cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
193
مشترکین
-124 ساعت
-37 روز
-530 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የአንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር ቤተሰቦችና ወዳጆቻቸው ለሁላችሁም ሰላምና ጤና እንድሆንላችሁ እየተመኛን ከፊታችን ማክሰኞ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም በማኅበራችን የተዘጋጀ ድንቅ የሥልጠና ጊዜ ይኖረናል ። በመሆኑም ሁላችንንም የአንድነት ቤተሰቦች በሙሉ ልክ 2:00 ማስታወሻና ደብተር ይዛችሁ እንድትገኙ በታላቅ ፍቅር እናሳስባለን ። በዕለቱ የሥልጠና የምክክር የውይይት ጊዜ ይኖረናል ። ስለዚህ እባካችሁ ማናችሁም አትቅሩ ከበረከቱም አትጓደሉ እእእእንንንወወወዳዳዳችችችኃኃኃለለለንንንንንን😍😍😍❤❤❤❤
نمایش همه...
📚ርዕስ:- ሕይወቴ 📝ድርሰት:- ተመስገን ገብሬ 📜ይዘት:- ግለ ታሪክ 📆የመጀመሪያ ዕትም:- 2001 📖የገፅ ብዛት:- 190 📌አዘጋጅ:- 📌ማጋራት አይዘንጋ! @ETHIO_PDF_BOOKS1 @ETHIO_PDF_BOOKS @YETMHRTPDF @BHERE_TREKA
نمایش همه...
ንባብ ለሕይወት-1.pdf17.71 MB
ሰርቫይቫል-101-መሪ-ሃሳብ.pdf5.94 MB
ሕይወቴ (ግለ ታሪክ) በተመስገን ገብሬ.pdf36.57 MB
የመጽሐፍ ግብዣ ❤❤
نمایش همه...
የነገው ሰው! አንድ ሰው ለብዙ አመት ያገለገለው ባለጠጋ አለቃው በድንገት ከዚህ አለም በሞት በተለየበት ወቅት አንድ ሰው እንዲህ ሲል ጠየቀው፡ “ለመሆኑ ይህ ባለጠጋ አሰሪህ ሲሞት ወደ ገነት (ጀነት) የሄደ ይመስላሃል?” አለው፡፡ ይህ አገልጋይ ጊዜ ሳያባክን፣ “ወደ ገነት (ጀነት) የሄደ አይመስለኝም” በማለት መለሰ፡፡ “ለምን እንዲዚያ አሰብክ?” ተብሎ ሲጠየቅ፣ “ወደ ገነት (ጀነት) የሚወስደውን አይነት ዝግጅት ሲያደርግ ስላላየሁት” ብሎ መለሰ ይባላል፡፡ ወደ ገነት (ጀነት) የመግባት ዝግጅቱ አስፈላጊነት የላቀ የመሆኑ እውነታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ታሪኩን በዚህ ምድር ላይ ስላለው የየእለት ሕይወታችን መለስ አድርገን ስናስበው የሚያስታውሰን አንድ እውነት አለ፡፡ የዛሬ ዝግጅታችን ወደየት አቅጣጫ እንደምንሄድና ነገ የት እንደምንገኝ አመልካች ነው፡፡ የነገው ትልቅና ስኬታማ ሰው በዛሬው ዝግጅቱ ያስታውቃል፡፡ የነገው አስተማሪ በዛሬው ተማሪነቱ ያስታውቃል፡፡ የነገው መልካም የትዳር ሰው ዛሬ ባለው ጨዋ የፍቅር ሕይወት ግንኙነቱ ያስታውቃል፡፡ የነገው ጨዋ መሪ በዛሬ የሚከተለውን ጨዋ መሪ ተጠንቅቆ በመምረጡ ያስታውቃል፡፡ የነገው አዋቂ በዛሬ አንባቢነቱ ያስታውቃል፡፡ የነገው ጨዋ ባለሃብት ዛሬ በገንዘብ ላይ ባለው አመለካከቱ ያስታውቃል . . . ፡፡ ነገ ራስህን የምታገኘው እድል ያመቻቸልህ ነገር ላይ ሳይሆን ዛሬ በቂ ዝግጅት ያደረክበት ነገር ላይ ነው፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
نمایش همه...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

የማለዳ ቃል!! ኢሳይያስ 58 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል። ¹¹ እግዚአብሔርም ሁልጊዜ ይመራሃል፤ ነፍስህንም በመልካም ነገር ያጠግባል አጥንትህንም ያጠናል፤ አንተም እንደሚጠጣ ገነት፥ ውኃውም እንደማያቋርጥ ምንጭ ትሆናለህ። 🔥 በዚህ ክፍል እግዚአብሔር በመስጠት ውስጥ ያለውን በረከት እየተናገረ ነው የሚሰጥ ሰው እግዚአብሔር መልካም ያደርግለታል ቃሉ የሚናገረው በረከቶች ያገኘዋል ክብር ለጌታ ይሁን 🔥 የምንሰጠው ለሰዎች መልካም የምናደርገው በረከትን ለማግኘት አይደለም ስለዳንን ነው የእግዚአብሔር ልጆች ስለሆንን ነው ስለዚህ መልካም ማድረግ ለሰዎች መስጠት መቆረስ ፍሬያችን ነው 🔥 እግዚአብሔር የብዙዎች ጥላ ማረፊያ የብዙዎች መባረኪያ ምክንያት ያድርጋችሁ""አሜን ብሩኳኖች ናችሁ🙏🙏❤❤ https://t.me/tobecharitable https://t.me/tobecharitable
نمایش همه...
አንድነት በጎ አድ. ማኀበር

❤አቅመ ደካሞችን መርዳት፦ ሥነ ልቦናዊ እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ላሉት ሰዎች እንደርስላቸዋለን እንረዳቸዋለንም።❤ አንድነት በጎ አድራጎት ማኅበር (አበአማ)❤

🥰 1
ከታሪኩ ተማሩ እስኪ😘😱
نمایش همه...
ዛሬም የጌታ ነው ። አንድ ጊዜ አንድ ሰው ነበር አሉ ። እንግዲህ ሰውየው ለመኖር የተሰጣውን እድሜ ለሦስት ከፍሎ ለመኖር ዓቀደ። ከዚያ በኃላ እንዲ ብሎ ዓቀደ፦ የመጀሪያውን 40 እጅሜ ለራሴ እኖራለሁ ።ያውም የራሴን Business ጀምሬ ሃብታም እሆናለሁ፣ #ገንዘብ_አከማቻለሁ ፣ ትምህርት እማራለሁ ፣ የግሌን ሕይወት በአጠቃላይ አበለጽጋለሁ ብሎ ስለ ግሉ ሕይወቱ ብቻ ዓቅዶ ቁጭ አለ። ሁለተኛውን 40 እድሜ ደግሞ ለቤተሰቤ እኖራለሁ ፣ አግብቼ ልጆችን ወልዳለሁ ፣ ልጆቼን ወግ ማዕረግ አደርሳለሁ፣ ሚስቴን አስደስታለሁ ብሎ አረፋ። ሦስተኛውን 40 ደግሞ #ለእግዚአብሔር_እኖራለሁ አለ።🤭🫢 እንግዲህ ሰውየው ያቀዳቸው እቅዶች ሁሉ መልካም ሆነው ሚዛኑን ያልጠበቀ መሆኑ ግርምትን ይጭራል ። ታዲያ ይህ ምን ቢሆን ጥሩ ነው !🙄 ሁለቱንም አርባ አመታት ጨርሶ #አሸለበ😭😭 እንዴት ያሳዝናል ። ታሪኩን ያገኘሁት ከመንፈሳዊ መጽሐፍ ነው። ታሪኩ ጥቂት ነገሮችን ያስገነዝበናል 1.እድሜ የእግዚአብሔር ሥጦታ እንጂ እኛ እንደፈለግን መርጠን የሚንገዛበት Package አይደለም ። 2. ይህችህ ምድር ጊዜያዊ መኖሪያ እንጂ የዘላለም ቤታችን አይደለም ። ባይሆን እኛ እንግዶችና መጻተኞች እንጂ 1ጴጥ 2:11 3. እኛ በዚህ ምድር በምንም ነገር ላይ እርግጠኞች መሆን እንደማንችል ይልቁን ሁሉን አዋቂ እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን ማወቅ አለብን ። ስለነገ ምናወቀው ነገር የለንም ባይሆን ነገ በእግዚአብሔር እጅ መሆኑን እናምናለን ። ስለዚህ ወገኖቼ ዛሬ የተሰጣን በምህረቱ ብዛት እንጂ በእኛ አቅም በመልካምነነታችን የሆነው አንድም ነገር የለም ።ታዲያ #እኛና የእኛ የሆኑት ሁሉ የእግዚአብሔር አይደሉምን ? ታዲያ ትምክህታችን ወዴት አለ? ይዘህ የመጠሆ ነገር ሳይኖር ይዘህ ለማትሄደው ነገር ስትጨነቅ የዘላለምን ሕይወት እንዴት ቸል ትላለህ ? አንቺም እህቴ በተመሳሳይ !! ዮሐንስ 9 (John) 4፤ ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች። ዮሐንስ 12 (John) 35፤ ኢየሱስም፡— ገና ጥቂት ጊዜ ብርሃን ከእናንተ ጋር ነው። ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማም የሚመላለስ ወዴት እንዲሄድ አያውቅም። ሉቃስ 12 (Luke) 15፤ የሰው ሕይወት በገንዘቡ ብዛት አይደለምና ተጠንቀቁ፥ ከመጐምጀትም ሁሉ ተጠበቁ፡ አላቸው። ያዕቆብ 4 (James) 13፤ አሁንም፡— ዛሬ ወይም ነገ ወደዚህ ከተማ እንሄዳለን በዚያም ዓመት እንኖራለን እንነግድማለን እናተርፍማለን የምትሉ እናንተ፥ ተመልከቱ፥ ነገ የሚሆነውን አታውቁምና። 14፤ ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና። 15፤ በዚህ ፈንታ፡— ጌታ ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል። 16፤ አሁን ግን በትዕቢታችሁ ትመካላችሁ፤ እንደዚህ ያለ ትምክህት ሁሉ ክፉ ነው። ✍🗒 Fish T Share share share join us https://t.me/ZOEEternallife
نمایش همه...
ZOE (ዞዊ) Eternal life

የምታገለግሉት ጌታ ክርስቶስ ነውና። ቆላ 3:24 ማደግህ በነገር ሁሉ እንድገለጥ ይህን አስብ ፥ ይህንም አዛወትር... ይህን ብታደርግ፥ ራስህንም የሚሰሙህንም ታድናለህና። 1ጢሞ 4:15-16 @ዞዊ ማለት የእግዚአብሔር ሕይወት ወይም ዘላለማዊ ሕይወት ማለት ነው ። መገኛ ምንጩም የኢየሱስን ሞትና ትንሣኤውን በማመን ነው ።

ጀምሮ የመጨረስ ጥቅሞች! (“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ) “የሚከፈልህ ለጀመርከው ነገር አይደለም . . . ጀምረህ ለጨረስከው ነገር ብቻ ነው የሚከፈልህ” – Gary Ryan Blair 1. በራስ መተማመን፡፡ አንድን ነገር ጀምረው የማይጨርሱ ሰዎች የሚደርስባቸው ክስረት ድርብ ክስረት ነው፡፡ በአንድ ጎኑ ተጀምሮ ያልተጨረሰው ስራ ክስረት ሲያደርስባቸው በሌላ ጎኑ ደግሞ ጀምረው ባለመጨረሳቸው ምክንያት በራሳቸው ላይ ያላቸው ግምትና አመለካከት እየወረደ ይሄዳል፡፡ ከዚህ በተቃራኒ አንድን ነገር ጀምረው ካልጨረሱ በስተቀር ያለማቆም ልማድ ያላቸው ሰዎች ይህ ነው የማይባል በራስ የመተማመን የስነ-ልቦና ድልን ያገኛሉ፡፡ ይህ ድል ለሚቀጥለው ስራቸው የተማመኑና የተረጋጉ ስለሚያደርጋቸው አንድን ነገር ጀምሮ የመጨረስ እንድርድረት (Momentum) ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ 2. በሰዎች ተቀባይነት፡፡ አንድን ነገር ጀምሮ ሳይጨርስ አንጠልጥሎ ዘወር የሚልና ሌላ ነገር ደግሞ የሚጀምር ሰው በማንም ሰውም ሆነ ተቋም ያለው ተፈላጊነት እጅግ የወረደ ነው፡፡ ስለሆነም፣ ጀምረው የማይጨርሱ ሰዎች በሕብረተሰቡ መካከል ተቀባይነት የማጣት አዙሪት ውስጥ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ በተቃራኒ አንድን ነገር ጀምረው የሚጨርሱ ሰዎች ቀድሞውኑ እጅግ ተፈላጊና ዋጋቸውም የከበረ ሰዎች ናቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በገቡበት ቦታ ሁሉ ይዘው የሚመጡት አንድን ነገር በጥራትና በብቃት የመጨረስ ልማድ የሚሰጣቸው የእድገት ፍጥነት ይህ ነው አይባልም፡፡ 3. ተወዳዳሪነት፡፡ ጀምሮ የመጨረስ ነገር ያልበራለትና ያንንም ልማድ ያላዳበረ ሰው በሄደበት ስፍራ ሁሉ ሲጀምር መካከለኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ደግሞ መጨረሻ ሆኖ ራሱን ያገኘዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው አሁን ባለንበት ውድድር እጅጉን በተስፋፋበት ዘመን ቀደም ብሎ የመገኘት ጉዳይ ካሳሰበው በመጀመሪያ ሊያዳብር የሚገባው ጀምሮ የመጨረስን ልማድና ክህሎት ነው፡፡ ጀምሮ የመጨረስ ምስጢር ቀድሞውኑ የገባቸውና ያንንም ያዳበሩ ሰዎች በሕብረተሰቡ መካከል ያላቸው ተወዳዳሪነት እጅግ የላቀ ነው፡፡ ከዚህ ተወዳዳሪነታቸው የተነሳ ካለማቋረጥ የእድገትን መሰላል ሲወጡ ራሳቸውን ያገኙታል፡፡ 4. ሌላ በር መከፈት፡፡ አሁን በእጁ ያለው ነገር ደግሞ ሌላ ነገር ወልዶና ተባዝቶ ማየት የማይመኝ ሰውም አይገኝም፡፡ አንድን ነገር ጀምሮ የመጨረስ ብቃቱን ያላዳበረ ሰው ይህን ሁኔታ ቢመኘውም የሕልም እንጀራ ሆኖ ያገኘዋል እንጅ በእጁ ማስገባት ያስቸግረዋል፡፡ ጀምሮ የመጨረስ ብልሃት የገባው ሰው በፍጹም በአንድ የእድገት ደረጃ መክረም የማይችል ሰው ነው፡፡ እንዲህ አይነቱ ሰው በእጁ ያለውን ተግባር በብቃት ሲያጠናቅቅ ወደደም ጠላም ያጠናቀቀው ስራ የሚወልደውን ሌላ የላቀ ስራ መረከቡ አይቀርም፡፡ https://t.me/Dreyob https://m.youtube.com/user/naeleyob623 https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/
نمایش همه...
Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.