cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ትምህርት ሚኒስቴር - Minstry Of Education Ethiopia

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
5 455
مشترکین
+2024 ساعت
+697 روز
+99630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

#MoH በአገር አቀፍ ደረጃ ሲሰጥ የነበረው የጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና ተጠናቋል። የጤና ባለሙያዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈተና በሃገር አቀፍ ደረጃ ግንቦት 15 እና 16/2016 ዓ.ም በተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች ተሰጥቷል። ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Health Officer, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Technology, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatrics Nursing እና Emergency & Critical Care Nursing ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቁ የጤና ባለሙያዎች በኮምፒውተር በታገዘ የፈተና አሰጣጥ ስርዓት ፈተናውን ወስደዋል። ✅የትምህርት ሚኒስቴር  የተረጋገጡ ዜናዎችን ለሌሎች ያጋሩ! @education_Minstry @education_Minstry
نمایش همه...
👍 10
ዛሬ ይጠናቀቃል! የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን እንዲልኩ የተሰጣቸው ጊዜ ዛሬ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም ያበቃል፡፡ ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ መግለፁ ይታወቃል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 12 5
#NationalExam #Online ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና መንግሥት በሚያዘጋጃቸው ኮምፒውተሮች እንደሚከናወን የሀገር አቀፍ ትምህርት፣ ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኢቢሲ ገልጿል። አንዳንድ ወላጆች " በኦንላይን ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና የመፈተኛ ኮምፒውተር እንድናቀርብ ተጠይቀናል " ብለዋል። አገልግሎቱ ግን ይህንን በሚመለከት ለትምህርት ቤቶች ያስተላለፈው መልዕክት እንደሌለ እና ወላጆች መጠየቃቸውም ተገቢ አለመሆኑን ገልጿል። የኦንላይን ፈተናው መንግስት በሚያዘጋጀው አቅርቦት እንደሚከናወን አመልክቷል። ተማሪዎች ለፈተና ሲመጡ የሚጠበቅባቸው አንብቦ እና በቂ ዝግጅት አድርጎ የተመዘገቡበትን መታወቂያ ይዞ መምጣት ብቻ ነው ብሏል። ነገር ግን ትምህርት ቤቶችም ሆኑ ተማሪዎች የግል ኮምፒውተሮቻቸውን ለፈተናው መጠቀም ከፈለጉ #እንደማይከለከሉ አገልግሎቱ አሳውቋል። ሁሉም ተማሪዎች በኦንላይ እንዳይፈተኑ የመሰረተ ልማት አለመሟላት እንቅፋት ሊሆን ስለሚችል ዘንድሮ #በተወሰኑ ተማሪዎች ብቻ እንደሚጀመር ገልጿል። በሌላ በኩል ፥ በወረቀት ለሚሰጠው ፈተና የህትመት ስራው ወደ #መጠናቀቅ መቃረቡን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ለኢቢሲ በሰጠው ቃል አመልክቷል። ይህ እንዴት ይታያል ? የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በኦንላይን ለሚሰጠው ፈተና  " ትምህርት ቤቶች ሆኑ ተማሪዎች #የግል_ኮምፒዩተራቸውን ለፈተና መጠቀም አይከለከሉም " ብሏል። ተማሪዎች የራሳቸውን ኮፒዩተሮች ይዘው ሲገቡ በውስጡ ለፈተና ደህንነት የሚያሰጋ ወይም ፈተናውን እንዲሰሩ የሚያግዛቸው የተለያየ ዶክመት ተደብቆበት እንዳልሆነ የሚረጋገጥበት ምን አይነት መንገድ እንዳለ አልተብራራም። ሌላው ተፈታኞች በፈተና ወቅት በኢንተርኔት ድረ ገጾችን በመጎብኘት ጥያቄ የሚሰሩበት መንገድ እንዳይኖር ስለሚወሰደው የጥንቃቄ እርምጃ የተብራራ ነገር የለም። መሰልና ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮች ችግር ይዘው እንዳይመጡ ከወዲሁ ማሰብና ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
نمایش همه...
👍 11 5👏 1
#ETA የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰኔ ወር 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎቻቸውን መረጃ እስከ ግንቦት 16/2016 ዓ.ም እንዲያስገቡ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን አሳስቧል። ተቋማቱ የተፈታኞቻቸውን መረጃ ትምህርት ሚኒስቴር ያዘጋጀውን ቴምፕሌት በመጠቀም መላክ እንዳለባቸው ባለሥልጣኑ አስታውሷል። (የባለሥልጣኑ መልዕክት ከላይ ተያይዟል።) @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 4👏 4😁 3🥰 2
Photo unavailableShow in Telegram
ትምህርት ሚኒስቴር የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን አሳወቀ። በ2016 ዓ/ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ተፈታኞች ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 እስከ 21/2016 መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። የአገልግሎት ክፍያ  500.00 ብር በ ' ቴሌ ብር ' ብቻ የሚፈጸም መሆኑ አስገንዝቧል። #ለመጀመሪያ_ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማቸው በኩል መሆኑን የገለጸው ሚኒስቴሩ አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎችን በተቋማቸው በኩል እንደሚደርሳቸው አሳውቋል። @tikvahethiopia
نمایش همه...
👍 4🔥 1👏 1
#ይለማመዱ በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና #በኦንላይን የሚወስዱ ከሆነ ፈተናውን የሚወስዱበት አድራሻ ላይ በመግባት መለማመድ ይጀምሩ፡፡ ተፈታኞች ከተደለደላችሁበት ክላስተር ውጪ ሲስትሙን መጠቀም እንደማትችሉ ያስታውሱ፡፡ በተለያዩ ቦታዎች ዘንድሮ የመልቀቂያ ፈተናውን የሚወስዱ የበይነ መረብ ተፈታኞች ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል፡፡ ፈተናው የሚሰጥባቸው አድራሻዎች፦ 👉 https://c2.exam.et 👉 https://c3.exam.et 👉 https://c4.exam.et 👉 https://c5.exam.et 👉 https://c6.exam.et (ተፈታኞች የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ በተያያዘው ምስል ላይ ይገኛል፡፡) @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 10 6👏 3
#Update የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆኗል፡፡ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ብቻ ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡ ስለሆነም ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድርግ አስፈላጊ በመሆኑም ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የበይነ መረብ ተፈታኞች ባሉበት ሆነው ልምምድ ማድረግ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር የተላከውን የይለፍ ቃል እና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡ በዚሁ መሠረት መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡ ተፈታኞች ከተደለደሉበት ክለስተር ውጪ ሲሰትሙን መጠቀም #እንደማይችሉ አገልግሎቱ አሳስቧል። (ፈተናው የሚሰጥበት አድራሻ እና ተፈታኞቹ የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ ተያይዟል።)
نمایش همه...
17👍 10🔥 1
Photo unavailableShow in Telegram
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የ Social and Behavior Change (SBC) ትምህርት በድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ደረጃ መስጠት ሊጀምር ነው፡፡ ዩኒቨርሲቲው የፕሮግራሙን ማስጀመሪያ መርሐግብር አከናውኗል፡፡ በፕሮግራሙ ስርዓተ ትምህርት ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡ ፕሮግራሙ ተማሪዎች የማኅበራዊ እና ባህሪ ለውጥ ፕሮጀክቶችን በአግባቡ ለመተግበር የሚያስችላቸውን ዕውቀትና ክህሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው፡፡ ፕሮግራሙ በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና በዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ትብበር የተጀመረ ሲሆን የ SBC የልህቀት ማዕከል በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ መቋቋሙም ታውቋል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 14 6🔥 5
Photo unavailableShow in Telegram
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አመራረጥ አዲስ መመሪያ በመዘጋጀት ላይ እንደሚገኝ ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡ ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሃብት ብክነት እና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ አስተያየታቸውን ለፋና ቴሌቪዥን የሰጡት ትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እንደገለፁት፤ በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የሱፐርቪዥን ቡድን በመላክ ዩኒቨርሲቲዎቹ ያሉባቸውን ችግሮች መጠናቱን ገልፀዋል፡፡ "ዩኒቨርሲቲዎች የብዙ ደሃ ሕዝብ ሃብት የሚፈስባቸው ቦታዎች ናቸው" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ስለዚህ ተቋማቱ በሙስናና ብልሹ አሰራር የተጨመላለቀ አስተዳደር ሊኖራቸው አይገባም ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች በዋናነት የተማረ የሰው ኃይል ከማምረት ይልቅ፣ ህንጻ ማምረት ላይ የተሰማሩ ተቋማት እንደነበሩ ያስታወሱት ሚኒስትሩ፤ "ዩኒቨርሲቲዎች የሚታለቡ የጥገት ላሞች ናቸው" የሚለው የአንዳንድ ግለሰቦች አባባል አሁን ላይ አይሠራም ብለዋል፡፡ ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ ከፍተኛ አመራሮች በሙሉ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የሚያዝ የገንዘብ ሚኒስቴር መመሪያ መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ኃላፊዎቹም በህግ የሚጠየቁበት አግባብ መኖሩንም አክለዋል፡፡ ይህንን አሰራር በመከተል "ሦስት ጊዜ መጥፎ የኦዲት ግኝት ያለበት ዩኒቨርሲቲን የሚመሩ አመራሮችን በሙሉ እንቀይራለን" ሲሉ ተናግረዋል፡፡ @tikvahuniversity
نمایش همه...
👍 14 3🔥 3
Photo unavailableShow in Telegram
"የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና መቼ ይሰጣል" የሚሉ በርካታ ጥያቄዎች ደርሰውናል፡፡ የሪሚዲያል ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ብቻ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል፡፡ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ባደረገው ማጣራት የሪሚዲያል ፈተና ከሰኔ 1-7/2016 ዓ.ም ወይም ከሰኔ 8-14/2016 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ ዘንድሮ ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሪሚዲያል ትምህርታቸውን ከታህሳስ ወር ጀምሮ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም፡፡
نمایش همه...
👍 13 5🔥 1