cookie

ما از کوکی‌ها برای بهبود تجربه مرور شما استفاده می‌کنیم. با کلیک کردن بر روی «پذیرش همه»، شما با استفاده از کوکی‌ها موافقت می‌کنید.

avatar

ማኅበረ ቅዱስ ፋኑኤል

نمایش بیشتر
پست‌های تبلیغاتی
199
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-17 روز
-230 روز

در حال بارگیری داده...

معدل نمو المشتركين

در حال بارگیری داده...

፲፬) ክርስቶስን በግድ ሞተ የሚሉ ከሓድያን:- ክርስቶስ ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ነው። ሐማሚ ኢሐማሚ ነው። ቅድመ ተዋሕዶ ሥጋ (ባሕርየ ሰብእ በጠቅላላው) በግድ የሚራብ፣ በግድ የሚጠማ፣ በግድ የሚሞት ነበረ። በተዋሕዶ ሥጋ ቃልን ገንዘብ ባደረገ ጊዜ በፈቃዱ የሚራብ፣ በፈቃዱ የሚጠማ፣ በፈቃዱ የሚሞት ሆኗል። "ወእምዝ ዐርገ ዲበ ዕፀ መስቀል በፈቃዱ" እንዲል (ሃይ.አበ. ፹፬፣፲፬)። © በትረማርያም አበባው የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው።
نمایش همه...
Betremariam Abebaw

Betremariam Abebaw is on Facebook. Join Facebook to connect with Betremariam Abebaw and others you may know. Facebook gives people the power to share and makes the world more open and connected.

ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፭ #የምዕራፍ #ሁለት #መጨረሻ ፯) ንስጥሮስ:- የንስጥሮስ ክሕደት አንዱን ክርስቶስን ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ የሚል ነው። መጻሕፍት ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ እንደሆነ ነገሩን እንጂ ከየትኛውም ቦታ ላይ ሁለት እንደሆነ አልነገሩንም። "ቃልም ሥጋ ሆነ ጸጋንና እውነትንም ተመልቶ በእኛ ዐደረ፥ አንድ ልጅም ከአባቱ ዘንድ እንዳለው ክብር የሆነው ክብሩን አየን" እንዲል (ዮሐ. ፩፣፲፬)። ንስጥሮስ አያዋሐድም አያገናዝብም። በተዋሕዶ የቃል ገንዘብ ለሥጋ የሥጋ ገንዘብ ለቃል እንደሆነ አያምንም። "ቃል እውነትን ተመልቶ በእኛ አደረ" የሚለውን መነሻ አድርጎ ምንታዌን (ሁለትነትን) አስተምሯል። ማደር ማለት እኛ በቤት ውስጥ እንደምናድረው ያለ ነው። እንደምታውቁት እኛ በቤት ስናድር የቤቱ የራሱ አካል እንዳለው የእኛም የራሳችን አካል አለን። በቤቱ እናድራለን እንጂ ቤቱን አንሆንም። ቤቱ የእኛ ገንዘብ ነው። እኛ ግን የቤቱ ገንዘብ አይደለንም። ምንም ዓይነት መገነዛዘብ ስለሌለን ተዋሕዶ የለንም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ግን ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ስለሆነ አብሲማዳኮስ እየተባለ ይጠራል። ቅዱስ ጳውሎስም አዋሕዶ "በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ__" ብሎታል (ገላ. ፩፣፩-፪)። አንዱ ክርስቶስ አምላክም ሰውም ስለሆነ መካከለኛ እየተባለ ይጠራል። "አንድ እግዚአብሔር አለና፥ በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ ርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው" እንዲል (፩ኛ ጢሞ. ፪፣፭)። ከዚህም እንደምታዩት ክርስቶስን አንድ አለው እንጂ ሁለት አላለውም። ስለዚህ የንስጥሮስ ክሕደት ልብ ወለድ መሆኑ ታወቀ። እኛስ ከተዋሕዶ በኋላ ክርስቶስን ሁለት አንለውም። "ንሕነሰ ኢንቤ ክልኤቱ እምድኅረ ትድምርት" እንዳለ መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ (ድርሳን ፳፫)። የተሰቀለው የማርያም ልጅ፣ ያልሰተቀለው የአብ ልጅ ብለን ሁለት አናደርገውም። ቅዱስ ጳውሎስ አዋሕዶ "ዐውቀውስ ቢሆኑ የክብርን ጌታ ባልሰቀሉትም ነበር" ብሏል እንጂ ወልድን ከመሰቀል ውጭ አላደረገውም (፩ኛ ቆሮ. ፪፣፰)። ምራቁን እንትፍ ብሎ ጭቃ ያደረገውም፣ ዕውሩን ያዳነውም ያው አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው (ዮሐ. ፱፣፮-፯)። ክርስቶስን አምላክ ብቻ (ዕሩቅ ቃል) ነው እንዳንለው ለአምላክ ምራቅ የለውም። ሰው ብቻ (ዕሩቅ ብእሲ) ነው እንዳንለው ደግሞ ሰው በምራቁ ዕውርን ማዳን አይችልም። ስለዚህ አንዱን ክርስቶስን ለሁለት አንከፍለውም። እንደ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ አዋሕደን "ሞተ በሥጋ ወሐይወ በመንፈስ" እንለዋለን እንጂ (፩ኛ ጴጥ. ፫፣፲፰)። ሁለትነት በተዋሕዶ ጠፍቷል። እስመ ተዋሕዶ አእተታ ለምንታዌ እንዲል። ንስጥሮስ በ431 ዓ.ም በኤፌሶን በተደረገው አለማቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ጉባኤ ተወግዟል። ይህ ጉባዔ ሲደረግ አፈ ጉባኤው መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ ሲሆን በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ቴዎዶስዮስ ዘይንእስ ነበር። ፰) ከፍሎ ተዋሐደ የሚሉ:- እነዚህ ደግሞ ሥጋ ቃልን ገንዘብ ሲያደርግ በምልዐት አይደለም። የፀሐይ ብርሃን በመስኮት ተከፍሎ እንደሚገባ ከፍሎ ተዋሐደ የሚሉ አሉ። ነገር ግን ቅዱስ ማር ኤፍሬም "ወኢተዋሐደ በመንፈቀ ህላዌ" ብሎ ስለሚናገር ክሕደታቸው መሠረት አልባ መሆኑ ታወቀ (ሃይ.አበ.፵፯፣፴፪)። ቃል ሥጋን ሲዋሐድ ከሥጋ የተከፈለ ነገር የለም። ኩለንታ አካለ ሥጋን ኩለንታ አካለ ቃል ገንዘቡ አድርጎታል። ሥጋም ቃልን ገንዘቡ ሲያደርግ ኵለንታ አካላ ቃልን ኩለንታ አካለ ሥጋ ገንዘቡ አድርጎታል። ፱) አርዮስ:- አርዮስ ወልድ ፍጡር በመለኮቱ ያለ ከሓዲ ነው። ይኽውም ማንም ያልፈጠረው ፈጣሪ አብ ብቻ ነው። አብ መጀመሪያ ወልድን ፈጠረ ከዚያ በወልድ ፍጥረታትን ፈጠረ የሚል ክሕደትን አስተማረ። ነገር ግን አርዮስ በዮሐንስ ወንጌል ይሸነፋል። ዮሐንስ መጀመሪያ ቃል ነበር። ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበር ብሏል። ወልድ የአብ ቃል ከሆነና ወልድ ሳይኖር አብ ነበረ ካለ ቃል የሌለው (መናገር የማይችል) አብ ነበረ ያሰኝበታል። ይህ ደግሞ ትልቅ ስድብ ነው። በኒቅያ የተሰበሰቡ ፫፻፲፰ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ወልድ ከአብ ተወለደ እንጂ አልተፈጠረም አሉት። አርዮስ ግን ተወለደ ማለት ያው ተፈጠረ ነው አለ። ሊቃውንቱ ደግሞ አይ እኛ የምንወልደውን አልፈጠርነውም ብለውታል። "ሁሉ በእርሱ ሆነ" ስለሚል ፍጥረታትን ሁሉ የፈጠረ ስለሆነ ወልድን ፍጡር በመለኮቱ አንለውም ሲሉት አርዮስ ግን ፈጥሮ ፈጠረበት አለ። እንደዚያማ እንዳትል "ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም" ይልብሀል ብለው መፈናፈኛ አሳጥተው ኃይለ ቃል ጠቅሰው አሸንፈው አውግዘውታል (ዮሐ. ፩፣፩-፫)። በዘመኑ የነበረው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሲሆን የጉባኤው ሊቀመንበር እለእስክንድሮስ ነበረ። ፲) አርሲስ:- እነዚህ ከሓድያን ደግሞ ጌታ ነፍሳትን ለማዳን በነፍስም በሥጋም ወደሲኦል ሄዷል ብለው የሚናገሩ ናቸው። ነገር ግን ወንጌል እንደሚነግረን ነፍሱ ከሥጋው በዕለተ ዓርብ መጋቢት ፳፯ ቀን እንደተለየችና ሥጋውንም ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ገንዘው እንደ ቀበሩት ስለተጻፈ ክሕደታቸው መሠረት የለሽ ነው (ዮሐ.፲፱፣፵)። ፲፩) አውጣኪ:- መለኮት ሥጋን ውጦታል ያለ ከሓዲ ነው። ስለዚህ ሥጋ ወደመለኮትነት ስለተለወጠ አልታመመም የሚል ነው። ነገር ግን ቃል ሥጋ ሲሆን የሥጋ ገንዘብ ለቃል፣ የቃል ገንዘብ ለሥጋ ሆኗል። በዚህ ጊዜ መጠፋፋት ስለሌለ ሥጋ ግዙፍነትን፣ ውስንነትን እንደያዘ ቃልን ገንዘቡ በማድረጉ ረቂቅነትን፣ ምሉዕነትን ገንዘብ አደረገ። ቃልም ረቂቅነትን፣ ምሉዕነትን እንደያዘ ሥጋን ገንዘቡ በማድረጉ በድንግል ማኅፀን ተወሰነ፣ ታየ፣ ተዳሰሰ። ቃልና ሥጋ ሲዋሐዱ ያለ መጠፋፋት፣ ያለ መለወጥ ስለሆነ መለኮት ሥጋን ዋጠው የሚለው ትምህርት አያስኬድም። መለኮት ሥጋን ውጦት ቢሆን ኖሮስ ባልተራበ ባልተጠማ ባልተሰቀለ ነበር። ነገር ግን መለኮት ሥጋን ስላልዋጠው ክርስቶስ በሥጋ ተራበ፣ ተጠማ፣ ተሰቀለ እየተባለ ተገልጿል (ሉቃ. ፬፣፪፣ ዮሐ. ፲፱፣፳)። ፲፪) ሰባልዮስ:- ሰባልዮስ እንደ እስልምና እምነት ለፈጣሪ አንድ አካል አለው የሚል የነበረ ከሓዲ ነው። ይህ አንዱ አካል በብሉይ ኪዳን አብ፣ በሐዲስ ኪዳን ወልድ ከዚያ መንፈስ ቅዱስ ተባለ ይላል። ነገር ግን እግዚአብሔር በአካል ሦስት መሆኑን "እኔም አብን እለምናለኹ ለዘለዓለምም ከእናንተ ጋራ እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል" ብሎ ገልጿል (ዮሐ. ፲፬፣፲፮)። በዚህ ጊዜ አብን እለምናለሁ ያለ ወልድ ሌላ፣ አብ ሌላ፣ አጽናኝ የተባለው ሌላ መሆኑ በግልጽ ተጽፏል። አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የአካላት ስም ነው። እግዚአብሔርን አንድ ነው የምንለው በባሕርይው ነው እንጂ በአካል ሦስት ነው። ፲፫) መቅዶንዮስ:- ይህ ከሓዲ ከሥላሴ አንዱ የሆነውን መንፈስ ቅዱስን ፍጡር ያለ ነው። በዚህም ክፉ ትምህርቱ በ381 ዓ.ም በቴዎዶስዮስ ዘየዐቢ ዘመን በጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት ሊቀ መንበርነት በቁስጥንጥንያ አለማቀፋዊ የቤተ ክርስቲያን ጉባዔ ተወግዟል። መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ እንደሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ተገልጿል። "የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ" እንዲል (ኢዮ. ፴፫፣፬)።
نمایش همه...
በትረማርያም አበባው Betremariam Abebaw

አቀድም አእኵቶቶ ለእግዚአብሔር

Photo unavailableShow in Telegram
ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ቤት ናት። የሚሰበሰቡባትም አማኞች ናቸው እንጂ ኢአማኞች አይደሉም። የተወገዘ ሰውና እምነቱ ሌላ የሆነ ሰው ግን ቤተ ክርስቲያን እንዳይገባ ቅዱሳን አባቶቻችን ሥርዓት ሠርተዋል። "ይዕቀብዎሙ ለአናቅፀ ቤተ ክርስቲያን ከመ ኢይባኡ ኀቤሃ እደው እለ ኢኮኑ ምእመናነ አው ምእመናን ውጉዛን" ብሎ ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፩ በግልጽ ይነግረናል። ትርጉሙ ምእመናን ያልሆኑ ወይም ምእመን ሆነው ለጊዜው በቀኖና የተለዩ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስትያን እንዳይገቡ የቤተ ክርስቲያንን ደጆች ይጠብቁ ተብሎ ተገልጿል። ይህንን ተግባር ለማከናወን ከዐሥሩ የክህነት መዓርጎች አንዱ የሆነው ዐፃዌ ኆኅት (በር ዘጊ) ይሾማል። አሁን አሁን ግን እየተደረገ ያለው ሌላ ነው። ለምሳሌ ላሊበላ፣ ጎንደር ደብረ ብርሃን ሥላሴ፣ ባሕርዳር ገዳማት ላይ እና በጠቅላላ በቅርስነት ከተመዘገቡት ቅዱሳት መካናት የሌላ እምነት ሰዎች እንዲገቡና እንዲጎበኙ እየተደረገ ነው። ይህ ሁሉ ከክርስትናው ቀኖና ይልቅ Secularism እየመራን ለመሆኑ ማሳያ ነው። ቱሪስት ሃይማኖቱ ሌላ ከሆነ ቤተ ክርስቲያን ሳይገባ ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ያሉ ነገሮችን መጎብኘት ይችል ነበር። ይህ ግን እየሆነ አይደለም። ቅዱስ ጳውሎስ ተዋደዱ ብሎ ስለፍቅር ሲያስተምር መዋደድን በተሳሳተ ዐውድ ተርጉመውት ሚስታቸው ከሌላ ወንድ ጋር እንድታድር እስከ መፍቀድ የደረሱ ሰዎች ነበሩ። እኛ ኦርቶዶክሳውያን የሰውን ልጅ ሁሉ በእግዚአብሔር አርዓያ የተፈጠረ በመሆኑ እንወደዋለን። መውደዳችንን ለመግለጽ ብለን ግን ከማያምኑት ጋራ በአንድነት አንጸልይም። በጸሎት አንተባበርም። በሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮች በፍቅር እንኖራለን እንጂ። ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ን ከጨረስን በኋላ እስከ ርክበ ካህናት ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን እንማማራለን። © በትረማርያም አበባው
نمایش همه...
ሌላው ካቶሊኮች መንፈስ ቅዱስን ከአብም ከወልድም የሠረጸ ነው ብለው ያስተምራሉ። እኛ ግን ከአብ ብቻ የሠረጸ እንደሆነ እንናገራለን። "ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችኹ አጽናኝ ርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል" እንዲል (ዮሐ.፲፭፣፳፮)። መንፈስ ቅዱስ ከአብ የሠረጸ ነው ስንለው መሥረጹ አካላዊ ሆኖ ነው። ከወልድም ሠረጸ (ወጣ) እንዳይሉማ ወልድም ከአብ የተገኘ (የወጣ) ነው። ወልድም መንፈስ ቅዱስም ከአብ ሲወጡ ደግሞ አንድ ጊዜ ነው። መቀዳደም የለባቸውም። ወልድም ከአብ የወጣ ይባላል። "ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለኹ ደግሞ ዓለምን እተወዋለኹ ወደ አብም እኼዳለኹ" እንዲል (ዮሐ.፲፮፣፳፰)። መንፈስ ቅዱስም ከአብ የወጣ ይባላል። ሊቃውንት የወልድን ከአብ መውጣት ልደት ብለው ሲለዩት የመንፈስ ቅዱስን ከአብ መውጣት ደግሞ መሥረጽ ይሉታል። መጻሕፍት መንፈስ ቅዱስ ከአብ እንደወጣ (እንደሠረጸ) ይናገራሉ እንጂ ከወልድ እንደወጣ አይናገሩም። የመንፈስ ቅዱስ ከአብ መውጣትና የወልድ ከአብ መወለድ ከሰው ኅሊና በላይ ነው። "ልደተ ወልድ ወፀአተ መንፈስ ቅዱስ እምአብ ይትነከር ወኢይትነገር ወይትሌዐል ላዕለ ኵሉ ኅሊና" እንዲል (ሃይ.አበ. ፲፣፲፪)። ትርጉሙም ከአብ የወልድ መወለድ የመንፈስ ቅዱስ መሥረጽ በዕፁብ ይወሰናል እንጂ እንዲህ ነው ተብሎ አይነገርም ከኅሊና ሁሉ የራቀ ነው አይመረመርም ማለት ነው። © በትረማርያም አበባው የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው። ክፍል ፬ በነገረ ክርስቶስ ላይ የተነሡ ከሓድያንን እንመለከታለን።
نمایش همه...
Betremariam Abebaw

Betremariam Abebaw is on Facebook. Join Facebook to connect with Betremariam Abebaw and others you may know. Facebook gives people the power to share and makes the world more open and connected.

ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፫ #የካቶሊክና #የኦርቶዶክስ #ልዩነት ካቶሊካውያን ከእኛ ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሚለዩት በዋናነት በነገረ ክርስቶስና ምሥጢረ ሥላሴ ነው። በነገረ ክርስቶስ ክርስቶስን አንድ አካል ሁለት ባሕርይ ሲሉ እኛ ግን አንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው እንላለን። መለካውያን ኦርቶዶክስ የሚባሉት የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬን እና ሌሎችም ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት ውጭ ያሉት ኦርቶዶክሶች አንድ አካል ሁለት ባሕርይ በማለት ከካቶሊኮች ጋር ይመሳሰላሉ። በምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት ደግሞ ካቶሊኮች መንፈስ ቅዱስን ዘሠረጸ እምአብ ወእምወልድ ሲሉት እኛ ግን ዘሠረጸ እም አብ ብቻ እንለዋለን። ከካቶሊኮችና ከመለካውያን ኦርቶዶክሶች ጋር ክርስቶስን በአካል አንድ በማለት አንድ ስለሆንን ይህንን ጉዳይ አንመለከተውም። የልዩነታችን ምንጭ የሆነው የእነርሱ ሁለት ባሕርይ የሚለው ትምህርታቸውና የእኛ አንድ ባሕርይ የሚለው ትምህርታችን ነው። ይህንን በደንብ ለመረዳት መጀመሪያ ባሕርይ የሚለውን ትርጉም ማወቅ ያስፈልጋል። ባሕርይ ማለት አካላዊ ህልወ አካል ማለት ነው። ይኽውም አካል ያልሆነ ነገር ግን በአካል ያለ አካል የሚገልጠው የአካል መሠረት ማለት ነው። ይህ ባሕርይ አካል አይደለም። ነገር ግን ደግሞ ከአካል የተለየ ስላልሆነ አካላዊ ይባላል። ይህንን በምሳሌ ዘየሐጽጽ (ጉድለት ባለቤት ምሳሌ) ብንመለከተው ለምሳሌ እሳት ይሞቃል። የእሳት ሞቃትነት የእሳት ነበልባል ነው አይባልም። ነገር ግን ደግሞ ሞቃትነት ከነበልባሉ ተለይቶ ብቻውን የሚገኝ ነገር አይደለም። መሠረቱ ነበልባሉ ነው። ስለዚህ ሙቀትን ነበልባላዊ ልንለው እንችላለን። ይኽውም ከነበልባል ያልተለየ መሠረቱ ነበልባል የሆነ፣ ነበልባልን የሚገልጥ ማለት ነው። በመጻሕፍቶቻቸው በጌታ በሐዋርያት የተነገረውን ነገረ ክርስቶስን ጠንቅቀው ያስተማሩን ክቡር መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ አካልን ባሕርያዊ ብለው ከተረጎሙት በኋላ ባሕርይን ደግሞ አካላዊ ብለውታል። ምክንያቱም ከአካል የተለየ ባሕርይ፣ ከባሕርይ የተለየ አካል ስለሌለ ነው። ከነበልባል የተለየ ሙቀት፣ ከሙቀት የተለየ ነበልባል የለምና። ሊቁ ኪራኮስም በሃይማኖተ አበው ይህንን ገልጿል። ሥላሴ በባሕርይ አንድ ናቸው እንላለን። አንድ እንደሆኑም "ይትዋሐዱ በመለኮት ወይትሌለዩ በአካላት" ብሎ ሊቁ በሃይማኖተ አበው ገልጾታል (ሃይ.አበ. ፺፯፣፫)። አንዲት የሥላሴ ባሕርይ ግን ሦስት ኩነታት አላት። እነዚህም ቃል መሆን፣ ልብ መሆን፣ እና እስትንፋስ መሆን ናቸው። ካቶሊካውያን ከሁለት አካል አንድ አካል ለማለት ሥላሴ በአካል ሦስት ስለሆኑ ወልድ በተለየ አካሉ ከአካለ ሥጋ ጋር ተዋሕዶ አንድ ሆኗል ይሉና በባሕርይ ግን ሦስቱ አካላት አንድ ስለሆኑ ባሕርየ ሥላሴ ከሥጋ ባሕርይ ጋር ከተዋሐደ አብና መንፈስ ቅዱስም ሰው ሆኑ ያሰኛል በማለት የባሕርይ ተዋሕዶ የለም ብለው ሁለት ባሕርይ ይላሉ። ሁለት ባሕርይ ካሉ ዘንድ ባሕርይ በግብር ስለሚገለጽ ሁለት ግብረ ባሕርይ ይላሉ። ይኽውም መለኮት የመለኮትን ሥራ ይሠራል ሥጋም የሥጋን ሥራ ይሠራል ይላሉ። ነገር ግን አንዲት የሥላሴ ባሕርይ ሦስት ኩነት ስላላት በቃል ከዊን ሰው ሆነ እንላለን እንጂ በልብ ከዊን ወይም በእስትንፋስነት ከዊን ሰው ሆነ ስለማንል አብና መንፈስ ቅዱስ ሰው ሆኑ አያሰኝም። የሐዋርያት ተከታይ የነበረው ቅዱስ አግናጤዎስም በሃይማኖተ አበው "ኀደረ አሐዱ አካል እምሠለስቱ አካላት ውስተ ከርሣ ለእግዝእትነ ቅድስት ድንግል ማርያም። ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል ወልድ በእመቤታችን በንጽሕት ድንግል ማርያም ማኅፀን አደረ። በእንተ ተዋሕዶተ መለኮት ዘንትናገር በዝየ ዘህልው በወልድ። በዚህ አንቀጽ መለኮት ከትስብእት ጋር ተዋሐደ ብለን የምንናገርለት በወልድ ያለ ነው። ወአኮ በእንተ አብ ወመንፈስ ቅዱስ። ስለ አብ ስለ መንፈስ ቅዱስ አይደለም" ይላል (ሃይ.አበ.፲፩፣፫) ። ከዚህ ላይ መለኮት ዘህልው በወልድ ተብሎ የተገለጸው ከዊነ ቃልነት ነው። ወንጌላዊው ዮሐንስም የባሕርይ ከዊን ስም በሚጠራበት ስም "ቃል ሥጋ ኮነ" አለ (ዮሐ. ፩፣፲፬)። ስለዚህ ባሕርየ ሥላሴ በቃል ከዊን ከባሕርየ ትስብእት ጋር ተዋሕደው አንድ ሆኑ እንላለን። ደግሞም ለአንድ አካል አንድ ባሕርይ ይኖረዋል እንጂ ሁለት ባሕርይ የለውም። ሰው የነፍስና የሥጋ አንድ መሆን ውጤት ነው። ከሁለት አካል አንድ አካል፣ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ የሆነ ነው። በጊዜ ሞት ሥጋ ወደመቃብር ሲወርድ ነፍስ ከነ አካሏ ከነባሕርይዋ ወደ ገነት ወይም ወደሲኦል ትገባለች። በትንሣኤ ዘጉባኤ ሁላችንም ከሞት ስንነሣ ሥጋና ነፍስ እንደገና በፍጹም ተዋሕዶ አንድ ሆነው ይኖራሉ። ሰው የነፍስና የሥጋ ተዋሕዶ ስለሆነ አንድ አካል ሁለት ባሕርይ አንለውም። አይ ሰውንም አንድ አካል ሁለት ባሕርይ እንለዋለን ከተባለ ግን ወልደ እግዚአብሔር ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋንም ነፍስንም ስለነሣ ሎቱ ስብሐት አንድ አካል ሦስት ባሕርይ ወደማለት ክሕደት ያደርሳል። ለአንድ አካል አንድ ባሕርይ ነው ያለው። ክርስቶስን አንድ አካል ካሉ አንድ ባሕርይ ማለት ግድ ይላቸዋል። ቅዱሳት መጻሕፍትም ከየትኛውም ቦታ ላይ ክርስቶስን አንድ ብለው ጠሩት እንጂ ሁለት ብለው አልጠሩትም። አንድ ብለው ሲጠሩት ደግሞ በአካልም በባሕርይም ነው። "በርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷ፟ልና" እንዲል (ዮሐ. ፫፣፲፮)። ክርስቶስ የሠራውን ሥራም በተዋሕዶ እንናገራለን እንጂ ይህ የሥጋ ሥራ ይህ የመለኮት ሥራ እያልን አንነጣጥለውም። በአንድ ባሕርይ የአምላክነትንም የሰውነትንም ሥራ ይሠራል እንጂ። "በአሐዱ ህላዌ ይገብር ዘክልኤቱ ህላዌያት" እንዲል (ሃይ.አበ. ፵፯፣፴፪)። ካቶሊካውያንና መለካውያን ኦርቶዶክሶች አንድ አካል ማለትን ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት፣ ሁለት ባሕርይ ማለትን ከንስጥሮስ ወስደው ግማሽ ጣዖት ግማሽ ታቦት ሆነው ይኖራሉ። ንስጥሮስ ሁለት አካል ሁለት ባሕርይ ባይ ነው። በንስጥሮስ እሳቤ የሚታመም የማርያም ልጅ ነው፣ የማይታመም የእግዚአብሔር ልጅ ነው፣ የሚታየው የማርያም ልጅ ነው የማይታየው የአብ ልጅ ነው እያለ አንዱን ክርስቶስን ለሁለት ከፍሎ ያስተምራል። ቅዱስ ጳውሎስ "ጠላቶቹ ሳለን ከእግዚአብሔር ጋራ በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን" ብሎ በተናገረው ቃል ንስጥሮስ ይረታል (ሮሜ ፭፣፲)። ንስጥሮስ ወልደ እግዚአብሔር አይሞትም ብሎ ነበር። ነገር ግን "እግዚአብሔር በልጁ ሞት ታረቀን" ስለሚልበት ክሕደቱ መሠረት የለሽ መሆኑ ታወቀ። በተዋሕዶ የሥጋ ገንዘብ ሁሉ ለቃል፣ የቃል ገንዘብ ሁሉ ለሥጋ ስለሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ አብ ወልደ ማርያም ነው። አንዱ ክርስቶስ አምላክም ሰውም ነው። አንዱ ክርስቶስ ረቂቅም ግዙፍም ነው። አንዱ ክርስቶስ ምሉእም ውሱንም ነው። ይህ ደግሞ በተዋሕዶ ነው። ተራበ የተባለውም፣ የተራቡትን አጠገበ የተባለውም ያው አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። በመስቀል የተሰቀለውም በኪሩቤል ጀርባ የነበረውም ያው አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
نمایش همه...
ክርስቶስ ማለት ትርጉሙ ቅቡዕ (የተቀባ) ማለት ነው። ክርስቶስ የተቀባ መባሉ ግን ስለሰውነቱ ነው እንጂ በቃልነቱስ ቅድመ ዓለምም ክቡር ነው። መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስ "እለሰ ርቱዐ የአምኑ ይሜህሩ ከመ በሥጋሁ ተቀብዐ ቃል። አንድ አካል አንድ ባሕርይ ብለው የሚያምኑ ግን ከበረ መባሉ በሰውነቱ እንደሆነ ያስተምራሉ። እመሰ አማን ውእቱ አምላክ ቅብዐተ ኢይጽሕቅ። ሥጋን ያልተዋሐደ ዕሩቅ ቃልስ ከሆነ ከበረ መባልን አይሻም። እስመ አልቦ ኀበ ይቤ ከመ ተቀብዐ ቃለ እግዚአብሔር ። የእግዚአብሔር ቃል ከበረ የሚል የለምና። እምአመ ኮነ ሰብአ ከማነ ተቀብዐ ከመ ሰብእ። እንደ እኛ ሰው በሆነ ጊዜ በሰውነቱ ተቀብዐ ይባላል እንጂ" ብሎ እንደተናገረው። ቅባቶች ማቴዎስ ወንጌል አንድምታ ያለውንም ቃል ይይዙና መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ነው ለማለት ይጥራሉ። ነገር ግን ቃሉ የሚል "ወገባሪሁሰ ለውእቱ ሥጋ መንፈስ ቅዱስ እስመ ውእቱ ቀብዖ" ነው። በደንብ ተመልከቱት "ቀብዖ" አለ እንጂ "ቅብዐ ኮኖ" አላለም። በቀባዒነት ደግሞ ሦስቱም አንድ ስለሆኑ ቀብዖ ቢል ያስኬዳል። © በትረማርያም አበባው የፌስቡክ ገጼ:- Betremariam Abebaw https://www.facebook.com/profile.php?id=100075547015721 ነው። የዩቲይብ ቻናሌ:- ንሕነ ዘክርስቶስ https://youtube.com/@edenawizechristos?si=6V4y-73OM3LTzhAf ነው። ቀጣይ ክፍል ፫ የካቶሊክ፣ የመለካውያን ኦርቶዶክስና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልዩነት ምን እንደሆነ እንመለከታለን
نمایش همه...
Betremariam Abebaw

Betremariam Abebaw is on Facebook. Join Facebook to connect with Betremariam Abebaw and others you may know. Facebook gives people the power to share and makes the world more open and connected.

ነገረ ክርስቶስ ምዕራፍ ፪ ክፍል ፪ #የቅባትና #የተዋሕዶ #ሃይማኖት #ልዩነት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ እና የቅባት አስተምህሮ መሠረታዊ ልዩነት ያለው ነገረ ክርስቶስ ላይ እና ምሥጢረ ሥላሴ ላይ ነው። ነገረ ክርስቶስ ላይ ቅባቶች ሰው አምላክ ሲሆን ክብር (ቅብዕ) የሆነው መንፈስ ቅዱስ ነው ይላሉ። እኛ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች ደግሞ ለሥጋ ክብር (ቅብዕ) የሆነው ቃል ነው እንላለን። ለመሆኑ ሥጋ ክብርን አገኘ ማለት ራሱ ምን ማለት ነው የሚለውን አስቀድመን ማወቅ ይገባናል። ሥጋ ክቡረ ባሕርይ ሆነ ማለት አምላክ ሆነ ማለት ነው። ይኽውም ሥጋ ቃል መሆኑን ይገልጽልናል። ሥጋ ከበረ ማለት የቃልን ገንዘብ ሁሉ ገንዘቡ አደረገ ማለት ነው። የቃልን ገንዘብ ሁሉ ገንዘቡ አድርጎ የከበረው ደግሞ በተዋሕዶ ነው። ይህንንም ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ በሃይማኖተ አበው ገልጾታል። "ሥጋ ረከበ ዕበየ ወብዙኀ ፍድፍድና በተሳትፎቱ ወበተዋሕዶቱ ምስለ ቃል" ብሏል (ሃይ. አበ. ፴፩፣፲፰)። በግልጽ ሥጋ ክብርን ያገኘው ከቃል ጋር በመዋሐዱ ነው ይላል እንጂ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ (ክብር) ሆኖት ነው አይልም። ይህ የቅዱስ አትናቴዎስ ቃል ለቅባቶች መፈናፈኛ የማይሰጥ ክሕደታቸውን የሚያፈራርስ ዋና ቃል ነው። ቅባቶች ብዙ ጊዜ ቀባ፣ ተቀባ እና የመሳሰሉ ቃላትን ሲያገኙ ክሕደታቸውን የሚደግፍላቸው ይመስላቸዋል። ነገር ግን የእነርሱን ክሕደት የሚደግፍ አንድም ሊቅ የለም። ለምሳሌ ቅዱስ ዳዊት "ጽድቅን ወደድህ ዐመፃንም ጠላህ ስለዚህ፥ ከባልንጀራዎችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ" ይላል (መዝ. ፵፬፣፯)። ቅባቶች ይህንን ይይዙና አብ ቀቢ፣ ወልድ ተቀቢ፣ መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ ይላሉ። የዳዊትን ቃል በደንብ ተመልከቱት እንደዚህ አይልም። የደስታ ዘይት የተባለ መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን ክብር ነው። ጽድቅን ወደድክ ማለት ሰው መሆንን ወደድክ፣ ዐመፃን ጠላህ ማለት ሰው አለመሆንን ጠላህ። ስለዚህ ባልንጀራዎችህ ከተባሉ ከነቢያት የሚበልጥ የደስታ ዘይትን (ክብርን) ቀባህ (አከበረህ) ይላል። ምክንያቱም የነቢያት ክብር የጸጋ ክብር ነው። ሥጋ ግን ቃልን በተዋሐደ ጊዜ ያገኘው ክብር የባሕርይ ክብር ስለሆነ እለከማከ ከተባሉ ነቢያት የበለጠ ክብርን ማግኘቱን ይገልጻል። እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ ተብሏል። እግዚአብሔር የሚለው ስም ደግሞ ሦስቱም አካላት ማለትም አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም የሚጠሩበት ስም ነው። "አንሰ ሶበ እቤ እግዚአብሔር እብል በእንተ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" እኔ እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ ሦስቱን መናገሬ ነው እንዲል (ሃይ.አበ. ፺፮፣፮)። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ ቀባህ ቢል ለአብም ለራሱ ለወልድም ለመንፈስ ቅዱስም ይነገራል። ለአብ ቢነገር አብ ቀባዒ (አክባሪ) መሆኑን ይነግረናል። ለወልድ ቢነገር ሥጋን በተዋሕዶ ያከበረው ራሱ ወልድ መሆኑን ይነግረናል። ለመንፈስ ቅዱስ ቢነገር መንፈስ ቅዱስ ቀባዒ (አክባሪ) መሆኑን ይነግረናል። ሦስቱ አካላት በማክበር አንድ ስለሆኑ ቀባዒ፣ ቀባዒ፣ ቀባዒ ይባላሉ። "የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሃዎች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል" የሚለውም ምሥጢሩ አንድ ነው (ኢሳ. ፷፩፣፩)። በቀባዒነት ሦስቱም አካላት አንድ ናቸው። ምክንያቱም በክብር አንድ ናቸውና። "ዕሩያነ መዓርግ ወክብር" እንዲል በክብር በመዓርግ አንድ ናቸውና (ሃይ.አበ. ፻፲፫፣፪)። በሥላሴ ዘንድ ያለው አካላዊ ግብር መውለድ ማሥረጽ፣ መወለድ፣ መሥረጽ ነው እንጂ ቀባዒ፣ ተቀባዒ፣ ቅብዕ የሚል አካላዊ ግብር የለም (ሃይ.አበ.፹፬፣፭) ። በግብረ ባሕርይ ግን ሦስቱ አካላት አንድ ስለሆኑ ሦስቱም ቀባዕያን ይባላሉ። ለሥጋ ቅብዕ የሆነው ግን ከላይ ቅዱስ አትናቴዎስ እንደተናገረው ቃል ነው። ወልድ ዋሕድ በተዋሕዶ ከበረ ብለን የምንናገረው የቅዱስ አትናቴዎስን ቃል አብነት አድርገን ነው። ሦስቱ አካላት በግብረ ባሕርይ አንድ ስለሆኑ በግብረ ባሕርይ በመጻሕፍት የአንዱ ስም ቢጠቀስ እንኳ ሁለቱንም የሚመለከት ጉዳይ መሆኑን መረዳት ይገባል። ለምሳሌ ትንሣኤን በተመለከተ ራሱ ወልድ "ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት በሦስተኛው ቀን አስነሣዋለሁ" ብሎ ቤተ መቅደስ ስለተባለ ሰውነቱ ተናግሯል። ከሙታን መካከል የሚነሣም በራሱ ሥልጣን እንደሆነ ተናግሯል (ዮሐ. ፪፣፲፱)። ከሙታን ማስነሣት ግን ግብረ ባሕርይ ስለሆነ ለጊዜው ወልድ ብቻ ቢጠቀስም ይህ ጉዳይ አብንም መንፈስ ቅዱስንም የሚመለከት መሆኑን መረዳት ይገባል። በሌላ ቦታ እግዚአብሔር አስነሣው ተብሎ የሦስቱንም ስም በሚያመለክት ተገልጿልና (የሐዋ.ሥራ ፪፣፴፪)። በአካላዊ ግብር ወላዲነትና አሥራጺነት ለአብ ብቻ ይሰጣል። ተወላዲነት ለወልድ ብቻ ይሰጣል። ሠራፂነት ለመንፈስ ቅዱስ ብቻ ይሰጣል። ለግብረ ባሕርይ ሲነገር ግን ሦስቱም አካላት ወላድያን ሊባሉ ይችላሉ። ለምሳሌ እኛ በጥምቀት ከሦስቱም ስለተወለድን በዚህ አግባብ በግብረ ባሕርይ ካየነው አብም ወልድም መንፈስ ቅዱስም ወላዲ፣ ወላዲ፣ ወላዲ ሊባሉ ይችላሉ (መጽሐፈ መነኮሳት)። ስለዚህ ከምን አንጻር እንደተነገረ ማስተዋል ይገባል። በተጨማሪ ብዙ ጊዜ አምላካዊ ሥራዎችን ግብረ መንፈስ ቅዱስ እያለ ይገልጻቸዋል። በዚህ ጊዜ በተለየ መንፈስ ቅዱስ ይጠራ እንጂ አብንና ወልድንም የሚመለከት ጉዳይ መሆኑን መረዳት ይገባል። ቅባቶች የተሸወዱት ከዚህ ነው። ለምሳሌ "ዘአንገሦ ለሥጋ አዳም በመንፈስ ቅዱስ" የሚለው መንፈስ ቅዱስ ቅብዕ መሆኑን ይገልጻል ይላሉ። ዘአንገሦ የሚለው ቃል በማዋሐድ፣ በማንገሥ ሦስቱ አካላት አንድ ስለሆኑ በተለየ መንፈስ ቅዱስ ይጠራ እንጂ አብና ወልድንም ይመለከታል። ይህንን በደንብ ግልጽ የሚያደርግልን ከዚያው ቀጥሎ ቁጥር ፮ ላይ የነገሩን ባለቤት ሳይለውጥ "ዘለብሶ ለአዳም መዋቲ" ብሎ ቀጥታ ሥጋን ስለተዋሐደ ስለወልድ መናገሩ ነው። ይህን የመሰለ በመጽሐፍ ቅዱስም "እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኀይልም ቀባው" ተብሏል (የሐዋ. ሥራ ፲፣፴፰)። ይኽውም በግብረ መንፈስ ቅዱስ አዋሐደው ማለት ነው። ረቂቅ ሥራዎችን ለመንፈስ ቅዱስ አድሎ ቢናገርም አብንና ወልድንም ይመለከታልና። ይህንን የበለጠ ግልጽ የሚያደርግልን "ኢየሱስም መለሰ፥ እንዲህ ሲል፦ እውነት እውነት እልኻለኹ፥ ሰው ከውሃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደእግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም" የሚለው ቃል ነው (ዮሐ. ፫፣፭)። አሁን ከዚህ ላይ የምንወለደው ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው ለማለት አይደለም። ረቂቅ ልደትን እንደምንወለድ የሚገልጽ ቃል ነው። መንፈስ ቅዱስ በተለየ ቢጠራም የምንወለደው ግን ከሦስቱም ነው (ማቴ. ፳፰፣፲፱)። መምህረ ዓለም ቅዱስ ቄርሎስም "ሶበ ቃል ሥጋ ኮነ አሜሃ ንብል ተሰምየ ክርስቶስሀ ኢየሱስ። እስመ እንከ ተቀብዐ ቅብዐ ሐሴት እመንፈስ ቅዱስ በኀበ እግዚአብሔር አብ" ያለው ይህንኑ የሚገልጽ ነው።
نمایش همه...
نمایش همه...
ድንቅ ምስክርነት በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ || Bermel kidus Giorgi's

ድንቅ ምስክርነት በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ || Bermel kidus Giorgi's

https://youtu.be/dUR2isn21bQ

ጌታ ለምን ተአምር አደረገ መቅድመ ወንጌል አውሳብዬስና አሞንዮስ አራት ምክንያት አለው ይላሉ:- ፩. ሰይጣን ጌትነቱን ከሃሊነቱን ያውቅ ዘንድ። ፪.ተአምራቱን አይተው ባላመኑት ላይ መፈራረጃ ይሆን ዘንድ። ፫. ላመኑበት ኃይል ጽንዕ ይሆናቸው ዘንድ። ለመዋጋት ኃይል ይሆናቸው ዘንድ። ፬. ከክህደት ወደ ሃይማኖት ከኃጢአት ወደ ጽድቅ ለተመለሱ መሪ ትሆናቸዋለችና።  መ/ር ንዋይ ካሳሁን
نمایش همه...