قناة للْمࢪأة السلفية 𐙚
رفتن به کانال در Telegram
https://t.me/https_Aselefya وَمَن جَاهَدَ فَإِنَّمَا يُجَاهِدُ لِنَفْسِهِ ۚ إِنَّ اللَّهَ لَغَنِيٌّ عَنِ الْعَالَمِينَ
نمایش بیشتر1 544
مشترکین
-124 ساعت
-97 روز
-830 روز
آرشیو پست ها
🧷 ያልፋል ብለን እንደጠበቅን ብዙ ዘመናት አለፉ''
አሁንም ሀሳባችን አልቀየርንም "ያልፋል"
https://t.me/https_Aselefya
🧷﴿رَبَّنا لا تُزِغ قُلوبَنا بَعدَ إِذ هَدَيتَنا وَهَب لَنا مِن لَدُنكَ رَحمَةً إِنَّكَ أَنتَ الوَهّابُ﴾
https://t.me/https_Aselefya
🧷ሰላም......ለእነዚያ መልካም ልብ ላላቸው ጊዜ ለማይቀይራቸው ህይወት ለማታታልላቸው መንገድ ለማይለያያቸው ሰዎች..
https://t.me/https_Aselefya
~በዱንያ ላይ ስንኖር መፈተንና መውደቅ የለም ማለት አይደለም
➡ግዑዝ አይደለንም ይከፋናል እንወድቃለን እንሳሳታለን
↪የሠዎች ንግግር ይሠብረናልም ስራቸውም ደግመን ማገገም የማንችል እስከሚመስለን ድረስ ይሠብረናል
🏷ግን አማኝ አይደለን መልሠን ራሳችንን በተስፋ እንገነባለን ትላንት ላይ ያለፈው ነበር ያልነው ለዛሬ ብርሀን ለነገ ደግሞ ተስፋ ይሆነናል
💡በራሳችን ውስጥ ያለውን ተስፋ ለማለምለም ግን ካጠፋነው ጥፋት ራሳችንን ይቅርታ እንጠይቅ ከራሳችንጋ እንታረቅ
ለምን በሚል ፀፀት ራስጋ እንደመጣላት አክሳሪ የለም
እናማ ስንሳሳት ነፍሳችንን ይቅርታ ጠይቀን ጉዞ ወደፊት
https://t.me/+mLtckY6PZKFlNTRk
🧷ሰላም.....ለእነዚያ ከህይወታችን ሲገቡ እንደ አበባ ለሚያፈኩን ሰዎች..
https://t.me/https_Aselefya
﴿ وَلا تَيأَسوا مِن رَوحِ اللَّهِ إِنَّهُ لا يَيأَسُ
مِن رَوحِ اللَّهِ إِلَّا القَومُ الكافِرونَ ﴾
ከአሏህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ!!እነሆ ከሀዲያኖች እንጅ ከአላህ እዝነት ተስፋ አይቆርጡም
🎀
🧷ናፍቀሺኛል አትበል 🤚
የማይመስል ምክኒያት ደርሶ በመቆለል
መመለስ አስበህ ናፍቀሽኛል አትበል
አንተ እንደፈለከው ሲያሻህ ስትመጣ፣
ሲያሻህ ደሞ ስቴድ የሚሻል መረጣ ፣
ካኖርክባት ቦታ ቁማ ምጠብቅህ ፣
ያቺ የድሮዋ ያቺ የምቶድህ ፣
ትኖር የነበረች ያንተንም የሷንም ፣
ደስታ ምለግስህ ያለምላሽ ጥቅም፣
ነገ ላይ እንድረስ ዛሬን እንሻገር፣
ትልህ የነበረች ያንተዋ ገራገር፣
ያቺ የማትርቅህ በደግ በክፉ፣
ወዳጄ ያልካቼው እንዳላየ ሲያልፉ፣
አዎ ያንተዋ ሴት ህመምህ የሚያማት፣
አብራ ምታነክስ ላገኛህ እንቅፋት፣
ምቶደውን ወዳ ስጠላም ርቃ ፣
ወረት ሳይለውጣት የግዜ ፈረቃ፣
ቀድማ ምትሞትልህ ስላንተ ተጨንቃ፣
ያቺ የዋህ ጎንህ
ኗሪዋ እንዳመልህ
ድግምግም ጥፋትህ ሳያሳጣት ተስፋ፣
ፍቅሬን ቤቴን ስትል ዕልፍ ቀን ስገፋ፣
የሆዷን በሆዷ አፍና እንደምንም ፣
ስስቅ የምታቃት ፀብ እንዳይለመልም፣
ያቺ ሚስኪኗ ሴት የተውካት አቅለህ፣
የትም አቴድ ያልካት መውደዷን ኮንነህ፣
ላለፈችው ስቃይ ለቻለችው መአት
አሏህ ግፉን ቆጥሮ አስቦ ሊክሳት
አዲስ ሂዎት ሰጥቷት
ዛሬ ሌላ ሴት ናት አታውቃትም ከቶ
ፍፁም ተቀይራ ከልቧም ሰው ገብቶ
አንተን ላንተነትህ ለምኞትህ ትታ
ከነምናምንህ ትናንትን ረስታ
ሌላ አለም ውስጥ ናት የልኳን አግብታ
እናም እየውልህ
የማይመስል ምክኒያት ደርሶ በመቆለል
መመለስ አስበህ ናፍቀሽኛል አትበል
እውነታው ወዲህ ነው
ታውቃለህ አውቃለው
መመለስ ያሻኸው ሳይሆን ስለናፈክ
የኔ አይነት አተህ ነው ሁሌም ላንተ ኗሪ
እንዳልክ ይሁን ብላ ለሳቅ ደስታህ ጣሪ
ያንተን ቀን ለመውለድ የራሷን ቀባሪ
በቃ ስላጣህ ነው
አንተን የምችልህ ከናመልህ ባህሪ።
https://t.me/https_Aselefya
🧷اللهمَّ اجعل كل ما نسعى إليه من خير يسعى إلينا في خير و اجعله قريبًا غير بعيد و عاجلًا غير آجل يا واسع الفضل።
https://t.me/https_Aselefya
« التناقض علامة البطلان »
«መወናበድ የቡጥላን ምልክት ነው።»
ﺍﻷﺣﺒﺎﺵ ﻳﻘﻮﻟﻮﻥ ﻓﻲ ﺍﻟﺴﺠﻮﺩ " ﺳﺒﺤﺎﻥ ﺭﺑﻲ ﺍﻷﻋﻠﻰ " - ﻭﻓﻲ ﻧﻔﺲ ﺍﻟﻮﻗﺖ ﻳﻨﻜﺮﻭﻥ ﻋﻠﻮ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻰ ﻋﺮﺷﻪ ! ﻫﺬﺍ ﻣﻦ ﺗﻨﺎﻗﺾ ﺍﻷﺣﺒﺎﺵ ﻓﻲ ﺍﻟﻌﻘﻴﺪﺓ
አህባሾች በሱጁዳቸው ላይ እንዲህ ይላሉ፡-
" ﺳﺒﺤﺎﻥ ﺭﺑﻲ ﺍﻷﻋﻠﻰ "
«ጥራት የተገባህ ጌታዬ ሆይ የበላይ ነህ።»
በዛው ሰዓት አላህ ከዐርሹ በላይ መሆኑን ይቃወማሉ።
ይህ አህባሽ በዐቂዳ ዙሪያ መወናበዱን እና እርስበርስ መጋጨቱን ያስረዳል።
منقل
🧷መሰተር ትልቅ ውበት ነው
ሴት ልጅ ስትሰተር ነው ውድነቷ እንቁነቷ
ከርካሽ ቦታዎች ስትርቅ ያኔ ነው ውበቷ
ሀዕያ አይናፋርነት ጋር ስትርነቷን ስታሟላ
የውቦች ውብ የእንቁዎች እንቁ ምርጥ
ጀዋሂር የምቶነው።
https://t.me/https_Aselefya
🧷አንድ ወፍ አበባ ወደደ አሉ
አበባዋ ነጭ ነበረች "መልኬ ቀይ ሲሆን እኔም እወድሃለሁ አለችው" አሉ፣
ታድያ ወፉ ለወደዳት አበባ የትኛዉንም መስዋዕት ሊከፍል ዝግጁ እንደሆነ ሊያሳያት ወሰነ ክንፉን ቆረጠና ደሙን አፈሰሰላት አበባዋም ቀይ ሆነች።
አበባዋ ወፉ ምን ያህል እንደሚወዳት አወቀች።
ልትወደዉም ወሠነች
ግን ጊዜው አልፎ ነበር ዘገየ ወፉ በፈሰሰው ደም ብዛት የተነሳ ሞቷል💧
አብዝቶ ላሰበልህ አስብለት ቦታ ለሠጠህም ቦታ ስጠው የወደደህንም ሰው በፍቅሩ አታሹፍ ተረዳው
በጣም የወደደህን ሰው ካጣህ እንደርሱ የሚወድህ ሰው መልሰህ አታገኝም እወቅ። የተሰበረ ቀልብ መልሶ አይጠገንምና።💧
🎀
መልካም ሴት - ከዱንያ ጌጣጌጥ ሁሉ የላቀች ናት!
ቁርኣን እና ሐዲስ ምን ይላሉ?
ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል: "ዱንያ (ይች ዓለም) ጌጣጌጥ ናት፤ ከዱንያ ጌጣጌጥ ሁሉ በላጭ ደግሞ መልካም ሴት ናት።" (ሶሒህ ኢብኑ ማጀህ፣ 1516)
ይህ ሐዲስ ስለ መልካም ሴት ምንነት ጥልቅ ማብራሪያ ይሰጣል። ዱንያ በውስጧ ብዙ ፈተናዎችና ጌጣጌጦች ቢኖሯትም፣ ከሁሉም በላይ ግን መልካም ሴት ትበልጣለች።
ታዲያ መልካም ሴት ማለት ምን ማለት ነው?
መልካም ሴት ማለት ለአባቷ ኩራት፣ ለወንድሟ ክብር፣ ለባሏ ሀብት፣ ለልጇ ደግሞ ውድ ስጦታ ናት።
ወንድሞቼ:
የትዳር አጋር ስትመርጡ መልካም ሴትን ፈልጉ። ቁንጅናዋን ሳይሆን ስነ ምግባሯን ተመልከቱ።
እህቶቼ:
መልካም ሴት ለመሆን ትጉ። ለቤተሰቦቻችሁ ኩራት ሁኑ። ትልቅ ዋጋ እንዳላችሁ እወቁ።
በወንድማችሁ አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
