cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

የነብያት ሀይማኖት

وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ Και ο Θεός σας είναι Ένας Θεός (ኢስላማዊ ዳዕዋ) (ንፅፅር) (ጥያቄና መልስ) (ሳይንስ እና ኢስላም) (ኢስላም ጠል ለሚያነሱት መልስ)

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
226
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
اطلاعاتی وجود ندارد7 روز
-230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

ጉዳዮቻችን (፩) ........ ዛሬ ላይ በዙሪያችን ይብዛም ይነስም ዋቢ የምናደርጋቸው ዑለማእ አሉ ማለት ይቻል ይኾናል። ቀጣዩ ትውልድ ግን ከወዲኹ የዕውር ድንብር ጉዞ ለመጓዝ የተሰናዳ ይመስላል። ይህ በእሳት-ራት የሚመሰል ትውልድ በቅንጥብጣቢ መረጃ ሆዱን ሞልቶ "ልቦቻችን በዕውቀት ተሞልቷል" እንዳሉት አይሁዶች በመረጃ ቁምጣን እየተንገላታ ነው። መረጃ ብቻ የሚሰጠው ሚዲያም በዕውቀት አስተማስሎ (animation) የወጣቱን ለም ጭንቅላት አራሙቻ እየዘራበትና ውድ ጊዜውን እየቀማ በምናብ ዓለም ከፍ ብሎ እንዲንሻለል አድርጎታል። አንድ ሐቅ አለ ይኸውም ነገር-ዓለሙ ኹሉ ሰው-ሰራሽ (artificial) በኾነበት ተጨባጭ ዕውን (real)ኾነህ ለመገኘት መሞከር በራሱ በባለጌዎች መሐል ብቻኽን ጨዋ ለመኾን ከመሞከር በላይ ነውር ነው። ወዳጄ ሉጥ (ዐለይሂ አሰላም) በነዛ ቆሻሾች መሐል ብቻውን ከምን እንደተቆጠረ ልብ ይሏል። ዛሬ ላይም ከተለመደው ውጭ ግን ደግም በትክክል ትውልድ ቀራጭ ሐሳብ ይዘህ ብትመጣ፣አንተ ያኔ በቆንጥር ጫካ ውስጥ የበቀልህ ጽጌሬዳ ነህ። ወይ ይቀጥፉኻል፣ አሊያም ቆንጥሩ ተብትቦኽ ትጠፋለህ። አኹን ላይ አሰላሳይ (ሙፈኪር) ነን የሚሉቱ የትላንቶቹ ዳዒዎቻችን ምን ሲያሰላስሉና ሲያስተምሩ እንደከረሙ ከፍሬያቸው እያየን ነው። በነሺዳ ስም በዘፈን መንፈስ የነሆለለ፣መናገር እንጂ ማዳመጥም መማርም በሽታው የኾነ፣ ኢስላምን እሱ በፈለገበት መንገድ እየመነዘረ መኖር የሚሻ፣ለልጆቹ በጭራሽ አርኣያ መኾን የማይችል ከንቱ ትውልድ ተፈጥሮኣል። ያሉን እጅግ ጥቂት ዑለማም ቢኾኑ በባዶ ሆዱ ቀንበር ለመጎተት እንደሚታትር በሬ ናቸው። በሬ ሆዱ ባዶ ከኾነ ቀፎ ጭንቅላቱ ቀንበር አይጎትትም። ረባኒይ ሊባሉ የሚችሉ ዑለሞቻችን ሐብታምቻችን ለካልሲ መግዣ በሚያወጡት ሳንቲም ቤተሰባቸውን ሰብስበው ይኖራሉ። ታዲያ እንደምነው በባዶ ሆዳቸው ይህንን ባላዋቂነት የገዘፈ ወጣት መጎተት የሚቻላቸው? https://t.me/E_M_ahmoud
نمایش همه...

😢 1
نمایش همه...
فضيلة الشيخ العلامة الدكتورجيلان خضر غمدا الإثيوبي / شرح العقيدة الطحاوية

Photo unavailableShow in Telegram
የአሁኑ የኡለሞች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሸይህ ዶ/ር ጀይላን ኸድር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/drjeilan
نمایش همه...
የአሁኑ የኡለሞች ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሸይህ ዶ/ር ጀይላን ኸድር ይፋዊ የቴሌግራም ቻናል https://t.me/drjeilan
نمایش همه...
ፍልስጥኤም በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው። 2፥251 "በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ "ፊልሥጢን" فِلَسْطِين ማለት "ፍልስጥኤም" ማለት ሲሆን በአንድ ወቅት የፍሊሥጢን ንጉሥ "ጃሉት" جَالُوت ማለትም "ጎልያድ" እና ሠራዊቱ ከጧሉት ማለትም ከሳኦል ሠራዊት ተዋግተዋል፦ 2፥249 ጧሉትም በሠራዊቱ ታጅቦ በወጣ ጊዜ፡- «አላህ በወንዝ ፈታኛችሁ ነው፥ ከርሱም የጠጣ ሰው ከእኔ አይደለም፡፡ ያልቀመሰውም ሰው በእጁ መዝገንን የዘገነ ሰው ብቻ ሲቀር እርሱ ከእኔ ነው» አለ፡፡ ከእነርሱም ጥቂቶች ሲቀሩ ከርሱ ጠጡ፡፡ እርሱ እና እነዚያም ከእርሱ ጋር ያመኑት ወንዙን ባለፉት ጊዜ፡- «ጃሎትን እና ሠራዊቱን በመዋጋት ለኛ ዛሬ ችሎታ የለንም» አሉት፡፡ እነዚያ እነርሱ አላህን ተገናኝዎች መኾናቸው የሚያረጋግጡት፡- «ከጥቂት ጭፍራ በአላህ ፈቃድ ብዙን ጭፍራ ያሸነፈች ብዙ ናት፤ አላህም ከታጋሾች ጋር ነው» አሉ፡፡ فَلَمَّا فَصَلَ طَالُوتُ بِالْجُنُودِ قَالَ إِنَّ اللَّهَ مُبْتَلِيكُم بِنَهَرٍ فَمَن شَرِبَ مِنْهُ فَلَيْسَ مِنِّي وَمَن لَّمْ يَطْعَمْهُ فَإِنَّهُ مِنِّي إِلَّا مَنِ اغْتَرَفَ غُرْفَةً بِيَدِهِ ۚ فَشَرِبُوا مِنْهُ إِلَّا قَلِيلًا مِّنْهُمْ ۚ فَلَمَّا جَاوَزَهُ هُوَ وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ قَالُوا لَا طَاقَةَ لَنَا الْيَوْمَ بِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ ۚ قَالَ الَّذِينَ يَظُنُّونَ أَنَّهُم مُّلَاقُو اللَّهِ كَم مِّن فِئَةٍ قَلِيلَةٍ غَلَبَتْ فِئَةً كَثِيرَةً بِإِذْنِ اللَّهِ ۗ وَاللَّهُ مَعَ الصَّابِرِينَ ከዚያም በጦርነቱ ተፋልመው ተስፋ በቆረጡ ጊዜ ዳውድ ጃሉትን ገሎታል፦ 2፥250 ለጃሉት እና ለሠራዊቱ በተሰለፉም ጊዜ፡- «ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አንቧቧ፤ ጫማዎቻችንንም አደላድል፤ በከሓዲያን ሕዝቦችም ላይ እርዳን» አሉ፡፡ وَلَمَّا بَرَزُوا لِجَالُوتَ وَجُنُودِهِ قَالُوا رَبَّنَا أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًا وَثَبِّتْ أَقْدَامَنَا وَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ 2፥251 "በአላህም ፈቃድ ድል መቷቸው፥ ዳውድም ጃሉትን ገደለ"፡፡ فَهَزَمُوهُم بِإِذْنِ اللَّهِ وَقَتَلَ دَاوُودُ جَالُوتَ ቁርኣን ላይ ስለ ፍልስጥኤማውያን የሚናገረው እነዚህ አናቅጽ ላይ ነው። ሚሽነሪዎች፦ "ፍልስጥኤማውያን ፍልስጥኤም የምትባል አገር የላቸውም" እያሉ ባላነበቡት ነገር ይዘባርቃሉ። ፈጣሪ እስራኤልን ከግብጽ ምድር እንዳወጣ ሁሉ በጥንት ጊዜ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር አውጥቶ የራሳቸው ግዛት ሰቷቸዋል፦ አሞጽ 9፥7 እስራኤልን ከግብጽ ምድር፥ ፍልስጥኤማውያንንም ከከፍቶር፥ ሶርያውያንንም ከቂር አላወጣሁምን? ኢዮኤል 3፥4 ጢሮስና ሲዶና የፍልስጥኤምም ግዛት ሁሉ ሆይ! ከእናንተ ጋር ለእኔ ምን አለኝ? በውኑ ብድራትን ትመልሱልኛላችሁን? "የፍልስጥኤምም ግዛት" የሚለው ይሰመርበት ፍልስጥኤም ግዛት ከነበረች ለምን መብቷ አይከበረም? እስራኤላውያን ቦታቸው መጥተው ሰፈሩባቸው እንጂ ጥንትም ቢሆን የእስራኤል ቅም አያት አብርሃም ከከላዳውያን ኡር በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀምጧል፦ ዘፍጥረት 21፥34 "አብርሃምም በፍልስጥኤም ምድር ብዙ ቀን እንግዳ ሆኖ ተቀመጠ"። ፍልስጥኤም መጤ ሳትሆን የራሷ ምድር ስለሆነ "በፍልስጥኤም ምድር" የሚል ኃይለ-ቃል ተጽፏል። ባይብል ላይ ብዙ ቦታ "የፍልስጥኤም ምድር" እያለ ይናገራል፦ ኤርምያስ 25፥20 የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ "የፍልስጥኤም ምድር" ነገሥታትንም ሁሉ አስቀሎናንም ጋዛንም አቃሮንንም የአዞጦንንም ቅሬታ"። ዘጸአት 13፥17 እንዲህም ሆነ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር "በፍልስጥኤማውያን ምድር" መንገድ አልመራቸውም። ፍልስጥኤማውያን የራሳቸው አገር አላቸው፥ እስራኤላውያን የሰፈሩበት ከነዓን ሁሉ ሳይቀር የፍልስጥኤማውያን ምድር ነው፦ 2ኛ ነገሥት 8፥2 ሴቲቱም ተነሥታ እንደ እግዚአብሔር ሰው ቃል አደረገች፤ ከቤተ ሰብዋም ጋር ሄዳ "በፍልስጥኤም አገር" ሰባት ዓመት ተቀመጠች"*። ሶፎንያስ 2፥5 "የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ"፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው። ዛሬ አገር እና ግዛት እንደሌላቸው እና መጤ እንደሆኑ ታይቶ እየተፈናቀሉ ነው፥ አሏህ ነስሩን ያቅርብላቸው! አሚን። ይህንን የምንለው ስለ ሐቅ እና ስለ ፍትሕ ነው፥ "ኢሥላም ሰም እና ወርቅ የያዘ ቅኔ ነው፥ ሰሙ ሐቅ ሲሆን ወርቁ ፍትሕ ነው" ስንል ዕውር ድንብ ጸለምተኛ ሙግት ይዘን ሳይሆን ጠቅሰንና አጣቅሰን በመሞገትና በመሟገት ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን! አሚን። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom ወሠላሙ ዐለይኩም
نمایش همه...
ወሒድ የንጽጽር ማኅደር

ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ-አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Photo unavailableShow in Telegram
በጁሪሽ የሚገኝ አንድ ፍልስጤማዊ ገበሬ መሬቱ የቤተሰቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የኦቶማን ማህተም ያለበት የ117 አመት የሽያጭ ሰነድ ይዞ የሚያሳይ ፎቶ። ይህ የ73 ዓመቱ ፍልስጤማውያን ከአያታቸው የተወረሱት ይህ ሰነድ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጠብቆ የቆየው የተበጣጠሰ ጠርዝ ባለው የፕላስቲክ ፍሬም ውስጥ ነው ብለዋል። "ይህ ከኦቶማን ዘመን የወጣ ሰነድ ነው አያቴ አብዱልፈታህ መንሱር በጁሪሽ 60 ሄክታር መሬት መግዛቱን የሚያሳይ ነው። ሰነዱ መሬቱ በአብዱልፈታህ መንሱር የተገዛ መሆኑን ያረጋግጣል። ከስር ደግሞ የኦቶማን ማህተም አለ። ይህ መሬት የኛ ቤተሰብ ንብረት ከ 1906 ጀምሮ ነው።
نمایش همه...
😍የጁመዐ ቀን(يَوْمِ الْجُمُعَةِ)😍 عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ مَنْ قَرَأَ سُورَةَ الْكَهْفِ فِي يَوْمِ الْجُمُعَةِ أَضَاءَ لَهُ مِنَ النُّورِ مَا بَيْنَ الْجُمُعَتَيْنِ የአላህ መልክተኛ እንዲህ አሉ ➯የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃን ያበራለታል። 📙 6470 المحدث الألباني خلاصة حكم المحدث صحيح في صحيح الجامع 📙 ↩️ عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه ، أن رسول الله ﷺ قال : غُسْلُ يَوْمِ الجُمُعَةِ وَاجِبٌ عَلَى كُلِّ مُحْتَلِمٍ ➷ ከአቢ ሰዒድ ኹድሪይ ረዲየላሁ ዐንሁ የተያዘ ሀዲስ መሊክተኛው ሶላላሁ ዐለይሂ ወሰላም እንዲህ አሉ፦የጁመዕ ቀን ለይ ትጥበት በሁሉም ለዒባደህ በደረሰ ሁሉ ሰው ላይ ግዴታ ነው። 📙رواه البخاري. 📙ኢማሙ ቡኻሪይ ዘግበውታል ↩️ عن أوس بن أوس رضي الله عنه قال : قال النبي ﷺ :((إنَّ مِنْ أفْضَلِ أيَّامِكُمْ يَوْمَ الجُمُعَةِ فَأكْثِرُوا عَلَيَّ مِنَ الصَّلَاةِ فِيهِ ؛ فَإنَّ صَلَاتَكُمْ مَعْرُوضَةٌ عَلَيَّ)) ➧ከአውስ ረዲየላሁ ዐንሁ የተያዘ ሀዲስ ረሱላችን ሶላለሁ ዐለይሂ ወሰላም እንዲህ አሉ ፦ ከበላጭ ቀኖቻችሁ ውስጥ ትልቁ ቀን ጁምዐ ነው በዚህ ትልቅ ቀን በኔ ላይ ሰላዋትን በብዛት አውዱብኝ ሰላዋታቹህ እኮ በተመደቡ መለኢካዎች አማካኝነት ወደ እኔ ይደርሰኛል። رواه أبو داود. አቡ-ዳውድ ዘግበውታል ↩️ عن زيد بن خارجة رضي الله عنه ، أن رسول الله ﷺ قال : ((صَلُّوا عَلَيَّ وَاجْتَهِدُوا فِي الدُّعَاءِ ، وَقُولُوا : اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ)) ➭ከዘይድ ኢብኑ ኸርጀታ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና ረሱል ሶላላሁ ዐለይሂ ወሰላም እንዲህ አሉ ፦ ➼በጁመዕ ቀን በኔ ለይ ሰላዋትን አውርዱ በዱዓ ለይ ታገሉ በሉም አላህ ሆይ በመሊክተኛው ሙሐመድ ሶላላሁ ዐለይሂ ወሰላም እና ባቤተሰባቸውም ለይ ሶለዋትህን ውዳሴህን አውርድ። 📙رواه النسائي. 📙 ጥራት ይገባውና አምላካችን አላህ እንዲ ብሏል 📜 قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾ [الأحزاب: ٥٦] አላህ እንዲህ ይላል {አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ;እናንተ ያመናቹ ሆይ በሱ(በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ} ↩️ عن أنس بن مالك رضي الله عنه ، عن النبي ﷺ أنه قال : ((الْتَمِسُوا السَّاعَةَ الَّتِي تُرْجَى فِي يَوْمِ الجُمُعَةِ بَعْدَ العَصْرِ إلَى غَيْبُوبَةِ الشَّمْسِ)) ✔️ከአነስ ረዲየላሁ ዐንሁ ከመልዕክተኛው ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰላም ያችን የጁመዕ ቀን ውስጥ ያለችውን ሰዐት ከዐስር ሶላት በኋለ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ ባለው ሰዐት ፈልጓት በዚች ሰዐት በዱዓ ጠንከር በሉ። 📙رواه الترمذي. 📙ቲርሚዚይ ዘግበውታል 🕋«اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ»🕋 https://t.me/+LbALJ_1IzU1iNGJk
نمایش همه...
የነብያት ሀይማኖት

وَإِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌ وَاحِدٌ Και ο Θεός σας είναι Ένας Θεός (ኢስላማዊ ዳዕዋ) (ንፅፅር) (ጥያቄና መልስ) (ሳይንስ እና ኢስላም) (ኢስላም ጠል ለሚያነሱት መልስ)

4_5841476004429695658.mp37.57 MB
"የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም!" ~ በነብያችን ﷺ ላይ የሚሳለቅ እራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም። የላካቸው አምላክ "መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ" ብሏቸዋል። ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው። ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር። አላህ ግን እራሱ ለመልእክተኛው ﷺ ተከላካይ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡- (فَٱصۡدَعۡ بِمَا تُؤۡمَرُ وَأَعۡرِضۡ عَنِ ٱلۡمُشۡرِكِینَ ۝ إِنَّا كَفَیۡنَـٰكَ ٱلۡمُسۡتَهۡزِءِینَ ۝ ٱلَّذِینَ یَجۡعَلُونَ مَعَ ٱللَّهِ إِلَـٰهًا ءَاخَرَۚ فَسَوۡفَ یَعۡلَمُونَ ۝ وَلَقَدۡ نَعۡلَمُ أَنَّكَ یَضِیقُ صَدۡرُكَ بِمَا یَقُولُونَ ۝ فَسَبِّحۡ بِحَمۡدِ رَبِّكَ وَكُن مِّنَ ٱلسَّـٰجِدِینَ ۝ وَٱعۡبُدۡ رَبَّكَ حَتَّىٰ یَأۡتِیَكَ ٱلۡیَقِینُ) "የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው። እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል። (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ። አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን። ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን። እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ።" [አልሒጅር፡ 94-99] ስለዚህ ተሳላቂዎቹ ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ﷺ ዝና የበለጠ ይገንናል። የውሾቹ ስም ይከስማል። ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና?! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ። ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ? በጭራሽ! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም። ግን የነብያችንን ﷺ ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን? መልሱ ግልፅ ነው። 1. አንዳንዶቹ በነብዩ ﷺ እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው። “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም? 2. ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው። ስለሆነም ሙሐመድን ﷺ ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል። እውነታው ግን ተቃራኒው ነው። ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው። ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጮሃሉ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም!! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው!....። ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል። ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር። ባይሆን ከኛ አንድ ነገር ይጠበቃል። ከሃዲዎችን የነብያችንን ﷺ ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል። አዎ የነቢዩ ﷺ ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል!! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ﷺ እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደ መልእክተኛው ሱና ይቅረብ፤ ትእዛዛቸውንም ይፈፅም፤ ከከለከሉትም ይራቅ። ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል። የአላህንና የመልክተኛውንም ﷺ ውዴታ ያፍሳል። ያ ሱብሓላህ! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ?! ያ ወሃ፞ቡ አንተ ወፍቀን! ኣሚን (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 08/2005) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
نمایش همه...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

كناشة ابن منور

یک طرح متفاوت انتخاب کنید

طرح فعلی شما تنها برای 5 کانال تجزیه و تحلیل را مجاز می کند. برای بیشتر، لطفا یک طرح دیگر انتخاب کنید.