Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union
رفتن به کانال در Telegram
This is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.
نمایش بیشتر4 434
مشترکین
-124 ساعت
-157 روز
-8430 روز
آرشیو پست ها
ለሙስሊሙ
ከዘመናዊ ትምህርት ወደ ኋላ መቅረት
3ት መሠረታዊ ችግሮቻችን
1ኛ) ማህብረሰባችን ለትምህርት ያለው ግንዛቤ በጣም የወረደ ነው
2ኛ) የእኛ ተማሪዎች ከታች እስከ ላይ አያነቡም
3ኛ) የእንግሊዘኛ ቋንቋ እጥረት
እነዚህ 3ት ችግሮች ህዝበ ሙስሊሙ ከትምህርት ወደ ኋላ የቀረባቸው መሠረታዊ ምክነያቶች ናቸው ።
== የእኛ ተማሪዎች ከታች እስከ ላይ አያነቡም
የሙስሊም ተማሪዎች ትምህርት ምን ያደርጋል ፣ ምን ይጠቅመናል በሚል እሳቤ የተሞሉ ስለሆነ ትምህረት ቤት ደርሶ መመለስ እንጂ ስራዬ ብሎ አያጠናም አንድ ተማሪ ካላጠና በትምህረቱ ውጤታማ አይሆንም Entrance exam ወዘተ ፈተናዎችን ይወድቃሉ ለኡማው አለኝታ መሆን ሲገባቸው በሱስቦታ ፣ በፊልም ፣ በድራማ የተጠመደ ትውልድ እየፈጠርን ነው ። ለዚህ ደግሞ እንደ ዋነኛ ምክነያት ሊሆን የሚችለው ዲኑን አውቆ ፣ ለምን እንደሚማር አውቆ ጠንክሮ በመማር ፋንታ ችላ ብሎ ከማጥናት መዘናጋቱ ነው ። ስለዚህ ሁላችንም ያለነን ሀላፊነት በመጠቀም ( ኢማም የሆነው እንደ ኢማምነቱ ፣ አስተዳደር የሆነው እንደ አስተዳደርነቱ ፣ አባት እንደ አባትነቱ ወዘተ ) ሙስሊሙ ተማሪ በደንብ እንዲያነብ ማድረግ ላይ መሰራት አለብን ።
ሙስሊም ተማሪዎች ት/ት ቤት ደርሶ መመለስ ሳይሆን በደንብ አምብበው ለኡማው የሆነችን ቀዳዳ እንዲዘጉ ማድረግ ሁላችንም ከጫፍ ማድረስ ያለብን ተልዕኳችን መሆን አለበት
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ሊታወቅ የሚገባው- ሴኩላሪዝም!
ዘውዳዊው ስርዓት የመንግስትን ስራ በቤተ- ክህነት የበላይ ጠባቂነት እየሰራ "የክርስቲያን ደሴት!" ትርክትን በሚነዛበት ወቅት ሀገር ሴኩላር ትሆን ዘንድ ከማንም በፊት ከማንም በላይ የለፋው የደከመው የየዚያኔው ሙስሊም ማህበረሠብ ነው:: የዚያኔ ሲታገሉም ሆነ ዛሬ በሕገ- መንግስቱ አንቀፅ (11) ሴኩላሪዝም የሚለው መሠረታዊ መርሆ "መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም:: ሀይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም::" የሚል ነው::
በዚህም መሠረት ሃይማኖቶች በመንግስት ተቋማት ውስጥ ጣልቃ የመግባል መብትም ሆነ ስልጣን የላቸውም :: ለምሳሌ ሙስሊሞች በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ "ሁሉም ተማሪ እስልምናን ካልተቀበለ መማር አይችልም: ሁሉም ተማሪ ሶላት ካልሰገደ ከግቢ እንዳይገባ: ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጀምሮ ሁሉም ሴት ተማሪዎች እና ሰራተኞች ኒቃብ ካለበሱ መማር አይችሉም!" ማለትን አይችሉም:: ምክንያቱም ዩኒቨርሲቲዎች የመንግስት ተቋማት እስከመሆናቸው ድረስ ጣልቃ ሊገባባቸው ስለማይችል::
ልክ እንደዚሁ በተመሳሳይ ዩኒቨርሲቲዎች በውስጥ ያለውን ማህበረሠብ "በእኛ እሳቤ ልክ ካልተሰፋችሁ አትማሩም:: ደስ የሚለንን ልብስ ልበሱ:: ደስ እንደሚለን ሁኑ::" በማለት የራሳቸውንም ሆነ የባዕዳንን እምነት እና ፍልስፍና የመጫን መብትም ሆነ ስልጣን የላቸውም:: ኤቴይስትነትንም ሆነ ሌላ የምዕራቡ አለምንና የኢስራኤልን ድቅል እሴት በተማሪው ላይ የሚጭኑበት መንገድ አይኖርም:: ምክንያቱም ሴኩላሪዝም ማለት እምነትየለሽነት ወይንም የአይሁዶችን መገለጫ ከምዕራቡ አለም ጋር ደቅሎ ማቅረብ አይደለምና::
ይህንን ደግሞ እንኳን በቢላሉል- ሐበሽ ልጆች ላይ አይደለም አውሮፓ እንኳ ማስፈፀም አልቻሉም:: ይህንን እንኳን በኡሙ አይመን ልጆች ላይ አይደለም በራሳቸው አጥር በራሳቸው ገንዘብ በሰሩት ከባቢ ውስጥ መተግበር አይችሉም:: ይህንን እንኳን በሀገራችን በገንዘባችን በተገነባ ተቋም ውስጥ አይደለም በባዕድ ሀገር እንኳ ቢሆን እንታገለዋለን:: በፍፁም የመከባበርን እሴት እንዲንዱ አንፈቅድም:: መራቆት የእነርሱ እምነትየለሽ መገለጫ ከሆነ መሸፋፈን የእኛ የእስልምና ተከታዮች መገለጫ ነው::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት
በ 2017ዓ.ል አዲስ ገቢ ሙስሊም ተማሪዎች ምንም አይነት ችግር እንዳይደርስባቸው እንደ አባትና እናት ሆነው የሚቀበሉ የጀመዓ አሚሮች ስልክ ቁጥር ከዚህ በታች አስቀምጦላችኋል ።
ማሳሰቢያ ፡ አሚሮቹን የተኛውንም አይነት ጥያቄ መጠየቅ ትችላላችሁ
1# አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
📌 AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252
Main and FBE Campus
📌 ኢስማዒል አብዱሮ - Main campus - 0936906322
📌 አብዱረሂም አሚን - FBE Campus - 0995477358
AAiT (5 Kilo) Campus
📌 ማህፉዝ ነጋሽ - AAIT - 0996220264
4 Kilo Campus
📌 ዘይድ ሳዲቅ - 4kilo - +251992546811
📌 መስዑድ ውበቱ - 4kilo - +251905877461
Sefere Selam Campus
📌 ሙሐመድአሚን - s.selam campus - 0917046439
📌 ኑር አወል - s.selam campus - ++251951044287
Ldeta Campus
📌ያህያ አባ ረሻድ - Ldeta Campus - 0965435476 or 0777435476
📌 አብዱልዓዚዝ ሙሄ - Ldeta Campus - 0909534342 or 0777534342
2 # ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ
A) Abdulhakim = 0920129706
B) Abbaas = 0919764876
3# ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ
ለአማርኛ ተናጋሪዎች
A. አልፈሪድ ጀሚል 0916680333
B. አደም ሲኖር 0988869967
C. ሰዐድ 0940000476
ለኦሮምኛ ተናጋሪዎች
A. አህመድ 0933490816
ለደቡብ ቋንቋ ተናጋሪዎች
A. ሙከረም +251994309746
B. ሰአድ +251940000476
ለቤንሻንጉል ቋንቋ ተናጋሪዎች
A. ፉአድ 0920306585
B. ዩሱፍ 0915181415
ለአፋርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች
A. ሙሀመድ 0906723054
ለቡሬ ካምፖስ
A. ቶፊቅ 0923285140
B. አብዱሰላም 0989914191
4# መቱ ዩኒቨርስቲ
Mattu Main Campus
1 አጅመል ነጂብ 0943595705
2 ሙጃሂድ ነፍሶ 0967017401
Mattu University Bedele Campus
1 አማን ቱላ 0916332852
2 ሙክታር ጀማል 0923621116
5# ሰላሌ ዩኒቨርስቲ
A) ማህዲ ቡሴይሪ = 0917395959
B) ሙስጠፋ አብዲ = 0918298649
6# መቅደል አምባ ዩኒቨርሲቲ
A) ኑረዲን ናስር = 0970444169
B) ሳቢት = 0972222769
C) ኢብራሂም = 0938554692
7# ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ
A) Ahmedin salim = +251902837001
B.samir A/semad 0963244320
C.Fuad husen 0967713010
D.Ali Tekaling 0916774673
@wkumuslimsbot
8# ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ
A) ALFERID TALEGIN 0955033686
B) JEMAL AHMED 0909282436
C) NUREDIN ABDELA 0986855753
D) FUAD KHEDIR 0910585267
E) FURKAN JEMIL 0968278025
9# ጂማ ዩኒቨርስቲ
Main CAMPUS
A) Abdulselam Redwan =0949446651
B) Sudeis Abdurahman= 0954716238
C) Selahadin mustefa = 0901602827
Kito CAMPUS
A) Abdulaziz 0973370337
B) Zubeir 0966794078
C )Qasim +251945948764
Agri campus
A) Abdulkerim korma =0939403349
B) ABDULHAFIZ OUMER =0902920175
C) FAANOOS SANO=0939875930.
Beko CAMPUS
A) Ayub= +251925538127
B) Munir = 092 121 8490
C) Umer- 096 631 9047
10# ኢንጂባራ ዩኒቨርስቲ
A)Hamza Zeben. 0930998579 Amir
B)Nuradin lema 0977974191. M/Amir
C)Suleyman meksud 0934352155
D)Adil Nasir. 0953080736
E) Muhammed Teshome 0903030397
ይቀጥላል ......................👇👇👇
https://t.me/EHEMSU
ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ሙስሊም እህት ወንድሞቻችን:-
በመጀመሪያ የአላህ ሰላም እዝነት እና ረድዔት በእናንተ ላይ ይሁን :: ምስጋና ሁሉ ሁሉንም ችግር አልፋችሁ በውጤት ለእዚህ ስኬት እንድትበቁ ላስቻለው ጌታችን አላህ የተገባ ይሁን :: እንደ አንድ ሰውነት ሆነን እንድንደጋገፍ እና እንድንረዳዳ ባስተማሩን አዛኙ ነብይ ላይም የአላህ ውዳሴ እና ሰላም ይስፈን ::
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ሙስሊም እህት ወንድሞቹን በኢስላማዊ ፍቅር እና እንክብካቤ አቅፎ ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቋል :: ስለሆነም እናንተ እህት ወንድሞቻችን ከምንም በላይ ከደም በላይ የሚያጋምደንን የኢስላም እህት ወንድማማችነት በማሰብ ማንኛውም የምትፈልጉትን መረጃ እና እገዛ በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች በኩል ትጠይቁ ዘንድ እንጠይቃለን ::
📌 AAU MUSLIM STUDENTS UNION - 0909524252
Main and FBE Campus
📌 ኢስማዒል አብዱሮ - Main campus - 0936906322
📌 አብዱረሂም አሚን - FBE Campus - 0995477358
AAiT (5 Kilo) Campus
📌 ማህፉዝ ነጋሽ - AAIT - 0996220264
4 Kilo Campus
📌 ዘይድ ሳዲቅ - 4kilo - +251992546811
📌 መስዑድ ውበቱ - 4kilo - +251905877461
Sefere Selam Campus
📌 ሙሐመድአሚን - s.selam campus - 0917046439
📌 ኑር አወል - s.selam campus - ++251951044287
Ldeta Campus
📌ያህያ አባ ረሻድ - Ldeta Campus - 0965435476 or 0777435476
📌 አብዱልዓዚዝ ሙሄ - Ldeta Campus - 0909534342 or 0777534342
AAU Muslim Students' Union
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ኢቅረዕ ከሚለው መለኮታዊ ትዕዛዝ የተወለደው ዩኒቨርሲቲ!
አዕምሮን አሠልጥኖ: ሀሳቦችን ጠፍጥፎ ከሀልዮት ባሻገር በግብር የሚገለፁ አብዮቶችንና ስልጣኔዎችን በመፈብረክ ለዓለም የፈለገውን ቅርፅ የሚሰጠው ታላቁ የልሕቀት ማዕከል ከዘመናት በፊት ፋጡማ ፊህር ከምትባል ሞሮካዊ ማህፀን ነበር የተወለደው:: "ኢቅረዕ- አንብብ!" በሚለው መለኮታዊ ትዕዛዝ ውስጥ ያደገችው ፋጡማ ቀረዊዩን ዩኒቨርሲቲን ለዓለም አስተዋወቀች:: ይህም "ኢቅረዕ- አንብብ!" በሚል ቋሚ ምሶሶ ላይ የተገነባው መካነ- አዕምሮ ብዙ አሳቢያንና ሀያሲያንን በመፈብረክ የዓለምን ስርዓት ይዘውር ጀመር::
ይህንንም በመከተል በቱኒዚያ ኢዚቶና ዩኒቨርሲቲ (በአንዳንድ ፅሁፎች ኢዚቶና እንደሚቀድም ተቀምጧል): በግብፅ አል- አዝሐር ዩኒቨርሲቲ ተመሰረቱ:: እነዚህም ዩኒቨርሲቲዎች የአለም ስልጣኔ አስኳል ሆነው ዘለቁ:: በመጨረሻም በእነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች scholarship አግኝተው የተማሩና የተመራመሩ የምዕራቡ አለም ሰዎች በ11ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ ላይ ቦሎኛ ዩኒቨርሲቲን በጣልያን: ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲን ደግሞ በእንግሊዝ አቋቋሙ::
ከዚያም ቡሃላ ሙስሊሞች በመለኮታዊ ትዕዛዝ ሰርተውት የነበረውን ማዕከል እነርሱ በስራ ሰሩት:: ሙስሊሞች ከመለካታዊው ትዕዛዝ እየሸሹ እውቀትና ንባብን ሲዘነጉ: እነርሱ ደግሞ ከመለኮታዊ ትዕዛዛቸው እየሸሹ እውቀትና ንባብን ይይዙ ጀመር:: በስተመጨረሻም በእነዚህ የልህቀት ማዕከሎች ውስጥ የተቀመጡ የእውቀት ጡቦች ፍሬ አፍርተው አብዮቶችን አቀጣጠሉ:: ከእንግሊዝ እስከ ሩሲያ: ከፈረንሳይ እስከ ጀርመን የተለያዩ ለውጦች ተካሄዱ:: ያም ሁኔታ ዛሬ ያለንበትን ተጨባጭ ፈጠረ::
እነሆ ዛሬ የሙስሊሙ አለም ፀንሶ የወለደው ያሳደገው ዩኒቨርሲቲ የሚባል ማዕከል አድጎና ጎልምሶ የእናት ጡት ነካሽ ሆኗል:: ሆኖም ሊወቀስ የሚገባ ካለ እኛው ራሳችን ነን::
የተውነውን ትላንት ዛሬ እንኑረው!
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
"እስላም ለመንግስት ግብር ይከፍላል እንጅ እንዴት መንግስትን ቀለብ ይከፈለን ብሎ ይጠይቃል?" - በ1949 በግብፅ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት አቶ ደመቀ
ሙስሊም ስለሆኑ ብቻ የትምህርት እድል በመነፈጋቸው እነ ሐጂ በሽር ዳውድ: ሸህ ዐብዱል ሀዲ: ዐብዱልከሪም ዩሱፍ እንዲሁም ሌሎች ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሀገራቸው የተነፈጉትን በሱዳን በርሃ አቆርጠው ከግብፅ አዝሃር ዩኒቨርሲቲ አገኙ:: ሆኖም ፓስፖርት የላቸውም:: ድጋፍም የሚያደርግላቸው አልነበረም:: ለክርስቲያኑ ተማሪዎች መንግስት ፓስፖርትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ያደርግ ስለነበር "እንደሌሎች ተማሪዎች እኛም መብት ይኑረን!" የሚል ጥያቄን ይዘው ግብፅ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አመሩ::
በወቅቱ የኤምባሲው ጉዳይ አስፈፃሚ የነበረው አቶ ደመቀ ተማሪዎቹን ከእግራቸው እስከ አናታቸው በአርምሞ እየተመለከተ ፊቱን ጥቁር ጭምድድ አድርጎ ሁለት እጆቹን ከሁሉት ጆሮዎቹ እየጠቀጠቀ "ግሩም! ግሩም! ጆሮ የማይሰማው የለም! እስላም ለመንግስት ግብር ይከፍላል እንጅ እንዴት መንግስትን ቀለብ ይክፈለን ብሎ ይጠይቃል?" አለና የቢሮውን ዘበኛ በደወል ጠርቶ "እባክህ እነዚህን ምንነታቸው ያልታወቀ ፍጡሮች በቶሎ አስወጣልኝ!" አለው::
ተማሪዎቹ ተቆጥተው ወደ ዩኒቨርሲቲው ተመለሱ:: ጉዳዩንም ወደሚዲያ በማውጣት አለምአቀፍ አጀንዳ አደረጉት:: የአፄ ሀ/ስላሴ መንግስትም ውጥረቱን ለማርገብ ብሎ አቶ ደመቀን ከቦታው አንስቶ ፊታውራሪ ታፈሰን ዋና አምባሳደር አድርጎ ላከ:: ተማሪዎቹም ጥያቄያቸውን ምንም ሳይሸማቀቁ ወገባቸውን ቀጥ አድርገው መሬት ሳይስሙ ለፊታውራሪ ታፈሰ አቀረቡ:: ፊታውራሪ ታፈሰም ዘበኛውን ጠርቶ "እኔኮ በኢትዮጵያ ዘውድ መጫን እንጅ ሌላ ስልጣን ምንም አልቀረኝም:: ታዲያ እነዚህ ምንነታቸው ያልታወቁ እስላሞች መሬት ሳይስሙ በድፍረት እንዴት ያነጋግሩኛል?" በማለት "አስወጣልኝ!" አለው:: ቀጠል አድርጎም "ስለጥያቄያችሁ ከአስር ቀን ቡሃላ እዚያው ባላችሁበት እንድታውቁ ይደረጋል:: እዚህ ግን እንዳትመጡ!" አለ::
ሆኖም ተማሪዎቹ የተባሉትን ለሌሎች ተማሪዎች ተናግረው ቁጥራቸውን መቶ ገደማ በማድረስ ተመልሰው መጡ:: የሶላት ሰዓት ደርሶ ነበርና እዚያው በኤምባሲው ሳሎን ሶላት እየሰገዱ አምባሳደሩን ይጠብቁት ጀመር:: አምባሳደሩም እየሰገዱ ሲያያቸው ደንገጥ ብሎ እየተንቀጠቀጠ "እናንተ ልጆች ስሙ! አሁን በፖሊስ ባስይዛችሁ የግብጽ ፖሊሶች መጥፎዎች ናቸው:: የአገራችንን ስም ያጠፋሉ:: ••• የአስር ቀን ጊዜ ስጡኝ:: ጃንሆይን በቴሌግራም ልጠይቅ:: ስጥ ካሉኝ እሰጣችሗለሁ:: አሁን እባካችሁ ውጡልኝ::" አለ:: እነሱም ወጡለት:: በማግስቱም "የረከሰውን ለማጥራት!" በሚል በግብፅ የነበሩትን ኢትዮጵያውያን ቀሳውስት ጠርተው ፀበል ረጩ:: እጣንም አጨሱ::
10ኛው ቀን ደርሶ ሄዱ:: ፊታውራሪ ታፈሰ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቶ ፀሐፊውን ላከ:: በዚህ ከተናደዱት ሙስሊም ተማሪዎች መካከል ኡስታዝ ዓሊ ሀይደር በጥፊ አጮሉት:: ሁከት ተፈጠረ:: የግብፅ ፖሊሶች ተጠርተው መጥተው "ውጡ!" አሉ:: ተማሪዎች "አንወጣም!" አሉ:: በመጨረሻም ፖሊሶቹ አግባብተው አስወጧቸው:: ተማሪዎቹም "ሀይለስላሴ ከእነአጫፋሪዎቹ ይውደም!" እያሉ ሄዱ::
ከዚያም ቡሃላ አምባሳደሩ "5ቱ አስተባባሪዎች ተይዘው ወደ ኢትዮጵያ ይላኩልኝ!" አለ:: ፖሊስም ከአዝሃር ሄደው ሊይዙ ሲሉ የአዝሐር ዩኒቨርሲቲ የውጭ ጉዳይ የነበሩት ሸህ አብዱልሐሚድ "ፖስፓርትና ቀለብ አልሰጥም ካለ ኢትዮጵያዊ አይደሉም ማለት ነው:: ኢትዮጵያዊ ካልሆኑ ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ ይወሰዱልኝ ማለት አይችልም:: አዝሐር ሁሉን ችሎ ያስተምራቸዋል:: አዝሐር እንደ ቫቲካን ነው:: ማንም ሊነካቸው አይችልም::" በማለት በቁጣ ተናገሩ:: የዚህን ጊዜ ፖሊስ ቃላቸውን ተቀብሎ ሊለቃቸው "ወንጀለኛ ናችሁ?" ብሎ ጠይቆ አይደለንም እያሉ በሚመልሱበት ሰዓት ሐጂ በሽር ዳውድ "እኔ ወንጀለኛ ነኝ!" አሉ:: ሁሉም ደንግጠው "ምንድን ነው ወንጀልህ?" አሏቸው:: እሳቸውም "ወንጀሌማ ሀ/ስላሴና አጫፋሪዎቹ ትልቅ ሀጢያት ነው የሚሉት ነው- ሙስሊም መሆኔ!" ሲሉ መለሱ:: በቤቱ ውስጥ የነበሩት ሁሉ አለቀሱ:: ሐጂ በሽርንም እቅፍ አድርገው "በአላህ እንምላለን! ወንጀለኛው ሀ/ስላሴ እንጂ አንተ አይደለህም::" ሲሉ አፅናኑት::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምንም እንኳ ሙስሊም በዝ በሆነ አካባቢ የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች በሕገ- መንግስቱ የተደነገገላቸውን የሃይማኖት ነፃነት መብትን ሴኩላሪዝምን በመፃረር እንዳይከውኑ ያደርጋል:: ሃይማኖቶቻው ልበሱ ብሎ ያዘዛቸውን ኒቃብ አትለብሱም ብሎ ይከለክላል::
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ እምብርት ላይ የሚገኝ ብሎም የሀገሪቱ መለያ በመሆን የሚታወቅ ዩኒቨርሲቲ ቢሆንም በቅርቡ በጀመረው የተቋም ማሻሻያ ውስጥ አዲስ ባወጣው መመሪያ በሕገ- መንግስቱ የተደነገጉትን የሃይማኖት ነፃነት መብትና ሴኩላሪዝምን በመፃረር የሙስሊም ተማሪዎችን መሠረታዊ መብት ተጋፍቷል::
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሀገራችን ቀደምት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን እስካሁን ባለው ሁኔታ በየትኛውም የሙስሊም ተማሪዎች መብት ጣልቃ አይገባም::
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከቀደምት የሙስሊም ሱልጣኔቶች መገኛ በሆነችው በታሪካዊቷ የጅማ አባጅፋር መናገሻ ጅማ ከተማ የሚገኝ ቢሆንም አባጅፋር ተወልደው ባረፉበት ሀገር የአባጅፋር ልጆችን ሕገ- መንግስታዊ መብት ይጋፋል:: ሃይማኖታቸው ያዘዛቸውን ኒቃብ መልበስን ይከለክላል:: ሙስሊም በዝ በሆኑ አካባቢዎች እንደ ባህላዊ ልብስ የሚቆጠሩትን እንደ አማኢማና ሙደወር አይነት ልብሶች ተለብሰው ወደዩኒቨርሲቲው መገባታቸውን ይከለክላል::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
📌 የኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ባወጣው አዲስ መመሪያ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ሙሉ ለሙሉ እንደማያከብር አሳውቋል:: በመመሪያው ላይ እንደተቀመጠው ሙስሊም ተማሪዎች በሕገ- መንግስቱ የተጠቀሰውን የሃይማኖት ነፃነት እና የሴኩላሪዝም መብት ተከትለው ከዩኒቨርሲቲው ጣልቃ ገብነት በመራቅ የሃይማኖት ነፃነት መብታቸውን መተግበር እንደማይችሉ ነው::
📌 የሲዖል ዩኒቨርሲቲ የሙስሊሙ ቁጥር የሀገሪቱን 0.00381 ፐርሰንት በሆነባት ደቡብ ኮሪያ ዋና ከተማ ሲዖል የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊሞች በሀገሪቱ ውስጥ ህዳጣን ናቸው ብሎ እንኳ መብታቸውን ለመግፈፍ ሙከራ ከማድረግ ይልቅ መብታቸውን አክብሮ ያስተምራል:: ተማሪዎች ኒቃብን ጨምሮ ማንኛውም አይነትን ልብስ ይለብሳሉ:: ተማሪዎች የሶላት ሰዓት ሲደርስ ሌሎችንም ሆነ ራሳቸውን ሳያስቸግሩ በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የመስገጃ ስፍራ (Prayer room) አዘጋጅቶ ሃይማኖታቸውን በነፃነት እንዲተገብሩ ያደርጋል::
📌 ኬፕ ታውን ዩኒቨርሲቲ በምዕራቦቹ አፓርታይድ ስር ለዘመናት በተጨቆኑትና ከጭቆና ቡሃላ በየትኛውም የነፃነት ጉዳይ በማይደራደሩት ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ ነው:: በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙት ሙስሊም ብዛታቸው የሀገሪቱን 1.7 ፐርሰንት ያክሉን ሲሆን የሃገሪቱን ሙስሊም ማህበረሰብ ህዳጣን ናቸው ብሎ በየትኛውም ሁኔታ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ለመጨቆን አይሞክርም:: ተማሪዎች ከኒቃብ ጀምሮ የትኛውንም አለባበስ በነፃነት ይለብሳሉ:: ከሶላት ጋር ተያይዞ የሚሰግዱበትን ቦታ የተለየ የመስገጃ ቦታ (Prayer Room) አዘጋጅቶ እንዲሰግዱ ያስችላል::
📌 ማንችስተር ዩኒቨርሲቲ ከሴኩላሪዝም ጀምሮ የተለያዩ የዲሞክራሲ መብቶችን አስጠብቃለሁ ብላ በምትሞግተውና የሙስሊሟ ቁጥርም 6.5 ፐርሰንት በሆነባት ሀገረ እንግሊዝ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ነው:: ሆኖም ሙስሊሞችን ህዳጣን ናቸው ብለው ለመጨቆን ለመሞከር ሳይሞክሩ በሴኩላሪዝምና በሃይማኖት ነፃነት መብት ላይ ተመርኩዘው ከኒቃብ ጀምሮ የፈለጉትን እንዲለብሱ ከማድረግ ጀምሮ በዩኒቨርሲቲያቸው ውስጥ የመስገጃ ቦታ በማዘጋጀት እንዲሰግዱ ያደርጋሉ::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምንም እንኳ ሙስሊም በዝ በሆነ አካባቢ የሚገኝ ቢሆንም ሙስሊም ተማሪዎች በሕገ- መንግስቱ የተደነገገላቸውን የሃይማኖት ነፃነት መብትን ሴኩላሪዝምን በመፃረር እንዳይከውኑ ያደርጋል:: ሃይማኖቶቻው ልበሱ ብሎ ያዘዛቸውን ኒቃብ አትለብሱም ብሎ ይከለክላል::
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሀገሪቱ እምብርት ላይ የሚገኝ ብሎም የሀገሪቱ መለያ በመሆን የሚታወቅ ዩኒቨርሲቲ ቢሆንም በቅርቡ በጀመረው የተቋም ማሻሻያ ውስጥ አዲስ ባወጣው መመሪያ በሕገ- መንግስቱ የተደነገጉትን የሃይማኖት ነፃነት መብትና ሴኩላሪዝምን በመፃረር የሙስሊም ተማሪዎችን መሠረታዊ መብት ተጋፍቷል::
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ከሀገራችን ቀደምት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ሲሆን እስካሁን ባለው ሁኔታ በየትኛውም የሙስሊም ተማሪዎች መብት ጣልቃ አይገባም::
ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከቀደምት የሙስሊም ሱልጣኔቶች መገኛ በሆነችው በታሪካዊቷ የጅማ አባጅፋር መናገሻ ጅማ ከተማ የሚገኝ ቢሆንም አባጅፋር ተወልደው ባረፉበት ሀገር የአባጅፋር ልጆችን ሕገ- መንግስታዊ መብት ይጋፋል:: ሃይማኖታቸው ያዘዛቸውን ኒቃብ መልበስን ይከለክላል:: ሙስሊም በዝ በሆኑ አካባቢዎች እንደ ባህላዊ ልብስ የሚቆጠሩትን እንደ አማኢማና ሙደወር አይነት ልብሶች ተለብሰው ወደዩኒቨርሲቲው መገባታቸውን ይከለክላል::
📌 የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ በፊት ከነበረው የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ እውነታ በሚፃረር መልኩ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚፃረር መመሪያ በነሐሴ 2016 ዓ.ል እንዳወጣ የቅርብ ትዝታ ነው::
አዲሱ መመሪያ በአንቀፅ 6 (6) ላይ "ከደህንነት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ማንነትን ለመለየት ሲባልና ከፀጥታ ጋር በተገናኘ ምክንያት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ፊትን በመሸፈን ማንነትን ለመለየት አዳጋች የሚያደርጉ አለባበሶችን መልበስ አይፈቀድም::" በማለት በየትኛውም የሰለጠነው አለም ክፍል ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ሀይማኖታቸው አዟቸው የሚለብሱትን ኒቃብ የደህንነት ስጋት በማለት እምነቱን ዝቅ ለማድረግ በሚመስል መልኩ በተዘዋዋሪ ይከለክላል::
ከዚህ በመቀጠል አንቀፅ 7(2) "ማንኛውም ተማሪ በግሉ የፈለገውን ሃይማኖት የመከተል መብት አለው:: በማንኛውም ቦታ በግሉ የሌላውን ሰው እምነት: ስሜት: ፀጥታ: ወዘተ... በማያውክ ሁኔታ የግሉን ፀሎት ማድረግ ይችላል:: ይህ ግን በመጮህና የሌላውን ሰው ነፃነትና ፀጥታ በሚነካ መልኩ መሆን የለበትም::" በማለት የጀመዓ ሶላትን ብሎም በግል የሚሰገድን የጀህር ሶላት በይፋ ከመከልከል ባሻገር ተማሪዎች ሕገ- መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም በሌሎች ሀገራት ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚተገበረው የብቻ የመስገጃ ቦታ እንዳይጠይቁ ሲባል በመመሪያው አንቀፅ 7(2) ላይ "በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአገራችንን ሕገ- መንግስታዊ ድንጋጌ በመከተል የተለየ የአምልኮ ቦታ መጠየቅ: መስራትም ሆነ የተወሰነ ህንፃ ወይም ዶርም ለአምልኮ/ ሃይማኖታዊ ስብሰባ መጠቀምም ሆነ በቡድን ተሰባስቦ ሃይማኖታዊ ስርዓት ማካሄድ የተከለከለ ነው::" ሲል ይደነግጋል::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ጭቆናም ሆነ ትግል አዲስ አይደሉም!
በአለም ላይ ያለ ትግል የተወገደ ጭቆና የለም:: በአለም ላይ ያለ መስዋዕትነት የተገኘ ነፃነት የለም:: በአለም ላይ ያለ ትብብር የመጣ እኩልነት የለም::
ዛሬ ላይ በዩኒቨርሲቲዎቻቸው ውስጥ ኒቃቢስቶችን በእኩልነት የሚያስተምሩት ብሎም ለሙስሊሞች መስገጃ ቦታ አዘጋጅተው የሚያስተናግዱት የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲዎች በአንድ ወቅት ሀይማኖትን የሚጨቁኑ ነበሩ:: በአንድ ወቅት ተማሪዎች ጥቁር ስለሆኑ እንዳይማሩ ይከለከሉ ነበር:: በአንድ ወቅት ተማሪዎች ከሃይማኖት እንዲርቁ ይገደዱ ነበር:: ለዚህ ሲባል ት/ቤቶች ለ2/3 አመታት ተዘግተዋል:: ለዚህ ሲባል ተማሪዎች ተባርረዋል:: ግን ታገሉ:: በዚያም ምክንያት ዛሬ ላይ ሞዴሎች ሆኑ::
እዚሁ አፍሪካ ሀገረ ታንዛኒያ ከ19 አመታት በፊት የነበረችበትን ሁኔታ ማዬት እንችላለን:: እንኳን ኒቃብ ሻሽ እንኳ ከፀጉር ላይ ጣል አድርጎ መማር አይቻልም ነበር:: ሶላትማ ፈፅሞ አይታሰብም:: ግን ታገሉ:: ህፃናት ላይ ጥይት ተደግኖባቸው ሳለ ታገሉ:: አሸነፉም:: ያ ድል ዛሬ ላይ ሒጃቢስቷ ማማ ሳሚያ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት እንድትሆን አስችሏታል:: ያ ድል ዛሬ ላይ ለተማሪዎች የሶላት ሰዓት ሲደርስ ት/ት እንዲቆም ማድረግ ችሏል::
በሌሎች ሀገራቶችም በተመሳሳይ ዛሬ የምንቀናባቸው ለውጦች የመጡት ባደረጉት እልህ አስጨራሽ ትግል ነው:: በእኛም ሀገር ዛሬ ላይ የምናየው ከትላንት የተሻለ ሁኔታ ያለ ቀደምቶቻችን ትግል እና መስዋዕትነት አልመጣም:: ለዚህ ሲባል ብዙዎች እናት ሀገራቸውን ጥለው ሄደዋል:: ለዚህ ሲባል ብዙዎች ህይዎታቸው ጠፍቷል:: ለዚህ ሲባል ብዙዎች ለእስር ተዳርገዋል:: ለዚህ ሲባል ብዙዎች ከትምህርት ተባርረዋል:: ለዚህ ሲባል ብዙዎች ውድ ጊዜያቸውንና አዕምሯቸውን ከፍለዋል::
ዛሬም ከትላንት አይለይም:: ዛሬም ለውጥ ይመጣ ዘንድ ከጥበብ የተዋሃደ ትግል ያስፈልጋል:: ዛሬም ለነፃነት ሲባል የሚሰጥ ጊዜና ሀሳብ ያስፈልጋል:: ዛሬም ለእኩልነት ሲባል የሚከፈል መናበብና መተጋገዝ ያስፈልጋል:: ካልሆነ ግን የአባቶቻችንን አደራ የበላን ከንቱዎች: የዛሬውን ሀላፊነት የዘነጋን ደካሞች ብሎም የነገን አማና ከቦታው ያላደረስን ተዋቃሾች እንሆናለን:: አላህም ይጠይቀናል!
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ኒቃብ ለብሰው መማርን ከለከለ!
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጀመረው የለውጥ ሂደት ውስጥ ከዚህ በፊት ለአመታት ኒቃብ ለብሰው ሲማሩ የነበሩ ተማሪዎችን ከእንግዲህ ቡሃላ ለብሳችሁ እንዳትገቡ ሲል አሳውቋል:: ካፌም ላይ ኒቃቢስቶች አገልግሎት እንደማያገኙ ገልፇል:: ከዚህም በተጨማሪ ሰሞኑን የቅድመ ምረቃ መግቢያ ፈተናን ለመውሰድ የተመዘገቡ ኒቃቢስቶች በር ላይ ከፍተኛ እንግልት እንደደረሰባቸውና ከፈተናም እንደተስተጓጎሉ ገልፀዋል::
እንደ አጠቃላይ ዩኒቨርሲቲው በተለያየ መልኩ የሙስሊም ተማሪዎችን የነፃነት መብት የሚገድቡ የተለያዩ መመሪያዎችን አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ነው::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
የተማሪ ነፍስ ከበድ ትላለች:: ትምህርቷን ከዲኗ እንድታቆራኝ ስትጠዬቅ "አቦ ተውን! እኔ አሁን ተማሪ ነኝ! ትምህርቴን ልማርበት! ለዲኑ ቀስ ተብሎ ይደረስበታል!" ትላለች:: ትምህርትንና ዲንና አቆራኝታ እንድትይዝ ተጠይቃ ለዚያ ደግሞ አላስፈላጊ የሆነው ቦታ ላይ የምታባክነውን ሰዓት ወደዚህ ማምጣቷ በቂ እንደሆነ ስትነገር "ምንም እንኳ ተማሪ ብሆን ወጣት ነኝ! አለሜን ልቅጭበት! ለዲን ቀስ ተብሎ ይደረሳል::" ትላለች::
ኧረ ተው አለምን እንቅጭ ስትይ አለምሽ እየተቀጨ ነው ተብላ እንድትስተካከል ዳግም ሲነገራት ጥፋቷን እንደማመን ትልና "ግን እኮ ለተውበቱ ይደረስበታል:: አሁን የወጣትነት ዘመን ስለሆነ ዲግሪና ብር መሠብሠቢያ ነው::" ትላለች:: እሺ ይሁን ግን ቢያንስ ሶላት ጀምሪ ስትባል "እኔ ቃልቻ መሠልኳችሁ እንዴ? ተው እንጂ!" ብላ ከጀመረቸው አዙሪት ውስጥ ሰተት ብላ ትገባለች:: ኧረ ተይ እሺ ሒጃብ ልበሺ ተብላ ስትጠየቅም በዚያው አዙሪት ላይ ሆና "ምን ማለታችሁ ነው? እኔ መችም አላህ እራሱ የሴትን ልጅ ሰውነት ውብ አድርጎ ፈጥሮ ሳለ እንዳይታይ ሸፍኝው የሚል አይመስለኝም::" የሚል ምክንያት ታቀርባለች::
ለሚቀርቡት የኸይር ጥሪዎች ሁሉ Made in satan & nafsya የሆኑ ማዘናጊያዎችን ታቀርባለች:: ግን እስከመች? በሰይጣን ማዘናጊያዎች እና ማታለያዎች ተወድሮ በተሰራ መረብ ውስጥ ሆና እስከመች? የተፈጠረችበትን ትክክለኛውን አላማ ረስታ እስከመች? ተይ ነፍሴ ተይ! ወዮልሽ ነፍሴ ተይ! አኼራን ዘንግተሽ ከዱንያ ጋር የሙጥኝ አትበይ:: ዘውታሪውን አለም ረስተሽ አላፊውን አለም ተይ:: ዱንያ ዘውታሪ ብትሆንኮ ለአንቺ ባልደረሰች ነበር:: ራስሽን መርምሪ:: ለራስሽ ስትይ ለዲንሽ ኑሪ:: ወኔ ይኑርሽ:: ለመቃብርሽ የሚሆን ስንቅ መሰነቅ ላይ በርቺ::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
"ወንዶቹ ልጆቼን በሚገባ አስተምሬያለሁ:: ሴቶቹ ግን አልተማሩም:: ምክንያቱም ኢስላም ተገላልጦ መማሩን ስለማይፈቅድ ነው::" (ሸኽ ኸሊፋ ዐብደላህ)
ሸኽ ኸሊፋ ይህንን ንግግር የተናገሩት በአፄ ሀ/ስላሴ ዘመነ መንግስት ቢሆንም እስካሁኗ ጊዜ ድረስ የብዙ ሙስሊም አባቶች እሮሮ ነው:: ከዚህ አረፍተ ነገር ተመሳሳይ የሆነ ነገር ሀሩን ሚዲያ ከሀገራዊ ምክክር ጋር ተያይዞ ባዘጋጀው ዝግጅት ላይ የቀረቡ አባት ሲናገሩ ሰምቻለሁ:: ሶስት ልጆቻቸው ኒቃብ እንዳይለብሱ ስለተከለከሉ ከትምህርት ገበታ እንደራቁባቸው አውስተዋል::
እስከ መች ይቀጥል ይሆን? መች ይሆን ማብቂያው? መች ይሆን መቋጫው? ይህንን የታሪክ እዳ ይህ ትውልድ የመዝጊያ ምዕራፍ ሊያዘጋጅለት ይገባል:: በአላህ ፈቃድ:: ከአላህ ጋር::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ሴኩላሪዝም !
ሙስሊም ተማሪዎችን ለማጥቃት ለዘመናት በመገልገያነት የዋለ የዳቦ ስም!
የመንግስት እና የሃይማኖት ጋብቻ በ1966ቱ አብዮት ፍቺ እንደሆነ ታሪካዊ እውነታ ነው:: ቤተ ክህነት ከቤተ መንግስት ጋር ቋጥራው የነበረው የ80 ጋብቻ አብዮቱን ተከትሎ በመጣው የእኩልነት ነፋስ ከስሟል:: ከዚያ በመለስ በ1983 ወደ ስልጣን የመጣው የኢሕአዴግ ስርዓት የሃይማኖት እኩልነትን ነፃነትንና ሴኩላሪዝምን በሕገ- መንግስቱ ውስጥ በመደንገግ የደርጉ መንግስት ጀምሮት የነበረውን በጎ ጅማሬ አጠናከረ:: በዚህም የኢትዮጵያ ሙስሊም ለዘመናት ሲታገልለት የነበረው አጀንዳ እልባት ያገኘ መስሎት እልል አለ::
ሆኖም ከዚያ ቡሃላ የነበረው ስርዓት ሲያወራ የነበረው የይስሙላ እኩልነት ነፃነትና ሴኩላሪዝምን ነበር:: ከወረቀት በዘለለ ለሙስሊም ማህበረሰብ በተግባር የደረሰው ምንም ትሩፋት አልነበረም:: መብቴን ያስጠብቅልኛል ብሎ ያሰበው የሴኩላሪዝም መርሕ ትርጓሜው ተለውጦ ማፈኛው ሆኑ:: ሕገ- መንግስት በአንቀፅ 11 ላይ በግልፅ እንዳስቀመጠው የሴኩላሪዝም ትርጓሜ "መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም:: ሃይማኖቶችም በመንግስት ጉዳዮች ጣልቃ አይገቡም::" የሚለው ከወረቀት ላይ ቀርቶ ሴኩላሪዝም በሚል የዳቦ ስም ሙስሊሞችን እምነት የለሽ ለማድረግ ብዙ እንቅስቃሴ ተደረገ:: ሃይማኖታዊ ቃላቶችን ከመተርጎም: አለባበስን ከመምረጥ አንስቶ በሶላት አሰጋገድ ዙሪያም ድንጋጌዎችን አወጣ::
ሆኖም ግን ይህ ከሴኩላሪዝም አልነበረም:: ሴኩላሪዝም መሠረቱን የመንግስት እና የሃይማኖትን መለያያት ማስፈን ሆኖ በአፈፃፀም ደረጃ ከሀገር ሀገር ቢለያይም ፈፅሞ ግን በሌሎች ሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ መግባትን አይፈቅድም:: ለአብነት አለማዊው አለም የዴሞክራሲ እና የሴኩላሪዝም ምሳሌ አድርጎ የሚያያትን አሜሪካ መመልከት እንችላለን:: የአሜሪካ ኮንግረስ እ.ኤ.አ በ1984 ያወጣው Equal Access Act (የእኩል ተጠቃሚነት ደንብ) በ2ኛ ደረጃ ት/ት ቤቶች እና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል ያሉ የተለያዩ ነጥቦችን በመዘርዘር የመንግስት ሴኩላር ኮሌጆች የእምነት ማካሄጃ ቦታዎችን እስከ ማመቻቸት ይፈቅዳል:: እንግዲህ ይህች ሀገር የሴኩላሪዝምን ፅንሰ -ሀሳብ ለዘመናት ተቀብላ አሳድጋ ለወግ ማዕረግ ያደረሰችው ሀገረ አሜሪካ ነች:: ግና እንኳንም ተማሪዎችን ከሃይማኖታዊ ተግባራት ማገድ ይቅርና የፀሎት ቦታዎችን እንዲገነቡ ፈቅዳላቸው በሰፊው እየተንቀሳቀሱ ነው::
በእኛ ሀገር ያለው ሁኔታ ግን አድሮ ቃሪያ ነው:: በዘንድሮው አመትም ልክ እንደ በፊቱ የሰላም ሚኒስቴር ይህንኑ ሴኩላሪዝም እንደ ዳቦ ስም በመጠቀም በትምህርት ተቋማት ውስጥ ከሙስሊም ተማሪዎች የአለባበስ እና የአሰጋገድ ሁኔታ ጋር ገደብ ለማስቀመጥ የሚጥር አዋጅ ለማውጣት ተንቀሳቅሶ በሙስሊሙ ትግል ከረቂቁ ላይ ሊፋቅ ችሏል:: ሆኖም ረቂቁ ትምህርት ሚኒስቴር ለሚያወጣው ዝርዝር መመሪያ ክፍት የሆነ በር ትቶ ያለፈ መሆኑ ሚኒስቴሩ አሁንም በሴኩላሪዝም ስም የሙስሊሞችን መብት ለማፈን የሚውል መመሪያ ያወጣ ይሆን ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል:: ያም ሆነ ይህ ግን መብታችንን ከእስከዛሬው በተሻለ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ሳይሸራረፍ የማስከበር ታሪካዊ ሀላፊነት አለብን::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ስለ ህብረታችን!
📌 በጥቂት ወንድሞች አነሳሽነት ከአመታት በፊት በሀሳብ ደረጃ እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን ላለፉት 3 አመታት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ከዚህ ደርሷል:: ባለፉት አመታት ለ2 ተከታታይ ጊዜ ከሁሉም የዩኒቨርሲቲ ጀመዓዎች የተውጣጡ አሚሮች ተሰባስበው ምክክር ያደረጉ ሲሆን በዚያ መሠረት በተደረገ እንቅስቃሴም ከወራት በፊት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት እውቅና አግኝቷል::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
ለኢስላም እና ለሙስሊሞች አስተዋፅዖ እንዲያደርግ ሲጠየቅ "እኔ አንድ ነኝ:: ሰራሁ አልሰራሁ ምን ላጎድል?" ይላል:: "ማን?" ከተባለ ምላሹ ሁሉም በሚባል ደረጃ ነው:: ሀሳብ ሲጠየቅ እነ እገሌ ሀሳብ ከሰጡ ይበቃል ይላሉ:: ሶደቃ ስጡ ሲባል እነ እገሌ ከሰጡ ይበቃል ይላል:: ጉልበታችሁን አዋጡ ሲባል እነ እገሌ ካዋጡ ይበቃል ይላሉ:: ከዚያስ? ከዚያማ ውጤቱ ከታች እንደምጠቅሰው ታሪክ ይሆናል::
ንጉሱ ከህዝቡ መካከል ምን ያክሉ እንደሚወዱት ለመለዬት በማሰብ ከአደባባይ በርሜል አስቀምጦ እኔን የምትወዱ በበርሜል ቀዳዳ ወተት አስገቡ ሲል ያዛል:: አንዱ መጣና ሁሉም ሰው ወተት ማስገባቱ አይቀርም:: እኔ ማንም ሳያየኝ ውሃ ላስገባ ብሎ ውሃ ጨመረ:: የጊዜ ገደቡ አብቅቶ በርሜሉ ሲከፈት በርሜል ሙሉ ውሃ ተገኘ:: ለካስ ሁሉም ሰው ሌላው ወተት እየጨመረ ነውና ማንም ስለማያየኝ ውሃ ከትቼ ልሂድ ብሎ ውሃ ነው የጨመረው::
የእኛም ሁኔታ እንደዚሁ ነው:: ሁሉም ለእነ እገሌ እያስጠጋ አመርቂ ለውጥ እንዳይመጣ አድርጓል:: ለውጥ ይመጣ ዘንድ ሁሉም የየራሱን ሀላፊነት ሊወጣ ግድ ይላል:: ያለውን መስጠት:: የቻለውን መስራት:: ከዛሬ ከአሁን ጀምሮ ማለት ነው::
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
@EHEMSU @EHEMSU @EHEMSU
