cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ቀሰም Freshman

💡ቀሰም Freshman Campus ለሚማሩ ተማሪዎች ፤ ቲቶሪያሎችን ፣ጠቃሚ የንባብ ስልቶችን ፤Soft Copy የሆኑ አጋዥ የንባብ ማቴሪያሎችን ፣ትምህርታዊ መረጃዎችን እና አነቃቂ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ለተማሪዎች ንቃት የሚተጋ ቻናል ነው!📚 📩For comment :- @Qesem_fam

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
19 686
مشترکین
-1124 ساعت
+1527 روز
+1 84630 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

የጂኒየስነት ሚስጢር ክፍል 🚩 👀ቆይ እናንተ ሁሉንም ቀለሜ አርጋችሁ ሜዲስን እንዳንገባ ልታረጉ ነው ዴ😑 ✔️ ለማንኛውም ወደ ገደለው .....! ➡️  ቀለሜነት ሲነሳ ብዙዎች ከላይ የሚሰጥ ልዩ ጸጋ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን እንደዛ አይደለም። ቀለሜነት ለራሳችን የሚመቸንን የአጠናን ስልት ከማወቅ እና በምናጠናበት ግዜ ምቹ ሁኔታን ከመፍጠር የሚመነጭ ሁሉም ሰው ውስጥ ያለ ጸጋ ነው። ባጭሩ ሁሉም ሰው ቀለሜ መሆን ይችላል እያልኳችሁ ነው። አትቀልዳ አላቹሁ ኣ ❓     😎  3ቱ ተማሪዎች   ፦ ✅️  ሁላችንም ትምህርት ቤት ውስጥ የማይጠፉ 3 አይነት ተማሪዎች አሉ። 📍 የመጀመሪያው ሁሌ Library ሚመላለ፣ የሚቸክል ግን ውጤት የማይሰቅል። 📍 ሁለተኛው Library የሚመላለስ፣ የሚቸክል በዛው ልክ ውጤት የሚሰቅል።🤓(ፈረንጆቹ Nerd የሚሉት አይነት) 📍 ሶስተኛው ግን Library አይመላለስም፣ ሲቸክል አይታይም፤ ክላስ ውስጥም ፈታ ብሎ ነው የሚማረው ውጤት ግን ይሰቅላል። 🔎 ዛሬ የዚህን ልጅ ምሥጢር ነው የምነግራች ፦ ( ነግሮ ነው እንዳትሉኝ ስለሆንኩ ነው ❓) ✅️ መጀመሪያ ከሦስቱ የተማሪ አይነቶች እኛ የትኛው ነን ❓ የሚለው ራሳችሁን ጠይቁ። ✏️ የመጀመሪያው ተማሪ ምን አይነት የአጠናን ስልት መከተል እንዳለበት ግራ ገብቶት Library ካልተመላለሰ የሚወድቅ እየመሰለው የሚደክም ተማሪ ነው። ✏️  2ኛው ማንበብ በጣም የሚወድ በትምህርት Obsessed የሆነ ተማሪ ነው(የዚህ ተማሪ ችግሩ ምንድን ከትምርትጨ ውጪ ሌላ ዓለም ያለ አይመስለውም )። ✏️  3ኛው ግን ማንበብ ባለበት ሰዓት የሚያነብ፤ ግዜውን በአግባቡ የሚጠቀም፤ እንዴት ማንበብ እንዳለበት የሚያውቅ ተማሪ ነው። እናንተ የትኛው ናችሁ ❓    ✅️  የቀለሜነት 3ቱ stepዎች ፦ ⭐️  ቀለሜ ለመሆን የመጀመሪያው Step ፍላጎት ነው። አብዛኛው ተማሪ የሚሸወደው ያለ ፍላጎቱ ስለሚያነብ ነው። የማንበብ ፍላጎት ሳይኖራችሁ Exam ስላለባችሁ ብቻ ወይ ደግሞ ቤተሰብ አጥኑ ስለሚላችሁ ብቻ የምታነቡ ከሆነ ተሸውዳችኋል። ጊዜአችሁን ነው ምታባክኑት። ያለፍላጎት ማጥናት ማለት ድንጋይ ላይ ውኃ ማፍሰስ ነው ምንም አይገባችሁም። ስለዚህ የማንበብ ፍላጎት እንዲኖራችሁ በተቻላችሁ አቅም ክላስ ውስጥ መከታተል ይኖርባችኋል። ክላስ ውስጥ መከታተል፤ ያልገባችሁን መጠየቅ የማንበብ ፍላጎት እንዲኖራችሁ፤ ስታነቡም ቶሎ እንድትረዱት ያደርጋችኋል። ⭐️  እሺ አሁን ፍላጎት አለን። እንዴት ነው ቀለሜ የምንሆነው ❓ለምትሉ ደግሞ ሁለተኛው እና ዋናው Step የአጠናን ስልት መምረጥ ነው። የአጠናን ስልት እንደየሰዉ ጠባይ ይለያያል። ስለዚህ የራስን ጠባይ ማወቅ ነው። እንዳንዱ ጫጫታ ውስጥ ሁኖ ማንበብ የሚወድ ሰው አለ። በዛው ልክ ደሞ ሲያጠና ምንም አይነት ድምፅ መስማት የማይፈልግ የነፋስ ሽውታ እንኳን የሚረብሸው ሰው አለ። ረዢም ሰዓት ማጥናት የሚወድ አለ፤ ከ30 ደቂቃ በላይ ማጥናት የማይችልም ሰው አለ። Library ማጥናት የሚመቸው አለ፤ Library የማይመቸው አለ። ሌሊት የሚመቸው አለ፤ ሌሊት የማይመቸው አለ። እናንተ ከየትኞቹ ናችሁ ❓ እናንተ የምታውቋቸው ቀለሜዎች Library ስለሚገቡ ብቻ አትግቡ። ሌሊት ስለሚያነቡ አታንብቡ...ወዘተ። እናንተ የሚመቻችሁን ከናንተ ጋር የሚሄደውን አድርጉ። ሙዳችሁን ፈልጉ ...! ⭐️  የሚመቻችሁን ቦታ እና የአጠናን ስልት ከመረጣችሁ በኋላ የመጨረሻው step ሚሆነው ወደ ጥናት መግባት ነው። ስታነቡ የምታጠኑት ትምርት Main Concept ላይ ማተኮር አለባችሁ። ዝም ብላቹ ሙሉ መጽሐፉን እንደ ልቦለድ ማንበብ የለባችሁም። ስታነቡ Short ኖቶችን የእየያዛችሁ መሆን አለበት ( short note መያዛችሁ በአጭሩ ለመከለስ እንዲሁም ለማስታወስ ይረዳችኋል)። ሌላው ያነበባችሁትን በቃላችሁ ለማስታወስ መሞከር፤ በቃላችሁ መድገም። ታዲያ ስታነቡ እንዳትሰላቹ ራሳችሁን ሳታስጨንቁ ዘና ብላችሁ። አንብባችሁ ስትጨርሱ ምን ያህል እንደተረዳችሁት ለማወቅ ጥያቄዎችን ከተለያዩ መጽሐፍቶች መስራት። የሚከብዳችሁ ጥያቄ ካለ ደግማችሁ ማንበብ። ይሄን ማድረግ ያነበባችሁትን ነገር እንዳትረሱት ያደርጋል። በተጨሚሪም የExam ቀን Over Tension አትሁኑ። ከExam በፊት በደንብ አንብቦ መግባት፤ ያነበቡትን መስራት(ፈተና ስትሰሩ ረዥም ጊዜ የሚወስዱ ጥያቄዎች ላይ ጊዜ አታጥፉ)። ክላስ ውስጥ ያልገባችሁን ጠይቁ (መምህራችሁን ወይም የገባውን ተማሪ)። የማስታወስ አቅማችሁ እንዲጨምር፤ የንባብ ልምዳችሁም እንዲዳብር ከትምህርት ውጪ በትርፍ ግዜያችሁ የተለያዩ መጻሕፍቶችን አንብቡ። ጊዜአችሁን በአግባቡ ተጠቀሙ አልባሌ ነገሮች አታብዙ። ማንበብ ባለባችሁ ሰዓት አንብቡ። ትምህርታችሁ ላይ ትኩረት አድርጉ። ከላይ የነገርኳች የሦስተኛው ተማሪ የቀለሜነት ምሥጢር ይሄው ነው። 👆 በመጨረሻም ቀለሜነት Through Process የሚመጣ ነገር ስለሆነ ከላይ ያልኳችሁን ነገሮች ደጋግማችሁ ካደረጋችሁ። ቀለሜ የማትሆኑበት ምንም አይነት ምክንያት የለም። ቀለሜነት ይለምልም ‼️ ⏱  ክፍል 🚩 ይቀጥላል......... @Qesem_Freshman ❤️
نمایش همه...
👍 13 3🥰 2
🙂አንዳንዴ እኮ ምንም ሳይጎድለን ትዕግስት ማጣት ብቻ ባለንበት ያስቀረናል። ይቺ አለም ትንፋሹን ዋጥ አርጎ ለረጅም ጊዜ የቆየ የሚያሸንፍባት መድረክ ናት። 🔺 ለምሳሌ መዝናናት ፈታ ማለት እያማረህ ግን ቆይ እስኪ ዛሬ ይለፈኝ ማለት ከጀመርክና ያን ጊዜ ለሚጠቅምህ ነገር ከተጠቀምከው አትጠራጠር ትክክለኛው መንገድ ላይ ነህ። ያ ተከታታይ ድራማ ዛሬ ይለፈኝና ጥናት ላጥና ማለት ከጀመርሽ ለውጡን በቅርቡ ታዪዋለሽ። ትዕግስት ማለት ገንዘብ አውጥቶ ፈታ ማለት ያምርህና ግን ለምን አንደኛዬን ጥሩ ጊዜ ሲኖረኝ አልዝናናም ብሎ ወጥሮ መስራት ነው። @Qesem_Freshman ❤️
نمایش همه...
🥰 16👍 14❤‍🔥 7🔥 2🙏 2
Repost from Qesem Crypto
Imagine you 5 years from now: - You're in the best shape - You own a thriving business - You own rental properties - Your assets are making you richer - You're dating your favorite person The only way you can make that happen is if you take action now. Don't dream. Do. Qesem Crypto  ⭐
نمایش همه...
👍 2 1
ውዶቻችን ይሄን Bot Start በሉልን!ለኛ ይጠቅመናል🥰 https://t.me/dogshouse_bot/join?startapp=UFiI1ytzQ_SNI0AieBLfvA
نمایش همه...
❤‍🔥 3🥰 3🤝 2👍 1😍 1
የጂኒየስነት ሚስጢር  ክፍል ሰባት.........! 📚 ውዶቼ ቀለሜዎችን ከሚያቁት እንካቹሁ በሉ በተባልነው መሰረት ስለ-አጠናን-ስልት ላወጋችሁ ወደድኩ።     የአጠናን ስልት  ❓ 📚 በትምህርት አለም ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ እንደ spinal cord  የምናየው ነገር ቢኖር ንባብ ነው። ትምህርት እና ጥናት (ንባብ) የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ ናቸዉ፤  እና ብዙዎቻችን ንባብ አስፈላጊ መሆኑን እናውቃለን፤ ማንበብ እንዳለብንም እናምናለን ግን በአንድም ይሁኑ በሌላ ምክንያት አናነብም። አንገርምም ❓      ግን የምር  ለምን አናነብም ❓ 📚 ለንባብ እንቅፋት ከሚሆኑብን ነገሮች መካከል ፦ 📍 ለራስ ዝቅተኛ ቦታ መስጠት ( ባነብም አይገባኝም የሚል እሳቤ) አንዱና ዋነኛ ነው፤ እስቲ ይሄ አይነት ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የሆነ ነገር ልበል ፦ 💬 አንባቢ ለመሆን ስናስብ ማድረግ ያለብን ቅድመ ሁኔታዎች ፦ ( የምርም ይሰራል ) 📍 class አለመቅጣት ( አስቸኳይ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር መቅጣት የለብንም፥ class ከገባንም በኃላ ትኩሰት ሰጥተን መከታተል፤ short note መውሰድ፣ እንደሰማውት ከሆነ የግቢ መምህራን ከሚፅፉት ይልቅ ሚያወሩት ፈተና ላይ ማምጣት ይቀናቸዋል፤ እና በሚያወራበት ጊዜ ከአፍ ከፍ እየለቀምን note  መያዝ ይጠቅማል ። 📍 ሁል ጊዜ ቋሚ የሆነ የንባብ ፕሮግራም ሊኖረን ይገባል፤ ያለንበትን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ቋሚ ፕሮግራም ቀርፀን ወደ ተግባር መቀየር። 📍 መከተል ያለብን የንባብ ሙድ በተመለከተ የራሴን ሙድ ላካፍላችሁ፥ SQ3RA ይባላል detail ለማየት ያህል ፦ ✏️ S= Survey ( የገረፍታ ንባብ ማለትም ስለምናነበው ነገር ለማወቅ ይረዳናል፤ ለ 1 ገፅ ምን ያህል ደቂቃ ይበቃል ካላችሁ ደግሞ minimum 4 min ) ✏️ Q= Questioning( by using WH questions, why... How..  በሚሉት logical  ጥያቄዎች ማውጣት፤ አስተውሉ ምናወጣው ጥያቄ አመራማሪ እና ከበድ ማለት አለበት።) ✏️ 3R=3 round Reading (እስኪገባን ድረስ ደጋግመን ማንበብ) ✏️  A= answering the questions 💭 አለቀ ይሄን ካረጋችሁ ቀለሜነት የግላችሁ ነው ።    በመጨረሻሞ  ❓            #ነፃ #ምሳ #የለም።   ሁሉም-ለምሳው-መከፈል-ያለበት-ክፍያ-መክፈል-አለበት። የፈለገውነውን field  መግባት ፈልገን ፣ ጥሩ ውጤት ማምጣት አምሮን፣ እንቅልፍም አምሮን፣ እንደፈለግንም መሆን አሰኝቶን ወፍ ሲያምርህ ይቅር !! እንድትበሉ ክፈሉ ...!   💡 ነፃ ምክርም የለም ❓በሉ  ክፈሉ ( tipወንም ሳትረሱ ...! )* 📚 ለሁላችንም መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንልን፤ የፈለግነው field  የሚያስገባ ውጤት ለካ እንደዛ ከሆነ  ሀገሩ ሁሉ ዶክተር ሊሆን  ነው ❓ ብቻ የA+ መዓት ይክበባችሁ ። ( አሜን በሉ ❓ አሜን ለሁላችን  ..! ) 🔜 ክፍል 8 ይቀጥላል......... @Qesem_Freshman ❤️
نمایش همه...
👍 23😍 8❤‍🔥 6 5🙏 2
Repost from Qesem Crypto
Photo unavailableShow in Telegram
TRADING FACTS YOU WISH YOU KNEW Qesem Crypto  ⭐
نمایش همه...
የጂኒየስነት ሚስጢር  ክፍል ስድስት.........! ያለው የሰጠ ንፉግ አይባልም ❓ 💭 ይሄን ታውቁ ይሆን ❓ የሽምደዳ እና የኮንሴፕት ትምህርቶች ለየቅል ናቸው ። እንዴት ❓ተከተሉኝ 📚 ሽምደዳ ቃል በቃል መፅሐፉ ላይ የሰፈሩትን ዓ.ነገሮች አእምሮ ላይ ማስፈር ነው። ኮንሴፕት ግን ከዚ ይለያል የኮንሴፕት ትምህርት ከናንተ የሚፈልገው እዛጋ ምን አይነት ሃሳብ ያትታል የሚለውን ብቻ ነው  ስለዚህ ሃሳቡን እንጂ የቋንቋ መዋቅሩን ከመፅሐፉ መውሰድ አይጠበቅባችሁም ማለት ነው። ተግባባን ❓ 📚 በውነቱ የሽምደዳ ትምህርት የሚባል ነገር በሰብጀክት ደረጃ አይቼ አላውቅምየለምም (እንደኔ) ። ይልቁንም በአንዳንድ ቦታዎች ላይ  ሽምደዳ ግድ የሚሆንባቸው ሰብጀክቶች እንዳሉ እሙን ነው (በተለይ የሶሻል subjects ..... ✏️ ይሄን ካልኩ ዘንዳ ስለ ሽምደዳ ከማውራት ይልቅ ስለ ኮንሴፕት ማውራቱ ሞር ኢንክሉሲቭ ሆኖ እናገኘዋለን። 📚 እኔ በግሌ የምመክራቹህ የኮንሴፕት ትምርቶችን ለማጥናት የሚያስፈልገው ቋንቋ ብቻ ነው ብዬ ነው።ረዥም ፅሑፍ ሳነብ ይሰለቸኛል..ይቸከኛል....ይደብረኛል...ምናምን ልትሉ ትችላላቹ ግን የዚ ሁሉ መፍትሔው ቋንቋውን(English) በጥራት ማወቅ ነው። ማንም ሳያዝህ ረዥም ልቦለድ ታነብ የለንዴ ❓ ማንም ሳያዝሽ የፍቅር ታሪኮችን አድነሽ ታነቢ የለንዴ ❓ እኮ!  ጠቡ ከማንበብ ሳይሆን  ከሚነበበው ጋር ነው ማለት ነው።     📚 እኔ እያልኳቹህ ያለሁት ያ ልቦለድ ባማረኛ መፃፉ ነውንጂ ልባችሁን ስቅል አድርጎት አንድታነቡት የጠራችሁ  በእንግሊዝኛ የተፃፈ ልቦለድ ብታገኙ ባላየ ታልፉታላቹህ ነው። እኔ እያልኳቹህ ያለሁት ሂስትሪ መፅሐፍን አንስታችሁ በካልቾ ጠልዙት ጠልዙት የሚላችሁ በእንግሊዝኛ መፃፉ እንጂ በአማረኛ ተተርጉሞ ቢቀርብ አዳሜ  በሁለት ቀን ትጨርሺው ነበር ነው። ስለዚህ ጠቡ ከሰብጀክቱ ጋርም ሳይሆን ከቋንቋው ጋር ነው ማለት ነው። 📚 አሁን ስኮፑ ጠበበ አ ❓ .... ሐተታ አላብዛባቹህ  የእንግሊዝኛ ቋንቋ ችሎታችሁን ፈትሹ! 📚 ሌላው የማንበቢያ ወቅት ላይ ያለ ችግር ነው።  የኮንሴፕት ትምህርቶች በባህሪያቸው የናንተን አሪፍ ሙድ ላይ መሆን ይፈልጋሉ። bad የሚባል ሙድ ላይ ሁናቹህ ብታነቧቸው ጉንጭ ማልፋት ብቻ ነው ትርፉ! even እየያዛቹሀቸው ሁላ ሊመስላችሁ ይችላል በጊዜው ስታነቧቸው ግን በኋላ ወደ ጥሩ ስሜት ተመልሳቹ ያንኑ ገፅ መልሳቹ ብታነቡት አዲስ ይሆንባችሁና ያኔ እንዳላነበባቹ ይገባቹሃል። ስለዚህ በቀን ሁሌ 5 ገፅ መንበብ አለብኝ ብላቹ ወስናቹ አንዳንዴ እየደበራቹህም ጭምር አምስት ገፁን ለመሙላት ብትታትሩ ገደል ነው የሚከታቹህ!  የኮንሴፕት ትምህርቶች ላይ ገፅ 18 ሳይገባህ ገፅ 19ኝን ብታነበው መዘዙ የያዝከው Unit እስኪያልቅ እንደተደናበርክ summary ላይ ትደርሳለህ! 📚 ስለዚህ ውድ ተማሪዎች እንደኔ ጥሩ ሙድ ላይ ስትሆኑ ገፅ መቁጠሩን አቁማቹህ በደንብ ገፋ አድርጋችሁ አንበቡ ባይ ነኝ። የማስታወስ ችግር ❓ 📚 እርግጥ ነው አብዛኞቻችን የማስታወስ ችግር አለብን ብለን እናምናለን። ግን ልብ በሉ ማንኛውም አእምሮ በአጭርም ሆነ በረዥም የጊዜ ርቀት ላይ የተተገበሩ ክንውኖችን ለማስታወስ የሚጠቀመው መርህ አንድ ነው እሱም ክንውኑ ከተለመደው ወጣ ያለ(extraordinary) ነገር በክንውኑ ውስጥ ሲኖር ነው።አንተ እንደ ልቦለድ ተርርር አድርገህ ያነበብከው የሂስትሪ ትምህርት ከወር በኋላ ለፈተና ስትቀርብ ቢጠፋህ ይገርመሀልን ዴ ❓ የዛሬን ሳምንት ምን አይነት ውሎ እንደዋለ የማያስታውስ ስንት አለ ከኛ ውስጥ ❓ ማክሰኞ ለት ከሰአት የት ነበርክ ብትለው ጭራሽ የማይመልስ "አባ መርሳት" ተማሪ ብዙ ነንኮ።  ስለዚ ባጭሩ አለማስታወስህን መንቀፍ አቁምና ordinary የንባብ ስልትህን(ተርርር🙈) ወደ marked events የበዙበት extraordinary የንባብ ስልት ተሸጋገር!  just make a difference  ተግባባን ❓ 💬 ለምሳሌ እኔ ነገሮች እንዲታወሱኝ የማደርግበት ዘዴዬ የገባኝን ለሌላ ጓደኛዬ በመተንተን ና በያንዳንዱ ፓራግራፍ መጨረሻ 'ምን አይነት ጥያቄዎች ከዚህ ሐተታ ሊወጡ ይችላሉ ❓' በማለት አስባለሁ። ጊዜ ካለኝ ሊወጡ የሚችሉ ከባባድ ጥያቄዎችን ራሴ አውጥቼ አስቀምጥና አልፋለሁ። (ሁሉም ቀለሜ የራሱን ልዩነት መፍጠሪያ መንገድ ራሱ ያውቃል። የማያቅ ይሰርቃል ..!) 📚 አብዝቼው እንዳላሰለቻቹህ የማጥናቱን ነገር ይሄን ያክል ካልኳቹህ ሌሎች ተማሪዎችም ከሚሰጧቹህ አስተያየት ጋር በቂ ስለሚሆን ስለፈተና ሁለት ነገር ልበላቹህና ይብቃኝ.... ( ተከተሉኛ ❓)       🔎  ስለ ፈተና 📍 የኮንሴፕት ትምህርት ፈተና ላይ የቀለልህን ጥያቄ በጣም በጣም ትኩረት ስጠው! 📍 አጤሬራ መያዝ አእምሮህን አለማመን ነውና  'ከሃዲ' ብለህ የሰደብከው አእምሮህ ከአጤሬራው ውጭ ያሉ ጥያቄዎችን አሰላስሎ ይመልስልኛል ብለህ ካሰብክ የዋህ ነህ ማለት ነው። (just አትያዙ! ለማለት ነው ..!)......ጨረስኩ ..! 🔜 ክፍል 7 ይቀጥላል......... @Qesem_Freshman ❤️
نمایش همه...
👍 17🥰 6❤‍🔥 3
Repost from Qesem Crypto
Photo unavailableShow in Telegram
Hello, here are the highlights for this morning: 💰 Over the past week, net inflows into spot BTC-ETFs totaled +$238.4 million, compared to an outflow of -$37.3 million the week before. 📈 😱 Santiment: After a brief rebound that sparked hope, cryptocurrencies have once again pulled back, bringing fear back to the crypto market. 😨 ⚡️ Japanese company Metaplanet acquired an additional 42.47 BTC worth $2.42 million. The purchase occurred when the price of BTC dropped below $54,500. 💸 🔪 Messari's CEO stated that Messari will start a war against the corrupt and illegal agency (SEC) in the coming months. ⚔️ 🚀 Celo is launching the Dango Layer 2 testnet as the first step towards joining the Ethereum ecosystem. 🌐 #news Qesem Crypto  ⭐
نمایش همه...
Repost from Qesem Crypto
Photo unavailableShow in Telegram
Guys, don't tell that making money is HARD ❌ Even 20 years old guys who work with me make in 5-10 times more than their parents 🔥 It all depends on the path you choose: working for someone 9/5 to pay the bills, or working on your own for just 20 minutes a day and earning thousands of dollars 😎 Software developer tells and shows how his subscribers earn from 1000$ every day 10 FREE SPOTS LEFT, subscribe now!  —  https://t.me/+QOjeTm_N4f9kNDky
نمایش همه...
የጂኒየስነት ሚስጢር ክፍል አምስት..........!   📚 ከራሴ ልምድ በመነሳት ስለ አጠናን ዘዴዎች አንዳንድ ነገሮችን ላንሳላችሁ ፦ 💭 በመጀመሪያ ስታጠኑ በተቻላችሁ መጠን ላለመጨናነቅ ሞክሩ። ስለ ውጤት መውረድ ወይም ስለትምህርቱ ክብደት እያሰባችሁ በጭራሽ ለማጥናት አትሞክሩ ምክንያቱም ምንም ትርፍ የለውም። ራሳችሁን ዘና አድርጉ motivated ሆናችሁ አጥኑ እመነኝ ትኩረት እስከሰጣችሁት ድረስ የማይሳካ ምንም ነገር የለም። አመናችሁኝ ❓ እንቀጥል ..! 💭 የተወሰኑ እኔን የጠቀሙኝን የጥናት ዘዴዎች ልንገራች ፤ ተከተሉኝ ፦ 📍 ጥያቄ አውጡ ❓ 📚 እስካሁን ከብዙ ሰዎች እንደሰማችሁት ጥያቄዎችን መስራት ውጤታማ የሆነ የጥናት ዘዴ ነው። የ worksheet , አጋዥ መፅሐፍት ፣ እንዲሁም text book  ጥያቄ መስራት ጠቃሚ እንደሆነ ታውቃላችሁ ብዬ አስባለሁ። ዛሬ እኔ ሌላ ቴክኒክ ላሳያችሁ....ምን በሉኛ ❓    በራሳችሁ ጥያቄ አውጡ። 📚 እኔ አስተማሪ ብሆን ኖሮ ምን ጥያቄ ነበር ልጆቼን የምፈትናቸው ብላችሁ አስቡ። ይሄንኑ ጥያቄ ራሳችሁን መልሳችሁ ፈትኑ። ከጓደኞቻችሁ ጋር ስሩት ። ለምን ይጠቅማል ያላችሁ እንደሆነ ከማንበብ በተጨማሪ የጥያቄ አወጣጥ (exam question concept) ታገኙበታላችሁ ። ላውጋችሁማ ❓ 📚 እኔ የማልረሳው አንድ ታሪክ አለ። የ elementary ተማሪ እያለሁ ሳይንስ አስተማሪያችን ፈተና ሲቃረብ አካባቢ አሳይመንት ሰጠን። አሳይመንቱ እኛ በራሳችን ጥያቄ አውጥተን ከነመልሱ ሰርተን ማስገባት ነው።  የሚገርመው ነገር እኔ ያወጣሁአቸውን ጥያቄዎች ፋይናል ፈተና ላይ በብዛት አገኘሁአቸው። የመምህራንን exam question psychology ስታገኙ ትምህርቱ ልክ እንደ ውሀ ቀላል ነው ሚሆንላችሁ።     📍concept ያዙ ❓ 📚 በጣም ብዙ ተማሪዎች በደንብ እያጠኑ ግን ውጤታማ ሳይሆኑ ሲቀሩ ይታያል። ለምን ❓ ከተባለ የሚያነቡት መፅሐፉ ላይ ያለውን ፅሁፍ እንጂ Conceptun አይደለም። የምናነበው ነገር ስለምንድነው  እያወራ ያለው ❓ ምን እንድንይዝ ነው የተፈለገው ❓ ብለን ራሳችንን መጠየቅ አለብን። ✏️ ቆይ ጥናታችን ውጤታማ እንዲሆን ምን እናድርግ ❓ 💡 ክላስ አትቅጣ 📚 ይብዛም ይነስም teacherሩ የሚነግረን concept ዋጋ አላት። ጂኒየስም ይሁን አይሁን የሚያስረዳበት መንገድ ይጣፍጥም አይጣፍጥ ክላስ ተከሰት ። 💡 ከጓደኞቻችሁ ጋር ተጠያየቁ።  📚 አሪፍ ጀማ ሰርታችሁ ጥያቄ ፍለጡ ፤ ጥሩ እና መልካም ጓደኞች ጋር የሚደረግ ጥረት ትልቅ effect አለው ። 💡 informal way ተጠቀሙ። 📚 በጨዋታ (በቀልድ) አስታካችሁ የያዛችሁትን ዕውቀት ልትረሱ ብትፈልጉ ራሱ አትችሉም ፣ በፌዝ መልክ አውሩት። እንደ ጉርሻ ❓ 📚 ከformal ጥናት ውጪ በሆናችሁ ጊዜ በማያጨናንቃችሁ መልኩ meditate አድርጉት ። ተመስዕጦ ራስን ለማግኘት ምርጥዬ መንገድ ነው ። (የግል ምክር ) 🔎 በተለየ መልኩ ደግሞ 💭 📍 አልችልም የሚል ሀሳብን አስወግዱ። ትችላላችሁ ...! መቻልን ተሸክሞ የመጣ የለም ሁሉም በምድር በጥረቱ አበጅቶት ነው ።  📍 በሚመቻችሁ ጊዜና ቦታ አጥኑ። ቀን or ማታ  ላይብረሪ ወይም ከሰው ጋር  ብቻ እናንተ በለመዳችሁት setting ( የምታውቁትን ጎበዝ ተማሪ ሳይሆን የራሳችሁን መንገድ ፍጠሩ ..!) 📍ፈታ በሉ ፤ ግን ከትምሮ መቼም አትራቁ። because ርቆ መመለስ ከባድ ነው ሚያረግባችሁ ...ስትኖሩ ተማሪ መሆናችሁን አትርሱ ...! 🔜 ክፍል 6 ይቀጥላል......... @Qesem_Freshman ❤️
نمایش همه...
ቀሰም Academy

💡ቀሰም Academy ከHigh school እስከ Campus ለሚማሩ ተማሪዎች ፤ ቲቶሪያሎችን ፣ጠቃሚ የንባብ ስልቶችን ፤Soft Copy የሆኑ አጋዥ የንባብ ማቴሪያሎችን ፣ትምህርታዊ መረጃዎችን እና አነቃቂ መልዕክቶችን በማዘጋጀት ለተማሪዎች ንቃት የሚተጋ ቻናል ነው!📚 📩For comment :- @Qesem_fam Buy ads:

https://telega.io/c/QesemAcademy

👍 24❤‍🔥 6🥰 5🎉 2🔥 1🤗 1
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.