Mere- Protestantism
رفتن به کانال در Telegram
ቅድስና ለእግዚአብሔር!! የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፍን ለመግዛት፦ በቴሌግራም አድራሻ፦ @Kenu_lemma ላይ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ።
نمایش بیشتر2 419
مشترکین
+324 ساعت
+967 روز
+24330 روز
آرشیو پست ها
2 419
ነገ ቅዳሜ ነው። #ምን_ትመክረኛለህ? መልሶች ነገ ይቀጥላሉ። በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ጥያቄዎቻችሁን አሁንም መላክ ትችላላችሁ።
2 419
ምን ትፈልጋለህ?
ዛሬ ሴሚናር ነበረኝ። ያቀረብነው ሴሚናር በ Cervical cancer screening techniques ላይ ትኩረት ያደረገ ነበር። ለአንድ ሙሉ ሳምንት ቀንና ሌሊት ተግተን፣ መጻሕፍትን አገላብጠን፣ ወደ 100 ስላይድ የሚጠጋ ያህል ግዙፍ PowerPoint አዘጋጀን።
ትላንት ማምሻውን ታዲያ ሴሚናሩን የምናቀርብለት ዶክተር፦ "ለማቅረብ ያዘጋጃችሁትን ላኩልኝ" አለን፤ ላክንለት። ከአንድ ሰዓት በኋላ ግን መልእክት መጣ፦ "ብዙ ነገሮችን ዳስሳችኋል፤ ግን እኔ የምፈልገውን አላካተታችሁም!" አለ ዶክተሩ።እንዴት ያለ ድካም ነው! እኛ በሺዎች የሚቆጠሩ ገጾች ያሏቸውን መጻሕፍት አገላብጠን፣ ብዙ ደክመን ስንዘጋጅ... ለካ የርሱ ፍላጎት ከ40 ገጽ የማይበልጡትን የ WHO እና የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር (FMOH) መመሪያዎች (Guidelines) ብቻ ማየት ነበር። ብዙ ስናሳድድ፣ ትላልቁን መጻሕፍት ስናገላብጥ... ለካ የዶክተሩ እርካታ ያለው በነዚያ ጥቂት ገጾች ውስጥ ነበር። አይይይ... ልፋት! አሁን ሁሉንም አፍርሰንና በድጋሚ ሠርተን ሴሚናሩን በድል አጠናቅቀናል፤ ይህ ክስተት ግን አንድ ጥያቄ ራሴን እንድጠይቅ እያደረገኝ ነው፦
''ጌታ ሆይ፤ ሳገለግልህ፣ ስሮጥልህ አንተ የምትፈልገውን ነገር እያካተትሁ ነው? ወይስ ብዙ ቦታ እየረገጥሁ አንተ የምትፈልጋት ትንሽ ነገር ትቼ ይሆን? ብዙ ሮጬ የገነባሁት አንተ 'አላረካኝም፤ የምፈልገውን አላካተተም' ብለህ የምትመልሰው ይሆን? ምን ትፈልጋለህ፣ ምን ላካትት ጌታ ሆይ?''
ብዙ ''የአገልግሎት ስላይድ'' ገንብተን እግዚአብሔር የሚፈልገውን ጥቂት ነገር የሚያጣብን እንዳንሆን ሁልጊዜ ራሳችንን መመርመር ያስፈልገናል።
ጌታ ግን እንዲህ ሲል መለሰላት፤ “ማርታ፣ ማርታ፤ ስለ ብዙ ነገር ትጨነቂያለሽ፤ ትዋከቢአለሽም፤ የሚያስፈልገው ግን አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ማርያም እኮ የሚሻለውን ድርሻ መርጣለች፤ ይህም ከእርሷ አይወሰድም።”__ሉቃ 10፥41-42 በእርሱ እግር ሥር ጸጥ ብሎ መቀመጥ፣ ልብን ለእርሱ መሥጠትና የርሱን የፍቅር መመሪያ መቀበል ያድርግልን።
2 419
ዛሬ ላይ ብዙዎቻችን ቀሽም ወንጌል ሰባኪዎች ነን። ይህም የሆነው ሲበዛ ሰነፍ እና ራስ ተኮር ስለሆንን ነው። ሰዎችን ለመገናኘት አስፓልት እንኳን ለመሻገር ፈቃደኛ አይደለንም። ስለ ክርስቶስ በማውራት የሚመጣ ማኅበራዊ መገለል እንዳለ እናውቃለን፤ ነገር ግን እርሱን ጨክነን እንዳናልፍ ያደረገን ስለ ጓደኞቻችን፣ ቤተሰቦቻችን ወይም የሥራ ባልደረቦቻችን መዳረሻ በበቂ ሁኔታ ግድ የማይሰጠን መሆናችን ነው።
_ ሪካርድ ፊሊፕስ
ወንጌል ለሰዎች የማድረስ ተልእኮ አጋጣሚዎችን ነቅቶ የመፍጠር እና መጠቀም ጉዳይ ነው። ስለማናስተውል እንዲሁም በራሳችን ሐሳብ ተወጥረን ስላለን እንጂ ሁላችንም በየቀኑ በርካታ ወንጌልን የመስበክ አጋጣሚዎች አሉን። እስቲ ነገ አእምሯችንን ከፍተን አጋጣሚዎችን እንቃኝ። ቢያንስ ለአንድ ሰው ክርስቶስ ያመጣልንን መልካም ዜና የምሥራች ብለን እናድርስ።
2 419
ትላንት በተደረገው የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፍ ምረቃ ላይ ተገኝተው ስለ መጽሐፉ ማብራሪያ የሰጡት ፓስተር ሰሎሞን አበበ ገብረ-መድኅን ፖርኖግራፊ የሚለውን ቃል ወደ አማርኛ ሲተረጉሙት እንዲህ ብለው ነበር፦''የእርቃን ጋጠወጥነት''
እኔም ትላንት የተማርኹት ቃል ነው😁
2 419
ለዚህ ሳምንት ይብቃን። ያልመለስሁላችሁ ካላችሁ ይቅርታዬ ይድረሳችሁ🙏 ጌታ ቢፈቅድ እና ብንኖር ቀጣይ ሳምንት ቅዳሜ ደግሞ ሌሎች ጥያቄዎችን መመለስ ጀምራለሁ።
ከአሁን ጀምሮ ለቀጣይ ሳምንት የሚመለሱ ጥያቄዎቻችሁን መላክ ትችላላችሁ። ጥያቄዎቹ በመጡበት ቅደም ተከተል የምመልስ ይሆናል🙏
ማሳሰቢያ፦
ጥያቄዎቹን ስትጽፉ በዚህ መሠረት ይሁን፦
1. እድሜያችሁን + ጾታ አስቀድሙ
2. ጥያቄያችሁን (በተቻለ መጠን በአጭሩ)
3. ''ምን ትመክረኛለህ?'' በሚለው ሐረግ ጥያቄያችሁን አጠናቅቁ።
በዚህ መሠረት ከሌሎች ዓይነት ጥያቄዎች የእናንተን ለመለየት ይረዳኛል።
ጥያቄዎቻችሁን እዚህ ላይ አስቀምጡ👇
https://ngl.link/kenu_lemma
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
#10 ተስፋ መቁረጥ
ልክ ብለሃል ወንድሜ። ምንም ደኅና ሰው የመሆን ተስፋ የለህም! ጎበዝ ነህ ራስን በደንብ አውቀሃል።
አሁን ግን... መስቀሉን እይ! አሁን ግን ጸጋውን እይ።
በራስህ ስትሆን ተስፋ የለህም፦
''በዚያን ዘመን ከክርስቶስ ተለይታችሁ.... በዓለም ላይ ያለ ተስፋና ያለ እግዚአብሔር እንደ ነበራችሁ አስታውሱ።'' ኤፌ 2፥12
በክርስቶስ ስትሆን፦
''የክብር ተስፋ የሆነው በእናንተ ውስጥ ያለው ክርስቶስ ነው።'' (ቆላ 1፥27)
በክርስቶስ ያለህ ተስፋ ብቻ ሳይሆን የክብር ተስፋ ነው። ራስህን ወደ መስቀሉ አምጥተህ፤ ራስህን በክርስቶስ ውስጥ ተመልከት። ስሜትህ፣ ሰይጣን፣ ዓለም የሚነገሩህን ሳይሆን ክርስቶስ የሚነግርህን ስማ!!
ይህን እመክርሃለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ
#9 አሥራዎቹ እድሜ
19 ዓመትህ ነው። ወሲባዊ ፍላጎት አለህ፤ ለየትኛውም የፍቅር ግንኙነት ፍላጎት ግን እስካሁን ኖሮህ አያውቅም።
ይህ ጤናማ ነው። ወሲባዊ ፍላጎት እግዚአብሔር በመልካምነቱ ለሰው ልጅ ሁሉ የሰጠው በጎ ስጦታ ነው። ነገሩ በራሱ እጅግ መልካም ነው። ነገር ግን ይህ ፍላጎት በየትኛውም ደረጃ ወደ ተግባር መውረድ ያለበት በትዳር ውስጥ ነው። አንተም 19 ዓመትህ ነው። እንደ ጌታ ፈቃድ ከኖርከው ይልቅ የምትኖረው ይበልጣል። ስለዚህ ትክክለኛውን ሰው አግኝተህ የምታፈቅርበት እና ወደ ትዳር የምትገባበት እድሜ ከፊትህ አለ። ስለዚህ እንደ ክርስቲያን ራስህን በመግዛት ኑር።
ራስህ እንዳይገዛህ ራስህን ግዛው እንጂ!!
ይህን እመክርሃለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
#8 Relationship
እኔ እንዲህ አድርግ ወይም አታድርግ ከምልህ ይልቅ ሁለት ነገሮችን ብቻ ልንገርህ እና አንተው መወሰን እንድትችል እድሉን ልስጥህ፡፡ ''የፍቅር ግንኙነት ልጀምር?'' የሚለው ጥያቄህን መመለስ ያለበህ ሁለት ነገሮችን ከመዘንህ በኋላ ነው፡፡
1. ለትዳር የሚበቃ የፍቅር ግንኙነት ምን ዓይነት ኀላፊነቶች አሉበት? ጥቂቶቹን ብቻ ልዘርዝርልህ
👉 መሪነት (መንፈሳዊ + አካላዊ)
👉 የሕይወት ራእይ እና ወደ እርሱ የተጀመረ እንቅስቃሴ
👉 ለመለወጥ እና comfort zone ለመልቀቅ ፈቃደኛ መሆን
👉 የተናገሩትን የመፈጸም እና በተግባር የመኖር አቅም
👉 ጤናማ Communication skill
👉 ወሲባዊ ቅድስና
👉 ስሜታዊ ብስለት (የራስን ስሜት የመግዛት ችሎታ ሲደመር የሌላውን ሰው ስሜት መረዳት)
👉 የግጭት አፈታት ጥበብ
👉 ታማኝነት
2. ''እነዚህን ኀላፊነቶች አሁን እኔ መወጣት እችላለሁ ወይስ ትንሽ ጊዜ ይቀረኛል?'' ብለህ ራስን ጠይቅ እና በዚህ እድሜ ወደ ፍቅር ግንኙነት ልግባ አልግባ የሚለውን ራስህ ወስን፡፡
ወንድሜ እነዚህ ባሕርያት ከሌሉህ ወደ የፍቅር ግንኙነት ውስጥ መግባት ብትችል እንኳን በአጭር ጊዜ ውስጥ ነገሮች ወደ ሲኦል ይለወጡብህ እና ካልወጣው ብለህ ማስቸገርህ እይቀርም😁
ይህን ስልህ ደግሞ የፍቅር ግንኙነት ኀላፊነት ብቻ ነው ብለህ እንዳታስብ አደራ፡፡ በጣም በርካታ በረከቶች አሉት፡፡ ነገር ግን በረከቶቹ ብዙ ጊዜ የሚመጡት እነዚህን ኀላፊነቶችህን በአግባቡ ስትወጣ ነው፡፡ ካልሆነ ነገሮች ይከብዱሃል፡፡ ለወሲባዊ ቅድስናህም ፈተና ከመሆን ያለፈ ምንም ተስፋ ላይኖረው ይችላል፡፡ ስለዚህ ብዙ ነገር አገናዝበህ ወስን።
ደግሞም አትቸኩል!!
ይህን እመክርሃለሁ፡፡
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
#7 ፍርሃት
ፍርሃትን መጋፈጥ ፍርሃትን አያስወግድም። የፍርሃቱን ምንጭ መርምረህ ማስወገድ ካልቻልህ ፍርሃቱን መጋፈጥህ ብቻውን ነጻ አያወጣህም። ስለዚህ ''ተቃውሞን እና ውድቀትን ለምን እፈራለሁ?'' ብለህ ሥሩን መርምረው እና ከእርሱ ጋር ተፋጠጥ። ሥሩን ሳትነቅለው ፍርሃቱን አትነቅለውም። እና የፍርሃቱ ሥር ምን ይሆን?
👉 በሰው አድናቆት (external validation) ላይ የተመሠረተ የራስ ዋጋ?
👉 ፍጹም ሆኖ ለመታየት መፈለግ? (perfectionism)
👉 ካለፈ ውድቀት በልጅነት የደረሠብህ ጠባሳ? (Childhood trauma)
.
.
.
እንዲህ እያልህ ሥሩን ፈልገህ አግኘው። ከዚያ እርሱን መታገል አለብህ።
ፍርሃትን ለመጋፈጥ ወንጌልን መስበክ ያልከውም ጥንቃቄ ይፈልጋል። ወንጌልን የምንሰብከው የራሳችንን ችግሮች ለመፍታት መሆን የለበትም። ሰዎች ወደ ድነት መንገድ እንዲመጡ ለመጥራት ነው ቀዳሚ ግባችን መሆን ያለበት። እውነት ነው ወንጌል ስንሰብክ እኛም ከብዙ ነገር እንፈወሳለን ግን ይህ primary motive አይደለም።
ምን ላንብብ ላልከኝ የ Edward T. Welch መጻሕፍትን ብታነብ በተለይ when people are big and God is small የሚለው መጽሐፍ ጥሩ መጽሐፍ ነው።
ይህን እመክርሃለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
#6 ፖርኖግራፊ
መጽሐፌ ላይ ይህን ዓይነቱን ሁኔታ የኅሊና ነውጥ ስል ገልጬዋለሁ። ርጋተ ኅሊና በሚለውም ምዕራፍ በስፋት መፍትሔውን አስቀምጫለሁ። እና መጽሐፉን አግኝተህ ብታነብ መልካም ነው።
ግን ከፖርኖግራፊ መውጣት እና መዳን ይቻላል። ብዙ እንደ ደከመህ እረዳለሁ። ነገር ግን እጅ አትስጥ። መታገልህን አታቁም! ነገር ግን በትክክለኛው መንገድ መታገል አለብህ። አንዳንዴ ደጋግመን የምንወድቀው በተሳሳተ መንገድ ስለምንታገል ነው።
በቅርብ ይህን በስፋት የምናስተምርበት ፕሮጀክት ይጀመራል። እርሱን መጀመራችንን ስናሳውቅ ፈጥነህ ተመዝገብ።
ይህን እመክርሃለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ
#5 ፖርኖግራፊ
ከፖርኖግራፊ ለመውጣት በሚደረግ ትግል ውስጥ ደጋግሞ መውደቅ እጅግ የተለመደ ነው። ትልቁ መፍትሔ ለምንድን ነው እየወደቅሁ ያለሁት የሚለውን በመመርመር ለእርሱ ተገቢ ምላሽ መስጠት ነው።
በዚህ ጉዳይ በቅርቡ ትልቅ ፕሮጀክት ለመጀመር እየተንቀሳቀስን ስለሆነ እርሱ ሲጀመር ብትቀላቀል እጅግ ብዙ ትማራለህ።
ይህን እመክርሃለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
# 4 Breakup
ሁለት ነገሮችን አጥፍተሻል፦
1. የራስሽን ዋጋ (self worth) ከጓደኛሽ መኖር አንጻር ለክተሻል። ከጓደኛሽ ጋር የነበረሽ ግንኙነት ሲፈርስ አብዛኛው የሕይወትሽ ክፍል የፈረሰው ለዚህ ነው።
2. ሰው አይወደኝም ብለሻል። ችግሩ መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ይውደዳችሁ አይልም። ሰው ውደዱ ነው የሚለው። ቤተ ክርስቲያን የምንሄደው፣ ከወንድሞች ጋር ኅብረት የምናደርገው ስለሚወድዱን አይደለም፤ ስለምንወድዳቸው ነው። ስለዚህ ማንም እንዲወድድሽ መኖር የለብሽም! ለመውደድ ነው መኖር ያለብሽ።
መፍትሔው
1. ስለ ራስሽ ያለሽ ዋጋ በክርስቶስ ካገኘሽው ማንነት ይመዘዝ። የራስሽን ዋጋ በሌላ ሰው በመመሥረትሽ ንስሐ ገብተሽ ከክርስቶስ ጋር ያለሽን ግንኙነት አድሽ። ክርስቶስ አንቺን በሚያይሽ መንገድ ራስሽን ለመመልከት ተግተሽ ቃሉን ማጥናት እና መጸለይ አለብሽ። ከዚያም conditional ከሆነ self worth ነጻ ትወጫለሽ። እርሱ ውስጥ መሰወር ይሆንልሻል። (ቆላ 3፥3)
2. ካለፈው breakup ጊዜ ወስደሽ አእምሮሽ ላይ በመሥራት ፈውስ አግኚ። ለራስሽ ''ደኅና ነኝ'' እያልሽ መናገር አቁመሽ ከሕመምሽ ጋር ፊት ለፊት ታግለሽ ተፈወሺ።
3. ሰውን መውደድ ላይ አተኩሪ። መውደድ እንድትችይ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳሽ ጸልይ።
2 419
ዛሬ የፖርኖሲስ ትውልድ መጽሐፋችን በድምቀት ተመርቋል። ካሰብኩት በላይ የጌታ መገኘት ነበረ። እንዲሁም በርካታ ሰዎች ተገኝተዋል። የቤተ ክርስቲያኑ ወንበር ሞልቶ ሰዎች ውጭ ተቀምጠው ነበር።
የአዳማ ሕዝብ❤️
ጌታ ክብሩን ይውሰድ።
በዚሁ አጋጣሚ ትላንት በምርቃቱ ዝግጅት ተወጥሬ በርካታ የ #ምን_ትመክረኛለህ? ጥያቄዎችን ሳልመልስ ቀርቻለሁ። አሁን ገብቼ ጥያቄዎቹን ልመልከት እና በተቻለኝ መጠን በአጭሩ ለመመለስ ልሞክር። እያንዳንዱ ጥያቄ ላይ በጥልቀት መሄድ ባለመቻሌ ከወዲሁ ይቅርታዬ ይድረሳችሁ🙏
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
# 3 ''ማንም አይወደኝም'' የሚል አስተሳሰብ
በመጀመሪያ ማንም አይወደኝም የሚለውን አስተሳሰብህን ብትመረምረው መልካም ነው። ''ማንም እንደማይወደኝ ለምን አስባለሁ?'' ብለህ ጠይቅ።
👉 አንድ ሰው እንደማይወድህ ስላወቅህ ወይም ስለተነገረህ Overgeneralize አድርገህ?
👉 ያለመወደድ ስሜት ስለሚሰማህ ብቻ በ emotional reason ተጠቅመህ?
👉አንተ የሌሎችን አእምሮ ማንበብ ስለምትችል፣ Mind reader ስለሆንህ?
ማለትም የእውነት ማንም አይወድደኝም የሚለው ስሜት አንተ ውስጥ ብቻ ያለ እና አንተው የፈጠርኸው እና አምነህ እየኖርህ ያለኸው ነገር ሊሆን ይችላል። so እርሱን በደንብ አጣራ።
2. የትሕትና መንፈስ እንዲሰጥህ አጥብቀህ መጸለይ አለብህ። ትሕትናን በሕይወትህ ተለማመድ። አንዳንዴ ያለመወደድ ስሜት የሚሰማን ስለ ራሳችን በጣም ስለምናስብ እና ሰው ሁሉ በታላቅ ክብርና እንክብካቤ እንዲቀበለን ስለምንፈልግ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ከዚያ ካሰብነው expectation ትንሽ ሲጎድልብን ያለመወደድ ስሜት ይሰማናል። So ትሑት መሆን እና የተለየ እንክብካቤ አለመፈለግ ወሳኝ ነው።
3.ሌላውን ሰው ውደድ። ያለመወደድ ስሜትህ የአንተ ሌሎችን አለመውደድ ነጸብራቅ ሊሆን ይችላል። ኅላፊነትህ መውደድ እንጂ መወደድ እንዳልሆነ ለራስህ አስታውስ። ከምትቀበለው ይልቅ የምትሰጠው ላይ ይበልጥ ትኩረት አድርግ።
4. ሌላው በደንብ መጸለይ አለብህ፤ ነገሩ መንፈሳዊ ተጽእኖም ሊኖረው ስለሚችል።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ
#2 Relationship
ስለ አንቺ እና ስለ እርሱ ማንነት ስለማላውቅ specific ነገር ለማስቀመጥ ይከብደኛል ነገር ግን ከአጠቃላይ መርህ አንጻር ብታደርጊ ብዬ ማስባቸውን ነገሮች Stepwise ላስቀምጥልሽ፦
1. ጤናማ ግንኙነት ውስጥ መሆንሽን አረጋግጪ። (አንዳንድ ጊዜ toxic relationship ውስጥ ያሉ ልጆች በርካታ ችግር ያለባቸው እና ያልበሰሉ መስሎ እንዲሰማቸው ሊደረጉ ይችላሉ)
ያው ጤናማ ካልሆነ ግንኙነታችሁ ፈጥነሽ መውጣት ምርጫ የለውም።
2. ጤናማ ግንኙነት ውስጥ ካለሽ እና እውነትም ግንኙነቱን የሚረብሹ ባሕርያት ካሉሽ፦ በደፈናው ችግር አለብኝ ከማለት ይልቅ በዝርዝር እወቂያቸው። ምንድን ነው ያጠፋሁት? ምን ማድረግ ነበረብኝ? .. እያልሽ ነገሮችን ለመተንተን፣ ለማሰብ እና ለመጻፍ ሞክሪ። በዚህ ውስጥ ሁለታችሁ መውሰድ ያለባችሁ የጋራ እርምጃ ካለ በግልጽ ብትነጋገሩ ጥሩ ነው።
3. የጻፍሻቸው ችግሮች እዛው relationship ውስጥ እያለሽ ሊፈቱ የሚችሉ መሆናቸውን ፈትሺ። ይህ ከጓደኛሽ ጋር መነጋገርንም ይፈልጋል። Relationship ሁለት እድገት የጨረሱ ሰዎች የሚገናኙበት ሳይሆን ሁለት ሰዎች በመደጋገፍ አብረው የሚያድጉበት ነው። ስለዚህ ለማደግ መፍቀድ፣ ሌላው ባለማደጉ የሚመጡ ጉዳቶችን መቀበል እና ይቅር ማለት ይፈልጋል። So ብዙ ጉልበት ይጠይቃል። (እዚህ ደረጃ ላይ መፍታት ከቻላችሁ በጣም ተመራጭ ነው)
4. Relationship ውስጥ እያለሽ መፍታት የማትችያቸው እና ጊዜ የሚያስፈልግሽ ዓይነት ከሆነ ግንኙነታችሁ ሳይፈርስ በመስማማት ጥቂት ጊዜ እረፍት መውሰድ ትችላላችሁ። አንቺም የራስሽ ባሕርይ ላይ እርሱም የራሱ ላይ ለመሥራት ግልጽ አሣይመንት እና የቀን ገደብ ተሰጣጣችሁ በመስማማት እረፍት መውሰድ ይቻላል። (ይህ መንገድ ለአንዳንዶች ሲሠራ አይቻለሁ ለሌሎች ደግሞ አይሠራም)
5. ከነዚህ ድርጊቶች በኋላ ምንም ለውጥ ከሌለ መለያየቱን ማሰብ ይቻላል።
ሌላው your assumptions ነገሮችን እንዳያከብዱብሽ ፈራለሁ። ለምሳሌ፦
👉 ጸልየን ነው የገባነው ብለሻል ግን ጸልያችኋል ማለት ነገሮች አልጋ በአልጋ ይሆናሉ ማለት አይደለም።
👉 እንጋጫለን ብለሻል ይህ ግን ጤናማ ነው። ግጭት አፈታቱ ነው ዋናው።
👉 እድሜሽ ደግሞ 23 ነው ማለት ገና የምታድጊበት እድሜ ነውና በባሕርይሽ አለመርካትሽ ትክክል ነው።
ዋናው መልእክት ግን ይህ ነው፦
አሁን ''ቸኩዬ ገባሁ'' የሚል ስሜት እንዳለሽ ሁሉ ነገ ''ቸኩዬ ወጣሁ'' የሚል ስሜት እንዳይኖርሽ በመረጋጋት አስቢ፣ ጸልዪ ግን ሳትጨነቂ ይሁን።ሕይወት በጣም ሰፊ ናት።
ይህን መክርሻለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ?
#1 ስለ ቅናት
በመጀመሪያ ቅናት አንድ ባሕርይ ብቻ አይደለም። ይልቁንስ የአራት ክፉ ሐሳቦች ድምር ውጤት ነው። እነዚህም፦
1. ራስን ወዳድ ወይም Self centered መሆን
2. የውድድር መንፈስ- ማለትም ከሌላው ጋር ውድድር ውስጥ መግባት
3. የሌላውን ድል እንደ ራስ ውድቀት አድርጎ መመልከት
4. ክፋት (ሌላው እንዲወድቅ በልብ መመኘት)
ስለዚህ ከቅናት መላቀቅ ከእነዚህ አራት ሐሳቦች መፋታት ይጠይቃል። እና አራቱን ክፉ ሐሳቦች ለመስበር የሚሆኑ ጥቂት መንገዶችን ብቻ ላስቀምጥ፦
1. Self centered ከመሆን ለመፋታት፦ ''እኔ በዓለም ካሉ 8 ቢሊየን ሕዝቦች መካከል አንዱ ነኝ'' ብሎ ማሰብ ወሳኝ ይመስለኛል። ዓለም በእኔ ዙሪያ አትሽከረከርም። ይልቁንስ እኔን ጨምሮ መላ ዓለም የምትሽከረከረው በፈጣሪዋ በእግዚአብሔር ዙሪያ ነው። እርሱ ነው ማዕከሏ። So God centered መሆን ወሳኝ እርምጃ ነው።
2.ከውደድር መንፈስ ለመፋታት፦ ''የእኔ ዋጋ ከሌላው መብለጥ ላይ አይመሠረትም'' ብሎ ማሰብ እንዲሁም ራስን እንደ ልዩ (unique but not superior) አድርጎ መመልከት።
3. የሌላውን ድል የራስ ውድቀት አድርጎ ከመመልከት ለመፋታት፦ ትልቁ መፍትሔ scarcity mindset ማስወገድ ነው። ማለትም እግዚአብሔር ባለጠጋ አምላክ ነው ስለዚህ ለሌላው ሲሰጥ ከእኔ መቀነስ አይጠበቅበትም!! አጽናፈ ዓለም ለሁሉም የሚበቃ በረከት አለው። እንዲሁም ተገላቢጦሹንም ማሰብ ጠቃሚ ነው፤ ማለትም፦ የእነርሱ ውድቀት ለእኔ በረከት ያመጣል? መልሱ አያመጣም ከሆነ፦ የእርሱ በረከትም ለእኔ ውድቀት አያመጣም።
4. ክፋትን ወይም ምቀኝነትን ለመፋታት፦ ራሳችንን በእነርሱ ቦታ በማስቀመጥ ርኅራኄን ማሳደግ አስፈላጊ ነው። እነዚህ ሰዎች እኮ እንደ እኛው ሰው ናቸው ማለትም ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ ድካም... አለባቸው ስለዚህ ይህ በረከት ይገባቸዋል። እና ለጥቂት ጊዜያት ከውስጥህ ጋር እየታገልህም ቢሆን መልካም ነገር መመኘት፣ ''እንኳን ደስ አለህ'' እያሉ መናገርን፣ ብቻ በተለያየ መንገድ ደስታን መግለጥን መለማመድ ያስፈልግሃል። ከዚያ ራሱ አድጎ ባሕርይህ ይሆናል።
በቅን ልብ ነገሩን ወደ ክርስቶስ መስቀል ስለወሰድኸው በጥረትህ ውስጥ እርሱም ይረዳሃል።
ይህን እመክርሃለሁ።
2 419
#ምን_ትመክረኛለህ? ቻሌንጅ!!
በ Anonymous ፕላትፎርም የተላኩ በርካታ ጥያቄዎችን ሳልመልስ በመቅረቴ በውስጥ የአንዳንድ ልጆች ቁጣ ተቀስቅሷል። ለዚህ ይቅርታ ጠይቃለሁ። ያው እናንተም እንደምትረዱኝ ከጊዜ መጣበብ የተነሣ አንዳንዴ ገብቼ ጥያቄዎችን አለፍ አለፍ እያልሁ ከማየት ባለፈ በቋሚነት ለመከታተል አልቻልሁም። አሁን ግን ይህን ክፍተት ለመሙላት እና ከሁሉ ጋር በቅርበት ለመቆየት #ምን_ትመክረኛለህ? የሚል አዲስ ሳምንታዊ ቻሌንጅ ለመጀመር እቅድ አለኝ።
በዚህ መሠረት ለሳምንት ያህል የሚመጡ ጥያቄዎችን ሰብሰብ አድርጌ ቅዳሜ እለት የመመለስ እቅድ አለኝ። ስለዚህ ምክር የምትፈልጉባቸውን ነገሮች አስቀምጡልኝ። የምችለውን ለመመለስ እና እናንተን ለማገዝ፣ የማልችለውን ደግሞ ወደሚመለከተው አካል Refer ለማድረግ ሞክራለሁ።
ማሳሰቢያ፦
ጥያቄዎቹን ስትጽፉ በዚህ መሠረት ይሁን፦
1. እድሜያችሁን አስቀድሙ
2. ጥያቄያችሁን (በተቻለ መጠን በአጭሩ)
3. ''ምን ትመክረኛለህ?'' በሚለው ሐረግ ጥያቄያችሁን አጠናቅቁ።
በዚህ መሠረት ከሌሎች ዓይነት ጥያቄዎች የእናንተን ለመለየት ይረዳኛል። እንዲሁም በሳምንቱ ቀድመው ለተጻፉ ጥያቄዎች ቅድሚያ የምሰጥ ይሆናል። አንዳንድ ጊዜም ጊዜ ሲኖረኝ ከቅዳሜ ሌላ ተጨማሪ ቀን ላይ ለመመለስ ሞክራለሁ።
ወደፊት የቴሌግራም ቦት ወይም ሌላ አማራጭ እስከሚኖረን ጥያቄዎቻችሁን እዚህ ላይ አስቀምጡ👇
https://ngl.link/kenu_lemma
2 419
3. ራስን ማጥፋት መፍትሔ ሳይሆን መሸነፍ ነው፦ ራስሽን ብታጠፊ ቤተሰቦችሽን የምትበቀያቸው ይመስልሽ ይሆናል፤ ነገር ግን ራስን ማጥፋት የሰይጣን ማታለያ እንጂ መፍትሔ አይደለም። የሞተ ሰው ከጊዜ በኋላ ይረሳል፤ በመሆኑም ራስሽን በማጥፋት አንቺን ሙሉ በሙሉ የሚጎዳ እና እድልሽን የሚያበላሽ መሸነፍ እንጂ በማንም ላይ የምታመጪው በቀል የለም። ሕይወትሽን ጠብቀሽ በማለፍ ማሸነፍሽን ማሳየት አለብሽ። ይህ ጊዜ እንደሚያልፍ አትጠራጠሪ፤ ሰይጣን የሚነግርሽን አትስሚ!!!
4. ችግሩን ከሥሩ ለመፍታት እቅድ ይኑርሽ፦
ቦታ፣ ከተማ ወይም አገር መቀየር ብቻውን የውስጥ ሰላም አይሰጥም፤ ምክንያቱም የትም ብትሄጂ ከእናትሽ በላይ ቅስም ሰባሪ የሆኑ ሰዎች ሊገጥሙሽ ይችላሉ። መፍትሔው የውስጥ ጥንካሬሽን ማሳደግ እና የችግሩን መሠረት መፍታት ነው። አሁን ትኩረትሽን ሥራ ፍለጋሽ ላይ አድርጊ፤ የራስሽን ገቢ ስታገኚ ከቤት ወጥተሽ ራስሽን ችለሽ ለመኖር እና የተረጋጋ ሕይወት ለመምራት በቂ እድል ታገኛለሽ።
5. በግልጽ ተወያዪ፦ ከእናትሽ ጋር ተረጋግተሽ በመነጋገር ንግግራቸው ምን ያህል እየጎዳሽ እንደሆነ በግልጽ አስረጂአቸው። ይህ የማይሆን ከሆነ እና መረበሽሽ ከቀጠለ ግን፣ ሥራ እስክታገኚ ድረስ ጊዜያዊ ማረፊያ (ዘመድ ወይም ታማኝ ጓደኛ) ፈልጊ። ነገር ግን የምትሄጂበት ቦታ አስተማማኝ እና ደኅንነቱ የተጠበቀ መሆኑን እርግጠኛ ሁኚ፤ ምክንያቱም ሴት በመሆንሽ ምክንያት የሕይወት ዘመን መዘዝ ሊያመጡብሽ የሚችሉ ብዙ ዐደጋዎች ሊገጥሙሽ ይችላሉ እና ራስሽን መጠበቅ አለብሽ። የአሁኑ ሁኔታ ስለመረረሽ ብቻ የምትወስኚው ውሳኔ እድሜሽን ሁሉ የሚያበላሽ ነገር ይዞ እንዳይመጣብሽ መጠንቀቅ አለብሽ።
ነገሩን በጥንቃቄ፣ በጥበብ፣ በትዕግሥት ያዥው። ይህ ሁሉ ያልፋል። በተረፈ በውስጥ ብታወሪኝ ደግሞ መልካም ነው።
