ አድርጎ መፍጠር ይችል ነበር::ያንን አለማድረጉ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ወይም ደግ አለመሆኑን ያሳያል' አለ:: ​አሜሪካዊው ክርስቲያን ፈላስፋ አልቪን ፕላንቲንጋ 'The Nature of Necessity' በሚለው መጽሐፉ ለተጠየቀው ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ሰጠ::ፕላንቲንጋ የማኪን መከራከሪያ ለማፍረስ የሞከረው 'የሎጂክ ወሰን' እና 'የነፃ ፈቃድ'( Free will defense )ባህሪ ላይ በማተኮር ነው፦ ​አንደኛ በሎጂክ የማይቻሉ ነገሮች (Logical Impossibilities)​ፕላንቲንጋ እንዳለው ​በፍልስፍና እና በሎጂክ ህግ 'በሎጂክ የማይቻል ነገር' የሚባለው የፈጣሪ የአቅም ማነስ ሳይሆን: የሀሳቡ ወይም የቃላቱ ራሱ እርስ በእርስ መጋጨት እና ትርጉም አልባ መሆን ነው:: ለምሳሌ ኢአማንያን 'ፈጣሪ ሁሉን ቻይ ከሆነ ራሱ ሊሸከመው የማይችለውን ድንጋይ መፍጠር ይችላል?' የሚል አጣብቂኝ ጥያቄ ያነሳሉ:: ነገር ግን 'ሁሉን ቻይ አካል' እና 'እሱ ሊሸከመው የማይችለው ድንጋይ: የሚሉት ሁለት ሀሳቦች በቃላት ደረጃ እርስ በእርሳቸው የሚጋጩ ተቃራኒ ሀሳቦች ናቸው:: ሁሉን ቻይነት (Omnipotence) ማለት በሎጂክ ሊከናወኑ የሚችሉ ነገሮችን በሙሉ ማድረግ እንጂ: እንደ 'ባለ አራት ማዕዘን ክበብ' ወይም 'ሊሸከሙት የማይችሉት ድንጋይ' ያሉ ትርጉም አልባ እና እርስ በእርስ የሚቃረኑ ሀሳቦችን መፍጠር ማለት አይደለም:: ስለዚህ ነገሩ ያልተደረገው ፈጣሪ የመሸከም ወይም የመፍጠር አቅም አጥቶ ሳይሆን: ሀሳቡ በራሱ በሎጂክ ደረጃ የማይቻል ስለሆነ ነው:: ​ሁለተኛ ነፃ ፈቃድ እና በግድ ማሰራት(Transworld Depravity) ​አንድ ሰው 'እውነተኛ ነፃ ፈቃድ' አለው ከተባለ ያንን ሰው 'በግድ ሁልጊዜ መልካም ብቻ እንዲመርጥ ማድረግ በሎጂክ እርስ በእርሱ የሚጋጭ (Contradiction) ነው!​ፈጣሪ ሰዎችን በግድ መልካም ብቻ የሚያደርጉ አድርጎ ቢፈጥራቸው ኖሮ ሰዎች ነፃ ፈቃድ ያላቸው ፍጡራን አይሆኑም ነበር:: እውነተኛ ነፃ ፈቃድ ለመስጠት ደግሞ ሰዎቹ የመሳሳት እና ክፉ የመምረጥ እድል/አማራጭ ሊኖራቸው ይገባል:: ​በስተመጨረሻም የፕላንቲንጋ ድምዳሜ 'እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ቢሆንም እንኳ ነፃ ፈቃድ ያላቸውን ፍጡራን ፈጥሮ በዚያው ቅጽበት በግድ መልካም ብቻ እንዲሰሩ ሊያደርጋቸው አይችልም::ስለዚህ የክፋት/መከራ መኖር የእግዚአብሔርን ሁሉን ቻይነት ወይም ፍጹም ደግነት በሎጂክ አይቃረንም::' የሚል ነው:: ​በፍልስፍናው ዓለም ይህ ክርክር ከተጠናቀቀ በኋላ በሰፊው የታመነበት ውጤት የፕላንቲንጋን አሸናፊነት ሚያስረግጥ ነው:: አብዛኞቹ የአካዳሚክ ፈላስፎች (ኢ-አማንያንን ጨምሮ) ፕላንቲንጋ 'የሎጂክ የመከራ ጥያቄን'(The Logical Problem of Evil) ሙሉ በሙሉ ማፍረሱን ተቀብለዋል::ማኪ ራሱ በበኩሉ የፕላንቲንጋ ምላሽ የነበረበትን የሎጂክ አጣብቂኝ እንደፈታው በኋላ ላይ አምኗል::ግን ይህ ውጤት ክርክሩን ወደ ሌላ አቅጣጫ አዛውሮት ነበር የተቋጨው ::የፕላንቲንጋ 'Free Will Defense' የሎጂክ አጣብቂኙን ቢፈታውም ኢ-አማንያን ክርክሩን ከሎጂክ ጥያቄ ወደ 'Evidential Problem of Evil' (የመከራው መጠን እና አይነት አሳማኝነት) አዞሩት። ​በጠቅላላው ማኪ 'እግዚአብሔር እና ክፋት በሎጂክ አብረው ሊኖሩ አይችሉም' ብሎ ሲሞግት ፕላንቲንጋ ደግሞ 'በነፃ ፈቃድ ምክንያት ሁለቱ በሎጂክ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ' በማለት ክርክሩን በበላይነት አጠናቋል። Evidential Problem of Evil (በማስረጃ ላይ የተመሰረተው የመከራ ጥያቄ) በፍልስፍና እና በሃይማኖት ጥናት (Theology) ውስጥ 'መከራ እና ፍጹም ፈጣሪ በሎጂክ አብሮ መኖር አይችሉም' ከሚለው ይልቅ 'በዓለም ላይ ያለው የመከራ መጠን: አይነት እና ከንቱነት ፈጣሪ የመኖሩን እድል በጣም ያቀጥነዋል/ያሳንሰዋል' የሚል መከራከሪያ ነው:: ​አልቪን ፕላንቲንጋ 'ፈጣሪ እና መከራ በሎጂክ ደረጃ አብረው ሊኖሩ ይችላሉ' ብሎ ማስመስከሩን ተከትሎ: ኢ-አማንያን (Atheists) መከራከሪያቸውን ከቀጥታ የሎጂክ ግጭት ወደዚህ በማስረጃ/በእድል (Probability) ላይ የተመሰረተ የአመንክዮ አቀራረብ አዞሩት:-ሁሉን ቻይ: ሁሉን አዋቂ እና ፍጹም ርህሩህ የሆነ ፈጣሪ ካለ :ያለ በቂ/መልካም ምክንያት የሚከሰት ህመም ወይም መከራ እንዲኖር አይፈቅድም! ነገር ግን በዓለም ላይ ምንም አይነት መልካም ነገር የማይወጣቸው: ከንቱ እና እጅግ በጣም አሰቃቂ የሆኑ የመከራ አይነቶች (Gratuitous Evils) አሉ:: ስለዚህ ሁሉን ቻይ እና ፍጹም ርህሩህ የሆነ ፈጣሪ የመኖር እድሉ እጅግ በጣም አነስተኛ ነው (ወይም የለም):: ​ይህንን መከራከሪያ በስፋት ወደ ፍልስፍና ዓለም ያመጣው አሜሪካዊው ፈላስፋ ዊልያም ሮው(William Rowe) ሲሆን:ሀሳቡን በሁለት ታዋቂ ምሳሌዎች ያስረዳል፦ የመጀመሪያው የጫካው ሚዳቆ (The Fawn in the Forest)ነው ::ሰው በማይደርስበት የራቀ ደን ውስጥ የመብረቅ አደጋ አጋጥሞ ሰደድ እሳት ይነሳል::በዚያ እሳት ውስጥ አንድ የዱር ሚዳቆ በጽኑ ተቃጥሎ ለቀናት እየተሰቃየ ይሞታል:: ​ይህ መከራ የሰውን ነፃ ፈቃድ አይመለከትም:: ለማንም ሰው ትምህርት ወይም 'የነፍስ ማነፅያ' አይሆንም: ምክንያቱም ማንም አላየውምና::​ጥያቄውም: ሁሉን አዋቂ እና ርህሩህ ፈጣሪ ይሄን አሰቃቂ ህመም ሚዳቆዋ ሳትሰቃይ ቀጥታ እንድትሞት ማድረግ ወይም ማስቀረት አይችልም ነበር? ነው:: ​ሁለተኛው ምሳሌ ደሞ የህፃናት መበደል/መሰቃየት ነው::በንጹሃን ህፃናት ላይ የሚደርሱ አሰቃቂ ጥቃቶች በሽታዎች እና ሰቆቃዎችን ኃላፊነት ማን ይወስዳል? የሚል:: @ourrthought

photo content

photo content