Musalla App
All things about the Musalla App https://onelink.to/quvuv3 Direct contact @ContactMusalla ይህ ቻናል ሙሰላ አፕን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚተላለፉበት ነው። መተግበሪያውን ለማግኘት https://onelink.to/quvuv3 በቀጥታ እኛን ለማግኘት @ContactMusalla
نمایش بیشتر📈 تحلیل کانال تلگرام Musalla App
کانال Musalla App (@musalla_app) بازیگری فعال است. در حال حاضر جامعه شامل 11 280 مشترک است و جایگاه را در دسته متفرقه دارد.
📊 شاخصهای مخاطب و پویایی
از زمان ایجاد در невідомо، پروژه رشد سریعی داشته و 11 280 مشترک جذب کرده است.
بر اساس آخرین دادهها در تاریخ 08 ژوئیه, 2026، کانال فعالیت پایداری دارد. در ۳۰ روز گذشته تغییر اعضا برابر 370 و در ۲۴ ساعت گذشته برابر 1 بوده و همچنان دسترسی گستردهای حفظ شده است.
- وضعیت تأیید: تأیید نشده
- نرخ تعامل (ER): میانگین تعامل مخاطب 65.89% است و در ۲۴ ساعت نخست پس از انتشار، محتوا معمولاً N/A% واکنش نسبت به کل مشترکان کسب میکند.
- دسترسی پستها: هر پست به طور میانگین 0 بازدید دریافت میکند. در اولین روز معمولاً 0 بازدید جمعآوری میشود.
- واکنشها و تعامل: مخاطبان بهطور فعال حمایت میکنند؛ میانگین واکنش به هر پست 0 است.
📝 توضیح و سیاست محتوایی
نویسنده این فضا را محل بیان دیدگاههای شخصی توصیف میکند:
“All things about the Musalla App https://onelink.to/quvuv3
Direct contact @ContactMusalla
ይህ ቻናል ሙሰላ አፕን የሚመለከቱ መረጃዎች የሚተላለፉበት ነው። መተግበሪያውን ለማግኘት https://onelink.to/quvuv3
በቀጥታ እኛን ለማግኘት @ContactMusalla”
به لطف بهروزرسانیهای پرتکرار (آخرین داده در تاریخ 09 ژوئیه, 2026)، کانال همواره بهروز و دارای دسترسی بالاست. تحلیلها نشان میدهد مخاطبان بهطور فعال با محتوا تعامل دارند و آن را به نقطه اثرگذاری مهم در دسته متفرقه تبدیل کردهاند.
در حال بارگیری داده...
| تاریخ | رشد مشترکین | اشارات | کانالها | |
| 09 ژوئیه | +6 | |||
| 08 ژوئیه | +1 | |||
| 07 ژوئیه | +9 | |||
| 06 ژوئیه | +24 | |||
| 05 ژوئیه | +8 | |||
| 04 ژوئیه | +3 | |||
| 03 ژوئیه | +12 | |||
| 02 ژوئیه | +28 | |||
| 01 ژوئیه | +4 |
| 2 | አላሁ አክበር! አላሁ አክበር! ላ ኢላሃ ኢለላህ አላሁ አክበር! አላሁ አክበር....
"ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሐል አዕማል!"
(አላህ ከእኛም ከእናንተም መልካም ሥራዎችን ይቀበል!)
በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ በዓል በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሳችሁ።
በዓሉን ከቤተሰብዎ እና ከወዳጅ ዘመድዎ ጋር በደስታ ያሳልፉ! ዒድ ሙባረክ! 🎁🐏 | 4 872 |
| 3 | 🎉 ዒድ ሙባረክ! | ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም! 🌙🐑
الله أكــبر، الله أكــبر، الله أكــبر،
لا إلــه إلا الـلــــه،
والـلــه أكــبر، الـلــه أكــبر، ولـلــه الحمــد.
እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል-አድሃ (የአረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አላህ (ሱ.ወ) የሑጃጆችን ሐጅ፣ ጾመኛውን፣ ኡድሂያ አራጁንና መልካም የሰራውን ሁሉ ስራውን ይቀበለው!
ይህ የዒድ በዓል፡-
✨ የነብዩላህ ኢብራሂምን (ዐ.ሰ) ታዛዥነት የምንማርበት፤
✨ በኡድሂያ (እርድ) ድሆችን የምናስደስትበት፣እና
✨ የቤተሰብ ዝምድናን የምናጠናክርበት በዓል ነው።
ሙሰላ ቲም ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ የተባረከ፣ የደስታ እና የሰላም በዓል እንዲሆን ይመኛል! ዒድ ሙባረክ! 🎈 | 5 245 |
| 4 | 🌟የአመቱ ታላቁ ቀን ነገ ነው!
አልሀምዱሊላህ! አላህ (ሱ.ወ) በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት ታላቁ የዐረፋ ቀን ነገ (ማክሰኞ) ነው! ለዚህ ድንቅ ቀን ከወዲሁ እንዘጋጅ፡-
1. የጾም ቱሩፋት (በረካ)፡ነገን ለመጾም ከወዲሁ ኒያ እናደርግ የዐረፋን ቀን የጾመ ሰው አላህ የሁለት ዓመት (ያለፈውን እና የሚመጣውን) ወንጀል ይምርለታል! ሱብሀነላህ!
2. በላጩ ዱዓ፡
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) "ከዱዓዎች ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው፤እኔ እና ከኔ በፊት ያሉት ነብያቶች ካሉት ሁሉ በላጩ ደግሞ ፤ ላኢላሃ ኢልለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ፤ ለሁልሙልኩ ወለሁል ሓምዱ ወሑው ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" የሚለው ነው። ብለዋል።
ነገ አላህን ማንኛውንም ነገር ከመጠየቅ ወደኋላ እንዳንል! ለዱንያችንም፣ ለአኼራችንም፣ ለጤናችን ፣ ለትዳራችን፣ ለቤተሰባችን ... ከልብ አልቅሰን እንለምነው ። ማንም የማያውቀውን የልባችንን ስብራት እንንገረው። ለአላህ የሚከብደው ምንም ነገር የለም፤ ስለዚህ ትላልቅ ነገሮችን በሙሉ እንጠይቀው! የትኛውንም ዱዓ እንዳትረሱ ዛሬ ማታ የዱዓ ዝርዝር (ሊስት) ጻፉ!
በተለይ ነገ ከዓስር እስከ መግሪብ ያለውን ወርቃማ ሰዓት ለማንም አትስጡ። ክፍል ገብታችሁ፣ በር ዘግታችሁ፣ ስልክ አጥፍታችሁ እጃችሁን ወደ ሰማይ በማንሳት አላህን በግል አናግሩት። "ጌታዬ ሆይ! እኔ ደካማ ነኝ፣ አንተ ግን ሀያል ነህ... ማረኝ!" በሉት።
አላህ የነገውን ቀን ጾመው፣ ዱዓቸው ተቀባይነት አግኝቶ ከእሳት ነጻ ከሚወጡት ባሮቹ ያድርገን! አሚን! 🤲 | 5 835 |
| 5 | 🕋 ለበይከሏሁመ ለበይክ! የአመቱ ታላቁ ቀን ደረሰ!
በእነዚህ ቀናት የዓለማችን ልዩ ስፍራ በሆነችው መካ፣ ሚሊዮኖች "ለበይከሏሁመ ለበይክ" እያሉ የሐጅ ስነ-ስርዓትን ለመፈጸም እየተዘጋጁ ነው። በአካል እዚያ መገኘት ባንችልም፣ ልባችን እዚያው ነው!
ያልደረስነውን አላህ (ሱ.ወ) በቅርቡ ከሚያስተናግዳቸው እንግዶቹ (ሑጃጆች) እንዲያደርገን፣ ዘንድሮ ለሄዱት ደግሞ ሐጃቸውን "ሐጅ አል-መብሩር" (ተቀባይነት ያለው ሐጅ) እንዲያደርግላቸው ከልብ ዱዓ እናድርግ! 🤲
እኛስ?
የአመቱ ታላቁ ቀን ከነገ ወዲያ ነው! የፊታችን ማክሰኞ የዙል-ሒጃ 9ኛ ቀን፣ ማለትም የዐረፋ ቀን ነው! የዐረፋ ቀን አላህ (ሱ.ወ) ባሮቹን ከእሳት ነጻ የሚያወጣበት፣ ዱዓዎች ተቀባይነት የሚያገኙበት፣ እና ዲናችን ሙሉ የሆነበት ታላቅ ቀን ነው! ለዚህ ቀን ከወዲሁ ልዩ ዝግጅት ያስፈልገናል፡-
• መጾም (ያለፈውን እና የሚመጣውን የ2 ዓመት ወንጀል ያስምራል)
• ዱዓን ማብዛት
• ተክቢራ ማብዛት
አላህ ቀኑን በአግባቡ ከሚጠቀሙት ያድርገን🤲 | 5 269 |
| 6 | 🪨 ሸይጧንን መውገር - የውስጥን ፈተና ማሸነፍ
ሑጃጆች በሚና የ"ጀመራት" ስነ-ስርዓትን ሲፈጽሙ (ጠጠር ሲወረውሩ) የምናየው፣ አባታችን ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጃቸውን ሊያርዱ ሲሄዱ ሸይጧን ሊያሳስታቸው በመጣ ጊዜ ጠጠር በመወርወር ያባረሩበትን ታሪክ ለማስታወስ ነው።
አባታችን ኢብራሂም ሸይጧንን ጠጠር ወርውረው አባረሩት። የኛስ ሸይጧን? ወደ መስጊድ ስንሄድ፣ ሰደቃ ልንሰጥ ስናስብ፣ ወይም ሱናን ልንተገብር ስንል ሸይጧን "ይቀርብሃል፣ ጊዜ የለህም፣ ሰዎች ምን ይሉሃል" እያለ ያዘናጋናል።
የአባታችን ኢብራሂምን ፈለግ በመከተል እኛም በውስጣችን የሚመጣውን የሸይጧን ጉትጎታ በእምነትና በቁርጠኝነት "ጠጠር ወርውረን" (እምቢ ብለን) እናባርረው! አላህ ያግራልን 🤲 | 5 424 |
| 7 | "አባቴ ሆይ የታዘዝከውን ስራ!" - የልጁ ታዛዥነት
ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) አላህ ያዘዛቸውን ለልጃቸው ለእስማዒል ሲነግሩት፣ የልጁ ምላሽ እጅግ አስገራሚ ነበር!
"ለምን?" ብሎ አልጠየቀም፤ አልተቆጣም፤ ለመሸሽም አልሞከረም። ይልቁንም "አባቴ ሆይ የታዘዝከውን ስራ፤ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ" በማለት አስደናቂ ታዛዥነትን አሳየ!
የእስማዒልን ታሪክ ስናወሳ፣ ለወላጆቻችን ያለንን ክብርና ታዛዥነት ራሳችንን እንጠይቅ። ወላጆቻችን የሚያዙን ወደ መልካም ነገር ሆኖ ሳለ ስንቶቻችን ነን "እሺ" ብለን በታዛዥነት የምንቀበለው? አላህ የወላጆቻችንን ሐቅ የምንወጣ ያድርገን! 🤲 | 6 089 |
| 8 | ታላቁ ፈተና - በጣም የምንወደውን ለአላህ መስጠት
ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በእርጅና ዘመናቸው ያገኙትን፣ ብቸኛ እና እጅግ የሚወዱትን ልጃቸውን (እስማዒልን) እንዲያርዱ በሕልም ታዘዙ። የአላህ ነብያት ሕልም ደግሞ ራዕይ (ወህይ) ነው።
ይህ ፈተና በታሪክ ውስጥ ከታዩት ፈተናዎች እጅግ ከባዱ ነበር! ኢብራሂም ግን የልባቸው ቁራጭ የሆነውን ልጃቸውን ለአላህ ትዕዛዝ ሲሉ አሳልፈው ለመስጠት አላመነቱም።
እኛ ልጃችንን እንድናርድ አልታዘዝንም። ነገር ግን አላህን ለማስደሰት ስንል የትኛውን የምንወደውን ነገር (ምቾታችንን፣ መጥፎ ጓደኛን፣ የተከለከለ ፍላጎትን) መስዋዕት አድርገናል? ሁላችንም አላህ ይቀበለን 🤲 | 6 400 |
| 9 | 💧ጥረት እና እምነት - (የሶፋ እና መርዋ ትምህርት)
ህጻኑ እስማዒል በውሃ ጥም ሲያለቅስ፣ እናታችን ሀጀር ዝም ብላ አልተቀመጠችም። ውሃ ለመፈለግ በሶፋ እና መርዋ ተራራዎች መካከል ሰባት ጊዜ ተመላለሰች (ሮጠች)። አላህም ጥረቷን ተመልክቶ በህጻኑ እስማዒል እግር ስር ልዩ የሆነውን የዘምዘም ውሃን አፈለቀላት!
ተወኩል ማለት ቁጭ ብሎ መጠበቅ ማለት አይደለም። አላህን ማመን እና የራስን ጥረት (ሰበብ) ማድረስን ይጠይቃል። ሀጀር ሰበብ አደረሰች፣ አላህ ደግሞ ተዓምር ሰጣት!
ሁላችንም ለዱኒያም ሆነ ለአኼራ ስኬታችን የራሳችንን ጥረት እናድርግ! አላህ ተዓምሩን ያሳየን! 🤲 | 7 158 |
| 10 | 🏜 ታላቁ መመካት - የእናታችን ሀጀር ታሪክ
የዙል-ሒጃ ቀናት እና የሐጅ ስነ-ስርዓቶች የነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና የቤተሰባቸውን ታላቅ መስዋዕትነት የምናስታውስባቸው ቀናት ናቸው።
ነብዩ ኢብራሂም ባለቤታቸውን ሀጀርን እና ህጻኑን እስማዒልን ሰውም ሆነ ውሃ በሌለበት በረሃ (መካ) ትተዋቸው እንዲሄዱ በአላህ ታዘዙ። እናታችን ሀጀርም "ይህን እንድታደርግ አላህ አዞሃልን?" ብላ ጠየቀች። "አዎ" ሲሏት፣ "እንግዲያውስ አላህ እኛን መቼም አይጥለንም!" በማለት አስገራሚ የሆነ እምነቷን አሳየች።
እንደ እናታችን ሀጀር በአላህ ላይ ሙሉ ተወኩል ይኑረን፤እርሱ መቼም አይጥለንም! | 7 283 |
| 11 | የተረሳውን ሱና ህያው እናድርግ!
የዙል-ሒጃ አስርት ቀናት የዚክር ቀናት ናቸው! ሰሃባዎቹ ኢብኑ ዑመር እና አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) በእነዚህ ቀናት ወደ ገበያ ሲወጡ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ተክቢራ ይሉ ነበር፤ ሰዎቹም አብረዋቸው ተክቢራ ያደርጉ ነበር።
በመንገድ ላይ፣ በቤታችን፣ በስራ ቦታችን ይህንን እንበል፡-
"አላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ ወላሁ አክበር፣ አላሁ አክበር፣ ወሊላሂል ሐምድ! | 7 432 |
| 12 | 🌟 ከአለም ቀናት ሁሉ በላጮቹ ቀናት ነገ ይጀምራሉ።
እነዚህ 10 ቀናት አላህ (ሱ.ወ) በቁርኣን የማለባቸው ታላላቅ ቀናት ናቸው። የረመዳን የመጨረሻዎቹ 10 ሌሊቶች በአመት ውስጥ በላጭ ሲሆኑ፣ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ደግሞ ከቀናት ሁሉ በላጭ ናቸው!
ከነገ ጀምሮ ጾም፣ ቁርኣን፣ ሰደቃ እና ዚክር እናብዛ! አላህ ከሚጠቀሙት ያድርገን! | 8 023 |
| 13 | ⏳ ወደ በላጮቹ 10 ቀናት መግቢያ ላይ ነን!
ከአመቱ ቀናት ሁሉ ታላቅ ወደሆኑት የዙል-ሒጃ (የሐጅ ወር) የመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት ልንገባ የ ቀናት ዕድሜ ብቻ ቀርቶናል! አሁን የምንገኝበት የተከበረው የዙል-ቂዕዳ ወር ማሳረጊያ ላይ ነው።
በዚህ ሰዓት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናን ከየአለማቱ ወደ ተከበረችው መካ ጉዟቸውን ጀምሯል። አካላችን እዚያ መገኘት ባይችልም፣ ልባችን እና ዱዓችን ግን ከእነርሱ ጋር ነው! 🕋✨
ረመዳን ሲመጣ ቤታችንን እና ልባችንን እንደምናጸዳው ሁሉ፣ ለእነዚህ "ወርቃማ 10 ቀናት" ዝግጅት አላህ (ሱ.ወ) ካከበራቸው ወራት ውስጥ ነንና ከወንጀል ርቀን በኢስቲግፋር (ምህረትን በመጠየቅ) እንቀበላቸው!
አላህ ሆይ! ያንን የተከበረ ቤት ለመዘየር፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ለማድረግ፣ በዐረፋ ተራራ ላይ መቆመን በቅርቡ ወፍቀን! አሚን 🤲 | 10 261 |
