fa
Feedback
Assignment supporters

Assignment supporters

رفتن به کانال در Telegram

ለ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው የማንኛውንም የትምህርት አይነት በ የትኛውም የክፍል ደረጃ የተሰጣችሁን assignment ከ አንድ ቀን ባነሰ ግዜ ውስጥ በ ከፍተኛ ጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሰራት ከፈለጉ ያናግሩን👇👇 @positive_thinkerrr ወይም 0994409904 ይደውሉ።

نمایش بیشتر
362
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
✏️ ምደባ እየጠበቅን እንቀልዳ እስቲ፦ 📚 የት ዮኒቨርስቲዎች ከደረሳችሁ ምን ይዛቹሁ መሄድ አለባችሁ ፦ (ለቀልድ) 📍 ለመጀመርያ ጥቂት ግቢዎች ብቻ  እናያለን ፦ 💡 ድሬደዋ 💬 ሽንት ቤቱ አይነፋም = ፖፖ (popo) እንዳትረሱ ፤ ====================== 💡ሰመራ 💬 አቤት ሙቀት = ግልገል ሱሪ ስለማትለብሱ መርጦ (ሽርጥ) አትርሱ ። ====================== 💡ብሌሆራ 💬 የካፌ ምግብ ምንም አይነፋም = 10 ኪሎ በሶ አትርሱ (ኧረ እሱም ያንሳል ) ====================== 💡አዳማ 💬 ከጅብ ጋር ስለምትማሩ =  ጅበኛ ቋንቋ መማር አትርሱ ፤ ====================== 💡 አርባምንጭ 💬ሙዝ ብቻ ስለሆነ ሀገሩ ፤ ማባያ የሚሆን ዳቦ በኩንታል አትርሱ ====================== 💡ጅማ 💬 እንኳን ተማሪ አህያም ያስሠርቃል ፤ ለመንዘላዘል ተዘጋጁ ። ====================== 💡 ጎንደር 💬 ጀግኖቻቸው ካላወደሳችሁ ስለሚቀየሙ ፤  የአፄ የቴድሮስ ትያትር ተለማመዱ (ፉከራ እና ሽለላ ብትጨምሩ አይከፋመ ።) ====================== 💡ሃረማያ 💬 በሳምንት 6 ቀን ስጋ ስላለ ፤ የጥርስ መጎርጎሪያ ስቲኪኒ አትርሱ ፤ ©assignment_supporters ===== To discuss📜👇   📌 @positive_thinkerrr 🗒️To inform and send your assignment 🖌️ 📌@assignment_supporters #Share📌 🔖@assignment_supporters

በቀጣይ ግቢ የምትገቡ የ ተፈጥሮ ሳይንስ( Natural science) ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ። 📚 የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች👇   📌 MATHEMATICS ( for natural science) 📌 GENERAL PHYSICS 📌 GEOGRAPHY 📌 LOGIC & CRITICAL THINKING 📌 COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL I 📌 PSYCHOLOGY 📌 PHYSICAL FITNESS 🥺 እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች እንመልከት።                            📌 MATHS 📚 11 ኛ እና 12 ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው አብዛሀኞቹ ፡ የተወሰነ ለውጥ( modification) ነው ያለው። 📚 በይበልጥ ፈተና ሲውጣ Basic ነገር ነው የሚያወጡት Module ማንበብ ለዚ ግዜ በጣም ወሳኝ ነው Module በደምብ ሳታነቡ Reference እንዳገልጡ አደራ Defintion , Properties , Exercises ..... module ላይ ያለውን በደምብ ያዙ የሚሰጣቹ Course outline ላይ ያለውንም ነጥብ በደምብ ተመልከቱ ምን ላይ ማተኮር እንዳለባቹ ይረዳቹሀል::                   📌 Logic and critical thinking 📚 ይህ course ለእናንተ አድስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው። የ concept ተማሪ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል ፡ እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው🙈። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል ። ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም☹️። 📚 ለማንኛውም ለ logic and critical thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ። 1ኛ) Concise introduction to logic 2ኛ)  freshman logic 📌 Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት😴። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን  ፈተና ትሰሩታላችሁ😸 ምክንያቱም የከባድ ጥያቄዎች ጣሪያ የሚባሉ ጥያቄዎች መፅሀፉ ላይ አሉ። ኸረ እንዳውም ከመፅሀፉ Exercise ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ፈተና ላይ ቀጥታ ያወጡታል🙈🙈። የግቢ መምህሮች በጣም የሚጠቀሙት መፅሀፍ ነው👏👏። 📌 Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የ logic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ👏😘። የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ ( concept) በቀላሉ ለመረዳት freshman logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የ concept ጥያቄዎችም አሉት😴😍። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ 1ኛ) መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት ፡ ፒዲኤፍ ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት። A+ tutorial Class ላይ ትምህርቱ ግልፅ በሆነ መንገድ ስለሚሰጥ እዛ ላይ ተመዝግባችሁ መማር። 2ኛ) freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው። 3ኛ) Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ🕺 ፡ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት😴። ከዛ A ታመጡና መቀወጥ🕺💃🕺💃😁😁።                   📌 Communicative English skill I ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡🙈። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ🤔 📚 Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%) 📚 Grammar ( Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው ፡ Concise ላይ የተለቀቁ ኖቶችም ሊጠቅማችሁ ይችላል።) ኮርሱ A+ tutorial class ላይ እጅግ በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ ይሰጣል ብዙ ተማሪዎችም A+ አምጥተውበታል ተመዝግባችሁ ተማሩ።                             📌 Geography ለ Geography ም አዲስ አይደላችሁም። ነገር ግን ይህ ትምህርት አንዴ ተነቦ የሚተው አደለም በተፈጥሮው ይተናል ብል ይቀላኛል 🤷‍♂ ስለዚህ ብትችሉ ስታነቡ Note ያዙ ቀጣይ ስትደግሙት Note ብቻ ማንበብ ነው የሚጠበቅባቹ ከ module ውጪ ፈተና አይወጣም PPT እንደ Apetizer ውሰዱ 😂 እንዳልኳቹ ስለሚረሳ ቶሎ ቶሎ ሳይበዛ ከልሱት አንዳንዴ Module ስታነቡት ደስ ላይል ሰለሚችል Note እየያዛቹ ዋና ዋና ነጥቡን አንብቡ 👍::                           📌 Psychology 📚ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል:: ይህ ትምህርት ለየትው የሚያረገው በደምብ መረዳትን ይጠይቃል Module ካነበባችሁ በቂ ቢሆንም Module በደምብ የማያብራራው ሀሳብ ስለሚኖር Google ማድረግ በጣም ተመራጭ ነው በይበልጥ ከ ምዕራፍ 3 ጀምሮ የ Case ጥያቄ ስለሚበዛ በደም Exercise መስራት ይጠቅማቹሀል በቀላሉ Google ላይ በ Topicu ርዕስ worksheet search ብታረጉ ከፈተናው ተመሳሳይ ጥያቄ ታገኛላቹ። ሌላኛው አማራጭ YouTube ነው እኛ ሀገር በስፋት ባይለመድም በአጭር ግዜ Concept ለመረዳት ፍቱን ነው ሞክሩት ። 11 ምዕራፎች ሲኖሩት ቢበዛ እስከ ምዕራፍ 8 ብትማሩ ነው አታስቡ  A+  የናንተ ናት 👍 ኮርሱ A+ tutorial class ላይ እጅግ በጣም ግልፅ በሆነ መንገድ ይሰጣል ብዙ ተማሪዎችም A+ አምጥተውበታል ተመዝግባችሁ ተማሩ።                         📌 General Physics General physics የምትማሩት ከ 11 እና 12 የተለየ ነገር የለውም ከናንተ የሚጠበቀው Module ማንበብና የተወሰነ Refer አድርጋቹህ ጥያቆዎችን መስራት ነው እንጂ የተለየ አዲስ ነገር የለውም::                           📌 Physical fitness ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው😁። ስለዚህ የ ስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ😂። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም::  pass or fail ነው የምትባሉት። በመጨረሻም የ natural science ተማሪዎች የመጀመሪያ ሴሚስተር የምትወስዷቸውን ኮርሶች እና አጋዥ መፅሀፍ በ PDF ቀጣይ እንልክላችሗለን:: 📌 Join and share 👇👇 @assignment_supporter @assignment_supporter ▬▬▬▬▬▬▬▬

📖ማንኛውንም አሳይመንት በጥራት እንሰራለን! የምንሰራው ✅ከ9-12 ✅ለRemedial ✅ለFreshman ✅ለCollege ✅ለUniversity ✅ለSummer and Extension any Department Assaigment በጥራት እንሰራለን✍️ አሳይመንቶን በዚ ይላኩ 👉 @positive_thinkerrr @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

👉Clauses of Concession ------------------------------------------- ☑️Although(ምንም እንኳ) ☑️Though(ምንም እንኳ) ☑️Even though(ምንም እንኳ) ☑️Inspite of(ምንም እንኳ) ☑️Despite(ምንም እንኳ) ☑️Inspite of the fact that(ምንም እንኳ) ☑️Despite the fact that(ምንም እንኳ) እነዚህ ከላይ የዘረዘሩት Clauses of concession ይባላሉ።      🔘🔘Usage(አገልግሎታቸው) 📙To describe two contrasting ideas.( ሁለት የማይስማሙ ፡ የሚጋጩ ፡ የሚቃረኑ ሀሳቦችን ለመግለፅ ከላይ የተዘረዘሩትን clauses of concession እንጠቀማለን።) ለምሳሌ ለፈተናው በደንብ ተዘጋጅተህ ነበር ነገር ግን ፈተናውን ማለፍ ሳትችል ቀረህ። ስለዚህ ሁለት የማይስማሙ ሀሳቦቼ አሉ። 🔶ሀሳብ 1፡ ለፈተናው በበቂ ሁኔታ መዘጋጀት። 🔷ሀሳብ 2፡ ፈተናውን መውደቅ። ሀሳብ 1 ከ ሀሳብ 2 ጋር ሊስማማ የሚችለው ፈተናውን ማለፍ መቻል በሚለው ሀሳብ ነበር፡ ፈተናውን ማለፍ አለመቻሉ ሁለቱ ሀሳቦች የሚጋጩ እንድሆኑ አድርጓቸዋል። ስለዚህ በአማርኛ እንድህ ብለህ ትናጋለህ፡ "ምንም እንኳ ለፈተናው በደንብ ተዘጋጅቼ የነበረ ቢሆንም ፈተናውን ማለፍ አልቻልኩም ነበር።" ስለዚህ 👉👉ምንም እንኳ የሚለው አፍራሽ የአማርኛ ቃል ከላይ የተዘረዘሩትን clauses of concession ን ይተካልናል። ስለዚህ ምንም እንኳ ብለን በ እንግሊዝኛ መናገር ወይም መፃፍ ብንፈልግ Clauses of concession ንን እንጠቀማለን። ነገር ግን አጠቃቀማቸው ላይ ልዩነት አለ። ልዩነቱ ምንድን ነው? እንዴትስ እንጠቀም የሚለውን እንመልከት!               #1⃣ ☑️Although ☑️Though ☑️Even though  +Sub+verb ☑️Inspite of the      fact that ☑️Despite the      fact that ስለዚህ although, even though, though , inspite of the fact that ና despite the fact that ብለን ከተናገርን ውይም ከፃፍን በሗላ subject ይከተላል ከ subject ቀጥሎ verb ይከተላል። ከላይ ያለውን ምሳሌ በ English እንድህ እንላለን፡ 📗📕Although I prepared well, I couldn't pass the exam.ስለዚህ Although + I(sub) + prepared(verb) ስለዚህ በ although ቦታ though, even though,  inspite of the fact that ና despite the fact ተክተን አሁን ያየነውን example መስራት እንችላለን ምክንያቱም አጠቃቀማቸው ፡ ትርጉማቸውም ተመሳሳይ ስለሆነ። ስለዚህ 📕📕Despite the fact that I prepared well, I couldn't pass the exam.              #2⃣ 🔶Inspite of   +  noun or  🔷Despite        noun phrase ስለዚህ inspite of ና despite ካልን ቡሗላ ቀጥሎ መምጣት ያለበት noun ወይም noun phrase ነው ማለት። ቅድም በ although የሰራነውን አሁን ደግሞ በ inspite of ና despite ሲሰራ ምን እንደሚመስል እንመልከት። 🔘🔘Inspite of my preparation, I couldn't pass the exam. 🔘🔘Despite my preparation,  I couldn't pass the exam. 🔴inspite of + my preparation(noun) 🔵despite + my preparation(noun) ስለዚህ ሁሉም ምሳሌዎች በትርጉምም በአገልግሎትም ተመሳሳይ ናቸው ነገር ግን የምንጠቀምበት መንገድ ነው ልዩነቱ። Examples ☑️Even though John works hard, he earns minute.(ምንም እንኳ John ጠንክሮ ቢሰራም የሚያገኘው ግን ትንሽ ነው።ሁለት የማይስማሙ ሀሳቦች) Even though + John(subject) + works(verb) ☑️Inspite of hard working, John earns minute.(ምንም እንኳ ጠንክሮ ቢሰራም john ትንሽ ነው የሚያገኘው።) 🔴🔴ሲነበቡ Although(ኦልዞ) Though(ዞ) Even though(ኢቭን ዞ) ከተመቻችሁ join and share 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter ▬▬▬▬▬▬▬▬

📚 እንደሚታወቀው አብዛኞቻችን የ ኢትዮጵያ ተማሪዎች እና English subject አንተ ትብስ አንተ ትብስ ÷  አትድረስብኝ አልደርስብህም ተባብለን ተከባብረን እና ተቻችለን ነው የምንኖረው😂። ለዛም ነው ብዙዎቻችን መሰረታዊ የሚባለውን የ ሰዋ ሰው ህግ(Grammar) በ ቅጡ ለይተን የማናውቀው። የ was እና የ were ጥቅምን እንኳን ለይተን ለማወቅ የምንቸገር ብዙዎች ነን። 📚 በ ኢትዮጵያም ሆነ በ አለም ከሚሰጡ የ ዩኒቨርሲቲዎች መግቢያ ፈተና Entrance Exam መካከል አንዱ የ እንግሊዝኛ ትምህርት ነው። 🤔 ታዲያ ምን መፅሀፍ ባነብ ነው አመርቂ ውጤት የማስመዘግበው❓ምን ምን ላይ ትኩረት ባደረግ ነው አመርቂ ውጤት የማስመዘግበው❓ 📚 እኔ ከ 11 ኛ ክፍል በፊት የ እንግሊዝኛ ትምህርት ምንም አልችልም ነበር። ከ ድንጋይ ላይ ውሀ የማፍሰስ ያክል ነበርን እኔ እና አቶ እንግሊዝኛ😁። አሁን እንኳን ወይ ዘሮ ዬ ብያታለሁ። ጥቂት የማይባሉ አመታትንም በ ፍቅር አብረን አሳልፈናል😘😍 ። 📚 በ አዱኛ ጓዴ የተፃፈው Advance English Worldwide Book ደግሞ እኔን እና እንግሊዝኛን በማጀናጀን የጦፈ ፍቅር ውስጥ እንድንገባ በማድረግ የ አንበሳውን ድርሻ ተወጥቷል😎። 📚 አሁን ወደ ገደለው ብገባ ይሻለኛል። ምን አልባት ሌላ ጊዜ እንግሊዝኛ ማወቄ በ ትምህርቱ አለም ምን ያክል ውጤታማ እንዳደረገኝ በሰፊው እንዳስሰው ይሆናል። 📚 ለ Entrance ተፈታኞች የ ማስተላልፈው ነገር ቢኖር በ Entrance Exam ላይ የ እንግሊዝኛ ትምህርትን ከፍተኛ ውጤት ማምጣት ከፈለጋችሁ Advance English Worldwide Book ከበቂ በላይ ነው😋። ሰምታችሁኛል ኣ😳❓ከበቂ በላይ ነው። 📚 እንደውም የ እንግሊዝኛን Entrance Exam የሚያወጣው Advance worldwide book ን የፃፈው ሰው ነው መሰል🙈። ትምህርት ሚኒስቴር አልሰማም አሉ እሺሺ😤🤭። ሌላ መፅሀፍ ማንበብ አይጠበቅባችሁም። ምን አልባት መማሪያ መፅሀፉ ላይ ያሉትን አንዳንድ ኖቶች እና ምሳሌዎችንም አንብቧቸው። 🤔 ምን ምን ላይ ትኩረት(focus) እናድርግ❓ 📚 አሁን ያላችሁ ጊዜ አንድ ወር ከምናምን ነው። በጣም በቂ ጊዜ ነው ብሎ ለመናገር ይከብዳል። ስለዚህ ባለችን ትንሽ ጊዜ ምን ምን ላይ ትኩረት አድርገን ጥሩ ውጤት እናምጣ❓ 🌹 Grammar 👇 👉 Tense. 👉 Adverbial Clause. 👉 Conditional sentence. 👉 Inversion. 👉 Subject verb agreement. 👉 Indefinite pronoun. 👉 Quantifier. 👉 Comparision. 👉 Participle Adjectives. 👉 Deduction. 🌷VOCABULARY( Compilation and substitution)👇 👉 Phrasal verbs.( ከ 12 ኛ ክፍል መፅሀፍ በስተጀርባ ታገኙታላችሁ) 👉Confusing Words.( ከ Advance book በስተጀርባ ታገኙታላችሁ።) 🌺 Writing Skill👇 👉 Types of paragraph(pieces of writing.) 👉 Punctuation and Capitalization.(Advance ላይ የሚገርም ኖት አለላችሁ😍።) 👉 Letter Writing. 👉 Research.(Advance ላይ የለም😢። Google አርጉ❗️) 📚 ከዛ ደግሞ Communication, Paragraph Coherence እና  Word order ላይ የ ብዙ አመት ጥያቄዎችን ተለማመዱ። Advance ላይ አሪፍ ኖት ታገኛላችሁ። በተለይ Communication ላይ መሰረታዊ የሚባሉ ህጎችን በዝርዝር ተቀምጠዋል             ═══◉❖◉════        🦁• https://t.me/assignment_supporter •🦁        🦁• https://t.me/assignment_supporter •🦁 ▬▬▬▬▬ 📌sʜᴀʀᴇ📌▬▬▬▬▬

♻️ Cell Wall Structure and Function ♻️ ♦️What is Cell Wall? ➖ Cell wall is rigid and protective layer around the plasma membrane ➖ Discovered by Robert hooke in 1665 ➖ Cell wall non-living rigid structure ➖ Found in plants, fungi, prokaryotes and protists ➖ Composition of cell wall varies in different groups ♦️Characteristics of Cell Wall ➖ Cell wall is a rigid and protective layer around the plasma membrane ➖ It is a non-living structure ➖ Animal cells do not have a cell wall ➖ Found in in most plant cells, fungi, bacteria, algae, and some archaea ➖ Cell wall has many important functions in a cell including protection, structure, and support ♦️Cell Wall Structure ✍️Structure of Prokaryotes Cell Wall ➖ Cell wall is made up of peptidoglycon ➖ Peptidoglycan made up of polysaccharide chains cross-linked by unusual peptides containing D-amino acids ➖ A notable difference between the cell walls of gram-positive and gram-negative bacteria is the substantially thicker peptidoglycan layer in gram-positive bacteria. ➖ Cell wall of gram-positive bacteria contains teichoic acids ✍️Structure of Fungi Cell Wall ➖ Fungal cell wall is made up of three main components ✍️Chitin ➖ Polymers consisting mainly of unbranched chains of β-(1,4)-linked-N-Acetylglucosamine in the Ascomycota and ➖ Basidiomycota, or poly-β-(1,4)-linked-N-Acetylglucosamine (chitosan) in the Zygomycota ➖ Both chitin and chitosan are synthesized and extruded at the plasma membrane ✍️Glucans ➖ Glucose polymers that function to cross-link chitin or chitosan polymers ➖ β-glucans are glucose molecules linked via β-(1,3)- or β-(1,6)- bonds and provide rigidity to the cell wall while α-➖ ➖ glucans are defined by α-(1,3)- and/or α-(1,4) bonds and function as part of the matrix ✍️Proteins ➖ Enzymes necessary for cell wall synthesis and lysis in addition to structural proteins are all present in the cell wall. ➖ Most of the structural proteins found in the cell wall are glycosylated and contain mannose, thus these proteins are called mannoproteins or mannans. 🌀Structure of Plant cell wall ➖ Cell wall is made up of 4 layers ➖ Middle lamella, primary, secondary and tertiary wall I) Middle lamella ➖ Cementing layer between the cells ➖ It is made up of ca & mg pectates II) Primary cell wall ➖ Found in growing cell ➖ It has high hemicelluloses & less cellulose content III) Secondary cell wall ➖ Found in mature cell ➖ It has high cellulose & less hemicelluloses content IV) Tertiary cell wall ➖ Laid down on secondary wall ➖ Found in tracheids of gymnosperms ♦️What is Pits? ➖ Cell wall is not uniform in thickness throughout ➖ Certain places cell wall are not laid down, such places are called pits ♨️Pits are of two types I) Simple Pit ➖ Pit chamber is uniform in diameter ➖ Found in angiosperms II) Bordered pit ➖ Pit chamber is flask shaped ➖ Found in gymnosperms ➖ Number of plasmodesmata or cytoplasmic strands are present in pit ♦️ Functions of cell wall ➖ Maintains shape of the cells ➖ Protects cell from mechanical injury ➖ Allows materials to pass in and out of the cell ➖ Prevents undue expansion of cell when water enters by osmosis ⬜️◽️▫️▫️https://t.me/assignment_supporter▫️▫️◽️⬜️ ⬜️◽️▫️▫️https://t.me/assignment_supporter▫️▫️◽️⬜️

🔗Mathematics formulas🔗 እንዳትሸወዱ አይጠቅመኝም ብላችሁ እንዳታልፉት !! Maths calculations ላይ  ይጠቅማችኋል 1. (α+в)²= α²+2αв+в² 2. (α+в)²= (α-в)²+4αв 3. (α-в)²= α²-2αв+в² 4. (α-в)²= (α+в)²-4αв 5. α² + в²= (α+в)² - 2αв. 6. α² + в²= (α-в)² + 2αв. 7. α²-в² =(α + в)(α - в) 8. 2(α² + в²) = (α+ в)² + (α - в)² 9. 4αв = (α + в)² -(α-в)² 10. αв =1. (α + в + ¢)² = α² + в² + ¢² + 2(αв + в¢ + ¢α) 12. (α + в)³ = α³ + 3α²в + 3αв² + в³ 13. (α + в)³ = α³ + в³ + 3αв(α + в) 14. (α-в)³=α³-3α²в+3αв²-в³ 15. α³ + в³ = (α + в) (α² -αв + в²) 16. α³ + в³ = (α+ в)³ -3αв(α+ в) 17. α³ -в³ = (α -в) (α² + αв + в²) 18. α³ -в³ = (α-в)³ + 3αв(α-в) ѕιη0° =0 ѕιη30° = 1/2 ѕιη45° = 1/√2 ѕιη60° = √3/2 ѕιη90° = 1 ¢σѕ ιѕ σρρσѕιтє σƒ ѕιη тαη0° = 0 тαη30° = 1/√3 тαη45° = 1 тαη60° = √3 тαη90° = ∞ ¢σт ιѕ σρρσѕιтє σƒ тαη ѕє¢0° = 1 ѕє¢30° = 2/√3 ѕє¢45° = √2 ѕє¢60° = 2 ѕє¢90° = ∞ ¢σѕє¢ ιѕ σρρσѕιтє σƒ ѕє¢ 2ѕιηα¢σѕв=ѕιη(α+в)+ѕιη(α-в) 2¢σѕαѕιηв=ѕιη(α+в)-ѕιη(α-в) 2¢σѕα¢σѕв=¢σѕ(α+в)+¢σѕ(α-в) 2ѕιηαѕιηв=¢σѕ(α-в)-¢σѕ(α+в) ѕιη(α+в)=ѕιηα ¢σѕв+ ¢σѕα ѕιηв. » ¢σѕ(α+в)=¢σѕα ¢σѕв - ѕιηα ѕιηв. » ѕιη(α-в)=ѕιηα¢σѕв-¢σѕαѕιηв. » ¢σѕ(α-в)=¢σѕα¢σѕв+ѕιηαѕιηв. » тαη(α+в)= (тαηα + тαηв)/ (1−тαηαтαηв) » тαη(α−в)= (тαηα − тαηв) / (1+ тαηαтαηв) » ¢σт(α+в)= (¢σтα¢σтв −1) / (¢σтα + ¢σтв) » ¢σт(α−в)= (¢σтα¢σтв + 1) / (¢σтв− ¢σтα) » ѕιη(α+в)=ѕιηα ¢σѕв+ ¢σѕα ѕιηв. » ¢σѕ(α+в)=¢σѕα ¢σѕв +ѕιηα ѕιηв. » ѕιη(α-в)=ѕιηα¢σѕв-¢σѕαѕιηв. » ¢σѕ(α-в)=¢σѕα¢σѕв+ѕιηαѕιηв. » тαη(α+в)= (тαηα + тαηв)/ (1−тαηαтαηв) » тαη(α−в)= (тαηα − тαηв) / (1+ тαηαтαηв) » ¢σт(α+в)= (¢σтα¢σтв −1) / (¢σтα + ¢σтв) » ¢σт(α−в)= (¢σтα¢σтв + 1) / (¢σтв− ¢σтα) α/ѕιηα = в/ѕιηв = ¢/ѕιη¢ = 2я » α = в ¢σѕ¢ + ¢ ¢σѕв » в = α ¢σѕ¢ + ¢ ¢σѕα » ¢ = α ¢σѕв + в ¢σѕα » ¢σѕα = (в² + ¢²− α²) / 2в¢ » ¢σѕв = (¢² + α²− в²) / 2¢α » ¢σѕ¢ = (α² + в²− ¢²) / 2¢α » Δ = αв¢/4я » ѕιηΘ = 0 тнєη,Θ = ηΠ » ѕιηΘ = 1 тнєη,Θ = (4η + 1)Π/2 » ѕιηΘ =−1 тнєη,Θ = (4η− 1)Π/2 » ѕιηΘ = ѕιηα тнєη,Θ = ηΠ (−1)^ηα 1. ѕιη2α = 2ѕιηα¢σѕα 2. ¢σѕ2α = ¢σѕ²α − ѕιη²α 3. ¢σѕ2α = 2¢σѕ²α − 1 4. ¢σѕ2α = 1 − ѕιη²α 5. 2ѕιη²α = 1 − ¢σѕ2α 6. 1 + ѕιη2α = (ѕιηα + ¢σѕα)² 7. 1 − ѕιη2α = (ѕιηα − ¢σѕα)² 8. тαη2α = 2тαηα / (1 − тαη²α) 9. ѕιη2α = 2тαηα / (1 + тαη²α) 10. ¢σѕ2α = (1 − тαη²α) / (1 + тαη²α) 11. 4ѕιη³α = 3ѕιηα − ѕιη3α 12. 4¢σѕ³α = 3¢σѕα + ¢σѕ3α » ѕιη²Θ+¢σѕ²Θ=1 » ѕє¢²Θ-тαη²Θ=1 » ¢σѕє¢²Θ-¢σт²Θ=1 » ѕιηΘ=1/¢σѕє¢Θ » ¢σѕє¢Θ=1/ѕιηΘ » ¢σѕΘ=1/ѕє¢Θ » ѕє¢Θ=1/¢σѕΘ » тαηΘ=1/¢σтΘ » ¢σтΘ=1/тαηΘ » тαηΘ=ѕιηΘ/¢σѕΘ             ═══◉❖◉════        🦁• https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter•🦁    ▬▬▬▬▬ 📌sʜᴀʀᴇ📌▬▬▬▬

👆New Textbook ከ 9ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች አዲሱ መፅሃፍ ከላይ ተለቆላቸዋል። መፅሃፉ ገና አልታተመም✋ ስለዚህ ሁሉም ተማሪዎች በ Pdf ከደረሳቸው ይገባል። የ 2016 የ 12ኛ ክፍል ፈተና ✍ Old Curriculum =9th--11th ✍ New Curriculum =12th ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ። ሼር አርጉት https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

ክፍል ሁለት ...... በአጠቃላይ ለስኬት አንዱ ቁልፍ ግብ ማስቀመጥ ሲሆን ግብ ስናስቀምጥም ከላይ የዘረዘርናቸውን 5 ነገሮች ማካተት አለበት፡፡ ግባችን እነዚህን ነገሮች ሲያሟላ እያንዳንዱ እንቅስቃሴያችን ግባችንን ከማሳካት ጋር ይሆናል፡፡ እነዚህ ማንኛውም ግብ ሊያሟላቸው የሚገቡ ነገሮች ቢሆኑም የበለጠ ስኬታማ ለመሆን ተጨማሪ በግብ ውስጥ መካተት እንዳለባቸውም የተለያዩ ምሁራን ይናገራሉ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ የተወሠኑትን ለመጥቀስ ያህል ግብ በምናስቀምጥት ጊዜ ግባችን ሰፊ መሆን አለበት፡፡ ግባችን በጣም ትንሽ  ከሆነች በቁርጠኝነት እንድንሠራ እያደረገንም፡፡ የመንግስት መስሪያ ቤት ተቀጥረን ለመስራት ብናቅድ ይህን እንዳሣካን ባለንበት ቀጥ ብለን ነው የምንቀረው፡፡ ስለዚህ ግባችን ሠፊ መሆን አለበት። ሌላው ግባችን ማካተት ያለበት ነገር ደግሞ ዉጣ ውረድ የሚጠይቅ መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ስኬት የዉጣ ውረድ ውጤት ነው፡፡ ነገሮች አልጋ በአልጋ ከሆኑልን ብዙም ውጤታማ አንሆንም፡፡ የተወሳሰቡ ሰራዎችን የሚከተል ግብም ተመራጭ ነው፡፡ ሁሌ ተመሳሳይ የሆነ ነገር ስንሠራ ብዙዎቻችን እንሰለቻለን፡፡ በመሆኑም የበለጠ ስኬታማ ለመሆን ግባችን ውስብስብ ስራዎች የሚፈልግ መሆን አለበት፡፡      ሰዎች ለምን ግብ አያስቀምጡም? ስኬታማ መሆንን የማይፈልግ ሰው ይኖራል ብሎ ማሠቡ ተገቢ ባይሆንም ግብ የማናስቀምጥ ግን ብዙዎቻችን ነን፡፡ ከስኬት ቁልፎች አንዱ ግብ ማስቀመጥ እደሆነም ከላይ ለማየት ሞክረናል፡፡ ነገር ግን ግብ ሳያስቀምጡ ስኬት “ላም አለኝ በሰማይ” ነው፡፡ ታዲያ ሰዎች ለምን ግብ አያስቀምጡም? ብለን መጠየቅ ያሥፈልገናል፡፡ ግብ ላለማስቀመጥ ዋናው ምክንያት የምንፈልገውን አለማወቅ ነው:: ማንኛውም ሰው የሚፈልገውን ማወቅ ቀላል መስሎ ሊታየው ይችላል፡፡ ነገር ግን የምንፈልገውን በትክክል ማወቅ እጅግ አስቸጋሪ ነገር ነዉ::ምክንያቱም ፍላጎታችን በየጊዜዉ የሚቀያየር በመሆኑ ነዉ::ለዚህም  ነው ያየነው ሁሉ የሚያምረን፡፡ የሚያዝናና ኳስ ስናይ እግር ኳስ ተጨዋች መሆን ያምረናል፣ የኦሊምፒክ ሰሞን ደግሞ ሯጭ መሆን ያምረናል፡፡ ፊልም ስናይ አርቲስት መሆን እንፈልጋለን፣ አንድ የፈጠራ ስራ ስናይ ጥሩ ኢንጂነር መሆን ያምረናል፣ የሲ አይ.ኤ ንና ሞሳድን ዝና ስንሰማ ሰላይ መሆን ይከጅለናል ::የተሳካ ቀዶ ጥገና ስንሰማ ደግሞ ዶክተር መሆን በእጅጉ እንመኛለን:: አሪፍ ህንፃ ስናይ ባለ ሐብት መሆን እንቋምጣለን፡፡ ኧረ ስንቱ…፡፡ ስለዚህ  የእኛ ትክክለኛ ፍላጎት የትኛው ነው? ፍላጎታችንን በትክክል ካወቅን ግብ ማስቀመጥ አይከብደንም፡፡ “ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ” እንዲሉ አንድ ወጣት የስኬታማነትን ቁልፍ ለማወቅ ፈልጎ ዝነኛውን የግሪኩ ፈላስፋ ሶቅራጥስን የስኬትን ቁልፍ እንዲነግረው ጠየቀዉ ይባላል፡፡ ሶቅራጥስም ወጣቱን ና እየሄድን እነግርሃለሁ ብሎ በባህር ውስጥ እየተራመዱ መሄድ ጀመሩ ፡፡ እየሄዱ እያለም ሶቅራጥስ ወጣቱን ምን እንደሚፈልግ ዳድም ይጠይቀዋል፡፡ ወጣቱም የስኬት ምስጢርን እንድትነግረኝ ፈልጌ ነው ይለዋል፡፡ ባሕሩ መሀል እንደደረሱ ሶቅራጥስ ወጣቱን አንገቱን ይዞ አሰጠመው፡፡ ወጣቱም አየር ለማግኘት ይፈራገጥ ጀመር፡፡ ሶቅራጥስ ግን ሊለቀው አልቻለም፡፡ ወጣቱም ኧረ እባክህ ልቀቀኝ ልትገለኝ ነው እያለ ቢጮህም ሶቅራጥስ አለቀቀውም፡፡ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ሶቅራጥስ ወጣቱን ከውሃው አወጣውና ለምን ይፈራገጥ እንደነበርና እንዲለቀው የጠቀበትን ምክንያት ይጠይቀዋል፡፡ ወጣቱም አየር ፈልጌ ነዉ ይለዋል፡፡ሶቅራጥስም ወጣቱን “አየህ አየር እንደሚያስፈልግሀ ስታውቅ እንደዚህ ከተፈረገጥክ ስኬታማ መሆን ከፈለግህም መጀመሪያ ምን እንደምትፈልግ እወቅ” ብሎ መለሰለት ይባላል፡፡ ስለዚህም ወደ እንቅስቃሴና ትጋት የምንገባው ውስጣችን እንድናገኘዉ የሚፈልገዉን ነገር ማወቅ ስንችል ነው፡፡ ማንኛውም ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ሰው በመጀመሪያ ፍላጐቱን ማወቅ ግድ ይለዋል፡፡ ነገሩን ስናጠቃልለው ሰዎች ግብ የማያስቀምጡበት ዋነኛው ምክንያት ፍላጐታቸውን ማወቅ አለመቻላቸው ነው፡፡ ግብ ከማስከመጣችን በፊት ፍላጐታችንን ጠንቅቀን ማወቅ ታላቅ የቤት ሥራ ይሆናል፡፡ 2. የውስጥ መነሳሳት (Motivation) ግብ ስላስቀመጥን ብቻ ስኬታማ እንሆናለን ማለት አይደለም፡፡ ግባችንን ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት ያስፈልገናል፡፡ በመሆኑም ሁለተኛው የስኬት ቁልፍ ውስጣዊ መነሳሳትን መፍጠር ነው፡፡ ይህን ውስጣዊ መነሳሳታችንን ለማምጣት ደግሞ ያቀድነውን እቅድ በተለያዩና ሊታዩን በሚችሉ ቦታዎች ማስቀመጥ  ይመከራል፡፡ ያስቀመጥነው ግብ ሁልጊዜ ስናየው የበለጠ ለመስራት እንነሳሳለን፡፡ ሌላው ውስጣችንን ለማነሳሳት ልንጠቀምበት የምንችለው ነገር ግባችንን ካሳካን በኋላ ልናገኘው የምንችለውን ስሜት በማሰብ ነው፡፡ ግቤን ሳሳከ ምን አያለሁ፣ ምን እሰማለሁ፣ ምንአይነት ስሜት ይሰማኛል የሚሉትን ጥያቄዎች ሁል ጊዜ በማንሳት ውስጣዊ መነሳሳትን ልናመጣ እንችላለን፡፡ 3.   ፅናት (persistence)    ስኬት ጽናት ለሌላቸዉ ጀርበዋን የምትሰጥ ወይዘሮ ናት፡፡ከእያንዳንዱ ስኬታማ ሰዉ በስተጀርባ ጽናት ይኖራል፡፡ነገሮች ሁሉ አልጋ በአልጋ ሆነዉለት ስኬታማ የሆነ ማግኜት ይከብዳል፡፡  በምሳሌ ለማስረዳት ያህልም ሁለት ዋሽንት የሚነፉ ሰዎች ነበሩ ይባላል፡፡አንደኛዉ ሲነፋ ሁሌም ዝናብ ይዘንባል ፡፡ሌላኛዉ ሲነፋ ግን አይዘንብም፡፡ዋሽንት ሲነፋ ዝናብ በሚዘንብለት ሰዉ የሚያዩት ሁሉ ይገረሙበታል፡፡ ሁለቱም ግን ተመልካች አላቸዉ፡፡ከእለታት በአንድ ቀን ዋሽንት ሲነፋ ዝናብ የማይዘንብለትን የሚመለከቱት ሰዎች ሲነፋ የሚዘንብለትን የሚመለከቱትን ሰዎች ዋሽንት ሊያሰሙዋቸዉ ጋበዙዋቸዉ፡፡ተጋባዦችም ዋሽንቱን ከሰሙ በሁዋላ ለጋበዙዋቸዉ ሰዎች እነርሱም በተራቸዉ ዋሽንት ሲነፋ ዝናብ የሚዘንብለትን ሰዉ ያዩት ዘንድ ጋበዙዋቸዉ:: ተጋባዦች ሲያዩ ሰዉዬዉ ሲነፋ ከቆየ በሁዋላ ዝናብ ይዘንብ ጀመር::  በጣም ተገረሙ ::ዋሽንት የሚነፋዉንም ሰዉየ እርሱ ሲነፋ ለምን ዝናብ እንደሚዘንብ ይነግራቸዉ ዘንድ ጠየቁት::ሰዉዬዉም "አይ እኔ ስነፋ አይደለም ዝናብ የሚዘንበዉ ነገር ግን ዝናብ እስከሚዘንብ ነዉ የምነፋዉ"ብሎ መለሰላቸዉ ይባላል::አዎ እኛም ያቀድነዉ እስከሚዘንብልን ድረስ መጽናት ያስፈልገናል:: ይህ ካልሆነ ግን ስኬትን ማምጣት ከባድ ነዉ:: በመጨረሻም       “CHANGE YOUR WAY BUT NOT YOUR GOAL" ብዬ ላብቃ።               መልካም የስኬት ጊዜ!!! 📜Via unknown source Join us @assignment_supporter

የስኬት ቁልፎች (The key to success)- ክፍል አንድ ስኬት አንድ የታቀደ እቅድ(ግብ)በትክክል መፈፀም ማለት ነው፡፡ ከዚህ ዐረፍተ ነገረ መረዳት የምችለው ነገር ቢኖር ከስኬት በፊት ምንጊዜም የታቀደ ግብ ሊኖር እንደሚገባ  ነው፡፡ ስኬት ግብ ለሚያቀምጡ ብቻ የተሠጠች ነች ማለት ነው፡፡ ለዚህም ነው “ If you fail to plan, you are planning to fail’ የሚሉት ምሁራን፡፡ ከስኬት ቁልፎች መካከል አንዱ ግብ ማስቀመጥ(Goal setting) ሲሆን ሌሎች ደግሞ የዉስጥ መነሳሳት(Motivation) እና ጽናት (persistence) ናቸዉ:: 1.  ግብ ማስቀመጥ ( Goal setting) ማንኛውም ስኬታማ መሆን የሚፈልግ ሰው እቅድ ማቀድ እንዳለበት ከተስማማን እቅዱስ ምን ምን ማሟላት አለባቸው? የሚለውን ጥያቄ ማንሳቱ ጠቃሚ ነዉ፡፡  ማንኛውም ዓይነት እቅድ “SMART ” መሆን አለበት:: ትርጓሜውም እንደሚከተለው ይተነተናል፡፡ S- Specific ( ግልጽና የተወሠነ) M-Measurable (የሚለካ) A- Achievable (ሊሳካ የሚችል) R- Realistic (እውን ሊሆነ የሚችል) T- Time framed ( በጊዜ የተወሰነ) i).  specific ( ግልጽና የተወሠነ) እቅድ (ግብ) በግልፅ የሚታወቅ መሆን ይገባዋል፡፡ ግልጽነት የሚጎድለዉ እቅድ እንዴት እንደምናሳካዉ ለማወቅ ከባድ ነዉ::ብዙ ሰዎች ግባቸውን ሲጠየቁ “የተሻለ” የምትለዋን ቃል በማስቀደም ሌሎችን ፍላጎታቸውን ያስከትላሉ፡፡ የተሻለ ትምህርት፣ የተሻለ ቤት፣ የተሻለ ገቢ ፣የተሻለ የስልጣን ቦታ ወዘተ ይላሉ፡፡ ይህ አይነቱ ግብ ግልጽነትና ዉሱንነት ይጎድለዋል፡፡ ለስኬታማነትም ሊያበቃን አይችልም፡፡ እንደነዚህ አይነት ሰዎች ብዙ ጊዜያቸው የሚያጠፉት ከአንዱ አንዱ በመንከራተትና በመወዛገብ ነው፡ የተረጋጋ ህይወት ለእነርሱ ተረት ነው፡፡ የተሻለ ገቢ ለማግኜት የሚያቅድ ሰውና የ3000 ብር ደመወዘኛ የ3200 ብር ደመወዝ ያለው የስራ ማስታወቂያ ከወጣ ያለ ጥርጥር ስራውን ይቀይራል፡፡ ምክንያቱም እቅዱ የተሻለ ማግኜት ነውና፡፡ ለዚህም ነው እንዳንድ ሰዎች ከእድሜያቸው በላይ መስሪያ ቤት ሲቀያይሩ የሚኖሩት፡፡ በተመሳሳይ የተሻለ ትምህርት የሚፈልግና ዲግሪ ያለዉ ሰው በአጋጣሚ መንገድ ጠፍቶበት በዩኒቨርሲቲ በር ሲያለፍ የድህረ-ምረቃ ትምህርት ማስታወቂያ ቢያነብ ትምህርቱ ይጥቀመውም አይጥቀመውም ዘሎ ገብቶ ይመዘገባል፡፡ ተምሮ ሲወጣ ግን በህይወቱ ምንም ዋጋ ላይጨምር ይችላል፡፡ በአጠቃላይ ግብ በግልጽ ተወስኖ የተቀመጠ መሆን ይገባዋል፡፡ የተሻለ ገቢ በማለት ፈንታ በወር ማግኜት የሚፈልገውን የገንዘብ መጠን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡ የተሻለ ትምህርት በማለት ፈንታም ዲግሪ፣ ማስተርስወይም ፒ.ኤች. ዲ እና የመሣሰሉትን ቢያቀምጥ ይመረጣል፡፡ ii). Measurable (የሚለካ) ሌላው ግብ ስናስቅምጥ ማስተዋል የሚገባን ነገር ግባችን የሚለካ መሆን አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰዎችን የሚረዳ ድርጂት ለማቋቋም ያቀደ ሰው ምን ያህል ሰዎችን እንደሚረዳ በግልፅ ማስቀመጥ አለበት፡፡ ቤት ለመሰራት ያቀደም ሰው ቢሆን የቤቱን ስፋት አይነት እና የመሳሰሉትን በግልፅ  ማስቀመጥ አለበት፡፡ አለበለዚያ አንድ ሰው ብቻ የምታሰገባ ቤት ቢሰራም ቤት ቤት ነውና እቅዱን እዳሳሣካ ሊቆጥረው ይችላል፡፡ በመሆኑም ማንኛውም ግብ የሚያስቀምጥ ሰው ግቡ የሚለካ መሆን አለበት፡፡ iii). Achievable (ሊሳካ የሚችል) አሁንም ግብ ስናስቀምጥ ግባችን ሊሳካ የሚል መሆኑን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ይህን በምሳሌ ለማስረዳትም አንድ የ7ኛ ክፍል ተማሪ ዛሬ ላይ ሆኖ የዛሬ 10 ዓመት ፒ.ኤች.ዲ ዲግሪዉን እንደሚይዝ ቢያቅድ እቅዱ ሊሳካ የሚችል አይደለም፡፡ ምክንያቱም ስርዓተ-ትምህርቱ ከ7ኛ ክፍል ወደ ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ በ10 ዓመት ያጠናቅቅ ዘንድ አይፈቅድለትም፡፡ በኢትዮጵያ ስርዓተ ትምህርት መሠረት ከ7ኛ ክፍል ፒ.ኤች.ዲ. ዲግሪ  ለመያዝ ቢያንስ 14 ዓመታትን ይፈጃል፡፡ ስለሆነም ይህን እቅድ ያቀደ ሠው እቅዱን ሊያሳካ አይችልም፡፡ ስለዚህም ሁጊዜ ግብ ስናስቀምጥ ሊሳካ የሚችል መሆኑንና አለመሆኑን ማሠብ ይኖርብናል፡፡ iv). Realistic  (እውን ሊሆን የሚችል) አራተኛው ግብ ሊያካትተው የሚባው መስፈርት ደግሞ እውን ሊሆን የሚችል መሆኑን ነው፡፡ ይህ ቀጥታ ከተፈጥሮ ጋር የሚያያዝና ልንቀይራቸው የማንችላቸውን ነገሮች ማቀድ እንደሌለብን የሚያስገነዝብ ነው፡፡ “change the changeable, accept the unchangeable” እንዲሉ ምሁራን በተፈጥሮ እውን ሊሆን የማይችልን ነገር ማቀድ ድካሙ ነው ትርፉ፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው “የዛሬ ዓመት መልዓክ ለመሆን ቢያቅድ እቅዱ እቅድ መሆኑ ቀርቶ ቅዠት ነው የሚሆነው፡፡ ስለሆነም ግባችን በገሃዱ አለም እውን ሊሆን የሚች መሆን አለበት፡ v). Time framed ( በጊዜ የተወሰነ) የመጨረሻውና ግብ ስናስቀምጥ ማካተት ያለብን ነገር ግባችን በጊዜ-የተወሰነ መሆኑን ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህ ችግር ከሌሎች ማሟላት ከሚገቡን ነገሮች የበለጠ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡ “መኪና ሳልገዛማ አልሞትም” ሲል የምንሠማው ሰው መኪና መቼ እንደሚገዛ ግን አያውቀውም፡፡ የዛሬ 20 አመትም ይህንን ሲደግመው እናሠማለን፡፡ ግብ ስናስቀምጥ ምን ጊዜም በጊዜ የተወሰነ መሆን ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ ነገ እሠረዋለሁ እያልን እድሜያችንን መፍጀታችን ነዉ፡፡       📜Via unknown source Part 2 ይቀጥላል..... Join us @assignment_supporter

👨‍💻ለተማሪዎች👩‍💻 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ለተማሪዎች የሚጠቅሙ 4 የአንድሮይድ አፕሊኬሽኖች ልንገራቹ፡ ❇️ተማሪዎች፤ የሃይ ስኩል እና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደራራቢ አሳይመንቶች ሊሰጣችሁ ይችላል፡፡ ተደራራቢ የቤት ስራዎች፣የግሩፕ አሳይመንቶች፣ፕሮጀክቶች፣ ተደራራቢ ጥናቶች ተማሪዎች ላይ ጫና ሊያበዛ ይችላል፡፡ ይሄ ጫና ደሞ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል፡፡    ⛔️በትምህርት ወቅት ጫና እንዳይፈጠርባችሁ ዋናውና ቁልፍ መፍትሔ ለየአንዳንዱ ነገር ፕሮግራም ማዘጋጀት ነው፡፡ ⭕️ቀጥሎ የምነግራችሁ 4 አፕሊኬሽኖች ተማሪዎች በትምህርት ወቅት ጫና ሳይፈጠርባቸው ትምህርታቸውን ባግባቡ በመከታተል በትምህርታቸው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ የሚረዱ አፕሊኬሽኖች ናቸው፡፡ ዓለም ዓቀፍ እውቅናም የተሰጣቸው አፕልኬሽኖች ናቸው። 1️⃣ School Planner Application 🧲 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ ✅ ይህ አፕሊኬሽን የቤት ስራዎችን፣ የግሩፕና የግል አሳይመንቶችን፣ፕሮጀክቶችን፣የእያንዳንዱን ክላስ ሰዓትና ቀን…ማንኛውም ትምህርት ነክ አክቲቪቲዎቻችሁን ኦርጋናይዝ ያደርግላችኋል፡፡ ፕሮግራም ያወጣላችኋል። ✅ ይህ አፕሊኬሽን በየቀኑ በፕሮግራማችሁ መመሰረት በየቀኑ መስራት ያለባችሁን ለምሳሌ ጥናት ወይም የቤት ስራ፣የግሩፕ አሳይመንት፣ የላብራቶሪ ሙከራ ….ባጠቃላይ  ጠዋት ምን ማድረግ እነዳለባችሁ፡፡ ከሰዓት ምን መስራት እንዳለባችሁ ማታ ምን መፃፍ እንዳለባችሁ ያስታውሳችኋል…. ✅ የምታስረክቡት አሳይመንት ወይም ፕሮጀክት ካለባችሁ የምታስረኩብበት ቀን "በዚህ ቀን ነው፡፡ ቀኑ እየደረሰ ነው…" እያለ ያስታውሳችኋል፡፡ 2️⃣Brilliant 🧲 ▬▬▬▬▬ ❇️ ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በተለይ በሂሳብ፣ በሳይንስና በኮምፒውተር ሳይንስ ጥሩ ውጤት ለማምጣት በጣም የሚጠቅም አፕ ነው፡፡ ❇️ይህ አፕሊኬሽን እየሸመደዳችሁ እንዳታጠኑና በተለይ ረጃጅም ቃላት የሚበዙባቸው የትምህርት አይነቶችን ዘርዘር ያሉ ገለፃዎችን በመጠቀም ሳትሰለቹ  ትምህርቶቹን በቀላሉ እንድታጠኗቸውና እንዲገባችሁ ይረዳል ። 3️⃣Grammarly  🧲 ▬▬▬▬▬▬▬ ✅ ይህ አፕሊኬሽን ደሞ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ያሳድጋል፡፡ ✅ የተለያዩ ESSAY በእንግሊዘኛ ስትፅፉ  የግራመር ስህተታችሁን ያርማል፣ትክክለኛ ቃላት እንድትመርጡ ይረዳል፡፡ ረጃጅም አረፍተ ነገሮችን ስትፅፉ የሲንታክስ ስህተታችሁን ያርማል፡፡ ✅ በእንግሊዘኛ የመፃፍ ችሎታችሁን ቀስበቀስ ያሳድጋል፡፡ 4️⃣Mendeley  🧲 ▬▬▬▬▬▬ ✅ Research በምትሰሩበት ግዜ ለጥናታችሁ  የሚሆኑ የተለያዩ ሪሶርሶች እንዴት እንደምታገኙ ይረዳችሃል፡፡ ❇️ለጥናታችሁ ወይም ለሪሰርቻችሁ የሚጠቅሙ መፅሃፎችን፣ጥናታዊ ፅሁፎችን፣ ምክረ ሃሳቦችን እንዴት እንደምታዘጋጁ ያስተምራቸኋል፡፡ ❇️ለሪሰርቻችሁ የተጠቀማችሁባቸውን የተለያዩ የጥናታዊ ፁሁፎች ፃሃፊዎችን፣የመፅሐፍት ደራስያን ፣ምሁራንን ስማቸውን በመጥቀስ ጥናታችሁ ላይ በማካተት እንዴት ወይም ክሬዲት እንደምትሰጧቸው ያስተምራችኋል፡፡    🛑Share to Your Friends kindly 🛑                   ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬    ✅For more  Join us 👇👇👇 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬          ⬇️ Join and Share ⤴️👇       ╔═══════════╗       ❇️      @assignment_supporter     ❇️       ❇️      @assignment_supporter     ❇️       ╚═══════════╝ Inbox 👇 @positive_thinkerrr ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ @positive_thinkerrr ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬

🔗Mathematics formulas🔗 እንዳትሸወዱ አይጠቅመኝም ብላችሁ እንዳታልፉት !! Maths calculations ላይ ይጠቅማችኋል 1. (α+в)²= α²+2αв+в² 2. (α+в)²= (α-в)²+4αв 3. (α-в)²= α²-2αв+в² 4. (α-в)²= (α+в)²-4αв 5. α² + в²= (α+в)² - 2αв. 6. α² + в²= (α-в)² + 2αв. 7. α²-в² =(α + в)(α - в) 8. 2(α² + в²) = (α+ в)² + (α - в)² 9. 4αв = (α + в)² -(α-в)² 10. αв =1. (α + в + ¢)² = α² + в² + ¢² + 2(αв + в¢ + ¢α) 12. (α + в)³ = α³ + 3α²в + 3αв² + в³ 13. (α + в)³ = α³ + в³ + 3αв(α + в) 14. (α-в)³=α³-3α²в+3αв²-в³ 15. α³ + в³ = (α + в) (α² -αв + в²) 16. α³ + в³ = (α+ в)³ -3αв(α+ в) 17. α³ -в³ = (α -в) (α² + αв + в²) 18. α³ -в³ = (α-в)³ + 3αв(α-в) ѕιη0° =0 ѕιη30° = 1/2 ѕιη45° = 1/√2 ѕιη60° = √3/2 ѕιη90° = 1 ¢σѕ ιѕ σρρσѕιтє σƒ ѕιη тαη0° = 0 тαη30° = 1/√3 тαη45° = 1 тαη60° = √3 тαη90° = ∞ ¢σт ιѕ σρρσѕιтє σƒ тαη ѕє¢0° = 1 ѕє¢30° = 2/√3 ѕє¢45° = √2 ѕє¢60° = 2 ѕє¢90° = ∞ ¢σѕє¢ ιѕ σρρσѕιтє σƒ ѕє¢ 2ѕιηα¢σѕв=ѕιη(α+в)+ѕιη(α-в) 2¢σѕαѕιηв=ѕιη(α+в)-ѕιη(α-в) 2¢σѕα¢σѕв=¢σѕ(α+в)+¢σѕ(α-в) 2ѕιηαѕιηв=¢σѕ(α-в)-¢σѕ(α+в) ѕιη(α+в)=ѕιηα ¢σѕв+ ¢σѕα ѕιηв. » ¢σѕ(α+в)=¢σѕα ¢σѕв - ѕιηα ѕιηв. » ѕιη(α-в)=ѕιηα¢σѕв-¢σѕαѕιηв. » ¢σѕ(α-в)=¢σѕα¢σѕв+ѕιηαѕιηв. » тαη(α+в)= (тαηα + тαηв)/ (1−тαηαтαηв) » тαη(α−в)= (тαηα − тαηв) / (1+ тαηαтαηв) » ¢σт(α+в)= (¢σтα¢σтв −1) / (¢σтα + ¢σтв) » ¢σт(α−в)= (¢σтα¢σтв + 1) / (¢σтв− ¢σтα) » ѕιη(α+в)=ѕιηα ¢σѕв+ ¢σѕα ѕιηв. » ¢σѕ(α+в)=¢σѕα ¢σѕв +ѕιηα ѕιηв. » ѕιη(α-в)=ѕιηα¢σѕв-¢σѕαѕιηв. » ¢σѕ(α-в)=¢σѕα¢σѕв+ѕιηαѕιηв. » тαη(α+в)= (тαηα + тαηв)/ (1−тαηαтαηв) » тαη(α−в)= (тαηα − тαηв) / (1+ тαηαтαηв) » ¢σт(α+в)= (¢σтα¢σтв −1) / (¢σтα + ¢σтв) » ¢σт(α−в)= (¢σтα¢σтв + 1) / (¢σтв− ¢σтα) α/ѕιηα = в/ѕιηв = ¢/ѕιη¢ = 2я » α = в ¢σѕ¢ + ¢ ¢σѕв » в = α ¢σѕ¢ + ¢ ¢σѕα » ¢ = α ¢σѕв + в ¢σѕα » ¢σѕα = (в² + ¢²− α²) / 2в¢ » ¢σѕв = (¢² + α²− в²) / 2¢α » ¢σѕ¢ = (α² + в²− ¢²) / 2¢α » Δ = αв¢/4я » ѕιηΘ = 0 тнєη,Θ = ηΠ » ѕιηΘ = 1 тнєη,Θ = (4η + 1)Π/2 » ѕιηΘ =−1 тнєη,Θ = (4η− 1)Π/2 » ѕιηΘ = ѕιηα тнєη,Θ = ηΠ (−1)^ηα 1. ѕιη2α = 2ѕιηα¢σѕα 2. ¢σѕ2α = ¢σѕ²α − ѕιη²α 3. ¢σѕ2α = 2¢σѕ²α − 1 4. ¢σѕ2α = 1 − ѕιη²α 5. 2ѕιη²α = 1 − ¢σѕ2α 6. 1 + ѕιη2α = (ѕιηα + ¢σѕα)² 7. 1 − ѕιη2α = (ѕιηα − ¢σѕα)² 8. тαη2α = 2тαηα / (1 − тαη²α) 9. ѕιη2α = 2тαηα / (1 + тαη²α) 10. ¢σѕ2α = (1 − тαη²α) / (1 + тαη²α) 11. 4ѕιη³α = 3ѕιηα − ѕιη3α 12. 4¢σѕ³α = 3¢σѕα + ¢σѕ3α » ѕιη²Θ+¢σѕ²Θ=1 » ѕє¢²Θ-тαη²Θ=1 » ¢σѕє¢²Θ-¢σт²Θ=1 » ѕιηΘ=1/¢σѕє¢Θ » ¢σѕє¢Θ=1/ѕιηΘ » ¢σѕΘ=1/ѕє¢Θ » ѕє¢Θ=1/¢σѕΘ » тαηΘ=1/¢σтΘ » ¢σтΘ=1/тαηΘ » тαηΘ=ѕιηΘ/¢σѕΘ             ═══◉❖◉════        🦁• @assignment_supporter•🦁        🦁• @assignment_supporter•🦁    ▬▬▬▬▬ 📌sʜᴀʀᴇ📌▬▬▬▬

✳️ Freshman course ላይ Assignment እንዴት እንሰራለን ? ውድ ቤተሰቦች የብዙወቻችሁ ጥያቄ ነው .....ዛሬ በ @positive_thinkerrr ይመለሳል ። Highschool ላይ  አሳይመንት ሰርታችሁ ሊሆን ይችላል  በ ልሙጥ ወረቀት or በ line paper ጥፋችሁ ከዛ በ ስቴፕራል አስዛችሁ ምናምን🙈 ፤ Campus ላይ ይችን እንዳትሞክሯት  ለምሳሌ ለ psychology course ልክ እንደዚህ አድርጋችሁ ሰርታችሁ ብታስረክቡ  ይህ Departmentቱን መናቅ ነው ተብላችሁ  የተማሪዎች ህብረት ልትቀርቡ ትችላላችሁ😁   ስቀልድ ነው ...መምህራኖች ወይ አይቀበሉአችሁም ወይ ትልቅ ማርክ ይቀንሱባችኅል Campus ላይ ደግሞ አይደለም አንድ ሶስት  ማርክ ቀርቶ 0.5 ምንያህል ትልቅ value እንዳላት ምታውቁት Grade ስታዩ ነው። ስለዚ Assignment አሰራር የ ራሱ የሆነ Style አለው። ከምስሉ ላይ እንደምታዩት Page cover አስጥፋችሁ ማስጠረዝ አለባችሁ። ሙሉው የምትጥፉበት paper ልሙጥ ወረቀት( A4 paper )ቢሆን ይመረጣል። ✳️ የ freshman ኮርሶችን assignment በ ሶስት ከፍለን እንያቸው 1⃣ የ case study assignments እነዚህ Assignments የሚሰጡን የ Calculation ትምህርት ባልሆኑት እንደ Anthropology እና Civics courseኦች ላይ ነው።ዓላማቸውም አንድ Title ይሰጠንና በዛ Title ተንተርሰን  ከ 7 እስ 10 page ያላነሰ የተለያዩ subtitleሎችን አካተን ሙሉ ገለጣ እንድንጽፍ ነው። ከዚህ ላይ ማተኮር ያለብን ነገር በምንሰራው Assignment ውስጥ እነዚህ ነገሮችን በቅደም ተከተል ማካተት ወሳኝ ነገር ነው። 📚1Table contents 📚2 introduction 📚3 main part 📚4 conclusion 📚5 reference አንዳንዴም እንደ ተሰጣችሁ Assignment instruction  Acronym ምናምን እንድትጥፉ ይደረጋል  ከላይ ያሉትን በ ዝርዝር ና በምሳሌ እንያቸው ተከተሉኝ.... 📍1 Table contents ይህ part assignment አችሁ ምንምን እንዳካተተ የተካተቱ contentoch የት page እንደሚገኙ የምንገልጥበት ክፍል ነው። ከምስሉ ላይ እንደምታዩት....😊 📍2 Introduction ይህ ክፍል ከስሙ እንደምንረዳው  የተሰጠን Title ምን እንደሚመስል በጨረፍታ ገረፍ ገረፍ እያደረግን የምናስተዋውቅበት  ነው። ምሳሌ የተሰጠን Title MANUFACTURING INDUSTRY IN ETHIOPIA  ቢሆን  Introduction ላይ Manufacturing industry በ Ethiopia ምን ይመስል ነበረ ከ past አንጻር  ፤አሁን ላይስ ስላለው ሁኔታ ....Ethiopian ለ  Manufacturing industry ምናይነት view አላቸው....እና መሰሎችን ገለጻ  መስጠት ነው። 📍3 main part ይህ ዋናው ክፋል ሲሆን Table contents ላይ ለተሰጠን ርዕስ ያስቀመጥናቸውን Subtitles እንዲሁም በነሱ ስራ ያሉ ሌላ titlochn በስፋት እየዘረዘርን  ሙሉ ማብራሪያ  የምንሰጥበት ክፍል ነው። 📍4 conclusion ይሄ ደግሞ main part ላይ  ለተሰጠን ርዕስ ያስቀመጥናቸውን Subtitles እንዲሁም በነሱ ስራ ያሉ ሌላ titlochn  በሙሉ ዘርዝረን ገለጻ የሰጠናቸውን points ፤  ያ የተንዛዛውን main part ( ቢያንስ  7-10  page ይደርሳል) እሱን ሁሉን points በሚያካትት መልኩ ከ አንድ page ባልበለጠ ወረቀት አሳጥረን መጻፍ ነው። ግን ይሄ ብቻ አደለም አንዳንዴም በ titlu ዙሪያ  የናንተን ሀሳቦች እንደ መደምደሚያ መጠቀም ትችላላችሁ ። 📍5 reference መቸም በተሰጠን ርዕስ ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ማንፈነቅለው ድንጋይ የለም  Google የለ (ግን Google ባይኖር ምን ይውጠን ነበር😘) ፤መጽሐፍት የሉ ሁሎችን  sources እንጎረጉራለን  ያገኘነውን መረጃም main part ላይ አስፍረናል ። ነገር ግን መምህራን ይሄን መረጃ የት አገኛችሁት ቢሉአችሁ መልስ መስጠት መቻል አለባችሁ ። ስለዚ ከዚ ከዚ አግንቻለሁ ለማለት መጨረሻ page ላይ Reference ብላችሁ sources ትዘረዝራላችሁ። Google ላይ መረጃ ስታገኙ ግን አደራ Reference ላይ Google ብላችሁ እንዳትጽፉ ነውር ነው።    ያገኛችሁበትን website link ነው ማስቀመጥ ያለባችሁ ።  ሞጅሉ ላይም ገልብጣችሁ Reference ላይ ሞጅል እንዳትሉ  modulu  ሲጀመረ የተዘጋጀው ከየት ነው? ዋናው Source  ያስፈልጋል። መጽሐፍትን እንደ Reference ከተጠቀማችሁ ደግሞ ApA format ተከትላችሁ Reference መጻፍ አለባችሁ Apa format ምንድን ነው? የ reference አጻጻፍ style ነው ምስሉን ተመልከቱ። Join and share endayresa🙏 ╔════════════╗ 📚JOIN: @assignment_supporter 📚JOIN: @assignment_supporter ╚════════════╝