cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ያሲራ(ታጋሽ ሴት)

ለሁሉም ጊዜ አለው... 🙏🙏 ፩) አጫጭር ታሪኮች ፪) ግጥሞች . . .

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
260
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
+47 روز
+530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ዋጋ በኤልሳ [FB] ክፍል - 75 ..... ፊዮሪን እየሳማት ነው ከስራቸው ሴራሚኩ ላይ ተቃጥሎ እያለቀ ያለ ወረቀት አለ ... አይኔን ማመን አቃተኝ ደርቄ ቀረሁ ፊዮሪ በድንጋጤ ዘላ ተነስታ ጋውን ደረበች ቢንያም በፌዝ ፈገግታ እያየኝ ተነስቶ ፊቴ ከኋላዋ አቅፎ አንገቷን ሳማት... አይኔን ከማየት ውጪ ለማስተባበል አልሞከረችም ፊቷ የተረበሸ ይመስላል ግን ሲስማት ለመከላከል እንኳን አልሞከረችም... ራሴን ተቆጣጥሬ ምንም ሳልል ምንም ሳላደርግ በቀስታ ወጣሁ በድንጋጤ ዲዳ የሆንኩም መሰለኝ ድምፄን ለመሞረድ እንኳን አቅም አጣሁ መኪናዬ ውስጥ ገብቼ ቁጭ አልኩ ማሰብ ያቃተኝም መሰለኝ ተከትላኝ ልታስተባብል እንኳን አልሞከረችም ለነገሩ ምን የሚስተባበል ነገር አለ?... የስጦታ ማሸጊያውን ከነካርቶኒው በጫጭቄ ከፈትኩት ሀብሉን ትክ ብዬ ካየሁት ቦሀላ ጣቴ ላይ ጠመጠምኩት መጮህ አማረኝ የመኪናዬን የጋቢና በር መስታወት በቦክስ ስመታው ግማሹ ረገፈ እጄ ደማ አበባውን ወርወረወርኩት ትንፋሼን መቆጣጠር አቃተኝ አንዴ ጮህኩ እምባዬ መጣ መኪናዬን አስነስቼ ቀጥታ ወደቤት ሄድኩ የዮኒ መኪና ያለልማዱ በጊዜ ግቢ ውስጥ ቆሟል የኔንም አቁሜ ገባሁ ዮኒ ኳስ እያየ ነበር በደማው እጄ የፊዮሪን ስጦታ ሀብል ይዤ ሲያይ ቲቪውን አጥፍቶት ዝም ብሎ አየኝ ፊትለፊቱ ሶፋው ላይ ተቀመጥኩ " ም... ምን ተፈጥሮ ነው? " አለኝ የሆንኩትን ለሱ ለመናገር ገና ሳስበው እናቱ እንዳባበለችው ህፃን እምባ ቀደመኝ... አጠገቤ መጥቶ ሲያቅፈኝ እንደሴት ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ... ትንሽ ቆይቶ እልህ የሞላው ትንፋሽ ተናነቀኝ እምባዬን ጠርጌ መጠጥ ቀዳሁ " ተረጋጋና ንገረኝ እሲ " አለኝ ስሄድ ያየሁትን ነገርኩት እሱም ከኔ በላይ ግራ የገባው ይመስላል " ዱሮስ ሴት..." አለ እውነት ለመናገር ከዚህ በፊት ፊዮሪን በቀልድ እንኳን ከሱ ተራ ሴቶች ጋር አውርዶ ሲያያት ልጣላው የምደርስበት ጊዜ ይበዛ ነበር አሁን ግን ምንም ቅር አላለኝም እንደውም እሱ ከሀዲ ከሚላቸው ሴቶች የባሰች መሰለችኝ " ግን ምክንያቷ ምንድነው? ወይስ የበፊት ፍቅሯ አገረሸባት? " አለ " አንድ ቀን እንደምበቀልህ እርግጠኛ ነበርኩ ብላኛለች " አልኩት " መቼ? " " ሳንታረቅ በፊት ማለት የኔን እውነት ሳልነግራት " አልኩትአልኩት " እና በቀሉ ይሄ መሆኑ ነው? ደግሞ እንደዛ እንዳልል ድንገት ነው የሄድከው" አለኝ " ምናልባት ሰርጋቸው ላይ ልትነግረኝ ይሆናላ " አልኩት " ለማንኛውም አንተ ተረጋጋ ደብረዘይት ወይም ናዝሬት ቢያንስ ለ 1 ሳምንት ሂድና እረፍ" አለኝ በሀሳቡ ከመስማማት ውጪ አማራጭ የለኝም.. በማግስቱ የአንድ ሳምንት ጓዜን ጠቅልዬ ወደ ደብረዘይት ሄድኩ ያረፍኩበት ሎጅ ፀጥታው ከምንም በላይ ደስ ይላል ግን መርሳት የፈለኩትን ነገር ሊያስረሳኝ አልቻለም... ምክንያቱ ደግሞ የፊዮሪ ተደጋጋሚ ስልክ ጥሪ እና ቴክስቶች ነበሩ.. 27 missed call ይላል ስልኬ መደወል ብታቆም ብዬ አነሳሁት " ና...ናኦዴ " የተሰበረ የሚንቀጠቀጥ ድምፅ " አቤት " " ደጋግሜ ስደውል ስልክ አታነሳም እኮ በሰላም ነው? " " ምን ፈልገሽ ነው? " አልኳት " ናኦዴ ተገናኝተን ማውራት አለብን ትላንት ያየኸው ሁሉ እንደምታስበው አይደለም" አለችኝ " እና እንዴት ነበር?... እኔ ያላየሁት የቀረ ነገር ነበር?.... ወይስ ያልገባኝ ነገር ነበር?... ምን እያረጋችሁ ነበር? አስረጂኝ እስኪ ካልገባኝ... እ?..." ሲቃ ተናነቀኝ " እባክህ እንደዚህ አትሁን ተረጋጋ " " ፊዮሪ " " ወዬ " " ትወጂኛለሽ? እንደዛ ነው የምታስቢው? " " ከምታስበው ከማንም ከምንም በላይ" አለችኝ ፈጣጣነቷ አበሳጨኝ ውሸቷ እንደ ህፃን እና እንደማያስብ ሰው እያየችኝ በውስጧ የምታሽካካብኝ ማሽካካት ከአይነ ህሊናዬ አልፎ ለራሴ በጆሮዬ ተሰማኝ " አሁን ያልሽው እውነትሽን ከሆነ ቃል ግቢልኝ " አልኳት " በፈለከው በምን? " አለችኝ " በምቶጃት አያትሽ በ እናና " አልኳት " እናናን " አለችኝ " እባክሽ ድጋሚ አትደውዪ ቴክስት አትላኪልኝ አታውሪኝ ድጋሚ አይንሽን ማየት ድምፅሽን መስማት አልፈልግም " " ናኦድ ምን እያልክ ነው? " " ተሰብሬ ማየት እና ብድርሽን መመለስ ነበር የምትፈልጊው አይደል? ተሳክቶልሻል " " ናኦድ ምን እያልክ ነው? " " እንዳልሽው የምትወጂኝ ከሆነ በቃ ተዪኝ ካደረግሽው በላይ አይንሽን ማየትና ድምፅሽን መስማት ነው ይበልጥ የሚገለኝ... ለኔ ፍቅር አደለም ትንሽ ክብር ካለሽ እርሺኝ " ብያት ስልኩን ዘጋሁት ብዙም ሳትቆይ ደወለች... ስልኬን ዘግቼ ሻንጣዬ ውስጥ ከተትኩት.. ከ 7 ቀን ቦሀላ ዛሬ የመመለሻዬ ቀን ነው ካሰብኩት በላይ ተረጋግቻለሁ ድጋሚ አዲስ አበባን ሳያት ስለሚሰማኝ ስሜት ባላውቅም አሁን ግን ወደራሴ ተመልሻለሁ በፊት ለበደልኳት ቅጣቴ እንደሆነ አምኛለሁ ግን ድጋሚ ማሰብ ያቃተኝ ብቸኛው ነገር ፊዮሪን ማመንና ድጋሚ ማፍቀር ነው ሌላ ማንነት ያላት የሰላሜ ጠንቅ የሆነች ሴት ሆናለች ከሷ ፍቅር ውጪ በ አንድ ሳምንት ውስጥ ራሴን አረጋግቼ ወደነበርኩበት ተመልሻለሁ ስልኬ እንደተዘጋ ነው አመሻሽ ላይ በተረጋጋ መንፈስ ወደ አዲስ አበባ ተመለስኩ ቤት ስገባ 1 ሰአት ሆኗል ማንም የለም ስልኬን ቻርጅ ሰክቼ ስከፍተው ወዲያው የፊዮሪ ስልክ መጥራት ጀመረ... ድምፁን አጥፍቼ ሳሎን ተቀምጬ መጠጣት ጀመርኩ ቦታ ስቀይር ነው መሰል የበፊት ንዴቴ ተመልሶ መጣ ብዙም ሳይቆይ የሳሎኑ በር ሦስቴ ተንኳኳ ፊዮሪ ነች....... ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል... @fkerofficial
نمایش همه...
ይድረስ ለአባቴ አባዬ...... አባብዬ አንተኮነህ ለኔ ጀግናዬ አለምን ማያ መስታወቴ ከክፉ ማምለጫ ጋሻዬ። ታውቃለህ ግን አባ ሳስበው ሳስበው አንድ ነገር አለ ውስጤን የሚጨንቀው ይመስለኛልና ውለታህን ከፍዬ ማልዘልቀው። ለዛሬ ማንነቴ አንተ መስዋዕት ሆነህ ብርሀን የሰጠኸኝ እንደሻማ ቀልጠህ እኔን ለማሳደግ ከሰው ተራ ወተህ እንደ እኩያህ ሳትሆን በጣም ተጎሳቁለህ ለዚህ አብቅተህኛል አንተ እየተገፋህ ይድረስ ለአባቴ ✍️✍️ ንገሩልኝማ ስለ እሱ ስናገር በእንባ እንደምሞላ ፍቅሩንም ለመግለፅ ቃላት እንደማጣ ያረገልኝ ሁሉ ከውስጤ እንዳልጠፋ። ብቻ እድሜ ይስጥልኝ አምላኬ አደራ ደስተኛ ያርግልኝ ይስጠውና ጤና። 👨👨👨👨👨👨👨👨👨👨 ሁላችሁም ለ አባቶቻችሁ share አድርጉላቸው የናንተው @tsedi12m @yetbebaleme @yetbebaleme @yetbebaleme
نمایش همه...
❤‍🔥 1
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል - 74 ........"ቢንያም? " አልኩት " አዎ " አለኝ ስሙ ስሰማው ረበሸኝ " ከኛ ህይወት ጋር ምን ያያይዘዋል? " አልኩት " ምንም " አለኝ "እኮ " አልኩት " እና ለሰርግ ፕሮግራም ተዘጋጅ በለኛ " አለኝ " ያውም ስር ሚዜ ሆነህ ነዋ " አልኩት " ተአምረኛ ቀን ነው " አለኝ " ተአምረኛ ብቻ? " አልኩት " ለምን እራት አትጋብዛትም? " አለኝ " መቼ? " አልኩት " ዛሬ ነዋ ከዚህ ቦሀላማ ወደኋላ የለም " አለኝ " ልጠይቃት እንዴ? " አልኩት " ምነው ቅር አለህ? " አለኝ " ወይ ቅር ማለት " አልኩና ስልኬን አውጥቼ ደወልኩላት " ወዬ ናኦዴ " አለችኝ " ደህና አረፈድሽ? " አልኳት " ይመስገን እንዴት አረፈድክ? " አለች " አለሁ ማታ ከተመቸሽ ለምን ራት አልጋብዝሽም? " አልኳት " ዛሬ እንኳን አልችልም መሰረዝ የማይችል ቀጠሮ አለኝ " አለችኝ " እሺ በቃ ነገ " አልኳት " ነገ እችላለሁ " አለችኝ " እሺ " ብያት ስልኩ ተዘጋ " እ? " አለኝ ዮኒ ሁሌ የሚገርመኝ ፀባዩ ነው እኔ ለማደርጋቸው ነገሮችና ለሚገጥሙኝ ነገሮች ከኔ በላይ የሚጓጓውና የሚጨነቀው ነገር አለ " ነገ " አልኩት " አሪፍ ሀሳብ አለኝ " አለኝ " ምን? " አልኩት " ሀብል እንግዛና ማታ ከቀጠሮ ሰአቷ በፊት ቤቷ መሄዷ ስለማይቀር ሰርፕራይዝ አድርጋት " አለኝ " በጣም አሪፍ ሀሳብ" አልኩት ከቢንያም ጋር ወጥተን ውድ እና ቆንጆ ሀብል ገዝተን ተመለስን በመሀል ዮኒ " ቀጣዩ ስጦታ ቀለበት ነው የሚሆነው " አለ " እሱ ደግሞ መች ይሆን ይሆን? " አልኩት " ለምን ከሳምንት ቦሀላ አናደርገውም? " አለኝ " አይፈጥንም? " አልኩት " ምን ይፈጥናል? እናንተ እኮ የምትተዋወቁት ዛሬ አደለም እሷም አንተም ጋር የአመታት ፍቅር አለ " አለኝ " እሱማ አዎ " አልኩት " የምትወደውን ነገር የግልህ ለማድረግ ምንም ቀጠሮ አያስፈልግም " አለኝ " ልክ ነህ ስለዚህ የዛሬ ሳምንት ፕሮፖዝ አረጋታለሁ " አልኩት " ሚዜ ለመሆን እንዴት እንደቸኮልኩ አታውቅም " አለኝ " አሀ ለካ ለገዛ ጥቅምህ ነው " አልኩት "ምን ብጠቀም ብጠቀም ከሙሽራው በላይ አልጠቀም " አለኝ " እሱስ አዎ " አልኩት " እኔን እዚህ ጋር ጣለኝ " አለኝ አንድ ሞል ስር ስንደርስ " ምን ትሰራለህ እዚህ? " አልኩት " ክርስቲ ቀጥራኛለች " አለኝ " እውነት? " " አዎ ላወራህ እፈልጋለሁ ለመጨረሻ ጊዜ ብላለች " " አውሩ " አልኩት " እሺ ደውል " ብሎኝ ወረደ ህይወት የታገሱበትን ፍሬ የማትነፍግ መሆኗ እንደዛሬ ገብቶኝ አያውቅም ሲያልሙት ሲመኙት የኖሩትን ሰው የራስ ከማድረግ በላይ ምን እድለኛነት አለ? ህይወት እድልም ከሆነች ከኔ በላይ እድለኛ ሰው አለ ይሆን? እንጃ... በኔና በፊዮሪ መካከል የነበረው ትልቅ የድብብቆሽ ግርዶሽ ተገልጦ ፀጥ ብሏል... ፀጥ ያለ ሰላም...ፀጥ ያለ ፍቅር ስራዬ ላይ እንደተተከልኩ ከምሽቱ 1 ሰአት ሆነ ሀብሉን ይዤ ወደ ፊዮሪ ቤት መንገዴን ጀመርኩ ሀብሉን ሳደርግላት ምን ትል ይሆን? ቀጠሮዋን ሰርዛው ከኔ ጋር ታመሽ ይሆን? ተከታታይ ፊልም ላይ ራሱ ልቤ እንደዚህ ተንጠልጥሎ አያውቅም መኪናዬን ከውጪ አቁሜ በሩን አንኳኳሁ ዘበኛው ከፈተልኝ " ፊዮሪ አለች? " አልኩት " አዎ ግቡ " አለኝ " ሀብሌን በስጦታ መጠቅለያ ከ ቀይ ፅጌሬዳ አበባ ጋር ይዤ ገባሁ የሳሎኑ በር ያለወትሮው ተዘግቷል ሁለቴ ባንኳኳም የሚከፍትልኝ አጣሁ ከፍቼ ገባሁ ፊዮሪ ሳሎን የለችም በቀስታ ገብቼ ባስደነግጣትስ የሚል ሀሳብ መጣልኝ ኪችን አየኋት የለችም... ደረጃውን ወጥቼ መኝታክፍሏን ድንገት ከፈትኩት.. ቢንያም አልጋ ላይ ከወገቡ በላይ ራቁቱን ሆኖ ፊዮሪን እየሳማት ነው ..... ይ...ቀ...ጥ ...ላ...ል @fkerofficial
نمایش همه...
❤‍🔥 2
ሰው ከትልቁ ደግነቱ ይልቅ ትንሿን ስህተት ያያል የሰው ፍፁም ስለሌለ አትጨነቅ ሁሌም መልካም አድርግ ለህሊናህ ታመን🙌
نمایش همه...
🙏 3
ይናፍቃል ብዬ🤦‍♀ ይናፍቃል ብዬ ድምፄን ባጠፋበት ስሜንም እረሳው ሌላ ስም ተካበት ከናፈኩት ብዬ ገለል ብል ከፊቱ ለተከታታይ ቀን ስጠፋ ከቤቱ መናፈቁን ትቶ መፈለጉን ረስቶ ትዝታዬን ጥሎ ከደጁ አውጥቶ እኔን በሰው ተካኝ ልናፍቀው ቀርቶ እግሬ ከቤቱ በር መውጣቱን አብስሮ ልቡን አዘጋጅቶ ለሌላ እንጉርጉሮ አጠገቡ እያለሁ አልጠግብሽም ብሎኝ እግሬ ደጁን ሲረግጥ ወዲያውኑ እረሳኝ ከናፈቀኝ ብዬ የሰራሁት ፌቨር እኔኑ መልሶ ያስናፍቀኝ ጀመር@yoakinnn
نمایش همه...
👍 3 1
Abo ktywa😭
نمایش همه...
🙏 4❤‍🔥 1
ርዕስ በናንተ😁 አቤት........ፀባይህ ሲያስጠላ መልክህ....ሴት ከሴት ሚያጣላ ወንዱን.....በቅናት ዛር የሚያባላ እሷ.........ለውብ መልክህ ብታደላ አንተም.....ከዚህ ብቴድ ከዛች ገላ ከቆንጆዋ ባለ ዛላ እኔም......ምማታበት ባጣ ባላ እርር ቆሽቴን ላስታግሰው ጠጣው ጠላ።😁
نمایش همه...
3
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል 73 " ፊዩ እኔ ናኦድ ነኝ " " እና ማን መሆን ፈልገህ ነበር? " አለችኝ " አይደለም!.. ልልሽ የፈለኩት እኔ ያንቺ የመጀመሪያሽ ናኦድ ነኝ! " " ሀሀሀ የምርህን ነው? " አለችኝ የፌዝ ሳቅ እየሳቀች " የምሬን ነው.. ህያብ!" አልኳት ልጅ እያለን እኔ ብቻ የምጠራት ቅፅል ስም ነው ህያብ.. ፊቷ ግራ የመጋባት ስሜት ይታይበታል " ሰክሬ የነገርኩህን መልሰህ ነግረኸኝ ፕራንክ ልታረገኝ ነው ? አውቄብሀለሁ " አለችኝ እውነቱ እየገባት ግን ማመን እንዳልፈለገች ፊቷ ይናገራል ሸሚዜን አውልቄ ጀርባዬ ላይ ያለውን የስሟን ንቅሳት አሳየኋት ተመልሼ ስዞር ፊቷ ተቀያይሯል ጉንጯ ቀልቶ ደምስሯ ተገታትሯል " ና...ናኦድ..." አለችኝ ሸሚዜን መልሼ ቆለፍኩት አፏን ከፍታ ቀረች አይኗ ከመቅፅበት ያዘለውን እምባ ዱብ..ዱብ ማድረግ ጀመረ አፏን ገጥማ አይን አይኔን አየችኝ በቀስታ ተጠግቼ ላቅፋት ክንዷን ስይዛት በእጇ ክንዷን አስለቅቃኝ ለብቻዋ የእራት መመገቢያው ጠረጴዛ ላይ ተቀመጠች ተከትያት ልቀመጥ ስል " ውጣልኝ " አለችኝ ሳግ በተናነቀው ድምፅ " እንደዚህ ሆነሽ እንዴት ትቼሽ እሄዳለሁ? " ብያት ትከሻዋን ስነካት ፍንጥር ብላ ተነስታ " ብቻዬን መሆን እፈልጋለሁ... ውጣልኝ! " አለችኝ ስሜታዊ ሆና ሌላ ቃል ከምትናገረኝ ብዬ ልወጣ ስል " ግን ለምን ? " አለችኝ ቆምኩ " ከዚህ ሁሉ አመት ቦሀላ ድጋሚ ልትሰብረኝ መጣህ? " የመናገር እድሉን የሰጠችኝ መሰለኝ ተመልሼ አጠገቧ ተቀመጥኩ " " አንድ ቀን እንደማገኝህ እና እንደምበቀልህ እርግጠኛ ነበርኩ!... ግን በፍፁም በዚህ አይነት መልኩ ትመጣለህ ብዬ አላሰብኩም " አለችኝ " ላስረዳሽ የማስረዳት እድል ብቻ ስጪኝ " አልኳት " እየሰማሁህ ነው " አለችኝ " ፊዩ... ፕሪፓራቶሪ እያለን የሆነው ነገር ሁሉ እኔ እንደዛ እንዲሆን አስቤ አይደለም የሆነው.. ያኔ............................" እኔ ጋር የነበረውን ታሪክና አጣብቂኝ ምንም ሳላስቀር በአጣኋት አመታት ሳይቀር ምን ያክል እንተደጎዳሁ እምባዬን ሳልደብቅ ነገርኳት አይን አይኔን እያየች ስትሰማኝ ከቆየች ቦሀላ እምባዬን ጠርጋ አቀፈችኝ "ይቅርታ አድርጌልሀለሁ " ብላኝ ድጋሚ ካቀፈችኝ ቦሀላ መጠጥ አምጥታ ስንጠጣ ቆይተን ለመጀመሪያ ጊዜ ከፊዮሪ ጋር አደርን ጠዋት ከእንቅልፌ ስነሳ ፊዮሪ ክንዴ ላይ ተኝታ አንድ እጇን ደረቴ ላይ አድርጋ ተኝታለች "ፈጣሪ ሆይ ህልም አይደለም በለኝ " አልኩ ለራሴ ፊዮሪን ሳላገባት በፊት አንድም ቀን ልተኛት አስቤ አላውቅም ነበር እንቅልፍ ሲወስዳት ህፃን ነው የምትመስለው በህይወት መኖሯን ለማረጋገጥ አፍንጫዋ ስር ጣትን አስጠግቶ ካልተረጋገጠ ልክ እንደሞተ ሰው ትንፋሿ አይሰማም ለካ የዘመናት ህልሞችም እውን የመሆኛ ቀን አላቸው ዘላለም ከእንቅልፏ ባትነቃ ዘላለም ክንዴን ተንተርሳ እኔም እሷም ሳንነሳ ዘመናት ቢያልፉ ብዬ ተመኘሁ እንቅልፍ ሲወስዳት እንዴት ነው የምታምረው? " ጎምበስ ብዬ ስሚያት ቀና ስል ነቃች አይታኝ ፈገግ አለችና አፍራ ፊቷን አዙራ ተኛች ክንዴን ስትለቅልኝ እጄን አስጠግቼ ሰአቴን ሳየው 2:25 ሆኗል ተነስቼ ልብሴን ለብሼ ግምባሯን ስሚያት ወጣሁ እንደዛሬ ፈገግታ ከፊቴ ላይ አልጠፋ ብሎኝ አያውቅም ዝምብሎ ሳቅ ሳቅ ይለኛል የህይወት ዘመኔ ቋጠሮ ተፈቷል ህይወቴ ሙሉ የሆነበት ቀን አንድ ብዬ መቁጠር ጀመርኩ ከዚህ ቦሀላ ገና ብዙ ዘመናት እንደምቆጥር አምናለሁ... ቢሮ ስሄድ ቢሮዬን ክፍቱን አገኘሁት.. ስገባ ዮኒ ቀድሞኝ ገብቶ ነበር ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆይቶ " ኧ" አለኝ " ኧ" አልኩት " ተሳካ እንዴ? " አለኝ " ና እቀፈኝ ይሄ ሁሉ ያንተ ሀሳብ ነው " አልኩት ዘሎ መጥቶ ካቀፈኝ ቦሀላ " ምን ተፈጠረ ?... ንገረኝ በናትህ.." አለኝ ምንም ሳላስቀር ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ነገርኩት ከኔ በላይ ሲደሰት ሳየው ገረመኝ " አንተ ጋርስ አዲስ ነገር አለ? " አለኝ " እውነት ይሁን ውሸት ባላውቅም ቢንያም ከውጪ መጥቷል የሚባል ወሬ አለ " አለኝ " ቢንያም? " አልኩት ..... ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል @fkerofficial
نمایش همه...
👍 3
ዋጋ በኤልሳ[FB] ክፍል - 72 .............." ዮኒ " አልኩት ዝም ብሎ ሲያየኝ ቆይቶ " ቆይ ለምን? አላውቅህም ነበር ማለት ነው? ፌቩ እኮ ትወድህ ነበር አንተም የምትወደው ፊዮሪን ነው እንደማፈቅራት እያወክ ? ለምን? አለኝ " እመነኝ ዮኒ እኔ ፈልጌ የሆነ ምንም ነገር የለም ...... " አንድም ሳላስቀር ሁሉንም ነገርኩት " እንዴት ልመንህ ፍፁም የማይመስል እንግዳ ነገር እኮነው " አለኝ " ተጠራጠርከኝ? " አልኩት " አንተን ሳይሆን የምትለውን ነው መቀበል የከበደኝ " አለኝ " እሺ " አልኩትና ስልኬን ከጠረጴዛው ላይ አንስቼ ለክርስቲ ደወልኩላት...ተነሳ " ወዬ ናኦዴ " አለች " ስለትላንቱ ጉዳይ እንድናወራ እፈልጋለሁ " አልኳት "ምንድነው የምናወራው? " አለችኝ " ሁሉንም ማስረዳት አለብን ድብብቆሹ እዚህ ጋር ይበቃል " አልኳት " ድብብቆሹ ስትል አንተ የፊዮሪ የመጀመሪያ ናኦድ መሆንህንም ነው? " አለች " አታደርጊውም! የመጨረሻችን ነው የሚሆነው " አልኳት " መጀመሪያችን የማይሆን ከሆነ መጨረሻችን ቢሆን የሚሻል አይመስልህም? " አለችኝ " ኖ አይሆንም " አልኳት " በ30 ደቂቃ ውስጥ ወስነህ አሳውቀኝ አለበለዚያ ታውቀኛለህ " ብላኝ ዘጋችው ዮኒ ስልኬን ተቀብሎ ቁጥሩን አየው አይኑን ማመን አልቻለም " የምር ክርስቲ ነች? " አለኝ " አሁንስ? " አልኩት " ይሄን ሁሉ ጊዜ እያወክ ወደድኳት እያልኩህ እንዴት አስቻለህ? " አለኝ " ልነግርህ ብዙ ጊዜ ሞክሬ ነበር ግን ፈራሁ ምን ብዬ ልንገርህ? ምን ተብሎ ይነገራል? " አልኩት " አላውቅም ብቻ እንደፈለክ አርገህ ልትነግረኝ ይገባ ነበር እኔኮ ሳላፈቅራት ጀምሮ አንተን ብላ እንደመጣች ታውቅ ነበር.. እንዴት አስቻለህ እኔኮ የበላሁት የጠጣሁት የተነፈስኩት አይቀረኝም ስነግርህ.. ከመቼ ጀምሮ ነው አንተ እንደዚህ ድብቅ የሆንከው?" አለኝ " ዮኒ አንተኮ እኔ ሳላውቃት በፊት ነው ያወካት እኔ ቢሮ ሳትመጣ በፊት መኪናዋን ስትከተል እና ስታደንቃት ነበር " አልኩት " አድናቆት ነዋ! እንደዚህ አልሆንኩም ነበር ያኔ ብትነግረኝም እንደዚህ አይሰማኝም ነበር ልቤን ሰብራዋለች አንተም ሰብረኸዋል " አለኝ " እሺ ይቅርታ የፈለከውን!... የፈለከውን ! እሆናለሁ የፈለከውን ልቀጣ እባክህ አትቀየመኝ እማን! አልደግመውም " አልኩት በእናቴ ከማልኩ ራስክን አጥፋ ብባል እንኳን እንደማደርገው ያውቃል " እሺ ተስማምቻለሁ... በአንድ ነገር ልትስማማ በእናትህ ቃል ግባልኝ ከዛ እንደበፊቱ እንሆናለን " አለኝ " በምን? " አልኩት " ከፊዮሪ ጋር የጀመርነው ነገር በሆነ ምክንያት ባይሳካ ሌላ ሴት ልታገባ እድሜህን ላታቃጥል ቆመህ ላትቀር " አለኝ " ዮኒ " አልኩት እጁን ለመሀላ ዘረጋልኝ " አልችልም " አልኩት " ለምን? " አለኝ " እንደማደርገው እርግጠኛ አይደለሁማ አላደርገውምም በእማ እኮነው ማል ያልከኝ " አልኩት " እያስመረጥኩህ ያለሁት ከኔ ጓደኝነት እና ከቃል ኪዳኑ ነው ልታጣኝ የማትፈልግ ከሆነ ቃልህን ስጠኝ " አለኝ ነፍሴ ሁለት ቦታ ልትቀደድ መሰለኝ ፊዮሪ? ወይስ ዮናስ? የጓደኛ እና የፍቅር ምርጫ ለሁለተኛ ጊዜ ህይወቴ ውስጥ የመጣ መሰለኝ " ዮኒ አይሆንም እባክህ እንደዚህ አይነት ምርጫ አታስመርጠኝ " አልኩት " እሺ አትጨነቅ በቃ ፊትህ ይናገራል እኮ " ብሎኝ ተነስቶ ወጣ ደነገጥኩ ድጋሚ ብቸኝነቴን ለዘላለም ስከናነብ ተሰማኝ ገና ከመውጣቱ ቤቱ ሊበላኝ የደረሰ መሰለኝ ተከትዬው ወጣሁ... " ዮኒ " አልኩት ዞሮ ቆሞ አየኝ ተከትዬው ደረስኩበት " እሺ ቃል እገባልሀለሁ " አልኩት እጁን ዘረጋልኝ " እማን! " ብዬ መታሁለት ምንድነው ያደረኩት? ራሴን በገዛ ፍቃዴ እንደሸጥኩ ተሰማኝ ምክንያቱም በእማ ምያለሁ ግን ፊዮሪ ካልተሳካች ነው ያለው አለመሳካት ደግሞ ቁርጥ ያለ ድምዳሜ ይፈልጋል እኔ ደግሞ ተስፋ አልቆርጥም.... ተያይዘን ወደቤት ገባን ክርስቲ ደወለች አነሳሁት " ወሰንክ? " አለችኝ " ጊዜ ያስፈልገኛል ክርስቲ ቢያንስ ዛሬን " አልኳት " ከዛሬ ማታ ግን አያልፍም " አለችኝ " እሺ " ብያት ስልኩን ዘጋሁት " እኔኮ ሴት ስታጣ ብቻ ነበር የምትጠጣ የሚመስለኝ ወንድም ስታጣ ትጠጣለህ ለካ " አለኝ እየሳቀ ጠርሙሱን እያነሳ በቃ ዮኒ እንደዚህ ነው... ነገር ሲተው ሰከንድ አይፈጅም ጥቂት ኩርፊያ እንኳን ለቀጣዩ ደቂቃ አያስቀምጥም " አሁንም እኮ አጥቻለሁ " አልኩት " ለነገሩ ልክ ነህ የትላንቱ ቀን ለፊዮሪም ቀላል አልነበረም " አለኝ " ማለት? " አልኩት " ሰርፕራይዝ አለህ ያልኩህ ትዝ አለህ? " አለኝ " አዎ " " ትላንት ከፊዮሪ ጋር ሁሉንም አውርተን ነበር አንተ የመጀመሪያዋ ናኦድ ከመሆንህ ውጪ... ስለ ስሜትህ ስለሁሉም.. እና እሷም እንዳፈቀረችህ አመነች ከትላንት ወዲያ ነው ምናምን ከመሸ ደውላልህ ነበር መሰለኝ አይደል? " አለኝ " አዎ " አልኩት " በአካል ስለፈራች በስልክ እንደምታፈቅርህ ልትነግርህ ነበር " አለኝ " የምርህን ነው? " አልኩት " ትላንትም ቢሮህ የመጣነው በኔ ማደፋፈር እንደምታፈቅርህ ልትነግርህ ነበር ግን ያ ነገር ተፈጠረና ተበላሸ " አለኝ በራሴ ብግን አልኩ " ግን ይገርማል .. አሁን ምን ትዝ እንዳለኝ ታውቃለህ? " አለኝ " ምን? " አልኩት " በሰፈሩት ቁና አሉ " አለኝ " ምንድነው ተናገራ " አልኩት " ትዝ ይልሀል? እንደምታፈቅራት ልትነግራት ቀጥረሀት ቢኒን እንደምታፈቅረው የነገረችህ?... ያ ተገላብጦ በሷ ላይ የሆነ ነው የመሰለኝ " አለኝ " እውነትም... እንዴት መጣልህ ? " አልኩት ፈገግ ብሎ ዝም አለኝ አይመሽ የለ መሸ ለፊዮሪ ከሞት የመረረ እውነቴን ከነጠላ ቀይ ፅጌሬዳ ጋር ይዤ መኪናዬን እያከነፍኩ ቤቷ ደረስኩ ዘበኛው በሩን ከፈተልኝ " አለች? " አልኩት " አዎ " አለኝ መኪናዬን ሰፈር እንዳቆምኩት ገባሁ ሳሎን ስገባ ፊዮሪ ስስ ብርድልብስ ለብሳ ሶፋ ላይ ተቀምጣ ቲቪ እያየች ነው በረጅሙ ተንፍሼ ገባሁ ገብቼ ግምባሯን ስሚያት ተቀመጥኩ " ምን እግር ጣለህ ከመሸ? " አለችኝ የያዝኩትን አበባ ሰጠኋት " ለኔ ነው? " አለችኝ " አዎ " አልኳት ወደአፍንጫዋ ጠጋ አድርጋ ካሸተተችው ቦሀላ " ክርስቲስ? " አለችኝ " ከክርስቲ ጋር ምንም የለንም " አልኳት "ማለት? " አለችኝ የፌዝ ሳቅ እየሳቀች " ባለፈውም ሳልፈልግ ነው የሳመችኝ " አልኳት " ቀልደኛ አስራህ ነው አግታህ? " አለችኝ " አስፈራርታኝ " አልኳት " ማለት በምን? " አለችኝ " ዮኒን አጊንቼው ነበር ሁሉንም ነግሮኛል " አልኳት ደነገጠች " ማ... ማለት ሁሉንም ማለት?... ም.. " ሳትጨርስ በሌባ ጣቴ ከንፈሯን ይዤ "ሽሽሽሽ" አልኳትና ስለቃት ልታወራ ስትል ሳምኳት አበባውን ለቀቀችው እምባዬ መጣ ቀጥሎ የሚሆነውን ሳስብ ይሁን ደስታ ይሁን አልገባኝም " ምነው? " አለችኝ እምባ ያቀረረ አይኔን አይታ "አፈቅርሻለሁ ዛሬም በፊትም ወደፊትም " አልኳት " ማለት ክርስቲ..." " ክርስቲ ታፈቅረኛለች እንጂ አላፈቅራትም አንድ እውነት ላንቺ በመንገር አስፈራርታኝ ነው የሳመችኝ " አልኳት " የምን እውነት? " "ፊዮ.. እኔ ናኦድ ነኝ " ይ...ቀ...ጥ...ላ...ል @yoakinnn
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ውስጤ የሆነ አይነት ሀሳብ አለ የሆነ አይነት ፅሁፍ ወደ ውጭ ገንፍሎ መውጣት የሚፈልግ የሆነ አይነት ግንፍል ብሎ ወጥቶ በራሱ ከፅሁፌ ላይ ስፍር ማለትን የሚሻ አለ አይደል ማውራት መፃፍ ፈልጌ መውጣት ያቃተው አይነት ሀሳብ ምን ብል ይሆን የምትረዱኝ ጭንቅላቴን ቁጥር ሰውነቴን ውርር መላው እኔን ክብብ ያደረገኝ መፃፍ መስፈርን ያሻ ግንፍል ማለትን የሚመኝ ምን ብዬ ባስረዳችሁ ይሆን የምትረዱኝ እህ ገጥሟቹ አያውቅም የሆነ ጥግ ላይ አይኔን ትክል አድርጌ አንዳች ሀሳብ ላይ ዝፍቅ አብሮኝ ያለን ሰው እስከመርሳት ምን እንደሚያወራ ስለማላዳምጥ እ እ ምን አልከኝ የሚል ተደጋጋሚ እርቆ መሄድን እንዳስተናግድ ያደረገኝ የሆነ እራስ ምታት የሆነ ሀሳብ ወጣ አልወጣም ትንቅንቅ ውስጤ አስቦ ጨርሶ እጄ ጋር ሲደርስ ድንግርግር አንድ ፊደል ላይ ችንክር ብሎ መቅረት እ ምን ልል ነበር የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ እ ምን አልከኝ አልሰማሁም እኮ እያልኩ ከራሴ አልፌ ሌላን ማደናቆር እህ ምን ልል ነበር እንዴ እንዳሉት መነተልኩ ይሆን እንዳላችሁት ነኝ ብዬ አምኜ መቀበሌን ውስጤ አመነ እንዴ እውነትም መንትያለው ብታዩ እራሴን ለማስረዳት እጄን ማወራጨት ጀመርኩ እኔ ከኔ ፊት ነው እንዴ የቆምኩት
نمایش همه...