fa
Feedback
Assignment supporters

Assignment supporters

رفتن به کانال در Telegram

ለ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው የማንኛውንም የትምህርት አይነት በ የትኛውም የክፍል ደረጃ የተሰጣችሁን assignment ከ አንድ ቀን ባነሰ ግዜ ውስጥ በ ከፍተኛ ጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሰራት ከፈለጉ ያናግሩን👇👇 @positive_thinkerrr ወይም 0994409904 ይደውሉ።

نمایش بیشتر
362
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
ⓛⓞሎⓒⓐካⓛል  ˢᵗᵘᵈᵉⁿᵗˢ 📚 የቃሉን ታሪካዊ አመጣጥ ባላቅም ከግቢ ቃላቶች category እንደሚመደብ አቃልሁ፤ ባጭሩ የቃሉ ፍች ባለከተማ ማለት ይመስለኛል ባለሀገር እንደሚባለው ማለት ነው። ዞሮ ዞሮ ሎካል ተማሪ ማለት ዩንቨርሲቲው በሚገኝበት ከተማ ላይ የሚገኙ የግቢው ተማሪዎች ወይም የከተማው ወጣቶች ናቸው፤ እኛ ግን mostly ሎካል የምትለዋን ቃል የምንጠቅምባት or የምናቃት በበጎ ሳይሆን በreversu ነው። ስለ ሎካል ተማሪዎች ወይም ስለ ከተማ ተደባዳቢዎች ለፍሬሽ ተማሪዎች ቅድመ ጥቆማ መስጠት በጣም አስፈላጊ ሆኖ ስለታየኝ ይቺን ምክር ቢጤ አሰናዳሁ( ተደባዳቢ ያልኳትን ቃል ደብዳቢ በሚለው ቀይሩት እሺ ።) 📚 ያው አሁን ላይ የትኛውም የኢትዮ ዩንቨርሲቲ በሚገኝበት አካባቢ የሚገኙ የከተማው ጎረምሶች ወይም  በግቢኛ ስማቸው ሎካሎች አንዳንዴ የተሳፈጣቸውን ወይም ዝም ብሎ ያስጠላቸውን ተማሪ ኮርኮም ማድረግ ለምዶባቸዋልና ብዙ አትንቀልቀሉ ከሎካሎች ጋርም አትሳፈጡ ለማለት እወዳለሁ። አንዳንድ ቦታ የሚገኙ ሎካሎች ደግሞ በጣም ሞኝ ከመሆናቸው የተነሳ ሴት ልጅን በቴስታ የሚማቱ ደደቦች ናቸው ። ብዙዎቹ ሎካሎች ሴቶችን አይነኩም ይሁን እንጂ ሴት ነኝ ብለሽ ከተበትሽ ያፈርጡሻል ። ወንዶችንማ ጭውት ነው ሚሉባቸው  ፦ ❌ ልብሳቸውን አስወልቀው ያስጨፍሯቸዋል ፤ አንጨፍርም ምናምን ካሉ ይገረፋሉ ። ❌ በጥፊ ፣በእርግጫ፣ በቴስታ ምናምን ይጠባብሷቸዋል ። ❌በፌሮ፣በቆንጨራ፣በሽመል፣በቆመጥ ምናምን ጉዳት ያደርሱባቸዋል ወይም ያሯሩጧቸዊል። 📚 ኧረ ብዙ ብዙ...ልብ ይበሉ  የትኛውም ግቢ ብትገቡ ከከተማው ልጆች ወይም ከባለከተሞች ጋር በምንም መልኩ እንዳትጣሉ መጣላት ይቅርና እንዳትሳፈጡ። አንዳንድ ግቢዎች ላይ የሚገኙ ሎካሎች እንኳን ተማሪን አስተማሪንም የሚገርፉ በመሆናቸው ጨዋ ለመሆን ሞክሩ። 📚 ጨብሲ🥂 ምናምን እያላቹ ከተማ ኦቨር የምትወጡ ልጆች ብትመቱ ወይም ስልክና ዶላር💸💵 ቢወሰድባቹህ ብዙ አትከፉ ፥ ምክንያቱም እነሱ ሳይደርሱባቹህ ስለደረሳችሁባቸው...( ሰክሬ ሎካል አከብራለሁ  መቼም አትሉኝም ❓ ለማንኛውም ከግቢ ውጭም ይሁን ግቢ ውስጥ ከሎካል ጋር አትነካኩ ከቻላቹ pis ለመፍጠር ሞክሩ ምክንያቱም ካንዱ ጋር ተጣላቹህ ማለት ከጀመዐዎቹ ጋር ተጣላቹህ ማለት ነው። So ትቢታችሁን ለጊዜው ዋጥ አድርጉና አርፋቹህ ተማሩ በተለይ first semister ላይ ብዙ ፍሬሽ ተማሪ ፍሬሽ ላለመምሰል ብሎ ካገኘው ጋር ይሳፈጣል፤የት እና በማን ላይ መተበት እንዳለበት አለማወቅ በራሱ የፍሬሽነት መገለጫ ነው ። ★ ሎካል፡ ስምህ ማነው? Me ፡ ዞግ🙏 ሎካል፡ የቺክህን ስልክ አምጣ? Me : 09794026....   📚 የተጠየከውን ቶሎ ሰጥተህ ካልተፋታህ "እሱን ስትገረፍ ታወራዋለህ " ምናምን ብሎ የማሰቢያ ጊዜ አይሰጥህም ጠባብሶ ይቀበልሃል ።በተጨማሪም ግቢ በምትገቡበት   ወቅት ወደ ከተማ ምናምን ስትወጡ በጣም መጠንቀቅ ይኖርባቹሃል ፤ ባጃጅ ላይ ወይም ታክሲ ላይ ከምላቹህ በላይ ንቁ ሁናቹህ ጠብቁ (ስልክ ምናምን...ዋ ብያለሁ ....!) ይቺን ምክር ብረት ገፍተው ደረታቸው ላይ ትንሽ ያዝ ሲያደርጋቸው ለሚተብቱትና በየዋህነት አልያም በድፍረት የማያውቁት ከተማ ላይ በማን ይነካኛል ስሜት ዘራፍ ለሚሉ ወንድሞች አድርሱልኝ። በተረፈ ግቢ ውስጥ የበላይ ለመሆን or ለድብድብ ግሩፕ አትፍጠሩ የትኛውም አይነት ግሩፕ ከተበተ ከሎካሎች ጋር መጣላቱ አይቀርምና ፡ ቡድንተኝነታችሁን ለትምሮ ወይም ለችግኝ ተከላ አርጉት።🌴🌱🌿📝✏️🖍 © ካምፓስ Join at and share 👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

SQ3R Studying Method 📖 🔆 The SQ3R method is a reading comprehension technique that helps students identify important facts and retain information within their textbook. 🔆 SQ3R (or SQRRR) is an acronym that stands for the five steps of the reading comprehension process. Try these steps for a more efficient and effective study session 😃 1. Survey 📚 Instead of reading the entire book, start by skimming the first chapter and taking notes on any headings, subheadings, images, or other standout features like charts. 2. Question❓ Formulate questions around the content of the chapter, such as, What is this chapter about? What do I already know about this subject? 3. Read 📖 Begin reading the full chapter and look for answers to the questions you formulated. 4. Recite 🗯 After reading a section, summarize in your own words what you just read. Try recalling and identifying major points and answer any questions from the second step. 5. Review 📝 Once you have finished the chapter, it’s important to review the material to fully understand it. Quiz yourself on the questions you created and re-read any portions you need to. ▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎▪︎ 👉 Share and join our channel for more study tips 🥸    🌟 @assignment_supporter🌟    🌟 @assignment_supporter🌟    🌟 @assignment_supporter 🌟 https://t.me/assignment_supporter

#Repost ✳️ የ ወልቂጤ University ፊልድ አመራረጥ ! 2⃣0⃣1⃣3⃣ 💥 የ ወልቂጤ ዮኒቨርስቲ የ 2013 ተማሪዎች በ በወቅቱ ሁሉም የትምህርት ክፍል ምደባቸውን (field ማለቴ ነው) አውቀው ነበር። 💥 ሁሉም 1ኛ አመት ተማሪወች (fresh) COC Exam ወስደው ነበር። 💥 የ COC EXAM ከ General neber  የተፈተኑት ( 9-12) ከተማሩት ነው ። subjectochu 👇👇 Biology :- Chemistry English Maths 💥 biology ke 9-12 nw gn ba bizat 9-10 nw 💥 13 tiyake neber 1 tiyake 2%alew 26%malet nw 💥Chemistry indeza ke 9-12 neber gn be bizat 11-12 nw isum indezaw 💥13 tiyake neber 1 tiyake 2%alew 26%malet nw 💥English freshman course yetamarnew nw abzagnaw mulu grammer neber 💥13 tiyake neber 1 tiyake 2%alew 26%malet nw 💥 Maths hulum freshman course nw  yaw  💥11 tiyake neber 1 tiyake 2%alew 22% malet nw ከ 4 ኮርሶች ከእያንዳንዱ  ጥያቄ 2%  በ አጠቃላይ 100% ይሆናል ከዛ ወደ 30% ይቀጥላል ማለት ነው።   💥 የትምህርት ክፍል ምደባው በ 4    ፊልዶች ላይ ያካለለ ነበር።    ማለትም ;🌷🌷🌷          1) MEDICINE          2) pharmacy          3) OTher Natural  scince          4) Enginering 💥 የ ውጤት አያያዙ የ  first semister GPA(50%),COC EXAM(30%) & Entrance result(20%)  የሁሉም  ከ 100% ይሰራናል። 💥 አመራረጡም ትንሽ  ዘዴ ይጠይቃል በ ውጤት ብቻ የፈለጉት ላይ መወጠጥ የለም😂😂 ። 💥 ስለ አመሪረጡ ደሞ 👇👇 መጀመሪያ  ይህ👇👇 የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ intake capacity ነው። 1) medicine 40-ተማሪ 2) pharmacy-40 ተማሪ 4)other-Natural የቀረው መሰለኝ 5) Enginering 500 ተማሪ *** በ ENGINEERING ሰር እነ computre scince ,soft-Enginering ,CIVIL engineering ,mechanical engineering ...... intake capacity ተጠቅመን አመራረጥ እንመልከት👇👇 መጀመሪያ ለመምረጥ የግቢው የሁሉም ተማሪ ውጤት ይለጠፋ የሚለጠፈው ስም ምናምን ሳይኖረው ነው በቻ ሁሉም የራሱን ውጤት ስለሚያቅ ያን ውጤቱን ይዞ ከተለጠፈው ውጤት ላይ ደረጃውን ያያል።    🍢🍢🍢 ሲቀጥል ከላይ የለቀኩት intake capacity ያለ ነገር አይደለም። በዚህ መሰረት አንድ ተማሪ medicine ለመግባት የሚፈልግ ከሆነ የ ውጤቱ ደረጃው ከ1-40 መሆን አለበት (አፈርማቲቯ አስቦ መግባት አለበት) ይህን ከሆነለት የመግባት እድሉ ምንም አያጠራጥረውም ገብቶ ያው ዶክተር ተሳክልኝ ሆነ ማለት ነው😂😂 ነገርግን ከዚህ አባል ውጭ ከሆነ የመግባት እድሉ አንድ አማራጭ ናት እሷም ምናልባት ከሱ በላይ ውጤት ያላቸው ተማሪወች ሌላ ቦታ ከሞሉ የመግባት probablity አለው። ነገርግን ይህ ተማሪ በሁሉም በኩል አንደኛ ምርጫውን ሜድሲንን ማለቴ ነው ካላገኘ ወደ ሁለተኛ ምርጫው ይታይለታል ወይ ? መልሱ አይታይለትም ነው። እንበልና ተማሪው 1 medicine, 2 pharmacy አድርጎ ቢሞላ ወይም ምርጫው ቢሆን የሜድሲን አድሉ ተዘጋ ወደ ፋርማ ላይወርድለት ይችላል ። ምክኒያቱም ፋርማን አንደኛ አርገው ለሞሉ ነው እድሉ የሚሰጠው እንጂ የነሱን መብት አያስነኩም። ይህ ተማሪ እነሱ በፈለጉት በሌሎቹ ይመድቡታል እንደ እድል ነው እንጅ ሁለተኛ ምርጫው የሚታይለት እንደ ውጤቱ አይደለም ማለት ነዉ ። የተግባባን ይመስለኛል? 💥💥   ከግቢው ተማሪወች አፈላልጌ ያገኘሁት መረጃ ነው። 💥💥  የወልቂጤ ተማሪወች አመራረጥ ነው እንደየ ግቢው በትንሹ ሊለያይ ይችላል። ❗️ውድ የ ቻናሌ ቤተሰቦች የ ግቢዎች አሰራር በየ ዓመቱ ሊቀያየር እንደሚችል Consider እያደረጋችሁ! ©Ethio university news ! ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  | @assignment_supporter                        https://t.me/assignment_supporter

💡 ካንፓስ tip ዘ TENSION 📙ጭለላ📖 📚 ግቢ ላይ ከሚያጋጥሙን ጥቂት ችግሮች ውስጥ አንዱ ከልክ ያለፈ ጭንቀት ወይም በግቢ ስሙ #Tension ብለን የምንጠራው ነገር ነው። ይሄ ችግር ብዙውን ጊዜ በአንደኛ አመት ተማሪዎች ላይ በስፋት የሚስተዋል ቢሆንም በሁሉም ዘንድ ማለትም ተመራቂ ተማሪዎችንም ሳይቀር የሚያጦዝ ደስ የሚል ሙድ ያለው ጭለላ ነው። እኔ ግን ጥሎብኝ የሚሰማኝ ሰው ሳገኝ ብዙ አወራለሁና ዛሬም ከሰማችሁኝ ትንሽ ስለ ግቢ Stress or Tension ባካፍላቹህ ደስ ይለኛል ፤ በተጨማሪም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለቴንሽን አዲስ በመሆናቸውና ከሁሉም በይበልጥ የታላላቆቻቸውን ምክር ስለሚቀበሉ ይቺን ምክር እንድታደርሱልኝ አደራ ማለት እወዳለሁ አይይ እንግዲህ ብዙ አታቅራራ ፡ ወደ ገደለው ግባ....! ‼️📚 Tension ብዙውን ጊዜ የሚገጥመን የሆነ ክስተት አንጎላችንን ሲቦጠብጠው እንደሆነ የአንጎል ስፔሻሊስትና የሳይኮሎጂ ሊቅ ለመሆን የሚመኙት Dr abz ይገልፃሉ አስከትለውም ጭንቅላታችን በጣም በሚጨናነቅበት ጊዜ የሚገጥመን failure ነው ይላሉ ።ስልካችንን አንዳንዴ busy ሲሆን stack እንደሚያደርገው ማለታቸው ነው።😂 በግቢ ተማሪዎች ሳይኮሎጂ ላይ ከፍተኛ ጥናት ያደረጉት ኢንጂነር እንደጠቀሱት ደግሞ " ግቢ ውስጥ ብዙውን ጊዜ ተማሪዎች በተለይም አንደኛ አመት ተማሪዎች ፈተና በሚቃረብበት ወቅት የሚገጥማቸው ከፍተኛ መጨናነቅ መንስኤው አስቀድመው ተገቢውን ዝግጅት አለማድረጋቸው ነው" በማለት ይጠቅሳሉ ። 💭 እኔም የኢንጂነሩን ጥናት ዋቢ በማድረግ የተወሰኑ ገጠመኞቼን ላካፍላቹህ ፦ ይለናል ጉ ጓደኛችን እስቲ ትንሽ እናዳምጠው 📚 የአንደኛ አመት ተማሪ እያለሁ Drawing ኮርስ አጨልሎኝ አድሮ ጥዋት ከፈተና በፊት ካፌ ላይ የተፎገርኩት ፉገራ እስካሁን ሳስታውሰው ያስቀኛል ፤ ምን መሰላቹህ pictorial drawing የሚሉት ነገር አልገባህ ብሎኝ እንቅልፍ ባይኔ ሳይዞር ወረቀት ላይ አፍጥጬ ስላደርኩ መሰለኝ ከምላቹህ በላይ ጭልል ብዬ ነበር እናም ምንም ቁምነገር ሳልይዝ ነጋና ቁርስ መብያ ሰዓት ደርሶ ሁሌም አብሮኝ የሚበላው ጓደኛዬ ጋር በመሆን ወደ ካፌ ሄድን ፡ ስንደርስም ያን ጨርቅ የመሰለ ፊቴን ታጥቤ ወደ ሆድ ሸንቁሬው አዝግ ሰልፍ አመራን ፥ የማይደርስ የለምና ተራችን ደርሶ ባንደኛው እጃችን ትሪና ኩባያ ይዘን በሌላኛው ደግሞ binder ( for drawing exam) ይዘን ወደ ጨላፊዎች ተጠጋን ጨላፊዋም ትሪህን አስጠጋ ስትለኝ ትሪዬን' ሰጠኋት ፨ የሚገርማቹህ ትሪ ብዬ ፍርፍሩን የተቀበልኩት በ binderu ነበር እሷም አውቃ ይሁን እንደኔ ጨልላ ባላቅም ጭልፋ ሙሉ ፍርፍር በትሪዬ' ሞላችልኝ ሆይ .. በBindeሬ ፍርፍር ማስደረጌን ያስተዋልኩት አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ በሳቅ ፍርፍር ብሎ ፍርፍሩ ሲደፋበት ነበር ። ብዙ ተማሪ እየሳቀብኝ እንደሆነ ሳይ ደግሞ ይብስኑ የምገባበት ጠፋኝ ( ሳሳዝን) ፤ እንዴትም ብዬ ከዛ ደባሪ ሙድ በመውጣት ፍርፍሬን ወደ ትሪዬ ገልብጬ ወደ መቀመጫዬ በመሄድ በእልህ ምግቡን ስበላው እሱም ለካ ቂም ይዞብኝ ነበር 😬 አነቀኝ ፡ ባክህ አልሰማህም በሻይ ድራሽህን ነው ማጠፋው ብዬ ወደ ኩባያዬ እጄን ስሰድ አለወትሮዋ ኩባያዋ ቀለለችኝ ምንሼ ነው ብዬ ወደ ኩባያዬ ሾፍ ሳደርግ ሻይም ሳላስቀዳ ነበር የተቀመጥኩት ( አይ drawing) ድጋሚ ይስቁብኛል ብዬ ባልፈራ ኖሮ ተነስቼ ሻይ አስቀዳ ነበር ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ከጓደኛዬ እየተዋስኩ ታሪካዊ ቁርሴን በላሁ ። 📚 ከዛ ከካፌው ወጣ ብለን እጃችንን በመታጠብ ላይ ሳለን ሳላስበው ጧ ብዬ ሳቅኩ አብሮኝ የነበረው ጓደኛዬ በመገረም " ይሄ ልጅ ዛሬ ምን ነካው" ሲል ባሰብኝ ፤ እንዴት ብዬ ልንገረው ገና ት ብዬ ስጀምር ሳቄ ይቀድመኛል ። እንዴትም ብዬ በምልክት ወደ ትሪው ጠቆምኩት ፥ ደንግጦ ትሪውን ይዞ ወደ ካፌ ሲሮጥ ህዝቤ ፈተናዋን ረስታ ሳቀችበት ብድር በምድር አሉ ፥ ለካስ freind ከኔው ብሳ ትሪዋን ይዛ ወደ ፈተና ልትገባ ነበር ።የሚገርም ግጥምጥሞሽ እያልኩ ፏ ብልጭ ብዬ ተፈተንኩ እላቹሃልው ። 💡 ገጠመኜን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ*! 📚 Final exam ሲቃረብ እንደዚህ አይነት የካፌ comedy መመልከት የተለመደ ነው ምክንያቱ ደግሞ ቅድም ኢንጅነሩ የጠቀሱት ቅድሚያ አለመዘጋጀት ነው። ⏰ ፈተና ሲደርስ ከሚስተዋሉ ገጠመኞች ውስጥ ጥቂቶቹ⚡️ 👉 ካፌ ላይ መፎገር 🤧 👉 ስልክን library, class, cafe etc መርሳት ወይም መጣል 👉 Calculator መርሳት / መጣል 👉 PC መርሳት ለዛውም space ( class) 👉 ያነበቡትን መርሳት 👉 ራስን መሳት ( በተለይ ሴቶች) 👉 ወዘተ.... 😜 ታድያ ምን ይሻላል ❓ 📌ፈተና ሳይደርስ ሁሉንም course cover ማድረግ 📌 ከጭንቀታም ጓደኛ መራቅ ( በሰላሙ ሰአት እናንተ ስታነቡ ከማያነበው ማለቴ ነው ።) 📌 ከጎበዝ ተማሪ ጋር መጎዳኘትና አብሮ ማንበብ 📌 ጥያቄዎችን በgroup መስራት 📌 ስለ ፈተና አወጣጥ ከታላላቆቻችን መጠየቅ ( from seniors)🕵‍♀ 📌 Information gather ማድረግ ፦ 📌 ከበግ ተራ በመራቅ ሴቶችን info መጠየቅ ( affirmative ምናምን ብለው ....) 📚 በተረፈ Tension መጠኑ ይለያይ እንጂ አይቀሬ ነገር በመሆኑ ፈታ በሉ። እንደኔ እንደውም Tension ምንም የማይዘው ተማሪ ካሮት አምራች ገበሬ ይመስለኛል፤ ምክንያቱም አንብቦ ሳይሆን የሚፈተነው position አስተካክሎ ነው ። ሲበዛ ነው እንጂ የማይነፋው ተማሪ ካነበበ እስከሚፈተን ድረስ Tension Normal ነው። ©ዘ ካምፓስ Join at and share 👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

📢 Department tip   📈 Economics 👩‍🏫 ECONOMICS  ምንድ ነው❓ ☘ኢኮኖሚክስ እያደገ የመጣ ኢኮኖሚ የእያንዳንዱ ህዝብ ኩራት ነው ፡፡ ስለሆነም በዚህ ኢንዱስትሪ ውስጥ በትክክል ማግኘት የተሻሉ አዕምሮዎችን እና እጆችን ማምጣት ያካትታል ፡፡ ☘ኢኮኖሚክስ የሀብት ማምረት እና ማሰራጨት ተግባራዊ እና ቲዎሪያዊ ሳይንስ ነው እሱ በሸቀጦች እና አገልግሎቶች ምርት ፣ ግዥ እና ሽያጭ ስርዓት ዙሪያ የተመሠረተ ነው ፡፡ ☘ይህ ብዙውን ጊዜ ነገ ኢኮኖሚውን መልሕቅ ከሚሰጡት አዕምሮዎች ከሚያሠለጥነው የትምህርት ዘርፍ ይጀምራል ፡፡ በዚህ ምክንያት ብዙ ትምህርት ቤቶች ስለ ኢኮኖሚክስ ደረጃቸውን አሻሽለዋል ፡፡ 👩‍🏫 ECONOMIST ማነው❓ ☘አንድ ኢኮኖሚስት በማኅበራዊ ሳይንስ ሥነ-ምግባራዊ ሥነ-ምግባራዊ ልምምድ የሚያደርግ ግለሰብ ነው። ☘ኢኮኖሚስቶች ብዙውን ጊዜ የአንድን አገር እድገት በተለያዩ መንገዶች ስለሚመሩ ንድፈ ሐሳቦች እና መሠረታዊ ነገሮች ያዘጋጃሉ እንዲሁም ይጽፋሉ ፡፡ ☘በዚህ ሙያዎች ውስጥ ብዙውን ጊዜ በአጠቃላይ ከሚታወቁ የፍልስፍና ንድፈ ሃሳቦች እስከ ማክሮ ኢኮኖሚያዊ ትንተና እና ጥቃቅን ኢኮኖሚያዊ ትንተና የሚይዙ ምስማሮች አሉ ፡፡ በተጨማሪም የፋይናንስ መግለጫ ትንተና ፣ ትንታኔያዊ ዘዴዎችን የሚያካትት ውሎ አድሮ ሌሎች ሞዴሎችን ከበስተጀርባ ማዳበር ይጀምራል ፡፡ ☘እንደ ኢኮኖሚስት በአንድ ጊዜ በሁለት የተለያዩ የኢንዱስትሪ ቅርንጫፎች ውስጥ በአንድ ጊዜ መሥራት ይችላሉ። ከሁሉም በላይ - ትንበያዎን እና ትንታኔዎን በዋና ችሎታዎ እንዴት ማድረግ እንደሚችሉ መማር ያስፈልግዎታል። ↘የኤኮኖሚስቶች ግዴታ ሌላው አስፈላጊ ቦታ በስታትስቲክስ ትንተና ፣ በሂሳብ እንዲሁም በኮምፒዩተር ፕሮግራም ውስጥ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም መረጃን በመገምገም ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡ ☘እንደ ሕግ እና ሕክምና ያሉ ከተደነገጉ ሙያዎች በተቃራኒው ፣ እንደ ኢኮኖሚስት ፈቃድ አያስፈልግዎትም ፡፡ ቢሆንም ፣ መያዝ ያስፈልግዎታል በሂሳብ ውስጥ አንድ ዲግሪ ወይም እስታቲስቲክስ እና በመቀጠል በኢኮኖሚክስ ውስጥ የፒ.ዲ.ዲ. ☘ስለዚህ ሥራዎን ለመጀመር በዓለም ላይ ካሉ እጅግ በጣም ኢኮኖሚያዊ ትምህርት ቤቶችን ዝርዝር ውስጥ መምረጥ ይችላሉ። 👩‍🏫እኔ ስኬታማ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ መሆን የምችለው እንዴት ነው❓ ☘ራስዎን ሲያዳብሩ እንዲሁም በአስተማሪዎች እና በፕሮግራሞች ላይ ብድር ሲያገኙ የተሳካ የምጣኔ ሀብት ባለሙያ መሆን ይችላሉ ፡፡     👩‍🏫 በ ቅድመ ምረቃ ዲግሪ መርሐ ግብር የስንት አመት ትምህርት ነው❓ አብዛኛዎቹ የኢኮኖሚክስ ዲግሪዎች ለሦስት ወይም ለአራት ዓመታት የሚቆዩ ሲሆን በዋነኝነት የሚሠጡት በንግግሮች በሴሚናሮች ነው ፡፡ 👩‍🏫ECONOMISTS ተፈላጊነት አላቸው❓ ☘በእርግጥ ፣ ኢኮኖሚስቶች ተፈላጊ ናቸው እናም በመጨረሻም እንደዚያው ይቆያሉ።          👩‍🏫በECONOMICS ተመርቄ ስራ ላላገኝ እችላለሁ🤔❓ ☘ በኢኮኖሚክስ ዲግሪ ሥራ ማግኘት ቀላል ነው? ☘የለም ፣ በጣም ቀላል አይደለም ፡፡ ይህ እውነት ሊሆን ቢችልም ፣ ሥራ የማግኘት ዕድልም እንዲሁ አይቀንሰውም ፡፡ 👩‍🏫 ECONOMICS ትምህርት ከባድ ነው ወይስ ቀላል🤔❓ ☘  ከባድ ነው ወይም ቀላል የሚለውን ሁሌም እንደምንለው ተምረን አ ላ የ ነ ው ም 🙄🙃😇ባንልም ት/ት ከተባለ ሁሉንም focus እስካላደረግን ድረስ ይከብዱናል ሀ ሲባል የሚከብድ ት/ት የለም 😏እራሳችን ካላከበድነው ድረስ ፖ ሲባል ደግሞ ውጤታማ ለመሆን አስተማሪ የሚያስተምረውን በደንብ ማዳመጥና የሚሰጡትን courses መከታተል, ከሚያውቁ ሠዎች መጠየቅና ራስን ማሳመን ናቸው እና እነሱን በደንብ መረዳት እና Practise ማድረግ ከቻላችሁ ደስ የሚል እና easy የሆነ ትምህርት ነው። በሌላ በኩል የቢኤ ኢኮኖሚክስ ተማሪዎች የበለጠ የጥራት ዘዴዎችን ስለሚጠቀሙ ብዙ ሂሳብ እንዲጠቀሙ አይገደዱም ፡፡ 💠ምንም እንኳን የተለያዩ የኢኮኖሚክስ ንዑስ ክፍሎች ቢኖሩም ፣ ሁለቱ ዋና ዋና የጥናት መስኮች የማይክሮ ኢኮኖሚክስ እና ማክሮ ኢኮኖሚክስ ናቸው ፡፡ የማይክሮ ኢኮኖሚክስ በግለሰቦች እና በኢንዱስትሪዎች መካከል ያለው ተለዋዋጭ ጥናት ነው ፣ ስለ አጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚክስ ስነ-ስርዓት የበለጠ የተጠና ጥናት ነው ፣ ይህም የአንድ አጠቃላይ ገበያ ወይም ሀገር የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጥናት ነው። 👩‍🏫 ገቢውስ ምን ያክል ነው😋❓ ☘ አንድ  ምሩቅ ስራ ላይ አሪፍ የሚባል ደሞዝ ያገኛል። ኢኮኖሚስቶች ብዙ ገንዘብ ያገኛሉ ☘አዎ አርገውታል. በተለይም ፣ ኢኮኖሚስቶች በአማካኝ እስከ 114,600 ዶላር ያህል ገቢ ያገኛሉ ፡፡😋 👩‍🏫 እንዴት ECONOMIST እሆናለሁ❓ ☘ኢኮኖሚክስ ለማጥናት ከወሰኑ እና ከዚያ በኋላ በመስክ ውስጥ የሙያ መስክን ለመከታተል ከወሰኑ በኋላ ፣ በመጨረሻም ወደ እርስዎ የሚመራ መመሪያ ያስፈልግዎታል ፡፡ ☘እንደ አረንጓዴ መስክ ፣ ኢኮኖሚስቶች ብዙውን ጊዜ የተወሰኑ የሥልጠና ደረጃዎችን ይለማመዳሉ። ስለሆነም እኛ አራት የሚያካትቱ አራት ደረጃዎች አድርገናል ፡፡ ደረጃ ➊ የባችለር ዲግሪ ያግኙ በኢኮኖሚ መስክ ውስጥ አንድ ሥራ ለመጀመር እንኳን በመጀመሪያ የመጀመሪያ ዲግሪ (ኢኮኖሚክስ) ደረጃ ወደ ኢኮኖሚክስ ውስጥ ለመግባት ብቁ መሆን አለብዎት ፡፡ በዚህ ደረጃ ፣ ስለ ኢኮኖሚክስ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳብ መማር ይጀምራሉ። በገንዘብ ትንተና ላይ በአጠቃላይ የተወሰኑ ተለዋዋጭ ስርዓተ-ጥለቶችን እና ፅንሰ-ሀሳቦችን ያስተዋውቁዎታል። ደረጃ ➋ የመምህርዎን ፕሮግራም ያጠናቅቁ በእርግጥ የባችለር ፕሮግራምዎ ከተጠናቀቀ በኋላ ወዲያውኑ የጌታውን ፕሮግራም መከታተል ያስፈልግዎታል ፡፡ ምክንያቱም የማስተርስ ፕሮግራም በተጨማሪም የምርምር ግኝቶችን ለማካሄድ እና ለማተም እድሉን በሚሰጥዎ በርእሰ ጉዳይ ላይ ያለዎትን እውቀት ያጠናክራል። ደረጃ ➌ የፒ.ዲ.ኤፍ. ፕሮግራም ያጠናቅቁ ብዙውን ጊዜ ፣ ​​ፒኤችዲ ዲግሪ በማይኖርዎት ጊዜ ትክክለኛ ደንበኞችን መሰብሰብ ያቅታዎታል ፡፡ በኤኮኖሚክስ ውስጥ የፒ.ዲ. ዲግሪዎች አብዛኛውን ጊዜ የአካዴሚያዊ ግኝትዎ ከፍተኛ ደረጃዎች ናቸው ፣ ስለሆነም ያንን ዲግሪ ለማጠናቀቅ ማቀድ አለብዎት። ምናልባት ፣ በዓለም ላይ ካሉ አንዳንድ ኢኮኖሚያዊ ት / ቤቶች አንዳንዶቹ ክፍት መስኮት እንዲሰጡዎት ከእይታ ውጭ አይደሉም። ደረጃ ➍ ማረጋገጫዎችን ይገንቡ እንደ ኢኮኖሚክስ ባሉ የሙያ ጎዳናዎች ውስጥ ፣ ብዙ የምስክር ወረቀቶች ሲያገኙ የመገለል እድሉ ከፍ ያለ ነው ፡፡ ጥያቄዎችን መጠየቅ እንደፈለጉ በመሰረታዊነት እነዚህ ዕድሎች በእይታ ውስጥ ናቸው ፡፡ በኢኮኖሚክስ ውስጥ የበለጠ በተማሩ እና በተተገበሩበት ጊዜ ገቢዎ በተመሳሳይ ይጨምራል ፡፡ ብዙውን ጊዜ በተለያዩ ድርጅቶች የሚመረጡ ስለሆኑ ኢኮኖሚስቶች ሥራ ፍለጋ ሲፈልጉ አልፎ አልፎ ያገቸዋል ፡፡ በእርግጥ ይህ ማለት በተለያዩ ተቋሞቻቸው ውስጥ በደንብ የሰለጠኑ ናቸው ማለት ነው ፡፡ ===== ━━━━━━━━━━━━━━━━━ Join at and share 👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች ይህን ፋይል አንብቡት 💥Students who want to be transferred from Natural Science to Social Science can submit their written application to the main or campus registrar offices. The application should be short but must contain the applicant’s full name, ID number and signature. Join at and share 👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ እይታ መብራት በማንኛውም ሰአት መብራት አለ።የራሱ ሰብስቴሽን ያለው ሲሆን እሱም ስራ ያቆመ ቀን Automatic Generator ስላለው ጨለማ አይሆንም። ቢሆን እንኳን ላይብረሪና የሴቶች ዶርም ጨለማ አያቀውም።ገነት በሉት😁። ውሃ ፅድት ያለ ውሃ አለ። አያሳስብም።በማንኛውም ሰአት ቧንቧዎች ክፍት ናቸው።የማይደርስበት ቦታ እንኳን ቢኖር በተማሪ ህብረት ፅ/ቤት ቢሮ በማመልከት ቅሬታ እንዲፈታ ማድረግ ትችላላችሁ። ኔትዎርክ በዚህ አመት ምንም ደስ አይልም።እያወራን እንኳን ይቆራረጣል። ሳካብድ "እ" ለማለት 5 ደቂቃ ሌላ ቃል ለመናገር 10 ደቂቃ ይፈጃል። ባንክ 1 ባንክ(የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ) በግቢው ውስጥ ሲኖር 3ATM ማሽኖች በተለያየ ቦታ ላይ አገልግሎት ይሰጣሉ። ከዩኒቨርሲቲው ውጭ በአስፓልት ዳር የተቀሩት ባንኮች እንደልብ(የወረፋው ነገር ሳይነሳ) ይገኛሉ። የመንገድ ሁኔታ ከዋናው አስፓልት ወደ ዩኒቨርሲቲ መገንጠያ የሚወስደው መንገድ ለቅርስነት ተፈልጎ የተቀመጠ የአባቶቻችንን ሃንዹራ ሃብት ይመስላል። አይታደስም።አይነካም መኪኖችና ባጃጆች በዚያ መንገድ ሲሄዱ መኪኖች "ሰለሜ ሰለሜ" ሲሉ ባጃጆች ከኋላ ከግራ ወደቀኝ እያሉ "ወያ ሰለሜ ሃያ" የሚሉ ይመስላሉ። መንገዱ ከመቆፋፈሩ የተነሳ ቀጥ ብሎ መሄድ የማይታሰብ ነገር ነው። በር ላይ የፍተሻው ነገር እንዳለ ሆኖ ቀጥታ ተሻግሮ የሚታይ ሰፊ የኮብል መንገድ በዳር እና በዳር በሸክላ ድንጋዮች አምሮ፡በፅድ ዛፎች ታጅቦ አለ። ግን እኛ ግቢ አስፓልት መቼ ይሆን ሚገባልን። ሁለት ዋና ትላልቅ ኮብል መንገዶች እንዲሁም ወደ ዶርም፡ወደቢሮዎችና ወደ መማሪያ ክፍሎች የሚወስዱ ትንንሽ ኮብል መንገዶች አሉት። ሰላማዊ እንቅስቃሴ በአካባቢው በማንኛውም ሰአት ሰላማዊ የሚባል እንቅስቃሴ አለ። የግቢው መግቢያ ሰአት 1:00 ቢተናቀቅም። ንግድና ግብይት የዩኒቨርሲቲው አካባቢ ብቻ ሳይሆን ደብረብርሃን ራሷ ብዙ መጀመር የሚችሉ የስራ ዘርፎች ቢኖሯትም ለተማሪ ሊያስፈልጉ የሚገቡ ነገሮች የተሟሉ ይመስላሉ። (ወይኔ ግን ደብረብርሃን ኑሮ ውድ ነው😜ነ) የኮምኒኬሽን ፅ/ቤት የፌስቡክ ገፅ እና ዋና ድህረገፅ አስተዳደር ነክ የሆኑ መረጃዎች ይሰራጫሉ የተማሪዎች ህብረት ቴሌግራም ቻናል በዩኒቨርሲቲው የተማሪ ህብረት ጉዳዮች ይሰራጩበታል። በተጨማሪም በሁሉም የብሎክ መዞሪያዎች ላይ ባሉ ሰሌዳ ድንጋዮች ላይ ማስታወቂያዎች ይለጠፋሉ። የትምህርት አሰጣጥ ከትምህርት ሚንስትር በተቀረፀለት አቅጣጫ የራሱን አካዳሚክ ካሌንደር ቀርፆ ይንቀሳቀሳል። የሚድና የፋይናል ፈተና በስኬጁል የሚሰጥ ይሆናል። የዲፓርትመንት አመዳደብ ከመጀመሪያው ሴሚስተር መውጫ ፈተና በኋላ ለኮሌጆች ምደባ የሚያመች COC ይኖራል። ከNatural Science Engineering and Technology Medicine Other Natural Science ከሶሻል ህግ (law) Other Social Science እነዚህ በመጀመሪያው ሴሚስተር የሚከፋፈሉ ኮሌጆች ናቸው። በመጀመሪያ አመት ሁለተኛ ሴሚስተር መውጫና ለ2ኛ አመት መግቢያ ግን ከኮሌጅ ወደ ዲፓርትመንት ለመግባት የሚደረግ ፈተና ይኖራል። ይህም ኢንጅነሪን ወደ ሁለት ኮሌጅ እንዲከፈል ይደረጋል። ወደ ኢንጅነሪንግ እና ወደ ኮምፒውቲንግ በጤና፣በሶሻል፣በናቹራል ሳይንስ ውስጥ ያሉ የዲፓርትመንት መረጃዎች ከላይ አስቀድመን በለቀቅናልቹ መረጃዎች ውስጥ ተካቷል። የግቢው ስርዓት የመግቢያ ሰአት እስከ 1:00 ብቻ ነው ከጥበቃዎችና ከሌሎች ሰራተኞች ጋር አምቧጓሮ መፍጠር አይቻልም ተማሪው ጥያቄውን ፊርማ በማሰባሰብ ለተማሪ ህብረት ወይም ለሚመለከተው ኮሌጅ ፅ/ቤ በማቅረብ ምላሹን ማግኘት ይችላል።በጩኸትና በእብሪተኝነት የሚመለስ ምላሽ አይኖርም። በግቢ ውስጥ የሚከናወኑ ተጨማሪ ተሳትፎዎች በክበባትና ማህበራት የተደራጁ የተለያዩ ስብስቦች ይኖራሉ። MESA(Mechanical engineering Students Association) በግቢ ውስጥና በአካባቢው የሚደረጉ ቀላል በጎ አድራጎቶችን በማስተባበር ይሳተፋል። ለተማሪዎች በየጊዜው የጥናት ና ለጥያቄ መልስ የሚያዘጋጅበት ዝግጅት ይኖራል። በሜካኒካል ኢንጅነሪንግ ዲፓርትመንት ተማሪዎች የሚነሱ ማንኛውንም ጥያቄዎች በተገቢው መንገድ መልስ እንዲሰጥ ጥያቄ ያቀርባል። ሆሄ ተስፋ የኪነጥበብ ቡድን በተማሪዎች የእውቀትና የክህሎት እንቅስቃሴ ላይ ሃዲድ በመሆን ይሳተፋል። የመፅሃፍ ምርቃት፣የሙዚቃ፣የስነፅሁፍ፣የውዝዋዜ፣የስዕልና ሌሎች የኪነጥበብ ዝግጅቶችን በማድመቅ ለተማሪ ዝግጅት ያዘጋጃል። በስነ ልቦና ለተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎች በቂ እንክብካቤና ስልጠና ይሰጣል። (CESA) Chemical Engineering Student Association የተቋቋመበት ሃሳብና አላማ እንደማንኛውም አሶሴሽን ቢሆንም እንቅስቃሴውን በሙላት አላየንም።በሂደት ላይ ያለ association ነው። ፀረ-ኤድስ፡ፀረሙስና... ሌሎች በኤሌመንተሪና በሃይስኩል ያየናቸው ክበባት በቋሚነት አሉ። ተማሪዎች በእነዚህ ክበባትና ማህበራት በመመዝገብ መሳተፍ፣ መጠቀም ይችላሉ። @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter ▬▬▬▬▬▬▬▬

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ አዲስ ለሚገቡ ለከተማው ያለ መረጃ ከአ. አ-ደ/ብርሃን 125km መነሻ፡ ላምበረት መነሃሪያ አማራጭ መነሻ: ቃሊቲ መነሃሪያ ታሪፍ፥ 80 ቢሆንም 100 ያስከፍላሉ ከቃሊቲ ሊጨምር ይችላል የጊዜ ርዝማኔ 1:30-2:00 የመንገድ ሁኔታ፥ ዳገት ቁልቁለት የሌለበት ለጥ ያለ መንገድ ከባህርዳርና ከጎንደር አካባቢ ለምትመጡ በደሴ በኩል መምጣት አማራጭ አላችሁ ከደሴ ደ/ብ 267 KM 5:30 ያህል ያስኬዳል። የሰላም ሁኔት፥ እጅግ አስተማማኝ የከተማዋ ሁኔታ ደብረብርሃን በሃገራችን በቅዝቃዜዋ የታወቀች ለኑሮም አመቺ የሆነች ቦታ ናት። በመጀመሪያዎቹ የአመቱ ወራት ከጥቅምት እስከ ታህሳስ መጨረሻ ዝቅተኛ ከ1-7 °C ከፍተኛ ከ13-24°C አየር ንብረት አለው።ማለትም በእነዚያ ወራት በቀንም ቅዝቃዜው ሊያመዝን ይችላል። ከጥር በኋላ ባለው የአየር ንብረት ግን ለቲሸርት አመቺ በሚሆን መልኩ ከ18-25/26 °C በመሆን እጅጉን ተስማሚ የአየር ንብረት ይኖረዋል።(የማይሞቅ የማይበርድ) ተማሪዎች ደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲ ደርሷችሁ ስትመጡ በተቻላችሁ መጠን ለለሊታችሁ ደህና ብርድ ልብስ ብትይዙ ምክራችን ነው። ለእንቅስቃሴም ቢሆን ደህና ሹራብ ነገር.. ዋናው ዩኒቨርሲቲ እዚያው ደብረብርሃን ከተማ ውስጥ ቢሆንም የህብረተሰብ እንቅስቃሴ ከሚበዛበት ከተማ የ4 ብር ታክሲ ከከተማው ወደኋላ በሚያስመልስ ርቀት (ጠባሴ ቀበሌ 09) ላይ ይገኛል።ጠባሴ ካሉት ሰፈሮች በወራጅ ወንዝ ምክኒያት ነፋሻማና ቀዝቃዛ ሰፈር በመሆኑ የተሰጠው ስያሜ ነው። የዩኒቨርሲቲው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው በ1999 ዓም ከተመሰረቱት የሁለተኛው ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ ነው። እስካሁን ለ14ኛ ዙር ያስመረቀ ሲሆን 52በላይ በመጀመሪያ ከ70በላይ በ2ኛ ዲግሪ አንዲሁም 2 ዲፓርትመንቶችን በሶስተኛ ዲግሪ መስጠት ጀምሯል። ከ2014 ዓም ጀምሮም ያስገነባውን የጤና ካምፓስ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ የካምፓሱን ብዛት 2 አድርጓል።በተጨማሪም አሁን የኢንጅነሪንግ ካምፓስ እያስገነባ ይገኛል። የፅዳት ነገር አያሳስብም። ጠዋት እና አመሻሽ ሽንትቤቶችና ቆሻሻ የሚበዛባቸው ቦታዎች በቀን ሁለት ጊዜ ይፀዳሉ። ላይብራረሪ 4 ላይብረሪዎች አሉ። ዋና ላይብረሪ በዋነኝነት የኢንጅነሪንግ ቢባልም የፍረሽማንና የጤና ዲፓርትመንት ማቴሪያሎችን አሟልቷል። ባለ ሁለት ፎቅ የሆነና በሶስቱም (G0,G1,G2,) ግራውንዶች ላይ ዋይፋይ የተሟላላቸው የኮምፒውተር ክፍሎች አሉት።ለኮምፒውተር ከተፈቀደ ቦታ ውጭ ኮምፒውተር ይዞ መግባት አይፈቀድም። ለካፌ፣ለዋናው(መገናኛ)ላውንጅ እና ለመማሪያ ክፍሎች ቅርብ የሆነ ነው። ሶሻል ላይብረሪ ለዶርሞች ቅርብ የሆነ የራሱ የኮምፒውተር ክፍሎችና ኮምፒውተሮች ያሉት።በየትኛውም ማንበቢያ ቦታ የግል ኮምፒውተርን ማስጠቀም የሚያስችል ነው። በዚህ አመት የዋይፋይ አቅርቦቱ ተቋርጧል።ባለ አንድ ፎቅ ብቻ ነው። ሴቶች ላይብረሪ(ወንድ ስለሆንኩኝ ሙሉ መረጃ ባይኖረኝም) ለዶርሞች ቅርብ የሆነ የራሱ የኮምፒውተር ክፍሎችና ኮምፒውተሮች ያሉት።የዋይፋይ አገልግሎት የተሟላለት ከሴቶች ውጭ መግባት የማይቻልበት ነው።( የሚንቀዠቀዥ አይን ያላቸው እዚህ የሉም)ባለ አንድ ፎቅ ብቻ ነው። የዶርም ሁኔታ 12main block የቀሩት mini block በድምሩ 41 የዶርም ብሎኮች ሲኖሩ በእያንዳንዳቸው ውስጥ ከ6-8 ተማሪ የሚይዙ ክፍሎች አሏቸው። ዋይፋይ ከብሎክ ውጭ አብዛኞቹ ቦታዎች ቢደርሱም ዶርም ድረስ የተወሰኑ ብሎኮች ያገኛሉ። ወደሁሉም የሚወስዱ መንገዶች በኮብል የተሰሩ ናቸው። ጠዋትና ማታ ይፀዳሉ(በናታችሁ ፍረሾችም ነባሮችም በትክክል እሩ ወይም ውሃ ድፉ) የዋይፋይ ሁኔታ ታስቦ ሲሰራ ሁሉም ዶርም ብቻ ሳይሆን በየመንዱ ሁሉ እንዲደርስ ተደርጎ ነበር።ነገር ግን በተለያየ ምክኒያት አብዛኞቹ ስራ አቁመዋል። ዶርሞች አካባቢ፡መገናኛ ላውንጅ ላይብረሪዎች፡ላይ አሁንም ይሰራል።በጥሩ ሞባይልና ኮምፒውተር እስከ 20MB/s ቢሰራም ራም 1 እና 2 ስልኮች 100-500 Kb/s ይሰራላቸዋል። Samsung ስልኮች ላይ ከቅርብ ጊዜ በኋላ አልሰራ ብሏል። ግን Certificate በመጫን ወይም ሊሰራ ይችላል።ወይም IP በመቀየር(10.18.196.xx) ይሰራል። አንዳንድ ኢንተርኔት ኬብል ባላቸው ክፍሎች ላይ ተማሪዎች Hotspot በማገናኘት ይጠቀማሉ። ይቀጥላል @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter ▬▬▬▬▬▬▬▬

👏👏congradulation 👏👏 ✅️All Assignment Solutions✅️ *Best offers on whole semester courses, quiz , online exams and all assignments* ✍🏻. .1.MASTERS 2.BA DEGREE 3.TVET ALL LEVEL/Diploma 4 Remedial 5 preparatory 6 distance                ✅Assignment                ✅Article review                ✅Term paper                ✅Business  plan                ✅data analysis                ✅Research                ✅Research proposal                ✅CV(Resume)                ✅Essay                ✅nternship reports               ✅practical Attachment     ✅short note     ✅questions ✅ppt preparation *_Fields of Specialisation_* ✅Business ✅ Mathematics ✅Accounting ✅Finance ✅Economics ✅Dissertation ✅Programming ( *c, c++,Java, python, data mining,machine learning,MATLAB etc* ✅Psychology ✅Sociology ✅Engineering ✅Statistics ✅Computer Science ✅Pharmacy ✅ English ✅Healthcare *etc* 👉 Discounts for all high school and remedial students All you have to do is send your presentation through this account. 0994409904 አሳይመንታችሁን በጊዜ እጥረት ወይም በተለያየ ምክንያት መስራት ካልቻሉ እንዳይጨነቁ👊!! ልክ እንደርሶ ሆነን አሳይመንቶውን በሚገባና በጥራት ሰርትን እናስረክቦታለን    🏁 ማንኛውንም አይነት አሳይመንቶች፣ 🏁 የዲግሪ/የማስተርሰ /ፕሮፖዛል 🏁ቢዝነስ ፕላን 🏁ለርቀት(Distance) ተማሪዎች 🏳️ Article review & CV 👊 እርሶ ጥናቶን ይበርቱ አሳይመንቱን ለኛ🤝‌‌ Don't worry if you can't do your assignment due to lack of time or other reasons!! Just like you, we will deliver the show to you with good and quality work 🏁 Any kind of assignment, 🏁 Degree/Master's /Proposal 🏁 Business plan 🏁 For distance students 🏳️ Article review & CV 🏳️any software and computer scince assignments 🚩🚩 and many others, including college and university assignments, we will deliver them with quality and speed. 👉 via Telegram at 👉 @positive_thinkerrr or You can reach us via +251994409904 Join our channel anyway 👉 https://t.me/assignment_supporter +251994409904

📢 Department tip PUBLIC HEALTH 👩‍⚕ 👩‍🏫 በ ቅድመ ምረቃ ዲግሪ መርሐ ግብር የስንት አመት ትምህርት ነው❓ ከዚህ ቀደም 4አመት የነበረ ቢሆንም በአዲሱ ትምህርት ከfreshman ጨምሮ በ4 አመት የሚያልቅ ትምህርት ነው ።      Course list for the Department of Public Health 👉Year I: Semester Communicative English Skills l Logic and critical thinking Psychology General physics Mathematics Geography Physical fitness 👉Year I Semester II Communicative English Skills ll General biology General chemistry Entrepreneurship Intro to emerging  technology Civics & moral Education Anthropology 👉Year II Introduction to public health Embryology and Histology Anatomy Physiology Biochemistry Medical Microbiology Pathology Health Service Management Human Nutrition Population and Development Health Economics Medical Parasitology Reproductive Health Health Ethics & Legal Medicine Environmental Health and Ecology Disaster Prevention & preparedness Inclusiveness Pharmacology Economics Global trends 👉Year III Biostatistics Epidemiology Health informatics Research methods Health Education Clinical laboratory methods Introduction to nursing art Physical diagnosis Community based training  (CBTP) Internal medicine –I Surgery –I Gynecology and Obstetrics-I Pediatrics –I 👉Year IV Psychiatry Ophthalmology ENT Dentistry Dermatology Diagnostic Radiology Gynecology and Obstetrics-II Surgery-II Internal Medicine-II Pediatrics-Il Community health attachment Team Training Program (TTP ) Student Research project Comprehensive qualifying exam 👩‍🏫 በHO ዘርፍ ላይ ብቁ እና ስኬታማ የሆነ ባለሙያ ምን ምን ሙያዊ ተግባራትን ያከናውናል❓ ☘What Public Health Services Do? ➺Observe health status to recognize and solve community health issues ➺Encourage community partnerships and action to identify and resolve health related issues. ➺Implement laws and regulations that secure health and ensure safety. ➺Ensure qualified public and personal health care staff. ➺Identify and investigate health issues and health hazards in the people. ➺Provide communities required personal health services and ensure the provision of health care. ➺Develop plans and policies that help individual and community health initiatives. ➺Search for new ideas and innovative solutions to health issues. ➺Notify, educate, and empower people regarding health problems and so... 👩‍🏫 HO  ስራ እድሉ እስከምን ድረስ ነው❓ ☘oww አዛ ነው🥺 ስራ ወፍ ግን ወደ ገጠር አካባቢ ላይ ይገኛል ገጠር ላይ እንደ Doctor ሆኖ መስራት 🥳 👩‍🏫  ትምህርት ከባድ ነው ወይስ ቀላል🤔❓ ☘ ያው ጤና ከተባለ ሁሉም መስዋዕትነት ይጠይቃል አዕምሮም ይፈልጋል 🙄ልፋትም አለው ለማስፈራራት ሳይሆን ቀድሞውኑ ለሚመጣው ነገር ለመዘጋጀት ነው ኢትዮ ላይ አብዛኛው እኛ ተማሪዎች የምንፈልገውን አለማወቅ እና አክብደን ስለምናየው ነው ውጤታማ ማንሆነው  IT'S FACT😏 👩‍🏫 ገቢውስ ምን ያክል ነው😋❓ ☘ አንድ የ HO ምሩቅ ስራ ላይ አሪፍ የሚባል ደሞዝ ያገኛሉ ያው ከሀገር ሀገር ከሆስፒታል ሆስፒታል ሊለያይ ይችላል ግን ለምሳሌ ያህል↘ 🌇Federal Ministry of Health of Ethiopia Public Health - Monthly About  ETB14,399 -ETB15,713 🌇Government of Ethiopia Public Health Officer - Monthly About  ETB8,122 -ETB8,871 🌇Jan Medical Center Public Health Officer - Monthly About  ETB5,93 0 -ETB6,445 🌇AIDS Healthcare Foundation Public Health Professional - Monthly About  ETB45,503 -ETB49,715 ━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  | @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter                      

#MizanTepiUniversity በ2016 ዓ.ም ወደ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ እና በ2015 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፍያ ነጥብ ያስመዘገባችው ተማሪዎች፤ የ2016 ዓ.ም ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 03 እና 04/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ የምዝገባ ቦታ -  የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ሚዛን አማን በሚገኘው ዋናው ጊቢ -  የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ጊቢ ወደ ተቋሙ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፡- ከ9ኛ እስከ 2ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ዋናውና ሦስት ኮፒ፣ ዘጠኝ 3 x 4 የሆ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ልብስ፣ የስፖርት ትጥቅ፡፡ ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

📢 Department tip 🧑‍⚖️ Law  ትንሽ የ ቆየ ገለጻ ነው። 👨‍⚖️ ትምህርቱ ሽምደዳ ሲሆን ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ማለት አይቻልም። ምክንያቱም ከመጀመሪያ አመት የመጀመሪያ ሴሚስተር ውጭ ያሉት የኮርሶች ፈተና open book ነው። open book ማለት መምህሩ የሚፈቅድላችሁን ማንኛውም መፅሀፍ ይዛችሁ መግባት ትችላላችሁ። 👨‍⚖️ ከዚህ በተጨማሪ የምትማሩዋቸውን ኮርሶች ማቴሪያል መፅሀፎች ከ መፅሀፍት ቤቱ ይሠጡዋችኃል። 👉ወደ ፈተናዎቹ ስንመለስ ከላይ እንዳልኳችሁ ከመጀመሪያ አመት ሁለተኛው ሴሚስተር ጀምሮ case  ይሆናል የምትፈተኑት። ይህም ማለት የሆነ የፍርድ ቤት ክርክር አይነት ይሰጣችሁና ውሳኔውን እናንተው የምትሰጡት ይሆናል። 👨‍⚖️እዚህ ጋር የማልደብቃችሁ ነገር English language ሞካሪ መሆን ይጠበቅባችኃል። ምክንያቱም ውሳኔያችሁን ከ civil code አንቀፅ ጠቅሳችሁ ማብራራት ስለሚጠበቅባችሁ። የመጀመሪያ አመት የመጀመሪያ ሴሚስተር👇👇( በአምናው የትምህርት ፖሊሲ)     1) introduction to law     2) legal system     3) legal history     4) customary law     5) English for lawyers     6) ICT የመጀመሪያ አመት ሁለተኛው ሴሚስተር 👇👇     1) law of person (case)     2) law of succession (case)     3) family law (case)     4) logic     5) legal research     6) jurisprudence 👨‍⚖️በመጨረሻም ከተመረቃችሁ በኋላ  ለ 6 ወር ያክል የደሞዛችሁን ግማሽ እየተከፈላችሁ ለ 6 ወር ያክል ስልጠና ትወስዳላችሁ። ለምሳሌ አማራ ክልል ከሆናችሁ ባህር ዳር ትሰለጥናላችሁ። በመጨረሻም ዳኛ። ከቆይታዎች በኋላ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚያወጣውን የጠበቆች ፈተና ተፈትናችሁ ጠበቃ መሆን ትችላላችሁ።   ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  | @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

👨‍🎓🧑‍🎓የተማሪዎች አይነት (types of learners) 📮ይህ ፅሁፍ ሁሉም የትምህርት ብቃት እንዳለው ነገር ግን የትምህርቱ ዘዴ እና አቀባበላችን እንደሚለያይ ያሳያል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ የተለያዩ አይነት ተማሪዎችን እና የሚቀላቸውን የመማር ዘዴ ማጣጣም ያስፈልጋል። የራሳችሁ የመማር ምርጫ ከየት እንደሆነ መመርመርም አትርሱ። 🧑‍🎓1— የእይታ ተማሪዎች (Visual learners) እነዚህ የተማሪ አይነቶች የሚገባቸው መማር በእይታ ሲሆን ነው። ያዩት ነገር እንዲሁ በቃል ከሚነገራቸው ይልቅ አይረሳቸውም። እነዚህ ተማሪዎች በተግባር ማየት ካልቻሉ በሃሳባቸው እየሳሉ ቢያነቡ በቀላሉ ማስታወስ ይችላሉ። 🧑‍🎓2— የተግባር ተማሪዎች (Kineshetic learners) እነዚህ በበኩላቸው ራሳቸው በተግባር የሞከሩት ነገር ቶሎ ይገባቸዋል፣ አይረሱትም። ሰው ሲያደርግ ከማየት በላይ ራሳቸው በማድረግ ይማራሉ። ለነዚህ ወደ ተግባር እየቀየሩ መሞከር ይመከራል። 🧑‍🎓3– የመስማት ተማሪዎች (auditory learners) እነዚህ አንድን ነገር ከሰሙት በቂያቸው ነው። ብዙ ከማጥናት በላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲያዳምጡ ይመከራሉ። የሰሙትን ነገር ይረዳሉ። 🧑‍🎓4– የጭንቀት ተማሪዎች (Stress learners) ያስጨነቃቸው ነገር አይረሳቸውም። ተጨናንቀው ግዴታ አውቄ መግባት አለብኝ ካሉ ማን እንደነሱ። ትኩረት መስጠት እና መጣር ይመከራሉ። 🧑‍🎓5— የመዝናናት ተማሪዎች (Ease learners) ዘና ፈታ ብለው ያነበቡት እና የተማሩት አይረሳቸውም። እነዚህ ሳይጨናነቁ፣ አእምሯቸውን ዘና አድርገው እና ጥሩ ስሜት ውስጥ ሆነው ቢያነቡ በጣም ውጤታማ ይሆናሉ። 🧑‍🎓6– የፅሁፍ ተማሪዎች (Scrubble learners) ለየት ባለ መልኩ ትምህርት ወደ አእምሯቸው የሚገባው ሲፅፉት ነው። እንዳልረሳው ብለው ቢፅፋም ስለማይረሱት ደግመው ላያዩት ይችላሉ። እነዚህ ሲያጠኑ ደጋግመው እንዲፅፉ እና ከጥናት በሗላም ራሳቸውን የሚፈትኑት ያጠኑትን በወረቀት ላይ ደግመው ለመፃፍ በመሞከር እንዲሆን ይመከራል። 🧑‍🎓7— የእምነት ተማሪዎች (trust learners) አነዚህ ከሚያምኑት ወይም ከሚያከብሩት አለያም ከባለስልጣን የተሰጠን ትምህርት በጭራሽ አይረሱም። ትምህርቱ ሳይሆን መምህሩ ነው ለነሱ ወሳኙ። ይሄን ከሆን የተማርነውን ከምናምነው ሰው እንደተነገረ አድርገን እያሰብን ድጋግሞ ከማጥናት የተሻለ ምክር አይኖርም። 🧑‍🎓8— በማስተማር የሚማሩ (teach learners) እነዚህ አንድን ነገር ካስተማሩት አለቀ—ተመጠጠ ማለት ይቀላል። እና ሁሌም ተማሪ ስለማይገኝ የተወሰነ አንብበው ቀሪውን– ቆም ብሎ፣ ተማሪዎች እንዳሉ ራስን አሳምኖ፣ ጮክ ብሎ በማስተማር ማጥናት ይመከራል። 🧑‍🎓9— ተመሳሳዩን በመስራት የሚማሩ (copy learners) ለየት ባለ ሁኔታ ያዩትን ወይንም የተማሩትን ነገር አስመስለው ሲሰሩት አይረሱትም። ያየነውን ነገር ደግመን ሁሉንም ቅደም ተከተል ሳንረሳ አስመስሎ ለመስራት በመሞከር እንዲያጠኑ ይመከራል። ⭐ማጠቃለያ፦ አንድ አይነት ዘዴ በመጠቀም የሁሉንም ተማሪዎች የመማር ምርጫ እና ብቃት ማሟላት አይቻልም። ©keleme© ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬, | @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter                      

📖ማንኛውንም አሳይመንት በጥራት እንሰራለን! የምንሰራው ✅ከ9-12 ✅ለRemedial ✅ለFreshman ✅ለCollege ✅ለUniversity ✅ለSummer and Extension any Department Assaigment በጥራት እንሰራለን✍️ አሳይመንቶን በዚ ይላኩ 👉 @positive_thinkerrr ☎️0994409904 Our channel 👇👇👇 🙏🙏join and share🙏🙏 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

ኘሮግራሙን የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች እነዚህን ይመስላሉ።

#ጥቆማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመንግሥት ከተመደቡለት ተማሪዎች በተጨማሪ በተወሰኑ የትምህርት መስኮች #የግል_አመልካቾችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን አሳውቋል፡፡ አመልካቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፦ 1.  በ2015 አና 2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፣ 2.  አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (UAT) በመውሰድ የሚቀመጥን መቁረጫ ነጥብ የሚያሟሉ፣ 3.  በ2015 ዓ.ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተምራችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ፣ 4.  ዩኒቨርሲቲዉ በ12ኛ ብሔራዊ ፈተና ውጤት መሠረት ድልደላ ሲያካሒድ አመልካቾች በመረጡት የትምህርት ፕሮግራም አማራጮች ውስጥ ለመደልደል ውጤታቸው ካላበቃቸው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት በሚያደርገው ድልደላ ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ተወዳድረው ለመደልደል ፈቃደኛ የሆኑ፣ 5.  ለጤና የትምህርት ዘርፎች ዩኒቨርሲቲው የሚጠይቀውን ተጨማሪ ምዘና ማለፍ የሚችሉ፡፡ የማመልከቻ ቀናት፦ ከህዳር 20 እስከ 26/2016 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ፦ ህዳር 28 እና 29/2016 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ የትምህርት መስኮችን በተከታዩ ሊንክ ይመልከቱ፦ 👇 Click Join at and share 👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

ኘሮግራሙን የሚሰጥባቸው የትምህርት መስኮች እነዚህን ይመስላሉ።

📢 Department tip 🩻 RADIOLOGY ራዲዮሎጂስት በሕክምና  ምስል ላይ የተካነ የዶክተር ዓይነት ነው ፡፡ የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች የተለያዩ ሁኔታዎችን ወይም ጉዳቶችን ለመመርመር ፣ ለመቆጣጠር እና ለማከም የሚረዱ እንደ ኤክስ-ሬይ ያሉ ምስሎችን ይተነትናሉ ፡፡ የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ከሬዲዮግራፍ አንሺዎች የተለዩ ናቸው ፡፡ ምንም እንኳን እነዚህ ሁለቱም ባለሙያዎች ከህክምና ምስል ጋር የሚሰሩ ቢሆኑም የራዲዮግራፍ አንሺዎች ማሽነሪውን የሚሰሩ ሰዎች ናቸው ➻ለሬዲዮሎጂ ባለሙያ የሆነ ዶክተር ራዲዮሎጂስት ይባላል ፡፡ 🔬 የምርመራ ራዲዮሎጂ ባለሙያዎችን እና የሕክምና የፊዚክስ ባለሙያዎችን ጨምሮ የተለያዩ የራዲዮሎጂ ዓይነቶች አሉ ፡፡ የሚከተሉትን ጨምሮ በርካታ የተለያዩ የራዲዮሎጂ ልዩ ዓይነቶች አሉ ፡፡ ➾ዲያግኖስቲክ ራዲዮሎጂ ዲያግኖስቲክ ራዲዮሎጂስቶች በሽታዎችን ለመመርመር እና ለማከም የሕክምና ምስሎችን ይጠቀማሉ ፡፡ የተለያዩ: - ኤክስሬይ radionuclides አልትራሳውንድ የኤሌክትሮ ማግኔቲክ ጨረር ➾ጣልቃ ገብነት ራዲዮሎጂ ጣልቃ-ገብነት የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች ህክምና የሌላቸውን ችግሮች ላለባቸው ሰዎች ህክምና ለመስጠት የህክምና ምስሎችን ይጠቀማሉ ፡፡ ለምሳሌ ፣ ጣልቃ ገብነት የራዲዮሎጂ ባለሙያ የቀዶ ጥገና አሰራርን ለመደገፍ የሕክምና ምስሎችን ሊጠቀም ይችላል ፡፡ ይህ ምስል የቀዶ ጥገና አሰራሮችን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወደ ፈጣን የማገገሚያ ጊዜያት ሊያመራ ይችላል ፡፡ ጣልቃ ገብነት ራዲዮሎጂስቶች በተለምዶ በቁልፍ ቀዳዳ ቀዶ ጥገና ላይ ይሰራሉ ​​፡፡ የቁልፍ ጉድጓድ ቀዶ ጥገና በትላልቅ ሰዎች ምትክ ትናንሽ ቁርጥራጮችን መሥራት እና ጥቃቅን ካሜራዎችን በመጠቀም በሰውነት ውስጥ ማየትን ያካትታል ፡፡ ➾የጨረር ኦንኮሎጂ አንድ የጨረር ኦንኮሎጂስት ካንሰርን ለማከም በጨረር ላይ የተመሠረተ ሕክምናን ይጠቀማል ፡፡ ይህ ቴራፒ የካንሰር ሴሎችን ለመጉዳት ከፍተኛ የኃይል ጨረር መጠቀምን ያጠቃልላል ፣ ይህም ተጨማሪ እንዳይሰራጭ ያደርጋቸዋል ፡፡ ምልክቶችን ለመቀነስ ወይም በአንዳንድ ሁኔታዎች ሁኔታውን ሙሉ በሙሉ ለመፈወስ ይረዳል ፡፡ ➾የሕክምና ፊዚክስ የሕክምና የፊዚክስ ሊቃውንት የፊዚክስን ግንዛቤ በመጠቀም የህክምና ልምድን በተለያዩ መንገዶች ይደግፋሉ ፡፡ ለምሳሌ የታካሚዎችን ደህንነት እና የውጤቱን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሕክምና ምስል ቴክኒካዊ ገጽታዎች ላይ ምክር መስጠት እና ማድረስ ይችላሉ ፡፡ አንዳንድ የህክምና የፊዚክስ ሊቃውንት እንዲሁ ተመራማሪዎች በመሆናቸው አዲስ የህክምና ቴክኖሎጂን በማዳበር ሚና ይጫወታሉ ፡፡ የሕክምና የፊዚክስ ሊቃውንት በዛሬው ጊዜ ሐኪሞች በተለምዶ የሚጠቀሙባቸውን እንደ ማግኔቲክ ድምፅ ማጉላት ምስል (ኤምአርአይ) ያሉ ብዙ መሣሪያዎችን አፍርተዋል ፡፡ 👩‍🏫RADIOLOGIST ኦች የት መስራት ይችላሉ❓ 🔬 የራዲዮሎጂስቶች በክሊኒካዊ ጽ / ቤቶች ፣ በሆስፒታሎች ወይም በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ መሥራት ይችላሉ ፡፡ የራዲዮሎጂስቶች ሥራ እንደየራሳቸው ሥራ ይለያያል ፡፡ 🔬 ሁሉም የራዲዮሎጂስቶች የሚከተሉትን ያጠቃልላል በሕክምና ምስል አያያዝ ዘዴዎች የሚከተሉትን ያጠቃልላል ▸የተሰላ ቶሞግራፊ (ሲቲ) ▸መግነጢሳዊ ድምጽን መለዋወጥ ▸ፖታሮን ኢነርጂ ቶሞግራፊ (ፒኤስኤ) ▸X-rays ▸አልትራሳውንድ ▸የኑክሌር ሕክምና ▸የተመጣጠነ ምስሎች...     👩‍🏫 በ ቅድመ ምረቃ ዲግሪ መርሐ ግብር የስንት አመት ትምህርት ነው❓ ☘ሙሉ የሬዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን 13 ዓመታት ያህል ይወስዳል ነገር ግን እንደ ነዋሪነት ትክክለኛ የሬዲዮሎጂ ልምምድ 8 ብቻ ነው ፡፡ ☘የራዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን የሚወስደው መንገድ ረጅም እና ከባድ ነው ፡፡☺️ የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች በመጀመሪያ ከአራት ዓመት ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ማግኘት አለባቸው ፡፡ ከዚያ በኋላ የ 4 ዓመት የህክምና መርሃግብር መከተል እና የ 2 ዓመት የመማሪያ ክፍል ትምህርትን ፣ ከዚያም የ 2 ዓመት ክሊኒካል ልምዶችን እንደ የህፃናት ህክምና ፣ የአእምሮ ህክምና ፣ የቀዶ ጥገና እና የውስጥ ህክምና የመሳሰሉትን የሚያካትት የህክምና ማስተር ዲግሪያቸውን ማግኘት አለባቸው ፡፡ ☘የሕክምና ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ በሬዲዮሎጂ መስክ ስፔሻሊስት ሆነው የሬዲዮሎጂ ነዋሪዎችን ማጠናቀቅ አለባቸው ፡፡ ☘ነዋሪዎቹ ወደ ተለየ የራዲዮሎጂ subareas መዞር እና የራሳቸውን ምርምር ማካሄድ አለባቸው። ☘የራዲዮሎጂ ነዋሪነት ከ 4 እስከ 5 ዓመት ሊወስድ ይችላል ፡፡ በመቀጠል ፣ ብዙ የራዲዮሎጂስቶች ስፔሻሊስት ለመሆን የጓደኝነት ጓደኞችን ያጠናቅቃሉ ፡፡ ☘በተጨማሪም ፣ አዳዲስ የሕክምና ቴክኖሎጂዎች ብቅ ማለት ራዲዮሎጂስቶች ቀጣይ የትምህርት ትምህርቶችን እንዲወስዱ እና እውቀታቸውን በየጊዜው ለማቆየት ተጨማሪ ስልጠና እንዲያገኙ ይጠይቃል ፡፡ ☘ስለዚህ ፣ የሬዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን በአጠቃላይ እስከ 13 ዓመት ሊወስድ ይችላል ፡፡ ረዘም ያለ ብቃቶች ቢኖሩም የሬዲዮሎጂ ባለሙያ ለመሆን ቢያስፈልግዎትም ሥራው ራሱ ብዙ የገንዘብና የግል ጥቅሞችን ያስገኛል ፡፡ 👩‍🏫 በ RADIOLOGY የሙያ ዘርፍ ላይ ብቁ እና ስኬታማ የሆነ ባለሙያ ምን ምን ሙያዊ ተግባራትን ያከናውናል❓ ☘ የራዲዮሎጂ ባለሙያዎች የሕክምና ምስል (ራዲዮሎጂ) አካሄዶችን ( ምርመራዎችን) በመጠቀም ጉዳቶችን እና በሽታዎችን ለመመርመር እና ማከም፡፡ እንደ ኤክስ-ሬይ ፣ የታመቀ ቶሞግራፊ (ሲቲ)ማግኔቲቭ ሬንጅ ምስል (ኤምአርአይ) ፣ የኑክሌር መድኃኒት ፣ ሲቲ ፒትትሮን ኢነርጂ (ፒኤስኤ) እና አልትራ። 👩‍🏫  RADIOLOG ከባድ ነው ወይስ ቀላል🤔❓ ☘የራዲዮሎጂ ባለሙያ መሆን ምን ያህል ከባድ ነው? የራዲዮሎጂ ባለሙያ መሆን አንድ ሰው የባዮሎጂ ፣ የፊዚክስ ፣ የኬሚስትሪ እና የመድኃኒትን ውስብስብነት በጥልቀት እንዲረዳ የሚጠይቅ ከባድ ሥነ-ስርዓት ነው። የእነሱ ምስል ቴክኒኮችን እንዴት እንደሚሠራ እና ፊዚክስ እና ባዮሎጂ እንዴት እንደሚገናኙ ለማወቅ የራዲዮሎጂስቶች ስለ ፊዚክስ ብዙ ማወቅ አለባቸው። 👩‍🏫 ገቢውስ ምን ያክል ነው😋❓ ☘አጭጮርዲንግ ቶ Salary.com፣ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ለሬዲዮሎጂ ባለሙያው አማካይ ደመወዝ እስከ ግንቦት 414,890 ፣ ​​28 እ.ኤ.አ. ከ $ 2020 ዶላር ነው ፣ ግን አጠቃላይው መጠን ከ 360,690 እስከ 479,890 ዶላር ነው ፡፡ የደመወዝ ብዛት በትምህርት ፣ በብቃት ፣ ተጨማሪ ሙያዎች ፣ በሙያዎ ውስጥ ያሳለ numberቸውን ብዛት ጨምሮ በብዙ አስፈላጊ ነገሮች ላይ በመመስረት በስፋት ሊለያይ ይችላል ፡፡😚 ከማንኛውም ሌላ ድር ጣቢያ በበለጠ በእውነተኛ-ጊዜ እና በመስመር ላይ ካሳ ውሂብ አማካኝነት Salary.com ትክክለኛውን የካሳ ግብዎን እንዲወስኑ ያግዝዎታል። በሜድስፔክ ዓመታዊ የሕክምና ማካካሻ ሪፖርት መሠረት ራዲዮሎጂ በሦስቱ ከፍተኛ ደመወዝ ከሚከፈላቸው የሕክምና ባለሙያዎች መካከል ቦታውን እንደያዘ ይቆያል ፡፡ ©✍️ Posh tube ! ━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  | @assignment_supporter             @assignment_supportre https://t.me/assignment_supporter

ማስታወቂያ ** ኅዳር 20 ቀን 2016 ዓም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች  እንዲሁም በ2015 ዓ.ም በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ነባር የሬሜዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከታህሳስ 08-09/2016 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የምዝገባ ቦታ፦ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - በዋናው ግቢ  ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ማሳሰቢያ ====== ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡ • የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒውን፣ • ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒውን • አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ፣ የስፖርት ትጥቅ ከላይ ተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡       ሬጅስትራር እና አልሙኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት                         ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ                         ሁሌም ለልህቀት! https://t.me/assignment_supporter

✳️ ምክር ቢጤ ለ ፍሬሾች 📚 ግቢ ውስጥ አሁን ባላችሁበት Condition dorm ውስጥ እስከ ምትላመዱ ድረስ  ማንንም ማመን አትችሉም  ማንንም። ስለዚህ እንዝላል አትሁኑ...  ልብሳችሁን ፣ጓዛችሁን  ሎከራችሁ ውስጥ ቆልፉ፤ በፍጹም ስልክ Charger አድርጋችሁ እንዳትወጡ  ትበላላችሁ even ጓደኛየ Fresh እያለን ቻርጅ አድርጓ ተኝቶ ጥዋት ሲነሳ ስልኩ የለም ...ዶርም ውስጥ ያሉ ጓደኞቹን በሙሉ ቢጠይቃቸው አላየንም ነው ያሉት ቢከሳቸውም ምንም መፍትሄ አላገኘም ። ብቻ አንዴ አትበሉ እንጅ ከተሰረቃችሁ ምንም መፍትሄ የለም። ሌላው ከዚህ ላይ ማንሳት የምፈልገው  የDorm ቁልፍ ቀድሞ ከ dormu አባል ለመጣው ልጅ አንድ ብቻ ስለሚሰጣችሁ  እንደፈለጋችሁ Dorm ውስጥ መግባት መውጣት ላትችሉ ትችላላችሁ ፤ ልጁ ሳይኖር ሲቀር ሁሌ  እየደወላችሁ ና ክፈትልኝ ማለት ያሰጠላችኅል ። ይሄን ለማስቀረት ስትሉም ቁልፏን በሩ ታች ስር እያስቀመጣችሁ ትሄዳላችሁ ይህ ትልቅ ስህተት ነው ❌ almost all በሚባል መልኩ ይችን ሙድ ሁሉ ያውቃታል  እናንተን መስረቅ የሚፈልግ አካል መጀመሪያ በደንብ ነው የሚያጠናችሁ ከዛ መውጣታችሁን ጠብቆ ታች ቁልፏን አግኝቶ ቢገባስ?......እሽ ማድረግ ስላለባችሁ ወደ መፍትሄው እንሂድ 📌1 ህጋዊው መፍትሄ ቁልፍ የያዘውን ልጅ  ቁልፍ በመቀበል እየተቀባበላችሁ መጠቀም። ግን ይሄ በጣም አዝግ ነው  አስባችሁታል ሁሌ እሱን እየጠበቃችሁ ....🤔 📌2 ህጋዊ ያልሆነው መፍትሄ🙈 ቁልፍ ማስቀረጽ🤷🏾‍♂  ...ይሄን ሁሉ ተማሪ የሚያደርገው ነገር ነው። ከ University አቅራቢያ ስራየ ብለው የሚጠብቋችሁ ቁልፍ ቀራጮች አሉ ከነሱ Original ቁልፍን በማስቀረጽ የራሳችሁን መያዝ ትችላላችሁ ሁነኛ መፍትሄ ነው። ግን ፕሮክተር ከያዛችሁ🤦🏾‍♂ .... ልትፈርሙ ትችላላችሁ ከባድ Risk አለው። 📚 ከግቢ  ውጭ fresh አደላችሁ ከተማውን ለማየት ከ ግቢ መውጣታችሁ አይቀርም ...ግን አደራ ብቻችሁን ላለመውጣት ሞክሩ  በስርቆት PHD ያላቸው localሎች እናንተን እየጠበቁ ነው 😋 ፣ ድንቅ ቴክኒኮችን ተጠቅመው  እንዴት እንደሚሸውዷችሁ አታውቁትም .... ስልካችሁን ፣ብራችሁን በ ፍቃደኝነት አስረክባችሁ ነው ምትመጡት። የምሬን ነው ምላችሁ ጓደኛየን  እንዴት እንደበሉት ብነግራችሁ አንድ ሙሉ ድርሰት ይወጣዋል በ group ሁነው Drama ሰርተው እንዴት እንዳሳመኑት እነሱ እና ፈጣሪ ብቻ ነው ሚያውቀው ስልኩ የለ ብሩ የ እጅ ስሀቱ ሳይቀር አስረክቧቸው የመጣ። እና ለግዜው ከ localoch ብትርቁ መልካም ነው።ዘው ብለው እራሳቸው መጠው ካወሯችሁ ጠርጥሩ..... የቤተሰብነቴን እንዲህ አልኀችሁ መልካም ቀን!!  ━━━━━━━━━━━━━━━━━ ©keleme© 📚••𝐉𝐨𝐢𝐧 𝐮𝐬,  | @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter