cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

በክርስቶስ

በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው ዮሐንስ ወንጌል 3፥36

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
779
مشترکین
-124 ساعت
-37 روز
-2230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ኢየሱስ አማላጅ ነው!!! " የ ኢየሱስ ምልጃ በ መፅሐፍ ቅዱስ " "ክፍል አንድ" 👉 ምልጃ ማለት በሁለት አካላት መካከል ባለ ጠላትነት ወይም በተፈጠረ አለመስማማት በሌላ ሶስተኛ ወገን የሚቀርብ ፀሎት ፣ልመና እና የማስታረቅ ክንውን ነው። 👉 ምልጃ በ በዳይ እና በ ተበዳይ አካላት የተፈጠረን ግጭት ለመፍታት ሌላ ሶስተኛው ወገን በ በዳዩ ስም ተበዳዩን የሚለምነው ልመና ነው። 👉 አማላጅ ማለት ደግሞ በሁለት የተጣሉ፣ የተራራቁ፣ የተቀያየሙ አካላት መካከል ገብቶ እርቅን ለማምጣት ወይም ለማስታረቅ ምልጃን የሚያቀርብ ነው። 📌 ኢየሱስ አማላጅ ነው ወይም ያማልዳል ሲባል በ ሰው እና በ እግዚአብሔር መካከል የነበረውን ጠላትነት ለመሻር ፣የሰውን ልጅ ከ እግዚአብሔር ጋር ለማስታረቅ ፀሎትን ፣ ልመናን እና ምልጃን የራሱን ደም በማፍሰስ አቅርቦለናል ማለት ነው ። 📌 የ ኢየሱስ ክርስቶስ ምልጃ በ መፅሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ከ ብሉይ ኪዳን ጀምረን እስከ አዲስ ኪዳን ያሉትን ከዚህ በታች እንመልከት:- 📌 1). “ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።”   — ኢሳይያስ 53፥12 👉 ነብዩ ኢሳያስ ከ ኢየሱስ ልደት ሰባት መቶ ዓመት አስቀድሞ ስለ ኢየሱስ ምልጃ ተናግሯል። 👉 ኢሳያስ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ ማለቱ ሃጥያተኞች ሳለን አመፃችንን እንዳይቆጥርብን ወደ እግዚአብሔር ለመነልን ።( ሉቃ 23:34) 👉 " ማለደ " የሚለው ቃል የ ዕብራይስጥ አቻው (יַפְגִּֽיעַ׃) ወይም (yap‌-gî-a‘) የሚል ነው ትርጉሙም አማለደ ማለት ነው። 👉 የ እንግሊዘኛ አቻውም ( made intercession ) የሚል ነው ትርጉሙ ምልጃን አደረገ ማለት ነው። 📌 2). ኢሳይያስ 59 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁵ እውነትም ታጥቶአል፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ለብዝበዛ ሆኖአል። እግዚአብሔርም አየ ፍርድም ስለሌለ ተከፋ። ¹⁶ ሰውም እንደሌለ አየ፥ ወደ እርሱ የሚማልድ እንደሌለ ተረዳ ተደነቀም፤ ስለዚህ የገዛ ክንዱ መድኃኒት አመጣለት፥ ጽድቁም አገዘው። 👉.እግዚአብሔር አምላክ ወደርሱ ምልጃን ሊያቀርብ የሚችል ማንም ሰው እንደሌለ በተረዳ ጊዜ የገዛ ክንዱ (ኢየሱስ ) መድሃኒት አመጣለት አማላጅም ራሱ ልጁ ሆነለት። 📌 3 ).“በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።”   — ዮሐንስ 1፥29 👉 ዮሐንስ ኢየሱስን የ እግዚአብሔር በግ ያለበት ምክንያት በ ሙሴ ሕግ ለ ሀጥያት ስርየት የሚሆነው ከ መንጋው በጎች በደል የሌለበት በግ ስለሆነ ነው ዘሌዋውያን 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁷ ማናቸውም ሰው ኃጢአት ቢሠራ፥ እግዚአብሔርም፦ አትሥሩ ካላቸው ትእዛዛት አንዲቱን ቢተላለፍ፥ ባያውቅም፥ ያ ሰው በደለኛ ነው፥ ኃጢአቱንም ይሸከማል። ¹⁸ ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት እንደ ግምጋሜህ መጠን ወደ ካህኑ ያመጣዋል ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሳተው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል። ¹⁹ እርሱም የበደል መሥዋዕት ነው፤ በእውነት በእግዚአብሔር ፊት በደለኛ ነው። 👉 ስለዚህ ኢየሱስ ለ ምልጃ የሚቀርብ የ አዲስ ኪዳን በግ ነው ስለታረደም አማለደን። 📌 4).ሉቃስ 22 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³¹ ጌታም፦ ስምዖን ስምዖን ሆይ፥ እነሆ፥ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ፤ ³² እኔ ግን እምነትህ እንዳይጠፋ ስለ አንተ አማለድሁ፤ አንተም በተመለስህ ጊዜ ወንድሞችህን አጽና አለ። 👉.ጌታ ራሱ ስለ አንተ አማለድኩ ብሎ እንዳማለደ በራሱ አፍ ተናግሯል። 👉."አማለድሁ" የሚለው የ ግሪክ ተመሳሳይ ፍቹ "ἐδεήθην" ወይም " edeēthēn"(ኤዴቴን ) የሚል ሲሆን ቀጥተኛ ፍቺው "መለመን "የሚል ነው። 📌5).ሮሜ 8 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ³³ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው? ³⁴ የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። 👉. እዚህ ላይ ጳውሎስ ራሱ" ስለኛ የሚማልደው "ብሎ ኢየሱስ እንደሚያማልድ እና በ ምልጃዉም ጳውሎስ ራሱ ተጠቃሚ እንደሆነ ነግሮናል ። 👉."የሚማልደው" የሚለው ቃል አገላለፁ አንድ ጊዜ ብቻ ተደርጎ ስለምያበቃ ምልጃ ሳይሆን ቀጣይነት ስለሚኖረው ምልጃ መሆኑን ያሳያል ። 👉. "የሚማልደው " የሚለው ቃል የ ግሪኩ ተመሳሳይ ቃሉ " ἐντυγχάνει" (ኢንቱግካኖ) የሚል ነው ትርጉሙም የሚያማለድ ወይም አማላጅ ማለት ነው ። 👉. እንግሊዘኛውም " interceding" ይላል አማላጅ ማለት ነው ። 👉 የ ግዕዙ ቃል ደግሞ "ወይትዋቀስ በ እንቲአነ " ይላል ትርጉሙም ስለኛ ይከራከራል የሚል ነው ይህም ምልጃውን የሚያሳይ ነው። 📌6). ዕብራውያን 7 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ²³ እነርሱም እንዳይኖሩ ሞት ስለ ከለከላቸው ካህናት የሆኑት ብዙ ናቸው፤ ²⁴ እርሱ ግን ለዘላለም የሚኖር ስለሆነ የማይለወጥ ክህነት አለው፤ ²⁵ ስለ እነርሱም ሊያማልድ ዘወትር በሕይወት ይኖራልና ስለዚህ ደግሞ በእርሱ ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ፈጽሞ ሊያድናቸው ይችላል። 👉. ጳውሎስ በሚገርም ሁኔታ የ ኢየሱስን ምልጃ ሲያስረዳ ምልጃው ያለፈ እና ከዚህ በኃላ የማይሰራ አድርገን እንዳናስበው ሲል "ሊያማልድ" ብሎ ነው ቀጣይነቱን የገለፀው። 👉. እዚህ ላይም "ሊያማልድ " ለሚለው ቃል በ ግሪኩ " ἐντυγχάνειν " ( ኢንቱግካኖ ) የሚል ነው ( to intercede ) ይህም ምልጃውን ሚናገር ቃል ነው ። 👉. እዚሁ ቃል ላይ ማወቅ ያለብን ነገር የ ኢየሱስ ምልጃ ከ ብሉይ ኪዳን ካህናት የተለየ መሆኑን ነው የሚለየውም የነሱ ምልጃ የሚለወጥ እና በ ሞት የሚቋረጥ ሲሆን የ ኢየሱስ ግን ማይለወጥ እና ዘላለማዊ ነው ( ዕብ 7: 23-24) 👉. እዚህ ላይ " ሊያማልድ " ለሚለው ቃል ግዕዙ " ተንበለ " ይለዋል ይህም ምልጃውን ሚናገር ነው። 📌7). 1ኛ ጢሞቴዎስ 2 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ⁵ አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤ ⁶ ራሱንም ለሁሉ ቤዛ ሰጠ፥ ይህም በገዛ ዘመኑ ምስክርነቱ ነበረ፤ 👉. መካከለኛው ማለቱ ኢየሱስ ሰውን እና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ በመካከል የገባ ስለሆነ ነው ። 👉. ኢየሱስ የ አዲስ ኪዳን መካከለኛ ያስባለው ምክኒያት ለሰው ልጆች በደል እና ሀጥያት ሲል ያፈሰሰው ደም የሚናገር፣ የሚጮህ እና የሚለምን ስለሆነ ነው ። “የአዲስም ኪዳን መካከለኛ ወደሚሆን ወደ ኢየሱስ፥ ከአቤልም ደም ይልቅ የሚሻለውን ወደሚናገር ወደ መርጨት ደም ደርሳችኋል።” — ዕብራውያን 12፥24 @jjjeesuuss
نمایش همه...
🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰🥰 @jjjeesuuss
نمایش همه...
🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀🤷‍♀ ✨✨✨✨✨✨✨✨ 🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟 🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍 ❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️ 🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍🤍 @jjjeesuuss
نمایش همه...
📍እኛ እንኳን አደረሳቹ የምንባባለው የጨዋታውን ውጤት ስለምናውቅ ነው እንጂ ይሄ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ጭንቅ ነበር ያው ውጤቱን የሚያውቅ በጨዋታው በሀል በጭንቅት ቁጭ ብድግ አይልም እንደውም ቁጭ ብድግ ለሚለው ውጤቱን ነግሮ ያረጋጋዋል!!{ወንጌል} ”“በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ፣ ይህን ነግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዟችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ።”“ ዮሐንስ 16:33 NASV #ኢየሱስ_እየተመራ_ይመስላል_ግን_አሸንፏል #እንኳን_አደረሰን @jjjeesuuss
نمایش همه...
2
እኛ 1 ኩባያ ውሃ የነፈግነው ጌታ ነው እኮ የዘላለም ህይወት በነፃ የሰጠን😕 #ምን_አይንት_ፍቅር_ነው🥺❤️ @jjjeesuuss
نمایش همه...
👍 3 1
ስለ እኛ ተንከራተተ ብዙ ተሰቃየ 😔🥹 ስለ ፍቅር ብዙ ሆነ ➕ ዘላለማዊ የፍቅር❤️ንጉስ የናዝሬቱ ኢየሱስ 👑 @jjjeesuuss
نمایش همه...
1
🥰🥰🥰🥰 @jjjeesuuss
نمایش همه...
نمایش همه...
💯 6👍 1
የእግዚአብሔር አሻራ የሌለበት የህይወት ምዕራፍ የለኝም @jjjeesuuss
نمایش همه...
❤‍🔥 2
👩‍💻👩‍💻 #ስለ_መጽሐፍ_ቅዱስ🧑‍💻🧑‍💻 ❖ የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ የተፃፈው በእብራይስጥ፣ በአረማይክ እና በኮይኔ ግሪክ ቋንቋዎች ነው። ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ • 66 መጽሐፍት • 1,189 ምዕራፎች • 31,173 አንቀፆች • 810,697 ቃላት • 3,566,480 ፊደላት ይገኛሉ። ❖ በጣም ረጅሙ መጽሐፍ- መዝሙረ ዳዊት ሲሆን • በጣም አጭሩ መጽሐፍ- ሶስተኛ ዮሐንስ • በጣም ረጅሙ ምዕራፍ- መዝሙረ ዳዊት 119 • አጭሩ ምዕራፍ መዝሙረ ዳዊት 117 ነው። ❖ የመጽሐፍ ቅዱስ አማካይ ስፍራ መዝሙረ ዳዊት 118:8 ነው። ❖በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ሰዎች መጠሪያ የሆነው ስም ዘካሪያስ ነው። ❖ ሙሉው መጽሐፍ ቅዱስ እና የትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ አስደናቂ መመሳሰል አላቸው። ይኸውም፦ • መጽሐፍ ቅዱስ #66 መጽሐፍ ሲኖሩት ትንቢተ ኢሳይያስ #66 ምዕራፎች አሉት። • የመጀመሪያው #39 የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝብ ነው። እንደዚሁም የመጀመሪያው የትንቢተ ኢሳይያስ #39 ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ እስራኤል ህዝቦች ነው። • የመጨረሻው #27 የመጽሐፍት ቅዱስ መጻህፍት የሚያስተምሩት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሆን፤ እንደዚሁም የመጨረሻዎቹ #27 የትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፎች የሚተርኩት ስለ ክርስቶስ መምጣት ነው። ❖ መጽሐፍ ቅዱስ ተፅፎ ያለቀው በ1600 ዓመታት የጊዜ ልዩነት ውስጥ ሲሆን ይህም ከ1500 ዓመተ ዓለም እስከ 100 ዓመተ ምህረት ድረስ ያለውን ዘመን ያጠቃልላል። ❖ መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው የጻፉት መጽሐፍ ነው።( 2ጴጥ 1:21) ❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ 49 የምግብ ዓይነቶች ተጠቅሰዋል፤ በተለይ "ጨው" #30 ጊዜ ተጠቅሷል። ❖ ከቤት እንሰሳት መካከል ስሟ ያልተጠቀሰ እንሰሳ "ድመት" ብቻ ናት። ውሻ #14 ጊዜ ተጠቅሷል። ❖ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ እራሳቸውን በራሳቸው ያጠፉ ሰዎች ሰባት ሲሆኑ እነርሱም፦ 1. አቤሜሌክ 2. ሳምሶን 3. ሳዖል 4. የሳዖል ወታደር 5. አኪጦፌል 6. ዚምራ 7. ይሁዳ ናቸው። ❖ በመጽሐፍ ቅዱሳችን ውስጥ ስለ ፀሎት 400 ጊዜ ስለ እምነት 500 ጊዜ ስለ ገንዘብና ሐብት ደግሞ 2,000 ጊዜ ተፅፏል። መጽሐፍ ቅዱስ ገንዘብን መውደድ የኃጢአት ሁሉ ስር ነው ይለዋል። ❖ መጽሐፍ ቅዱስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ እንግሊዝኛ የተተረጎመው በ 1388 ዓ.ም ነው። ምንጭ፦ ቅዱሳን መፅሐፍት @jjjeesuuss
نمایش همه...
👍 4