fa
Feedback
Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ

Swift Proxy Service /ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ

رفتن به کانال در Telegram

ማንኛውንም የትምህርት ነክ ጉዳዮችን በውክልና እናስጨርሳለን። 👉 ቴምፖራሪ ዲግሪ 👉ኦረጅናል ዲግሪ 👉ኦፊሻል ማስላክ 👉ኦተንቲኬሽን 👉Medium of instruction አና ሌሎችንም ጉዳዮችን ባሉበት ሆነው ማስፈፀም ይችላሉ። 👇 ቅርንጫፎቻችን 1. ባህር ዳር 2.ጎንደር 3.ደብረ ታቦር 4.ደብረ ማርቆስ 5.አዲስ አበባ ለበለጠ መረጃ👉905906455/924682247 ይደውሉ።

نمایش بیشتر
2 395
مشترکین
-724 ساعت
-547 روز
-12130 روز
آرشیو پست ها
🙏ሰላም ውድ ቤተሰቦች 🔊በድጋሚ ለማሳሰብ ያክል ጉዳይ በ እኛ (በ ስዊፍት) በኩል ስታስጨርሱ ውክልና ለማፃፍ መድከም ሳይጠበቅባቹ በእኛ በኩል በተመደቡ ልጆች የሚያልቅ ጉዳይ ሲሆን የሚላክላችሁን
🙏ሰላም ውድ ቤተሰቦች 🔊በድጋሚ ለማሳሰብ ያክል ጉዳይ በ እኛ (በ ስዊፍት) በኩል ስታስጨርሱ ውክልና ለማፃፍ መድከም ሳይጠበቅባቹ በእኛ በኩል በተመደቡ ልጆች የሚያልቅ ጉዳይ ሲሆን የሚላክላችሁን PDF print በማድረግ ለማህተም ሰነዶች ቢሮ ጋር በመሄድ በፈጣን መንገድ ጉዳያችሁን የምታስጨርሱ ይሆናል። 👆 ከላይ የሚታየው ከማህተም በፊት የተፃፈ ውክልና ማሳያ ነው።

🙏ሰላም ውድ ቤተሰቦች 👉 ስለ አዲሱ የኦሪጅናል ድግሪ ህትመት በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ:- 🔊በመጀመሪያ ዙር ወደ ት/ት ሚንስቴር የተላከው ዶክመንት ሕትመቱ የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡ ወደ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ይላካል ተብሏል። 🔊በግላችሁ ያመለከታችሁ እና ከህትመቱ ውስጥ ያላችሁበት አመልካቾች የግቢውን በቴሌግራም/ፌስቡክ ቼጅ ተጠባባቁ። 🔊በእኛ(በስዊፍት) በኩል ያመለከታችሁ:- ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተልን ስለሆነ አዲስ መረጃዎችን በእራሳችሁ አካውንት inbox የምናደርግ ይሆናል። 🔊አሁን ላይ ግቢው እየተቀበለው ያለው የህትመት ትዕዛዝ በመጪው ሰኞ ግንቦት 16 ለህትመት የሚላክ መሆኑን አሳውቀውናል። 🔊የህትመት ክፍያ የብር መጠን እስከ አሁን የተገለፀ ነገር የለም ።ክፍያው ግን ከህትመት መልስ ባህር ዳር ላይ እንደሚሆን ነው ያለው መረጃ። ⚡️⚡️ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ⚡️⚡️⚡️

. . . የውጭ ሀገር የት/ት ዕድልን በተለያዩ የውጭ ሀገራት በትምህርት ላይ ካሉ ተማሪዎች 👉''How to Apply''  ስለሚለው መረጃዎችን የምናጋራ ይሆናል በተለይ:- 👉Over all informations 👉CV 👉Motivation Letter 👉Cover letter 👉Necessary Documents 👉 Interview ላይ የምናተኩር ይሆናል። swift ስለእነኚህ እና መሰል ጉዳዮችን  ዕውቅና  ይሰጣል እየሰጠም ይገኛል:: 👉በተለያየ ምክንያት ጉዳዩን ማስጨረስ ያልቻሉትን ደግሞ  ጉዳዮችን በውክልና እያስጨረስን እንገኛለን። ማንኛውንም መረጃዎችንም በማንኛውንም ሰዓት መጠየቅ 📞/@proxy2106/inbox ይቻላል:: 🔊Swift Proxy Service   Bahir Dar Branch

🙏ሰላም ውድ ቤተሰቦች ይህ ቻናል በስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ/Swift proxy service / በኩል👉 ብቻ ስለሚሰጡ አገልግሎት መረጃ የሚያገኙበት እና የሚፈፀሙ ጉዳዮችን ለማሳያ ያኮል የምናሰራጭበት ቻናል ነው። ከዓላማዎቹ /ከሚያስጨርሳቸው ጉዳዮች  ውስጥ አንዱ ተማሪዎች በት/ት ቆይታቸው ውስጥ እንዲሁም ከተመረቁ በኋላ ማወቅ/ ማስጨረስ ስለሚጠበቅባቸው የት/ት ዶክመንቶች ዕውቅና መስጠት እና ጉዳዩንም በውክልና ማስጨረስ ይገኝበታል። ለምሳሌ:- ስንቶቻችን ከታች ስለተዘረዘሩት የት/ት ማስረጃዎች እና ደብዳቤዎች ግንዛቤው አለን? በምን መልኩስ ማስጨረስ እንደምንችል? 👉Temporary Degree ? 👉Original Degree ? 👉Student Copy ? 👉Official Transcript  ? 👉Grade Report 👉Medium of Instruction  ? 👉Authentication ? 👉Clearance ? 👉Recommendation Letter ? 👉Document Copy ? 👉ID Replacement  ? ... እና የመሳሰሉትን። 🔊Swift Proxy Service Bahir Dar Branch

🙏ሰላም ውድ ቤተሰቦች ይህ ቻናል በስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ/Swift proxy service / በኩል👉 ብቻ ስለሚሰጡ አገልግሎት መረጃ የሚያገኙበት እና የሚፈፀሙ ጉዳዮችን ለማሳያ ያኮል የምናሰራጭበት ቻናል ነው። ከዓላማዎቹ /ከሚያስጨርሳቸው ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ተማሪዎች በት/ት ቆይታቸው ውስጥ እንዲሁም ከተመረቁ በኋላ ማወቅ/ ማስጨረስ ስለሚጠበቅባቸው የት/ት ዶክመንቶች ዕውቅና መስጠት እና ጉዳዩንም በውክልና ማስጨረስ ይገኝበታል። ለምሳሌ:- ስንቶቻችን ከታች ስለተዘረዘሩት የት/ት ማስረጃዎች እና ደብዳቤዎች ግንዛቤው አለን? በምን መልኩስ ማስጨረስ እንደምንችል? 👉Temporary Degree ? 👉Original Degree ? 👉Student Copy ? 👉Official Transcript ? 👉Grade Report 👉Medium of Instruction ? 👉Authentication ? 👉Clearance ? 👉Recommendation Letter ? 👉Document Copy ? 👉ID Replacement ? ... እና የመሳሰሉትን። 🔊Swift Proxy Service Bahir Dar Branch

🙏ሰላም ውድ ቤተሰቦች ይህ ቻናል በስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ/Swift proxy service በኩል👉 ብቻ ስለሚሰጡ አገልግሎት መረጃ የሚያገኙበት እና የሚፈፀሙ ጉዳዮችን ለማሳያ ያኮል የምናሰራጭበት ቻናል ነው። ከዓላማዎቹ ውስጥ አንዱ ተማሪዎች በት/ት ቆይታቸው ውስጥ እንዲሁም ከተመረቁ በኋላ ማወቅ/ ማስጨረስ ስለሚጠበቅባቸው የት/ት ዶክመንቶች ዕውቅና መስጠት እና ጉዳዩንም በውክልና ማስጨረስ ይገኝበታል። ለምሳሌ:- ስንቶቻችን ከታች ስለተዘረዘሩት የት/ት ማስረጃዎች እና ደብዳቤዎች ግንዛቤው አለን? በምን መልኩስ ማስጨረስ እንደምንችል? 👉Temporary Degree ? 👉Original Degree ? 👉Student Copy ? 👉Official Transcript ? 👉Medium of Instruction ? 👉Authentication ? 👉Clearance ? 👉Recommendation Letter ? 👉Document Copy ? 👉ID Replacement ? ... እና የመሳሰሉትን። swift ስለእነኚህ እና መሰል ጉዳዮችን በግልፅ ያሳውቃል እሱ ብቻ አደለም ....ተማሪዎች በተለያየ ምክንያት ጉዳዩን ማስጨረስ ያልቻሉትን በውክልና እያስጨረስንላቸው እንገኛለን። ማንኛውንም መረጃዎችንም በማንኛውንም ሰዓት መጠየቅ 📞/@proxy2106/inbox ይቻላል

Repost from N/a
BiT Registrar Office
+5
BiT Registrar Office

Repost from N/a
🙏 ሰላም ውድ ቤተሰቦች የኦሪጅናል ዲግሪ ህትመትን በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ ሁሉ 👇 🎉🎉ሰበር መረጃ🎉🎉🎉 👉አዲሱን ውሳኔ መሰረት ያደረገ የኦሪጂናል ዲግሪ የህትመት ሂደት ተጀምሯል (ማመልከቻ መቀበል ከተጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል) ። 👉ከዚህ በፊት በመጨረሻ ዙር ላይ አመልክታችሁ የነበራችሁ እና በአዲሱ የት/ት ሚኒስቴር ውሳኔ ምክንያት የተመለሰባችሁ አመልካቾች ----- > ዶክመንታችሁ ለህትመት መላኩን አረጋግጠናል። 👉አሁን ላይ በእኛ በኩልም(Swift Proxy Service) የደንበኞቻችንን የኦሪጅናል ዲግሪ ትዕዛዝ እያመለከትን እንገኛለን...ይህም ቅፅ/ማመልከቻ በቀጥታ ወደ ት/ት ሚንስቴር የሚላክ ሲሆን  የኦሪጅናል ዲግሪ ህትመቱ ዳግም ወደ ግቢ እንደሚመለስ ነው የደረሰን መረጃ። 👉...የህትመት የጊዜ ቆይታውን በተመለከተ ለጊዜው የታወቀ መረጃ ባይኖርም አዲስ መረጃዎች ሲኖሩ የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ለተጨማሪ መረጃ 968849371/924682247 🔊ስዊፍት የግል ጉዳይ አስፈፃሚ ከባህር ዳር ቅርንጫፍ

​📢 አስቸኳይ ማሳሰቢያ ለሁሉም ተማሪዎች! 📢 ​በግቢው ቆይታችሁ ትምህርታችሁን በሰላም እንድታከናውኑ ቀዳሚው ተግባራችን የሁላችሁም ደህንነት እና ሰላም መጠበቅ ነው። ​ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከግቢው የጸጥታና ደህንነት ክፍል እንዲሁም ከአመራሮች የተላለፈውን ጥብቅ መመሪያ ተከትሎ የሚከተለውን ማሳሰቢያ እንድታውቁት እንወዳለን፦ 1⃣​የሰዓት ገደብን ማክበር፦ ከዚህ ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም ተማሪ ከተቀመጠው የመግቢያ ሰዓት ውጭ አምሽቶ ቢመጣ ወደ ግቢው በምንም ዓይነት ሁኔታ መግባት የማይችል መሆኑን እናሳስባለን። ❗️​ለጥንቃቄ ሲባል፦ ይህ መመሪያ የወጣው የተማሪዎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ያልተገመቱ ችግሮችን አስቀድሞ ለመከላከል ሲባል ነው። ​ኃላፊነት መውሰድ፦ ከሰዓት በኋላ መቆየት ለተለያዩ የጸጥታ ስጋቶች የሚያጋልጥ በመሆኑ፣ ተማሪዎች የራሳችሁን ደህንነት ለመጠበቅ ስትሉ በሰዓቱ ወደ ግቢ እንድትገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። ​⚠️ ማሳሰቢያ፦ መመሪያው ላይ ምንም ዓይነት ማለስለሻ (Compromise) ስለሌለ፣ በውጭ አምሽታችሁ እንግልት እንዳይገጥማችሁ ሁላችሁም ለዚህ መልእክት ከፍተኛ ትኩረት እንድትሰጡ እንጠይቃለን። ​የተማሪዎች ህብረት ጽ/ቤት

አስቸኳይ የማሳሰቢያ መልዕክት ​ለሁሉም የክፍል ተወካዮች (Class Representatives): ​ዛሬ ከሰዓት አስቸኳይ ስብሰባ ስላለ ሁሉም የክፍል ተወካዮች በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ እንድትገኙ እናሳስባለን። ስብሰባው እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ መገኘታችሁ የግዴታ ነው። ​ሰዓት: 8:30 ቦታ: ቀሃስ (KeHaS)

📢 የአንድነት እና የደግነት ጥሪ ለBIT ተማሪዎች በሙሉ! “ዛሬ የእኛ መቆም ለጓደኛችን ነገ ነው!” ሁላችንም እንደምናውቀው የIT 3ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ጓደኛችን ባጋጠመው የጤና እክል ምክንያት በህክምና ላይ ይገኛል። ይህ ወቅት ለእሱም ሆነ ለቤተሰቦቹ ፈታኝ ቢሆንም፣ እኛ ጓደኞቹ ግን ከጎኑ በመሆን ሸክሙን ልናቀልለት እንችላለን። ለጓደኛችን የሁለት ቀን (የእሁድ እና የማክሰኞ) የምግብ (ዘርፎር) ክፍያውን እንዲመለስለት (Refund እንዲደረግለት) በማሰብ፣ ከዛሬ መክሰስ ሰዓት ጀምሮ ፊርማ እያሰባሰብን እንገኛለን። ✨ ለምን መፈረም አለብኝ? ለአጋርነት፦ በህመም ላይ ላለው ወንድማችን "አለንልህ!" የምንልበት ቀላሉ መንገድ ነው። ለተግባራዊ እርዳታ፦ የምናሰባስበው ፊርማ ጓደኛችን ያላገኘውን አገልግሎት ገንዘቡ ተመላሽ ሆኖ ለህክምናው እንዲረዳው ያደርጋል። ለህሊና እርካታ፦ ዛሬ የምናደርገው ትንሿ ፊርማ ለጓደኛችን ትልቅ ተስፋ ናት። "አንድ ሰው ሲታመም ሁላችንም እንታመማለን፤ የአንዱ ችግር የሁላችንም ነው!" እባካችሁ! ከዛሬ ከሰዓት (ከምሳ ሰዓት በኋላ) ጀምሮ በምናደርገው የፊርማ ማሰባሰብ ሂደት ላይ ሁላችሁም በመሳተፍ የድርሻችሁን እንድትወጡ በጓደኝነት ስም እንጠይቃለን። የመፈረሚያ ቦታ፦ በካፌው በር ላይ የጓደኛችን ጤንነት በቅርቡ ተመልሶ ወደ መሃላችን እንዲቀላቀል የሁላችንም ጸሎት እና ድጋፍ አይለየው! ከአክብሮት ጋር፦ የ IT 3ኛ ዓመት ተማሪዎች ተወካዮች!

ለሁሉም 2 ተኛ አመት ተማሪዎች የቀረበ ጥሪ! የተማሪዎች ህብረት ፓርላማ (የክፍል ተወካዮች) ምርጫ የተማሪዎች ህብረት  አዳዲስ ተማሪዎች ወደ ግቢያችን ሲቀላቀሉ ፣ ሊወክሏቸው የሚችሉ ተማሪዎችን ፣ ከ ቀን 24/08/2018 ዓም ጀመሮ  የመምረጥ ሂደት  ይጀምራል። 📅 የምርጫው ቀን የሚጀመርበት ቀን፦ ሚያዝያ  24 ቀን 2018 ዓ.ም. የምርጫው ቦታ፦ በየመማሪያ ክፍላችሁ የተመራጮች ብዛት : - አንድ ወንድና አንድ ሴት በየሴክሽኑ ። ዕጩዎች ሊያሟሏቸው የሚገቡ ዋና ዋና መስፈርቶች (አንቀጽ 12) ተወካዮችን ስትመርጡ የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላታቸውን እርግጠኛ ሁኑ፦ ✍️ በዲስፕሊን ያልተቀጣ እና ታማኝ። ✍️ የትምህርት ውጤቱ (CGPA) 2.75 እና ከዚያ በላይ የሆነ። ✍️ በሃይማኖት፣ በፖለቲካ እና በብሔር አድልዎ የማያደርግ። ✍️ በስብሰባዎች ላይ ለመገኘት ፈቃደኛ እና ኃላፊነቱን የሚወጣ። ✍️ የተማሪዎችን መብት የሚያስከብርና ግዴታቸውን እንዲወጡ የሚደግፍ። ድምፅ መስጠት ለምን አስፈለገ? የክፍል ተወካዮች የእናንተ ድምጽ በዩኒቨርሲቲው መድረክ እንዲሰማ የሚያደርጉ፣ መብታችሁን የሚያስከብሩ እና በዩኒቨርሲቲው አስተዳደርና በተማሪው መካከል ድልድይ የሚሆኑ መሪዎች ናቸው።
"ብቁ ተወካይ መምረጥ መብታችሁም ግዴታችሁም ነው!"
የተማሪዎች ህብረት

Students Union Structure and Election Guidline_2 (1).pdf1.27 MB

ትናንት በነበረው የGC Cup ጨዋታ ወቅት ሜዳ ላይ የእጅ አምባር (Bracelet) ጥዬ ነበር። አምባሩ የእናቴ ስጦታ ስለሆነ ለኔ ትልቅ ዋጋ አለው። ​ያገኛችሁ ወይም ያለበትን የምታውቁ ሰዎች እባካችሁ ብትመልሱልኝ፤ ለውለታችሁ ተገቢውን ወረታ (ክፍያ) እከፍላለሁ። ሰ/ቁ: 0972646139 ​አመሰግናለሁ!

⏳ ሰዓቱ አሁን ነው! በሩ ተከፍቷል! ⏳ የምሽቱ ድምቀት፣ የዕውቀትና የመዝናኛ ማዕከል የሆነው "ልዩ የቡና ምሽትና የንቅናቄ መድረክ" እነሆ አሁን ሊጀመር ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ቀሩት! ☕️✨ ያላችሁበትን እርግፍ አድርጋችሁ ተውና ወደ ቀኃስ አምሩ! በባህላዊ ቡና መዓዛ እየታጀብን፣ በኪነ-ጥበብ እየተመሰጥን፣ ስለ ራሳችን የምንወያይበትና ትውልድን ከሱስ ለመታደግ ቃል የምንገባበት ታላቅ ምሽት ከፊታችን ይጠብቀናል። አሁኑኑ ይነሱ! ያመለጣችሁ ነገር እንዳይኖር... ሽልማቶቹን ሌሎች እንዳይወስዱባችሁ... የቤተሰባችን አባል ለመሆን ያላችሁ ዕድል እንዳያልፍ... 🏃‍♂️ ፈጠን ፈጠን እያልን ወደ ቀኃስ! "እኛ ተዘጋጅተናል፤ እናንተስ የላችሁም ወይ?" 🔥 📍 ቦታ፦ ቀኃስ አካባቢ 🕒 ሰዓት፦ አሁኑኑ! (2:00) #BiT_AntiDrug #የቡና_ምሽት #አሁኑኑ_ይቀላቀሉን

አስቸኳይ ማሳሰቢያ ለ BiT ተማሪዎች በሙሉ! 📢 ​ሰላም የዚህ ቻናል ተከታዮች፤ ​የተማሪዎች ህብረት መረጃዎችን ይበልጥ ተደራሽ እና ቀልጣፋ ለማድረግ BiT SU Official Informationየተሰኘ አዲስ እና ይፋዊ ቻናል መክፈታችንን እናበስራለን። ​ከዚህ በኋላ ማንኛውም ትኩስ መረጃዎች፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች፣ የካምፓስ ጥሪዎች እና ልዩ ልዩ ማስታወቂያዎች የሚለቀቁት በአዲሱ ቻናላችን ብቻ ይሆናል። የቆየው ቻናል በቅርቡ አገልግሎት ስለሚያቆም ሁላችሁም አሁኑኑ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ወደ አዲሱ ቻናል ተቀላቀሉ፦ ​🔗 የመቀላቀያ ሊንክ፦ https://t.me/BiTUnion12 ​ይህ መረጃ ለሁሉም ተማሪዎች እንዲደርስ ሼር በማድረግ ተባበሩ። ​BiT SU Official Information ትክክለኛ መረጃ ለተማሪዎች!