Ethio Crypto
رفتن به کانال در Telegram
Researching emerging crypto projects, tracking market news, and sharing trading insights.
نمایش بیشتر3 318
مشترکین
-224 ساعت
-247 روز
-9430 روز
آرشیو پست ها
3 317
በአንድ ቀን 1 ቢሊዮን ዶላር የሰራው ሰው፡ የጆርጅ ሶሮስ "የጥቁር ረቡዕ" ሚስጥር! ✨
በSeptember 1992 ዓ.ም መላው ዓለም በአድናቆትና በድንጋጤ የተመለከተው አንድ ክስተት ተፈጠረ። George Soros የብሪታንያን ማዕከላዊ ባንክ አሸንፎ በአንድ ቀን ውስጥ $1,000,000,000 ትርፍ ሰበሰበ!
ይህ የታሪክ ምዕራፍ "Black Wednesday" (ጥቁር ረቡዕ) በመባል ይታወቃል። ሶሮስ ይህን ያደረገው ሁሉም ሰው "የእንግሊዝ ፓውንድ (GBP) ጠንካራ ነው" ብሎ በሚያስብበት እና በሚገዛበት ሰዓት ነበር። እርሱ ግን የገበያውን ስውር ድክመት ቀድሞ በመረዳት ፓውንዱን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር "Short" አደረገው (ሸጠው)።
🧬 የሶሮስ ልዩ የትሬዲንግ ፍልስፍናዎች
1. የጀርባ ህመም ቲዎሪ (The Back Pain Theory) 🧘♂️
ሶሮስ አንድ አስገራሚ ተፈጥሮአዊ "ኢንዲኬተር" አለው። ትሬድ ውስጥ እያለ የጀርባ ህመም ከተሰማው፣ ያ ለእርሱ ትልቅ ምልክት ነው።
"ጀርባዬ ህመም ሲሰማኝ፣ በፖርትፎሊዮዬ ውስጥ የሆነ ስህተት እንዳለ አውቃለሁ።" ይላል።ይህ ስሜት ዝም ብሎ ጭንቀት ሳይሆን፣ ለዓመታት ካካበተው እውቀት የሚመነጭ "ውስጠ-ታዋቂ" (Intuition) ነው። ትሬዲንግ በቻርት ላይ ብቻ ሳይሆን በደምና በአጥንት ውስጥ የሚሰማ ጥበብ መሆኑን ሶሮስ ያስመሰከረበት ነጥብ ነው። 2. ትክክለኛ ትሬዲንግ "አሰልቺ" ነው! 😴 ብዙዎች ትሬዲንግን እንደ ካዚኖ ወይም እንደ ፊልም አስደሳች (Exciting) አድርገው ያስቡታል። ሶሮስ ግን እንዲህ ሲል ይመክራል፦
"ኢንቨስት ማድረግ አስደሳች እና የሚያዝናና ከሆነ ምናልባት ምንም ገንዘብ እየሰራህ አይደለም። ትክክለኛ ኢንቨስትመንት አሰልቺ (Boring) ነው።"ትርፋማ መሆን ማለት ስሜትን አውጥቶ መጣል፣ በዲሲፕሊን ህጎችን መከተል እና ውጤቱ እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ነው። ድራማ ከፈለግክ ወደ ሲኒማ ሂድ፤ ገንዘብ ከፈለግክ ግን አሰልቺውን ስርዓት ተከተል! 3. ስህተትን የመቀበል ጥበብ 🔄 ሶሮስ ሀብታም የሆነው ሁልጊዜ ትክክል ስለሆነ አይደለም። እንዲያውም እንዲህ ይላል፦ "እኔ ከሌሎች የምለየው ስህተቶቼን ቀድሜ በማውቄ እና ስህተቴን አምኜ ወዲያውኑ እርምጃ በመውሰዴ ነው።" The Man Who Broke the Bank of England" የተባለው ሶሮስ ያስተማረን ትልቁ ቁምነገር፡ ትሬዲንግ የስትራቴጂ ብቻ ሳይሆን የጥንካሬ እና የራስን ስሜት የመረዳት ጥበብ መሆኑን ነው። @ethiocrypto52
3 317
+1
የአንድ ቢሊዮን ዶላር "ጀርባ"! 💰
በአንድ ቀን ውስጥ $1,000,000,000 ትርፍ መስራት ይቻላል? ለጆርጅ ሶሮስ (George Soros) መልሱ "አዎ" ነው።
በ1992 ዓ.ም የብሪታንያን ማዕከላዊ ባንክ ያስጨነቀውና ፓውንድን ሰብሮ የታሪክ ስሙን በወርቅ የጻፈው ሶሮስ፣ አንድ ሚስጥራዊ "ኢንዲኬተር" አለው። ቻርት ላይ የማይታይ፣ ግን በደሙና በአጥንቱ ውስጥ የሚሰማው... "የጀርባ ህመም!" 🧘♂️
"ኢንቨስትመንት የሚያዝናና እና አስደሳች ከሆነ፣ ምናልባት ምንም ገንዘብ እየሰራህ አይደለም። ትክክለኛ ትሬዲንግ አሰልቺ (Boring) ነው!" — George Sorosየአለምን ሃብታሞች አስተሳሰብ የቀየረው የሶሮስ "Back Pain Theory" እና የማርክ ዶግላስ "Trading in the Zone" ስነ-ልቦና እንዴት ትርፋማ እንደሚያደርጉህ በዝርዝር ልናቀርብላችሁ ተዘጋጅተናል። 🔥 ቀጥሎ የሚመጣውን ሙሉ ትንተና ይጠብቁ! የትሬዲንግ ህይወታችን የሚቀይር ትምህርት በዝግጅት ላይ ነው። @ethiocrypto52
3 317
የሲልቨር ዋጋ $121 ከነበረው ከፍተኛ ክብረ ወሰን (ATH) በአሁኑ ወቅት ወደ 50% ገደማ ቅናሽ አሳይቷል።
@ethiocrypto52
3 317
የቢትኮይን 2026 ኮንፈረንስ በላስ ቬጋስ ለመጀመር 30 ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
ዝግጅቱ ከ April 27 - 29, 2026 በ The Venetian ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን፣ ከተማዋ በቢትኮይን ደጋፊዎችና በኦሬንጅ ቀለም እንደምትደምቅ ይጠበቃል።
@ethiocrypto52
3 317
እንደ TRM Labs ሪፖርት፤ የፕሪዲክሽን ማርኬትስ ወርሃዊ የትሬዲንግ መጠን $20 ቢሊዮን ደርሷል። ይህም በ2025 መጀመሪያ ላይ ከነበረበት $1.2 ቢሊዮን አንጻር ሲታይ እጅግ ከፍተኛ እድገት ነው።
@ethiocrypto52
3 317
+1
የክሪፕቶ Fear & Greed Index ወደ 9 ዝቅ ብሏል። ይህም ለተከታታይ 70 ቀናት በከፍተኛ ፍርሃት ውስጥ እንዲቆይ አድርጎታል።
ይህ ሁኔታ በ2022 ከነበረው የ FTX መፈራረስ ወዲህ ረጅሙ የፍርሃት ወቅት ሆኖ ተመዝግቧል።
@ethiocrypto52
3 317
+1
ቢሊየነሩ Kevin O'Leary የክሪፕቶ ገበያ መዋቅር ህግ መጽደቁ አይቀሬ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ህግ አንዴ ከጸደቀ በኋላ ቢትኮይን ወደ $200,000 እንደሚመነጠቅ (Pump) ትንበያውን ሰጥቷል።
@ethiocrypto52
3 317
ቢትኮይን ማርች 1 ላይ የጀመረው በ $66,800 አካባቢ ነበር።
በአሁኑ ሰዓት (ማርች 28) ዋጋው በ $66,200 - $66,400 መካከል ይገኛል።
በሚቀጥሉት 2-3 ቀናት ውስጥ የ $67,000ን ሬዚስታንስ ሰብሮ ካልወጣ በስተቀር ወሩን በ Red የመዝጋት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።
@ethiocrypto52
3 317
በ Polymarket ላይ ቢትኮይን እስከ ዓመቱ መጨረሻ አዲስ ክብረ ወሰን (ATH) የመስበር ዕድሉ ከ 15% በታች ወርዷል።
@ethiocrypto52
3 317
አንድ ትልቅ ባለሃብት (Whale) የ $26,928,000 የቢትኮይን Short Position ከፍቷል።
የዚህ ትሬድ የኪሳራ መድረሻ $98,570 ላይ ተቀምጧል።
@ethiocrypto52
3 317
በነገራችን ላይ "ታዋቂ መሆን የታማኝነት ማረጋገጫ አይደለም!" 🚫
በቅርቡ በሀገራችን የተሰማው የ1.7 ቢሊዮን ብር የፊንቴክ ማጭበርበር አንድ ትልቅ የቤት ስራ ጥሎልናል፦
አሳዛኙ እውነታ፦ ከ1,200 በላይ ሰዎች የተታለሉት ድርጅቱን አውቀውት ሳይሆን፣ የሚወዷቸው ታዋቂ ሰዎች ማስታወቂያ ስለሰሩለት ብቻ ነው።
የክሪፕቶ ትምህርታችን፦ ልክ እንደ FTX ወይም ሌሎች ትልልቅ ውድቀቶች፣ ዝነኞች ስለመሰከሩለት ብቻ አንድን ፕሮጀክት አትመን።
ትዝብት፦ በክሪፕቶም ሆነ በማንኛውም ኢንቨስትመንት ላይ "ከልክ ያለፈ ትርፍ" ቃል ከተገባልህና በታዋቂ ሰዎች ማስታወቂያ ብቻ ካጌጠ... ቆም ብለህ መርምር!
ሁሌም የራስህን ጥናት አድርግ (DYOR)! 🛡️
@ethiocrypto52
3 317
በደቡብ አፍሪካ የክሪፕቶ ATM ማሽኖች በተለያዩ ከተሞች (Johannesburg, Cape Town, Durban) በስፋት እየታዩ ነው።
እንደ CoinFlip ያሉ ኩባንያዎች ማሽኖቹን እያቆሙ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች በካሽ (ZAR) ቢትኮይንና ሌሎች ኮይኖችን በቀላሉ መግዛትና መሸጥ የሚያስችላቸው አዲስ አማራጭ ሆኗል።
@ethiocrypto52
3 317
💧Sui በ July 2025 ላይ $4.40 በመግባት በዓለም የክሪፕቶ ገበያ ከቶፕ 15 ውስጥ ተቀምጦ ነበር። ይህም በወቅቱ በከፍተኛ ፍጥነት እያደጉ ካሉ የ Layer-1 ኔትወርኮች ቀዳሚው አድርጎታል። 🚀
በወቅቱ ሁሉም ሰው "ትርፉ እንዳያመልጠኝ" በሚል ስሜት የ FOMO ቀጠና ውስጥ ገብቶ ነበር።
አብዛኛው ተገፋፍቶ በከፍተኛ ሁኔታ መግባት የጀመረበት እና ገበያውም እጅግ የናወጠበት (Volatility) ወቅት ነበር።
@ethiocrypto52
3 317
+1
ታይላንድ በሆርሙዝ ስትሬት በኩል የሚያልፉ መርከቦቿ እንዳይጠቁና በሰላም እንዲያልፉ (Safe Passage) ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ ደርሳለች።
@ethiocrypto52
3 317
ቢትኮይን በ 2026 አሁንም በጥቂት እጆች የተያዘ (Concentrated) ሆኖ ቀጥሏል።
Satoshi Nakamoto በ ~1.1M BTC አንደኛ ሲሆን፣ Coinbase custody በ ~990K BTC እና BlackRock በ ~770K BTC (ETF) ገበያውን በከፍተኛ ደረጃ እየተቆጣጠሩት ይገኛሉ።
@ethiocrypto52
3 317
+1
ሴናተር Elizabeth Warren በቻይናው Bitmain እና በትራምፕ ቤተሰብ የንግድ ግንኙነት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቀዋል።
@ethiocrypto52
3 317
+1
🇧🇹ቡታን (Bhutan) የያዘችውን የቢትኮይን ክምችት በከፊል መሸጥ መጀመሯ ታውቋል።
በሚሊዮን የሚቆጠር BTC ዝውውር ያደረገችው ለትርፍ Strategic Profit-taking እንጂ ገበያውን ለመልቀቅ እንዳልሆነ ተነግሯል።
አሁንም ቢሆን ሀገሪቱ ከፍተኛ የሆነ የቢትኮይን ክምችት (Reserve) አላት።
@ethiocrypto52
3 317
ቢትኮይን በ $73,000 እና $60,000 የ Liquidity Trap መሃል ስለሚገኝ ከፍተኛ Movement ይጠበቃል።
$73k ላይ የ $2.5B Short Squeeze ዕድል ሲኖር፣ $60k በታች ደግሞ የ $1.5B Long Flush ስጋት አለ።
@ethiocrypto52
3 317
የቢሊየነሮቹ ፍጥጫ፡ "የአለም ቁጥር አንድ አጭበርባሪ!" 🥊
ኢሎን ማስክ በሳም አልትማን ላይ አዲስ 'ቦምብ' ጥሏል። ነገሩ በአጭሩ እንዲህ ነው፦
ተረብ፦ ማስክ የOpenAIው ሳም አልትማን "ሰዎችን በማጭበርበር ረገድ ልዩ ተሰጥኦ አለው" (Super good at scamming) ብሎታል።
ምክንያቱ፦ ማስክ እንደሚለው ሳም "ድርጅቱን ለሰው ልጅ ጥቅም ብለን በጋራ መሰረትን" ብሎ አታልሎኝ፣ አሁን ግን ከማይክሮሶፍት ጋር ሆኖ ለትርፍ ብቻ እየሮጠ ነው በሚል ተቆጥቷል።
ስሙም ተቀይሯል፦ ማስክ አሁን ሳምን "Sam Altman" ማለቱን ትቶ "Scam Altman" (አጭበርባሪው አልትማን) እያለው ይገኛል።
ጉዳዩን ስንታዘበው፦ 🧐 ይህ ንግግር እንዲሁ የመጣ ሳይሆን፣ ሁለቱ በኤፕሪል 2026 ፍርድ ቤት ሊገጥሙ ጥቂት ቀናት ሲቀራቸው የተሰነዘረ የስነ-ልቦና ጥቃት ይመስላል። የዚህ ፍጥጫ ውጤት በAI አለም ላይ ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ስለሚችል በቅርብ መከታተሉ አይከፋም።
በነገራችን ላይ ማስክ ሳምን እንዲህ ሲረታው የመጀመሪያው አይደለም፤ እናንተስ በማን ወገን ናችሁ? የማስክ ክስ እውነት ይመስላችኋል ወይስ የቢዝነስ ቅናት?
@ethiocrypto52
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
