cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቤተ ዮሴፍ-Bete Yosef

"የትውልድ ራዕይ"

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
422
مشترکین
+324 ساعت
+217 روز
+3830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ሕንፀተ ቤታ (ሕንፀታ) በሰላም አደረሳችሁ! ሰኔ ፳፩ (ሕንፀታ ወቅዳሴ ቤታ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን) ከእመቤታችን ፴፫ቱ በዓላት አንዱ ነው፡፡ ጌታችንም ከእመቤታችን እና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ከሰማየ ሰማያት ወርዶ እመቤታችንን ታቦት፣ ሐዋርያትን ልዑካን አድርጎ፣ እርሱ ሠራዒ ካህን ኾኖ ቀድሶ ካቈረባቸው በኋላ ‹‹እምይእዜሰ አንትሙኒ ከመዝ ግበሩ፤ ከዛሬ ጀምሮ እናንተም እንደዚህ አድርጉ›› ብሎ አዝዟቸው በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ከዚህ በኋላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያንን አንፀዋል። እግዚአብሔር አምላክ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ፍቅር፥ ረድኤት፥ ጸጋ - የቡሩካን ሐዋርያቱን በረከት ያሳድርብን! አሜን! https://t.me/beteyosef
نمایش همه...
نمایش همه...
ሙዳየ ምክር - በእንተ ቅዱስ ቁርባን.pdf2.46 KB
#በእንተ_ቅዱስ_ቁርባን | ክፍል ፯ --------------------------- #ቅዱስ_ቁርባን_ከተቀበልን_በኋላ_ማድረግ_የሚገባን_ጥንቃቄ #ረ_አብዝቶ_መብላት_መጠጣት_አይገባም ለጊዜው አብዝተን ስንበላ ስንጠጣ ሆዳችንን እንዳያውከንና አውጥቶ ወደመጣል እንድንደርስ ነው፤ይህን ብናድርግ አውጥተን ወደ ጣልነው ኃጢአትና ዓለም የመመለስ ምልክት ነውና፡፡ ፍጻሜው ግን አብዝተን ስንበላ ስንጠጣ ለልባችን ሙቀተ ሥጋ ይሰማውና በሥጋው በደሙ ያገኘነው የመንፈስ ቅዱስ ሙቀት እንዳለየን ለበጎ ሥራ ምውታን እንዳንሆን ነው፡፡ መብል መጠጥ ሲበዛ ነፍሳችን ከኃጢአት ጋር ታግላ ማሸነፍ ያቅታታል ፤ የጠገበች ነፍስ ስትኖረን እንጂ የጠገበ ሥጋ ይዘን ወደ ሰልፉ ብንገባ እጅ ለመስጠት ጊዜ አይወስድብንም፡፡ ስለዚህም ሥጋን እያስራቡ ነፍስን ማበርታት ስለሚገባ የነፍሳችን ምግብ የሆነውን ቁርባን ተቀብሎ የሥጋን ድርጎ መቀነስ ይገባል፡፡ ይህን ያደረግን እንደሆነ ሥጋችን በነፍሳችን ቀንታ “ብፁዕ ውእቱ ዘይበልዕ እክለ በመንግስተ እግዚአብሔር-በእግዚአብሔር መንግስት እንጀራ የሚበላ ብፁእ ነው”(ሉቃ ፲፬፥፲፭)፡፡ #ሰ_በየጊዜው_መቁረብ_ይገባናል በየአንዳንዱ ቀንም ቢሆን ሥጋውን ደሙን መቀበል ለሚቻለው መልካም ነው፤ቅዱስ ወንጌል ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም፤የዕለት ምግባችንን ዛሬ ስጠን(ማቴ.፮፥፲፪)በማለት የሚናገረው ስለዚህ ነውና፡፡ በዚህ ታላቅ ጸሎት ውስጥ መምህራችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለምድራዊ መብል መጠጥ እንድንለምን የሚያስተምረን ይመስላችኋል ? እሱስ ስለማልፈው ምግብ ስለ ሥጋው ስለደሙ እንዲህ ብለን እንድንጸልይ በየዕለቱ ሥጋህን ደምህን ለመቀበል አብቃን በሉኝ ሲል እንዲህ አስተምሮናል፡፡ ከእሰክንድሪያ ቤተ ክርስቲን ሊቃነ ጳጳሳት አንዱ አቡነ ስምዖን በሹመት ዘመኑ ከአንዲት ቀን በቀር ከሥጋው ከደሙ ተለይቶ ሳይቀበል ውሎ አያውቅም ነበር፡ ፡ ነግር ግን እያንዳንዶቻችን ምክንያት እየፈጠርን ብዙ ቀናትን ሥጋውና ደሙን ሳንቀበል እናሳልፋቸዋለን፡፡ ከመብልና ከመጠጥ ሰውነታችንን ከልክለን መኖር እንደማችል ሁሉ ለነፍሳችንም ምግብነት ሥጋውና ደሙ በእያንዳንዱ ቀን ያስፈልጋታል፡፡ ከተቀበሉ በኋላ ኃጢአት ብሠራስ ? ከማግባቴ በፊት ብቀበል የትዳር ጓደኛ እንዴት ልመርጥ እችላለሁ ? ከማግባቴ በፊትስ እንዴት ብቻዬን ልቀበል እችላለሁ ? እንዲህ እንዲህ እያልን ብዙ ቅርንጫፍ ያለው የምክንያት ዛፍ በልባችን ተክለን በማያሳርፍ ጥላው ተጠልለን መኖር ፍጻሜው ጥፋት ነው፡፡ እኛ ዛሬ ለመቀበል የተመቸ ጊዜ ከሆነልን የትዳር አጋራችን ደግሞ እየተዘጋጀ በሚቀጥለው እንዲቆርብ ማድረግና እግዚአብሔር ለቅዱስ ቁርባን እንዲያበቃልን መጠየቅ ይኖርብናል፡፡ በዚህ ሰማያዊ ማዕድ ፊት ከሚያገለግሉ ካህናት ጀምሮ ማንም ቢሆን ከኃጢአት ንጹሕ ነኝ ብሎ የሚቀበል የለም፤በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ እያልን እንቀበላለን እንጂ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ከቁርባን በኋላ ሦስት ጊዜ መላልሶ ክዶ ነበር፡፡ ነገር ግን ሳይውል ሳያድር ንስሓ ገብቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመለሰ፡፡ ይህ ስለሆነም እኛም ዛሬ ንስሓን ተስፋ አድርገን እንቀርባለን፡፡ በዚያውም ላይ በሥጋው በደሙ በምናገኘው ኃይል ዲያብሎስን ድል እንነሳዋለን ብለን እንጂ በብቃታችንማ ምን ዐቅም ኖሮን ልንቀበለው እንችላለን ? ስለዚህ ከሥጋ ወደሙ መራቅ የለብንም፡፡ ከተቀበሉ በኋላ የትዳር አጋር የሚሆነን ሰው መምረጥ የሚከለክል ሕግ ቤተ ክርስቲያናን የላትም፤ሳታገቡ ብቻችሁን መቁረብ አትችሉም ማለትም አይቻልም፤ለቅዱስ ቁርባን የተጠሩ በመንገድ የተገኙት ሁሉ ናቸው እንጂ ዕገሌን ጥሩ ዕገሌን ተው የሚል የለምና፡፡ “እንግዲህ ወደ መንገድ መተላለፊያ ሔዳችሁ ያገኛችሁትን ሰው ሁሉ ጥሩ”እንዲል(ማቴ.፳፪፥፱)፡፡ ከምክንያት እንውጣ ፣ዛሬ ለመቁረብ እንዘጋጅ፤እያንዳንዷ ቀን ከክርስቶስ ጋር ራሳችንን የማናዋሕድባት ቀን ልትሆን ይገባታል፤እያንዳንዷ በዕድሜአችን ውስጥ የምታልፈው ቀን ለክብር ትንሣኤ የምታበቃን ልትሆን ይገባታል፤ ያለ ቁርባን ከክርስቶስ ጋር መዋሐድ ፣ያለ ቁርባንስ ትንሣኤ ዘለክብርን ማሰብ እንዴት ይቻላል ? “እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የሰውን ልጅ ሥጋ ካልበላችሁ ደሙንም ካልጠጣችሁ በራሳችሁ ሕይወት የላችሁም። ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ”(ዮሐ ፮፥፶፫-፶፬)”” ምንጭ ፡ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ |ከታኅሣሥ 1-15/2009 ዓ.ም| በሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ መልአክ https://t.me/beteyosef
نمایش همه...
ቤተ ዮሴፍ-Bete Yosef

"የትውልድ ራዕይ"

Photo unavailableShow in Telegram
#በእንተ_ቅዱስ_ቁርባን | ክፍል ፮ -------------------------- #ቅዱስ_ቁርባን_ከተቀበልን_በኋላ_ማድረግ_የሚገባን_ጥንቃቄ #ለ_ማየ_መቁረር_እንጠጣለን:: ከቆረቡ በኃላ ማየ መቁረር ወይም ጠበል መጠጣት ይገባናል፤ምክንያቱም ይህ ቁርባን የሚያቃጥል እሳት ነውና፡፡ በእርግጥ እሳተ መለኮትን በቃለ እግዚአብሔር በከበረው ቅዱስ ውኃ (ማየ መቁረር ) እናቀዘቅዛለን ማለታችን እንዳልሆነ መረዳት ይገባናል፡፡ እሳት በውኃ እንዲሸነፍ ይህን እሳተ መለኮት ካህናት በእጃቸው ዳሰው እኛን በአፋችን እንድንቀበለው ያደረገን ቸርነቱ ናውና፤ በምሕረትህ ብዛት ኃይልህን ለብሰን እንኖራለን ለማለት ነው እንጂ ፡፡ ከዚያ ቀጥለን መክፈልት(የሰንበት ጸሪቅ) እንበላለን እንጂ ማንኛውንም መብል መጠጥ እንዳገኘን የምንበላ አይደለንም፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን በሰንበት ቀን መክፈልት (የሰንበት ጸሪቅ) እንዲዘጋጅ የተደረገውም ያለምክንያት አይደለም፤ያውም በብርቱ ጥንቃቄ ጋጋሪ ተመርጦለት ከአንድ ሰው ቤት ሳይሆን ከብዙ ቤት ተውጣጥቶ መዘጋጀቱ መእመናን በዚህ ዕለት ሥጋውን ደሙን ሳይቀበሉ የማይውሉ መሆናቸውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የሚደነግግ ሰለሆነ ነው፡፡ #ሐ_ወደ_ሸንጎ_ከመሔድ_እንጠበቃለን:: በዚህ ቀን ምእመናንን ከሳሽም ሊከሳቸው ዳኛም ሊፈርድባቸው አይገባም፤ምክንያቱም ከፍርድ ነፃ የሚያደርገውን ሥጋውንና ደሙን ተቀብለዋልና፡፡ ፊያታዊ ዘየማንን በኃጢአት ይከሰው ዘንድ ኪሩብ መልአክ አልተቻለውም፡፡ አዳምን በመርገም ያሲዘው ዘንድ አሁን ለዲያብሎስ ሥልጣን የለውም፡፡ ክርስቶስ መከሰሱ መወቀሱ የአዳም ልጆችን ከወቀሳ ከከሰሳ ለማዳን ነውና፡፡ ንስሓ ገብተው፣ራሳቸውን ለካህን አስመርምረው ሥጋውን ደሙን ለሚቀበሉ መከሰስ መወቀስ የለባቸውም፡፡ እነዚህ ሰዎች ነፃ ናቸው፤አጋንንት ፣መናፍቃን ሊያፍሯቸው ፣ሊፈሯቸው ይገባል እንጂ ማንም ቢሆን ወደ ፍርድ ዐደባባይ ሊያቀርበው አይገባም፡፡ የአባታችን ከሳሽ ሰይጣን የተረታበት መሥዋዕት ነውና መቁረብ ማለት ሲኦልን ለቆ መውጣትና ወደ ገነት መግባት ነውና በገነት ምስጋና እንጂ ክስና ወቀሳ የለም፡፡ ስለዚህ ወደ ሸንጎ ሥፍራ ላለመድረስ እንጠነቀቃለን፡፡ #መ_ከልብስ_መራቆት_የተከለከለ_ነው :: በምንችለው ሁሉ ለቁርባን የተለየ ነጭ ልብስ እንዲኖረን ይገባል፡፡ በፍት.ሥጋ. ቀን. ፳፫ ላይ እንደተመዘገበው አንድ ክርስቲያን ሁለት ልብስ እንዲኖረው መታዘዙ አንዱ ለቁርባን እንዲሆን ነው፡፡ በኃጢአት ምክንያት ከጸጋ እግዚአብሔር ተራቁተን ዕርቃናችንን ቀርተን ነበር(ዘፍ. ፫፥፱)፡፡ ስለሁላችን በደል በተሠዋ በዚህ መሥዋዕት (ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ) የቀድሞውን ልብስ(ጸጋ) ተጎናጽፈናል(ማቴ.፳፮፥፳፮)፡፡ ስለዚህ በማይገባ የተፈጸመው በደላችን ዕርቃናችንን ቢያስቀረንም በማይገባ ሞት የተፈረደበት ክርስቶስ ደግሞ በጸጋ ላይ ጸጋ እንዲኖረን አድርጎናል፡፡ እኛ እንድንለብስ ክርስቶስ ተራቆተ ፡፡ የአዳም ዕርቃን በክርስቶስ ልብስ መገፈፍ ካሳው ተፈጽሞልናልና እና ከልብስ ባለመራቆት ይህን ስናስታውስ እንኖራለን፡፡ #ሠ_መስገድ_አይገባም:: መንፈሳዊ ሥራ ነውና ብሎ ከቁርባን በኋላ ሊሰግዱ አይገባም፤ ምክንያቱም ሥጋው ደሙ የመንግስተ ሰማያት መግቢያ ነውና፡፡ መንግስተ ሰማያት ከገቡ በኋላም ድካም መውጣት መውረድ የለም፡፡ መንግስተ ሰማያት የተነጸፈች እረፍት ናት ፤ማንም በገዛ ድካሙ ያገኛትም የሚያገኛትም አይደለችም፤የሠራነው ማንኛውም ሥራ ቢመዘን ለመንግስተ ሰማያት ዋጋ ሊሆን አይችልምና፡፡ ሥጋውና ደሙ የቸርነቱ ስጦታ እንደሆነ ሁሉ መንግስተ ሰማያትም የቸርነቱ ስጦታ መሆኗን እንድናውቅ ስለሚያስፈልግ ከቁርባን በኋላ ስግደት የተከለከለ ሆነ፡፡ ጌታችን ከመያዙ ጥቂት ቀደም ብሎ ወዙ እስኪወርድ በጌቴሰማኒ መስገዱ ለጻድቃን ዕረፍትን ለመስጠት እንደሆነ መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስግደት ብቻ ሳይሆን መንገድ መጓዝ ሌላም ወዛችን በግንባራችን እንዲወጣ የሚያድርግ አድካሚ ሥራ መሥራት የሚገባ አይደለም፡፡ “በላብህ በወዝህ ጥረህ ግረህ ትኖራለህ” የሚለው የመርገም ቃል ለዚህ ምድር እንጂ በሥጋው በደሙ ሕይወትነት ለምትወረሰው ዘለዓለማዊ ርስት አይደለምና፡፡ ነገር ግን ይህን ሁሉ ድካም ከቁርባን በፊት ቀደም ብሎ ማድረግ ይገባል፡፡ ምክንያቱም በብርቱ ትጋት ኃጢአትን በንስሓ ማስወገድ ይቻላልና፡፡ ከቁርባን በኋላ መስገድ ግን ሥጋውና ደሙ የማያስተሰርየው ኃጢአት አለና በድካሜ ወጥቼ ወርጄ አስተሰርየዋለሁ ማለት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ትዕቢት ከመሆኑም ባሻገር መጠራጠር ይሆናል(ማቴ ፳፮፥፳፮)፡፡ ይቀጥላል! https://t.me/beteyosef
نمایش همه...
ቤተ ዮሴፍ-Bete Yosef

"የትውልድ ራዕይ"

Photo unavailableShow in Telegram
#በእንተ_ቅዱስ_ቁርባን | ክፍል ፭ -------------------------- #ቅዱስ_ቁርባን_ከተቀበልን_በኋላ_ማድረግ_የሚገባን_ጥንቃቄ ለመቁረብ ዝግጅት እንደምናደርግ ሁሉ ከቁርባንም በኋላ የምናድጋቸው ጥንቃቄዎች አሉ፡፡ ስለ ክብረ ቅዱስ ቁርባን ራሳችንን በልዩ ልዩ ነገሮች ለእግዚአብሔር እንዲገዛ ከማድረጋችንም በላይ በቅዱስ ቁርባን ምክንያት ከእግዚአብሔር ጋር ተዋሕደናል እንጂ ብቻችንን አይደለንምና ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ ብዙ ጥንቃቄ እንድናደርግ ታዝዘናል፡፡ #ሀ_አፋችንን_በልብስ_እንሸፍናለን:: ቅዱስ ሥጋዉንና ክቡር ደሙን ከመቀበል ቀጥሎ የምናከናውነው ቀዳሚ ተግባር አፋችንን መሸፈን ነው፤ይህን እንድናደርግ መታዘዛችን በብዙ ምክንያት ነው፡፡ #ሥርዓተ_መግነዙን_ለማሳየት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከመስቀል አውርደው በድርብ በፍታ እንደገነዙት በቅዱስ መጽሐፍ ተጽፏል(ማቴ ፳፯፥፶፱ ዮሐ ፲፱፥፴፰-፵፩)፡፡አሁን በቤተ መቅደስ የምቀበላው ሥጋና ደም ዮሴፍ ዘአርማትያስ ይቀብረው ዘንድ ከጲላጦስ ዘንድ የተካሰሰበት የዕለተ ዓርቡ ክርስቶስ ነው ፡፡ ቤተ መቅደሱን እንደ ቀራንዮ አድርገን ሥጋዉን ደሙን በተቀበልንበት ጊዜ አፋችንን በልብሳችን መሸፈናችን ፡ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ እንዲህ በድርብ በፍታ ገንዘውህ ነበር ፡፡ አሁን ግን በድርብ በፍታ ተገንዘህ ወደ መቃብር አትወርድም ፣በእኔ ልብ ውስጥ አድረህ ትኖራለህ ማለታችን ነው፡፡ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን መታደሉ ፡- ቤተ ክርስቲያን የቀራንዮ፣ከርሠ ምእመናን ጌታችን የተቀበረበት ጎልጎታ ምሳሌ ሲሆኑ ምእመናን እንደቆረቡ አፋቸውን መግጠማቸው የጌታችን መቃብር በጥርብ ድንጋይ የመገጠሙ ምሳሌ እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲን ያስተምራሉ፡፡ #መሸፈን_የአንክ_ የተደሞ_ምሳሌ_በመሆኑ ጌታችን የተሰቀለባት ዕለት ሁሉን ያስደነገጠችና ያስደነቀች ዕለት ዓርብ ናት፡፡ በዚህች ዕለት የእግዚአብሔር ትዕግስቱ ሁሉን በአንክሮ ዝም እንዲል አድርጎታል፡፡ ቀንድ እያለው በቀንዱ የማይበረታታ ላሕም ለሚያርዱትና ለሚያወራርዱት አንገቱን ዘንበል የሚያድርግ ፤በሸላቾቹ ፊት የማይናገር በግዕ ፤ወልደ እግዚአብሔር ክርስቶስ በሰማይና በምድር የሚኖረውን ሁሉ ፍጥረት ያስደነቀውን ሥራ በመስቀል ላይ ሠራ፡፡ ስለዚህ መላእክት በመስቀሉ ዙሪያ እንዳች ቃል አልተናገሩም ፤ ከአንድ መልአክ በስተቀር ሁሉም መላእክት ሰይፋቸውን አልመዘዙም ፡፡ በተያዘባት ሌሊት ከአንድ ሐዋርያ ከቅዱስ ጴጥሮስ በቀር ማንም ሴይፉን አላነሳም፤በዕለተ ዓርብም ከአንድ መልአክ በቀር ማንም ስለእርሱ አልተናገረም ፣እኛም በዚያን ዕለት ካሉ ሰዎች ጋር እንዳለን ሆነን ዛሬ በአንክሮ ዝም እንላለን፡፡ በመስቀል ላይ የተገለጠውን ፍቅር ልብ ሊመረምረው አይችልም፤አንደበት ሊተረጉመው ዓቅም አይኖረውም፡፡ ስለዚህም ዝም ብለን ለማድነቅ ወስነን አፋችንን እንሸፍናለን፡፡ #ራስን_ከኃጢአት_የማራቅ_ውሳኔ_ነው:: ቅዱሳን የሕሊና ጸሎት ሲጀምሩ አንደበታቸውን ከመናገር ይገታሉ፤ይኸውም በሁሉም ጊዜ በልባቸው ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር እንዲያመቻቸው ነው፡፡ አንደበትን መጠበቅ ኃጢአትን ለማሸነፍ ከሚደረጉ ተጋድሎዎች መካከል ዋናው ነው፡፡ ሰው አንደበቱንና ሆዱን መጠበቅ ከቻለ በሌላው አይሸነፍምና፡፡ ከቅዱስ ቁርባን በላይ ምን የኃይል ምንጭ አለ ? ከዚህ ጊዜ ወዲያስ ከኃጢአት ጋር ልንርቅበት የምንችለው ሌላ ምን አጋጣሚ ሊኖር ይችላል ? ስለዚህም እንደተቀበልን ውሳኔአችንን በዚያው በማዕዱ ፊት በካህናት ምስክርነት እናረጋግጣለን፡፡ “በአንደበቴ እንዳልስት አፌን በዝምታ እጠብቃለሁ፤ ለአንደበቴም ጠባቂ አኖርሁ ፤ከዝምታ የተነሳ እንደ ዲዳ ሆንሁ ፣ ለበጎ እንኳን ዝም አልሁ፣ቁስሌ ታደሰብኝ ፤ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ “ የሚለውን መዝሙር በልባችን እንዘምራለን(መዝ ፴፰፥፩-፫) ይቀጥላል! https://t.me/beteyosef
نمایش همه...
ቤተ ዮሴፍ-Bete Yosef

"የትውልድ ራዕይ"

Photo unavailableShow in Telegram
#በእንተ_ቅዱስ_ቁርባን | ክፍል ፬ -------------------------- #በቅዱስ _ቁርባን_ጊዜ_መደረግ_ያለበት_ጥንቃቄ #መ_በተመስጦ_ሆኖ_መቆም አሳባችንን ከሥጋዊ ሕልውና አውጥቶ ከሰማያዊያን ጋር የሚያሰልፍልን ተመስጦ ነው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ አንድ ሆነን ለመሰብሰባችን ምክንያቱ ሰማያዉያን መብልና መጠጥ ለመሳተፍ ነው፤እስከ ቅዳሴው ጊዜ ድረስ ሊቃውንቱ በቅኔ ማኅሌት ፣ካህናቱ በሰዓታት፣ምእመናኑ በጾሎት ይቆያሉ፡፡ በቅዳሴ ጊዜ ግን ሁሉም ገጸ ሕሊናውን ወደ መቅደሱ አዙሮ የቅዳሴውን ዜማ ብቻ ያዳምጣል፡፡ ቅዱሳን መላእክት ሳይቀሩ በተልእኮ ከሰው ጋር በሚሳተፉበት በዚህ ጊዜ ሁሉም ሕሊናውን ወደ ሰማያዊው መቅደስ አንሥቶ ምድራዊውን ዓለም ረስቶ ከሰማያዊው ማዕድ የሚሳተፉበትን ጊዜ መጠባበቅ አለበት፡፡ በቅዳሴው መካከል ዲያቆኑ እየመላለሰ “ተንሥኡ ለጸሎት” በማለት የሚያውጀው ምእመናን ወደ ዝንጋዔ እንዳይመለሱ ፣ተመስጧቸውን እንዳያቋርጡ ለማትጋት ነው፡፡(ፍት.መን.አን. ፲፪)ስለሆነም መላልሰው ለዐሥር ጊዜ ያህል በንባብም በዜማም ይህን ቃል ያሰማሉ፡፡ በአንዳንድ ቅዳሴዎች ደግሞ “በሰማይ የሀሉ ልብክሙ -ልባችሁ በሰማይ ይሁን “ የሚል ትእዛዝ አለ፤ምእመናንም መልሰው “እወ የሀሉ በሰማይ ልብነ -እውነት ነው ልባችን በሰማይ ሊኖር ይገባል “ ብለው ይመልሳሉ፡፡ ይህ ኅብስት ከምድራዊነት ወደ ሰማያዊነት ተለውጦ ተቀብለነው ይህን ዓለም በወዲያኛው ዓለም ለውጠህ የምትሰጠን መቼ ይሆን ? በማለት ሕሊናቸውን ወደ ሰማይ ይልኩታል፡፡ አስቀድመን እንደተናገርነው ትምህርተ ኅቡአት “አጽምሙ አእዛኒክሙ ወእለ ይትረአያ አዑሩ አእይንቲክሙ እለ በገሀድ-ውጫዊ ጆሮዎቻችሁን ውጫዊ ዐይኖቻችሁን ዝጉ” ብለው ካህናት ምእመኑን እንዲያስተምሯቸው ያዝዛል፡፡ በዓይነ ሕሊና የሚታይ በእዝነ ሕሊና የሚሰማ እንጂ በእዝነ ሥጋ የሚሰማ በዓይነ ሥጋ የሚታይ ምንም ምሥጢር በዚህ ቦታ ስለሌለ ነው፡፡ #ሠ_በኃዘን_ውስጥ_መሆን ሊቆርቡ ተዘጋጅተው ወደ ቤተ ክርስቲያን የተሰበሰቡ ካህናትና ምእመናን ዐሥራ ሰምንቱን የመስቀል ምዕራፎች ተጉዘው በተሸከሙት መስቀል ላይ ነፍሳቸውን ሰቅለው ቀራኒዮ ላይ እንደ ቆሙ ቅዱሳን ያሉ ናቸው ፡፡ ስለዚህም ነጭ ልብስ ለብሰው በኀዘን በፍርሃት ይቆማሉ ፤ ነጭ መልበሳቸው የልጅነት ክብራቸውና በሥጋዉ በደሙ የሚያገኙትን ጸጋና ክብር የሚያመለክት ነው ፡፡ ስለ ክብረ ቅዱስ ቁርባን ነጭ መልበስ የሚገባ ነው ፤ ውስጣቸው ግን ከቤታቸው ሲነሡ ጀምሮ በኃዘን ውስጥ ሊሆን ይገባዋል ፡፡ ቀራኒዮ ላይ ምን ደስታ ሊኖር ይችላል ? ለነፍስ እንጂ ለሥጋ ምንም ደስ የሚል ነገር አይገኝም፡፡ ስለዚህ በዚህ ቦታ ያሉ ምእመናንም ክርስቶስ በፊታቸው ላይ እንደተሰቀለ ሆኖ ተሥሎ እየታያቸው እስከ ቁርባን ሰዓት ድረስ በዓይነ ሥጋም እንኳን ባይሆን በውሳጣዊው ዓይናቸው ዕንባ ሊለያቸው አይገባም፤በአንቀጽ 12 ላይ ዋዛና ፈዛዛ እንዳይኖር የተከተከለው ለዚህ ነው፡፡ በመሥቀሉ ሥር እንደ ቆመችው እናቱና ጌታ እንደሚወደው ደቀ መዝሙሩ እንደ ዮሐንስ በብርቱ ኃዘን ውስጥ መሆን ይገባል፡፡ ቀዳስያኑም የቅዳሴ ልብሶቻቸው ነጫጭ እንዲሆኑ ታዟል፡፡ ነገር ግን ኃዘንተኞች መሆናቸውን ሊረሱት አይገባም፡፡የሚያምረውን ነጭ ወርቀ ዘቦ ግምጃ ለብሶ ድምፅን እያስረቀረቁ ውዳሴ ከንቱን መሻት አይገባም፤ ይልቁንም ነጭ በመልበሳቸው ፡ ሞት የማይገባው መለኮት በሥጋ ሞትን መቅመሱን ፣ነጭ ለብሰው ኃዘንተኞች በመሆናቸው ደግሞ፡ ሕያው ያልነበረ ሥጋ በመለኮት ሕያው ዘኢይመውት መባሉን ሊያስረዱ ይገባቸዋል፡፡ ለዚህ ነው ዮሐንስ አፈ ወርቅ በቅዳሴው “ብክይዎ ወላህውዎ እለ ታፈቅርዎ -የምትወዱት አልቅሱለት” ብሎ የተናገረው፡፡ ለእኔ ስትል ተሰቀልህ ፣ ለእኔ ስትል መራራ ሐሞትን ጠጣህ፣ለእኔ ስትል ተገረፍህ… እያሉ ሞት የማይገባው አምላክ ሞቶ ፣ሞት የሚገባን እኛ ደግሞ ወደ ዘለዓለም ሕይወት መግባታችንን እያሰብን ፣በእግዚአብሔር ቸርነት በእኛ ኃጢአት መካከል ያለውን ልዩነት እያመላለስን መቆም ይገባል፡፡ #ረ_አብዝቶ_መጸለይ በዚህ ጊዜ የግል ጸሎት እንዳይኖር ተከልክሏል፤ምክንያቱም ሁሉም አንድ ሆኖ መጸለይ ያለበት ስለ መስዋዕቱ ነውና፡፡ በውስጥ ያሉት ካህናቱ ለምእመኑ ፡- ለሥጋህ ለደምህ አብቃቸው ከቀሳፊ መልአክ ሰውራቸው እያሉ ይጸልዩላቸዋል፤በውጭ ያሉት ምእመናኑ ደግሞ ለካህናቱ ኅብስቱን ወይኑን ለውጥላቸው ፣ቅዳሴውን ፈጽመው ቁርባኑን ለማቀበል አብቃቸው እያሉ አንዱ ለአንዱ ይጸልዩላቸዋል፡፡ #ሰ_በየመዓረጋቸው_ሥጋውን_ደሙን_ሊቀበሉ_ይገባቸዋል ሥጋውን ደሙን መቀበል ከገባሬ ሠናዩ ካህን ይጀምራል፤ካህኑ እንደ ክርስቶስ አስቀድሞ ተቀብሎ ሊያቀብላቸው ይገባል፡፡ በቤተ መቅደስ ያሉ ካህናት ከተቀበሉ በኋላ ወደ ውጭ በመውጣት አስቀድመው በዕለቱ የተጠመቁ ሕፃናት የዕለት ሹማምንት ስለሆኑ ከሁሉም በፊት ሊቀበሉ ገባቸዋል፡፡ ከዚያ ቀጥሎ ሌሎች ሕፃናት ፣ደናግል፣መነኮሳት፣አረጋውያን፣ወጣት ወንዶች በቅደም ተከተል ሊቀበሉ ይገባል፤በሴቶችም በኩል ልክ እንዲሁ ይደረጋል፡፡ ለመቁረብ በሚቀርቡበት ጊዜ በመላእክት በተከበበ ቅዱስ ማዕድ እንደሚመገቡ እያሰቡ ሊቀበሉ ይገባቸዋል፤በቁርባን ጊዜ ቅዱሳን መላእክት ዙሪያውን ከበው ምእመናን ሲቀበሉ ለሰው የተሰጠውን ጸጋ እያደነቁ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፡፡ አባ ሕርያቆስ ስለዚህ ማዕድ ሲናገር “ቅድመ ዝንቱ ምሥጢር ግሩም-ግሩም በሚሆን በዚህ ምሥጢራዊ ማዕድ ፊት” ይለዋል፡፡ ግሩም ያሰኘው ግሩማን መላእክት ከበውት የሚቆሙ በሚገባ ሆነው ቢቀበሉት ግሩም ጸጋ የሚያሰጥ ስለሆነ ነው፡፡ ሥጋዉን ደሙን ግሩምነቱን እያሰቡ “ቅዱስ ሥሉስ” የሚለውን “እስመ ኃያል አንተ” እስከሚለው ድረስ ቁርባኑን እየተቀበሉ በህሊናቸው ሊጸልዩት ይገባቸዋል፡፡ ምንጭ ፡ ስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ |ከኅዳር 16-30/2009 ዓ.ም| በሊቀ ሊቃውንት ስምዓኮነ መልአክ ይቀጥላል! https://t.me/beteyosef
نمایش همه...
ቤተ ዮሴፍ-Bete Yosef

"የትውልድ ራዕይ"

Photo unavailableShow in Telegram
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.