cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

Amhara International

We strive to make Amhara cause International

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 291
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-2830 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ይሄ ቀን እንደሚመጣ አውቀን ከማንም በፊት ስንናገር ነበር። መምጫው የታወቀ ጠላት ዕዳው ገብስ ነው። ሕዝብ ያሸንፋል። ዛሬ የህዝብ ተወካይ ነኝ የምትል አማራ ነገ ሰብስቦ አንተም እንደ ፈጣንሎተሪ ብትፋቅ ፋኖ ነህ ብሎ ይዘባበትብሃል። ዛሬ መከላከያ ውስጥ ያለህ አማራ ነገ አስተኳሽና ጠላቴ ብሎ በጦሩ የትግራይ ተወላጆች ላይ ያደረገውን ባንተ ላይ ይደግምብሃል። የብአዴን ሰው ነህ? ዋና የሀይል መሠረትህ የሆነውን ሕዝብህን አጥተህ፣ ወግተህ ካበቃህ በኋላ በፖለቲካ አነጋገር አልቆልሀል፣ አብቅቶልሀል፣ ከሕዝብህ ከነጠለህ በኋላ አሁን ካደረገህ መቶ እጥፍ የጓዳ መጫወቻ አሻንጉሊቱ ያደርግሀል። ዛሬ እየቀበርከው ያለ ወገንህም አይምርህም፣ ነገ ይቀብርሃል። አማራ የሆንክ ደህንነት ነህ? ፖሊስ ነህ? ልዩ ኃይል? አድማ ብተና? ወይስ ኮማንዶ? እሣት ካየው ምን ለየው? አማራ ነህ? ወይስ አይደለህም? ነው ጥያቄው። ነገ በዘርህ ተለቅመህ ትነቀላለህ። አማራ የሆንክ የጦር ጀት አብራሪ ነህ? የአየር ኃይል መኮንን ነህ? ከእንግዲህ አትታመንም። በፍጥነት ተገልለህ በእነ እንቶኔ ትተካለህ። ጦርነቱ በአማራ ሕዝብ ላይ ነው የታወጀው። "የመስቀል ዶሮ በእንቁጣጣሽ ዶሮ ትስቃለች" ነው። ዛሬ ፋኖው ሌላ መስሎሀል። ፋኖ ሲሉ የአማራ ሕዝብ ማለታቸው ነው። ነገ ፋኖው አንተ ነህ። ነጣጥሎ ሊበላህ የቋመጠውን ተረኛ ጅብ ተፀየፈው። ክዳው። ውጋው። ምሥጢሩን አሳልፈህ ስጥ። ተነስና ከሕዝብህ ትግል ጋር ተቀላቀል። የውስጥ አርበኛ ሁንበት! የአውድማ አርበኛም መሆንክን አራጅህ እየመረረው ይይ! ጅብ እንኳ ወገኑ ሲጠቃ ይጮሀል። ሰው ከሆንክ ተነስ ለወገንህ! ሕዝብ ያሸንፋል። ታሪክ ምስክር ነው። ታሪክ እየተፃፈ ነው! ከሚያሸንፈው ጋር ሰልፍህን አስተካክል። ድል ለጀግናው የአማራ ሕዝብ!
نمایش همه...
Repost from A King Makers
Photo unavailableShow in Telegram
ጥላቻ መጥፎ ነው። በጥላቻ ምክኒያት ነው በዚህ ህዝብ ላይ ጦርነት ያወጅት። ፋኖ ሰቆቃና ግፍ የወለደው የህዝብ ልጅ ነው። ከመጥፋት እጀን አጣጥፌ ከምቀመጥ እየተዋደኩ እኖራለሁ ብሎ የሚዋጋ ሀይል ነው። ብዙዎቸ ጦርነቱን የደገፉት ለአምሓራ ያላቸው ገደብ አልባ ፎቢያቸውን መቆጣጠር ስላቃታቸ “ነው። ሁሉም ብሄሩን ያደራጀው አማራውን በመርገም ነው። የብሄርተኝነታቸው መሰረታዊ ሀውልት የጣሉት አማራ የሚባልን ፍጡር በጥላትነት በመፈረጅ ነው። ታዲያ ዛሬ በሚጠሉት ህዝብ ላይ ጦርነት ሲታወጅላቸው ጊዜው አሁን ነው ብለው አሰፍስፈው የአማራውን ስብራት እየጠበቁ ነው። ግን አይቻል በፍፁም ይሄንን ህዝብ እያረዱ እያሰደዱ እየወረሱ እየሰደቡ መኖሩ አብቅቶበታል። መከላከያ የህዝብና አገር ልጅ ነው በትንሽ ግሩፕ ጥላቻ ብቻ ተመርቶ በዝህ በተገፋ ህዝብ ላይ ጦርነት እንዲገባ አድርገውታል ግን መስሏቸው ነው እንጅ አይችሉም። የተበደለን የተገፋን የተገደለን ህዝብ በአፈሙዝ መግራት አይቻል። ስረአቱን በደንብ እናውቀዋለን። የነሱን ሀሳብና ፍላጎት ስለምናውቅ ነው ሀቅ የምንፅፈው። በ5 አመት የስልጣን ዘመናቸው ብቻ የቨፈጨፉት አማራ በሩሲያና በዮክሬን መካከል በሚደረገው ጦርነት ውስጥ የዛን ያህል ሰው አልሞተም። አሁን የነሱን የደም ጥማት ለማርካት ሲባል ከሀቅ አንሸሽም። ሱሌማን አብደላ
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
የአማራ ህዝብ ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ መሸጋገርን አስመልከቶ የተሰጠ አስቸኳይ መግለጫ አስቸኳይ መግለጫ ሐምሌ/28/2015 ዓ.ም የአማራ ህዝብ በደምና አጥንቱ ባፀናት አገሩ ላለፉት 50 ዓመታት ስርዓት ወለድ በሆነ ችግር በማንነቱ ሲጨፈጨፍ፣ ሲፈናቀል፣ ሲሰደድና በሴራ ከአገሪቱ ፖለቲካ እንዲገለል በማደረገ ከምጣኔ ሀብታዊና ማህበራዊ ጥቅሞች ውጭ ሆኖ ቆይቷል። ይባስ ብሎ ላለፉት አመታት በለውጥ ስም የኢትዮጵያን መንበረ ዙፋን የተቆጣጠረውና በጥላቻ ያደገው የዘረኛው ህዎሓት የብኩር ልጅ ኦህዴድ/ኦነግ በስልጠና፣በትጥቅና በስንቅ ባደራጃቸው ገዳይ ኃይሎቹ አማራውን ያለርህራሄ በጥይትና በገጀራ በመጨፍጨፍ የዘር ማጥፋት ፈፅመዋል። ሀብት ንብረቱን ዘርፈውና አውድመው ከሚኖርበት አካባቢ በማፈናቀል የዘር ማፅዳት ፈፅመዋል፤ ቅድመ አያቶቹ ባቀኗት ከተማ አዲስ አበባ እንዳይገባ ከልክለዋል፣ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ተዘዋውሮ እንዳይሰራ መንገድ ላይ እያገቱ ዘርፈዋል፣ ገድለዋል። አሁን አሁን ደግሞ ከመዝረፉና መግደሉ ባሻገር ህፃናትን ሁሉ ሳይቀር እያገቱ "ማስለቀቂያ" በሚል ዘዴ ከድሃ የአማራ እናቶች መቀነት በሚሊዬንስ ገንዘብ ይቀበላሉ፤ የአማራ ባለሃብቶች የባንክ አካውንቶችን አግደዋል። አርሶ አደሩ በጉልበቱ ዘርቶ እንዳይቅም በተጠና መንገድ የአፈር ማዳበሪያ በመከልከል ማሳው ጦም እንዲያድር አድርገዋል። ይህ ሀሉ አልበቃ ያለው ፋሽስቱ የኦህዴድ/ኦነግ ስርዓት ላለፋት አራት ወራት "ህግ ማስከበር" በሚል ሽፋን በአማራ ክፍለሀገር በመከላከያ ስም የተደራጀ የአንድ ዘር ታጣቂ ሰራዊት በማዝመት የዕምነት ተቋማትን አውድሟል፣ ሴቶችን ደፍሯል፣ ንፁሃንን ገድሏል፣ አሁንም ስፍር ቁጥር የሌለው ሰራዊት ወደ አካባቢው እያስገባ ይገኛል። የዚህ ሁሉ በደል ባለቤት የሆነው የአማራ ህዝብ የጀመረውን የህልውና ትግል ከፍ ወዳለ ደረጃ በማደረስ ከሐምሌ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ ከተሞችን ከፋሽስቱ ኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና መዋቅር በክንዱ ነፃ እያዎጣ ከተሞችን እየተቆጣጠረ ይገኛል። በተለይም በጎጃም፣ በጎንደር፣ በወሎና በሸዋ አብዛኛውን ከተሞች ፋኖ ከህዝቡ ጋር በመቀናጀት የአሽከሩን ብአዴን ብልፅግና መዋቅር በመበጣጠስ በአስገራሚ ፍጥነት እና ብቃት እየተቆጣጠራቸው ይገኛል። በመሆኑም የአማራ ህዝባዊ ግንባር የሚከተለውን ጥሪ ያስተላልፋል፦ 1ኛ) የአማራ ህዝብ በጀግኖች ልጆቹ የጀመረውን የገዥውን ስርዓት መዋቅር እየበጣጠሰ ከተሞችን የመቆጣጠር ጎዞውን አጠናክሮ እንዲቀጥል፤ 2ኛ) የአማራ ህዝብ የጀመረውን በክንዱ ነፃ የመውጣት ጉዞ ለማደናቀፍ በኩሊው ብአዴን በኩል ሐምሌ 27/2015 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምሮ ክልሉ ከቁጥጥራቸው ስር እንደወጣ በይፋ በመግለፅ ተጨማሪ የስርዓቱ ገዳይ ኃይል እንዲገባና ንፁሃንን እንዲጨፈጭፍ ፈቅደዋል። ክልሉም በወታደራዊ አገዛዝ ስር እንዲዎድቅ አዝዘዋል። ስለሆነም:- በአማራ ክልልም ይሁን ከክልሉ ውጭ የሚገኝ ማንኛውም ታጣቂ ፋኖ፣ የአማራ ልዮ ኃይል፣ የአማራ ፖሊስ፣ አድማ ብተና፣ ምልስ የሰራዊቱ አባላት፣ የሚሊሻ አባላትና ሌሎችም በሙሉ ከዛሬ ጀምሮ በክልሉ ያለው የስርዓቱ መዋቅር መፍረሱን በመረዳት ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ጎን እንድትሰለፉና ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን ትዎጡ ዘንድ ግንባሩ ጥብቅ ጥሪ ያደርጋል። 3ኛ) የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሙሉ የኦህዴድ/ኦነግ ፋሽስቱ ስርዓት ለግል ጥቅሙና ስልጣኑ ሲል ትናንት በእር በርስ ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ጓዶቻችሁን አስጨፍጭፏል፣ የተጨፈጨፉ ጓዶቻቸሁ አስክሬን በወግ ተሰብስቦ ለአፈር ሳይበቃ ከገዳዮቻችሁ ጋር "በሰላም ስምምነት ስም" ክህደት ፍፅሞባችኋል። ዛሬ ደግሞ ይባስ ብሎ በክፉ ቀን ያበላ፣ ያጠጣችሁንና የሸሸጋችሁትን ህዝብ እንድትዎጉ ተገዳችኋል። ትዕዛዙን ባለመቀበል እየከዳችሁ ከአማራ ኃይሎች ጎን እንድትሰለፉ ጥሪ እናቀርባለን። 4ኛ) በአገዛዙ ስቃይና መከራ ውስጥ የምትገኝው ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብ ከአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ጎን እንድትቆም ጥሪ ቀርቧል። 5ኛ) በስተመጨረሻም የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብ ዘብ የሆንከው ጀግናው የአማራ ፋኖ ከህዝብህ ጋር የጀመርከውን የነፃነት ጉዞ አጠናክረህ እንድትቀጥል ጥሪ እያቀረብን የአማራ ህዝባዊ ግንባር በቀጣይ ሁለት ቀናት ውስጥ ላልተወሰነ ጊዜ የማቆይ ኮማንድ ፖስት የሚያቋቁም መሆኑን ይገልፅል። ኮማንድ ፖስቱ በመላው የአማራ ከተሞች የሚተገበር ሆኖ የአማራን የህልውና የነፃነት ትግሉን ማቀጣጠልና ነፃ የወጡትን የአማራ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የዞን አውራጃዎችንና ከተሞችን በሚቋቋመው ኮማንድ ፖስት በተመደቡ የአማራ የትግል አካላት እንዲተዳደሩና ህዝቡም አካባቢውን እንዲጠብቅ ደንብ ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም ስለንብረትና እስረኛ አጠባበቅን በተመለከተ በኮማንድ ፖስቱ ተካቶ ደንቡ ይፋ ይሆናል። ድል ለአማራ ህዝብ ሐምሌ/28/2015 ዓ.ም የአማራ ህዝባዊ ግንባር
نمایش همه...
Repost from The Amhara Informer
ብአዴን የሚሉት የሙታን ስብስብ ላለፉት ሶስት አስርታት የአማራን ህዝብ ለባርነት መዳረጉ ሳያንስ አሁን ደግሞ በግልጽ ጦርነት አውጆ "ኑ ውረሩልኝ" ሲል ጌቶቹን ጋብዟል እግር እስከሚነቃ ቢሄዱ በራሱ ህዝብ ላይ ጦርነት ደጋግሞ ያወጀና ጦር ያዘመተ እንደ ብአዴን ከቶ የሚገኝ አይመስለኝም ገና ከጥንሱሱ በአማራ ህዝብ ጥላቻ የሰከረ፤ የአማራን ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ ህልውናውን ያጸና፣ ከአማራ ህዝብ ህልውና፣ መሠረታዊ ፍላጎቶችና ብሔራዊ መሻቶች በተቃርኖ ቆሞ ህልውናውን ያጸና እስትንፋሱንም ያስቀጠለ "መልከ ህወሓት" ድርጅት ነው የአማራ ህዝብ ይሄን የሙታን ስብስብ እና የአስተሳሰብ ጥገኛ የሆነን ጠላት ድርጅት አስወግዶ ህልውናው ከማጽናት፣ የራሱንና የሃገሪቱንም ነጻነት ከማረጋገጥ ውጭ አማራጭ የለውም ስለሆነም የጀመረውን ትግል አጠናክሮ መቀጠል የግድ ይለዋል ከዳር ላይደርስ የተጀመርከው ትግልም የለምና አማራዬ #ወጥር #ድልለአማራ
نمایش همه...
ለቅዳሜ ማለትም ለሃምሌ 29 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ ተጠራ። የሰልፉ ዓላማ በአማራ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥቃት እና በአዲስ አበባ ከተማ እየደረሰ ያለውን መዋቅራዊ ጥቃት ለማውገዝና ለማጋለጥ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል። የሰልፉ ጥሪ ውስጥ ውስጡንም እየተሰራበት እንደሚገኝ የሰልፉ አስተባባሪዎች ገልጸዋል። ይሄን መረጃም ለማውጣት የተገደድነው አገዛዙ ስለደረሰበት በማወቃችን መላው የአዲስ አበባ ሕዝብ ለቅዳሜ ዝግጅቱን እንዲያደርግ ለማሳወቅ ነው። ይሄንን የተቃውሟ ሰልፍ ከማድረግ የሚከለክለን ምንም አይነት ምድራዊ ኃይል የለም ሲሉ መረጃ አድራሾቹ ገልጸዋል። አዲስ አበቤ ጭቆናው ተስማምቶሃል ወይ? ▪︎አዲስ ከተማ ▪︎መርካቶ ▪︎አውቶብስ ተራ ▪︎አብነት ▪︎ሰባተኛ ኳስሜዳ ▪︎መሳለሚያ ▪︎አማኑኤል ▪︎ጎጃም በረንዳ ▪︎ልደታ ▪︎ጦርሀይሎች ▪︎ወይራ ▪︎ዘነበወርቅ ▪︎አየርጤና ▪︎አለም ባንክ ▪︎ኮልፌ ▪︎አጠናተራ ▪︎አስኮ ▪︎ዊንጌት ▪︎ሜክሲኮ ▪︎ተክልዬ ▪︎ከረዩ ▪︎አምሰተኛ ▪︎ፓስተር ▪︎መድሃኒአለም ▪︎ዮሃንስ ▪︎ፒያሳ ▪︎እሪበከንቱ ▪︎ገዳም ሰፈር ▪︎ቀበና ▪︎ፈረንሳይ ▪︎ቤላ ▪︎አራት አምስት ስድስት ኪሎ ▪︎ ቀጨኔ ▪︎መነን ▪︎ ሪቼ ▪︎መሿለኪያ ▪︎ጨርቆስ ▪︎በቅሎ ቤት ▪︎ ዮሴፍ ▪︎ሳሪስ ▪︎ቃሊቲ ▪︎አቃቂ ▪︎ ሀናማሪያም ▪︎ብስራተ ገብርኤል ▪︎ ንፋስ ስልክ ▪︎ቦሌ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን የምናቀርብ ይሆናል።
نمایش همه...
Repost from A King Makers
የግንባሩ ውጊያ በባለሙያ እጅ ነው። ለዚህም ነው በተለያዬ ቦታ የወገን ሃይል ድል የምንሰማው። ወደፊትም የአማራ ቀበሌዎች ወረዳዎችና ከተሞች ለአገዛዙ ወራሪ እሳት ሆነው ይለበልቡታል። መንገዶች፤ መተላለፊያዎች የግፈኞች መውደቂያ ይሆናሉ። ትናንት በሬ ያረድክለት፤ ጎተራህን ገልብጠህ የቀለብከው የአገዛዙ ጦር ዛሬ ሊያስርብህ ሊያራቁትህ ለተነሳ ገዢ አገልጋይ ሆኗል። ለክፋትና ለውድቀትህ መጣ፣ ዘር የሚያጠፋ ፣ ዘር የሚያፀዳ እንደህዝብ ልንዋጋው የሚገባ ጠላት ነው !! እንደሕዝብ እንዋጋው !! 1. ቀየህ መጓጓዣው መሆኑ ይብቃ። መንገዶችን እንዝጋ! 2. በየአካባቢው የፋኖ ድጋፍ ሰጪ መዋቅር መዘርጋት 3. የጠላትን እንቅስቃሴ ለፋኖዎች ማሳወቅ 4. ጠላትን በመረጃ ማሳሳት 5. የተማረኩ የጠላት ሃይሎች ለሰራዊቱ ግልፅ መልዕክት እንዲያስተላልፉ ማድረግ 6. የወገን ሃይልን የሚጎዳ መረጃ ከማሰራጨት መቆጠብ 7. ለጠላት ሃይል ምግብና መጠጥ መከልከል ድል ለአማራ ‼
نمایش همه...
Photo unavailableShow in Telegram
ደራሲና ፀሃፊ አሳዬ ደርቤ በ10ሺ ብር ዋስ ከእስር ተፈቷል። ከመኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ሃይሎች ተይዞ የታሰረው ደራሲና ፀሃፊ አሳዬ ደርቤ  በዋስትና ጉዳይ ክርክር ለማድረግ ትናንት ሐምሌ 10 ቀን 2015 ዓ/ም የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርቦ ነበር። ፍርድ ቤቱም አቃቢ ህግ በአሳዬ ላይ ያቀረበውን  ክስ ከመረመረ በኋላ  የተከሳሽ ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና  ጥያቄ በማዳመጥ ተከሳሹ በ10,000 ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ብይን ሰጥቷል። አሳየ የዋስትና መብቱ ተከብሮለት በአሁን ሰአት ከእስር ተፈቶ ወደ ቤቱ ገብቷል ሲል አሻራ ዘግቧል።
نمایش همه...
Repost from A King Makers
ውሳጣዊ ትግል እና አንዳንድ ጉዳዮች ❗️ - ዕብናት፣ የገጠመን አደጋ አረዳድ፣ ፖለቲካዊ መተጋገል፣ እና ቀሪ መሠረታዊ የአማራው ሀላፊነት፤ __ ዕብናት ፋኖዎች የገጠማቸው አደጋ ከሌላው አካባቢ የተለዬ ነገር የለውም። የተለዬ ነገር ካለ <<ይህ በእኛ አካባቢ ሊገጥም አይችልም >> የሚለው የጥቂቶች ቅድመ ግንዛቤ ብቻ ነው። ይህ ዕሳቤ አንድም እንደ አማራ ህዝብ የገጠመንን አደጋ ይዘት እና ቅርጹን በቅጡ ካለመረዳት የሚመነጭ ነው። አንድም የክልሉ አስተዳደር ላይ ያለ ያልተገባ ተስፋ እና ምክንያት አልባ አውንታዊ ዕይታ ነው። ለሰላም የሚሰጡ ዕድሎች እንዲሁም ችግሮችን በውይይት የመፍታት ልምምድ የሚደገፍ ነው። ሆኖም በእብናት ፋኖዎች የገጠማቸው ችግር በፋሽታዊ አገዛዙ ፖለቲካዊ ዕሳቤ የመቃኘት ውጤት በመሆኑ የትልቁ አደጋ ውልድ የሆነ ተቀጥላ እንጂ ልዩ ክስተት አይደለም። ስለዚህም የመፍትሔ መንገዱ ትልቁን ብሄራዊ አደጋ ያማከለ እንጂ ጊዜያዊ ዕልባት ላይ ያተኮረ መሆን የለበትም። አሁንም በሞኝነት አልያም በ ኢ-ምክንያታዊ ሰላማዊነት ስም ታጋዮችን ማስበላት እና ተጋድሎውን ማጓተት በጊዜ ቢቀር የተሻለ ነው። ፋሽዝም " ሁሉንም ወይም ሁሉንም " የሚል ዕሳቤ ይዞ የተነሳ በመሆኑ ለድርድር እና ለሽምግልና ቦታ የለውም። የአገዛዙ ፋሽስታዊነት ያልተረዳ የአካባቢ አመራር ይህንን ዕሳቤ ህግ በማስከበር ስም ከመፈጸም የተለዬ መንገድ ሊከተል አይችልም። ስለዚህ የአካባቢ አስተዳደሮች የወቅቱ የአማራ ተጋድሎ በተረዳ መልኩ መሄድ እስከሚጀምሩ ድረስ የአገዛዙ መሳሪያዎች እንደሆኑ ተረድቶ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ° ° ° የራስ ወገን ያልተረዳው እና ያልተቀበለው ትግል የትም አይደርስም። በተጨማሪም ከየትኛውም አደጋ በፊት ከራስ ወገን ከሚመጣው መጠንቀቅ ይገባል። ለዚህም ነው ትግል የሚጀምረው ከራስ ነው የሚለው ዕሳቤ ትክክል የሚሆነው። ይህ ከራስ ወገን ጋር የሚደረግ ትግል፣ ከራስ ጋር እንደሚነጋገር ሊታይ ይገባል። ከራሱ ጋር ያልተግባባ ሰው ራሱን ጠላት እንደማያደርግ ይልቁን ከራሱ ጋር እስከ መጨረሻው በሀቅ እንደሚነጋገር የዕርስ በዕርስ ልዩነቶችም ግልጽነት ላይ ተመስርቶ ባልተቋረጠ ንግግር [ ውይይት እና ክርክር ] የሚፈቱበትን ፖለቲካዊ ሂደት መከተል ይገባል። ° ° ° የትኛውም የአማራ አካባቢ የተለዬ አደጋ የለበትም፣ የተለዬ ዕድልም ሊገጥመው አይችልም። እንደ አማራ የገጠመንን አደጋ በጋራ የአደጋ መረዳት ላይ ተመስርተን በአንድነት ከመመከት ውጪ አማራጭ እንደሌለን መገንዘብ ይገባል። አገዛዙ በፈረቃ ሊያጠቃን የሚሄድበትን መንገድ የአደጋው ትክክለኛ ገጽታ አድርጎ በመውሰድ የማዘናጊያ ጊዚያዊ እፎይታን እንደ ዘላቂ ሁኔታ መረዳትም አይገባም። የጠላት ፍላጎት ለሁሉም ግልጽ ነው። አሁንም በራሳችን ችግር ማለትም እርስ ግምት እና የተፋለሱ ሀቆች እና በሴራ የተቀመሩ ፖለቲካዊ ተረኮች ላይ ተመስርቶ እርስ ከመወነጃጀል ወጥቶ የተበላሸውን የቀደመ መንገድ ቋጭቶ፣ አዲሱን መንገድ መጀመር የግድ ይላል። ለዚህ ደግሞ የአደባባይ እና የጓዳ የፖለቲካ ዲስኩሮችን በድፍረት እና በጥልቀት ማካሄድ ይገባል። ዕስር፣ እንግልት፣ ስደት እና ጥይት የማይፈሩ ሰዎች ሀሳብ እና አስተያየት ሊፈሩ አይገባም። ስለዚህም በድፍረት ያለገደብ በአግባቡ እንነጋገር፣ እንተጋገል። ° ° ° ፈለገ አማራ [ The Amhara Quest ] ከተቃውሞ ወደ ትግል እንዲሸጋገር ለማስቻል ዋነኛ የሚባሉት ተግባራት ሊከወኑ ይገባል። በእስካሁኑ ሂደት ያየናቸው የፖለቲካ ተሳትፎ ላይ የተወሰኑ ፓርቲዎች እና በቅርብ የተጀመረው ህዝባዊ የመሳሪያ ተቃውሞ [Armed resistance] ህዝቡ ለገጠመው ተጨባጭ አደጋ የተሰጡ ምላሾች [reactionary moves] ናቸው። የፓርቲ ፖለቲካ አደጋውን በልኩ ለመቀልበስ የማይችል ሲሆን የመሳሪያ ተቃውሞው ደግሞ የውጊያ ድሎችን ዘላቂ ማድረግ የሚችል ፖለቲካዊነት ይጎድላቸዋል። እናም የመሳሪያ ተቃውሞው ለሙሉ ድል እንዲበቃ እና የተቃውሞ ንቅናቄው ወደ ተደራጀ ህዝባዊ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ወይም ትግል እንዲገባ ሁለቱ የትግል መሠረታዊያንን ማሳካት አለብን። እነዚህም #ርዕዮት እና #ድርጅት ናቸው❗️ ትግል በዲሞክራሲያዊ የፓርቲ ፖለቲካ ካለው ፖለቲካዊ ተሳትፎ የተለዬ ቅርጽ እና ይዘት ያለው በመሆኑ አሁን ያለው የተዘበራረቀ አካሄድ ሊጠራ ይገባል። በአውደ ውጊያ የሚገኙ ድሎችም ሆነ በሚዲያ በፕሮፓጋንዳ በተደጋጋሚ ያስገኘናቸው ብልጫዎች ፈለገ አማራን እንዲያሳኩ ርዕዮት እና ድርጅት አስፈላጊ ናቸው። እዚህ ላይ ለማሳሰብ ያህል ቀድሞ ያነሳሁትን ሀሳብ በድጋሚ ልጥቀስ፤ 👇 አንደኛው አሁን ያሉትን የተለያዩ ንቅናቄዎች እና ስብስቦች አድገው ለብሄርተኛው ጥላ እና አታጋይ የሚሆን #ድርጅት የማዋለድ ተግባር ነው። ይህ አንድም በትብብር ሁለትም በጤናማ ውስጣዊ ትግል የሚሳካ ይሆናል። ድርጀት ስንል ከመደበኛ የፓርቲ መዋቅር ባለፈ መልኩ የትግሉ አውድ ያለበትን እና የሚፈልገውን ቅርጽ የያዘ እና ዳይናሚክ ሊሆን ይገባል። ሁለተኛው ተግባር የአማራ ብሄርተኝነትን ከሀሳብ ወደ ርዕዮተ አለም የመቀየር ነው። ይህም ሲባል የሚነሱትን ጥያቄዎች፣ የተቃውሞ ሀሳቦች እና መከሪያከሪያዎች ግልጽነት ኖሮት መዋቅር እና ደርዝ ባለው መልኩ የሚያስቀምጥ ተረክ ማንበር ይገባል። ለዚህ ደግሞ ያልተቋረጠ የአደባባይ እና የውስጥ ዲስኩር ማድረግ አለብን። ትግሉ ከዚህ በኋላ በበጎፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ሳይሆን ተልዕኮ እና መመሪያ ኖሮት ተዋረዳዊ በሆነ አካሄድ በአግባቡ ሊመራ ይገባል። የትኛውም መስዋዕትነት እንዲሁም አደረጃጀት ግለሰባዊ ሊሆን አይገባም። ሁሉም ታጋይ በድርጅት ውስጥ በግልጽ ፖለቲካዊ አሰላለፍ፣ በተልዕኮ ሊሰራ ይገባል። ለዚህ ደግሞ ከላይ የተነሱት ሁለቱ ማለትም ህሊናዊ መስመር የሚሆን ገዢ መርህ (ርዕዮት) እና አታጋይ ጥላ ተቋም [vanguard] ያስፈልጋል። ° ° ° እናም በአዲስ የተመሠረቱም ሆነ የቆዩ የትጥቅ ትግል መሪ ቡድኖች ማለትም አህኃ፣ የአማራ ህዝባዊ ኮሚቴ፣ አህግ፣ የአማራ አንድነት ሀይሎች፣ የአማራ ፋኖዎች ምክርቤት [ የምስራቅ አማራ፣ የሰሜን-ጎንደር ፋኖዎች አንድነት፣ የደቡብ [የሸዋ ፋኖ አንድነት እና በምዕራብ አማራ ያሉ ፋኖዎች ግንባር ] ፣ ተነጋግረው የጋራ ድርጀት ሊመሰርቱ ይገባል። የእንተባበራለን መልዕክቶች በራሳቸው በቂ አይደሉም። እነዚህ ቡድኖች እና ከዚህ ውጭ ያሉት የዲያስፖራ ህብረቶች በድርጀት ምስረታው እንዲሁም በርዕዮተ አለም መዋቀር ሂደቱ በንቃት በመሳተፍ የጋራ ርዕይ እና ተቋም መፍጠር ላይ ሊሰሩ ይገባል። በእውነት ላይ በተመሠረተ ትግል ተደራጅተን እናሸንፋለን። አንድ ርዕይ፣ አንድ ድርጅት ፣ አንድ ትግል፣ አንድ አማራ ! ድል ለአማራ ! #AmharaStruggle #Justice4Amhara #AmharaGenocide
نمایش همه...
♦ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታስሯል ! ዛሬ ጠዋት የመንግስት ኃይሎች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ፤ ለጥያቄ ትፈለጋለህ በማለት ከመኖርያ  ቤቱ ወስደውታል ። ይህ መረጃ ይፋ እስከሆነበት ሰዓት ፤ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ የት እንዳለ እና በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ ለማወቅ አልተቻለም ። @yidnekachewkebede .......................................... ሲፅፍ ያውቁታል። እነ ብርሃኑ ጁላ መፅሔቷን በሰው ጭምር አስነብበው "ምን ማለት ፈልጎ ነው?" እያሉ እንቅልፍ የሚያጡበት ነው።  መንገድ ላይ ብቻውን እየሄደ ቢያዩት "ይህኔ የሆነ ነገር እያሰበብን ነው" ብለው ይፈሩታል። ከቤቱ ባይወጣ "ይህኔ እየፃፈብን ነው" ብለው ይሰጋሉ። ሀሳብ የሚያስፈራቸው ገዥዎች ዛሬም ተመስገንን አፍነውታል። አገር የሚያፈርስ ነጣጣይ ሀሳብ ቢፅፍ ማንም አይነካውም ነበር። ተመስገን ግን ሰራዊቱን ሲበድሉት ለሰራዊቱ ይቆማል። በህዝብ ላይ የሚሰሩትን ያጋልጣል።   ሊያስፈራሩት ሲጠሩት አንድም ሳያስቀር ይፅፍባቸዋል። ተራ ፌስቡከኛ የሚያስጨንቃቸው ሰዎች ተመስገን እንቅልፍ ቢነሳቸው አይገርምም። @getachewshiferaw ድል ለአማራ‼️       ሞት ለፋሽዝምና ለአገዛዙ‼️ #AmharaStruggle #Justice4Amhara #AmharaGenocide @Akingmakers @amharainternational @informamhara
نمایش همه...
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.