fa
Feedback
Assignment supporters

Assignment supporters

رفتن به کانال در Telegram

ለ ሁሉም ነገር መፍትሄ አለው የማንኛውንም የትምህርት አይነት በ የትኛውም የክፍል ደረጃ የተሰጣችሁን assignment ከ አንድ ቀን ባነሰ ግዜ ውስጥ በ ከፍተኛ ጥራት እና ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሰራት ከፈለጉ ያናግሩን👇👇 @positive_thinkerrr ወይም 0994409904 ይደውሉ።

نمایش بیشتر
362
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
اطلاعاتی وجود ندارد30 روز
آرشیو پست ها
Mekele university አድራሻ ❓ 📚 በትግራይ ክልል ከአዲስ አበባ በ600 km አከባቢ ርቀት የምትገኝ ከተማ ነች መቀሌ ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 ሞቃታማ የምትባል ከተማ ነች ፤ በብዙ መልከ ደስ የሚሉ ህዝቦች ያሉባት ምርጥዬ ከተማ ናት ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በመቋሌ ዮኒቨርሲቲ 6 campus ኣሉ። 🎯 Social campus(ይሄ አዲ ሃቂ በሚባል ሰፈር ስለሚገኝ ወደ ፈለግከው ለመሄድ በጣም ኣመቺ ነው ። በቃ ራሱ ከተማ ማለት ነው ። 🎯 veterinary campus ፦ ይሄ ከከተማው ራቅ ይላል የህክምና ነክ ትምህርቶች የሚሰጡበት ግቢ ነው ። 🎯 mit (ይሄ ግቢ ተፈትነህ ነው ምትገባው እና ትንሽ ተማሪ ነው ሚቀበሉት ለቀለም ተማሪዎች ይመከራል)( ከ astu ጋ ተመሳሳይ ነው..!) 🎯arid ፦ የኣዘር ኣግሪ ግቢ ነው ግን በጣም ትልቅ ነው ። 🎯 ayder የmedicine ግቢ ነው ። 🎯 quiha ፦ የengineering ነው እና ኣዲስ ነው ከ ከተማ ትንሽ ራቅ ይላል ሁሉም ነገር ንፁህ ስለሆነ ደስ ይላል ። የካፌ ምግብ ❓ 📚 ምንም አይልም ፤ ለክፉ አይሰጥም ጥሩ የሚባል ትምህርት ጋር ስለሆነ በምግብ ብትጎዱም በማስተማር ይኩሳቹሃል ። የውሃ ፤ መብራት ፤ WIFI ❓ 📚 ውሃ በጣም ችግር ነው ለወር ገላችንን ሳንታጠብ አሳልፈን እናውቃለን ፤ ከተማዋ ላይ የውሃ ችግር ስላለ እዚም ያስቸግራል ። መብራት ጣጣ የለም ፤ ሁሌም አለ ፤ wIFi እንደ አቅሚቲ ለማስገባት ተሟክሯል ፤ መሻሻል ቢገባውም ያን ያክል የከፉ አይደለም ። ሽንት ቤት ❓ 📚ጥሩ ነው በንህፅና ለመያዝ ይሞከራል ፤ የውሃው ነገር እክን ቢሆንም የተሻለ ነገር አለው ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignmentsupporter https://t.me/assignment_supporter

#ዋቻሞ_ዩንቨርሲቲ አድራሻ ❓ 📚ከአዲስ አበባ 500 km አከባባ የምትርቅ ከተማ የሆነችው ሆሳዕና ላይ የሚገኝ የደቡብ ክልል ዮኒቨርስቲ ነው ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 መጀመሪያዎቹ ወራቶች በጣም ይበርዳሉ ሆኖም ግን ይለመዳል ፤ ከህዳር በኋላ ግን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ይሞቃል ። በተጨማሪም ከsecond semister በኋላ ዝናብ ስለሚበዛ ከሞቃታማ አካባቢ የምትመጡ ወንድም እህቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቹሃል ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሁለት ሲሆኑ እነሱርም፦ 🌴 Main campus ፡ የሚገኘው ሆሳዕና ከተማ ላይ ነው ። 🌴 Durame campus ፡ ይህ ግቢ ከዋናው ግቢ የ40ብር መንገድ ነው ። የተለያዮ ዲፓርትመንቶች አሉት ፦ ✅ Health and Medicine ✅ Engineering and Technology ✅ Business and Economics ✅ Other Social Science ✅ Agriculture ena Yemesaselutn የዮኒቨርሲቲው ሁኔታ ❓ 📚 Grade ላይ ትንሽ ችግር አለባቸው አስተማሪዎቹ hard ነገር ናቸው ። በተረፈ ግቢያችን ከሀገሪቱ ዩንቨርሲቲዎች አንፃር ሲታይ በተለይም ደግሞ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ ነው ማለት ይቻላል። ውሃ ፤መብራት እና WIFI ❓ 📚 ውሃ የለም በጣም ያስቸግራል ፤ ውሃ ባለመኖሩ ትንሽ ግቢው ሽታ አለው አንዳንድ አከባቢዎች ፤ መብራት ጥሩ ነው ፤ WIFI በቂ ባይባል ምንም አይልም በተለይ ማታ በፍጥነት ይሰራል ። ሽንት ቤት ❓ 📚 ሽንት ቤትም አስደሳች አይደለም ፤ በጣም የሚቸግረን ነገር እሱ ነው ፤ አርኪ አይደለም በጣም መሻሻል አለበት ። የፊልድ ምደባ ❓ 👉 Architecture መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ግቢው በቅድመ ፈተና አወዳድሮ ይቀበላል ። 👉 Medicine መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ ፍሬሽማን ኮርስ ስጨርሱ በመስፈርቱ መሰረት አወዳድሮ ተቀብሎ ያስተምራቹሃል ። 📚Medicine የሚገቡ ተማሪዎች የሚማሩት በንግስት ኢሌኒ ሪፈራል ሆስፒታል ሲሆን በግቢ ባስ እየተመላለሱ ይማራሉ ፤ አላለቀም እንጂ ለህክምና ተማሪዎች በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዶርም እየተሰራላቸው ነው ለጊዜው ግን እስከ አራተኛ አመት ድረስ በmain ግቢ እየተማሩ ነው ። 📚ከአዲስ አበባ ለምትመጡ ተማሪዎች ዩንቨርሲቲው የሚገኘው ከተማው መግቢያ አከባቢ በመሆኑ ግቢው በር ላይ መውረድ ትችላላችሁ ። የዕቃ ስርቆት ❓ 📚 ግቢውን እና ከተማውን በደንብ እስከምትለምዱት ድረስ ጎምቦር ፣ ሚካኤል እና ወንጂ ወደ ሚባሉት ሰፈሮች ባትሄዱ አሪፍ ነው ፤ ለምን መሰላቹልህ ብዙውን ጊዜ አንደኛ አመት ተማሪዎች በማን ላይ መተበት እንዳለባችሁና ከማን ጋር መቀለድ እንደሚገባ ስለማታቁ ነው ። ለማንኛውም ከሎካሎች ጋር ተጣላቹህ ማለት የግቢ እስረኛ ሆናቹህ ማለት ስለሆነ ብዙ አትፍጠኑ ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

Madda Walabo University አድራሻ ❓ 📚 ከአዲስ አበባ 429km ላይ በምትገኘዋ ባሌ ሮቤ ከተማ የሚገኝ ዮኒቨርሲቲ ነው ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 ብርዳማ ነው ግን ብዙም የሚካበድ አይደለም ወፍራም ልብስ መያዝ አለባቹህ እስክትለምዱት ድረስ ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሶስት ናቸው ። እነርሱም ፦ ✅ Main campus(Bale-Robe) ፡ የቴክኖ ግቢ ሲሄን በውስጡም የተለያዩ የትምህርት መስኮች ይገኛሉ። እነርሱም ፦ ➡ Engineering ⚡Civil engineering ⚡Cotem ⚡Electrical engineering ⚡Water engineering ⚡Mechanical engineering... ➡ Social science ➡Computer science ⚜IT ⚜IS ⚜CS ✅ ባሌ ጎባ(tena) - ከዋናው ግቢ የ5 ብር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ጎባ ላይ የሚገኝ ግቢ ነው ። በውስጡም ፦ 🏪Medicine 🏪HO 🏪Other science ✅ ሻሸማኔ ፡ Half of Social science students በዚ ግቢ ይገኛሉ ። የዮኒቨርስቲው ሁኔታ ❓ 📚 ግቢዎቹ በሙሉ የሌለ ሰላም ናቸው ፤ የሀገሩ ሰውም በጣም ምርጥ ነው ፤ ትምሮ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም ለጨባሽ ተማሪዎች በጣም አዛ ነው በተጨማሪም የተማሪው ቁጥር ይወስናል ፤ ብዙ ተማሪ ከተቀበሉ ትምሮውን ያከብዱታል ይሄ ደግሞ የተለመደ አሰራር ነው በሁሉም ግቢዎች ። የካፌው ምግብ ❓ 📚 የካፌ ምግብ ብዙም አይደለም፤ ለመበላት ትኝሽ የሚከብድ ነገር አለው በተለይ ከከተማ ለመጣ እና የጣፈጠ ነገር ለለሠደ ምንም አይመችም ። ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓ 📚 ግቢ ውስጥ 3 ላውንቾች (ምግብ ቤቶች) ምናምን ይገኛሉ ፤ እነሱን እንደ አማራጭ መጠቀም ይቻላል ። ከግቢ ውጭ ያሉ ምግብ ቤቶች ዋጋ እንደየጊዜው ተለዋዋጭ ነው ባጭሩ ከ 15-25 ባለው ዋጋ ይጠቃለላሉ። ሽንት ቤት ❓ 📚 አያሳስብም ጥሩ የሚባል ሽንትቤት አለ ፤ ፀዴ ባይሆንም ለክፉ አይሰጥም ...! ውሃ ፤መብራት ፤ WIFI ❓ 📚 ትንሽ ዋይፋይ ነው እንጂ መብራት እና ውሃ ፍፁም አይጠፋም ፤ በውሃ እና መብራት ችግር ግቢው ስሙ አይጠቀስም ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ አድራሻ ❓ 📚ጎንደር ከአዲስ አበባ በ727km ርቀት ላይ ትገኛለች። ከአዲስ ጎንደር በሀገር አቋራጭ ባስ ማለትም ሰላም ባስ ምናምን ከተጓዝን በአንድ ቀን እንደርሳለን። ወይም ደግሞ ከአዲስ አበባ ከመናሀርያ ወደ ባህርዳር ተጉዘን ከዛም በባህርዳር አድረገን ወደ ጎንደር መምጣት እንችላለን።፤ ነገር ግን የመጀመሪያውን ምርጫ ብትጠቀሙ ይሻላል፤ ወጪ እንዳይበዛባችሁም ከእንግልት ለመዳንም ከላይ የተዘረዘሩትን በባሶች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው። 📚 በplane መምጣት ለምትፈልጉ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በደቂቃዎች ውስጥ ጎንደር አየር ማረፊያ መድረስ ይችላሉ። it takes only 41 min ፤ ዋጋው ከ1800 - 2500 ድረስ ኢትዮ አየር መንገድ ያስከፍላል ። የአየሩ ሁኔታ ❓ 📚 ጎንደር በሰሜን ኢትዮጵያ ስለምትገኝ በጣም ከፍታ ቦታ ላይ ነች። ይህም የጎንደርን አየር ቀን ቀን ፀሐያማ መሸት ሲል ደግሞ ብርዳማ እንዲሆን አድረጎታል so ከቤታችሁ ስትመጡ ሹራብ ነገር ብትይዙ ይመረጣል። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዋናነት አምስት ጊቢዎች አሉት ፦ እነርሱም 1, GC ግቢ <health science college> 2. Fasil ግቢ <Engineering science> 3. ቴዲ <all natural science> except eng. Science, health science, and agr. Science. 4. ማራኪ ግቢ< all social science> 5, ጤዳ ግቢ<agricultural science> 📚 ማራኪ ፤ ቴዲ ቨተርነሪ እና ፋሲል ጊቢ የተያያዙ ጊቢዎች ሲሆኑ ጠዳ እና Health ጊቢ ደሞ የተለየ ቦታ ነው ያሉት ፡፡ የዕቃ ስርቆት ጉዳይ ❓ ⚠️ማስጠንቀቂያ ከመናኸሪያ ወደ ግቢ በምትሄዱበት ወቅትና ግቢ ከገባቹህ በኋላ ወደ ከተማ ምናምን ስትወጡ ንብረቶቻችሁን በንቃት መጠበቅ ይኖርባቹሃል ምክንያቱም ከተማው ላይ አዲስ ተማሪዎችንና የግቢ ተማሪዎችን የሚሰርቁ የተደራጁ ሌቦች አሉ ። የትምህርት ዘርፎች ❓ ❄ Health science college በሀገራችን ቀደምት ከመሆኑ የተነሳ በሀገርቱ ካሉ universityዎች አሪፍ የሚባል የትምህርት አሠጣጥ አለው ፤በhealth science college የተዋጣለት ግቢ ነው ። ✅ Engineering science የተከፈተው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም እንኳ በሀገራችን ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመርያውን ደረጃ የሚይዝ campus ነው። በውስጡ 8 የተለያዩ departments አሉ ፦ 1. Electrical and computer Engineering 2. Biomedical Engineering 🆕 3. Chemical Engineering 4. Mechanical Engineering 5. Civil Engineering 6. Construction management Engineering (cotem) 7. Industrial Engineering 8. Hydraulics Engineering 📚 ሲሆኑ ምናልባት ቀጣይ አመት የሚጨመሩ departments ይኖራል የሚል ተስፋ አለ። በተጨማሪም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ Engineering science ለተከታታይ 3 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዪኒቨርሲቲዎች 1ኛ በመውጣት ሃትሪክ ሰርቷል። ዩንቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ የካበተ ልምድ እና ዝና ያለው ሲሆን ደግሞ ለtechnology(engineering and CS) more ትኩረት እየሰጠ ይገኛል። 📚 first semester engineering courses ፦ 1.Applied one ( maths guide book ካላቹህ እንዳትረሱ) 2.mechanics 3.Drawing(drawing material እንዳትረሱ) 4.Communicative( English) 5.Civics 6. Engineering profession የካፌ ምግብ ❓ 📚 ጣፍጦም ባይሆን ይበላል ፤ ምንም አይልም ቀን ቀን አላቸው የሚደብሩ ምግቦች የሚቀርብበት ...! ከካፌ ውጪ ስላሉ ምግብ ቤቶች ❓ 📚 Non ካፌ ተማሪዎች ፋሲል ግቢ ውስጥ ወደ 4 ላውንጆች አሉ ፤ከአራቱ ላውንቾች ውስጥ አንዱ አሪፍ ሚባልው 600 ብር አከባቢ ወርሃዊ ኮንትራት ነው ምሳ እና እራት ብቻ ያካተተ ኮንትረት ነው ። ፋሲል Launge ፦ 1. በየአይነት 40-50 birr 2. ሽሮ 50 birr 3. የፍስክ ምግብ ከ60-70birr መምህራን launge ፦ 1. የፆም ከ40-80 ብር 2. የፍስክ ከ50-80 ብር ዋና launge ፦ 📚ይህ ምግብ ቤት ዋጋው ከመምህራን ላውንጅ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ምግባቸው ግን 1ኛ ነው ። ሽንት ቤት ❓ 📚 አሪፍ ነው ፤ ምንም አይልም .! ውሃ ፤ መብራት ፣ WIFI ❓ 📚 WIFI በጣም ገራሚ ነው ፤ የትኛውም ካንፓስ በሌለ ፍጥነት ነው የሚሰራው ፤ ውሃ እና መብራት የሀገሪቷ ችግር ስለሆነ አንዳንዴ ይጠፋል የሚያሳስብ ግን አይደለም ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

WELKITIE UNIVERSITY አድራሻ ❓ ደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ትገኛለች ። ከአዲስ አበባ የ85 ብር መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል ከተመሰረተ 10 አመቱን አስቆጥሯል ፤ በ 2004 ነበር የተመሰረተዉ ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 አየሩ አሪፍ የሚባል ነው ግን መጀመርያ አከባቢ ይሞቃል ፤ ለሴቶች ጥላ ነገር መያዝ ይኖርባቹሃል ትንሽ ፀሃዩ ያቃጥላል ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎችሁለት ብቻ ናቸው ። እነርሱም textile and main ይባላሉ ። ♨ textile ግቢ ከተማ ዉስጥ ያለ ሲሆን በውስጡም 🌻Textile 🌻Garment and 🌻 designing( exam አለው በፈተና ነው የሚገባው ። ) ✅MAIN ግቢ ፦ 📚 ከከተማዋ የ10 ብር ትራንስፖርት ሲሆን ጉብሬ የሚባል SUB CITY ቦታ ላይ ይገኛል ፤በዉስጡ ያሉት ዲፓርትመንቶች ደሞ ፦ 👉Engineering and Technology ✍civil ✍chemical ✍ Electrical ✍food process ✍HWRE(water) ✍mechanical ✍ cotm ✍architecture (ፈተና አለው በውድድር ነው ሚገባው..!) ⚠️ Note ፦ ▶ምህንድስና ክፍል ላይ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በጣም አሪፍ ነው ። 👉computer science ✍Software ✍ CS (computer science) ✍IS( Information system) ✍IT( Information technology) 👉 social science ✍midwifery ✍ nursing ✍FB ✍Law ✍Psychology ... 👉social/natural comptitional ✍ Mathematics ✍Sport ✍ Physics Health HO .. 🏩Medicine --> እስካሁን ግን በህክምና አላስመረቀም ገና ተቀብሎ በማስተማር ላይ ነው ። የካፌ ምግብ ❓ 📚 ምሳ ላይ በሳምንት ሶስት ቀን ዜrፎr (ስጋ ጣል ጣል) አለ ፤ አትክልትም አለ ግን ብዙም አይነፋም ፦ 🍛ምስር ፣ 🍳 ክክ እና 🍲 አሪፍ ሽሮ የምሳ ምግቦች ናቸው ። ቁርስ ደግሞ ፦ ፍርፍር ፤ ሩዝ እና ቅንጬ ይቀርባል ። ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓ 📚ግቢ ውስጥ 3 ላዉንቾች (ምግብ ቤቶች) አሉ ፤ ዋጋቸዉም 🍥በያይነት 13-15 🍥ፓስታ በሱጎ 13 🍥ፓስታበአትክልት 13-15 ነው ፤ በጣም ተመጣኝ ነው ። Non ካፌ ተማሪዎች ኩፖን ከገዛቹህ 12.5-13.5 ነው ። ☕ቡና 2.5 ☕ሻይ 1.5 ☕ቀሽር 3 ☕ስፕሪስ 3 ⚠️ Note ▶ 📚ካፌ ላይ ጨጓራ ምናምን ላለባቹህ ልጆች special ቡፌ አለ ከክሊኒክ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ከሆነ ያበደ ምግብ ይበርብላችሀዋል ። የግቢው ክሊኒክ ❓ 📚 ክሊኒክ በመሻሻል ላይ ቢሆንም እንደማንኛውም ግቢ ደስ የማይል ነገር አለው ፣ ከፓራስታሟል የተሻለ ኪኒን የላቸውም ። ውሃ ፤ መብራት እና WIFI ❓ 📚 ውሃ በፈረቃ ይለቀቃል ካልተለቀቀ ላውንች አካባቢ እንደልብ ስለሚገኝ ጣጣ የለም ፤ መብራትም አይጠፋም ፤ WIFi ትንሽ አዛ ነው ፤ ይሻሻላል የሚል ነገር አለ ። ሽንት ቤት ❓ 📚 ግቢው በዚ ላይ ችግር አለበት ደስ አይልም ፤ ይደብራል ፤ ማሻሻል ያለበት ነገር ነው ። የዶርም ሁኔታ ❓ 📚 ዶርምም ብዙም አያስደስትም ግን የብዙዎቹ ግቢዎች ችግር ስለሆነ ምንሞ አይደረግም መቻል ነው ። የዕቃ ስርቆት ❓ 📚 ግቢ ዉስጥ እና በዙሪያው አስፈሪ ነገር የለም ። ሰላማዊ ከተማ ነው ። ሀይማኖታዊ ተቋማት ❓ 📚 እንደሌሎች ግቢዎች ሃይማኖታዊ ተቋማት በቅርቡ ስለሚገኙ ምንም ዓይነት ጭንቅ እንዳይሰማቹህ ፤ እንደሙዳችሁ አለ ። ማሳሰቢያ ❗️ ⚠⚠⚠⚠⚠⚠ℹ 📚 በነገራችን ላይ ግቢው ዲሲፕሊን ላይ በጣም ሃርድ ነው medicine በተቀበል በ መጀመርያው አመት 16 medicine ተማሪዎችን አባሯል ፤ በዲሲፕሊን ምክንያት ማለት ነው ፤ እንዲሁም ሊመረቅ ሳምንት የቀረዉም ልጅ አባሯል እና ተማሪዎች ግድ ጸባያቸዉን ማስተካከል አለባቸዉ በተልይ ድብድብ ፤ጫት ፤ሲጋራ ምናምን ከባድ penalty አላቸው ። ሌላ ደሞ አንዳንድ ፍሬሽ ተማሪዎች ሊጠነቀቁ የሚገባቸዉ ነገር ጫት በብዛት ስላለ እንዳይሸወዱ ፤ በተለይ ጉብሬ ግቢ የሚደርሳቹህ ተማሪዎች በርጫ በበርጫ ስለሆነ ሀገሩ እንዳትዘናጉ ለማለት ነው ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

◦•●◉✿[ Dilla University ]✿◉●•◦ ዲላ ዩኒቨርስቲ ከአድስ አበባ 360ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 👉የአየሩ ሁኔታ ሚካበድ ሙቀት የለም ግቢው በጣም አርንጓዴ ነው ግን ከግቢው ውጪ ፀሃይ አለ፤በተወሰነ መልኩ ሞቃት ነው ለመልመድ ግን አይከብድም በውስጡ ያሉ ግቢዎች፡ ሶስት Techno: Engineering, CS Main :agree, physics... and Tena gbi: social... ትምሮ በጣም አይከብድም ግን እንድታጠኑ በትንሹ ለማጨናነቅ ይሞክራሉ ፤ በተረፈ እንደማንኛውም ግቢ ካልቸከልክ ትጫራለህ 👉የምግብ ቤቶች ዋጋ ባንፃራዊነት በጣም አሪፍ ና ተመጣጣኝ ነው ዋጋ 15–17 ብር ነው 👉የቡና ዋጋ ከ 3–5 ብር ነው በጣም አሪፍ የጨፌ ቡና ዲላ ይገኛል☕☕☕☕ 👉የካፌ ምግብ ብዙም አይደለም፤ ከግቢ ውጭ ግን አሪፍ ምግብ ቤቶች አሉ ከ13ብር ጀምሮ🍚🍟🍔🍕🍜 👉ፍርፍር በጣም ርካሽ ነው🍜🍜🍜🍜 👉ሙዝ የአንድ ብር አምስት ፍሬ 🍌🍌🍌 👗👟👞🎩👗👕👡👠👢👕👖🎒👔👚👘👚 👌 ያው ኑሮ በ ዲላ ርካሽ ነው የተለያዩ ኮንትሮባንድ እቃዎች ይገኛሉ 💍ልብስ እና ጫማም በጣም ርካሽ ነው ባጠቃላይ ትወዱታልቹህ ውሃ መቼም አይጠፋም ሻወር 24 ሰዓት መጠቀም ይቻላል፤ ዋን ለሜ ምንጭ እያለች ዲላ የውሃ ችግር አይታሰብም። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter or https://t.me/assignmentsupporter

ድሬዳዋ university፦ አድራሻ ❓ 📚 በድሬደዋ ከተማ የምትገኝ ፍቅር ነሆነች ዮኒቨርስቲ ነች ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 ሞቃታማ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ፦ ወፍራም ብርድልብስ አያስፈልግም ፤ አንሶላ እና አልጋ ልብስ በቂ ነው፤ የመጀመሪያዎቹን አራት ወራት ትንሽ ሊበርድ ይችላል ፡ ግንቦት ላይ ምናምን ግን በጣም ሞቃት ነው። የካንፓስ ብዛት ❓ 📚 ድሬ አንድ ግቢ እና ሶስት መግቢያ መውጫ በር ያለው ሲሆን ሁሉም filed of study እዛው ነው የሚሰጠው ሌላ ቅርንጫፍ የለውም ። 🎯 በተጨማሪም ሶስት ላይብራሪ ያለ ሲሆን እነሱም፦ 🏩 Tecno 🏩 Main 🏩 Fb/keranyo ✅ የሚሰጡ ፊልዶች በጥቂቱ ፦ 🌐IOT 🌐FBE 🌐other social science 🌐Computitional science 🌐Fashion design 🌐Architecture 🌐 Engineering 🗻Engineering fileds 1 mechanical 2 electrical 3 chemical 4 civil 5 textile 6 cotm 7 food 8 industrial 9 survey 📚 arcthicure and Medicine መግባት ለምትፈልጉ መግቢያ ፈተናና የEntrance ውጤትም ይታያል።Software engineering የለም ። 📚 FB ( faculty of business) total social fileds House of medicine ፤ ሁሉንምhealth science ያጠቃልላሉ ። 📚 Architecture and Fashion design መግባት የምትፈልጉ የመግቢያ ፈተና ስላለው እዛያሉ ሲኒየር ተማሪዎችን ስለፈተናው ኢንፎ ብትጠይቁ አሪፍ ነው ። Marketing መግባት ለምትፈልጉ ደግሞ ድሬ ላይ ልብስ ጫማና ምግብ ቅናሽ ነው ። የካፌ ምግብ ❓ 📚 ድሮ አዛ ነበር አሁን ግን በጣም ምርጥዬ ሆኗል ፤ በቃ ኢትዮጵያ ውስጥ አሪፍ ከሚባሉት አንዱ ነው ። ኀከካፌ ምግብ ውጪ ❓ 📚ምግብ ቤቶች ብዙም ውድ አይባሉም አሪፍ ነው። 🎯 ፍርፍር 11-15ብር 🎯 ፓስታ 13/15ብር 🎯 ድንች ለብለብ/ሰላጣ 11ብር 🎯 በአይነት...--------12ብር ከግቢ ውጭ 25ብር 🎯 ቡና 4ብር ------------6 /7 ከግቢ ውጭ 🎯 ሻይ 1.5 or 2---------3/4 ከግቢ ውጭ ሌላውም fair ነው ። ዶርም እና ሽንት ቤት ❓ 🎯 የዶርም እና የሽንትቤት ነገር አስደሳች አይደለም ስለ ግቢው ሁኔታ ብዙ ደስ የሚል ነገር አትጠብቁ ፤ በጣም አስጠሊ ነው ። የትምህረት ሁኔታ ❓ 📚የትምህርት አሰጣጡ ምናምን በጣም አሪፍ ነው፥ ላይፉም ሙድ አለው ብቻ እናንተ ኑ ፤ የድሬ ሰዎችም ሲበዛ ፍቅር ናቸው ይህን ስትመጡ ትመሰክራላችሁ ። የዕምነት ቦታ ❓ 📚መስጂድ እና ቤተ-ክርስቲያንም በግቢው አቅራቢያ ስለሚገኝ ይበልጥ ትወዱታላቹህ ። የረብሽ ጉዳይ ❓ 📚 አልፎ አልፎ አንዳንድ አለመረጋጋቶች ይከሰታሉ ፤ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ወደ መስጂዶችና ውደ ቤተ- ክርስቲያናት በመሄድ ራሳቸውን ከአላስፈላጊ እንግልትና ከፌደራል ዱላ ይከላከላሉ ። በአመት አንዴም ሁለቴም ግርግር አይጠፋም ። የዕቃ ስርቆት ❓ 📚 ወደ ድሬ ስትመጡ መጀመሪያ ቀጥ ብላቹህ ወደ ግቢ ግቡ ፤ ፍሬሽ ተማሪዎች ሲመጡ በየመንገዱና በመናሀሪያ በተለይም በታክሲ(ባጃጅ) ላይ ምናምን የናንተን መፍዘዝ ready ሆነው የሚጠብቁ ብዙ ሌቦች አሉ። አሸዋ ገራሚ የዝርፊያ ቦታ ነው በተለይ ጫማ ምናምን ለመግዛት ስትሄዱ ፤ ሰባተኛ፡ ማታ ማታ walk ለማድረግ ስትፈልጉ ፤ seido፡ ቀን ላይ እነዚህን ሰፈሮች በጥንቃቄ ማለፍ ይኖርባቹሃል ። በተለይ ስልክን ገንዘባችሁን ተጠንቀቁ...! ጫት እና ድሬ ❓ 🌲 ድሬ ከተማ ላይ እንደምታቁት ጫት ከምግብ በላይ አንገብጋቢና በጣም ወሳኝ ምግብ ነው ሆኖም ግን ለግቢ ተማሪዎች ጫት ስለማይመከር ለቅምሻም ቢሆን እንዳትሞክሩ። እመኑኝ የድሬ ጫት ከጥፍጥናው የተነሳ ሱስ ያሲዛል(አሉ)....! የውሃ እና መብራት ጉዳይ ❓ 📚ውሃ እና መብረት አያሳስብም ጨቅ ነው ። ትንሽ WIFI ነው እንጂ አዛ የሚያደርገው....! N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

#ዋቻሞ_ዩንቨርሲቲ አድራሻ ❓ 📚ከአዲስ አበባ 500 km አከባባ የምትርቅ ከተማ የሆነችው ሆሳዕና ላይ የሚገኝ የደቡብ ክልል ዮኒቨርስቲ ነው ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 መጀመሪያዎቹ ወራቶች በጣም ይበርዳሉ ሆኖም ግን ይለመዳል ፤ ከህዳር በኋላ ግን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ይሞቃል ። በተጨማሪም ከsecond semister በኋላ ዝናብ ስለሚበዛ ከሞቃታማ አካባቢ የምትመጡ ወንድም እህቶች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባቹሃል ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሁለት ሲሆኑ እነሱርም፦ 🌴 Main campus ፡ የሚገኘው ሆሳዕና ከተማ ላይ ነው ። 🌴 Durame campus ፡ ይህ ግቢ ከዋናው ግቢ የ40ብር መንገድ ነው ። የተለያዮ ዲፓርትመንቶች አሉት ፦ ✅ Health and Medicine ✅ Engineering and Technology ✅ Business and Economics ✅ Other Social Science ✅ Agriculture ena Yemesaselutn የዮኒቨርሲቲው ሁኔታ ❓ 📚 Grade ላይ ትንሽ ችግር አለባቸው አስተማሪዎቹ hard ነገር ናቸው ። በተረፈ ግቢያችን ከሀገሪቱ ዩንቨርሲቲዎች አንፃር ሲታይ በተለይም ደግሞ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ፍፁም ሰላማዊ ነው ማለት ይቻላል። ውሃ ፤መብራት እና WIFI ❓ 📚 ውሃ የለም በጣም ያስቸግራል ፤ ውሃ ባለመኖሩ ትንሽ ግቢው ሽታ አለው አንዳንድ አከባቢዎች ፤ መብራት ጥሩ ነው ፤ WIFI በቂ ባይባል ምንም አይልም በተለይ ማታ በፍጥነት ይሰራል ። ሽንት ቤት ❓ 📚 ሽንት ቤትም አስደሳች አይደለም ፤ በጣም የሚቸግረን ነገር እሱ ነው ፤ አርኪ አይደለም በጣም መሻሻል አለበት ። የፊልድ ምደባ ❓ 👉 Architecture መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ግቢው በቅድመ ፈተና አወዳድሮ ይቀበላል ። 👉 Medicine መማር ለምትፈልጉ ተማሪዎች ደግሞ ፍሬሽማን ኮርስ ስጨርሱ በመስፈርቱ መሰረት አወዳድሮ ተቀብሎ ያስተምራቹሃል ። 📚Medicine የሚገቡ ተማሪዎች የሚማሩት በንግስት ኢሌኒ ሪፈራል ሆስፒታል ሲሆን በግቢ ባስ እየተመላለሱ ይማራሉ ፤ አላለቀም እንጂ ለህክምና ተማሪዎች በሆስፒታሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዶርም እየተሰራላቸው ነው ለጊዜው ግን እስከ አራተኛ አመት ድረስ በmain ግቢ እየተማሩ ነው ። 📚ከአዲስ አበባ ለምትመጡ ተማሪዎች ዩንቨርሲቲው የሚገኘው ከተማው መግቢያ አከባቢ በመሆኑ ግቢው በር ላይ መውረድ ትችላላችሁ ። የዕቃ ስርቆት ❓ 📚 ግቢውን እና ከተማውን በደንብ እስከምትለምዱት ድረስ ጎምቦር ፣ ሚካኤል እና ወንጂ ወደ ሚባሉት ሰፈሮች ባትሄዱ አሪፍ ነው ፤ ለምን መሰላቹልህ ብዙውን ጊዜ አንደኛ አመት ተማሪዎች በማን ላይ መተበት እንዳለባችሁና ከማን ጋር መቀለድ እንደሚገባ ስለማታቁ ነው ። ለማንኛውም ከሎካሎች ጋር ተጣላቹህ ማለት የግቢ እስረኛ ሆናቹህ ማለት ስለሆነ ብዙ አትፍጠኑ ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

Madda Walabo University አድራሻ ❓ 📚 ከአዲስ አበባ 429km ላይ በምትገኘዋ ባሌ ሮቤ ከተማ የሚገኝ ዮኒቨርሲቲ ነው ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 ብርዳማ ነው ግን ብዙም የሚካበድ አይደለም ወፍራም ልብስ መያዝ አለባቹህ እስክትለምዱት ድረስ ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎች ሶስት ናቸው ። እነርሱም ፦ ✅ Main campus(Bale-Robe) ፡ የቴክኖ ግቢ ሲሄን በውስጡም የተለያዩ የትምህርት መስኮች ይገኛሉ። እነርሱም ፦ ➡ Engineering ⚡Civil engineering ⚡Cotem ⚡Electrical engineering ⚡Water engineering ⚡Mechanical engineering... ➡ Social science ➡Computer science ⚜IT ⚜IS ⚜CS ✅ ባሌ ጎባ(tena) - ከዋናው ግቢ የ5 ብር ርቀት ላይ በምትገኘዋ ጎባ ላይ የሚገኝ ግቢ ነው ። በውስጡም ፦ 🏪Medicine 🏪HO 🏪Other science ✅ ሻሸማኔ ፡ Half of Social science students በዚ ግቢ ይገኛሉ ። የዮኒቨርስቲው ሁኔታ ❓ 📚 ግቢዎቹ በሙሉ የሌለ ሰላም ናቸው ፤ የሀገሩ ሰውም በጣም ምርጥ ነው ፤ ትምሮ ብዙም አስቸጋሪ አይደለም ለጨባሽ ተማሪዎች በጣም አዛ ነው በተጨማሪም የተማሪው ቁጥር ይወስናል ፤ ብዙ ተማሪ ከተቀበሉ ትምሮውን ያከብዱታል ይሄ ደግሞ የተለመደ አሰራር ነው በሁሉም ግቢዎች ። የካፌው ምግብ ❓ 📚 የካፌ ምግብ ብዙም አይደለም፤ ለመበላት ትኝሽ የሚከብድ ነገር አለው በተለይ ከከተማ ለመጣ እና የጣፈጠ ነገር ለለሠደ ምንም አይመችም ። ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓ 📚 ግቢ ውስጥ 3 ላውንቾች (ምግብ ቤቶች) ምናምን ይገኛሉ ፤ እነሱን እንደ አማራጭ መጠቀም ይቻላል ። ከግቢ ውጭ ያሉ ምግብ ቤቶች ዋጋ እንደየጊዜው ተለዋዋጭ ነው ባጭሩ ከ 15-25 ባለው ዋጋ ይጠቃለላሉ። ሽንት ቤት ❓ 📚 አያሳስብም ጥሩ የሚባል ሽንትቤት አለ ፤ ፀዴ ባይሆንም ለክፉ አይሰጥም ...! ውሃ ፤መብራት ፤ WIFI ❓ 📚 ትንሽ ዋይፋይ ነው እንጂ መብራት እና ውሃ ፍፁም አይጠፋም ፤ በውሃ እና መብራት ችግር ግቢው ስሙ አይጠቀስም ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ አድራሻ ❓ 📚ጎንደር ከአዲስ አበባ በ727km ርቀት ላይ ትገኛለች። ከአዲስ ጎንደር በሀገር አቋራጭ ባስ ማለትም ሰላም ባስ ምናምን ከተጓዝን በአንድ ቀን እንደርሳለን። ወይም ደግሞ ከአዲስ አበባ ከመናሀርያ ወደ ባህርዳር ተጉዘን ከዛም በባህርዳር አድረገን ወደ ጎንደር መምጣት እንችላለን።፤ ነገር ግን የመጀመሪያውን ምርጫ ብትጠቀሙ ይሻላል፤ ወጪ እንዳይበዛባችሁም ከእንግልት ለመዳንም ከላይ የተዘረዘሩትን በባሶች ብትጠቀሙ አሪፍ ነው። 📚 በplane መምጣት ለምትፈልጉ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በደቂቃዎች ውስጥ ጎንደር አየር ማረፊያ መድረስ ይችላሉ። it takes only 41 min ፤ ዋጋው ከ1800 - 2500 ድረስ ኢትዮ አየር መንገድ ያስከፍላል ። የአየሩ ሁኔታ ❓ 📚 ጎንደር በሰሜን ኢትዮጵያ ስለምትገኝ በጣም ከፍታ ቦታ ላይ ነች። ይህም የጎንደርን አየር ቀን ቀን ፀሐያማ መሸት ሲል ደግሞ ብርዳማ እንዲሆን አድረጎታል so ከቤታችሁ ስትመጡ ሹራብ ነገር ብትይዙ ይመረጣል። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በዋናነት አምስት ጊቢዎች አሉት ፦ እነርሱም 1, GC ግቢ <health science college> 2. Fasil ግቢ <Engineering science> 3. ቴዲ <all natural science> except eng. Science, health science, and agr. Science. 4. ማራኪ ግቢ< all social science> 5, ጤዳ ግቢ<agricultural science> 📚 ማራኪ ፤ ቴዲ ቨተርነሪ እና ፋሲል ጊቢ የተያያዙ ጊቢዎች ሲሆኑ ጠዳ እና Health ጊቢ ደሞ የተለየ ቦታ ነው ያሉት ፡፡ የዕቃ ስርቆት ጉዳይ ❓ ⚠️ማስጠንቀቂያ ከመናኸሪያ ወደ ግቢ በምትሄዱበት ወቅትና ግቢ ከገባቹህ በኋላ ወደ ከተማ ምናምን ስትወጡ ንብረቶቻችሁን በንቃት መጠበቅ ይኖርባቹሃል ምክንያቱም ከተማው ላይ አዲስ ተማሪዎችንና የግቢ ተማሪዎችን የሚሰርቁ የተደራጁ ሌቦች አሉ ። የትምህርት ዘርፎች ❓ ❄ Health science college በሀገራችን ቀደምት ከመሆኑ የተነሳ በሀገርቱ ካሉ universityዎች አሪፍ የሚባል የትምህርት አሠጣጥ አለው ፤በhealth science college የተዋጣለት ግቢ ነው ። ✅ Engineering science የተከፈተው በቅርብ ጊዜ ቢሆንም እንኳ በሀገራችን ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመርያውን ደረጃ የሚይዝ campus ነው። በውስጡ 8 የተለያዩ departments አሉ ፦ 1. Electrical and computer Engineering 2. Biomedical Engineering 🆕 3. Chemical Engineering 4. Mechanical Engineering 5. Civil Engineering 6. Construction management Engineering (cotem) 7. Industrial Engineering 8. Hydraulics Engineering 📚 ሲሆኑ ምናልባት ቀጣይ አመት የሚጨመሩ departments ይኖራል የሚል ተስፋ አለ። በተጨማሪም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ Engineering science ለተከታታይ 3 አመት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ዪኒቨርሲቲዎች 1ኛ በመውጣት ሃትሪክ ሰርቷል። ዩንቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ የካበተ ልምድ እና ዝና ያለው ሲሆን ደግሞ ለtechnology(engineering and CS) more ትኩረት እየሰጠ ይገኛል። 📚 first semester engineering courses ፦ 1.Applied one ( maths guide book ካላቹህ እንዳትረሱ) 2.mechanics 3.Drawing(drawing material እንዳትረሱ) 4.Communicative( English) 5.Civics 6. Engineering profession የካፌ ምግብ ❓ 📚 ጣፍጦም ባይሆን ይበላል ፤ ምንም አይልም ቀን ቀን አላቸው የሚደብሩ ምግቦች የሚቀርብበት ...! ከካፌ ውጪ ስላሉ ምግብ ቤቶች ❓ 📚 Non ካፌ ተማሪዎች ፋሲል ግቢ ውስጥ ወደ 4 ላውንጆች አሉ ፤ከአራቱ ላውንቾች ውስጥ አንዱ አሪፍ ሚባልው 600 ብር አከባቢ ወርሃዊ ኮንትራት ነው ምሳ እና እራት ብቻ ያካተተ ኮንትረት ነው ። ፋሲል Launge ፦ 1. በየአይነት 40-50 birr 2. ሽሮ 50 birr 3. የፍስክ ምግብ ከ60-70birr መምህራን launge ፦ 1. የፆም ከ40-80 ብር 2. የፍስክ ከ50-80 ብር ዋና launge ፦ 📚ይህ ምግብ ቤት ዋጋው ከመምህራን ላውንጅ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ምግባቸው ግን 1ኛ ነው ። ሽንት ቤት ❓ 📚 አሪፍ ነው ፤ ምንም አይልም .! ውሃ ፤ መብራት ፣ WIFI ❓ 📚 WIFI በጣም ገራሚ ነው ፤ የትኛውም ካንፓስ በሌለ ፍጥነት ነው የሚሰራው ፤ ውሃ እና መብራት የሀገሪቷ ችግር ስለሆነ አንዳንዴ ይጠፋል የሚያሳስብ ግን አይደለም ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

WELKITIE UNIVERSITY አድራሻ ❓ ደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ትገኛለች ። ከአዲስ አበባ የ85 ብር መንገድ ርቀት ላይ ይገኛል ከተመሰረተ 10 አመቱን አስቆጥሯል ፤ በ 2004 ነበር የተመሰረተዉ ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 አየሩ አሪፍ የሚባል ነው ግን መጀመርያ አከባቢ ይሞቃል ፤ ለሴቶች ጥላ ነገር መያዝ ይኖርባቹሃል ትንሽ ፀሃዩ ያቃጥላል ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያሉ ግቢዎችሁለት ብቻ ናቸው ። እነርሱም textile and main ይባላሉ ። ♨ textile ግቢ ከተማ ዉስጥ ያለ ሲሆን በውስጡም 🌻Textile 🌻Garment and 🌻 designing( exam አለው በፈተና ነው የሚገባው ። ) ✅MAIN ግቢ ፦ 📚 ከከተማዋ የ10 ብር ትራንስፖርት ሲሆን ጉብሬ የሚባል SUB CITY ቦታ ላይ ይገኛል ፤በዉስጡ ያሉት ዲፓርትመንቶች ደሞ ፦ 👉Engineering and Technology ✍civil ✍chemical ✍ Electrical ✍food process ✍HWRE(water) ✍mechanical ✍ cotm ✍architecture (ፈተና አለው በውድድር ነው ሚገባው..!) ⚠️ Note ፦ ▶ምህንድስና ክፍል ላይ ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ በጣም አሪፍ ነው ። 👉computer science ✍Software ✍ CS (computer science) ✍IS( Information system) ✍IT( Information technology) 👉 social science ✍midwifery ✍ nursing ✍FB ✍Law ✍Psychology ... 👉social/natural comptitional ✍ Mathematics ✍Sport ✍ Physics Health HO .. 🏩Medicine --> እስካሁን ግን በህክምና አላስመረቀም ገና ተቀብሎ በማስተማር ላይ ነው ። የካፌ ምግብ ❓ 📚 ምሳ ላይ በሳምንት ሶስት ቀን ዜrፎr (ስጋ ጣል ጣል) አለ ፤ አትክልትም አለ ግን ብዙም አይነፋም ፦ 🍛ምስር ፣ 🍳 ክክ እና 🍲 አሪፍ ሽሮ የምሳ ምግቦች ናቸው ። ቁርስ ደግሞ ፦ ፍርፍር ፤ ሩዝ እና ቅንጬ ይቀርባል ። ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓ 📚ግቢ ውስጥ 3 ላዉንቾች (ምግብ ቤቶች) አሉ ፤ ዋጋቸዉም 🍥በያይነት 13-15 🍥ፓስታ በሱጎ 13 🍥ፓስታበአትክልት 13-15 ነው ፤ በጣም ተመጣኝ ነው ። Non ካፌ ተማሪዎች ኩፖን ከገዛቹህ 12.5-13.5 ነው ። ☕ቡና 2.5 ☕ሻይ 1.5 ☕ቀሽር 3 ☕ስፕሪስ 3 ⚠️ Note ▶ 📚ካፌ ላይ ጨጓራ ምናምን ላለባቹህ ልጆች special ቡፌ አለ ከክሊኒክ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ ከሆነ ያበደ ምግብ ይበርብላችሀዋል ። የግቢው ክሊኒክ ❓ 📚 ክሊኒክ በመሻሻል ላይ ቢሆንም እንደማንኛውም ግቢ ደስ የማይል ነገር አለው ፣ ከፓራስታሟል የተሻለ ኪኒን የላቸውም ። ውሃ ፤ መብራት እና WIFI ❓ 📚 ውሃ በፈረቃ ይለቀቃል ካልተለቀቀ ላውንች አካባቢ እንደልብ ስለሚገኝ ጣጣ የለም ፤ መብራትም አይጠፋም ፤ WIFi ትንሽ አዛ ነው ፤ ይሻሻላል የሚል ነገር አለ ። ሽንት ቤት ❓ 📚 ግቢው በዚ ላይ ችግር አለበት ደስ አይልም ፤ ይደብራል ፤ ማሻሻል ያለበት ነገር ነው ። የዶርም ሁኔታ ❓ 📚 ዶርምም ብዙም አያስደስትም ግን የብዙዎቹ ግቢዎች ችግር ስለሆነ ምንሞ አይደረግም መቻል ነው ። የዕቃ ስርቆት ❓ 📚 ግቢ ዉስጥ እና በዙሪያው አስፈሪ ነገር የለም ። ሰላማዊ ከተማ ነው ። ሀይማኖታዊ ተቋማት ❓ 📚 እንደሌሎች ግቢዎች ሃይማኖታዊ ተቋማት በቅርቡ ስለሚገኙ ምንም ዓይነት ጭንቅ እንዳይሰማቹህ ፤ እንደሙዳችሁ አለ ። ማሳሰቢያ ❗️ ⚠⚠⚠⚠⚠⚠ℹ 📚 በነገራችን ላይ ግቢው ዲሲፕሊን ላይ በጣም ሃርድ ነው medicine በተቀበል በ መጀመርያው አመት 16 medicine ተማሪዎችን አባሯል ፤ በዲሲፕሊን ምክንያት ማለት ነው ፤ እንዲሁም ሊመረቅ ሳምንት የቀረዉም ልጅ አባሯል እና ተማሪዎች ግድ ጸባያቸዉን ማስተካከል አለባቸዉ በተልይ ድብድብ ፤ጫት ፤ሲጋራ ምናምን ከባድ penalty አላቸው ። ሌላ ደሞ አንዳንድ ፍሬሽ ተማሪዎች ሊጠነቀቁ የሚገባቸዉ ነገር ጫት በብዛት ስላለ እንዳይሸወዱ ፤ በተለይ ጉብሬ ግቢ የሚደርሳቹህ ተማሪዎች በርጫ በበርጫ ስለሆነ ሀገሩ እንዳትዘናጉ ለማለት ነው ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

◦•●◉✿[ Dilla University ]✿◉●•◦ ዲላ ዩኒቨርስቲ ከአድስ አበባ 360ኪሜ ርቀት ላይ የሚገኝ ሲሆን 👉የአየሩ ሁኔታ ሚካበድ ሙቀት የለም ግቢው በጣም አርንጓዴ ነው ግን ከግቢው ውጪ ፀሃይ አለ፤በተወሰነ መልኩ ሞቃት ነው ለመልመድ ግን አይከብድም በውስጡ ያሉ ግቢዎች፡ ሶስት Techno: Engineering, CS Main :agree, physics... and Tena gbi: social... ትምሮ በጣም አይከብድም ግን እንድታጠኑ በትንሹ ለማጨናነቅ ይሞክራሉ ፤ በተረፈ እንደማንኛውም ግቢ ካልቸከልክ ትጫራለህ 👉የምግብ ቤቶች ዋጋ ባንፃራዊነት በጣም አሪፍ ና ተመጣጣኝ ነው ዋጋ 15–17 ብር ነው 👉የቡና ዋጋ ከ 3–5 ብር ነው በጣም አሪፍ የጨፌ ቡና ዲላ ይገኛል☕☕☕☕ 👉የካፌ ምግብ ብዙም አይደለም፤ ከግቢ ውጭ ግን አሪፍ ምግብ ቤቶች አሉ ከ13ብር ጀምሮ🍚🍟🍔🍕🍜 👉ፍርፍር በጣም ርካሽ ነው🍜🍜🍜🍜 👉ሙዝ የአንድ ብር አምስት ፍሬ 🍌🍌🍌 👗👟👞🎩👗👕👡👠👢👕👖🎒👔👚👘👚 👌 ያው ኑሮ በ ዲላ ርካሽ ነው የተለያዩ ኮንትሮባንድ እቃዎች ይገኛሉ 💍ልብስ እና ጫማም በጣም ርካሽ ነው ባጠቃላይ ትወዱታልቹህ ውሃ መቼም አይጠፋም ሻወር 24 ሰዓት መጠቀም ይቻላል፤ ዋን ለሜ ምንጭ እያለች ዲላ የውሃ ችግር አይታሰብም። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter or https://t.me/assignmentsupporter

ድሬዳዋ university፦ አድራሻ ❓ 📚 በድሬደዋ ከተማ የምትገኝ ፍቅር ነሆነች ዮኒቨርስቲ ነች ። የአየር ሁኔታ ❓ 📚 ሞቃታማ አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች ፦ ወፍራም ብርድልብስ አያስፈልግም ፤ አንሶላ እና አልጋ ልብስ በቂ ነው፤ የመጀመሪያዎቹን አራት ወራት ትንሽ ሊበርድ ይችላል ፡ ግንቦት ላይ ምናምን ግን በጣም ሞቃት ነው። የካንፓስ ብዛት ❓ 📚 ድሬ አንድ ግቢ እና ሶስት መግቢያ መውጫ በር ያለው ሲሆን ሁሉም filed of study እዛው ነው የሚሰጠው ሌላ ቅርንጫፍ የለውም ። 🎯 በተጨማሪም ሶስት ላይብራሪ ያለ ሲሆን እነሱም፦ 🏩 Tecno 🏩 Main 🏩 Fb/keranyo ✅ የሚሰጡ ፊልዶች በጥቂቱ ፦ 🌐IOT 🌐FBE 🌐other social science 🌐Computitional science 🌐Fashion design 🌐Architecture 🌐 Engineering 🗻Engineering fileds 1 mechanical 2 electrical 3 chemical 4 civil 5 textile 6 cotm 7 food 8 industrial 9 survey 📚 arcthicure and Medicine መግባት ለምትፈልጉ መግቢያ ፈተናና የEntrance ውጤትም ይታያል።Software engineering የለም ። 📚 FB ( faculty of business) total social fileds House of medicine ፤ ሁሉንምhealth science ያጠቃልላሉ ። 📚 Architecture and Fashion design መግባት የምትፈልጉ የመግቢያ ፈተና ስላለው እዛያሉ ሲኒየር ተማሪዎችን ስለፈተናው ኢንፎ ብትጠይቁ አሪፍ ነው ። Marketing መግባት ለምትፈልጉ ደግሞ ድሬ ላይ ልብስ ጫማና ምግብ ቅናሽ ነው ። የካፌ ምግብ ❓ 📚 ድሮ አዛ ነበር አሁን ግን በጣም ምርጥዬ ሆኗል ፤ በቃ ኢትዮጵያ ውስጥ አሪፍ ከሚባሉት አንዱ ነው ። ኀከካፌ ምግብ ውጪ ❓ 📚ምግብ ቤቶች ብዙም ውድ አይባሉም አሪፍ ነው። 🎯 ፍርፍር 11-15ብር 🎯 ፓስታ 13/15ብር 🎯 ድንች ለብለብ/ሰላጣ 11ብር 🎯 በአይነት...--------12ብር ከግቢ ውጭ 25ብር 🎯 ቡና 4ብር ------------6 /7 ከግቢ ውጭ 🎯 ሻይ 1.5 or 2---------3/4 ከግቢ ውጭ ሌላውም fair ነው ። ዶርም እና ሽንት ቤት ❓ 🎯 የዶርም እና የሽንትቤት ነገር አስደሳች አይደለም ስለ ግቢው ሁኔታ ብዙ ደስ የሚል ነገር አትጠብቁ ፤ በጣም አስጠሊ ነው ። የትምህረት ሁኔታ ❓ 📚የትምህርት አሰጣጡ ምናምን በጣም አሪፍ ነው፥ ላይፉም ሙድ አለው ብቻ እናንተ ኑ ፤ የድሬ ሰዎችም ሲበዛ ፍቅር ናቸው ይህን ስትመጡ ትመሰክራላችሁ ። የዕምነት ቦታ ❓ 📚መስጂድ እና ቤተ-ክርስቲያንም በግቢው አቅራቢያ ስለሚገኝ ይበልጥ ትወዱታላቹህ ። የረብሽ ጉዳይ ❓ 📚 አልፎ አልፎ አንዳንድ አለመረጋጋቶች ይከሰታሉ ፤ በዚህ ጊዜ ተማሪዎች ወደ መስጂዶችና ውደ ቤተ- ክርስቲያናት በመሄድ ራሳቸውን ከአላስፈላጊ እንግልትና ከፌደራል ዱላ ይከላከላሉ ። በአመት አንዴም ሁለቴም ግርግር አይጠፋም ። የዕቃ ስርቆት ❓ 📚 ወደ ድሬ ስትመጡ መጀመሪያ ቀጥ ብላቹህ ወደ ግቢ ግቡ ፤ ፍሬሽ ተማሪዎች ሲመጡ በየመንገዱና በመናሀሪያ በተለይም በታክሲ(ባጃጅ) ላይ ምናምን የናንተን መፍዘዝ ready ሆነው የሚጠብቁ ብዙ ሌቦች አሉ። አሸዋ ገራሚ የዝርፊያ ቦታ ነው በተለይ ጫማ ምናምን ለመግዛት ስትሄዱ ፤ ሰባተኛ፡ ማታ ማታ walk ለማድረግ ስትፈልጉ ፤ seido፡ ቀን ላይ እነዚህን ሰፈሮች በጥንቃቄ ማለፍ ይኖርባቹሃል ። በተለይ ስልክን ገንዘባችሁን ተጠንቀቁ...! ጫት እና ድሬ ❓ 🌲 ድሬ ከተማ ላይ እንደምታቁት ጫት ከምግብ በላይ አንገብጋቢና በጣም ወሳኝ ምግብ ነው ሆኖም ግን ለግቢ ተማሪዎች ጫት ስለማይመከር ለቅምሻም ቢሆን እንዳትሞክሩ። እመኑኝ የድሬ ጫት ከጥፍጥናው የተነሳ ሱስ ያሲዛል(አሉ)....! የውሃ እና መብራት ጉዳይ ❓ 📚ውሃ እና መብረት አያሳስብም ጨቅ ነው ። ትንሽ WIFI ነው እንጂ አዛ የሚያደርገው....! N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @https://t.me/assignment_supporter https://t.me/assignmentsupporter

አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዮኒቨርሲቲ አድራሻ ❓ 📚 በበረሃማዋ ከተማ በስምጥ ሸለቆ ዕንቁዋ በአዳማ ከተማ የሚገኝ አሪፍ ዮኒቨርሲቲ ነው ። የአየር ሁኔታ❓ 📚 ሞቃታማ በተለይ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ትንሽ ይሞቃል ፤ ይህን እንጂ ማታ ማታ ደግሞ ያልተጋነነ ብርድ ስለሚኖር ሹራብ ነገርም ያስፈልጋቹሃል ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በውስጡ ያለው ግቢ አንድ ለናቱ ነው አንድ ብቻ ነው ። የሚሰጡ Fields and Departments ❓ 📚 ASTU ላይ ብዙዎቻቹህ እንደምታውቁት ሁለት የትምህርት መስኮች ብቻ ይገኛሉ። ➡ Engineering & ✅ Applied science ናቸው ። 📚 ከሌላው ግቢ ትንሽ ለየት የሚያደርገው pre- engineering የሚያስተምረው ሁለት ሴሚስተር መሆኑ ነው ( department and school የምትመርጡት ሁለተኛ አመት ላይ ነው ማለት ነው ።) Pre-engineering courses ▶ -General Chemistry(🙄) ▶ - General Physics 1 ▶ - Applied Maths 1 ▶ - Communicative english. ▶ - Introduction to computing( Python). ▶ - Civic or Logical reasoning. ▶ - HPE( 0 ch) 🎯 Second semister courses ፦ ⏭ - Applied Maths 2 ⏭ - Technical drawing ⏭ - General physics 2 ⏭ - Computing ( c++) ⏭ - English writing ⏭ - Civic or Logic ⏭ - HPE(0 ch) 📚 Under Applied science pre-engineering courses ፦ ♒ Almost the same as Engineering except one course 🎯 Departments of Applied Natural Sciences are ፦ 🎯 Applied Biology 🎯. Applied Chemistry 🎯 Applied Geology 🎯 Applied Mathematics 🎯 Applied Physics 📚Under Engineering there are 3 schools ፦ 1. Electrical 2.Mechanical 3.Civil 📚 Under electrical engineering or CSE there are 3 streams ፦ A) Electrical and computer engineering B) Electronics and communication engineering C) Power and control engineering 📚 Under Mechanical engineering A. Chemical B. Mechanical C. Material 📚 Under civil and arc school.፦ A.Architecture B. Civil C. Water resource management and hydrolic Engineering D. Geomatics (በቅርብ የሚጀመር ....!) ✅ Note ፦ 🎯 Engineering ላይ Aerospace engineering and software engineering አሁን ላይ አይሰጥም ። በነገራቹህ ላይ የመግቢያ ፈተናው ብዙም አይከብድም፤ ፈተናው ከEntrance exam ጋር ተመሳሳይነት አለው። 📚 Content of exam subjects are ▶ Chemistry ▶ Biology ▶ Mathematics ▶ Physics and ▶ English የካፌ ምግብ ❓ 📚 አንደኛ ነው ምንም አይወጣለትም ፤ በቃ ምርጥዬ ነው ለማለት ቢከብድም የእናታቹሁ ሽሮ ብዙም ትዝ አይላችሁም ። ከካፌ ውጪ ያሉ ምግቦች ❓ 🎯 የምግብ ቤቶች ዋጋ ከ25-40 ብር ባለው range ይጠቃለላሉ። አሪፍ የሚባል ምግብ ያቀርባሉ ...! አዲስ ነገር ❓ 📚 ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገባቹህ ደግሞ አሪፍ ሽልማት ይበረከትላቹሃል ፤ በ2011 ከ3.76 በላይ ላመጡ 59 ተማሪዎች PC💻 ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል። እምናና ካቻምናም በተመሳሳይ ብዙ ተማሪዎች ተሸልመዋል ፤ ከ3.5 በላይ ያመጡም የተሸለሙበት ጊዜ ነበር ። ብቻ እናንተ ጠንክሩ እንጂ ለሽልማቱ አለንላቹህ ። ይሄ ነገር 2012 ጀምሮ ቆሟል ይቀጥላል ተብሏል ። 📚 ሌላም surprise አለ Engineering ለምትገቡ የአምስት ዓመቱን ትምህርት በአራት አመት የመማር ዕድል ሊያጋጥማቹህ ይችላል ግን በጣም ትልቅ ጥረት ያስፈልጋል (ፈተና አለው) ለApplied science ተማሪዎችም የአራት ዓመቱን ትምህርት በሶስት ዓመት ማጠናቀቅ የሚችሉበት መንገድ በተመሳሳይ መልኩ ማለትም በቅድመ ፈተና ተፈትነው በማለፍ ብቻ pre Engineering ሳይማሩ መመረቅ ይችላል። ውሃ ፤ መብራት እና wifi ❓ 📚 ምንም አያሳስብም ትንሽ ውሃው ሙቅ ነው እንጂ ሌላ ጣጣ የለም ፤ WIFI በሽ ነው .....! ሽንት ቤት ❓ 📚 ምርጥዬ ነው ፤ በቃ አያሳስብም የገነት ቁልፍ በሉት ...! N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ © ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

JIMMA UNIVERSITY አድራሻ ❓ 📚 ጅማ ዩኒቨርሲቲ ከኢትዮጵያ ዋና ከተማ ከሆነችዉ ከአድስ አበባ ደቡብ ምዕራብ በኩል የሚትገኝ ሲሆን ከአድስ አበባ እስከ ጅማ 390 km አከባቢ ነዉ። የአየር ሁኔታ ❓ ሞቃታማ ፥ ከአዳማ እና ከመሰል ሞቃት ሃገሮች ለሚመጡ ተማሪዎች ሙቀቱ ምንም ዓይነት ተጽእኖ የለውም እንዲያውም ሊበርዳቸው ይችላል፤ በግልባጩ ደግሞ ከብርዳማ አከባቢ ለሚመጡ ተማሪዎች የሙቀቱ መጠን ከፍ ያለ ይሆንባቸዋል ። ለማንኛውም ቀለል ያሉ ልብሶችን ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው። ስለ ዮኒቨርስቲው ❓ 📚 ድሮም ጀምሮ የፍቅር ከተማ ተብሎ በሚጠራዉ በጅማ ከተማ የሚገኝ አንጋፋና ለኑሮም ሆነ ለትምህርት ከየትኛዉም ዩኒቨርሲቲ የተሻለ ነዉ ብለን የሚናስበዉ ዩኒቨርሲቲ ነዉ። ጅማ ታርካዊና አንጋፋ በሆኑ በንጉስ አባጅፋር ታርክ የታወቀች ከተማ ስትሆን ዩኒቨርሲቲዉ ለከተማ ብዙም ሳይርቅ በከተማ ዉስጥ ነዉ ለማለት በሚያስችል ሁኔታ ይገኛል። ሌላዉ እና በጣም ደስ የሚል ታርካዊ ቦታ ቢኖር ንጉስ አባጅፋር ቤተመንግስት የሚገኘዉ ከዋናዉ ግቢ ብዙም ሳይርቅ መገኘቱ ነዉ። ለጉብኝት በፈለጋችሁ ጊዜ ሁለ መዝናናት የሚያስችል ቦታ ነዉ። በጅማ ዩኒቨርሲቲ በጣም የሚያማምሩ ህንፃዎች ከመኖራቸዉ ባሻገር ለመማርም በጣም ምቹ የሆኑ ህንፃዎች ናቸዉ። ጅማ ዩኒቨርሲቲ በጣም በፍጥነት እያደገች ትገኛለች። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በጅማ ዩኒቨርሲቲ አራት Campus ያለ ስሆን ከቅርብ ጊዜ በኋላ አንድ አድስ campus ስራ ይጀምራል ተብሎ ይገመታል። የአራቱ campuses ስማቸዉም እንደሚከተለዉ ነዉ፦ ✅# ዋና ጊቢ ( Main campus).. በዋና ግቢ የሚገኙ ኮሌጆች ፦ # ጤና እንስቲትዩት # ህግና አስተዳደር ኮሌጅ # የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ #ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ እና # ስነ ባህሪ ኮሌጅ ናቸዉ። ✅ ቤኮ ኮሌጅ ( College of business& economics) ከዋናዉ ግቢ ትንሽ የሚርቅና በመካከላቸዉ ትልቅ መንገድ ያለ ስሆን ዋናዉንና ቤኮ ግቢዉን የሚያገናኝ ትልቅ ድልድይ ይገኛል። ከዚህ የተነሳ የዋና ግቢ ተማርዎችም ሆነ የቤኮ ( college of business& economics ) ተማርዎች በድልድዩ በኩል ያለምንም መንገድ ችግር ይመላለሳሉ። ✅# የቴክኖሎጂ ግቢ የእንጂነርግ ተማሪዎች እና የcomputer science ግቢ ሲሆን ለመማርም ለመኖርም ምቹና በጣም አስደናቂ የሆኑ ህንፃዎች ያሉበት ግቢ ስሆን በመጀመሪያ ጊዜ የህንፃዎችን አሰራር ያዬ ሰዉ እዉነትም ይህ ህንፃ የእንጂነሮች ስራ ነዉ ብሎ ከማድነቅ ወደኋላ አይልም። የቴክኖሎጂ ግቢ ከዋናዉ ግቢ የ 5 ብር መንገድ ስሆን ከጅማ ከተማ ከመርካቶ የ 3 ብር መንገድ ነዉ። ✅4# የግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ፦ የሚገኘዉ ከቴክኖሎጂ ግቢና ከዋና ግቢ መሃል ይገኛል። የግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ ከዋናዉ ግቢ የ5ብር መንገድ ስሆን ከመርካቶ የ3 ብር መንገድ ነዉ። (በታክሲ) 📚በእያንዳንዱ ግቢ አንደኛ አመት ተማሪዎች ይመደባሉ ፤ የጂማ ዩኒቨርሲቲ ብሎኮች በጣም የሚያማምሩ ናቸው ። ትምሮ በጅማ ዩኒቨርሲቲ ትንሽ ከበድ ሊልባቹህ ስለሚችል በግቢው ምቾት እንዳትታለሉ ። የካፌ ምግብ ❓ የምግብ ነገር ከሌሎች ግቢዎች በሚመጡ ተማሪዎች የተመሰከረለት ነው። የግቢ ካፌ በጣም ተስማሚ ከመሆኑ የተነሳ non ካፌዎች ቁጥር አናሳ ነው ። ምግቡ Normal ነው አንዳንድ ምግቦች ሊደብሩ ይችላሉ በተለይ ለፍሬሽ ቢሆንም ግን ጨጓራ ምናምን አይነካም። ከካፌ ውጪ ስላሉ ምግቦች ❓ 📚በካፌው በተጨማሪ ግቢ ውስጥ እና ከግቢ ውጭ ያሉ ብዙ አማራጮች አሉ። ከግቢ ውጭ ያሉ ብዙ ምግብ ቤቶች አሉ ፥ በአይነትም በጥራትም አሪፍ የሚባሉ። በጣም የሚገርማቹህ ውድ የሚባልው ምግብ 3p ብር ነው ። 🎯 ፓስታ ፣ አይነት ፣ ሽሮ ምናምን ከግቢ ውጭ 20ብር ሲሆኑ ግቢ ውስጥ ደግሞ 25 ብር ናቸው። 🎯 ሻይ ሁለት ብር ሲሆን ቡና ደግሞ 3 ብር ነው። ለነገሩ ብዙም አይገርምም ሀገሩ ጅማ እኮ ነው በቡናማ አይታሙም። ከግቢ ውጭ የተለያዩ ፍራፍሬዎችን ማግኘት ይቻላል፤ 🍌 ሙዝ ፣ ብርቱካን፣ አቩካዶ ምናምን ነፍ ነው ፤ ሌላም የተለያዩ ጁስ ቤቶች ይገኝሉ ፥ ጁስ 15 ብር ነው ። ውሃ መብራት እና WIFI ❓ 📚 የብዙ ግቢዎች ችግር የሆነው የውሃ ጉዳይ ነው፤ ውሃ ጅማ ውስጥ ለአንድ ቀን ጠፋ ማለት ኒዎርክ መብራት ጠፋ ማለት ነው። የውሃ ችግር ጅማ ውስጥ የለም ማለት ይቻላል እንዳያሳስባቹህ ግን ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም አይባልም ግን በዛ ቢባል ለአንድ ቀን ነው ። መብራት ኖርማል ነው አንዳንዴ ብቻ ይጠፋል ፤ WIFI ለክፉ አይሰጥም አሁን ላይ መሻሻል እያሳዮ ነው ። 📚 በተረፈ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሀገራችን ቀዳሚ ከሚባሉት ዩንቨርሲቲዎች ግንባር ቀደም በመሆኑ ብዙ አስቸጋሪ ነገር አያጋጥማችሁም ። የሽንት ቤት ❓ 📚 በብዙ ግቢዎች እንደተለመደው ትንሽ የሚያስቸግር ነገር ቢኖረውም ከብዙ ካንፓሶች የተሻለ ነው ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ © ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

🏢 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 🏬 አድራሻ....❓ 💬 በኢትዮጽያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ውስጥ ይገኛል ። የአየር ሁኔታ ...❓ 💬 የመጀመሪያዎቹ ወራቶች መጠነኛ ብርዳማ ሆነው ወደ ኋላ ላይ ግን ሞቃታማ የአየር ንብረት አለው ። የካንፓሶች ብዛት ❓ 📚 በጣም ብዙ ማለትም አስራ ሰባት ይደርሳሉ ። እያንዳንዱ ካንፓስ የተለያየ ፊልድ ይሰጣል ። ያሉት ካንፓሶች ፦ 6 ኪሎ ፣ 5 ኪሎ ፣ 4 ኪሎ ፣ ሜክሲኮ ፣ ልደታ ፣ 18 ማዞሪያ ጥቁር አንበሳ ( hospital) ቃሊቲ ፤ ቢሾፍቱ (ደብረዘይት) ፤ ላምበረት ......ካንፓሶችን ያካትታል ። በካንፓሶች የሚሰጡ ፊልዶች ❓ 🏠6 kilo 💡 ለሶሻል ተማሪዎች ብቻ የሶሻል ዘርፍ ትምህርቶችን ይሰጣል ። 🏠5 kilo 💡 ለኢንጂነሪግ ( Software , electrical , biomedical , mechanical , civil , chemical ..የሚሰጥበት ካንፓስ ነው ። ✅ biomedical engineering ከሚሰጥባቸው ጥቂት ዩንቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ነው። 🏠4 kilo 💡 በዚ ካንፓስ computer science እና computer engineering ይሰጣል ። 🏠 18 ማዞሪያ 💡 የሜዲሲን ዘርፎች በ Other health የሚካተቱትን ይሰጣል ። 🏠 ጥቁር አንበሳ 💡 ይህ ካንፓስ አንጋፋ ሲሆን በውስጡም የMedicine ኮርስን ይሰጣል ፤ ተማሪዎች አፓረንትም በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ይወጣሉ ። 🏠 ላም በረት 💡 በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ላይ ብቻ አተኩሮ የሚሰራ ካንፓስ ነው ፤ AASTU የሚገኝበት ሲሆን APPLIED እና Enginering ኮርሶችን ይሰጣል ። 🏠ልደታ 💡በልደታ ካንፓስ የሚሰጡት ፊልዶች architecture ፤ cottom ፤ urban plannig እና የመሳሉትን ያካትታል ። 🏠 ሜክሲኮ 💡 ይህ ካንፓስ የcommerce ግቢ ነው ። ( marketing management , business administration, management የሚሰጥበት ካንፓስ ነው ።) 🏠 ሰፈረ ሰላም 📚 የጤና ዘርፍ ግቢ ነው ፤ ሜዲስን ነርሲንግ እና የመሳሰሉት ወደ ጥቁር አንበሳ 3ተኛ አመት ላይ ከመሄዳቸው በፊት የማሩበት ግቢ ነው ። 🏠 ቢሾፍቱ ካንፓስ 📚 AAU ደብረዘይት ላይ Veterinary medicine & Science collage አለው ። ደብረዘይት ነው የሚገኘው ካንፓሱ በጤና እና ሳይንስ ዘርፍ ይሰጣል ..! 💬ለኢንጅነሪግ ተማሪዎች ፧ ➡ የdrawing መሳሪያዎች መያዝ አለባችሁ ➡ Mathematics and Mechanics Statics guide books ይዛቹህ ብትሄዱ መልካም ነው ። የካፊው ምግብ ❓ 📚 ምግቡ ለክፉ የሚሰጥ አይደለም ከሌሎች ዮኒቨርሲቲዎች የተሻለ ነው ፤ በተለይ ደግሞ ሰፈረ ሰላም ካንፓስ ደስ የሚል ነው ። በሳምንት ውስጥ ካፌ የሚሰጡ ምግቦች ዝርዝር ስኬጁል ❓ 📚 ከሌሎች ዮኒቨርስቲዎች የተለየ አይደለም ቁርስ ፍርፍር ፤ ሩዝ ፤ ሻይ በዳቦ ፤ ስልስ ይቀርባል ፤ ምሳ እና እራት በሳምንት 2-3 ቀን ስጋ ምሳ እና እራት ይኖራል ፤ ሽሮ ፤ ምስር ፤ አታክልት የመሳሰሉት ምግቦች ይቀርባሉ ። ከካፌ ውጪ ስለሚገኙ ምግቦች እና ዋጋቸው ❓ 📚 ከሌሎች ግቢዎች የተለየ አይደለም ነገር ግን 4 ኪሎ ግቢ ምግብ ከሚታሰበው በላይ ቅናሽ ነው ። ዋጋቸው ከታች ተቀምጧል ...! ቀላል ምግቦች ፓስታ ፍርፍር... etc 20 -30 ብር ከባድ ምግቦች እንቁላል ፤ ስጋ ..etc 30-50 ብር ሻይ እና ቡና ...etc 2-4 ብር ይሆናል ። የሎከር ነገር ❓ 📚 ሎከር በጣም አስቸጋሪ ነው ፤ በዶርም ውስጥ አንድም የሚሰራ ሎከር ማግኘተ ይከብዳል ። አብዛኛው ተበላሽቷል አይሰራም ። ውሃ ❓ 📚ውሃ በተደጋጋሚ ይጠፋል ፤ በተለይ ደሞ የዕረፍት ቀናት ለአንድ ሰዓት ብቻ ተለቆ ይቆማል ፤ ከተማዋ ላይ የውሃ እጥረት ስላለ ግቢ ውስጥም የተለየ ነገር የለም ..! ...ሽንት ቤት ...❓ 📚 እንደ ካንፓሶቹ ቢለያይም አብዛኛው ግን በጣም አሪፍ የሚባል ነው ፤ በተለይ 4 ኪሎ በየቦታው ይገኛል ፤ የሚያስከፋ ነገር የለውም ሻል ያለ ነው ። በግቢው ስላለ የዕቃ ስርቆት፦! ❓ 📚 እንደካንፓሶቹ ቢለያይም ግርግር ፤ ረብሽ የሚባል ነገር ስለሌለ የስርቆት ነገር በጣም rare ነው ፤ ቸልተኛ ካልሆነ ስርቆቶ ብዙ የሚያሳስብ ነገር አይደለም ። የሃይማኖታዊ ተቋማት ፦ ❓ 📚 በብዙዎቹ ካንፓሶች በአቅራቢያቸው መስኪድ እና ቤተስኪያን ስላለ ሀይማኖታዊ ጉዳዮችን ለመከውን አያዳግትም ። N.B, ከላይ ያለው መረጃ ከ2012 ዓ.ም በፊት ያለውን ነገር የሚገልጽ ስለሆነ አሁን ያሉትን ለውጦች አላካተተም ። ➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ©ዘ ካምፓስ ━━━━━━━━━━━━━━━ Share with your friends 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter

Cornell Method: A Smart Way to Take Notes‼️ How to take organized notes. Here are the steps for taking notes using the Cornel
Cornell Method: A Smart Way to Take Notes‼️ How to take organized notes. Here are the steps for taking notes using the Cornell method: 1.Divide your paper into three sections: a two-inch margin on the left, a six-inch section for notes, and a two-inch summary section at the bottom. 2. During the lecture or reading, take notes in the six-inch section using keywords, abbreviations, and symbols. 3. After the lecture or reading, write a summary of the notes in the two-inch summary section at the bottom. This will help you review and remember the information later. In the left margin, write key questions or cues that relate to the notes in the main section. These cues will help you quickly review and study the material later. That's it! The Cornell method is a simple and effective way to take organized notes. #HowTo #Cornell #Note #EdMap #Simple @assignment_supporter

በዮኒቨርሲቲ ቆይታችሁ እነዚህ ነገሮች ብታረጉ ጥሩ ነው ❗️ 💡....ዲያሪ መፃፍ ..... 📚 የካንፓስ ቆይታ በጣም የሚገርሙ moment ያሉበት ነው ።በቃ 3 or 5 የደስታ ዘመናት ... የሚገራርም ሰው ታያላችሁ ....የሚወዛገብ ፤ የሚወሳሰብ የሚፈላሰፍ ፤ ምንም ዲጭ የማይልበት ፤ ተንከሲሲስ ፤ በጣም ጅል ፤ አራዳ ነኝ ባይ ገገማ ....ኧረ ምኑ ቅጡ ....በህይወታችን አዳዲስ ነገሮች ይከሰታሉ ። ነገር ግን እንረሳቸዋለን ቶሎ ቶሎ አዳዲስ ነገር ስለሚፈጠሩ ይረሳል ። እናንተ ደግሞ ከፈለጋችሁ መፃፍ ብታረጉት ፤ ወደፊት ፊልም የመስራት ዕቅድ ካላችሁ ሚገራርሙ ገፀባህራያት ታገኛላቹሁ....ብቻ በላይፋቹ የማታገኙት ዕድል ስለሆነ በርትታቹሁ?...አዳዲስ ነገር ሲኖር በወረቀት (ዲያሪ) "ወይም ስልካቹም ላይ ቢሆን አስፍሩት ..! ትዝታዎቻቹ ናቸው እንዳትረሱት...ሙድ የተያዘባችሁ ሙድ የያዛችሁትን ...የሚያስቅ ፤ የሚያሳዝን፤ የሚያናድድ ብቻ ....ቸክችኩ ቢያንስ ልጆቻችሁ ትሰጧቹሃላቹ እነሱም ካምፓስ ሊገቡ ሲሉ ....በየቀኑ ሳይሆን የሆነ ነገር ሲፈጠር ፃፉት ...አሁን ምንም ላይመስላቹሁ ይችላል ግን አልፎ ስታዩት የምርም ትደሰታላቹሁ ..... 💡አዲስ ቋንቋ መማር ......❗️ 📚 ዶርም የምትሰባሰቡት ከየአቅጣጫው ነው ። ብዙ የማታውቁትን የሚያቁ ይሄም አለ❓... ያምሃል...! የሚያስብሉ ዕውቀቶች ታገኛላችሁ ። አንዱ ደሞ ቋንቋ ነው ። በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ በርከት ያለ ተናጋሪ ያላቸው እንደ ኦሮሚኛ ፣ሲዳመኛ ፣ትግረኛ፣ ሱማሌኛ ቋንቋዎች የሚችሉ ልጆች ዶርም ካገኛችሁ በቀን 5 ቃልም ቢሆን ቀስ እያላችሁ ተማሩ .....የምር ይጠቅማቹሃል ። ቋንቋ መልመድ ጥሩ ነው ። ሁላቹም ጋር አዲስ ቋንቋ ከሌለ ደሞ ጓደኞቻችሁን የምታስታውሱበት አለ ኣ በቃ ....አዲስ የባህርማዶ አንድ ቋንቋ በጋራ ተለማመዱ ...ስፓንሽ ወይ ደሞ ፈረንች ...የተመቻችሁ በጋራ በቀን ትንሽ ነገር አጥኑ ። የ3 or 5 አመት ጓደኞቻችሁን ስትለዮዎቸው ማስታወሻ ይሆናቹሃል ። ፈታ እያላችሁ ጠዋት ላይ 5 ቃላት ምናምን ሸምድዱ የምርም ጓደኝነታችሁ ለማጠንከር ያግዛቹሃል ። 💡መክሊታችሁን ማዳበር ......! 📚 የሰው ልጅ በተፈጥሮ የተለያዩ መክሊቶች ተሰጥቶታል ። ታዲያ እናንተም የተፈጥሮ ስጦታችሁን በክበብ በመሳተፍ ማሳደግ አለባቹሁ፣ በገገሙ ትምህርት ብቻ ካንሰር ነው የሚሆንባቹሁ ...ትወና የምትሞክሩ....ግጥም መጣጥፍ የምትሞክሩ ....ስዕል ....ሃይማኖታዊ ነገሮች የምትሞክሩ ብቻ ግቢ ላይ ብዙ ክበቦች አሉ ...የሴቶች ...የበጎአድራጎት ...የሌለ የለም ....እና ተሳተፉ ማህበር አለ ...ዕቁብ፣ ዕድር ሁላ አለ (ቀልዴ ነው ...) ....በቃ በዓል ግዜ ደስ ይላል ። የምትወዱት ከኖርማል ትምህርታቹ ላይ የሚደበል ...ዘፈን ከሆነ ...ስፓርት ከሆነ ...ኳስ ከሆነ .....ብቻ የምትወዱትን አንድ ነገር አዳብሯቹሁ ። ተገኙ .....በገገሙ ትምሮ ብቻ አይነፋም ...! 💡 የተለያዮ EVENT እና TOUR እንዳትቀሩ ... በግቢ ቆይታ ፍራንክ ባይኖራቹ ራሱ ተበዳድራቹ ሀገር መጎብኘት አሪፍ ነው ። በቃ ceremony ሲኖር ....ይሂዱ ባክህ አትበሉ ዳግም የሚገኝ ነገር አይደለም ጦቢያን የምር የምታውቁበት ነው ። ትምህርተ ጋር ካልተጋጨ በየ ግዜው በአስተባሪዎች ጉዞ ይኖራል ። ስለዚህ.... አትቅሩ ...የመፅሀፍ ምረቃዎች ....አነቃቂ ንግሮች ...ትያአታራዊ ዝግጅቶች ይደረጋሉ .....አትቅሩ ....ታዋቂ ሰዎች በየግቢ እየመጡ በተለይ ወጣቶች የህይወት ልምዶቻቸውን ስለሚያጋሩ .....የምታደንቋቸው ሰዎች በየትኛው መንገድ ነው የተሳካላቸው ....የሚለው የህይወት ጉዞን ትማሩበታላቹሁ ...የፈታ ኢቨንቶችም አሉ በቃ ....ፈተና ሲያልቅ ምናምን ከች የሚሉ እና ሳትንዘላዘሉ ተሳተፉ ....እነ ሮፍናን ደግሰው መቼስ አይቀርም .....እነ እሸቱ መለሰ እየቀለዱ መቅረት ይከብዳል .... ⏰ አዳዲስ ነገሮች ሞክሩ ...አትፍሩ ❓ 📚 አዳዲስ ነገሮች የማድረግ ዕድሉ ስለሚኖረን ምንአቧቱ በእናት ሆድ አይለመድ አትፍሩ ሞክሩ ....ታዲያ ሱስ ምናምን ሳይሆን አሪፍ የሚባሉ ነገሮች የፍቅር ህይወትም ቢሆን ትምህርትን በማይነካ መልኩ ቢደረግ አይከፋም (ታዲያ ለሴሚስተር የሚቆይ ሳይሆን የምር መሆኑኑን ካመናችሁ ..) ....በግ ተራም ቢሆን አንዳንዴ መሄዱ ለክፉ አይሰጥም (አመራችሁ ዴ ቀልዴ ነው..) .....ሀገራቹ ሄዳቹሁ ለማውራትም ኮ መሞከሩ አይከፋም ።ግን ብዙ አትንዘላዘሉ ...ቸክሉ ...በቃ የሚያስደስታችሁን አዲስ ነገር ሞክሩ .....ብዙዎች ካንፓስ ሃይማኖተኛ ያረጋቸዋል አንዳንዶች ደሞ ...."ፈላስፈ አንዳነዶች ....ዘልዛላም ይሆናል ....አንዳንዴ ሳታስቡት ሃርድ ውስጥ ትገቡ ይሆናል ....ታዲያ ያን ግዜ አትጨናነቁ ...Normal ነው ። በተረፈ መልካም ካንፓስ! share and join for more👇 @assignment_supporter 💬በመጨረሻም ካንፓስ ላይ ቆይታቹሁ ልትደሰቱበት የሚችሉበትን የማትፀፀቱበትን ነገር ብቻ ከውኑ ። በቃ ያማረ የግቢ ቆይታ እንዲሆንላቹ ምኞቴ ነው ። ጥሩ ጥሩ ነገሮች ሊያውም የማይደገሙ ሲያጋጥማቹሁ አትለፉ እርግጥ ዋናው ጉዳያቹሁ ትምህርት ቢሆንም ...መደሰቱ መሳተፉ አይከፋም ። አይዞን በቆንጆ ሁኔታ ይታለፋል ። 📌 join and share 👇👇👇 https://t.me/assignment_supporter @assignment_supporter any comments 👇👇 @positive_thinkerrr

📢 ግቢ ውስጥ ስለሚኖሩ ሽወዳዎች🤩 ሽወዳዎቹ በnegative በኩል ከሆኑ ችግር ሊገጥማቹህ ስለሚችልና አንዳንድ የሞኝ ቀልድ ቀልደው በዛውም የሚያመሩ ተማሪዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ ንብረቶቻቹህ ላይ ባለፈው እንድልኳቹህ ጠንቀቅ ማለት ይበጃል ፤ ለምሳሌ አንዳንድ ነባር ተማሪዎች ወይም ፍሬሽ የዶርም አባላቶቻቹህ ለቀልድ ብለው ስልካችሁን ደብቀው ምናልባት ሰይጣን ሹክ ቢላቸው 🏃‍♀️🏃‍♂️...... እኔ አምናና ካቻምና የተወሰኑ ፍሬሾች እንደቀልድ ብዙ ንብረት እንደተበሉ አስታውሳለሁ  ስለዚህ ንብረቶቻችሁን በንቃት ለመጠበቅ ሞክሩ እንጂ positive ሽወዳዎችን ብትጠነቀቁም አለመሸወድ አትችሉም ። እንደውም አልሸወድም ብላቹህ ክባድ ስታበዙ ለፉገራ ጊዜ የሌለው senior ሁላ ሊሸውዳቹህ ይችላል ። የሰማችሁት ይመስለኛል ግን ላልሰማቹህ ፍሬው ሚል መጽሐፍ ላይ (by the way ቀለሜወች አንቡት ከፈለጋችሁ እለቅላችሁ አለሁ ፈታ ሚያረግ ቁም ነገር ያለበት ስለ fresh ተማሪ ሚዳስስ ነው)👇 🐒 አንዱ ጦጣ የሴቶች ሸኖ ዘው ብሎ ገብቶ ሲጠቀም አንዷ ቺከስ "ሰው አለ ?" ብላ በሩን ስታንኳኳ ፈታ ብሎ "ሰው አለ" አላት 😄 🙆‍♀️ ድምፁ የወንድ ስለሆነ ብትደነግጥም ልጅቱ ቀሽት ስለነበረችና ቀኑሽ የጦጣዎች መግቢያ ቀን ስለነበር 👩‍🎤" ፍሬው ነህ ? " አለችው 👀እሱም 👉 " እረ ፍሬው አይደለሁም እኔ ደምሌው ነኝ 👌😀😀" አላት ይባላል። አስቡት እሷ ፍሬው ነህ? ያለችው ፍሬሽ ነህ ወይ ለማለት ፈልጋ ነበር እሱ ግን ፍሬው የሚባል ግለሰብ የተጠራ ስለመሰለው እኔ ደምሌው ነኝ አለ ። so ቀለሜወች መሸወድ ላይቀር ይችላል coz compoundun እና ላይፉን ስለማታውቁት ... ጦጣ ምን ማለት ነው ብላቹህ ግራ እንዳትጋቡ ፡ ጦጣ  🐒 ማለት ግቢ ውስጥ እንደ ጦጣ ግራ የሚጋባ ማለት ነው like  Ⓒ COC TUTORIAL ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬                 sᴛʀɪᴠɪɴɢ ꜰᴏʀ ᴇxᴄᴇʟʟᴇɴᴄᴇ ═════════════════════════            🎲 JOIN AND SHARE https://t.me/assignment_supporter                            @assignment_supporter            🎲 Feedback and comment                          @positive_thinkerrr

⚪️እንዴት አድርገን ብናጠና ነው ፡ ግቢ ላይ ውጤት መስራት የምንችለው🤔? 💠 አንዳንድ መምህሮች ሙሉ chapter ሩን እንድትፅፋ አድርገው ፈተና የሚያወጡ አሉ። ለምሳሌ ፡ List and describe , explain and discuss ምናምን እያለ handout ቱ ላይ ያሉትን ኖቶች እንድትፅፋ አድርጎ የሚያወጣ መምህር አለ። 💠 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ concept ጥያቄ የሚያወጡ አሉ። የ እናንተን የመረዳት ችሎታ የሚጠይቁ ጥያቄዎችን የሚያወጡ መምህሮች አሉ። 💠 አንዳንድ መምህሮች ደግሞ የ case ጥያቄዎችን ይጠይቃሉ። የ case ጥያቄዎች ደግሞ የእናንተን የመረዳት ፡ የማብራራት ፡ እና ተግባራዊነት የሚጠይቁ ናቸው። በተለይ እንደ psychology መሰል ኮርሶች almost ሙሉ ጥያቄው case ሊሆን ይችላል። ስለዚህ እንዴት እናብብ🤔 🔔 የመጀመሪያው ፈተና ላይ መምህሩ ምን አይነት የፈተና አወጣጥ ስታይል እንዳለው አታውቁም🤷‍♂️። ➡️ከመጀመሪያው ፈተና በሗላ ግን የመምህሩን የፈተና አወጣጥ ስታይል ማወቅ ትችላላችሁ። ስለዚህ 🔸 የ ሽምደዳ ጥያቄዎችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በዛው ልክ handout ቱን በ straw ምጥጥ አድርጋችሁ ማንበብ ነው። በርግጥ ሽምደዳ boring ነው ፡ በተለያየ ስልት አንብባችሁ መያዝ ነው። 🔹 መምህሩ የ concept ጥያቄችን የሚያወጣ ከሆነ ፡ እናንተም በቻላችሁ መጠን የብልጠት አነባበብ መከተል ነው። በቻላችሁት መጠን ሳይንሱን ለመረዳት ብላችሁ አንብቡ። 🔺 የ case ጥያቄዎች ከበድ ይላሉ ። ስለዚህ ስታነቡ ፡ የምታነቡት ትምህርት ተግባራዊ እውነታውን ማወቅ ፡ የት የት ቦታ apply እንደሚደረግ ፡ advantage and disadvantage ን ማወቅ ። ከዛ በዚህ መሰረት ማብራራት ነው ከእናንተ የሚጠበቀው። 🔸 ስለዚህ የአጠናን ስልታችሁ እንደመምህሩ ፈተና አወጣጥ ቢሆን ብለን እንመክራለን።      🔺የጊዜ አጠቃቀም 🔻ሌላኛው ና መሰረታዊ ነገር ጊዜያችሁን በአግባቡ የመጠቀም ጉዳይ ነው። ምንድን መሰላችሁ ፡ ብዙዎቻችን ቆይ ነገ አነበዋለሁ ፡ ቆይ ቡሗላ አነበዋለሁ እያልን የመዘናጋት አባዜ አለብን። ይህ ደግሞ የምናነባቸው ትምህርቶች እንዲደራረቡን ያደርጋል። ከ ተደራረቡብን ደግሞ በ tension ልንጨልል እንችላለን። ስለዚህ በተቻለን መጠን ፡ ሳንዘናጋ ፈተናዎች ከመድረሳቸው በፊት ብናነብ መልካም ነው።       🔸 አለመሰልቸት 🔹ግቢ ላይ ፈተናዎች ፡ አሳይመንቶች ፡ ፕሮጀክቶች ይደራረባሉ። በተለይ በቀጣይ ወደ ግቢ የምትገቡ ፍሬሽ ተማሪዎች ፡ ለ እያንዳንዱ ሴሚስተር የሚሰጣችሁ ጊዜ አጭር ነው። በዚህ ምክንያት ፈተና ቶሎ ቶሎ ነው የምትፈተኑት ፡ አሳይመንት ተደራርቦ ነው የሚሰጣችሁ። ምናልባት ዛሬ ተፈትናችሁ ፡ ነገም ሌላ ፈተና ትፈተናላችሁ ። ከፈተና እንደተመለሳችሁ አሳይመንት ልትሰሩ ትችላላችሁ ምናምን። እና ይኸ መደራረብ መሰልቸን ያመጣል። ስለዚህ ፅኑ መሆን ይጠበቅባችሗል።    🔸ከመምህር ጋር ሰላማዊ መሆን። 🔻ሁሉንም ማለት ባይቻልም የግቢ መምህሮች ባህሪያቸው አስቸጋሪ ነው። በቻላችሁ መጠን ከመምህራኖቻችሁ ጋር ሰላማዊ መሆን ፡ በትህትና መነጋገር ፡ ለመምህሩ የሚመች ክላስ መፍጠር አለባችሁ። ከመምህር ጋር የምትንገራገጩ ከሆነ ግን ፡ ሆን ብሎ ውጤታችን ያወርድባችሗል። ብዙ ገጠመኝ ስለማውቅ ነው በዚህ ጉዳይ።   @assignment_supporter https://t.me/assignment_supporter