cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ustaz yasin nuru offcial

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
1 752
مشترکین
-124 ساعت
+307 روز
+8230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ልጆቻችሁን ዱዓ አስተምሯቸው። ተግባሩንም አስለምዷቸው። እናንተ ለነርሱ ብቻ ሳይሆን እነርሱም ለናንተ ዱዓ እንዲያደርጉላችሁ ለምኗቸው። ዱዓ ሲያደርጉም [አሚን] በሏቸው። ከአብዛኞቻችን በተሻለ እነርሱ ለአላህ ቅርብ ናቸው። በአላህ ፍቃድ ዱዓቸውም ተሰሚነት አለው። ምክንያቱም ወንጀል የለባቸውም። ተወዳጃች [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] «በደካማዎቻችሁ እንጂ በሌላ እርዳታን እና ሲሳይን ታገኛላችሁን?» : ኢማም ሻፊዒይም ሆኑ ሌሎች ልሂቃን ለኢስቲስቃእ ህፃናት እንዲወጡ መክረዋል። ኢማም ኢብኑ ረጀብ አል‐ሐንበሊይ [ረሒመሁላህ] ሰይዲና ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ህፃናት ኢስቲግፋር እንዲያደርጉላቸው ይጠይቁ ነበር። «እናንተ ኃጢኣት አልሰራችሁም!» ይላሉ። ሰይዲና አቡሁረይራ  [ረዲየላሁ ዐንሁ] ህፃናት የቁርኣን ተማሪዎችን «አላህ ሆይ አቡሁረይራን ማረው!» በሉ ይሏቸው ነበር። ዱዓ ሲያደርጉ "አሚን" እያሉ ይቀበሉም ነበር። አል‐አብ‐ቢይ ስለ ሸይኻቸው ኢብኑ ዐረፋ ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ: ‐ «[ሸይኼ] የኻቲማቸው ነገር አብዝቶ ያሳስባቸው ነበር። መልካምነት ካዩበት ሰው ሁሉ አላህ በኢስላም እንዲያከትምላቸው እንዲለምን ይማፀኑ ነበር። አንድ ቀን ህፃናት የሚጠቀሙበት ነገር ሰጡኝና «አንተ ዘንድ ላለው ልጅ ስጥ።» አሉኝ። ህፃኑ ሰባት ስንዝር የማይሞላ ልጅ ነበር። እርሳቸው ግን «አላህ የህፃንን ዱዓ ይቀበላልና አላህ በኢስላም ውስጥ ፀንቼ ዕንዲገድለኝ ለምንልኝ በለው።» አሉ። ልጆቻችንን ዱዓ ማስለመድ የእረፍት ጊዜያቸው አካል እንድናደርገው ለማስታወስ ነው ይህንን ያነሳሁት! የቀደምቶቻችን ነገር ግን ዐጂብ ነው! ይገርማል! ይደንቃል! በዱዓ እንተዋወስ! ደህና እደሩ!
نمایش همه...
👍 20 6
ከትልልቅ ወደ አሏህ መቃረቢያ ስራዎች ውስጥ የሙእሚን ወንድምህ ልብ ውስጥ ደስታን ማስገኘት ነው :: የኛ ነብይም  صلى الله عليه وسلم   ከስራዎች ሁሉ በላጩ ምንድነው ተብለው የተጠየቁ ግዜ  እንዲህ ብለዋል :- " ሙእሚን ሙስሊም የሆነ ወንድምህ ልብ ውስጥ ደስታን ማስገባት ,,  ወይም እዳውን መክፈልህ ,, ወይም እሱን ምግብ ማብላትህ ነው " ------------------ ዒዱም ከመቃረቡ ጋር በተለያየ  ምክንያት ደስታቸው ደፍርሶ ልባቸው ተከፍቶ ዒዱን የሚያሳልፉ ወንድሞችን  በቻልነው አቅም ልባቸውን በማስደሰት ወደ አሏህ መቃረባችንን እናጠንክር እንሳተፍ ውዶቼ :: ሁላችንም የበጎነት ባለቤቶች ነን:: በእነዚህ 👇👇አካውንቶች ድጋፋቹን መላክ ትችላላቹ :: AL-MEIWA ISLAMIC ORGANIZATION 📍СВЕ = 1000580908587 📍OROMIA = 1000094625077 📍ZEMZEM = 0033646410301 📍አቢሲኒያ = 159300099 📍HIJRA = 1000019190001 ☎️ስልክ : 0911449925 0961707090 0964707090 https://t.me/elmeewa
نمایش همه...
አል መእዋ የበጎ አድራጎት ግሩፕ ( المأوى)

ففروا إلى الله "The best of mankind are those who benefit mankind." Prophet Muhammad -peace be upon Him-

👍 8 1
ታቢዒዩ ኢማም ሙጃሂድ [ረሒመሁላህ] እንዲህ ይላሉ: ‐ «ከዐብዱላህ ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] ጋር ነዋሪ አልባ ሆኖ በቀረ ኦና ቤት አለፍን። «ሙጃሂድ ሆይ! አንተ ኦና ቤት ሆይ! ባለቤቶችህ ምን አደረጉ? ወዴት ሄዱ?!» ብለህ ተጣራ አሉኝ። እንዳሉት ተጣራሁ!… ከዚያም ኢብኑ ዑመር [ረዲየላሁ ዐንሁ] እንዲህ አሉ: ‐ «ሄዱ! ሥራቸው ብቻ ቀረ፤ እነርሱ ግን ሄዱ!» : ዛሬ የምንኖርበት ቤት የኛ አይደለም። የምንኖረበት በጊዜያዊነት ነው። ዘልዐለም የምንኖርበት ሀገር ዛሬ በምናሳልፈው ሥራችን የሚገነባው የአኺራ ቤታችን ነው። ሁሌም ወዲያ የሰደድነውን ሥራችንን እንመርምር። ነፍሳችንን ወደ ሰማይ ከፍ እናድርጋት። መሬት ለመሬት አንታሽ። አኺራችንን አላህ ያሳምርልን!
نمایش همه...
18👍 8🥰 4
✨የትኛው ይበልጥ ይደንቃቹሃል✨ 1⃣ የረሱልን ደም ድፋ ተብሎ ደሙን ጭልጥ አርጎ የጠጣውን ሶሀባ ፍቅር? 🥺 2⃣ ወይስ ሀቢቡና ለቀናት ሲለዩት ያማረ ገፅታው እና ሰውነቱ ከስቶ የጠበቃቸው ሶሀባ ፍቅር? 😍 3⃣ ነው ወይስ ሀቢቢ ከሞቱ በኋላ በህልማቸው አይቷቸው ከመጣ በኋላ አዛን ማውጣት ያቃተው ናፍቆት? 🥰 4⃣ አሊያም ደሞ እንደሞቱ ሲያረዱት ህልፈታቸውን በጉልበት ላለማመን ሰይፍ እመዛለሁ ያሉት ጥልቅ ፍቅር? 😭 5⃣ በጦር አውድማ ከቤተሰቧ ህልፈት ባሻገር የነቢ መኖር ያስደሰታትስ ቢሆን ታሪኳ የወርቅ ብእር እንጂ ሌላ አያሻውም መለክ እንጂ ሰው አይፅፈውም የተባለላት?                  https://t.me/ustaz_yasin_nuru_offcial
نمایش همه...
🥰 18👍 2 2🙏 2
የሚወዳትን ለሕይወቱም ተስማሚ የሆነችን ሚስት መሰጠት ዱንያ ላይ አሏህ ከሚሰጠው ትላልቅ ውለታዎችና ነገ አኼራ ላይም ለባርያው ያደረገለትን ውለታ ሲነግረው ከሚጠቀሱ ችሮታዎች ውስጥ አንዱ ነው ። ኢብኑ ሒባን በዘገቡት ሐዲስ ሰይዳችን ﷺ እንዲህ ይላሉ : " ﻟﻴﻠﻘﻴﻦ ﺃﺣﺪﻛﻢ ﺭﺑﻪ ﻳﻮﻡ اﻟﻘﻴﺎﻣﺔ ﻓﻴﻘﻮﻝ ﻟﻪ: ﺃﻟﻢ ﺃﺳﺨﺮ ﻟﻚ اﻟﺨﻴﻞ ﻭاﻹﺑﻞ ﺃﻟﻢ ﺃﺫﺭﻙ ﺗﺮﺃﺱ ﻭﺗﺮﺑﻊ؟ ﺃﻟﻢ ﺃﺯﻭﺟﻚ ﻓﻼﻧﺔ ﺧﻄﺒﻬﺎ اﻟﺨﻄﺎﺏ, ﻓﻤﻨﻌﺘﻬﻢ ﻭﺯﻭﺟﺘﻚ" 📗 صحيح ابن حبان : 7367 «.. በእርግጥ የቂያማ ቀን አንዳቹ ከጌታው ጋር ይገናኛል .. ከዛም ጌታውም ይለዋል : ግመልና ፈረስን አላመቻቸውልህም ?! የበላይ ሆነህ እንድትመራ አልተውኩህም ? እንትናን አልዳርኩህም ?! ጠያቂ ሁሉ ጠይቋት..እነሱን  ከልክዬ አንተን ዳርኩህ..» ይሄን ውለታን ጌታው የሰጠው አላህን ያመስግን ውለታውንም ይጠብቅ ። ለጥያቄውም መልስ ያዘጋጅ ። ያልተሰጠው ደግሞ እንዲሰጠው አላህን ከችሮታው ይጠይቅ ☺️
نمایش همه...
7👍 2🔥 2
Photo unavailableShow in Telegram
ዘንጊዎች በዘነጉ፣አሰታዋሾች ባሰታወሱ ቁጥር፣ በረገፈው ቅጠል፣ በፈሰሰው አሸዋ፣ ሰማይን ባደመቁት ክዋክብት፣ ውቂያኖስ በያዘው ጠብታ መጠን የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ሙሐመድ(ﷺ)ላይ ይሁን! አለይሂ ሰላቱ ወሰላም♥️
نمایش همه...
👍 10🥰 5 4
00:24
Video unavailableShow in Telegram
2.29 MB
👍 4 2🥰 1
02:02
Video unavailableShow in Telegram
2.79 MB
🥰 13 2
#የነብዩ ሰዐወ መቃብር ቁፈራ የተጋለጠበት!! የታሪክ መጻሕፍት በ557 ዓ.ሂ የተከሰተን አንድ አስገራሚ ጉዳይ ሳይጠቅሱ አያልፉም፡፡ ያ ዘመን የዐብባሳውያን ሥርወ-መንግሥት በመንኮታኮት ላይ የነበረበት ዘመን ነበር፡፡ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በአጐራባች አገራት ይኖሩ የነበሩ ክርስቲያን መንግሥታት አንድ ከባድ ሴራ ጠነሰሱ። ሴራቸው የሙስሊሞችን መዳከም ተገን አድርገው የነቢዩን አስከሬን ከነበረበት በመስረቅ ወደ ራሳቸው ግዛት መውሰድ ነበር፡፡ ይህን በማድረግም በሙስሊሞች ላይ ከፍተኛ ሞራላዊ ጉዳት ለማድረስ አሰቡ:: ስለዚህ ይህን ረቂቅ ተንኮል ለማስፈፀም ሁለት የተመረጡ  ሰላዮችን የሞሮኮ ኢስላማዊ አለባበስ በማልበስ ወደ መዲና ከተማ ሰደዱ ሰዎቹም ለነዋሪዎቿ ለፀሎት ወደ ቅድስቲቷ ከተማ የመጡ ሐጃጆች መሆናቸውን እንዲናገሩ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተሰጣቸው፡፡ ሁለቱ ሰዎች ተልዕኮኣቸውን ለመወጣት እንዲችሉ መስጂደል ነበዊ (የነቢዩ መስጂድ) አጠገብ ባለ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ፡፡ በጐረቤቶቻቸውም ዘንድ ለመታመን ሲሉ መስጂድ ማዘውተርና የዒባዳ ተግባራትን በጥልቀት ማከናወን የዕለት ተዕለት ተግባራቸው ሆነ፡፡ ዋናው ጉዳያቸው ግን የተላኩበትን ዓላማ ማስፈፀም እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፡፡ ይህን ተልዕኮ ለማከናወን የመጀመሪያ ሥራቸውንም ከነበሩበት ቤት አንስተው ወደ ነቢዩ መቃብር ለመድረስ ውስጥ ለውስጥ በመቆፈር መሿለኪያ ለማበጀት ቁፋሮ ጀመሩ፡፡ እንዳይነቃባቸውም በየቀኑ ትንሽ ትንሽ ብቻ እየቆፈሩ የሚያወጡትን አፈር በትናንሽ መያዣዎች አድርገው ጀለቢያቸው ሥር በማንጠልጠል አል-በቂፅ ወደሚባለው የመዲና  የቀብር ስፍራ እየወሰዱ ይደፉ ነበር። ሌሎቹ ነዋሪዎች ሰዎቹ በየዕለቱ ወደ ቀብር ሥፍራ የሚሄዱት የሞቱትን በመዘየር ሞትና አኼራን ለማሰብ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል፡፡ ሰዎቹ አንዳንዴ ሲደክማቸው መሿለኪያ ለማበጀት የሚቆፍሩትን አፈር ከሚኖሩበት ቤት አጠገብ ወዳለ ጉድጓድም ይደፉ ነበር። እንዲህ እያደረጉ በመጨረሻ መሿለኪያውን ከነቢዩ ሰዐወ ቀብር ጋር ሊያገናኙ ደረሱ፡፡ እዚህ ደረጃ ሲደርሱ ተልዕኮኣቸው ለመሳካቱ እርግጠኛ ስለነበሩ የትኩረት አቅጣጫቸው የነቢዩን አስከሬን ካወጡ በኋላ በምን መንገድ ወደ መጡበት ግዛት እንደሚያጓጉዙ ማቀድ ነበር፡ የተለያዩ ዘዴዎችን አውጥተው አወረዱ፡፡ በዚያው ወቅት አላህ የራሱን ሴራ እያሴረባቸው እንደሆነ ግን አላወቁም፡፡ የዘመኑ የሙስሊሞች መሪ የነበሩትና ከመዲና ብዙ ርቀው የሚኖሩት ኑረዲን ሙሐመድ ኢብኑ ዘንጂ በዚያው ሰሞን አንድ ለየት ያለ ሕልም እዩ፡፡ በሕልማቸው ውስጥ ነቢዩ ሰዐወ  ነበር የታዩዋቸው፡ ነቢዩ ወደ ሁለት ቀያይ ፀጉረ ልውጥ ሰዎች እያመለከቱ ከእነርሱ እንዲያድኗቸው ኑረዲንን ይማፀናሉ ይህን ከባድ ሕልም ሲመለከቱ ኑረዲን በድንጋጤ እየተንቀጠቀጡ ከእንቅልፋቸው ነቁ። ራሳቸውንም ለማረጋጋት ሶላት ከሰገዱ በኋላ ተመልሰው ወደ መኝታቸው ቢሄዳም አሁንም ያው ሕልም ተመልሶ መጣባቸው:: ሕልሙ ለሦስተኛ ጊዜ ሊመጣባቸው ከእንቅልፋቸው በመነሣት ከሚንስትሮቻቸው መካከል ሷሊሕና ብልህ የነበረውን ጀማሉዲን አል ሙሲሊ የተባለውን አስጠሩ፡፡ ያዩትን ሕልም ለጀማሉዲን ሲነግሩት ሕልማቸው በመዲና ውስጥ የሆነ እንግዳ ነገር እየተከናወነ መሆኑን እንደሚጠቁም አስረዳቸው፡፡ በአስቸኳይም ወደ ነቢዩ ከተማ በመሄድ ስለ ሕልሙ ለማንም ሳይናገሩ ሁኔታዎችን እንዲከታተሉ አሳሰባቸው፡፡ ኑረዲን ከለሊቱ የቀረውን ክፍል ለጉዞው ዝግጅት ሲያደርጉ አደሩ፡፡ ጀማሉዲንን ጨምሮ ሃያ ጭነት ከሃያ ሰዎች ጋር እንዲዘጋጅ አዘዙ፡ ከሻም(ሶሪያ) ተነስተው መዲና ለመድረስ የፈጀባቸው ዐሥራ ስድስት ቀናት ብቻ ነበር። መዲና ሲደርሱ በፍጥነት የሄዱት በመስጂደል ነበዊ ውስጥ ወደሚገኘው አልረውዳ ልዩ የሶላት ስፍራ ነበር፡፡ እዚያ በመሄድም ዱዓ አደረጉ:: ይሁን እንጂ ሕልሙን በተመለከተ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊያውቁ አልቻሉም፡፡ አማካሪያቸው ጃማሉዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸው ሁለት ሰዎች ምን ዓይነት እንደሆኑ እንዲነግሩት ሲጠይቃቸው ኑረዲን የሰዎቹን መልክና አለባበስ እንደሚያስታውሱና ቢያገኙዋቸው መለየት እንደሚችሉ ነገሩት፡፡ ጀማሉዲን ሰዎቹን ለመያዝና ሴራቸውን ለማክሸፍ ቆርጠው በመነሳታቸው ፈጣን እርምጃዎችን መውሰድ ጀመሩ፡፡ የመዲና ነዋሪዎች በመስጂዱ ውስጥ ሲሰበሰቡም እንዲህ የሚል ማስታወቂያ አስነገሩ፡፡ 'መሪያችን በሶደቃ ለመስጠት ነይተው ያመጡት ብዙ ሃብት አለ፡፡ ሶደቃውን ለማከፋፈል እንዲመቸን በችግር ውስጥ ያላችሁ ሰዎች ሁሉ እየመጣችሁ ስሞቻችሁን እንድታስመዘግቡ እንጠይቃለን የሚል፡፡ ይህን ማሳሰቢያ እንዳስነገሩ ሰዎች ሶደቃውን ፍለጋ ተንጋግተው መምጣት ሲጀምሩ ኑረዲን በሕልማቸው ውስጥ ያዩዋቸውን ሰዎች ለመለየት ዳር ቆመው እያንዳንዱን ሰው ይቃኙ ነበር። ብዙ ሰዎች መጥተው የድርሻቸውን እያነሱ ቢሄዱም ኑረዲን ተፈላጊዎቹን ሁለት ሰዎች ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻም ከሶደቃው ድርሻውን ያልወሰደ ሰው እንዳለ ሲጠይቁ የሆነ ሰው ·ከሞሮኮ የመጡ ሁለት ሰዎች አሉ፡፡ ሰዎቹ በጣም ሷሊሕ ሰዎች ስለሆኑ ሶደቃውን ለመቀበል አልፈለጉም አላቸው፡፡ ኑረዲን ይህን እንደሰሙ ሁለቱን ሰዎች በአስቸኳይ እንዲያመጧቸው አዘዙ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች እፊታቸው እንደቀረቡ ሰዎቹ ነቢዩ ሰዐወ በሕልማቸው ያመለከቷቸው ሰዎች መሆናቸውን በቀላሉ አወቁ። ሰዎቹንም “ለመሆኑ ከየት ነው የመጣችሁት? በማለት ጠየቁ፡፡ እነርሱም የመጣነው ከመግሪብ ነው፣ አመጣጣችን ለሐጅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህን ዓመት እዚሁ ለማሳለፍ ወስነናል' አሏቸው:: ኑረዲን ሰዎቹ የሆነ ያቀዱት ሴራ መኖሩን ቢጠረጥሩም ምን እንደሆነ በእርግጠኝነት ለመለየት ስላልቻሉ ድብቅ ሴራቸውን ይፋ እንዲያወጡ በማሰብ የተለያዩ ጥያቄዎችን አከታትለው ቢጠይቁም ምንም ፍንጭ ሳያገኙ ቀሩ፡፡ በዚህም የተነሣ ምንም እርምጃ ሊወስዱባቸው አልተቻላቸውም:: ኑረዲን ቀጥለው ያዘዙት ቤታቸው ይፈተሽ የሚል ነበር፡፡ ቤታቸው ሲፈተሽም በቤቱ ውስጥ ካስቀመጡት በርካታ ገንዘብ ውጭ ሊያስጠረጥራቸውና ሊያስወነጅላቸው የሚችል ምንም ነገር ሳይገኝ ቀረ፡፡ ለፍተሻ ወደ ቤታቸው የገባ ሰው አንድ በአንድ መውጣት ሲጀምር ኑረዲንም ምንም ምልክት በማጣታቸው ቤቱን ለቀው ሊወጡ ሆነ: በዚያች ቅፅበት ነበር አላህ የሙስሊሞቹ መሪ አንዳች ነገር አትኩረው እንዲመለከቱ ያደረገው ኑረዲን ወለሉን ሲቃኙ በወለሉ ላይ ከተነጠፉት ጣውላዎች ው አጥብቆ እንዳልያዘ አስተዋሉ፡፡ ይህን እንዳዩ ጐንበስ በማለት ጣውላውን ሲያነሱ የመዲናን ነዋሪዎች ጉድ ያሰኘ ክስተት ተስተዋለ። በወለሉ መሿለኪያ መቆፈሩን ነዋሪዎቹ ግን ይበልጥ የተደናገጡት መሿለኪያው ወዴት እንደሚያመራ ሲረዱ ነበር፨ መሿለኪያውን የቆፈሩት በከተማይቷ ውስጥ በሷሊሕነታቸው ይታወቁ የነበሩት ሁለቱ የሩቅ አገር እንግዶች መሆናቸው ሌላው ግርምታ የፈጠረ ጉዳይ ሆነ፡ እስከዚያን ጊዜ ድረስ ሁለቱ ሞሮኮኣውያን የሚታወቁት በጥልቅ ዒባዳቸውና በላቀ ኢስላማዊ ሥነ-ምግባራቸው ነበር፡፡ እጅግ የተናደዱት መሪ ኑረዲን ሁለቱን ሰዎች መግረፍ ሲጀምሩ ሰዎቹ በርግጥ ከመግሪብ (ሞሮኮ) አንዳልመጡና በመሪያቸው ከፍተኛ ገንዘብ ተከፍሏቸው የተላኩ ክርስቲያኖች መሆናቸውን የመጡትም የነቢዩን አጽም ቆፍረው በማውጣት በድብቅ ወደ አገራቸው ለመውሰድ መሆኑን አመኑ፡፡ ኑረዲን ሁለቱ ሰዎች በሞት እንዲቀጡ አዝዘው የተቆፈረው መተላለፈያም በአስተማማኝ መልኩ በአለት እንዲደፈን አደረጉ፡፡ ሴራውንም እንዳከሸፉ ወደ ሻም (ሶሪያ) ተመለሱ፡፡
نمایش همه...
👍 23 3
ሑጀቱል—ኢስላም ኢማም አቡሓሚድ ገዛሊ እንዲህ ይላሉ: — "ምክንያቱ ያልታወቀ ጭንቀት ኃጢኣትን ከመፈፀም እና ለመፈፀም ከማሰብ የሚመነጭ ነው። ቀልብ አላህ ፊት መቆምና መተሳሰብ እንዳለ ሲያስብና አስፈሪውን የቂያማ ድባብ ሲያስተውል ከሚሰማው ሃሳብ ይህ ጭንቀት ይወለዳል።" : ኢማም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ: — "ሱፍያን ኢብኑ ዑየይና ምክንያቱ ስለማይታወቅ ጭንቀት ተጠየቁና እንዲህ አሉ: — "መንስዔው በልብህ አስበኸው ያልፈፀምከው ኃጢኣት ነው። በልብህ ባሰብከው ኃጢኣት ምክንያት በጭንቀት ትቀጣለህ። ኃጢኣት የማይቀር ቅጣት አለው። በምስጢር ለተሰራው በምስጢር፤ በይፋ ለተሰራው በይፋ።" ❤️❤️❤️اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد صلى الله عليه وآله وصحبه أجمعين ❤️❤️❤️ ውስጣችንም ላያችንም ሰላም የሚያገኝበት፣  በሩቋ ሀገር ያሉትም ከአላህ የሆነ ራህመት የሚያገኙበት፣ ተረጋግተው የድል ሰላት የሚሰግዱበት፣  ለተጨነቁት ወንድሞቻችን ድልን ለታመመ መዳንን፣ ለሞቱት ሸሂድነትን  የሚወፈቁበት፣ በሰለዋት፣ የምናሳልፈው መልካም ቀን ይሁን።
نمایش همه...
🥰 9 6👍 5
یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.