cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ድምፀ ተዋሕዶ

ይህ መንፈሳዊ ቻናል መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ ማንኛውንም ታማኝ ኦርቶዶክሳዊ የሆኑ የቤተ ክርስቲያን መረጃዎችን እና መንፈሳዊ ክንውኖችን ለምእመኑ በፍጥነት፤ በጥራት ያቀብላል። የእግዚአብሔር ጸጋ እና በረከት በሁላችን ላይ ይደር። ድምፀ ተዋሕዶ ለንደን ለታማኝ መረጃዎ

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
11 105
مشترکین
-1924 ساعت
+407 روز
+37730 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
እንኳን ለ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካል አመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።መልካም በዓል። ✅ድምፀ ተዋሕዶ
نمایش همه...
9🙏 2🕊 1
ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ የሠራቸውን የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ባርከው መረቁ። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ  የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠበቂ የቦሌ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ  የሠራቸውን የተለያዩ ልማት ሥራዎችን ባርከው መረቁ። ብፁዕነታቸው በደብሩ የተሠሩትን የመንፈሳዊ ተልእኮውን የሚያግዙ የልማት ሥራዎችን  በዛሬው ዕለት የገበኙ ሲሆን  ከብፁዕነታቸው ጋር ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ  የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አክኪያጅ  መልአከ ብርሃን ሩፋኤል የማነ ብርሃን  የቦሌ ለሚ ኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጅ  መልአከ ፀሐይ አባ ገብረ ሥላሴ ሀብተ ማርያም የደብሩ አስተዳዳሪ፣ የሀገረ ስብከትና የክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት የሥራ ሐላፊዎች፣ የደብሩ የሰበካ ጉባኤና የልማት ኮሚቴ አባላት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣  የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን የአካባቢው ምዕመናን ተገኝተውበታል። በቦሌ ደብረ ምሕረት  ቅዱስ ሚካኤልና ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር  አቶ ተክለ መድኅን  ስለተሠራው የልማትና  ሥራ  አጠቃላይ ዝርዝር ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን  ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደተረገባውም አብራርተዋል። የተሠሩት የልማት ሥራዎች  ሁለገብ  ባለሁለት ወለል(G+2) ሁለገብ ሕንጻ፣ የግቢው የኮብል ድንጋይ ንጣፍና ከቅዱስ ሚካኤል ወደ ጻድቁ አቡነ ጎርጎርዮስ ቤተ ክርስቲያን የሚወስድ  ደረጃ መንገድ መሆናቸውን ገልጸዋል። ምክትል ሊቀ መንበሩ አክለውም በዚሁ ቤተ ክርስቲያናዊ ሥራ ከበጎ ምላሽና ክትትል ጀምሮ የተረባረቡትን፣ በጸሎት በአስተያየት፣ በገንዘብ፣በጉልበትና በቀና ልብ ድጋፍ ያደረጉትን  ሁሉ አመስግነዋል። በቀጣይም ባለ ዐሥር ወለል (G+10) ሕንጻ የሕክምና ማዕከል፣ ባለ ሃያ ወለል(G+20)  ሕንጻ ለኪራይ አገልግሎት የሚውል መኖሪያ ቤትና ሌሎች ልማቶችን ለመሥራት  በዝግጅት ላይ መሆናቸውን የገለጹ ሲሆን በዚህም ሀገረ ስብከቱ ክፍለከተማ ቤተ ክህነቱ የደብሩ ማኅበረ ካህናትን ምዕመናን ከጎናቸውን እንዳይለዩ  ጠይቀዋል። ብፁዕነታቸው አገልግሎቱን ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ላደረጉልን አባታዊ ክትትሎና ድጋፍ እናመሰግናለን ያሉት  የደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ አባ ገብረ ሥላሴ ሀብተ ማርያም በቀጣይም ለምናከናውናቸው ቤተ ክርስቲያን ተኮር ልማቶች አባታዊ  ክትትሉና ድጋፉ  እንዳይለያቸው  ተማጽነዋል። የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በበኩላቸው በብፁዕነታቸው  መመሪያ ሰጭነትና  አባታዊ ክትትል  መንፈሳዊ ተልእኮውን የሚያግዙ ሁሉን አቀፍ ልማቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ገልጸዋል። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ  በሰጡት ቃለ ምዕዳንና ቡራኬ የዛሬ ዓመት መምጣታቸውን አስታውሰው  የተሰጡት መመሪያዎች በተግባር በመዋላቸው ከደብሩ አስተዳዳሪ መልአከ ፀሐይ አባ ገብረ ሥላሴ ሀብተ ማርያም ጀምሮ በልማቱ የበኩላቸዝን ድርሻ የተወጡትን የሰበካ ጉባኤ አባላትን የልማት ኮሚቴ ማኅበረ ካህናቱን፣ ሰንበት ተማሪዎችን እንዲሁም  የአጥቢያው ምዕመናንን እናመሰግናለን ብለዋል። ብፁዕነታቸው የሆስፒታል፣የትምህርት ቤትና የመኖሪያ ቤት የልማት ሥራዎችን ለመሥራት መዘጋጀታችሁ  እጅግ  የሚበረታታ መሆኑ የገለጹ ሲሆን ጊዜ ሳይሰጠው ወደ ሥራ እንድትገቡና ትውልዳዊውና ቤተ ክርስቲያናዊውን  መልካም ልማት  በአፋጣኝ ተግባር ላይ እንዲውል  በጥብቅ አሳስባለሁ ብለዋል። ሀገረ ስብከቱ ከስብከተ ወንጌል ቀጥሎ  ትኩረት  የሚሰጠው ለራስ አገዝ ልማት መሆኑን የተጠቀሱ ሲሆን ከመንፈሳዊ አገልግሎቱ በተጨማሪ የብዙ ወጣቶች ሥራ ዕደል እንዲፈጠር ቤተ ክርስቲያን የበኩሏን ድርሻ መወጣት ይኖርባታል ብለዋል። ቀጥለውም የደብሩ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ከአገልግሎቱ ስፋት ከተገልጋዩ ብዛት እንዲሁም ከትውልዱ አኳያ ግንዛቤ ተወስዶ አዲስ ሰፊና ዘመኑን የሚናገር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን እንዲሠራ መመሪያ አስተላልፈዋል። በመጨረሻም ደብሩ በሚያደርገው  የቅዱስ ወንጌል አገልግሎትና የራስ አገዝ ልማት እንቅስቃሴ  ሀገረ ስብከቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግል  ብፁዕነታቸው ገልጸዋል። በደብሩ  የልማት  ሥራ  አገልግሎት ሰፊ  ሚናቸውን ለተወጡና ለደገፉ አካላት ከብፁዕ አቡነ ሄኖክ  ጀምሮ የደብሩ አስተዳዳሪ፣ ምክትል ሊቀ መንበሩ እና ልዩ ልዩ  አገልጋዮችና ምዕመናን ሽልማትና የዕውቅና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል። ✅የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ምን አይነት መዝሙሮችን ይፈልጋሉ?👇👇👇
نمایش همه...
ቆየት ያሉ ዝማሬዎች
አዳዲስ ዝማሬዎች
የንስሐ መዝሙሮች
የቸብቸቦ መዝሙሮች
ሁሉንም በአንድ ላይ
በዩኬና አየርላንድ ሀገረ ስብከት በርሚንግሀም ደብረ መድኃኒት ቅዱስ አማኑኤል የ፳፻፲፮ ዓ:ም ዕርገተ ክርስቶስ በዓል በአከባቢው ያሉ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያንና ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከበረ።
نمایش همه...
👍 2 1
የጋሞ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ልማት 24ተኛ ዓመት ምሥረታ በዓሉን አከበረ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የጋሞ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ልማት በጋሞኛ ቋንቋ ስብከተ ወንጌል አስተባባሪ ኮሚቴ የተመሠረተበትን 24ተኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት አክብሯል። ሰኔ 9 ቀን 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽርሐ ተዋሕዶ አዳራሽ በተካሄደው የ24ተኛ  ዓመት የምሥረታ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖና ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች እና በርካታ ምእመናን ተገኝተዋል። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በመድረኩ ባስተለለፉት መልእክት "የጋሞ ጎፋ ማኅበረሰብ በሃይማኖቱ እና በባሕሉ ጸንቶ የሚኖር ጠንካራ ህዝብ መሆኑን" ተናግረዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም " አስተባባሪ ኮሚቴው ፣ የአካባቢው ምእመናን የቅድስት ቤተክርስቲያንን አገልግሎት እንዲያገኙ ሕንጻ ቤተክርስቲያንን በማስገንባት ፣ ብሎም የአካባቢው ኦርቶዶክሳውያን በሚሰሙት ቋንቋ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲሰሙ ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች የሚበረታቱ እና ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው " ብለዋል። አስተባባሪ ኮሚቴው በ24 ዓመታት ጉዞው ውስጥ በጋሞ ሀገረ ስብከት የተለያዩ አካባቢዎች ሕንጻ ቤተክርስቲያን በሌለባቸው ስፍራዎች ቤተክርስቲያን በመገንባት እና የአካባቢው ማኅበረሰብ በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል እንዲደርሳቸው ልዩ ልዩ ሥራዎችን በማከናወን የተመሠረተበትን 24ተኛ ዓመት ለማክበር በቅቷል። ይሁን እንጂ ማስተባበሪያው የአካባቢውን ኦርቶዶክሳውያን በተለይም በጠረፋማ አካባቢዎች የሚገኙ ምእመናን ጠቃሚ የሚያደርጉ ዓይነተ ብዙ ሥራዎችን ቢሠራም ቋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ ባለመኖሩ በሚሰጠው አገልግሎት ላይ ተግዳሮት እንደሆነበት በመርሐ ግብሩ ላይ ተነስቷል። የአገልግሎቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥና  የሚስተዋለውን ችግር ለመቅረፍ ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በመድረኩ ጥሪ የቀረበ ሲሆን በመርሐ ግብሩ ላይ ለቅዱስነታቸው የማስታወሻ ሥጦታ ተበርክቶላቸዋል። ✅ ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ቴቪ ነው።
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
አባ ፍራንሲስ “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” አሉ አባ ፍራንሲስ ለኮሜዲያኑ "በፈጣሪ ላይ እንኳን መሳቅ ትችላላችሁ፣ ይህ መናፍቅነት አይደለም” ብለዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” በማለት ለተሰበሰቡት ታዋቂ ኮሜዲያኖች እንዲሁም አርቲስቶች ነበር የተናገሩት። አባ ፍራንሲስ ከመላው ዓለም ከተውጣጡ ከ100 በላይ ኮሜዲያን፣ የፊልም ተዋናዮች እና ጸሃፊዎችን በትናንትናው እለት በቫቲካን አግኝተው አነጋግረዋል። ከአባ ፍራንሲስ ጋር ከተገናኙ ታዋቂ ሰዎች መካከልም የአሜሪካ ታዋቂው የሾው ቢዝ አቅራቢ ውሁፒ ግልድበርግ፣ ጂሚ ፋሎን፣ ካነን ኦበሪየን፣ ክሪስ ሮክ እና ስቴፈን ኮልበርት እንደሚገኙበት ሮይተርስ ዘግቧል። በዚሁ ወቅት በጣሊያንኛ ንግግር ያደረጉት አባ ፍራንሲስ "በፈጣሪ ላይም መሳቅ እችላለን” ያሉ ሲሆን፤ ይህ ስድብ አይደለም እኛ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር እንደምንጫወት እና እንደቀልድ ሁሉ በፈጣሪ ላይም እንችላለን” ሲሉ ተደምጠዋል። “የሚያስከፋ እስካልሆነ ድረስ ስለ ፈጣሪ መቀለድ ችግር የለውም” ያሉት አባ ፍራንሲስ፣ “እያልኩ ያለሁት ነገር መናፍቅነት አይደለም፤ በአንድ ሰው ከንፈር ላይ እንዴት ፈገግታን መፍጠር እንዳለብህ ካወክ እና አንድን ሰው ፈገግ ካሰኝህ፤ እግዚአብሄርም እንዲስቅ ታደርጋለህ” ብለዋል። የሮማው ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ 30 ደቂቃ ከፈጀው እና ከመስመር ወጣ ያለ ነው የተባለውን ንግግራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ከኮሜዲያኖቹ ጋር እየተጨባበጡ ተቀላልቀደዋል። የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ አባ ፍራንሲስ በተደጋጋሚ በሚሰጧቸው ለየት ባሉ እና አነጋጋሪ አስተያየታቸው ይታወቃሉ። አባ ፍራንሲስ ከቀናት በፊት ቄሶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት በተቻለ መጠን አጭር እንዲያደርጉ ማሳሰባቸው ይታወሳል። አባ ፍራንሲስ አክለውም ለማስቀደስ እና ሌሎች በረከቶችን ለማግኘት ብለው ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጡ የዕምነቱ ተከታዮች በቄሶች አገልግሎት መርዘም ምክንያት እንቅልፍ እየጣላቸው ነው ብለዋል። ቄሶች ስለ ጌታ ከመጽሃፍ ቅዱስ ላይ ለምዕመናን የሚያስተምሩበት ጊዜ ከስምንት ደቂቃ መብለጥ የለበትም ሲሉ ሊቀ ጳጳሱ ተናግረዋል። ✅አል አይን የእግርጌ ማስታወሻ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መስመር ከሳተች ቆይታለች።ይልቅ አሁን ላይ ለተከታዮቻም ሆነ ውጪ ላለው ሰው በመጥፎ ዝንባሌዋ እና ወቅታዊ ልማዷ አስጊ እየሆነች ነው።
نمایش همه...
2🤔 2😢 2
01:44
Video unavailableShow in Telegram
አርባ ምንጭ ከተማ እንዲህ ባለ ድምቀት ብጹአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በልጅነት ክብር ተቀብላ ተባርካለች። ሁሌም ሙቀቱ የማይለየው የደቡብ ህዝብ ዛሬም አባቶቹን በክብር ተቀብሏል።በተለይ አርባ ምንጭ ብዙ ያልተደረገለት ብዙ ሊሰራበት የሚገባ ሀገረ ስብከት ነው።
نمایش همه...
27.85 MB
4🙏 2👍 1
ስርዓተ ጥምቀት ፈጽመው 123 ሰዎች ወደ ከኦርቶዶክሳዊ በረት ተጨምረዋል:: በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጲያ ክልል በሸካ ቤንች ሸኮ ምዕራብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በቤንች ወረዳ ቤተ ክህነት በምትገኘው በቲሹ ደብረ ገነት ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን በትናንትናው ዕለት ሰኔ 6/2016 ዓ/ም 123 ነፍሳት ሀብተ ወልድ እና ስመ ክርስትናን አገኙ።
نمایش همه...
11🙏 2👍 1😁 1
ስደተኛው ተመራቂ፤ “ብፁዓን እለ ይሰደዱ በእንተ ጽድቅ፥እስመ ሎሙ ይዕቲ መንግሥተ ሰማያት።ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፥መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።”ማቴ፡፭፥፲። ሊቀ ማዕምራን ፈንታሁን ሙጬ የቤተ ክርስቲያኒቱን መደበኛ ትምህርት ዜማውን አቋቋሙን እና ቅኔውን ከሕፃንነቱ ጀምሮ “በእንተ ስማ ለማርያም” እያለ ቁራሽ እንጀራ እየለመነ፥ ከመቃብር ቤት ደንጊያ ተንተርሶ እየተኛ እስከ ጥግ ድረስ ተምሮአል።የእናቱን ፍትፍት እየጎረሰ፥በአባቱ እጅ እየተዳበሰ አላደገም።ያደገው በደጀ ሰላም ፍርፋሪ ነው፥የቤተ ክርስቲያን ፍርፋሪ ደግሞ ስመ እግዚአብሔር የተጠራበት፥ቃለ እግዚአብሔር ያረፈበት፥በመስቀለ ክርስቶስ የተባረከ፥ምእመናን በሃይማኖት ያቀረቡት በመሆኑ መድኃኒት ነው። በዘመናዊም የከፍተኛ ፪ኛ ደረጃ ትምህርቱን በከፍተኛ ውጤት ካጠናቀቀ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መግባት ቢችልም ፈቃደ ነፍሱን በማስቀደም ወደ ቅድስት ሥላሴ ቴኦሎጂ ዩኒቨርስቲ በመግባት የመጀመሪያ ድግሪውን ይዟል።ይህ ለቀለም ቀንድነት የተፈጠረ ወንድማችን በዚሁ ይበቃኛል ሳይል ከውጭ ሀገር የኒቨርስቲዎች ጋር በመጸጻፍ በግል ጥረቱ የነፃ ትምህርት ዕድል በማግኘቱ ወደ አውሮፓ በመጓዝ ሁለተኛ ድግሪውን ሠርቶአል። ከሁሉም የሚደንቀው በዚያው እንዲቀር ብዙ ግፊቶች ቢኖሩበትም “የቤተ ክርስቲያን ውለታ አለብኝ፤”በሚል ቀና መንፈስ ወደሚወዳት ሀገሩና ወደሚመካባት ቤተ ክርስቲያኑ በመመለስ በተለያዩ ሃላፊነቶች እናት ቤተ ክርስቲያኑን አገልግሎአል። እንደሚታወቀው የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት አልጋ በአልጋ ሳይሆን በቀኖት ላይ የመረማመድ ያህል ነው። የቀን ዕረፍት የሌሊት እንቅልፍ አይሰጥም።ቢሆንም የጽድቅ ጉዳይ ስለሆነ ሁሉንም በጸጋ ተቀብሎታል። እንደገናም ከቤተሰብ አስተዳደር ጋር ያ ሁሉ ሃላፊነት ቢኖርበትም አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ ዩኒቨርስቲ ጋር በመጻጻፍ ዕድሉን በማግኘቱ ሦስተኛ ድግሪውን በኦን ላይን እየተማረ አጠናቅቆ ነበር። በመሆኑም ስደት በወጣ በሦስተኛ ወሩ ኢንዲያና ከሚገኝ Newburgh Theological Seminary ሰኔ ፭ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. የአቡየ ዕለት በዶክተሬት ድግሪ ተመርቋል።በሐዘን ውስጥ ደስታ ያለው እግዚአብሔር ስሙ የተመሰገነ ይሁን።እመ እግዚአብሔር ፀባዖት ድንግል ማርያምም የተመሰገነች ትሁን።በእውነቱ መጋቤ ሃይማኖት መምህር አንዱ ዓለም ዳግማዊ በዕለቱ በስፍራው በመገኘት ብቸኝነት እንዳይሰማው በማድረግህ ልትመሰገን ይገባሃል።ወንድም ማለት እንደዚህ በችግር ጊዜ በጎን የሚቆም ነው።ሌሎቻችንማ “ኩሉ ጻድቅ በጊዜ ርቱዕ፤” ሆነናል። ለምን ተሰደደ? እንደምታስታውሱት በጥር ፳፻፲፭ ታላቋ ቤተ ክርስቲያን ከከባድ ፈተና ውስጥ ገብታ ነበር። በሃላፊው መንግሥት የተመኩ፥የዘረኝነት ጎርፍ የጠረጋቸው ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ከሃይማኖት አፈንግጠው፥ቀኖና ሐዋርያትን ጥሰው፥መንፈስ ቅዱስ ካሰመረው መስመር ወጥተው በምዕራብ ሸዋ ወሊሶ በሕገ ወጥነት ኤጲስ ቆጶሳትን “ሾምን፤”ብለው ነበር።በወቅቱ ካህናትና ምእመናን እስከ ሞት ድረስ ሰማዕትነትን ተቀብለዋል።በዚህ ክፉ ሰዓት ጠቅላይ ሚንስትሩ የቤተ ክርስቲያኒቱን መብት ማስከበር ሲገባቸው፥ሕገ ወጥነትን በመደገፍ በሚንስትሮች ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገው ነበር። ንግግሩም “አርፋችሁ ተቀመጡ፤”አይነት ነበር። ወዲያውም የቤተ ክርስቲያን ደጆች በታጣቂዎች እየተሰበሩ፥ካህናትና ምእመናንም እየተገደሉ ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሕገ ወጦቹ ተላልፋ ተሰጠች።አያሌ ምእመናንም ታሰሩ፥ተገረፉ፥ከመንግሥት ሥራቸውም ተፈናቀሉ። በዚያ ቀውጢ ሰዓት ሊቀ ማእምራን ፈንታሁን ሞት ጥላውን ባጠላበት ከተማ እንደሚኖር እያወቀ ፥ራሱ በሥራ አስኪያጅነት በሚያስተዳድረው የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዢን ቀርቦ፥ጠቅላይ ሚንስትሩ በቤተ ከርስቲያኒቱ ላይ በድፍረት ለተናገሩት ነገር ሁሉ ቃል በቃል መልስ ሰጣቸው።በክፉ ቀን ለቤተ ክርስቲያኑ ጠበቃ ሆኖ በአደባባይ በትሁት ቃል እና በትሁት ሰብእና ተሟገታቸው። ይህንንም ያደረገው ሃይማኖታዊ ግዴታወን ለመወጣት ብቻ እንጂ ማንንም ለማስቀየም ወይም ማንም እንዲያጨበጭብለት አልነበረም።ነገር ግን ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ በደኅንነት ክትትል ስር ወደቀ። በመጨረሻም ለቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመሄድ አይሮፕላን ውስጥ ከገባ በኋላ አንቀው አስወረዱት።እንዳይሞት እንዳይሽር አድርገው የእግዚአብሔርን ካህን ቀጠቀጡት። በብረት ካቴና አስረውትም ከጨለማ ቤት ጣሉት። እነርሱ አጥንትን እንኳ ሊያደቅ በሚችል በትር እየደበደቡት ውዳሴ ማርያም ይደግም ነበር።”መከራውን ያስቻለችኝ እርሷ ናት፤”ይላል። ከዚህ ሁሉ ሥቅየት በኋላ የጀመረውን የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ ከጫፍ ለማድረስ፥እስከ ቁስሉ ወደ ሰሜን አሜሪካ መጣ።ለመቆም ለመቀመጥ፥ ለመተኛት ለመነሣት መከራ ሆነ።ሁሉ ነገር በሰው ድጋፍ ነበረ።አሁንም ወንድማችን ዶክተር አንዱ ዓለም ከፍተኛ ወጪ በማውጣት በሕክምና እንዲደገፍ በማድረጉ፥ሐዘኑን እስኪረሳ ድረስ በመንከባከቡ፥ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቪዥን መምሪያ የሚያስፈልጉትን ውድ ውድ ቁሳቁሶችን በሟሟላቱና ሀገር ቤት ድረስ አሜሪካዊ ባለሞያ ይዞ በመሄድ ሠራተኞቹ እንዲሰለጥኑ በማድረጉ ሊመሰገን ይገባዋል። ሊቀ ማዕምራን አሁንም “ከሚገባህ በላይ መሥዋዕትነት ከፍለሃል፥ይበቃህል፥በዚሁ ቅር፤”ለሚለው የወዳጆች ምክር ጆሮ ዳባ ልበስ ብሎ ሀገር ቤት ተመለሰ።ለአንድ ዓመት ያህልም ለቤተ ክርስቲያን ያለውን ራእይ ለማሳካት ታገለ።ነገር ግን የቤተ ክርስቲያን የውስጥ ጠላቶች አላንቀሳቅስ አሉት። አንዳንድ ወዳጆችም “እባክህ ለቤተ ክርስቲያንም ቢሆን ከምትሞትባት ብትኖርላት ይሻላል፥ሰላማዊ ዘመን ሲመጣ ታገለግላታለህ።ቃሉም የሚለው ‘ተኀባእ ኅዳጠ ምዕረ እስከ የኀልፍ መዓቱ ለእግዚአብሔር።የእግዚአብሔር ቁጣ እስኪያልፍ ድረስ ጥቂት ተሸሸግ ነው።’”ሲሉት ሳይወድ በግዱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ።ቤተ ክርስቲያን ግን በመላው ዓለም ስላለች መቼም ቢሆን አያጣትም፥ያገለግላታል።
نمایش همه...
7👍 4👏 1🤔 1
በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ከ 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ ተደረገ፡፡  ሰኔ 6 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ማኅበረ ቅዱሳን ከደጋፊ አካላት ጋር በመተባበር በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት ማኅበራዊ ድጋፍ አድርጓል፡፡  የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ በሀገራችን እያጋጠሙ ያሉ ሰፊ ማኅበራዊ ቀውሶች በምእመንመናን፣ በገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ላይ እያስከተሉት ያለውን ሁለንተናዊ ችግር ለማቃለል ሰፊ የማኅበራዊ ድጋፍ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽና በመተግበር በተገቢ ደረጃ ማኅበራዊና ሰብአዊ ሚናውን እየተወጣ እንዳለ ይታወቃል። ማኅበሩ እነዚህን ችግሮች በስፋት በማጥናት ላለፉት 6 ዓመታት በሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያው በኩል በአርሲ፣ በሐረር ፣በባሌ፣ በወሊሶ፣ በሻሸመኔ፣ በዶዶላ፣ በአጋርፋ፣ በጅጅጋ፣ በሲዳማ፣ በመተከል፣ በቤንሻጉል ጉምዝ፣ በፓዊ፣ በቡለን፣ ፣በሽሬ፣ በአክሱም፣ በያቤሎ፣ በጎንደር አዘዞ፣ በአዲግራት፣ በማይ ጨው፣ በሽረ እንደ ሥላሴ ፣በመቐለ፣ በደብረ ብርሃን፣ በደሴ፣ በወልዲያ፣ በላሊበላ ፣በሐይቅ እስጢፋኖስ፣ በወሎ ገራዶ፣ በደባርቅ ፣በጃን አሞራና በሌሎችም የሀገራችን ክፍል ለሚገኙ ተጎጅዎች ፕሮጀክቶችን በመንደፍ ድጋፍ አድራጊ ምእመናንና ተቋማትን እያስተባበረ የአልባሳት፣ የምግብ እና መሠል አስቸኳይ ድጋፎችን በስፋት ሲያደርግ ቆይቷል። አሁንም አጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህ መሠረት በዋግሕምራ ዞን አበርገሌ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖችና በአካባቢው ለሚገኙ ለተመረጡ 3 ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች 1.53 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት 202 ኩንታል የምግብ ግብዓቶች ድጋፍ አድርጓል።  ከዚህ ድጋፍ ውስጥ 1,000, 000 (አንድ ሚሊዮን ብር) ወጭው የተሸፈነው ግሎባል አሊያንስ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በሀገረ አሜሪካ ሜኔሶታ ከሚገኘው የርእሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ምእመናና አገልጋዮች ጋር በመተባበር ያበረከቱት ነው። ቀሪው ወጭ የተሸፈነው በሀገረ አሜሪካ ከሚገኘው የሲያትል ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ነው። ሰኔ 05-06 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታዎቹ በመገኘት በተደረገው በዚህ የእጅ በእጅ ድጋፍ ርክክብ ወቅትም፣ የማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከልና የሰቆጣ ማእከል ልዑካን፣ የግሎባል አሊያንስ ድርጅት ተወካይ እንዲሁም የወረዳው የመንግስት አካላት ኃላፊዎች ተገኝተዋል። በወረዳው ከ67 ሺህ በላይ የማኅበረሰብ ክፍሎች አሁንም ድረስ አስቸኳይ ሰብአዊ ድጋፍ የሚሹ መሆናቸውን በድጋፍ ሥርጭት ወቅት የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ለማኅበረሰቡ ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ የአማናዊው ዕውቀትና ጥበብ ምንጭ ለሆኑ በአካባቢው ለሚገኙ 3 ገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ተመሳሳይ ድጋፎች ተደርገዋል። ማኅበረ ቅዱሳን በቅርብ ጊዜያት ብቻ በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅና ጃን አሞራ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሰቆጣና አካባቢው ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በደቡብ ኦሞ በናጸማይ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ በሃይማኖት ተኮር ጥቃት ለተጎዱ የቅበት ኦርቶዶክሳውያን፣ በደብረ ብርሃን ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ መቐለ ኩሓ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በትግራይ አጽቢ ወንበርታ ወረዳ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች፣ የደብረ ሊባኖስ አቡነ ተክለሃይማኖት አንድነት ገዳምን ጨምረ በማኅበራዊ ቀውስ ለተጎዱ 6 ጥንታዊያን ገዳማትና ጉባኤ ቤቶች ከፍተኛ ድጋፎችን አድርሷል። ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ሰብአዊ ድጋፍ ለተጎጅ ወገኖች እንዲደርስ የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ አካላትን እያመሰገ፣ በቀጣይ ተመሳሳይ ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን፣ ማኅበራት፣ ልዩ ልዩ ተቋማትና በጎ አድራጊ ድርጅቶች የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲል ጥሪውን ያቀርባል። ድጋፍ ለማድረግ፡- በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡- 1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901 2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458 3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648 4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101 5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400 6. በጎ ፈንድ ሚ https://www.gofundme.com/f/uerc8... 7. በወገን ፈንድ ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ✅የማኅበረ ቅዱሳን ሙያና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ
نمایش همه...
2👍 1