cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥

╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗ ║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣ ╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩ አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶች የተለያዩ ፀሀፊዎች የስነጽሑፍ ስራዎች የሚቀርብበት ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ @ethio_leboled ✥--------------------✥ For your comment,feedback and promotion @Meki3 Thank you!

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
255
مشترکین
+224 ساؚت
+47 عوز
+1430 عوز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

Photo unavailableShow in Telegram
የዛሬው combo ላልጀመራቹ ጀምርዋት https://t.me/hamster_kombat_bOt/start?startapp=kentId5875888757
نمایش همه...
👍 1
Photo unavailableShow in Telegram
⚡️HamsteKombat ✅ከNotcoin ጋር ተመሳሳይ የሆነ ነው መልቲ ታፕ ስላላው እንደ Tapswap አሪፍ ነው ይሄኛውም ⚡️ በቅርቡ እስከ 50$ Reward ይኖራል ከአሁኑ ጀምሩ 🔗 https://t.me/hamster_kombaT_bot/start?startapp=kentId6405623892 ✅Bot ውስጥ እንደገባቹ play in 1 click የሚለውን ነክታቹ አስጀምሩ ✅ታስኮችን በመስራት ኮይን ማሳደግ ትችላላችሁ። ✅ትንሽ ኮይን እንደሰበሰባቹ Boost የሚለው ውስጥ በመግባት ታፕ የምትደረገው እና Recharge Speed አሳድጉ። ✅ Premium user 25k coin 😊 Normal user 5k coin @ethioleboled
نمایش همه...
የመጀመሪያዉ ስህተት የኔ ነበር! ከፈጣሪ ትዕዛዝ ዉጪ ሴት ስተዋወቅ! ህይወቴ ዉስጥ ልጨምራት ከፈጣሪ ተጋፍቼ ያመጣኋት ኢክራም የነበረኝን ብሩክንም አሳጣችኝ። ጌታዬ ልክ ነበር! ተሳስቶም አያዉቅም! አይሳሳትምም! ኢክራም ዛሬም መልካም ለመሆን ቅንጣት እንኳ አልረፈደባትም። ወደለመዱት መልካምነት መመለሾ ለኢክራም አይከብድም። ዛሬም የኢክራምን መልካም ስብዕና እናፍቃለሁ። የጋብቻ የጥሪ ካርዷን ስትልክልኝ አልማለሁ! እሷ ልሡ ከዘቀጡበት ፈልጋ ሰብስባ ያፀዳቻቸዉ ነብሶች ዛሬ እሷን እንደመታደግ ሲጠቋቆሙባት ሳይ እበሳጫለሁ። ኢክራም ከነክህደቷ ብዙ ንፁሀንን አፍርታለች። በጨዋዋ ኢክራም እጅ ንፅህናን የተቀበሉ በሙሉ ኢክራምን ወደነበረችበት ከፍታ የመመለስ ግዴታ አለባቸዉ። ብሩኬም መልካም ለመሆን ጊዜዉ አልረፈደበትም። ብሩኬ ለመበላሸቱ ምክንያት የሆኑትን ነገሮች ለማጤን ሞክሬ ነበር። ዋናዉ ፊልም ነዉ። ፊልሞቹን በከፊል ወስጄ ተመለከትኳቸዉ። ስሜት ተኮር ናቸዉ። "የሰዉ ልጅ የተመለከተዉን ነገር ይተገብራል" ይላል ስነ አእምሮ! የሰዉ ልጅ ባህሪዉን የሚገነባበት አንዱ መንገድ ሲደረግ ያየዉን በመማር (imitation) ነዉ። ብሩክ ለመበላሸቱ ይመለከታቸዉ የነበሩት ፊልሞች ግንባር ቀደም ምክንያት ናቸዉ። ሁለቱም ሰዎች ናቸዉ ተሳሳቱ! እኛ ስህተት ባይኖርብን ፈጣሪ እኛን አጥፍቶ ሌሎች የሚሳሳቱ ህዝቦችን ይፈጥር ነበር። ግን ዋናዉ ነገር ጥፋትን ተረድቶ ለመፅዳት መሞከር ነዉ። ጥፋቱ ክህደት ሆኖ ወንጀላቸዉን አገዘፈዉ እንጂ ብዙ መልካም ነገር ይኖራቸዋል። . ብርጭቆ መሬት ላይ ወድቆ ሲሰበር ከነበርኩበት የሀሳብ ሰመመን ነቃሁ! አንዱ ጠረዼዛ ላይ ያሉት ጥንዶች ናቸዉ የሰበሩት። ካፌዉ ዉስጥ አራቱ ቴብሎች ላይ ጥንዶች ተቀምጠዋል። ረሂማ እየሳቀች ወደኔ መጣች! ከኪሴ ልከፍል ብር እያወጣሁ ነበር። ረሂማ እየሳቀች "ወተቱስ?" አለችኝ። ወይኔ ለካ ቅድም ልታሞቀዉ ወስዳዉ ነበር እርስት አድርጌዋለሁ። "እሺ የታለ?" አልኳት እየሳቅኩ! "አሙቄዉ እዛ ቴብል ላይ ወተት ታዞ ነበር እና ለሹ የታዘዘ መስሏቸዉ ወሰዱት! አንተም ሙድህ ስለወረደ አዉቄ ነዉ ዝም ያልኩህ!" አለችኝ እየሳቀች። . ካፌዉ ዉስጥ ያሉትን ጥንዶች ተመለከትኳቸዉ! ይስቃሉ ፣ይጎነታተላሉ! እስከሚጣሉ ይጎነታተሉ አልኩ በልቤ! አዎ ተዋደዱ፣ከነፉ፣ተጣልተዉ አረፉ! ነዉ ከትዳር ዉጪ ያለ ፍቅቅሮሽ መዳረሻ። ሲከፋም የወንዱም የሴቷም ክብር በዝሙት ይገፈፍና ለንፁሀን የተከለከሉ ቆሻሻ መሆንን ነዉ የሚያተርፈዉ። . ፊርደዉስ ደወለችልኝ። አነሳሁት! "አንተ እዛ መቆዘሚያ ካፌህ ነህ አይደል?" አለችኝ። "አዎ ምነዉ ፊርዱ?" አልኳት "በዚህ ስሜት ዉስጥ ሆነህ መጠየቁ አግባብ ይሁን አይሁን አላዉቅም! ግን ፈዊ ፈቃደኛ ከሆንክ ካንተ ጋር ኒካህ ማሰር እፈልጋለሁ! ገንዘብ ምናምን የሚለዉ አያሳስብህ ነብዩ ሙሀመድ(ሰዐወ) የመጀመሪያ ሚስታቸዉን ኸዲጃን(ረዐ) ሲያገቡ እሷ በጣም ሀብታም ነበረች! የእዉነት ሀይማኖተኛ ከሆንክ ይሄ አይጠፋህም" አለችኝ። የኔ አንበሳ ይሄን ታሪክ ማወቋ በራሱ አስገርሞኛል። እንዴት እንዴት ነዉ ያገናኘችዉ? ቆንጆ ፖለቲከኛ ይወጣታል። ደሞ ለሡ ኒካህ ምን አላት? እድሜ ለአባቷ! ገንዘብ እንደልቧ ነዉ። እኔ የማስተዳድራት እንጂ የምታስተዳድረኝ ሴት ማግባት አልፈልግም። "ፊርዱዬ ከኔ ጋር ወንድምነቱ ይሻለናል እሺ! እኔ ለጋብቻ ብቁ ነኝ ብዬ አላምንም!" አልኳት። ለጋብቻ ብቁ ሆኜ ቢሆንማ ኢክራምን እስከአሁን አግብቼ ነበር። "ፈዉዛን እኔ ምን ያንሰኛል? ዉበት ከፈለግክ ማንም አይጠጋኝም ታዉቃለህ! ገንዘብ አለኝ እንደፈለግክ አድርገዉ! ከማንም እኔ እሻልሀለሁ።" አለች እየተነጫነጨች። በራስ መተመመኗ እና ግልፅነቷ በጣም ደስ ይለኛል። "ፊርዱ እኔ አንቺ ምንም ይጎድልሻል አላልኩም ግን እኔ ብቁ አይደለሁም! ለሌላ ጊዜ ብቁ ስሆን ግን ከዉበትሽ እና ከገንዘብሽ በላይ ሀይማኖትሽ ላይ ያለሽን አቋም ስለምፈልገዉ እሱን አሻሽይ!" አልኳት እየሳቅኩ። "እሺ በቃ እንደድሮዉ!" አለችኝ እንዳንኮራረፍ ፈርታ። "እሺ ፊርዱ ፈታ በይ!" አልኳትና ስልኩን ዘጋሁት። ረሂማ ሚስተናገድ ሰዉ የለም መሰለኝ አጠገቤ መጥታ "አንተ ግን ዛሬ ምን ሆነህ ነዉ?" አለች። መልሴን ሳትጠብቅ ወዲያዉ ስልኬን ከጠረጴዛ ላይ አንስታ ሰዓት አየች። እግረ መንገዷን ሰሞኑን የፃፍኩትን ግጥም ዋልፔፐር አድርጌዉ ስለነበር አየችዉ። እየሳቀች ጮክ ብላ አነበበችዉ "ስምሽ ጎዳደፈ አነሱሽ በክፉ፣ ከንፈር ማሳበጤ ይሄ ነዉ ወይ ትርፉ? ደግሜ ብስምሽ ይፀዳ ይሆን ወይ የህሊና እድፉ!" አሽኮረመመችኝ! ረሂማ ወዲያዉ ተስተናጋጅ ስለመጣ ትታኝ ሄደች። ወዲያዉ ስልኬ ጠራ! ረዊና ነበረች። አነሳሁት። "ፈዉዛኔ የት ነህ? አዲስ አበባ መጥቻለሁ!" አለችኝ። ረዊና ንፁህ እህቴ ናት! ሁሉንም ነገር ለሡ መተንፈስ ነበር የሚቀለኝ። "ስማ ከትምህርት ቤቱ ጀርባ ያለዉ ልብስ ቤት ነኝ! አትመጣም?" አለች! "መጣሁ!" ብያት ከካፌዉ ተነስቼ ወጣሁ። ከመሸሸጊያዬ ወጣሁ! የወዳጅ ጦር ቅርብ ርቀት ላይ ነዉ። ንፁህ እህትነት! ረዊና!           ♾#ተፈፀመ♾ እውነተኛ ታሪክ ስለሆነ  እንደድርሰት ልቦለዶች መጨረሻቸውን  አላሳመርነውም ምክንያቱም እውነተኛ ታሪክ  የእውነት ስለሚቀመጥ   ሁሉም ታሪኮች ፍፃሜያቸው አያምርም  ከታሪኩ የምንማረውን እንማራለን የምንቀስመውን እንቀስማለን። አንብባችሁ ከወደዳችሁት  ያላችሁን ሀሳብ አስቀምጡልኝ Like አርጉልን እኛ ሺ ፊደል ተጭነናል ፡                       ,,, ✦━━
نمایش همه...
👍 1
.              ♥️●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞እውነተኛ እና አስተማሪ ታሪክ💞                     #የመጨረሻው_ክፍል ...🖊ፊርደዉስ የተሰማኝን መሰበር ስለተረዳችዉ ያን ሰሞን ከጎኔ አትጠፋም ነበር። ትምህርት እየቀረች ሁላ እኔ ትምህርት የሌሉኝን ሰዓቶች አብራኝ ታሳልፋለች። የኢክራም መንፈስ እየለቀቀኝ ነዉ መሰል ግጥም ፃፍኩ! ለፊርዱ አነበብኩላት "ፀሀዩ ጠቋቁሮ ፣ ሰማይ ጠል ለበሰ፣ የክህደትሽ ክፋት ብዕሬን ነቅንቆ ጉድሽን አዳረሰ። ዱላ አልማዘዝም ከድታኛለች ብዬ፣ እችልበታለሁ በብዕር መቅጣቱን በፍቅር አባብዬ" . እኔ ከጀርባዬ ሲሰል የነበረዉን ድራማ እንዳወቅኩ ብሩኬም ሆነ ኢክራም እንዲያዉቁ አልፈለግኩም። ትንሽ ጊዜ ብሩኬ እና ኢክራም ላይ መዝናናት ፈለግኩ። ብሩኬን እንደድሮዉ በስርዓቱ አገኘዋለሁ! ቤቱ ሳይቀር እየሄድኩ አብሬዉ አሳልፋለሁ። የማዉቃቸዉን ነገሮች እጠይቀዋለሁ፣በዉሸቱ እዝናናለሁ። ኢክራምን ፌስቡክ ላይ እንደድሮዉ አወራታለሁ። ልክ ምንም እንዳልተፈጠረ! በነገራችን ላይ ፊርዱ የኢክራምን የፌስቡክ ፓስወርድ አሳይታኝ ስቄ አላባራሁም። "ብሩክ" ነበር ፓስወርዷ! ብሩክ የሚል ስም ይዞ አሁን ሰዉ እንደዚህ አይነት ተግባር ይፈፅማል? ለነገሩ በስም ከተባለ የነብይ ስም ይዘዉ እንዲህ ርካሽ ተግባር የሚፈፅሙም አይጠፉም። እምነት አንዴ ከተሸረሸረ መልሶ ማምጣት አይቻልም። ፈረንጆቹ እምነት እንደ ድንግልና ነዉ አንድ ጊዜ ከጠፋ መልሶ ማምጣት አይቻልም! የሚሉት ለዚህ ይመስለኛል። ጊዜዉ እየገፋ ሲመጣ ህመሙን ዉስጤ ማመቁ ስለሰለቸኝ ብሩኬን ላናግረዉ ወሰንኩ። . ብሩኬ ጋር ደወልኩለት! እነ ሄኖክ ሰፈር እንደሆነ እና ሲመለሾ እንደሚደዉልልኝ ነገረኝ። እነ ሄኖክ ሰፈር ማለት እነ ኢክራም ሰፈር ማለት ነዉ። ከሷ ጋር እንደሆነ እርግጠኛ ሆንኩ። ሲመለሾ ደወለልኝ። አገኘሁት። ሳየዉ ሳቄን መቆጣጠር አቃተኝ። እየሳቅኩ "የት ነበርክ?" አልኩት። በጥርጣሬ አይን እያየኝ "እዚሁ ነበርኩ ባክህ ማደያዉ ጋር!" ምናምን ብሎ ቀባጠረ። ዛሬ እዉነት እዉነቷን እንድናወራ ስለፈለግኩ በአይኔ የት እንደነበረ እንደማዉቅ የሚያሳይ ምልክት ሰጠሁት። የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ! ሰዉን በንግግሩ ዉስጥ ችግሩን ተረድቶ ማከም ነዉ የምማረዉ። ያወቅኩ መሆኑን ስለጠረጠረ እየሳቀ! "ባክህ ከሚስትህ ጋር ነበርኩ!" አለኝ። የሚስትነት ስሟን ለኔ፣ ተግባሩን ደግሞ ለሹ ከፋፍሎት መሆን አለበት ከሚስትህ ጋር ያለኝ! "ሚስትህ ስትል አስታወስከኝ ባይዘዌይ ሰሞኑን የሆነ ሰዉ አካዉንቷን ሀክ አድርጎት ነበርና ከብዙ ሰዉ ጋር ያደረገቻቸዉ ምልልሶች በሶፍት ኮፒ ተዘጋጅተዉ ሊላኩልኝ ነዉ!" አልኩት። ብሩኬ ደነገጠ! "ማነዉ ይሄ ባለጌ የሰዉ አካዉንት ሀክ የሚያደርገዉ?" አለኝ እየተበሳጨ። በዉስጤ እስቃለሁ። "አላወቅኩም ግን የሚጠቅምህን ነገር አግኝተንበታል ነዉ ያሉኝ! እነሱ ከኔ የሚፈልጉት ነገር ስላለ ጊቭ ኤንድ ቴክ መሆኑ ነዉ!" አልኩት ፊቱን እያነበብኩ። ከብሩኬ ጋር እያወራን የነበረዉ ዎክ እያደረግን ነበር። ዎክ እያደረግን እነ ረዊና ቤት አካባቢ ደረስን! ብሩኬ ወሬ ለማስቀየር ይሁን አላዉቅም "አንተ ግን እምነትን ልብላት ስልህ እምቢ አልክ አይደል?" አለኝ። የረዊናን እህት እምነትን ነዉ። ፈገግ ብዬ "ብሩኬ ቆይ ስንቱን ልተዉልህ?" አልኩት! ብሩኬ እንደድንጋይ ደርቆ "ማንን ተዉክልኝ?" አለኝ። እየሳቅኩ "ከእምነት ሌላ ምድር ላይ ያሉትን ሴቶች ሁሉ ትቼልሀለሁ!" ብዬ አስቀየስኩ። . ብሩኬ የኢክራም አካዉንት ሀክ መደረጉ በጣም አንገብግቦታል። "ፈዊዬ ጓደኛህ አይደለሁ! ቢያንስ የኔን እንዳይልኩልህ አድርግ!" አለኝ። "ያንተማ ቢላክልኝም ምንም ሚያስጨንቅህ ነገር የለም። እኔ ነኝ ማነበዉ! አንተ ከኔ ደብቀህ ከኢክራም ጋር የምታወራዉ ነገር ስለሌለ አትጨነቅ።" አልኩት። ከጀርባዬ ጭንቅላቱን ይዞ ቆሞ "ፈዉዛኔ ካነበብከዉ ያጣላናል!" አለኝ። የእዉነት እኔን ከመረጠ መጀመሪያ እሷን እንቢ አይልም ነበር! አንቺዉ ታመጪዉ አንቺዉ ታሮጪዉ አሉ! መጫወቱ ሲበቃኝ ወደ ብሩኬ ዞር ብዬ አይን አይኑን እያየሁ "ግን ምኗን ወደድከዉ?" አልኩት። ብሩክ ሁሉንም ማወቄን አረጋገጠ። "በቃ ሁሉንም እነግርሀለሁ!" አለኝ። ድራማዉ ከጀርባዬ ላለፉት ስምንት ወራት እየተተወነ እንደነበር ነገረኝ። ኢክራም ስለምታሳዝነኝ ነዉ ምናምን ብሎ ቀባጠረ! የእዉነት ቢያዝንላት የኔን ዉሳኔ እንድትተገብር ነበር ሊያበረታታት የሚገባዉ። "ብሩኬ እኔ ይቅርታ አድርጌልሀለሁ! ኢክራምን የምትወዳት ከሆነም ግንኙነታችሁን መቀጠል ትችላላችሁ!" አልኩት። ብሩኬን ላለፉት አስር አመታት አዉቀዋለሁ! በአንድ ሴት ምክንያት በቃኸኝ ልለዉ አልችልም። ምንም ዛሬ ቢከዳኝም ብዙ ከባባድ ጊዜዎቼን አብሬዉ አሳልፌያለሁ። ለኔ መልካም ሰዉ ነበር። ግን አንድ ፈተና ማለፍ አቃተዉ። . በቀጣዩ ቀን ከብሩኬ ጋር ተገናኝተን ስናወራ ሾለሡ አዉርቶ መዘባረቅ ሲጀምር "ቆይ ግን እኔን እንደዛ እወድሀለሁ እያለች የከዳችኝ ኢክራም አንተን ዞራ እወድሀለሁ ስትልህ ነገ ወደ ሌላዉ እንደማትዞር በምን እርግጠኛ ሆንክ? ቢያንስ በኔ አትማርም?" አልኩት። "ባክህ እኔ አልወዳትም!" አለኝ። "ታዲያ ለምን እሺ አልካት?" "እሷ እወድሀለሁ አለችኛ!" በጣም ተበሳጨሁ! ቢያንስ ኢክራምን ወዷት ሴትነቷ አሳስቶት ቢከዳኝ እሺ! ግን እንዲሁ ለመንዘላዘል ነዉ ክህደት የሰራብኝ? ከምር አበሳጨኝ! እምቢ ማለት አለመቻል ትልቁ ዝቅጠት ነዉ። ጠጣ እሺ! ቃም እሺ! ጓደኛህን ክዳ እሺ! በጣም ያሳፍራል። ከብሩኬ ጋር እንደድሮዉ ለመሆን ብሞክርም በፍፁም ሊሳካልኝ አልቻለም። እምነት ከተሸረሸረ ትልቅ አደጋ ነዉ። . ኢክራም ያደረገችዉ ነገር ምንም አስቀያሚ ቢሆንም ልቤ ዉስጥ ቅንጣት ጥላቻ ሊፈጠር አልቻለም። አሁንም በጣም ታሳዝነኛለች። ምናልባት ፈጣሪዬ ከሱ ቀድቼ ለኢክራም የተናገርኩትን ወዶልኝ ይሆን? "ያለፈዉንም የሚመጣዉንም ጥፋትሽን ይቅር ብዬሻለሁ!" ያልኳትን። አይ እንደዉም የወደፊቱን ይቅር ማለት ከሱ ሌላ ማንም እንደማይችል እያሳየኝ ነዉ የሚሆነዉ! ግን አሁንም ለኢክራም ያለኝ እዝነት አልቀነሰም። አንድ ቀን ሁሉንም ነገር ማወቄን ፌስቡክ ላይ ነገርኳት። በጣም ደነገጠች። እኔ አሁንም የድሮዋን ጨዋዋን ኢክራም ለመሆን ብትሻ ላግዛት ዝግጁ ነኝ። ግን ኢክራም ክህደቷን መቋቋም አቃታት መሰለኝ ከፌስቡክ ብሎክ አደረገችኝ። የተበደልኩት እኔ! ዘራፍ ባዩ ሌላ! ይገርማል። ፈጣሪዬ ግን ማገናኘት ካሻዉ ማንም አያግደዉምና ብሎክ ባደረገችኝ በነጋታዉ መንገድ ላይ ተገጣጠምን። ዉስጤ ላይ ምንም ጥላቻ የለም። ልክ እንደድሮዉ ፈገግ አልኩላት! ፈገግታዬን ስታይ ወደኔ መጣች። ሰላም ከተባባልን በኋላ ስለትምህርቷ አወራን! እሷ ግን ከመወዛገቧ የተነሳ ስለያዝኩት ቦርሳ ዘባረቀች። ኢክራምን ከረጅም ጊዜ በኋላ በአካል አገኘኋት! እንደሚሉት የተጋነነ የአለባበስ ለዉጥ አላስተዋልኩም! በርግጥ ጅልባቡ ወልቆ ቀሚሱም ጠቧል። የጠበቅኩት የተጋነነ ስለነበር ነዉ መሰለኝ ብዙም አልደነገጥኩም! . አሁን የሚቆጨኝ እኔ ስበላሽ ከጎኔ ሆና ያረመችኝን ኢክራምን ዛሬ የክህደት እና የስነ ምግባር ዝቅጠት ዉስጥ ስትዘፈቅ ልታደጋት አለመቻሌ ነዉ። ለሰዉ ልጅ ክብር ወሳኙ ነገር ከማንነት መሾመር የወጣን አፈንጋጭነት እንቢ ማለት መቻል ነዉ።
نمایش همه...
እሱም የቀድሞ ፍቅረኛዉን የሪሀናን ጓደኛ እና የአስር አመታት ጓደኛዉን የእኔን የትዳር ቅዠት ሲያማግጥ ህሊናዉ እንዴት ዝም አለዉ? ደግሞ እኮ ቃል በቃል "ኢክሩ እንድታገባ እንጂ ከማንም ወንድ ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!" ብዬዋለሁ። አደራ ብዬዉም ነበር! ጌታዬ ሆይ በከለከልከኝ መንገድ ላይ ተጉዤ የነገድኩት ንግድ ኪሳራን እንጂ አላተረፈልኝም! . ፊርደዉስ ቁርሱን ሰርታ አቀራርባ እንድንበላ ልትጠራኝ ስትመጣ አልጋዉ ላይ ተዘርሬያለሁ። ከአይኔ እንባ ይጎርፋል። እንሰቀሰቃለሁ። "ፈዉዛኔ ምን ሆንክብኝ?" አለች እየተንደረደረች መጥታ አንገቴን ቀና እያደረገች። በጣቶቼ ላፕቶፑን ጠቆምኳት። ሄዳ አነበበችዉ። ፊቷ ደም እንደለበሰ ወደኔ ዞራ "ብሩክ አንተን ከዳህ?" አለችኝ ስለ ብሩክ ታዉቅ ነበር። ፊርደዉስ ከኔ በላይ መበሳጨት ጀመረች። "ለኢክራም እኮ መልአክ ነበርክ ፈዊ! ምላሿ ይሄ ነዉ?" አለችኝ ንዴቷ ይበልጡኑ እየተቀጣጠለ። አልጋዉ ላይ ከወገቤ ቀና ብዬ ተስተካክዬ እየተቀመጥኩ "ብዙ ጊዜ ያለመድሽዉ ዉሻ ነዉ የሚነክስሽ!" አልኳት። "ፈዊ ኢክሩን ቆንጆ ቅጣት ልትቀጣት ይገባል!" አለች ፊርደዉስ ግድግዳዉን እየደበደበች እንደ እብድ ጮክ ብዬ እየሳቅኩ "ኢክራም እኮ ቅጣት አያስፈልጋትም እኔን ከድታ ብሩኬ ላይ የወደቀች ቀን ራሷን ቀጥታለች። ንፁህ ልቤን ረግጣ ፊልም ላይ ስትመለከተዉ የኖረችዉን ዝቅጠት ለመተግበር ስትሞክር እና ከቅዱሳን ተራ ስትወጣ ያኔ ራሷን ቀጥታለች። እኔ መቅጣት አይጠበቅብኝም። የሚታዘንላት ለንግስትነት የታጨች ዉብ ከመሆን ማንም እንዳሻዉ የሚጨልፋት ርካሽ መሆንን ስትመርጥ ያኔ ራሷን ቀጥታለች።" ንግግሬ ሲያልቅ ሰዉነቴ መንዘፍዘፍ ጀመረ። እየተንሰቀሰቅኩ አለቀስኩ። በህይወቴ እንዲህ ያለቀስኩባቸዉ ቀናት ዛሬ እና ኢክሩ ልታገባ ስትል ናቸዉ። ሁለቱም በኢክሩ ምክንያት! ደካማ ጎኔ ሴት ናት! ከሴት ደግሞ ኢክራም! ፊርደዉስ ለቅሶዬ ሲበረታ አልጋዉ ላይ ከጎኔ ቁጭ ብላ ማባበል ጀመረች። በእጆቿ እንባዬን ጠረገችልኝ። ደንዝዣለሁ። ብደበደብም የሚሰማኝ አይመስለኝም። ፊርደዉስ እጆቿን ወደ አንገቴ ወሰደቻቸዉ። ከንፈሬ ላይ ተለጠፈች። እኔ አያታለሁ ላስቆማት አልቻልኩም ደንዝዣለሁ! አይኔ እያየ ስልኳን አዉጥታ ከንፈሬ ላይ እንደተጣበቀች ሰልፊ ፎቶ አነሳች። ፊርደዉስ ዉርርዷን ፈፀመችብኝ። አደነቅኳት። ምንም የስነ አእምሮ ምሁር ብትሆን ሴት ልጅን ተንኮል አትበልጣትም። ዛሬ ካፌ ሳይሆን ቤት እንድንገናኝ ያደረገችዉ አጋጣሚዉን ለመጠቀም ብላ ነበር። በንፁህ አእምሮ ብሆን ኖሮ ሁሉም ይገባኝ ነበር። ግን የኢክራምን ጉድ ለማየት መጓጓቴን ፊርዱ ተጠቀመችበት። ፊርዱ ባደረገችዉ ነገር ምንም አልተቀየምኳትም። እልህ ተያይዘን ነበር! እሷ አሸነፈች አለቀ! አእምሮዬ ሲረጋጋ ፊርዱን በአክብሮት እንድታቆም ጠየቅኳት። ወዲያዉ አቆመች። አየኋት ቆንጆ ናት! ከኢክራምም የበለጠች ቆንጆ! ግን በሰዓቱ በፍፁም ስለሴት ማሰብ ስላልፈለግኩ ትቻት ወደ ሳሎን ሄድኩ። ፊርዱ የሰራችዉ ቁርስ ላይ እልሄን ተወጣሁበት! ፊርዱም መጥታ አብረን በልተን ተያይዘን ከቤቱ ወጣን!
نمایش همه...
●●●ነጠብጣብ●●●♥️             💞ሊጠናቀቅ አንድ ክፍል ቀርቶታል                            #ክፍል_17 ራሴን አረጋጋሁ እና ኢክሩ ልታናደኝ ፈልጋ እንጂ እንደዚህ የምታደርግ ልጅ እንዳልሆነች ብዙ ምክንያቶችን እየሰጠሁ ራሴን አሳመንኩት። እንደዉም እኔ እወድሻለሁ ስላት አይኗን ወደ ሰማይ እየሰቀለች "ፈዉዛኔ የኔ ድመት አንተ ትወደኛለህ። እኔ ላንተ ያለኝ ፍቅር ግን ካንተ በጣኣኣኣም ይልቃል።" ያለችዉን አስታወስኩ። ኢክሩ በሁለት ወር ዉስጥ ይሄን ፍቅሯን ከልቧ አስወጥታ ከነገስኩበት የልቧ ዙፋን ላይ ሌላ ሰዉ እንደማታስቀምጥ ለልሴ ነገርኩት። "ምንም ችግር የለዉም። መብትሽ ነዉ!" ብዬ መለስኩላት። አልተናደድኩልሽም እንደማለት ነበር ያሰብኩት። እኔ ፍቅረኛ ይዤ ከሆነ ጠየቀችኝ እንዳልያዝኩ ነገርኳት። . ወደ ማታ ላይ ብሩኬን አግኝቼ የተፈጠረዉን ነገር ነገርኩት። ኢክሩ ፍቅረኛ ይዛ ከሆነም ሁለቱን ለመነጣጠል ስል የፍቅር ግንኙነት ከሷ ጋር ልጀምር እንደምችል ነገርኩት። ማንም እንደኔ ሊያስብላት አይችልም ብዬ አምናለሁ። ቢያንስ ከኔ ጋር ከሆነች ዝሙት ላይ አትወድቅም። ሌላ ወንድ ኢኩ ላይ ስሜቱን ሲያስታግስ መመልከት አልፈልግም። ኢኩ ንግስት ሆና ባል ስታነግስ ነዉ መመልከት የምሻዉ። አንገቴን አቀርቅሬ "ብሩኬ ኢኩ የእዉነት የፍቅር ግንኙነት ጀምራ ከሆነ እኔ ኢኩን እና ልጁን ለማጣላት ከሷ ጋር የፍቅር ግንኙነት እስከመቀጠል ድረስ ለመጋፈጥ ወስኛለሁ።" አልኩት ብሩኬ እንደመቆጣት እያለ "በቃ ተዋት የራሷን ህይወት ትኑርበት!!" አለኝ ሳግ እየተናነቀኝ "ብሩኬ እኔ እኮ እንድታገባ እንጂ ከማንም ጋር እንድትንዘላዘል አይደለም የተዉኳት!!" አልኩት። "በቃ ተዋት አይመለከትህም!!" አለኝ አሁንም ቆጣ እንዳለ ነዉ። ብሩኬ ይሄን አቋሜን ስላልደገፈልኝ ተበሳጨሁ። ከዚህ በኋላ የምወስዳቸዉን እርምጃዎች እሱን ሳላማክር ለመዉሰድ ወሰንኩ። . ፊርደዉስ ክረምቱን በተደጋጋሚ እየደወለች እንድንገናኝ ትጠይቀኛለች። እኔ ግን ዉርርዷን ልትፈፅምብኝ እንደሆነ ስለማስብ ላገኛት ፈቃደኛ አልሆን አልኳት። እዉነት ለመናገር በኔና በሷ መካከል ሀይማኖት እና ማህበራዊ ስርዓታችን ልቅ መሳሳምን ባያወግዝ ኖሮ እኔ ነበርኩ ከንፈሯ እንደ ኢክሩ እስኪያብጥ የምስማት!! ግን ሰዉ እንደመሆኔ እንደ እንስሳ ማሰብ የለብኝም። ስጋዬ ይፈልጋል አልዋሽም!! ግን ፈጣሪዬን ማስቆጣት አልፈልግም። እሱን ካስቆጣሁ አንዷን ፊርደዉስን አግኝቼ ጌታዬን ላጣ እችላለሁ። እሱን ባስደስት ግን ጌታዬ የፊርደዉስ አይነት ሴቶች ካዝና በእጁ ነዉ። አንድ ቀን ሀሙስ እለት ፊርደዉስ ደዉላ የጓደኛቸዉን ልደት ስለሚያከብሩ እንድገኝ ጠየቀችኝ። ሙስሊም ስለሆንኩ ልደት እንደማላከብር ነገርኳት። "ኧረ ፈዉዛኔ ይሄን ያህልማ አታካብደዉ!!" አለችኝ። በሷ ቤት አክርሬባት ሞታለች። "ፊርደዉስ እኔ ሙዴ እንደዚህ ነዉ!! እንደየሙዳችን ብንሆን ይሻላል ከምንከራከር!" አልኳት "እሺ በጣም ጥሩ!! በርዝደይ ፓርቲዉ ላይ እኔም አልገኝም። ካንተ ጋር መገናኘት እፈልጋለሁ።" አለችኝ። ተስማምተን ቀጠሮ ያዝን። . ፊርደዉስ ስትስቅ ጉንጮቿ በጣም ይሰረጉዳሉ። በጣም ታምራለች። ሳር ቤት አካባቢ ተገናኘን። መኪና ይዛ ነበር የመጣችዉ። ገቢና ገብቼ ከዚህ በፊት ገብቼበት ወደማላዉቀዉ መናፈሻ ይዛኝ ሄደች። ቦታዉ በጣም ቆንጆ ነዉ። መኪናዋን ቦታ አስይዛ ካቆመችዉ በኋላ ከመኪናዉ ወርደን ዉቡ የሳር መናፈሻ ላይ የተቀመጡት ወንበሮች ላይ ተቀመጥን። "ፈዉዛኔ እኔ ማንንም ወንድ እንዳንተ ተለማምጬ አላዉቅም። ይህን ሁሉ የማደርገዉ እንድስምህ ስለተወራረድኩ ብቻ መስሎህ ከሆነ ተሳስተሀል! አንተ የራስህ አቋም አለህ። እንቢ ማለት መቻልን አስተምረኸኛል። እኔ ደግሞ አላማ አለኝ። ይሄን አላማዬን ለማሳካት ካንተ የተሻለ አማካሪ የማገኝ አይመስለኝም።" አለችና በረዥሙ ተነፈሰች ፊርደዉስ የኮምፒዩተር እዉቀቷ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ከነገረችኝ እቅዶቿ ተረዳሁ። ያለማቋረጥ ለአንድ ሰዓት እቅዷን ነገረችኝ። አሁን ፊርደዉስን በጣም አከበርኳት። በምችለዉ ሁሉ ላግዛትም ቃል ገባሁላት። . የኢድ አል አድሀ ማለትም የሀጅ ስነ ስርዓት እንዳለቀ ያለዉ የኢድ በዓል ደረሰ። ሁልጊዜም እንደማደርገዉ በስም ቅደም ተከተል ሰዎች ጋር እየደወልኩ እንኳን አደረሳችሁ እያልኩ በኢ ተርታ ያሉት ጋር ደርሼ ኢክራም ጋር ደወልኩ። የዛሬን አያድርገዉና ሌላ ጊዜ መጀመሪያ እሷ ጋር ደዉዬ ነበር ቀሪዎቹ ጋር በስም ቅደም ተከተላቸዉ የምደዉለዉ። አነሳችዉ "ኢኩዬ እንኳን አደረሰሽ!!" አልኳት። "እ ንኳን አብሮ አደረሰን!" አለችኝ እየተንጠባረረች "በዓል እንዴት ነዉ?" አልኳት "ጥሩ ነዉ አለችኝ" በአጭሩ። በመልሷ በጣም ተበሳጨሁ በስርዓቱ ተሰናበትኳትና ስልኩን ዘጋሁት። እኔ የስነ አእምሮ ተማሪ ነኝ ኢክራምን እንዲህ ያንጠባረራት ጉዳይ እንዳለ ተገለፀልኝ። አዎ ኢክራም ፍቅረኛ ይዛለች። ካንተ ሌላ ላፈር ስትለኝ የነበረችዉ ኢኩ በሁለት ወር ዉስጥ ሌላ ሰዉ ለምዳለች። ሰዉዬዉ ማን እንደሆነ ማወቅ ፈለግኩ። ኢክራምን በቅርብ ርቀት መሰለል ይኖርብኛል። ትኩረቴን ሙሉ ኢክራም ላይ አደረግኩ። አሁን ስላለችበት ሁኔታ በአምስት ቀናት ዉስጥ ሙሉ መረጃ ሰበሰብኩ። አዎን የኢክራም ህይወት ባልገመትኳቸዉ መንገዶች ሁላ ሳይቀር ተለዉጧል። ማመን የማልችላቸዉን መረጃዎች አገኘሁ።...    ብዙ ሰዎች ኢክሩ በፍፁም ጥፋተኛ እንዳልሆነች ነዉ የሚያስቡት። "ሳይቸግርህ ጭረሀት" "አንተ ነህ የተዉካት!!" ምናምን ይሉኛል። መተዉ ምን ማለት ነዉ? እኔ እኮ ኢክሩን በጊዜዉ ለማግባት ስለማልችል እንድታገባ ብዬ ነበር የተለየኋት። አደራ ያልኩት እኮ ፈጣሪዬን ነበር። እኔ እሷን የመናፈቅ እሳቴን አፍኜ ይብቃን ስላት ለሡ የወደፊት ህይወት ማማር እየተሰዋሁ እንደነበር ለምን አይገባቸዉም? ተዋት ይላሉ እንዴ? አቅሜን አዉቄ ለፈጣሪ አሳልፌ በሰጠሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? አስመሳይ ሁላ!! ለነገሩ የነሱ ወሬ ለኔ ምንም ነዉ። ያመንኩበትን ነገር እንጂ አላደርግም! ስሜት ያወረዉ ትዉልድ የሚታይ ድርጊት እንጂ የታፈነ ስሜት አይገባዉም። ኢክራም እንደተሰዋሁላት እንዲገባት ከፎቅ ላይ ራሴን መፈጥፈጥ አይጠበቅብኝም። ማንም ሳያዉቅ በልቤ እንደታፈንኩ እኖራለሁ። በኔ ዝምታ ዉስጥ ብዙ ትርጉም ነበር። እሷን በመተዌ ያሳለፍኩትን ስቃይ እኔ ነኝ የማዉቀዉ። እስከዛሬ ጠረኗ የማይረሳኝ ሰዉ እኮ ነኝ!! ከሷ በኋላ ማንንም ያላየሁ!! አዎ የሱመያን የድምፅ መስረቅረቅ አድንቄያለሁ ፣ የፊርደዉስን ዉበት አሞግሻለሁ ግን አንዳቸዉንም ከምላሴ አሳልፌ ልቤ ዉስጥ አላስገባሁም። በሁሉም ሴቶች ዉስጥ የምትታየኝ ኢኩዬ ነበረች። ሁሌም ቃሌን አስታዉሳለሁ። ስንለያይ ለልሴ የገባሁትን ቃል!! የማግባት የስነ ልቦና እና የገንዘብ አቅም ሲኖረኝ መጀመሪያ ኢኩዬን ፈልጌ ካላገባች ላገባት ለልሴ የገባሁትን ቃል!! ተዋት ይላሉ እንዴ? ለሡ አልጋዉን አደላድዬ እኔ መሬት ላይ በተኛሁ ገፋት ይላሉ እንዴ? ወረኛ ሁላ!! ሲጀመር እነሱ የመዉደድን ልክ የወደዱትን የራስ ከማድረግ አሻግረዉ መመልከት አልቻሉም። እኔ ዉዴታዬ በዝቶ ለኢክሩ ባል ተመኘሁላት!! ኢክሩ ንግስት እንድትሆን ከነክብሯ እንድትለየኝ አደረግኩ። ጌታዬን አስደስቻለሁ እሷ የፈለገችዉን ትበል ግድ የለም። እንደኔ ያሰበላት፣ ወደፊትም የሚያስብላት ሰዉ ግን የሚኖር አይመስለኝም። እንዳተኙ 4 ሰአት ላይ ቀጣዩን ክፍል ይጠብቁን ነጠብጣብ ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል እስከዛ Like share
نمایش همه...