ግሎባል ፋኖ ሚዲያ/ዓፋሚ/Global Fano Media/GFM
رفتن به کانال در Telegram
1 104
مشترکین
+124 ساعت
-107 روز
-6430 روز
آرشیو پست ها
የፅምዶ ወኪሎች በጎንደር/ አስቸኳይ መግለጫ ከራያ/ "ዓላማችን ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው" ኦላ/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 3
የፅምዶ ወኪሎች በጎንደር/ አስቸኳይ መግለጫ ከራያ/ "ዓላማችን ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው" ኦላ/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 2
የፅምዶ ወኪሎች በጎንደር/ አስቸኳይ መግለጫ ከራያ/ "ዓላማችን ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው" ኦላ/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል አንድ
የህውሃት መግለጫ/ በእስክንድር ላይ የተወሰነው ፍርድ/ የህወሓት የዲፕሎማሲ ክሽፈት/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 3
የህውሃት መግለጫ/ በእስክንድር ላይ የተወሰነው ፍርድ/ የህወሓት የዲፕሎማሲ ክሽፈት/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 2
የህውሃት መግለጫ/ በእስክንድር ላይ የተወሰነው ፍርድ/ የህወሓት የዲፕሎማሲ ክሽፈት/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል አንድ
"እምቢ ለዳግም ባርነት" ጎንደር/ "ተያይዘን እናልቃለን" ፅምዶ/ አፋር ወደ ሙሉ ውጊያ ገባ! የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 3
"እምቢ ለዳግም ባርነት" ጎንደር/ "ተያይዘን እናልቃለን" ፅምዶ/ አፋር ወደ ሙሉ ውጊያ ገባ! የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 2
"እምቢ ለዳግም ባርነት" ጎንደር/ "ተያይዘን እናልቃለን" ፅምዶ/ አፋር ወደ ሙሉ ውጊያ ገባ! የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል አንድ
እምቢ ለዳግም ባርነት!
( ከጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ )
የጠለምት አማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ እና ኮሚቴው የወከለው መላ ሕዝቡ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም. በመቀሌ ከተማ የሕወሓት ጽ/ቤት ውስጥ በትግራይ ቴሌቪዥን የተሰጠውን መግለጫ በአክንሮ ተከታትለናል፡፡ በመግለጫው የተመለከትነው እውነታ፣ "ትብብር ለጥፋት" መሆኑን ነው፡፡
ከድርጅታዊ ምስረታው ጀምሮ አማራን በጠላትነት ፈርጆ፣ የኢትዮጵያን የጋራ ማንነት ክዶ ለ"ታላቋ ትግራይ" የአገር ምስረታ የተነሳው ሕወሓት፣ በድኀረ-1983ቷ ኢትዮጵያ ከ"ትግራይ ሪፐብሊክ" ወደ "ትግራይ የበላይነት" ተሸጋግሮ በአገዛዛ ዘመኑ አማራውን ከሌሎች ወንድም ኢትዮጵያዊያን ለመነጠል፣ ባይተዋር አድርጎ ለመግዛት መዋቅራዊ ጥቃት መክፈቱ ታሪካዊ ሐቅ ነው፡፡
አማራው በማንነቱ የደረሰበት ግፍና መከራ (ሐሳዊ ትርክት፣ የዘር መጽዳትና ፍጅት፣…) እንዲሁም ያጣቸው ብሔራዊ ጥቅሞች መነሻ መሰረቱ በአማራ ጥላቻ የተዋቀረው የደደቢት ትርክት ነው፡፡ ትርክቱን ተከትሎ የተፈጠሩ ሥርዓታዊ መዋቅራዊ የጥቃት መሳሪያዎች የጥላቻ ማኒፌስቴው ማስፈጸሚያ ሆነዋል፡፡
የሕወሓት የፖለቲካ ግብ በአማራ ቁልቁለት የሚጸና የትግራይ የበላይነትን ማንበር ስለመሆኑ ከፈጠራቸው ሐሳዊ ትርክቶች፣ ከጥላቻ ፖለቲካው እና ከግዛት ተስፋፊነቱ መረዳት ይቻላል፡፡
የጠለምት አማራ ጉዳይም የሚታየው ከዚሁ አውዳሚ የፖለቲካ ባህሪው በመነሳት ነው፡፡ የጠለምት አማራ ሕዝብ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ የሚሻገር የመከራ ጊዜ፣ አፓርታይዳዊ አገዛዝ ተጭኖበት መቆየቱ መላ የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰቦች የሚያውቁት እውነታ ነው፡፡
የ1987ቱ ሕገ-መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በኃይልና በጭፍለቃ ተይዘን ከእናት ግዛታችን ስሜን በጌምድር አማራ ተነጥለን ለመኖር ተገደን ነበር፡፡ በዚያ የሕወሓት አገዛዝ ዘመን፣ አማራዊ ማንነታችን የጥቃት ምንጭ ሆኖብን የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሞብናል፡፡
ይህም ሆኖ ከበርካታ የሕዝብ ትግልና ውጣ ውረድ በኋላ እዚህኛው የትግል ምዕራፍ ላይ ብንደርሰም ወደዳግም ባርነት ሊመልሱን የሚፈልጉ አደገኛ እንቅስቃሴዎችን፣ የጀርባ ስምምነቶችን እያስተዋልን ነው፡፡
በመሆኑም የሚከተለውን ጥሪ እናቀርባለን፡-
1) ሕወሓት የጦር ወንጀል የፈጸመ፣ በዘር ማጥፋት ወንጀል መጠየቅ የሚገባው የሐገረ-መንግሥቱ ጠላት ሆኖ ሳለ፤ ይህ ኃይል በኖረበት ወንጀለኝነቱ እንዲቀጥል፣ ለአማራና ትግራይ ሕዝብ በሀቅ ላይ የተመሰረተ ዕርቅና መልካም ጉብርትናን ለማስቀጠል በማይጠቅም መልኩ፣ የሀገር ሰላምን በማያፀና፣ ይልቁንም ወደአገራዊ ፍርሰት የሚያስገባ የጥፋት ትብብር መፈጠሩን፣ አጥብቀን እናወግዛለን፡፡
የከፋኝ አርበኞች የትግል መነሻ በሆነው ጠለምት ምድር፣ ሕዝባችንን ለዳግም ባርነት ሊዳርጉ የሚችሉ ማናቸውንም የጥፋት እንቅስቃሴዎችን እንደማንታገስ እናሳስባለን፡፡ በዕጣ ፈንታችን ላይ ዕጣ ሊጣጣሉብን የሚፈልጉ የትኞቹንም ቁማርተኞች በዝምታ አንመለከትም፡፡ በቀጣይ ሊቃጣብን ለሚችል ወረራ ሕዝባችን የራሱን ተፈጥሯዊ የመከላከል መብቱን ለመጠቀም የሚገደድ በመሆኑ ራሱን ለሁንተናዊ ትግል እንዲያዘጋጅ እናደርጋለን!!
2) የጠለምት፣ ራያና ወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን በዘላቂነት እንዲጸና ስትታገል የቆየህው መላው የአማራ ሕዝብ እና ዲያስፖራ ወገናችን በሙሉ፡- በዚህ ታሪካዊ የትግል ምዕራፍ ላይ ቆመን፣ የሕወሓት ቡድን የተገንጣይነት ስሜቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ በጨመረበት በዚህ ጊዜ፣ የትግራይ ሪፐብሊክ ምስረታ እንቅስቃሴውን እውን ለማድረግ በትብብር ስም መምጣቱን አውቀህ፣ ይህን የጥፋት ዓላማውን ለማምከን በሚደረገው ትግል ተሳትፏችሁን አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ ታሪካዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
3) የአማራ ሕዝብ ለዘመናት ሲታገልላቸው የኖሩ ሦስቱም የአማራ ታሪካዊ ርስቶች ማለትም ጠለምት፣ ራያ እና ወልቃይት-ጠገዴ ከማንነትና ከርስት ባሻገር ቁልፍ አገራዊ የህልውና ጉዳዮች ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች በሕወሓት እጅ ዳግም ከወደቁ ድርጅቱ ለረዥም ዓመታት ሲሰራበት የቆየውን የመገንጠል አጀንዳውን እውን እንደሚያደርገው ታውቆ እነዚህ ግዛቶች የኢትዮጵያ ሀገረ-መንግሥት ህልውና ቁልፍ ጉዳዩች ሆነው መታየት እንዳለባቸው፣ የኢትዮጵያን አንድነት የሚወዱ ወገኖች ሁሉ የትግላችን አጋር እንዲሆኑ ለመላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊያን ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
በመጨረሻም፤
እኛ የጠለምት አማራዎች፣ ታሪካችን፣ ስሪታችን፣ ማንነታችንና ሥነ-ልቦናችን ጎንደሬ አማራ ነው፡፡ አስተዳደራዊ ፍላጎታችንም የማንነታችን አካል ከሆነው ከአማራ ሕዝብ ጋር በመሆኑ፣ አማራዊ ማንነታችን እና ተከዜ ወሰናችን በዘላቂነት እንዲከበር ለወጣንበት የትግል ዓላማ ፀንተን እንደምንዘልቅ እናረጋግጣለን፡፡
ሕዝባችን በየትኛውም አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ቢሆን እንኳ ለነጻነትና ለክበሩ ይፋለማል፡፡ በባህላቻን እጅ መንሳት እንጂ፤ እጅ መስጠት አናውቅም!! ከጠለምት አማራ የሚሰረቅ ማንነት፤ ዳግም የሚወረር መሬት የለም!!
እምቢ ለዳግም ባርነት!
ማይጠምሪ - ጎንደር ኢትዮጵያ
መስከረም 12/2019 ዓ.ም
አርበኛ እስክንድር ስለትብብሩ ሐሳብ ሰጠ/ ስለ ትብብሩ አልተወያየነም፣ አርበኛ ኪሩቤል ጎቤ/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 3
አርበኛ እስክንድር ስለትብብሩ ሐሳብ ሰጠ/ ስለ ትብብሩ አልተወያየነም፣ አርበኛ ኪሩቤል ጎቤ/ የሚሉትን በቀለብ ስዩምና በሙላት አድኖ ክፍል 2
