Assignment supporters
رفتن به کانال در Telegram
ለ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው የማንኛውንም የትምህርት አይነት በ የትኛውም የክፍል ደረጃ የተሰጣችሁን assignment ከ አንድ ቀን ባነሰ ግዜ ውስጥ በ ከፍተኛ ጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሰራት ከፈለጉ ያናግሩን👇👇 @positive_thinkerrr ወይም 0994409904 ይደውሉ።
نمایش بیشتر362
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
እስካሁን የምዝገባ ጥሪ ያወጡ ዩኒቨርስቲዎች ‼️
የዩኒቨርስቲ ጥሪዎችን በቅድመ ተከተል አስቀምጠናል።
⚡️ዛሬ ህዳር 18/2016 ነው
✔️Kebri-dahri University
➩ህዳር 13 & 14
✔️Bulehora University
➩ህዳር 15 & 16
✔️Wollegga University
➩ ህዳር 17 & 18
✔️Raya University
➩ህዳር 17 & 18
✔️Kotebe University
➩ ህዳር 20 & 21
✔️Wolkite University
➩ ህዳር 20 & 21
✔️Gambela University
➩ህዳር 21 & 22
✔️Aastu( A.A) University
➩ ህዳር 23
✔️Dirredawa University
➩ ህዳር 23, 24 & 25
✔️Worabe University
➩ ህዳር 24 & 25
✔️Odabultum University
➩ህዳር 24 & 25
✔️Astu(Adam University
➩ ህዳር 24-25
✔️Borana University
➩ ህዳር 27-28
✔️Bonga University
➩ህዳር 27 & 28
✔️Aksum University
➩ ህዳር 27 & 28
✔️Dilla University
➩ህዳር 28 & 29
✔️Mekelle University
➩ ህዳር 28, 29 & 30
✔️Arsi University
➩ ተህሳስ 4 & 5
✔️Wachamo University
➩ተህሳስ 5 & 6
✔️Haramaya University
➩ተህሳስ 5, 6 & 7
✔️JIMMAA UNIVERSITY
➩ ታህሳስ 01 እና 02
Join at and share
👇👇👇👇👇👇
@assignment_supporter
@assignment_supporter
https://t.me/assignment_supporter
📌 ወደ ካምፓስ ስንሔድ ምን ምን ነገሮችን ይዘን መሔድ አለብን❓
👉 ከበሶ እስከ ዳቦቆሎ
👉 ከለውዝ ቅቤ እስከ ማርማራታ
👉 ከሻንጣ እስከ ፒኪኒ
ሰላም ውዶቼ እንደምን አላችሁ ❓
📚 እስቲ ዛሬ ተማሪዎች ወደ ካንፓስ ሲገቡ መያዝ ያለባቸው ነገሮች እንመልከት ፦
📌 በምግብ ዘርፍ ፦
📚 እናትህ በር አንኳኩታ ከእንቅልፍ ቀስቅሳ ልጄ ቁርስ ደርሷል ብላ መጥራት ወፍ በቃ ቀርቷል ። አሁን ጠዋት 1:30 ተነስተህ ለሻይ እና ዳቦ መሰለፍ አለብህ በቀን 3 ካልተሰለፍክ ዶርም ድረስ በሰሃን አይቀርብልህም መቼስ ደሞም እንደማሚ WOW የሚያስብል ግሪስ እንዳይመስል.... ናላ የሚያዞር ፈውስ ነው ሚቀርብልህ... ኮብል ከምስር ጋር ፥ ሽሮ ያለ ዘይት ፤ ስጋ ወጥ ያለ ስጋ ለመብላት ነው ተሰልፈህ የምትውለው ። አስበው በዛ ላይ ችከላ አለ ይሞረሙረሃል ከዛ እናትህ ትናፍቅሃለች ታዲያ በበሶ ካልሆነ በምንም አታገኛትም ። በሶ ሆድ ብቻ መሙላት አይደለም ናፍቆት ማረሳሻም ነች ። ብትወድም ባትወድም በሶ ያዝ ፤ ኩኪስ ፤ ዳቦቆሎ ፤ የመሳሰሉ በባህላቹ ያሉ ደረቅ የስንቅ ምግቦች በደንብ ያዙ ታመሰግነኛለህ ።
💡 በሶ
💬 በሶ ብትወድም ባትወድም ጥቂትም ቢሆን ያዝ መበጥበጡ ራሱ LIFE አለው ፤ ለአንድ ሴሚስተር ከ2-5 ኪሎ በቂ ነው ብዬ አስባለሁ ፍሬሽ ስትሆኑ ግን የካፌ ምግብ ስለማይስማማቹ እስከ 6 አርጋቹሁ ያዙ ። በሶ ስትይዙ ከቻላቹሁ በማሸጊያ ፌስታል አሽጋችሁ ብትይዙ ለመያዝም ያመቻቹሃል ለሙዱም አሪፍ ነው ።
💡 ኩኩሲ ፡
📚እኔ ኩኩሲ በጣም ነው የምወደው ስለዚህ በኩንታል ልይዝ አስቢያለሁ እና በሶ ለማትወዱ አሪፍ መፍትኤ ነው ከ2-3 ኪሎ ለሴሚስተር ብትይዙ በጣም አሪፍ ነው ። ኩኩሲ ነፍስ የሆነ ነገር ነው ኩኩሲ በበሶ አስባቹሁታል ። ግን እመኑኝ ካልቆጠባቹሁ የዶርም ጀመኣ 3 ቀን አያቆያትም እና ስንቅ መሆኑን አስባቹሁ ቢያንስ ሁለት ወር ማስቀመጥ ይኖርባቹሃል ። አገኘው ብላቹሁ ጨርግዳቹ ጨርግዳቹ በሳምንት ጨርሳቹሁ ጨላ ሲነጥፍ በኃላ ጉድ እንዳትሆኑ እንደውም ገንዘብ እስኪጠር ኩኩሷን አትንኳት ከነካቹሁም በቁጠባ ።
💡 ዳቦቆሎ ፦
💬 ይቺም በጣም አሪፍ ነገር ናት እስከ 2 ኪሎ ብትይዙ አትጎዱም ። ስትተክዙ ማታከዣ ስትቸክሉ ማቻከያ ትሆናለች ። ዳቦ ቆሎም መቆጠብ አለበት እና ለቁጠባ አሪፉ መንገድ ማሸግ ነው ። 2 ኪሎው ዳቦቆሎ 3 እሽግ ፌስታል ቢወጣው አንድ እሽግ በወር የሚል ዕቅድ ይዛቹሁ መቆጠብ ትችላላቹሁ ።
💡 የለውዝ ቅቤ ፤ ማር ፤ ማርማራታ ፤ የመሳሰሉ የሚቀቡ ምግቦችም ፦
💬 ማር ካልሆነ አብዛኞቹ በከተማ ስለምታገኙ እዛው የዳቦ ዋጋ አጣርታችሁ የማይጎዳ ከሆነ ሸመትመት ማረግ ትችላላችሁ ነገር ግን የማር ሀገር የምትኖሩ ከሆነ በደንብ ያዙ ትፈወሳላችሁ እመኑኝ በተረፈ በቃ (ማር ሀገራቹሁ ምርጥዬ ከሆነ ይዛቹሁ ኑ ሌሎቹን ከመጣቹሁ ወዲህ በተመደባችሁበት መግዛት ትችላላቹሁ) ደሞ አንዳንድ ግቢ ፍራፍሬ በጣም ርካሽ ነው በተለይ ወደ ደቡብ ታዲያ ደቡቦች ለምግብ እንዳታስቡ ያረጋቹሃል ። ያው የጠገበ ስለትምህርቱ ስለማያስብ አትጎዱ እንጂ ሰርክ ሀሳባቹሁ ፈውስ መሆን የለበትም ተመርቋቹሁ ስራ ስትይዙ ታማርጣለቹሁ ለግዜው ያገኛቹሁትን ጠርጋቹሁ በደንብ ቸክላቹሁ በአሪፍ ግሬድ መመረቅ አስቡ ። ደሞ ክረምት ነው በቆሎም አለ ትግጣላችሁ .....
💬 ምግብ እንደሙዳችሁ የሚመቻችሁን እና በየሀገራችሁ ለስንቅ የሚዘጋጁ ነገሮችን ያዙ ( ግቢ መግባት የሚችሉትን ) ሽንብራም ፤ በሶም ፤ ማርም ብቻ ይሆናል ያላችሁትን እና የሚሞዳችሁን ፈውስ ያዙ ።
📌 በቁሳቁስ ዘርፍ ፦
💡 ሻንጣ ፦
📚 ብዙዎች ቀለል ብለው መግባት ይሞዳቸዋል ፥ አንዳንዶች ደሞ እንደ ሰርግ ካልታጀብን ይላሉ ብዙዎቻችሁ መረዳት ያለባችሁ ነገር ግቢ ስትገቡ የምትገቡ እናንተ እንደሞዳችሁ እና እንደአቅማችሁ ፥ እንደ አስተሳሰባችሁ እና ፍላጎቶቻችሁ እንጂ ስለ ሰዎች አትጨናነቁ እነሱ የራሳችሁ ቢዝነስ ይወርኩ ። እናንተ በራሳችሁ የሚሞዳችሁን እና የሚያስፈልጋችሁ ነገር አድርጉ ።
💬 ጀለስ 4 ግብዳ ሻንጣ ተሸክሞ ግቢ ስለሚቆሰው እኔም የሚል ፎክክር ትታችሁ ምንድነው ሚያስፈልገኝ ❓አቅሜ የቱ ያክል ነው ❓በሉ ቤተሰብ አታስቸግሩ ከሌሎች እኩል ለመሆን በሚል የFamily ኑሮ አታናጉ ። እናም እንደሙዳቹሁ ተራመዱ ።
📚 ሻንጣ (እንደኔ) አንድ በጀርባ የሚነገት Bag ብትገዙ ( ከሌላችሁ ካላችሁ ግልግል ) እና ሌላ ትንሽዬ (የምትጎተተዋ) ብርድልብስ እና የመሳሰሉ ትልልቅ ነገሮች የምትይዙበት ሻንጣ ቢኖራችሁ አሪፍ ነው ።
💬 ለበዓል እና ለዕረፍት ወደ ቤተሰብ ስትመጡ ለቀናት የሚሆን ልብሳችሁን በጀርባ ሚነገተው Bag ትይዛላችሁ የተቀሩትን ደሞ በቀረችው ቦርሳ ግቢ ታስቀምጣላችሁ ( ሙሉ ዕቃ በየግዜው ስለማታንኳትቱ ማለት ነው) ነገር ግን እንደ ግቢው ርቀት ፥ እንደ እናንተ የሸመታ ብዛት ፥ እንደ ያዛችሁተ ዕቃ ነው የሚወሰነው ስለዚህ በፍላጎታችሁ መሰረት ብትይዙ መልካም ነው ።
🎗በተረፈ እንደኔ ከቻላችሁ ለክላስ የምትሆን አነስ ያለች 250 -300 ብር የምትገዛውን Bag እዛው ግቢ ብትገዙ አሪፍ ነው ( በፊት ካላችሁም ስትመጡ ዕቃ ነገር ያዙባት እና በዛው ትማሩባታላችሁ ። )
📌 የልብስ ሸመታ ፦
📚 ይሄም የሚወሰነው እንደደረሳችሁ ግቢ የአየር ንብረት እና የእናንተ ሙድ ነው ፤ መቼስ ሰመራ ደርሶህ መርጦ ሳትይዝ አትሄድም ፤ መቼስ ደብረብርሃን ደርሶህ ከጋቢ ማይተናነስ ጃኬት መያዝ አትረሳም ፤ ብቻ እንደግቢው እና ሙዳችሁ እና አቅማችሁ ይወሰናል ፤ ፋሽን ተከታይ ናችሁ ❓ዘናጭ ናችሁ❓ ደሃ ናችሁ
❓ቀለል ያለ አለባበስ ይመቻቹሃል ወይስ ቂቅ ካካለችሁ ይጨንቃቹሃል ብቻ ሙዳችሁ ምንድነው ብላችሁ " እንደ ሙዴ " ብሎ መቀወጥ ነው ። ምን ያክል ልብስ ልያዝ ምናምን ለምትሉ (በግሌ)
💡 ለወንዶች ፦
📚 3-5 ሱሪ እና 1ቱታ ፤ 1 ቁንጣ ፤ 2-3 ቲሸርት ፤ 2-3 ሸሚዝ ፤ 1-2 ጃኬት ፤ 6-8 ካልሲ ፤ 3-5 ፓንት ፤ 2-3 ሽፍን ጫማ + 1 ነጠላ ጫማ ፤ 1-2 ቀበቶ ፤ የረሳሁት ነገር ካለ እጨምራለሁ ።
💡ለሴቶች ፦
📚 ሴቶች ግቢ ሲገቡ በጣም ግብዳ ሻንጣ ሲሸክፉ ሁሌ እመለከታለሁ ብዙ ግዜ በምንድነው የሚሞሉት ብዬ ጠይቄ መልሱ አላገኘሁም ። ለማንኛውም ሴቶችዬ የእናንተ አለባበስ ወዲ በሉት ወዲ ለማለት ትንሽ ይከብዳል ። ብቻ ከታይት እስከ ጉርድ እንዳሻችሁ እና እንደፍላጎቶቻችሁ ሸምቱ (ሂጃብ እና ነጠላውም እንዳይረሳ እህትአለም) እንደምክር Body ነገር በከትከት አርጋችሁ ያዙ እኔ ነኝ ያልኳቹሁ ታተርፋላችሁ ።በተረፈ በንፅህና ስለማትታሙ ካልሲ እና ፓንት በርከት አርጎ የመያዝ ግዴታ የለባችሁ (ጭብጨባ ለሴቶች )
N.B: PC ያላችሁ ይዛችሁ ባትገቡ ይመረጣል ። ሁሉም ተማሪ አዲስ ስለሆነ ማን ምን አይነት ፀባይ እንዳለው አታቁም so 1st semester ያለ PC ብትጀምሩ የተሻለ ነው።።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
👉የትምህርት ሕይወታችሁ ከእኛ ጋር ብሩህ ነወ።👈
Join at and share🙏🙏
👇👇👇
@assignment_supporter
@assignment_supporter
https://t.me/assignment_supporter
Question or Comment
👇👇👇
@positive_thinkerrr
#HawassaUniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት እና ለ2015 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም‼️
#ቲክቫህ_ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራርን ጠይቆ ተከታዩን ዘገባ አጋርቷል።
አሁን ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ገዢው ፓርቲ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝና ስልጠናው እስከ ህዳር 30/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ኃላፊው ገልፀዋል።
በመሆኑም በታህሳስ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል ነው ኃላፊው የገለፁት።
Note:
ከላይ በምስሉ የሚታየው መልዕክት ለነባር መደበኛ ፕሮግራም የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የተላለፈ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።
በነሐሴ 2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ ገብተው የነበሩ የ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች፥ ወደ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት መዘዋወራቸውን ተከትሎ
የተላለፈ የምዘገባ ጊዜ መልዕክት መሆኑን ገልፀዋል።
[ዘገባው የቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ነው]
ለጥቆማ 👉@ positive_thinkerrr
➡️@ assignment_supporter
Repost from ATC NEWS
#HawassaUniversity
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት እና ለ2015 ዓ.ም ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም‼️
#ቲክቫህ_ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ዙሪያ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራርን ጠይቆ ተከታዩን ዘገባ አጋርቷል።
አሁን ላይ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሀገሪቱ ገዢው ፓርቲ ስልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝና ስልጠናው እስከ ህዳር 30/2016 ዓ.ም እንደሚቆይ ኃላፊው ገልፀዋል።
በመሆኑም በታህሳስ የመጀመሪያ ሁለት ሳምንታት ውስጥ ጥሪ ሊደረግ እንደሚችል ነው ኃላፊው የገለፁት።
Note:
ከላይ በምስሉ የሚታየው መልዕክት ለነባር መደበኛ ፕሮግራም የመጀመርያ ዲግሪ ተማሪዎች የተላለፈ መሆኑን ኃላፊው አብራርተዋል።
በነሐሴ 2015 ዓ.ም ወደ ተቋሙ ገብተው የነበሩ የ1ኛ፣ 2ኛ እና 3ኛ ዓመት ተማሪዎች፥ ወደ 2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ዓመት መዘዋወራቸውን ተከትሎ
የተላለፈ የምዘገባ ጊዜ መልዕክት መሆኑን ገልፀዋል።
[ዘገባው የቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ነው]
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news
📢ስንቶቻችሁ ዝግጁ ናችሁ❓
📚 ስለምትይዙት ሻንጣ ሳይሆን ጫናዎችን ለመጋፈጥ በ ስነ ልቦና ምን ያክል ዝግጁ ናችሁ❓
🙄 ለ አንድ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ ከ አሁን በፊት ከሚሰጠው መደበኛ ጊዜ ማነሱ የማይቀር ነው። በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ 2 unit ልትጨርስ ትችላላችሁ። ፍሬሽ ናችሁ ብለው አስተያየት ካላደረጉላችሁ☹️::
አሳይመንት እና ፈተና ሊደራረብባችሁ ይችላል። ይህ ነገር የሚሆነው ለትንሽ ጊዜ ስለሆነ ወደ ፊት ሊመጣ ያለውን ተስፋ እያደረጋችሁ ፡ ለእያንዳንዱ እንቅስቃሴዎችሁ ዕቅድ እና ፕሮግራም አውጥታችሁ በፅናት እና በብቃት እንደምታልፋት እርግጠኛ ነኝ። ደግሞ ለአንድ ሴሚስተር በግ ተራ እና over መውጣት ይለፋችሁ🤨።
😂 ሀይስኩል እና መሰናዶ ላይ ፍትፍት አድርገው ፡ ብትንትን አድርገው ሲያስተምሯችሁ የነበሩ ወርቅዬ መምህራኖቻችሁን ግቢ ስትገቡ አታገኛቸውም። በቃ በአጭሩ የግቢ መምህራኖች እንደምትፈልጉት አድርገው ላያስተምሯችሁ ይችላሉ። ስለዚህ ጎበዝ senior ተማሪዎችን እና Google ን እንዳትፋቷቸው።
🙏 አደራ አደራ አደራ የምላችሁ ነገር ቢኖር ፡ ብዙ ኪሎሜትሮችን አቋርጣችሁ የምትሔዱት ለመማር ፡ የሆነ ነገር ለማግኘት ነው። ስለዚህ፡
የመጀመሪያ አመት ላይ ውጤት ስሩ። አሁንም አደራ የምላችሁ ነገር የመጀመሪያ አመት ላይ ትኩረታችሁን ወደ ትምህርት አድርጉ እና ውጤት ስሩ።
📍 ውጤታችሁ በየ ሴሚስተሩ በምትወስዱት credit hours መሰረት እየተደመረ ነው cumulative የሚሰራው። ስለዚህ፡
🎈የመጀመሪያ አመት ላይ ውጤት ከሰራችሁ ፡ በሚቀጥሉት አመታት ውጤታችሁ ዝቅ ቢል እንኳን ያን ህክል በጣም አይወርድም።
🎈የመጀመሪያ አመት ውጤት ካልሰራችሁ ግን ፡ በቀጣዮቹ አመታት አሪፍ ውጤት ብትሰሩ ራሱ በለፋችሁበት እና በሰራችሁ ልክ አይሆንም ውጤቱ።
📚 የመጀመሪያ አመት ውጤት ብዙ ገፀ በረከት አለው።
👉 ወደምትፈልጉት ዲፓርትመንት ትገባላችሁ።
👉 የሚቀጥሉትን አመታት በአንፃራዊነት ፈታ ብላችሁ ትማራላችሁ።
👉አትጫሩም😜። ሲጀመር ግቢ ላይ ትንሽዬ ካነበባችሁ መጫር አይታሰብም።
👉 ደግሞ ውጤት ሰራን ብላችሁ፡ እንዳትደነፋ እሺ። Be calm!
👉 የሀገሪቱ የትምህርት ስርአት ነው ውጤት ስሩ ብዬ እንዲጨቀጭቃችሁ ያደረገኝ። በምትገቡበት ዲፓርትመንት ዘላቂ የሆነ ዕውቀት እንዲኖራችሁ አድርጋችሁ አንብቡ። ለ interview ይጠቅማችሗል። አትሸምድዱ Google ን ተጠቀሙ።
ስለ ግቢ ብዙ ነገር ማለት ይቻላል እሱንም live ገብታችሁ ልትኮመኩሙት ነው😎......
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @assignment_supporter
📢 Department tip
Management ማኔጅመንት !
👨🏫 ማኔጅመንት በ faculty of Business and Economics ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአዲሱ ስርአተ ትምህርት ፍሬሽማን ኮርስን ጨምሮ የ 4 አመት ትምህርት ነው።
👩🏫 ማኔንጅመንት ስትገቡ የምትማሯቸው ትምህርቶች mostly business ነክ around (60%) , Decision making ( 25%) እና ሌሎችም። ስለዚህ ወደ business አለም መግባት የሚፈልግ አንባቢ ተማሪ ይወጣዋል።
👩💼 ማኔጅመንት ስትማሩ የምታውቋቸው መሰረታዊ ነገሮች ፡
📌 ከዚህ በፊት አክብደን ያየነውን የቢዝነሱን አለም በቀላሉ መረዳት እንችላለን።
📌 የአንድ ድርጅት manager ስንሆን ወይም ደግሞ የራሳችንን ድርጅት ስናስተዳድር ፡
👉 ድርጅቱን እንዴት በአግባቡ መምራት እንደምንችል ፡
👉 ከ ደንበኞች ፍላጎት እና ጥያቄ ጋር መጣጣም የሚችል አገልግሎት እንዴት መስጠት እንደምንችል ፡
👉 የምንመራውን ድርጅት እንዴት ትርፋማ ማድረግ እንደምንችል ፡
👉 ሰራተኞቹን እንዴት በአግባቡ መምራት እንደምንችል
👨🎓👩🎓 በ ማኔጅመንት የተመረቀ ሰው የት የት ቦታ ላይ መስራት ይችላል⁉️
➡️ በመንግስት ተቀጥራችሁ መስራት ከፈለጋችሁ በሁሉም የ Natural and Social Science ዘርፍ ከፍተኛ የስራ ዕድል አለው። ለምሳሌ ፡
👩💼 ባንክ 👨💻 አየር መንገድ
👨💼 ጉምሩክ 👩💻ሲቪል ሰርቪስ
➡️ ከመንግስት ድርጅቶች ውጭ ተቀጥራችሁ መስራት ብትፈልጉ
🔺 NGO- USAID, Save The Children.
🔺 Hotel Manager
🔺 Financial analyst
🔺 Business analyst
🔺 Financial director ወዘተ መሆን ትችላላችሁ።
➡️ በግላችሁ መንቀሳቀስ የሚያስችል capital ካላችሁ ደግሞ የትኛው business የት ቦታ ላይ apply እንደሚደረግ ተግባራዊ ዕውነታውን(pragmatism) ስለምትማሩ በቀላሉ ትርፋማ መሆን የሚያስችል የራሳችሁን ድርጅት ማንቀሳቀስ ትችላላችሁ።
🏣 ስለ ገቢው
😋 በሀገራች ካሉ የመንግስት እና የግል ሰራተኞች መካከል ማኔጀሮች ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ካላቸው ተርታ የሚመደቡ ናቸው።
👨💼የትምህርቱ ክብደት/ቀላልነት
በ ማኔጅመንት የትምህርት ዘርፍ ውስጥ የሚሰጡ አብዛሀኞቹ ኮርሶች ከ calculation ነፃ የሆኑ theory ስለሆኑ ፡ ማንበብ ብቻ ነው የሚጠይቁት።
" No one knows the secret of decision making without management"
© Posh tube !
━━━━━━━━━━━━━━━━━
📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @assignment_supporter
http://t.me/assignment_supporter
🎁ልዩ ምክር❤️🔥
┄┄┄┄┉✽»🌹 ✿ 🌹»✽┉┉┄┄┄
ግመልን ስትጠይቅ ቀበሮነትህን አትርሳ
ግመሉ ወንዙን እንደተሻገረ ቀበሮውም ለመሻገር መጣና ስለወንዙ ጥልቀት ለማወቅ ከወንዙ በወድያኛው ዳር ያለውን ግመል ጠየቀው። ግመሉም ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ እንደሆነ ነገረው።
ቀበሮውም ጉልበት ድረስ ከሆነማ አያሰምጠኝም በማለት ለመሻገር ወደ ወንዙ ገባ። በሚያሳዝን ሁኔታ ወንዙ
ያሰምጠው ጀመረ። ይሄኔ ቀበሮው ግመሉ እንደሸወደው ተረዳና እንደምንም ተፍጨርጭሮ ወደ ነበረበት ተመለሰ፤ ራሱንም ከሞት አተረፈ።
ይሄኔ በንዴት ጮክ ብሎ "አንተ ያምመሀልን? ጥልቀቱ ጉልበት ድረስ ነው አላልክምን?" አለው።
ግመሉም "አዎና! ታዲያ በራሴ ጉልበት ነው እንጂ ያልኩህ ባንተ ጉልበት መች አልኩህ?" በማለት መለሰለት። ቀበሮው በልምድ የቀደመውን አካል መጠየቁ ትክክል ቢሆንም የግመሉን ማንነት መርሳቱ ግን ስህተት ነበር። ግመሉም ልምዱን ማካፈሉ ትክክል ቢሆንም የቀበሮውን ማንነት ግን መርሳት አልነበረበትም።
ሁለት ሰዎች ሲነጋገሩ እንደየራሳቸው ተሞክሮ ቢነጋገሩም የአንዱ ልምድ ለሌላው መፍትሔ ሊሆን ግድ አይደለም። ባይሆን የአንደኛውን የህይወት ልምድ ለሌላኛው መጥፊያው ሊሆን ይችላልና ጥንቃቄ ማድረጉ ግድ ይላል። ለምሳሌ አንድ ሁለት ሴቶች አረብ ሀገር ሰርተው ተመልሰው ውጤታማ ቢሆኑ ሁሉም አረብ ሀገር የሄደ ሰው ውጤታማ ይሆናል ማለት አይደለም፡፡ ስለዚህ የሰዎችን የህይወት ተሞክሮ ወደ እራሳችን ህይወት አምጥተን ለመትግበር ስንዘጋጅ ማስተዋልና ጥንቃቄ አይለየን፡፡
መልካም ቀን🙏🙏
ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
©#Inspire_Ethiopia
join👉 https://t.me/assignment_supporter
ስለ ግቢ3⃣
🔷WELCOME/እንኳን ደህና መጡ
ግቢ ስትገቡ ከሚጠብቋቹህ የፍሬሽነት ክስተቶች መካከል ግንባር ቀደሙ Welcome ceremonyም ተጠቃሽ ነው
የተለያዩ የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራሞች ይሰናዳሉ የማውቃቸውን ብቻ በትንሹ ላስተዋውቃቹህ
☑️፩ የግቢ welcome
ይህ የእንኳን ደህና መጡ ፕሮግራም በግቢ ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን ምንም አይነት ክፍፍል የሌለው ሁሉንም ተማሪ ወደ ግቢ በጥሩ መስተንግዶ ከነባር ተማሪዎች ማለትም ከክበባትና ከተማሪ ህብረት አባላት ጎን በመሆን የግቢው አስተዳደር የሚያሰናዳው welcome ceremony ነው።
በዚህ ሴሪሞኒ ላይ የሚታደሙት ወይም አቀባበል የሚደረግላቸው ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን ወላጆችም ጭምር ናቸው ( የእንግድ ማረፊያ በማዘጋጀት ቡና ምናምን ...)
☑️፪ ሀይማኖታዊ
ይህ Welcome ፕሮግራም ደግሞ ፍሬሽ ተማሪ በገባ በሳምንቱ or በሆነ time interval ውስጥ አሪፍ ዝግጅት ተሰናድቶ የሚዘጋጅ ደስ የሚል ceremony ነው
ዝግጅቱ ከዩንቨርሲቲው ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አይኖረውም ።
ሙሉ ወጪው የሚሸፈነው በተማሪዎች ነው ማለትም በፍቃደኛ የእምነቱ ተከታዮች ማለት ነው።
ዝግጅቱ የሚሰናዳው እንደየ ሀይማኖት ተቋሟቱ ስርዓት ነው ።
♦️ኦርቶዶክሶች በግቢ ጉባዔ
♦️ሙስሊሞች በግቢ ጀመዓ
♦️ፕሮቴስታንቶች በማህበር
♦️ሌላም የማላውቀው ካላ like that...አማካኝነት የሚያዘጋጁት ፕሮግራም ነው ።
እንደኔ እይታ ይህ Welcome ለሁሉም ተማሪ በጣም ጠቃሚ ነው ብዬ አምናለሁ coz ለግቢ ህይወታችን መቃናት መንፈሳዊ ህይወት ትልቅ ድርሻ ስላለው ።
☑️፫ ክልላዊ/ከተማዊ
ይሄኛው Welcome ድሮም የነበረ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን እየደመቀ የመጣ ዌልካም ነው
ክልላዊ Welcome አሁን ላይ እምብዛም ነው ማለት የተወሰኑ ክልሎች ብቻ ናቸው በክልል ደረጃ ....
ያው የጊዜው በሽታ ሆነና ከክልልም አልፈን ዘር መቁጠር ጀምረናልና .....
በአንድ ክልል ውስጥ አስራ ምናምን ከተሞች በተለያየ ጊዜና ቦታ welcome ሊያዘጋጁ ይችላል ።
እዚህ ጋር አክቲቪስትነት አይሁንብኝ እንጂ ይሄንንም አይነት የwelcome ceremony እደግፈዋለሁ ምክንያቴ ደግሞ የብዙ ተማሪዎች ችግር ነው ማለትም የመጀመሪያዎቹ ሳምታት ለብዙ ፍሬሾች በጣም ከባድ ናት at that time ከማንም በላይ ሆኖ የሚንከባከበን ነባር ተማሪ ማግኘት ጥቅሙ እንጂ ጉዳቱ አይታየኝም ። ሆኖም ግን አሁን ላይ ያለው የዘረኝነት ቫይረስም ሊረሳ አይገባም ፤ ያገርህን ልጅ የምትፈልገው ባንዲራ ለመስቀል (ለጉራ፣ከሌሎች በልጦ ለመታየት) ከሆነ ጥንቅር ብሎ ይቅርብህ ፥ አንቅረህ ትፋው coz አንተ ግቢ የገባከው ድንቁርናን ለማሸነሽ እንጂ ለመዝቀጥ አይደለምና 🆗?
የበርጮሎጂስቶች 🙊 ፣ የጨብሲዎች🙊 ፣የቺኮዚሞች🙊 እና የሌሎች ምናምኖች Welcome ስለመኖሩ አላቅም 😕 ባውቅም አላስተዋውቅም ።
እኔም ለቻናሌ አዲስ የሆናቹህ ተማሪዎችን WELCOME ብያለሁ።
@positive_thinkerrr
━━━━━━━━━━━━
❤Join & Share
@assignment_supporter ✅️
❤@assignment_suporter
━━━━━━━━━━━━
📌አሁንም_ውጤት መስቀል_ቀጥሏል 📌
💡 አስተውሉ!! ግቢ ላይ ለመቆየት በጣም ወሳኙ ነገር GPE ጥሩ መሥራት ነው።
በሁሉም ግቢ የአንድ course Grade ከ100 ይያዛል ።
በአብዛኛው ግቢ 3 ነገር ተደምሮ ነው ከ 100 የሚያልቀው ። እነሱም ፦
🔑 Assignment (15-20%)
🔑 Mid exam (30-35%)
🔑 Final exam(40-50%) ናቸው
ከነዚህ ውስጥ ለግዜው assignment አሪፍ አድርጎ መስራት እና ከዛ ጋር የተገናኙ ጉዳዮቹን እንዳስሳለን ለጥራቱ አያስቡ 100% የተረጋገጠ ነው።
👌tutorial እና final exam በተመለከተ የ አባሎችን መጠን በመንገንዘብ በቅርቡ ለመጀመር እንሞክራለን። እስከዛው ግን ሼር ሼር በማድረግ የ አባሎችን መጠን እንጨምር።🙏
Freshman ላይ በጣም ወሳኝ ነገር ተወዳዳሪ ሆኖ መገኘት ነው። ብልጦች ደግሞ ያን ለማድረግ ያላቸውን አማራጭ ሁሉ ይጠቀማሉ ምከንያቱም ያን ካላደረጉ ህልማቸውን ሊማሩ አይቻላቸውም ። next የምትማሩት ፊት በመጀመሪያ አመት ውጤት ይወሰናል።
የእኛ ሥራ ተማሪዎችን ከህልማቸው ጋር ማገናኘት ነው።
ከርሶ የሚጠበቀው ለ ፈተና መዘጋጀት ብቻ ነው። ስለ አሳይመንት እኛ እያለን መጨነቅ አያስፈልግም።
ቡዙዎች እየተቀላቀሉ ነው። እርሶስ ምን ይጠብቃሉ ።
ይፍጠኑ! join ይበሉ ! !
🚩our channel
👇👇👇👇👇👇
@assignment_suporter
@assignment_suporter
@assignment_suporter
https://t.me/assignment_supporter
contact me at👇👇
@positive_thinkerrr
ለበለጠ መረጃ:- 0994409904
Engineering ምንድነው!?
🌽 ኢንጂነር ጓደኛዬ👷♂ ራሱን ሲክብ አንድ ጊዜ " ከፈጣሪ በታች ፈጣሪዎች ኢንጂነሮች ናቸው💪" ብሎኝ ነበር። እስከዚህም ባይሆንም ግን በመጠኑ ልክ✅ ነው። ሙሉ በሙሉ ማለት ይቻላል የሰው ልጅ የሚጠቀምባቸው ፈጣራዎች🛃 የተፈጠሩት በመሃንዲሶች🛠(በኢንጂነሮች) ነው። ምትነዱት መኪና 🏎፣ የምትኖሩት ቤት ፣ የምትጠቀሙት Software📱 (telegram) ፣ ልብስ የምታጥቡበት ማሽን⏲ ፣ ብር የምታወጡበት ATM 💳፣ በመኪናዎች የሚሄዱበት መንገድ 🛣፣ ሁሉንም መጥቀስ እስከማይቻል ♾ ድረስ አንጂነሪግ ከሰው ልጆች👩🏭 ሕይወት ጋር ተዛምዷል🧶። ምክንያቱም ተፈጥሮ ያለበት ሁሉ ኢንጂነሪንግ⛓ አለ ። እስካአሁን በአለም ላይ ያሉ ነገሮች ተፈጥሮ ካልሰራቻቸው🧨 በእርግጠኝነት ኢንጂነሮች🧿 ናቸው የሰሩት
🌽 የሰው ልጅ👨🦱 በተፈጥሮ የሚገኙ ነገሮችና ተፈጥሮን ( Energy⚡️ or Material🧩 ) በመጠቀም የሰውን ህይወት የተሻለ📻 ለማድረግ ወደሚረዱ መሳሪያዎች መቀየር 🎯 Engineering (ምህንድስና🌉) ነው፡፡ መቀየር ሲባል መፍጠር📸 ፣ መስራት📱 ፣ ማቀድ📈 ፣ መጠገን🪄 ፣ መቆጣጠርና😳 ፣ ማሻሻልን⛓ በውስጡ ያጠቃልላል ።
🛡For a Formal definition🛡
🌽 The American Engineers Council For Proffesional development ሲገልጸው The creative application of scientific principles to design or develop structures, machines, apparatus, or manufacturing processes, or works utilizing them singly or in combination; or to construct or operate the same with full cognizance of their design; or to forecast their behavior under specific operating conditions; all as respects an intended function, economics of operation and safety to life and property. ይለዋል።
ኢንጂነሪነግ በኢትዮጵያ
🌽 ኢትዮጵያ🇪🇹 ዉስጥ ግን አብዛኛውን ጊዜ ኢንጂነሪንግ🍴 ከ civil Engineering ጋር ይምታታል🥢 ። ምህንድስና (Engineering) ቤት እና መንገድ⛪️ መስራት ብቻ አይደለም❌ ። Scientist ነው ማለትም አይደለም🚫። Mathematician, Physicist እና Aerospace Engineer Theodore von Korman🎅 አሳምሮ እንደገለፀው "Scientist Study The World as it is Engineers Create the world that have never been " ብሏል።
🌽 Engineering የወጣው ከላቲን ingenium(Cleverness) እና ingenaire(To devise) ከሚሉ ቃላቶች ነው ። በአንድ ላይ ጉብዝና የተሞላው ፈጠራ 👼 ይሆናል። ይሄ በሁሉም ዘርፎች ላይ ነው ስልካችሁ ሰውነቱን በMechanical🪖 Engineering, የውስጥ Processoroቹን በ Electrical🎤 Engineering, ባትሪው በChemical🤮 Engineering, አፖቹ በSoftware Engineering 📀ይሰራሉ። ኢንጂነሪንግ ቤትና መንገድ መስሪያ ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ችግር ፈቺ መሳሪያዎችን ለመስራት ምንጠቀምበት እውቀትን በተግባር መተግበሪያ እውቀት✳️
የሚሰጡ ትምህርቶች‼️
🌽 የመጀመሪያ አመት የኢንጂነሪንግ ትምህርቶች ላይ Basic Programming💻 , Applied Mathematics I & II🎲, Engineering Drawing🏙, Engineering Mechanics✂️, እና ሌሎች ትምህርቶች ይሰጣሉ። ከዛ ምትፈልጉትን ኢንጂነሪንግ አይነት ከመረጣችሁ👉 በኋላ የሚሰጡት ትምህርቶች እየተለያዩ ይመጣሉ🌈(ወደፊት እናያቸዋለን)። መሠረታዊ ተብለው ሚጠሩት🗣 ግን Mathematics, Physics እና የሳይንስ ትምህርቶችን ናቸው።
🌽 ከዚህም በተጨማሪ ➕ Computer Programming ⌨💻 እውቀትም ወሳኝ👍 ነገር ነው። ምክንያቱም ፈጠራዎች (መሳሪያዎችን) ከመሰራታቸው በፊት🧤 የተለያዩ ሁኔታዎች ላይ በመክተት በአካል ሳይገኙ n computer ሙከራ(Simulate) ማድረግ ይቻላል። ለምሳሌ 🧿AutoCAD የተሰኘው Software Application ነገሮችን ለመስራት ፣ ለመገጣጠምና ለመፈተሽ 🏹 ይጠቅማል። ስለዚህ እንደዚህ አይነት software Application እንዴት መጠቀም እንዳለብን ማወቅ🤓 አለብን ማለት ነው። ለዚህም ነው አብዛኛዎቹ Pre-Engineering ትምህርቶች Computer Programmingን የሚያስተምሩት😎።
የሚያስፈልጉ ክህሎቶች
🌽 እነኚህ👆 ትምህርቶች ላይ ፍላጎቱ የሌላችሁ🤢🤮 ተማሪዎች ብትገቡ ስለ ሚከብዳችሁ ባትገቡ ይመረጣል😬። ምክንያቱም የትምህርቱ ክብደት እየጨመረ📈 እንጂ እየቀነስ 📉አይሄድም:: ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ በትንሹም🤌 ቢሆንም እንዳያችሁት ደግሞ አብዛኞቹ አስተማሪዎች👴 ማስተማሩን በትንሹ ነው ሚያደርጉት። ሁሉም ተማሪ ራሱን💪 ማስተማርን እንደ ህይወት ህግ መያዝ🧠 አለበት።
🌽 Ramanujan👨🏽 እና G.H. Hardy👨🦳 (ሁለቱም አዋቂና ታላቅ ሰዎች ነበሩ) Mathematiciaኖች🧮 ናቸው። ሌሎች አስተማሪዎች Ramanujan ከህንድ ሀገር የሚልካቸውን📝 የሂሳብ proofs Formal ስለልነበሩ😫 ሲመልሱት G.H. Hardy ግን ተቀብሎ ስላስተማረው🤗 በCambridge University ዉስጥ አብረው👬 የመስራት እድሉን አግኝተው ነበረ።
🌽 G.H. Hardy ታላቁን🙆♂ ሰው እና የልብ ጉዋደኛውን💙 Ramanujanንን ሲገልጸው🈚️
🌽 "He was in a way my discovery; I didn't invent him but like all the great men he invented himself. The difficulty for me then is not i do not know enough about him but that i know and feel too much."
🌽 በመሀል Hardy ካለው🗣 ምንወስደው ቁልፍ🔑 ነገር ምንድነው? ታላላቅ💎 ሰዎች ራሳቸውን በራሳቸው ነው ታላቅ የሚያደርጉት💪። የሚፈጠሩት እንቅፍቶች ለሁሉም ሰዉ ከባድ ናቸው። በዛን ሰዓት ግን ማሳለፊያ የሚሆነን ለምንሰራው ነገር ፍቅር 🖤 ሊኖረን ይገባል። There is no royal road towards geometry, you must go through the ditches and failures. እንደ ሌላ ሰው በትምህርት ሳይሆን በጣኦታት🕎 ማምለኪያ ስፍራ ላይ ነው Ramenujan ሂሳብን ያወቃትም ሚሰራም✍ የነበረው። ያለ ፍቅር ትግል ግን በሸክም➕ ላይ ሌላ ሸክም➕ ነው። ራስን ማስተማር ታላቅም😍 ራስ ቻይም 😎 ያደርጋል። ሁሉንም ትምህርቶች ላይ ምክንያት ያለው ስራ 👍 ሁሌም ጥሩ ዉጤትን ያመጣልና ለምንሰራው ስራ ፍቅር ቢኖረን ይመረጣል🤤።
SHARE SHARE በማድረግ ለሁሉም ይዳረስ🙏🙏🙏🙋♂️
our channel 👇👇👇👇
@assignment_supporter
@assignment_supporter
@assignment_supporter
https://t.me/assignment_supporter
🎯 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።
❇️Worksheet
🔰Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡ ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።
❇️የአጠናን መንገድ(ስልት)
🔰እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?
🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።
🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።
🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።
ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔
🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷♀።
ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ
🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።
🎯 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።
🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።
🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።
❇️የጊዜ አጠቃቀም
🔰ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።
❇️ አለመሰልቸት
🔰ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።
❇️ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።
🔰ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።
❇️Google
🔰ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘።
😍☺️እና በስተመጨረሻ አንደሰ በጣም አሪፍ ቲፕ ልጨምርላችሁ።
አሳይንመንት ሳትጨናነቁ በ አንድ ትዛዝ ብቻ አሪፍ ውጤት መስራት ትችላላችሁ። እንዴት ካላችሁኝ😊 ባለኝ የ 5 አመት ልምድ መሰረት የተሰጣችሁን የትኛውንም አሳይመንት በቅልጥፍና እና በጥራት እሰራላችኃለው ዋጋውም ተመጣጣኝ ነው።
አናግሩኝ👇
@positive_thinkerrr
☎️ 0994409904
😊 The End
መድረስ ላለበት ቦታ SHARE SHARE በማድረግ ለሁሉም ይዳረስ🙏🙏🙏🙋♂️
@assignment_supporter
@assignment_supporter
@assignment_supporter
https://t.me/assignment_supporter
🎯 ግቢ ላይ ውጤት እንዴት መስራት እንችላለን።
❇️Worksheet
🔰Worsheet ማለት መምህሩ የሆነ chapter አስተምሮ እንደጨረሰ በተማራችሁት ትምህርት ዙሪያ ከበድ ከበድ ያሉ እና የ concept ጥያቄዎች ከተለያዩ መፅሀፍት አውጣጥቶ ፈተና ሊደርስ አካባቢ የሚሰጣችሁ ነው። በተለይ ፈለጣ የሚበዛበት ዲፓርትመንት የምትገቡ ልጆች worksheet የተለመደ ነው። መምህሩ worsheet ከሰጣችሁ ፡ ፈተናውን በዚህ መልክ ተዘጋጁ ማለቱ ነው። ከ worksheet ቱ ላይ ጥቂት የማይባሉ ጥያቄዎች ፈተና ላይ ይወጣሉ። መምህሩ ጥያቄዎቹን የሚያወጣው ከ መፅሀፍ ስለሆነ የጥያቄዎቹን መልስ ከዛው መፅሀፍ ታገኙታላችሁ ፡ ከሌለ ደግሞ Google ማድረግ ይጠበቅባችሗል። ስለዚህ የሚሰጣችሁን worksheet ጥሩ አድርጋችሁ ከሰራችሁ ፡ ፈተናውን ትሰሩታላችሁ።
❇️የአጠናን መንገድ(ስልት)
🔰እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔?
🎯 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ።
🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ።
🎯 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው።
ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔
🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷♀።
ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ
🎯 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው።
🎯 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ።
🎯 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው።
🗣 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።
❇️የጊዜ አጠቃቀም
🔰ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።
❇️ አለመሰልቸት
🔰ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።
❇️ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን።
🔰ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።
❇️Google
🔰ለ ግቢ Google በጣም ወሳኝ ነገር ነው። Assignment መስራት ብትፈልጉ ፡ practical education በ video ማየት ብትፈልጉ ፡ የተለያዩ መፅሀፎችን እና የመፅሀፍ solution ማውረድ ብትፈልጉ ፡ ምናልባት መምህሩ የሰጣችሁ ኖት ካልገባችሁ እና ሳይንሱን መረዳት ብትፈልጉ ፡ Google ለነዚህ ሁሉ በቂ መፍትሔ አለው። ስለዚህ Google ን የቅርብ ወዳጅ አድርጋችሁ ወጤት መስራት ትችላላችሁ ፡ ሳይንሱን መረዳት ትችላላችሁ። በዚሁ አጋጣሚ ለ Google ምስጋና ማቅረብ እፈልጋለሁ😘።
እና በስተመጨረሻ አንደሰ በጣም አሪፍ ቲፕ ልጨምርላችሁ።
አሳይንመንት ሳትጨናነቁ በ አንድ ትዛዝ ብቻ አሪፍ ውጤት መስራት ትችላላችሁ። እንዴት ካላችሁኝ ባለኝ የ 5 አመት ልምድ መሰረት የተሰጣችሁን የትኛውንም አሳይመንት በቅልጥፍና እና በጥራት እሰራላችኃለው ዋጋውም ተመጣጣኝ ነው።
አናግሩኝ👇
@positive_thinkerrr
☎️ 0994409904
😊 The End
SHARE SHARE ለሁሉም ይዳረስ🙏🙏🙏🙋♂️
@assignment_supporter
@assignment_supporter
@assignment_supporter
Repost from Assignment supporters
📖ማንኛውንም አሳይመንት በጥራት እንሰራለን!
የምንሰራው
✅ከ9-12
✅ለRemedial
✅ለFreshman
✅ለCollege
✅ለUniversity
✅ለSummer and Extension any Department Assaigment በጥራት እንሰራለን✍️
አሳይመንቶን በዚ ይላኩ 👉 @positive_thinkerrr
Our channel 👇👇👇
🙏🙏join and share🙏🙏
@assignment_supporter
https://t.me/assignment_supporter
✳️ Freshman course ላይ Assignment እንዴት እንሰራለን ?
ውድ ቤተሰቦች የብዙወቻችሁ ጥያቄ ነው .....ዛሬ በ @positive_thinkerrr
ይመለሳል ።
Highschool ላይ አሳይመንት ሰርታችሁ ሊሆን ይችላል በ ልሙጥ ወረቀት or በ line paper ጥፋችሁ ከዛ በ ስቴፕራል አስዛችሁ ምናምን🙈 ፤ Campus ላይ ይችን እንዳትሞክሯት ለምሳሌ ለ psychology course ልክ እንደዚህ አድርጋችሁ ሰርታችሁ ብታስረክቡ ይህ Departmentቱን መናቅ ነው ተብላችሁ የተማሪዎች ህብረት ልትቀርቡ ትችላላችሁ😁 ስቀልድ ነው ...መምህራኖች ወይ አይቀበሉአችሁም ወይ ትልቅ ማርክ ይቀንሱባችኅል Campus ላይ ደግሞ አይደለም አንድ ሶስት ማርክ ቀርቶ 0.5 ምንያህል ትልቅ value እንዳላት ምታውቁት Grade ስታዩ ነው። ስለዚ Assignment አሰራር የ ራሱ የሆነ Style አለው።
ከምስሉ ላይ እንደምታዩት Page cover አስጥፋችሁ ማስጠረዝ አለባችሁ።
ሙሉው የምትጥፉበት paper ልሙጥ ወረቀት( A4 paper )ቢሆን ይመረጣል።
✳️ የ freshman ኮርሶችን assignment በ ሶስት ከፍለን እንያቸው
1⃣ የ case study assignments
እነዚህ Assignments የሚሰጡን የ Calculation ትምህርት ባልሆኑት እንደ Anthropology እና Civics courseኦች ላይ ነው።ዓላማቸውም አንድ Title ይሰጠንና በዛ Title ተንተርሰን ከ 7 እስ 10 page ያላነሰ የተለያዩ subtitleሎችን አካተን ሙሉ ገለጣ እንድንጽፍ ነው። ከዚህ ላይ ማተኮር ያለብን ነገር በምንሰራው Assignment ውስጥ እነዚህ ነገሮችን በቅደም ተከተል ማካተት ወሳኝ ነገር ነው።
📚1Table contents
📚2 introduction
📚3 main part
📚4 conclusion
📚5 reference
አንዳንዴም እንደ ተሰጣችሁ Assignment instruction Acronym ምናምን እንድትጥፉ ይደረጋል ከላይ ያሉትን በ ዝርዝር ና በምሳሌ እንያቸው ተከተሉኝ....
📍1 Table contents
ይህ part assignment አችሁ ምንምን እንዳካተተ
የተካተቱ contentoch የት page እንደሚገኙ የምንገልጥበት ክፍል ነው።
ከምስሉ ላይ እንደምታዩት....😊
📍2 Introduction
ይህ ክፍል ከስሙ እንደምንረዳው የተሰጠን Title ምን እንደሚመስል በጨረፍታ ገረፍ ገረፍ እያደረግን የምናስተዋውቅበት ነው። ምሳሌ የተሰጠን Title MANUFACTURING INDUSTRY IN ETHIOPIA ቢሆን Introduction ላይ Manufacturing industry በ Ethiopia ምን ይመስል ነበረ ከ past አንጻር ፤አሁን ላይስ ስላለው ሁኔታ ....Ethiopian ለ Manufacturing industry ምናይነት view አላቸው....እና መሰሎችን ገለጻ መስጠት ነው።
📍3 main part
ይህ ዋናው ክፋል ሲሆን Table contents ላይ ለተሰጠን ርዕስ ያስቀመጥናቸውን Subtitles እንዲሁም በነሱ ስራ ያሉ ሌላ titlochn በስፋት እየዘረዘርን ሙሉ ማብራሪያ የምንሰጥበት ክፍል ነው።
📍4 conclusion
ይሄ ደግሞ main part ላይ ለተሰጠን ርዕስ ያስቀመጥናቸውን Subtitles እንዲሁም በነሱ ስራ ያሉ ሌላ titlochn በሙሉ ዘርዝረን ገለጻ የሰጠናቸውን points ፤ ያ የተንዛዛውን main part ( ቢያንስ 7-10 page ይደርሳል) እሱን ሁሉን points በሚያካትት መልኩ ከ አንድ page ባልበለጠ ወረቀት አሳጥረን መጻፍ ነው። ግን ይሄ ብቻ አደለም አንዳንዴም በ titlu ዙሪያ የናንተን ሀሳቦች እንደ መደምደሚያ መጠቀም ትችላላችሁ ።
📍5 reference
መቸም በተሰጠን ርዕስ ዙሪያ መረጃ ለማግኘት ማንፈነቅለው ድንጋይ የለም Google የለ (ግን Google ባይኖር ምን ይውጠን ነበር😘) ፤መጽሐፍት የሉ ሁሎችን sources እንጎረጉራለን ያገኘነውን መረጃም main part ላይ አስፍረናል ። ነገር ግን መምህራን ይሄን መረጃ የት አገኛችሁት ቢሉአችሁ መልስ መስጠት መቻል አለባችሁ ። ስለዚ ከዚ ከዚ አግንቻለሁ ለማለት መጨረሻ page ላይ Reference ብላችሁ sources ትዘረዝራላችሁ። Google ላይ መረጃ ስታገኙ ግን አደራ Reference ላይ Google ብላችሁ እንዳትጽፉ ነውር ነው። ያገኛችሁበትን website link ነው ማስቀመጥ ያለባችሁ ። ሞጅሉ ላይም ገልብጣችሁ Reference ላይ ሞጅል እንዳትሉ modulu ሲጀመረ የተዘጋጀው ከየት ነው? ዋናው Source ያስፈልጋል። መጽሐፍትን እንደ Reference ከተጠቀማችሁ ደግሞ ApA format ተከትላችሁ Reference መጻፍ አለባችሁ Apa format ምንድን ነው?
የ reference አጻጻፍ style ነው ምስሉን ተመልከቱ።
Join and share endayresa🙏
╔═════════════════════╗
📚JOIN: @assignment_supporter
📚JOIN: @assignment_supporter
╚═════════════════════╝
✅Software ENGINEERING‼️
👩💻 ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ በአሁኑ ሰአት በብዙ ተማሪዎች ተፈላጊ እየሆነ የመጣ የ ኢንጅነሪንግ ፊልድ ነው ።የተለያዩ ሶፍትዌሮች ወይም አፕልኬሽኖችን ለመስራት እና ለመፍጠር በዩኒቨርሲቲ የሚሰጠው ትምህርት ዘርፍ ' ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ' ተብሎ ይጠራል።
🟢 በ ቅድመ ምረቃ ዲግሪ መርሐ ግብር የስንት አመት ትምህርት ነው❓
✅ በአብዛኞቹ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ላይ 5 አመት የሚወስድ ሲሆን እንደ እነ መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ላይ ደግሞ የ 4 አመት ትምህርት ነው ።
🎚 ምን አይነት ተማሪ ነው Software Engineeering መግባት ያለበት❓
⏰ Software Engineering ለመግባት programming ላይ አሪፍ ፍላጎት እና ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎች ቢገቡበት ይመረጣል።ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ ላይ የሚሰጡ የ programming language ትምህርቶች ላይ ጎበዝ ለመሆን Maths ላይ አሪፍ ብትሆኑ ይመረጣል።
✅ Software Engineeering የሚገቡ ተማሪዎች ግዴታ ማወቅ ያለባቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው❓
🔵 ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ የሚማር ተማሪ ከታች የተዘረዘሩትን የ Programming Language የትምህርት ዘርፍ ግዴታ መውሰድ እና ማወቅ ይጠበቅበታል👇።
▶️Some of main programming languags are
👩💻• C++
👨💻• JAVA
👩💻• PYHTON
👨💻• C#
👩💻• HTML
👨💻• CSS
👩💻• JAVASCRPT
🔵 በ Software Engineeering የሙያ ዘርፍ ላይ ብቁ እና ስኬታማ የሆነ ባለሙያ ምን ምን ሙያዊ ተግባራትን ያከናውናል❓
▶️ ሶፍትዌር ኢንጅነሪንግ የተለያዩ አፕሊኬሽን ስራዎችን መስራት ና መፍጠርን ያካትታል ማለትም Application Ena Software Develope ማድረግ ነው።
➡️A SOFTWARE ENGINEER is someone who:
🔵• Designs, builds, and tests software applications.
🔵• Understands user requirements and solves problems using coding/technology.
🔵• Uses programming languages to turn instructions into something a computer can understand.
✅ በ Software Engineeering የተመረቀ ሰው ምን ምን ስራዎችን መስራት ይችላል❓
1. Applications Developer
2. Cyber Security Analyst
3. Game Developer
4. Information Systems Manager
5. IT Consultant
6. Multimedia Programmer
7. Web Developer
8. Web Designer
9. Software Engineer
🌞 Software Engineeering የስራ እድሉ እስከምን ድረስ ነው❓
🌑 በ Software Engineeering ተመርቄ ስራ ላላገኝ እችላለሁ🤔❓ አትስጉ ሰፊ የሆነ የስራ ዕድል ይገኝበታል እንደውም ከለሎች የ Engineering ፊልዶች የሚለይበት አንድ ነገር የግድ የ መንግስት ስራ ላይ መቀጠር አይጠበቅባችሁም። በ Software Engineering የተመረቀ ተማሪ በራሱ የተለያዩ ስራዎች መስራት ይችላል።
📚 የ Software Engineeering ትምህርት ከባድ ነው ወይስ ቀላል🤔❓
🌎 በ Software Engineering ስር ከሚሰጡ ኮርሶች መካከል አብዛሀኞቹ programming languages ናቸው እና እነሱን በደንብ መረዳት እና Practise ማድረግ ከቻላችሁ ደስ የሚል እና easy የሆነ ትምህርት ነው።
➡️ ገቢውስ ምን ያክል ነው😀❓
🟣 አንድ የ Software Engineering ምሩቅ ስራ ላይ አሪፍ የሚባል ደሞዝ ያገኛል። በ ወር በትንሹ መነሻ ደሞዝ ከ10,000 ብር እና ከዛ በላይ ታገኛላቹ በዛ ላይ ከ መደበኛ ስራ ውጪ በግል የራሳችሁን ስራ ለመስራት ስለሚመች በጣም አሪፍ ገቢ ይኖራችኋል።
Join at and share
👇👇👇👇👇👇
@assignment_supporter
@assignment_supporter
@assignment_supporter
❓❓
ለነባር ተማሪዎች “ግቢ ውስጥ በተለይም አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ጥሩ ውጤት ያስመዘግቡ ዘንድ እንዴት እንዲያጠኑ ትመክራላቹህ? “ተብለዉ ለተጠየቁት ምን መልስ ሰጡ📝
🧑🏽🏫ተማሪ 1⃣
አንደኛ አመት ተማሪዎች ውጤታማ መሆን ከፈለጉ ከአሁኑ ሞጅሎችን በራሳቸው አረዳድ ማንበብ መጀመር አለባቸው እንጂ በዚህ ሰዓት ሌክቸረር እየጠበቁ መማር አያዋጣም ምክንያቱም ሌክቸረሮች ቀስ ብለው ማስተማር ይጀምሩና ልክ ሴሚስተሩ ሊያልቅ ሁለት ሳምንት ምናምን ሲቀረው የቀሩትን chapterች reading assigment ብለው ይሰጣሉ ይሄ ደግሞ አስተማሪ እየጠበቁ የሚያጠናውን ተማሪ ይበልጥ ይጎዳል።
🧑🏽🏫ተማሪ 2⃣
እኔ ለአድስ ገቢ ተማሪዎች የምሠጠው ምክር በሚያነቡበት ግዜ በደንብ አድርገው ሀንድአውት ብቻ ቢያነቡ በእርግጠኝነት ጥሩ ውጤት ይሰራሉ ከሀንድአውትውጭ የሚወጣ ጥያቄ የለም በተለይ ፍሬሽማን ኮርስ ላይ እንደኔ ግንዛቤ ለብቻ በደንብ ማንበብእመርጣለሁ እየተጠያየቅን ብናነብ ይሻላል እሚሉ ተማሪዎች አሉ በእርግጥ ይህ ጥሩ ቢሆንም መጀመሪያ አንብቦ ከተረዳው ቡሀላ ቢጠያየቁ አሪፍ ነው ደግሞ በምታነቡ ግዜ ሞጅል ላይ ያለ ነገር ቀላል ነው ብላችሁ አትለፉ ዋጋ ያሥከፍላችዃል በፊት ተምሬዋለሁ አቀዋለሁ እሚባል ነገር በጣም ነው እሚጎዳው ምክንያቱም ኮርሱ ላይ ያሉት አብዛሀኞቹ ታች ክላሥ የተማራችሁት ሥለሆነ ቀላል ሊመሥላችሁ ይችላል ፈተና በምትሰሩበት ግዜ ደግሞ ጥያቄውን በደንብ ለመረዳት ሞክሩ ምክንያቱም አንድ ፊደል ታሥበላለች በተረፈ ማንበብ ነው በተለይ ፍሬሽማን ኮርስ ላይ እመረጣችሁት ፊልድ እንድትገቡ።
🧑🏽🏫ተማሪ 3⃣
እኔ በተሳሳትኩበት እንዳትሳሳቱ ትንሽ ነገር ላካፍላችሁ።
የምትፈልጉትን ነገር ማግኘት ትፈልጋላችሁ ፥ እንግዲያውስ ውጤት መስራት ያስፈልጋችኋል።
➡ አሁን ያላችሁበትን ጊዜ ተጠቀሙበት።Fresh man courseኦች ለማንበብ ብዙም አስቸጋሪ ስላልሆኑ ባላችሁ ጊዜ አየት አየት ብታደርጓቸው አይከፋም። ምክንያቱም ገና ክላስ ከመጀመሩ quize የሚል አስተማሪ አይጠፋም። በ quizeና በትናንሽ ፈተናዎች የተጠረቃቀመ ውጤት ጥቅሙ ያኔ ስታዩት ይገባችኋል።
➡ ያላችሁበትንም ይሁን የሌላ ጊቢ ጥያቄዎች ከመስራት ወደኃላ እንዳትሉ። ጥቂት አንብባችሁ ብዙ ጥያቄ ብትሰሩ ታተርፋላችሁ....
🧑🏽🏫 ተማሪ 4⃣
ይህ መልእክት አዲስ ለምትገቡ ተማሪዎች ነው እባካችሁ የያዛችሁትን fresh man program pdf አንብቡ በመጀመሪያው ሴሚስተር ለምትወስዱት 6 or 7 ኮርሶች 1 ወር አይሰጧችሁም የምሬን ነው እኛንም እያደረጉን ያለው ያንን ነው....እባካችሁ ትምህርት ሙድ ውስጥ ግቡ...እዚ መጥታችሁ ጊዜ አጠረኝ ሆዴን አመመኝ ብትሉ እመኑኝ ማንም አይሰማችሁም 5 እና ከዛ በላይ chapter ያላቸውን 6 ኮርሶች በ 1 ወር ከ 10 ቀን ባልሞላ ግዜ ውስጥ ነው እንድትወስዱ የምትገደዱት አስቡበት... ይህን ጊዜ ተጠቀሙበት...አመሰግናለው።
SHARE SHARE ለሁሉም ይዳረስ🙏🙏🙏🙋♂️
@assignment_supporter. @assignment_supporter. @assignment_supporter. @assignment_supporter
📌Target-REMEDIAL Students !
BIOLOGY REMEDIAL MODULE
( NATURAL STUDENTS )
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
Join ▮ @assignment_supporter💡
Join ▮ @assignment_supporter💡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
اکنون در دسترس! پژوهش تلگرام ۲۰۲۵ — مهمترین بینشهای سال 
