AlltechUp.com
رفتن به کانال در Telegram
etechup.com የቴክኖሎጂ አለምን ያዳርሳል! 🚀 የቅርብ ጊዜ ፈጠራዎች፣ ጥልቅ ትንታኔዎች፣ ዜናዎች፣ ወርክሾፖች እና ምርጥ የዘርፉ ምርቶችን ይከታተሉን💻📱 ከAI እስከ ፋይናንስ ቴክኖሎጂ፣ ከAi እስከ ጌሚንግ እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም መመሪያዎች—ሁሉንም አካትተናል። 💡
نمایش بیشتر3 429
مشترکین
+124 ساعت
-187 روز
-9530 روز
آرشیو پست ها
3 429
የዊንዶውስ 10 መዘጋት (Crash) መንስኤዎች እና መፍትሄዎች
.
.
.
ዊንዶውስ 10 ድንገት ሊዘጋ (Crash ሊያደርግ) የሚችልባቸውን ሰባት ዋና ዋና ምክንያቶች እና ለእያንዳንዱም ትክክለኛ መፍትሄዎች ከዚህ በታች ቀርበዋል፦
---
🙋 1. የሙቀት መጨመር (Overheating)
ኮምፒውተርዎ ከልክ በላይ ሲሞቅ ስርዓቱን ከጉዳት ለመጠበቅ በራሱ ሊዘጋ ይችላል።
* መንስኤ: - የአየር ማናፈሻ ቀዳዳዎች መዘጋት፣ የአቧራ ክምችት፣ ወይም የማቀዝቀዣ ስርዓት (Fan) ብልሽት ሊሆን ይችላል።
መፍትሄዎች:-
* የኮምፒውተርዎን አየር ማናፈሻ ቀዳዳዎች ሁልጊዜ ንጹህ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
* ኮምፒውተሩን ለስላሳ ቦታዎች (እንደ አልጋ ወይም ሶፋ) ላይ ከመጠቀም ይቆጠቡ።
* በየጊዜው የኮምፒውተርዎን ውስጠኛ ክፍል አቧራ ያጽዱ።
* ለላፕቶፖች የማቀዝቀዣ ፓድ (Cooling Pad) ይጠቀሙ።
---
🙋 2. የተበላሹ ወይም ያረጁ ድራይቨሮች (Outdated or Faulty Drivers)
ድራይቨሮች ሃርድዌርዎ ከዊንዶውስ ጋር በትክክል እንዲግባባ ያደርጋሉ። ሲበላሹ ወይም ሲያረጁ ስርዓቱ ሊዘጋ ይችላል።
* መንስኤ: - አዲስ የዊንዶውስ ዝመና፣ የተበላሸ የድራይቨር ጭነት ወይም ጊዜ ያለፈባቸው ድራይቨሮች
* መፍትሄዎች :-
ወደ Device Manager ይሂዱ እና ችግር ያለባቸውን ድራይቨሮች ያዘምኑ (Update ያድርጉ)።
* የቅርብ ጊዜው ድራይቨር ችግር ካመጣ፣ ወደ ቀድሞው ስሪት ይመለሱ (Roll Back Driver ያድርጉ)።
* የሃርድዌር አምራች (ለምሳሌ፡- NVIDIA፣ AMD፣ Intel) ድረ-ገጽ በመሄድ የቅርብ ጊዜውን ድራይቨር አውርደው ይጫኑ።
---
🙋 3. የሃርድዌር ብልሽት (Hardware Malfunction)
የኮምፒውተርዎ ዋና አካላት ሲበላሹ ዊንዶውስ ሊዘጋ ይችላል።
* መንስኤዎች : - የራም (RAM) ችግሮች፣ የሃርድ ድራይቭ/ኤስኤስዲ (HDD/SSD) መበላሸት፣ ወይም የኃይል አቅርቦት ክፍል (PSU) ብልሽት ሊሆን ይችላል።
* መፍትሄዎች:-
* ራም (RAM):- የዊንዶውስ Memory Diagnostic Tool (የማስታወሻ ምርመራ መሣሪያ) በመጠቀም ራምዎን ይሞክሩ።
* ሃርድ ድራይቭ/ኤስኤስዲ :- የዊንዶውስ Check Disk (chkdsk) ትዕዛዝን በመጠቀም ሃርድ ድራይቭዎን ለስህተቶች ይፈትሹ።
* PSU :- የሃይል አቅርቦትዎ በቂ ሃይል መስጠቱን ወይም አለመሆኑን ያረጋግጡ። በብልሽት ከተጠረጠረ በአዲስ ይተኩት።
* እርግጠኛ ካልሆኑ ባለሙያ ያማክሩ።
---
🙋4. ብዙ ፕሮግራሞችን በአንድ ጊዜ መክፈት (Too Many Programs Running)
በአንድ ጊዜ ብዙ ሃይል የሚጠይቁ ፕሮግራሞችን ሲከፍቱ ኮምፒውተሩ ከመጠን በላይ ይጫናል።
* መንስኤ:- በቂ ያልሆነ ራም፣ ወይም ሲፒዩ (CPU) በከፍተኛ አቅም መስራት ነው።
* መፍትሄዎች :- Task Manager ይክፈቱ እና ብዙ ሲፒዩ (CPU) ወይም ሜሞሪ (Memory) የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን ይዝጉ።
~ አስፈላጊ ከሆነ የኮምፒውተርዎን ራም ይጨምሩ።
~ በሚሰሩበት ጊዜ አላስፈላጊ የሆኑ የጀርባ ፕሮግራሞችን (Background Apps) ያጥፉ።
---
🙋 5. የሶፍትዌር አለመጣጣም (Software Conflicts)
* መንስኤ : - ሁለት ፕሮግራሞች ወይም አንድ ፕሮግራም ከዊንዶውስ ጋር በትክክል መስራት ሲያቅተው ወይም አዲስ የተጫነ ሶፍትዌር ወይም ዝመና/Update ከሌሎች ፕሮግራሞች ጋር አለመስማማት ነው።
* መፍትሄዎች :- ችግሩ የጀመረው አዲስ ፕሮግራም ከጫኑ በኋላ ከሆነ ያንን ፕሮግራም ያጥፉ ወይም Uninstall ያድርጉ።
* ፕሮግራሙን በአስተዳዳሪነት (Run as Administrator) ለመክፈት ይሞክሩ።
* የፕሮግራሙን Compatibility Mode (የተጣጣሚነት ሁኔታ) በመጠቀም በድሮው የዊንዶውስ ስሪት ላይ እንዲሰራ አድርገው ይክፈቱት።
---
🙋 6. የተበላሹ የስርዓት ፋይሎች (Corrupted System Files)
ዊንዶውስ ለመስራት የሚጠቀምባቸው ወሳኝ ፋይሎች ሲጎዱ።
* መንስኤ : - ያልተጠበቀ መዘጋት፣ የሃርድዌር ብልሽት፣ ወይም የተበላሸ የሶፍትዌር ጭነት።
* መፍትሄዎች : -
* System File Checker (SFC) ትዕዛዝን ይጠቀሙ። Command Promptን በአስተዳዳሪነት ይክፈቱ እና
sfc /scannow ብለው ይጻፉ። ይህ የተበላሹ ፋይሎችን ይጠግናል።
* DISM መሳሪያውን ይጠቀሙ። ከ sfc በፊት DISMን ማስኬድ ጥሩ ነው።
---
🙋 7. ቫይረሶች ወይም ማልዌር (Viruses or Malware Attacks)
* መንስኤ : - አደገኛ ሶፍትዌሮች ዊንዶውን በማጥቃት ኮምፒውተሩን ሊያዘጉት ይችላሉ። መንስኤውም ተንኮል አዘል ድረ-ገጾችን መጎብኘት ወይም አጠራጣሪ ፋይሎችን ማውረድ ነው።
* መፍትሄዎች : - የተሟላ እና የዘመነ አንቲቫይረስ ፕሮግራም (እንደ Windows Defender) በመጠቀም ኮምፒውተርዎን ሙሉ በሙሉ ይመርምሩ (Full Scan) ያድርጉ
* የስርዓትዎ ፋየርዎል (Firewall) ሁልጊዜ በርቶ መሆኑን ያረጋግጡ።
* ከማይታመኑ ምንጮች ሶፍትዌር አይጫኑ።
---
እነዚህን መፍትሄዎች በቅደም ተከተል በመጠቀም የዊንዶውስ 10ን የመዘጋት ችግር መፍታት ይችላሉ። ችግሩ ከቀጠለ፣ ምናልባት ዊንዶውስን እንደገና መጫን (Format/Reinstalling Windows) የመጨረሻው መፍትሄ ሊሆን ይችላል።3 429
+5
እነዚህ ፎቶግራፎች #በተገዛ (Paid) Ai የተቀየሩ ናቸው:: ያረጁ፣ የተበላሹ፣ የደበዘዙ፣ መጽሄት/መጽሃፍ ላይ የታተሙ፣ ጥቁር እና ነጭ የሆኑ . . . ፎቶግራፎችን ፍጹም በማይታመን ሁኔታ ይታደሳሉ። በመሆኑም የዚህ ዓይነት አገልግሎት ማግኘት የሚፈልግ ብዙ ሰው ሊኖር ስለሚችል በዝቅተኛ #ክፍያ ልንሰራላችሁ አቅደናል። ፍላጎት ያላችሁ @y7_666 ላይ ጻፉልን።
3 429
+1
ምን ትላላችሁ❓🙋
.
.
.
ምንም እንኳን ልብስ ሰፊ በሚያስንቁ ባለሙያዎች (ማዝገም) ምክንያት እንዳቀድኩት ባይፈጥንልኝም/ባይሆንልኝም ከቴክኖሎጂ፣ Ai እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ከማዘጋጀው ድረገጽ በመቀጠል #ticktock እና #Youtube የመጀመር ሀሳቡ አለኝ። ይሁን እንጂ በተለይም በርካታ ሰዎች #በAi ዙሪያ ያለውን አስደናቂ ፈጣን ለውጥ ማወቅና መጠቀም ጊዜ የማይጠይቅ በመሆኑ ፍላጎት ካላችሁ በአንድ ሳምንት ውስጥ #ticktock እጀምራለሁ። (100 ኮሜንት ላይ ከደገፋችሁ ልክ የዛሬ ሳምንት እጀምራለሁ - ቀኑን Save አድርጉ)
ከተች ያለው ፎቶግራፍ #Ai እንዴት እንደለወጠው ተመልከቱ፤ እናንተም በትንሽ ተጨማሪ እውቀት የተቀደደ የድሮ ፎቷችሁን ሳይቀር መመለስ ትችላላችሁ።
.
.
.
🙋ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇
🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
3 429
#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ . . .
ገመና ለማየት የሚንጋጋ ህዝብ ሁልጊዜ የወጥመድ ሰለባ ነው። ቁምነገር ሲጋራ ዞር ብሎ የማያይ ህዝብ የሴት ራቁት ሲባል ይርመሰመሳል። (ምን ያህል ሰው #React ፣ ምን ያህል #Comment እና ምን ያህል #Share እንዳደረገ ተመልከቱ - በነገራችን ላይ ይሄን #Mekdii የሚል አካውንት Unfollow በማድረግ ራሳችሁን አርቁ)
የሆነው ሆኖ #Comment ላይ የተቀመጠው ማስፈንጠሪያ (#link) (is.gd/j72BFq) የቴሌግራም አይደለም:: የቴሌግራም ሊንክ '#በt.me . . . ' ነው የሚጀምረው::
ይህ ማስፈንጠሪያ (#link) አጭር ሊንክ (Shortened URL) ሲሆን is.gd በሚባለው አጭር ሊንኮችን ለመፍጠር የሚያገለግል ታዋቂ አገልግሎት ሰጪ ድረ ገጽ የተቀየረ ነው። አጭር ሊንኩ ወደ የትኛው ድረ-ገጽ እንደሚያመራ ወይም Redirect የሚሆንበት ድህረ ገጽ URL expander ወይም URL unshortener ላይ አስገብተን ስናረጋግጥ https://www.google.com/search?q=obqj2.com ሆኖ እናገኘዋለን:: ይሁን እንጁ ይህ የድረገጽ አድራሻ ምን ሊሆን እንደሚችል በማየት ብቻ ማረጋገጥ አይችልም::
-----
ሆኖም ግን የፌስቡክ ገጹ በራሱ በማማለል ለማጭበርበር የተዘጋጀ እንደሆነ የሚያመላክቱ ይዘቶች በብዛት ስላሉት የተጠቀሰው ማስፈንጠሪያ (#link) አደገኛ የመሆን እድሉ እጅግ ሰፊ ነው::
#አደገኛ ሲባል:-
1. የማልዌር (Malware ድህረ ገጽ:-
ይህ ማለት ስትነኩት ወደ ኮምፒውተራችሁ ወይም ስልካችሁ ቫይረስ ወይም ሌላ አደገኛ ሶፍትዌር የሚያስገባ ድህረ ገጽ ሊሆን ይችላል::
2. የፊሺንግ (Phishing) ድህረ ገጽ:-
የግል መረጃችሁን (የይለፍ ቃል/Password፣ የቴሌ ብር፣ የባንክ መረጃ . . . ) ለመስረቅ የተዘጋጀ ሐሰተኛ ድህረ ገጽ ሊሆን ይችላል::
3. አፀያፊ ወይም የማይፈለግ ይዘት (Obscene or Unwanted Content):- የራቁትና የወሲብ ወይም ሌሎች ከሞራልና ከስነምግባር የሚቃረኑ ይዘቶች የሚጋሩበት ሊሆን ይችላል::
#ማድረግ_የሌለባችሁ
ማስፈንጠሪያውን (Linkን) ከመንካት ተቆጠቡ:: በፌስቡክ የምታገኙት ተመሳሳይ ማስፈንጠሪያም ሆነ መንነቱ ከማይታወቅ ሰው በEmail፣ በWhatsApp፣ በTelegram ወይም በሌላ መንገድ የሚላኩላችሁን አጠራጣሪ ሊንኮች በፍጹም አትንኩ። ምንም የሚያጓጓ ነገር በሌለበት ሁኔታ ወይም የማታውቁት/የሌላችሁ ነገር የተጋራ ይመስል በመንጋ መንጋጋትም አግባብ አይደለምና ረጋ ብትሉ ቅቤ ይወጣችኋል። 👌
.
.
.
🙋ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇
🙏🙆
#Telegram👇
https://t.me/horntechcom
#የፌስቡክ_ገጽ 👇
https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
#Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
3 429
✅ የAi "ቀይ መስመር" እንዲሰመር ተጠየቀ. . . 200 ታላቅ ሰዎች የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዓለም አቀፍ "ቀይ መስመር" እንዲሰመር ጥሪ አቀረቡ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ 8 የቀድሞ የአገራት መሪዎች፣ 10 የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች፣ 70 ዓለም አቀፍ ግዙፍ ኩባንያዎች፣ እና ሌሎችም 120 ታዋቂ የቴክኖሎጂ ሰዎች በቡድን ባቀረቡት ጥሪ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ ህጋዊ አስገዳጅ ዓለም አቀፍ ገደቦች ካልተጣሉ መጪው ጊዜ እጅግ አሳሳቢ እንደሆነ ገልጸዋል። ከታዋቂ ቴክኖሎጂስቶች መካከል የAi አባቶች በመባል የሚታወቁት ካናዳውያኑ የኮምፒውተር ሳይንቲስቶች ጂኦፍሬይ ሂንተን እና ዮሹዋ ቤንጊዮ (በ2018 በጋራ የዲጂታል ዓለም የኖቤል ሽልማት አሸናፊዎች) እንዲሁም እና የኦፕንኤአይ ተባባሪ መስራች ዎይቺክ ዛረምባ ይገኙበታል። ለመንግስታት ባቀረቡት ጥሪም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የስራ አጥነት፣ ሰው ሰራሽ ወረርሽኞች እና የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል ዓለም አቀፍ "ቀይ መስመር" እንዲዘረጋ አስገንዝበዋል። በAi የሚሰሩ የጦር መሳሪያዎች፣ ከፍተኛ የሳይበር ጥቃቶች እና ከሰው ቁጥጥር ውጭ ማሰብ፣ መስራትና መፈጸም የሚችል ጠቅላላ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AGI) እንዲታገዱም በአጽንኦት ጠይቀዋል። ለዚህም ሲባል በ2026 መጨረሻ ላይ ዓለም አቀፍ የቁጥጥር አካል እንዲቋቋም እና በመመሪያዎቹ ላይ ስምምነት እንዲደረስም አሳስበዋል። . . . ለተጨማሪ ተያያዥ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇 🙏🙆 #Telegram👇 https://t.me/horntechcom #የፌስቡክ_ገጽ 👇 https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/
3 429
አሜሪካ የመንግስታ መስሪያ ቤቶች ላማ (Llama) እንዲጠቀሙ ፈቀደች. . . ላማ (Llama) የተሰኘው የሜታ (Meta) ሰው ሰራሽ ልህቀት ሥርዓት (Ai system) በአሜሪካ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የእለት ተእለት ስራዎች ጥቅም ላይ እንዲውል ፈቃድ አገኘ ሮይተርስ አንድ ከፍተኛ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣንን ጠቅሶ ዛሬ እንደዘገበው መንግስት መስሪያ ቤቶች የሜታ ፕላትፎርምስ (Meta Platforms) ላማ (Llama) Ai እንዲጠቀሙ የተፈቀደው የትራምፕ አስተዳደር የንግድ ሰው ሰራሽ ልህቀቶችን በመንግስት ስራዎች ለማካተት የሚያደርጉት ጥረት አካል ነው:: በዚህም መሰረት የአሜሪካ የመንግስት ጠቅላላ አገልግሎት አስተዳደር (General Services Administration - GSA) ላማን በፌደራል መስሪያ ቤቶች ጥቅም ላይ እንዲውል በግዢ ዝርዝር ውስጥ እንደሚያካትት ይፋ አድርጓል:: የአሜሪካ የመስሪያ ቤቶች ላማን በነጻ መሞከር የሚችሉበት ሥርዓት የተዘረጋ ሲሆን በቀጣይ ቀናት ውስጥ GSA ላማን የመንግስትን የደህንነት እና የህግ መስፈርቶች የሚያሟላ መሆኑን ማረጋገጫ እንደሚሰጥ ይጠበቃል: ላማ የጽሁፍ፣ የቪዲዮ፣ የምስሎች እና የድምጽን ጨምሮ ማናቸውም ውስብስብ ሥራዎች በፍጥነትና በጥራት የማከናወን አቅም ያለው ትልቅ የቋንቋ ሞዴል (large language model - LLM) ነው። GSA ከዚህ ቀደም የሜታ ተወዳዳሪዎች የሆኑት አማዞን ዌብ ሰርቪስስ (Amazon Web Services)፣ ማይክሮሶፍት (Microsoft)፣ ጎግል (Google)፣ አንትሮፒክ (Anthropic) እና ኦፕን ኤአይ (Open AI) የመሳሰሉ ድርጅቶች የፈጠሯቸውን የሰው ሰራሽ ልህቀቶች (AIs) በግዢ ዝርዝር ውስጥ ማካተቱን ሮይተርስ በዘገባው አስታውሷል:: ለተጨማሪ ተመሳሳይ መረጃዎች ተቀላቀሉ 👇👇 . . . #Telegram👇 https://t.me/horntechcom #የፌስቡክ_ገጽ 👇 https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/ Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
3 429
#ታላቅ_የምስራች
"ቴሌክላውድ (telecloud)" አገልግሎቶች በሚያስደንቅ ዋጋ - #ከኢትዮቴሌኮም
.
.
.
---
#ኢትዮ_ቴሌኮም በ"ቴሌክላውድ (telecloud)" ያቀረባቸው አገልግሎት:-
🙋 Computer Services (የኮምፒዩተር አገልግሎቶች) : - ይህ አገልግሎት ኮምፒውተሮችን፣ ሰርቨሮችን እና የቨርቹዋል ማሽኖችን ከኢትዮ ቴሌኮም የዳታ ማዕከል (data center) #በሊዝ መከራየት (መጠቀም) የሚያስችል ነው፤ ግለሰቦች ወይም ተቋማት የራሳቸውን ውድ ኮምፒውተሮች ከመግዛት ይልቅ ተከራይተው ለመጠቀም ያስችላቸዋል።
🙋 የStorage Services (የመረጃ ማከማቻ አገልግሎት):- ድርጅቶች እና ግለሰቦች የራሳቸውን ውድ የሆኑ ሃርድዌር ከመግዛት ምንም ዓይነት የጥገና ወጪ የሌለው የኢትዮ ቴሌኮም #የCloud መሠረተ ልማት ላይ መረጃዎቻቸውን በአስተማማኝ ሁኔታ ማከማቸትና መጠቀም የሚያስችሉበት አገልግሎት ነው።
🙋 Network Services (የኔትወርክ አገልግሎቶች):- ይህ አገልግሎት ከኢንተርኔት ግንኙነት በተጨማሪ ድርጅቶች የራሳቸውን ቨርቹዋል ኔትዎርክ (VPN) ወይም ሌሎች የኔትወርክ አገልግሎቶችን ከኢትዮ ቴሌኮም የCloud ማዕከል ተከራይተው መጠቀም የሚያስችል ነው።
ይህ በመሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የሚወጣን ወጪ በመቀነስ ትኩረታቸውን በዋና የንግድ ስራቸው ላይ እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል።
🙋 Security Services (ደህንነት አገልግሎት):- ግለሰቦች ወይም ተቋማት ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የራሳቸው የሳይበር ደህንነት ቡድን እና መሳሪያ ከማዘጋጀት ይልቅ የኢትዮ ቴሌኮምን የደህንነት አገልግሎቶች በመጠቀም የሳይበር ጥቃቶችን መከላከል እና መረጃዎቻቸውን መጠበቅ የሚችሉበት ነው።
🙋 Backup Services:- ይህ አገልግሎት ወሳኝ መረጃዎች እና ፋይሎቻቸው ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ በኢትዮ ቴሌኮም #Cloud ላይ ለማስቀመጥ ያስችላቸዋል። ድንገተኛ አደጋ፣ የሃርድዌር ብልሽት ወይም ሌሎች ችግሮች ቢፈጠሩ ከዚህ ተቀማጭ መጠባበቂያ በቀላሉ ለመመለስ ያስችላል።
🙋 Container Services:- ይህ አገልግሎት አፕሊኬሽኖችን እና ሶፍትዌሮችን በ"ኮንቴይነር" (container) ውስጥ በማስቀመጥ በቀላሉ እና በፍጥነት ከተለያዩ ሲስተሞች ጋር እንዲሰሩ ያደርጋል። ይህም ገንቢዎች (developers) አፕሊኬሽኖችን መገንባትና አገልግሎት መስጠት ያስችላቸዋል።
🙋 Database Services:- ተቋማት የራሳቸውን ውድ እና ውስብስብ የዳታቤዝ ሲስተሞችን ማቋቋም አይጠበቅባቸውም፤ ይህን አገልግሎት በመጠቀም #በCloud የተመሰረቱ ዳታቤዝ አገልግሎቶችን በቀላሉ ለመጠቀም ያስችለል።
🙋 Enterprise Application:- ይህ የንግድ ተቋማት የሚፈልጓቸውን የተዘጋጁ ሶፍትዌሮች እና አፕሊኬሽኖች በቀጥታ ከCloud ጋር ለማገናኘት የሚያስችል አገልግሎት ነው። ለምሳሌ እንደ የደንበኞች አገልግሎት (CRM)፣ የሂሳብ አያያዝ (ERP) እና ሌሎች የንግድ ሥራዎችን ለማስተዳደር የሚያገለግሉ ሶፍትዌሮችን ያካትታል።
.
.
.
እያንዳንዱ ከላይ የተጠቀሱት አገልግሎቶች ደግሞ የተለያዩ አማራጮች አሏቸው።
ለምሳሌ #የሁለቱን ልጥቀስላችሁ🙏
1. #የኮምፒውተር_አገልግሎቶች (Computer Services)
ይህ አገልግሎት የሚከተሉትን ያካትታል።
👌 Elastic Cloud Server (ECS):- ይህ አገልግሎት የተፈለገውን ኦፕሬቲንግ ሲስተም (እንደ ዊንዶውስ ወይም ሊኑክስ) መርጣችሁ መጠቀም የምትችሉበት ቨርቹዋል ሰርቨር (Virtual Server) ነው። እንደ ፍላጎታችሁ ሲፒዩ፣ ራም እና ስቶሬጅ በቀላሉ መጨመር ወይም መቀነስ ትችላላችሁ።
👌 Bare Metal Server (BMS):- ይህ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በግል ብቻ የምትጠቀሙበት ፊዚካል ሰርቨር ነው። ከቨርቹዋል ሰርቨር ውጭ ምንም አይነት የመሃል ሶፍትዌር (virtualization layer) የለውም። ከፍተኛ ፍጥነት ለሚጠይቁ ስራዎች ሙሉ ሰርቨሩን ልክ እንደግል ኮምፒዩተር/ላፕቶፕ መጠቀም ይችላል።
👌 Image Management Service (IMS):- ይህ አገልግሎት የሰርቨር ምስል (image) ለመፍጠር፣ ለማስተዳደር እና ለማጋራት ያስችላል። ሰርቨሩን አንድ ጊዜ ካዘጋጁ ትክክለኛ ቅጂ (image) በመያዝ፣ ሌሎች ሰርቨሮችን በፍጥነት ለመፍጠር የሚያስችል ነው።
👌 Auto Scaling (AS):- ይህ አገልግሎት የአፕሊኬሽን ወይም የድረገጽ የትራፊክ ፍሰት በመከታተል፣ ሲጨምር ተጨማሪ ሰርቨሮችን በራሱ ይጨምራል፤ ሲቀንስ ደግሞ ይቀንሳል። (በጣም ወድጄዋለሁ)
---
2. #የክላውድ_ማከማቻ_አገልግሎቶች (Cloud Storage Services)
እነዚህ አገልግሎቶች የሚያካትቱት:-
👉 Elastic Volume Service (EVS):- ይህ አገልግሎት ለECS እና BMS ሰርቨሮች የብሎክ ስቶሬጅ (block storage) ያቀርባል። EVS ልክ እንደ ኮምፒውተር ሃርድ ድራይቭ ነው። በተለይም ሰርቨር ለመጫን እና የፕሮግራሞችን መረጃ ለማስቀመጥ ተመራጭ ነው።
👉 Object Storage Service (OSS):- ይህ አገልግሎት እንደ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች እና ሌሎች ፋይሎችን ለማስቀመጥ ይጠቅማል። OSS ብዙ መረጃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማስቀመጥ ጥሩ አማራጭ ነው።
👉 Scalable File Service (SFS):- ይህ አገልግሎት የብዙ ተጠቃሚዎች መረጃ በአንድ ላይ እንዲቀመጥ ያደርጋል። SFS ልክ በኔትወርክ ላይ እንዳለ ሼር (network share) ይሰራል፤ ይህም ፋይሎችን ከብዙ ሰርቨሮች በአንድ ጊዜ ለመድረስና ለመጠቀም ያስችላል።
.
.
.
#ኢትዮቴሌኮም እነዚህን የዘመኑ አገልግሎቶች በሚያስደንቅ ዋጋ አቅርቦ በአገር ውስጥ ቋንቋዎች በስፋት አለማስተዋወቁ ግርምትና ግርታ የሚፈጥር። ተቆነጃጅቶ ጨለማ ውስጥ መቀመጥ ምን ይሉታል❓ በፍጹም የማይጠበቅ!😪
.
.
.
በግል ወይም በተቋም ደረጃ መጠቀም ለምትፈልጉ ለየትኛው አገልግሎት የትኛውን መምረጥ እንደሚጠበቅባችሁ እና ተያያዥ የምክር አገልግሎቶችን ለአንድ ወር በነጻ እሰጣለሁ። በውስጥ ልታናግሩኝ ትችላላችሁ🙏
3 429
+2
#ታላቅ_የምስራች
"ቴሌክላውድ (telecloud)" አገልግሎቶች በሚያስደንቅ ዋጋ - #ከኢትዮቴሌኮም
.
.
.
ከዚህ ቀደም "ቴክኖሎጂክስ-አፍሪካ-ኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ አጋርቻችሁ ነበር። (ሙሉ ጽሁፉ https://www.facebook.com/share/p/1Fdww1JR1D/ ላይ ይገኛል )
በጽሁፉ ማጠቃለያ ላይ እንደ ቅሬታ ያቀረብኩት Ethio telecom በሁዋዌ የተገነባ ከፍተኛ አቅም ያለው የክላውድ ፕላትፎርም (Huawei Cloud Stack) ቢኖረውም አገልግሎቱ ከዋጋ አንጻር ተደራሽ አለመሆኑ ነበር። በተለይም በዘርፉ ክህሎትና የፈጠራ ብቃት ላላቸው ግለሰቦች እና ስታርትአፖች በዝቅተኛ ዋጋ (በልዩ ድጋፍም ቢሆን) አገልግሎቱ ቢሰጥ የሚኖረው አገራዊ ፋይዳ አሁን ከሚፈለገው ትርፍ በላይ እንደሆነ አመላክቼ ነበር።
ስለሆነም #ኢትዮቴሌኮም ከምገምተውና ከምጠብቀው በላይ በርካታ ተያያዥ አገልግሎቶችን ሊታመን በማይችል ዋጋ መስጠት መጀመሩ በእጅጉ የሚያስደስትና የሚያቦርቅ ዜና ነው። በወር 24 ብር የሚከፈልበት የኮምፒዩተር #ስቶሬጅ ኪራይ አገልግሎት ሳይቀር አላቸው (ከዚህ በኋላ ላፕቶፕ መግዛት ለምኔ?)
.
.
.
3 429
የቴክ ግምገማ (Tech Review)
#Surface_Laptop 7 - "የማክቡክ ገዳይ"በአገራችን እጅጉን ምርጥ እና አስደናቂ የሆነን ነገር፣ ምርት፣ ውበት. . . " ገዳይ ነው!" ይባላል። በእንግሊዝኛም ተመሳሳይ አገላለፅ ይጠቀማሉ:: ከምንም የላቀውን የሚገልጹበት ቃል "Killer . . . " ነው:: ይሁንና የማይክሮሶፍቱ Surface Laptop 7 Killer የተባለው ከላይ በተገለፀው መልኩ አይደለም:: ጭራሽ የአፕል ምርጥ የቅርብ ጊዜ ምርት የሆነውን MacBook Air M3 ገዳይ ወይም "The Macbook Killer" ነው የተባለው:: ማይክሮሶፍት አዲሱን Surface Laptop 7 ሲያስተዋውቅ ዋና ዓላማው አድርጎ የገለፀው የአፕልን ማክቡክ (MacBook) ለመፎካከር ከተቻለም ለመብለጥ ነበር። ላፕቶፑ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሰፊ ተቀባይነት አግኝቶ የተጠቃሚዎች እና የገበያ ብልጫ አግኝቶ ብዙዎች "Macbook killer" ሲሉ ጠርተውታል:: በዚህ ምክንያትም አፕል በመጪው የአውሮፓውያን ዘመን መለወጫ አካባቢ ለገበያ ለማቅረብ መርሃ ግብር ይዞለት የነበረው MacBook Air M4 በተጠናቀቀው ሀምሌ ወር ለሽያሽ ለማቅረብ ተገዷል:: ስለሆነም ከ20 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት እና በቴክኖሎጂ ምርቶች ገምጋሚነት የሰራው #የcreativeblog ፍሪላንሰር ኢያን ኢቨንደን ዳሰሳን ወደአማርኛ መልሼ አቅርቤዋለሁ:: ---
#ዲዛይንበዲዛይን ረገድ Surface Laptop 7 ከቀደሙት ሞዴሎች ብዙም የተለየ አይደለም። አሁንም ሳሳ ያለና የሚያምር አሉሚኒየም 'አካል' አለው። ከ13.8 ኢንች እና ከ15 ኢንች ስክሪን አማራጮች ጋር ቀርቧል። የቀለም አማራጮችም አዲስና ማራኪ ናቸው። ክብደቱ 1.66 ኪሎ ግራም አካባቢ በመሆኑ ለመያዝ ቀላል አድርጎታል።
#ፍጥነትይህ ላፕቶፕ እጅግ በጣም ፈጣን የሆኑትን አዳዲስ የኮዋልኮም ስናፕድራጎን ኤክስ (Qualcomm Snapdragon X) ፕሮሰሰሮችን ይጠቀማል። ይህ ፕሮሰሰር የሰው ሰራሽ እውቀትን (AI) በተሻለ ሁኔታ ይሰራል። እንደ 'Surface AI' የመሳሰሉ አዳዲስ ተግባራትን አካትቷል። ይህ ፕሮሰሰር ከማክቡክ ኤም (M) ቺፕስ ጋር ሊወዳደር የሚችል ፍጥነት እንዳለው እየተነገረ ነው።
#የባትሪ ዕድሜSurface Laptop 7 ብዙ ሰዓት የሚቆይ ባትሪ እንዳለው ተገልጿል። በአንድ ቻርጅ እስከ 20 ሰዓታት ድረስ መጠቀም እንደሚቻል ተፈሌገልጿል።
#ሶፍትዌርSurface Laptop 7 የተጫነለት ኦይሬቲንግ ሲስተም Windows 11 ነው።
#ፕሮሰሰርአዲሱ ስናፕድራጎን ኤክስ ፕሮሰሰር (ARM) ቴክኖሎጂን ስለሚጠቀም አንዳንድ የዊንዶውስ ፕሮግራሞችን ለመጠቀም የተለየ የኢሙሌሽን ቴክኖሎጂ (emulation) ይጠይቃል። ይህም አንዳንድ ጊዜ ፍጥነቱን ይቀንሰዋል።
#ማሳያ (Display)2496 x 1664 pixels ነው። ይህም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ምስሎችን ለማየት ከማስቻሉም ባሻገር ለጨዋታ (Gaming)፣ ለሞሽን፣ ለሶፍትዌር ፕሮግራሚንግ፣ ለ3d እና ለሌሎችም የግራፊክስ ስራዎች ተመራጭነት አስገኝቶለታል።
#ሰው_ሰራሽ ልህቀት (Ai)የራሱ የማይክሮሶፍት ከሆነውን ኮፓይለት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር የተዋሃደ ሲሆን በጥሩ ሁኔታ እንዲሰራ ተመስክሮለታል።
#ዋጋውበአማካይ $900 USD አካባቢ ሲሆን በእጅጉ ተመጣጣኝ እንደሆነ ተነግሮለታል። ከአጠቃላይ የተጠቃሚዎች ምላሽ በመሆነሳት ከ2024/25 ከወጡ ላፕቶፖች ቀዳሚ ተብሎለታል። በዚህም ለዓመታት በዘርፉ ሲያነክስ የነበረው ማይክሮሶፍት ከረጅም ጊዜ ጥናት እና ሙከራ በኋላ ያመጣው ላፕቶፕ የ"ማክቡክ ገዳይ" እንዲባል አስችሎታል።
#ጉድለትSurface Laptop 7 የሚጠቀመው ስናፕድራጎን ኤክስ ፕሮሰሰር (ARM) መሆኑ ብቸኛ ጉድለቱ ተብሎለታል። በዚህ ምክንያት ተጠቃሚዎች አንዳአንድ ሶፍትዌሮችን በEmulation ለመጠቀም ከመገደዳቸውም በላይ ጭራሽ የማይቀበላቸው (የማይሰሩ) የዊንዶውስ ሶፍትዌሮች መኖራቸውም ታውቋል። ይሁንና አሁንም በዊንዶውስ አርኤም (Windows on ARM) ላይ ያሉ የሶፍትዌር ችግሮች ሙሉ በሙሉ አልተፈቱም። ስለሆነም የላፕቶፑ ተመራጭነት የማያጠራጥር ቢሆንም ከመግዛት በፊት ገዢው የሚያስፈልጉት ሶፍትዌሮች ARM ፕሮሰሰር የሚሰሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ በጣም አስፈላጊ ነው። . . . #Telegram👇 https://t.me/horntechcom #የፌስቡክ_ገጽ 👇 https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/ #Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
3 429
የቴክ ግምገማ (Tech Review)
#Samsung_Galaxy_S25UltraየSamsung Galaxy S25 Ultra ስማርትፎን በ2025 ከወጡ ስልኮች መካከል እጅግ የላቀ ቦታ ይዟል:: ይህም ያደረገው በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ላይ የተመሰረቱ ባህሪያትን እና የአጠቃቀም በመላበሱ ነው::
#ንድፍየS25 Ultra ንድፍ ቀደም ባሉት ሞዴሎች ላይ የተመሰረተ ነው:: ነገር ግን ይበልጥ ለአያያዝ ምቹ እና ለእይታ ማራኪ ዘመናዊና ተደርጎ የተነደፈ ነው። የቲታኒየም ፍሬሙ (Titanium frame) ስልኩን ጠንካራ እና በቀላሉ ለጉዳት የማይጋለጥ አድርጎታል::
#ስክሪንባለ 6.9 ኢንች ዳይናሚክ AMOLED 2X ስክሪን አለው። ይህ ስክሪን እጅግ በጣም ደማቅ ቀለሞችን፣ ጥርት ባለ ምስል እና እስከ 120Hz የሚደርስ የማደስ ፍጥነት (refresh rate) ያቀርባል። ይህም ለቪዲዮ እይታ፣ ለጨዋታ (Gaming) እና ለዕለታዊ አጠቃቀም እጅግ በጣም ምቹ አድርጎታል።
#ፕሮሰሰርስልኩ በSnapdragon 8 Elite For Galaxy ፕሮሰሰር የሚሰራ ነው:: ይህም እጅግ በጣም ፈጣን ያደረገው ሲሆን ትልልቅ ጨዋታዎች (Gaming)፣ በርካታ ዲጂታል ስራዎች (multitasking) እና የላቁ የሰው ሰራሽ ልህቀት ተግባራት በአንድ ጊዜ ያለምንም ችግር ለማከናወን ያስችለዋል።
#የባትሪ ዕድሜበ5000mAh ባትሪ ተገጥሞለታል:: የተሻሻለው የሶፍትዌር እና የፕሮሰሰር ቅልጥፍናም የባትሪ ዕድሜውን አሳድጎታል። በአንድ ሙሉ ቻርጅ እስከ 31 ሰዓታት ቪዲዮ ማየት ይቻላል።
#የካሜራ ሲስተምS25 Ultra በካሜራው ጥራት ተወዳዳሪ የለውም። ዋና ካሜራው (main camera)የ200MP ነው፤ ሁለት የ50MP ቴሌፎቶ ሌንሶች (telephoto lenses) እና የ12MP አልትራዋይድ ሌንስ (ultrawide lens) አለው። እነዚህ ካሜራዎች በተሻሻለው የAI ProVisual Engine በመታገዝ የትኛውንም አይነት ፎቶ ወይም ቪዲዮ በከፍተኛ ጥራት ለመቅረጽ ያስችላሉ።
#ሰው ሰራሽ አስተውሎት (Ai)Galaxy S25 Ultraን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ፎቶዎችን ለማንሳት ያስቻለው የካሜራው AI ነው። ይህ Ai ምስል ለማስተካከል፣ ዳራ (Background) ለመለየት እና ሌሎችም በርካታ ተግባራትን ለማከናወን ያስችላል። በተጨማሪም ቪዲዮዎች በሚቀርጹበት ወቅት ያልተፈለጉ ድምጾችን ለማጥፋት የሚያስችል (Audio Eraser) የተባለ አዲስ ባህሪ አለው። Galaxy S25 Ultra የተካተተበት የካሜራው Ai ብቻ አይደለም። ዋነኛው መለያ ባህሪው በሰፊው የተካተቱት ሌሎች የAI ተግባራት ናቸው። ከእነዚህም መካከል:- * Circle to Search በእይታ ገጹ (Screen) ላይ የተፈለገውን በቀጥታ እንዲፈልግ (Search እንዲያደርግ) ያስችላል። * Live Translate በስልክ ጥሪ ጊዜ ድምጽ እና ጽሑፍን በቀጥታ ይተረጉማል። * AI ProVisual Engine በAi ታግዞ ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን ጥራት ያሻሽላል።
#ዋጋዋጋው እንደየአገሩ እና የማከማጃ (Storage) አቅሙ ይለያያል። የሁሉም ራም 12GB ሲሆን ማከማቻው (Storage) ግን 256GB፣ 512GB እና በ1TB ለገበያ የቀረበ ነው። እንደየአገራት የታክስ መጠንም የዋጋ ልዩነቶች አሉት። በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ 12GB ራም ተመሳሳይ ሆኖ 512GB ማከማቻ (Storage) $170,000 ብር እና 1TB እስከ $220,000 ብር አካባቢ ይሸጣል:: በተለያዩ አገራት በ1TB ማከማቻ (Storage) ከ $1500 - $2000 የአሜሪካን ዶላር እንደሚሸጥ ድረገጾች ላይ የሚገኙ የዋጋ መግለጫዎች ያመለክታሉ። ይህ ዋጋ በጣም ከፍተኛ ቢሆንም አቅሙ ላላቸው እና አዳዲስ ነገሮችን ለሚፈልጉ ሰዎች ምርጥ ምርጫ ነው።
#ጉድለቶችበአንድ ጊዜ ከፍተኛ ፕሮሰሰር ስለሚጠቀም በተለይም ቪድዮ ሲቀርጽ ተሎ ይግላል:: በተጨማሪም ከፍተኛ ባትሪ ይጠቀማል:: በተጨማሪም የካምፓኒው መረጃ ባትሪው እስከ 31 ሰዓታት ቪድዮ ማሳየት እንደሚችል ቢገልጽም በተግባር ግን በመደዋወልም ከ24 ሰዓታት በላይ አገልግሎት አይሰጥም:: . . . . #Telegram👇 https://t.me/horntechcom #የፌስቡክ_ገጽ 👇 https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/ #Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
3 429
#እንወያይ👌🙋ከሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ውጭ ህይወትን ማሰብ ዘግናኝ ነው:: ከእነዚህ ዘርፎች ውጭ ፈጣን ለውጥ ዝግ ነው:: የቀጣዩ ዘመን የሀብትና የእውቀት ማዕከል ሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ለመሆናቸው መጠራጠር አይገባም:: ለምሳሌ እነዚህ ቁልፍ ዘርፎች:- 1. የፈጠራ እና የእድገት ማነቃቂያ (Catalyst for Innovation and Growth) ናቸው:: 👌 በሌላ መንገድ የሳይንስ፣ የህክምና፣ የምህንድስና፣ የምርታማነት እና የሌሎችም ዘርፎች አዳዲስ ግኝቶችን እና ፈጠራዎችን ማሳካት ቀርቶ ማሰብም አይቻልም:: የገበያ ሥርዓቶችና አወቃቀሮች ሳይቀር የሚመሩት በሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ይሆነል፤ አሁንም ተጀምሯል። በሂደቱ ተገቢ እውቀትና ክህሎት ጨብጦ አዳዲስ የኢኮኖሚ እድሎችን መፍጠርና ከዘርፉ የድርሻን መጨበጥ ግድ ነው። 2. የእውቀት ተደራሽነት እና ስርጭት (Democratization of Knowledge and Access) ከሰው ሰራሽ ልህቀት (AI) እና ቴክኖሎጂ ውጭ አይታሰብም። ለተማሪዎች ሳይቀር የትምህርት ጥራትን በማሻሻል እና ተደራሽነቱን በማስፋት እኩልነትን ማረጋገጥ የሚያስችል መንገድ ነው። 3. የሰው ልጅ ችሎታ የሚሰፋውም (Augmentation of Human Capabilities) በእነዚህ ዘርፎች ነው:: አድካሚ እና ተደጋጋሚ ስራዎችና አሰራሮችን ለማሻሻል፣ ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት እና ለውጤታማነትም ቁልፍ ዘርፎች ናቸው:: ግራፊክስ ዲዛይነሮች፣ ሰዓሊያን፣ ጸሃፊያን፣ ሙዚቀኞች እና ሌሎችም የፈጠራ ባለሙያዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን ማበልጸግ የሚችሉት በተለይም Ai በመጠቀም ነው። --- በአጠቃላይ AI እና ቴክኖሎጂ የእውቀትና የክህሎት ቋት፣ የፈጠራና የሀብት ማዕከል፣ የግል እና የህብረተሰብ ችግሮች መፍቻ ቁልፍ፣ የወደፊት ጉዞ መንገድ ናቸው። ለዚህም ነው በአግባቡ መጠቀም እና ማስተዳደር ወሳኝ የሚሆነው። ይሁን እንጂ የሰው ሰራሽ ልህቀት (AI)፣ የቴክኖሎጂ እና ተያያዥ መረጃዎችን፣ እውቀዮችና ክህሎቶችን ከዓለም እኩል ለመቀራመት የቋንቋ እንቅፋቶች ጠንካራ ግንብ ፈጥረዋል። በጋራ ይሄን ግንብ የሚያፈርስ አንዳጅ እርምጃ ካልወሰድን በግልም እንደአገርም ተነጥለን መቅረታችን ነው። ከዚህ ግንዛቤ በመነሳት (ብዙዎቻችሁም ደጋግማችሁ በጠየቃችሁኝ መሰረት) የመፍትሄ ጠጠር ለመወርወር ዝግጅት እያጠናቀቅኩኝ ነው። በግሌ ለመጀመር እንጂ ከስራው ስፋት አንጻር ብቻዬን የምዘልቀው ስራም አይደለም። ስለሆነም ለጊዜው በአስፈላጊነቱ ላይ የሁላችንም የጋራ መግባባትና መነሳሳት መኖር አለበት። በአማርኛ ጀምረን በሌሎች አገር በቀል ቋንቋዎችም ለመቀጠል ቁርጠኝነቱ የሁላችንም ሊሆን ግድ ይላል። ለዚህም የመጀመሪያው በጉዳዩ የማመን፣ የመነሳሳትና የቁርጠኝነት መግለጫ ለዚሁ ስራ ሲባል የተከፈቱትን የቴሌግራም እና የፌስቡክ ገጽ መቀላቀል ነው። ቢያንስ እኔ ጋር ያላችሁት ከ27K በላይ ተከታዮች መቀላቀል ሲጠበቅባችሁ ቴሌግራም 4.8K ፌስቡክ ደግሞ 1.5K አካባቢ ብቻ ናችሁ የተቀላቀላችሁት። በዚህ ሁኔታ እንዴት ነው ያቀድነውን ማሳካት የምንችለው❓ እስቲ እንወያይበት❗🙏🙆 #Telegram👇 https://t.me/horntechcom #የፌስቡክ_ገጽ 👇 https://www.facebook.com/share/17AWTKkm8X/ #Horntech #Technology #Innovation #Ethiopia
Horntech.com - የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ማህበረሰብ ግንባር ቀደም ምርጫ - በቅርብ ቀን🚀
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
