fa
Feedback
Save Amhara✍️

Save Amhara✍️

رفتن به کانال در Telegram

“Do what you can, with what you have, where you are.” ―Theodore Roosevelt.

نمایش بیشتر
2 603
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-137 روز
+3030 روز
آرشیو پست ها
ሠላም በሌ ።ባህር ዳር ላይ የገጠመኝን ጉድ ላካፋልህ ስለፈለኩ ነው። ስሜ ለጊዜው ይቆይ አስፈላጊ ከሆነ እነግርሃለው ። እኔ የጤና ባለሙያ /ሃኪም ነበርኩ ባህር ዳር አንድ የግል ክሊኒክ ነው የምሠራው እና የመንግስት ሃይሎች በድንገት እያለፋ ነበር እና በሩ ክፋት ስለነበር እና እኔንም ገዋን ለብሼ ስላዩኝ ወደ ክሊኒኩ ገቡ ከዛ የሚታከሙ ፋኖዎች የታሉ ጥቆማ ደርሶናል አሉ።አይ የሉም አልኳቸው ፣ገብተው አዩ ፣ባጋጣሚ ወጣት ታካሚ አልነበረም፣ከዛ ፍኖን አክምሃል ተጠቁመናል አለኝ ።እኔ እኮ ሠው የሆነን በሙሉ ነው የማክመው ፣ይሄን ሁሉ አመት የተማርኩትም ፣ለሠው ልጂ ሁሉ ሳላዳላ ላክም ነው አልኩት፣፣ከዛ ውጭ ላለው ጓደኛው በኦሮሞኛ ካወራ በኋላ ፣ሁለቴ በጥፊ ከመታኝ በኋላ ፣ክላሹን እነካካ ፣አንተ የት ነበርክ አልሠማህም እንዴ ? አለኝ ፣በዚህ መሃል የማክማቸው ሠዎች ፣ግማሹ በልመና ግማሹ ፣እኛን ግደለን ሃኪሙን ተወው የሚሉ ትልልቅ እናትና አባቶች ሲጠጉን እኔን ወደውጭ ጎትቶ አውጥቶ የሆነ ጎዳ የሚመስል በረንዳ ያለው ቤት አሰገብቶ ፣።ስማ አለኝ እኛ የአማራን ወጣት ሳናጠፍ ፣ሴቶችን ደፍረን ፣በሽታ አስይዘን ነው የምንወጣው ፣ጌዜው የኛ ነው ፣የናተ ጊዜ አብቅቷል ጠግባቹሃል ኦሮሞ አይገዛንም ስላለቹህ ዋጋቹህን አየሰጠናቹህ ነው ፣ሰለዚህ እኛን ያልተባበረ አማራ ይረሸናል ፣አናም ብረሽንህ ማንም አይጠይቀኝም ፣ስለዚህ ተዘጋጅ አለኝ፣ እኔም ከመደናገጤና ከመረበሸ የተነሳ ፣የምሞት ከሆነ ቢያንስ አንዱን አውሬ ይዤ መሞት አለብኝ ብየ ወሠንኩና በእጄ ላይ  ከገዋኔ ኪስ ካለ ከእስክርቢቶ ወጭ ምንም አልነበረም ግን በሡም ቢሆን ለመውጋት ሞከሬ አይቀርም ነበር ፣ግን በጣም የሚሳዝነው እንደዘ አማራ የተባለ ሳናጠፋ አንሄድም ሲል ከጎኑ ሁለት የአማራ ሚኒሾች የሠሙ ነበር ። ከዛ የመጨረሻ ኑዛዜዬን ልናገር ብየ እባክህ ለናተም ቢሆን በነጻ አክማለሁ ፣ከአካውንቴ ያለውንም ያለኝ ብር አሰጥሃለው  ልጅ አለኝ አትግደለኝ ስለው ፣አሽ 40 ሺ ብር አምጣ አለኝ አይ አሁን አልያዝኩም በአካውንት እልካለሁ አልኩ ፣አሽ 10 ሰአት ላይ ከመኮድ ጀርባ የሆነ ዛፍ አለ ከዛ እጠብቀሃለሁ 40 ሺ ብር ታመጣለህ ካለሆነ መጥቼ አንተንም ክሊኒኩንም ነው የማቃጥለው አለኝ።እኔም በደስታ እሽ ብየ ።እኔም ነፍሴ ተረፎ ሁሉንም ነገር ትቸ ህይወቴን ይዤ ወደ አአ ተሰደድኩ! (የሐኪሞች ሰቆቃ )

ሰብስክራይብ ያድርጉ❗️❗️❗️ የአማራ ፋኖ በጎንደር፤ ከአማራ ፋኖ በጎጃም ኦርኬስትራ ቡድን ጋር ጎንደር ቋራ ላይ❗️ https://youtu.be/NZmEpDVpiJ8?si=wsxueTnbGOgHObmQ

ምስክር ከፈረሱ አፋ❗️ ደብረ ማርቆስ ከተማ ሰፍሮ የሚገኘው ማን ነው? አገዛዙ በከተማ ቦታ የገዛቸው ተላላኪ ሚሊሻዎች፣ ሆዳም አድማ ብተና እና ፖሊስ እንዲሁም ዙፋን ጠባቂው ሰራዊት ነው። ከንቲባው በሰጠው ማስረጃ መሰረት ደብረ ማርቆስ ከተማ የሚፈጸሙ ስርቆት እና ዝርፊያዎች በእነዚህ ቡድኖች ይፈጸማል። ደብረ ማርቆስ ከተማ ፋኖን ተደገፋለህ እየተባለ በጅምላ እየታሰረ እስከ 300 ሺህ ብር ድረስ ከፍሎ የተለቀቀ ነጋዴ አለ። ምሽት 1፡00 ስዓት ላይ ከ5 ኪሎ ወደ ትንሿ ድብዛ ት/ቤት በሚወስደው መንገድ ከ50 በላይ ሰዎች በአድማ ብተና እና ሚሊሻ ተንበርከኩ ተብለው ብራቸውን እና ስልካቸውን ተዘርፈዋል። ዞን ፍርድ ቤት፣ መምህራን ኮሌጅ፣ ሃያ ሜትር እና ሸዋ በር መስመር በመከላከያ እና አድማ ብተና ብዙ ሰዎች ስርቆትና ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል።

የአማራ ፋኖ በጎጃም፤ ሐዲስ አለማየሁ ክፍለ ጦር❗️ ሰብስክራይብ ያድርጉ❗️ https://youtu.be/f1NSoHl_qDA?si=_yT22UoDmigdnmof

https://t.me/blum/app?startapp=tribe_blumvnd-ref_BB2s7RWDzW Hey there! 🌟 Join BlumVND, challenge other tribes, and earn epic rewards! 🎉🔥 ጠቀም ያለ ብር ያስገኛል❗️ሳይዘናጉ ይጫወቱት❗️ plss.

ሰበር ዜና! አቶ ሲሳይ ዳምጤ ጥቃት ደርሶበት ሆስፒታል ገባ! የቀድሞ የአማራ ክልል የሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ የነበረው ና አሁን የክልሉ የገጠር መሬት አጠቃቀም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ በዛሬው ዕለት ደቡብ ጎንደር ቀጠና በፋኖ በተሰነዘረበት ጥቃት ቆስሎ ደብረታቦር ሆስፒታል መግባቱን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጀነራል ነጋ ተገኝ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ፋኖ ፀዳሉ ደሴ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል። ፋኖ ፀዳሉ ደሴ አክሎም በትላንትናው ዕለትም ከሰባት ላይ በላይ የብልፅግና አመራሮች በልዩ ኦፕሬሽን ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ ገልጿል። ዝርዝር መረጃዎችን "251 ዛሬ" ላይ ይጠብቁን። ኢትዮ 251 ሚዲያ

https://t.me/blum/app?startapp=ref_BB2s7RWDzW Join me on Blum and let's earn together! Use my invite link to join the fun. 🌟 ይጫወተቱ❗️ 10k blum= 500 ዳላር ይሻጣል!

የአማራ ፋኖ፤ የሚታገለው ለሥልጣን ነው ሲባል ምን ማለት ነው❓ የአማራ ፋኖ በጎጃም፤ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሤ ክፍለ ጦር ሰብሳቢ እስቲበል ዓለሙ፤ በቂ ማብራሪያ አለው። ያዳምጡት❗️ https://youtu.be/VBg29fsVXp8?si=HkfzNGk3h1gzaCOB

እነሆ የድል ዜና ከደንበጫ ‼ የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ  ሻለቃ 1 ጠላትን ዛሬ 17/12/2016ዓ.ም ወደ ደጋዳሞት የተንቀሳቀሰን ጠላት አርበድብዶ ቀጥቶታል።እጅግ ከፍተኛ ሙትና ቁስለኛ ጠላት አንስቷል።ቀኝጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር!!!! ፋኖ እስቲበል አለሙ

መረጃ❗️ የአማራ ፋኖ በጎጃም ጥሎት የነበረ የትራስፖርት እና የታክሲ እቅባ መነሳቱ ይታወቃል። ይህም ተከትሎ ዛሬ ሥራ ለመጀመር የተንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች በተላላኪ ሚሊሻ ሲደበደቡና የመኪናቸው መስዕታዋት ሲሰበር ታይቷል። በደብረ ማርቆስ ከተማ ዛሬ ሥራ ለመጀመር የተንቀሳቀሱ የባጃጅ አሽከርካሪዎች "ማን ፈቅዶልህ ሥራ አቁምህ ነው ዛሬ ሥራ የጀመርህ?" በሚል በተላላኪና ከሃዲ ሚሊሻ በሰደፍ ሲደበደቡና የባጃጃችው መስዕታወት በሰድፍ ሰብሯል። በተያያዘ፤ ታርጋቸው የተፈታባቸው ባለባጃጆች 2500 ብር ቅጣት ከፍላችሁ ውስዱ ተብለዋል። የተሸጉ ሱቆችና ግሮሰሬዎችም እስከ 10 ሺህ ብር ድረስ መጠየቃቸው ታውቋል። በተጨማሪ፤ የመናኽሪያ ተሽከርካሪዎች ስምሪት አንሰጣችሁም ተብለው፣ ሥራ አልጀመሩም! ይዛመት!

የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደቡ ተነስቷል፤ ተጋድሎው ይቀጥላል።       ነሐሴ 16 ቀን 2016 ዓ.ም ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተሰጠ መግለጫ ------------------------------------------------- ድርጅታችን ከነሐሴ 07 ቀን 2016ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ግዜ ከአምቡላንስ በስተቀር መንገዶች ለተሽከርካሪወች  ዝግ እንዲደረጉ ያወጣው መመሪያ ያለ ምንም መሸራረፍ ሲተገበር ቆይቷል። የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደቡ የተጣለባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች የፋኖ ኃይል በወራሪው ሰራዊት ላይ በከፈተው ዘመቻ በሚደረግ የተኩስ ልውውጥ በንፀሃን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ማስወገድን፤ የጠላትን የመረጃ ሰወች እና የሎጅስቲክስ እንቅስቃሴ ማክሸፍን፤ ጠላት በገፍ ያስገባውን መሳሪያ በመማረክ የወገንን ወታደራዊ አቅም ማሳደግን፤ የህልውና ተጋድሎውን በማጋጋል የአማራን ህዝብ ከጭፍጨፋ መታደግን ታሳቢ ያደረገ ነበር። ላለፋት 10 ቀናት በተተገበረው በዚህ ዘመቻ ትልቅ ፓለቲካዊ፣ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ድሎችን አግኝተንበታል። የፋኖ ኃይል በኢትዮጵያ የፖለቲካ አየር ውስጥ ትልቅ ትኩረት የሚሰጠው የፖለቲካ ተዋናይ መሆኑን በተለይም የተደራጀ አመራር እና ስምሪት የሚሰጥበት በሁሉም ማዕዘናት ህዝብ የሚደግፈው እና የሚቀበለው ኃይል መሆኑን እንዲሁም ማዕከላዊነትን የጠበቀ የትግል ምዕራፍ ላይ መሆኑን በሚገባ ተረጋግጧል። በተለይም የአማራ ህዝብ ለህልውናው ሲሉ መሪር መስዋዕትነት የሚከፍሉለት ሀቀኛ ልጆቹ የመረጡትን ውጤታማ የትግል መንገድ በተግባር ሲደግፍ እንደ ህዝብ የሚከፍለውን መስዋዕትነት ለመቀበል የተዘጋጀ መሆኑን በይፋ ያረጋገጠበት ክስተት ሆኖ አልፏል። የአማራ ብልፅግና የሚባለው የጨፍጫፊወች ተላላኪ እና መንገድ መሪ ቡድን በአማራ ህዝብ ላይ የተጣበቀ መዥገር እንጅ በአማራ ህዝብ የፖለቲካ ሚዛን ላይ የጉድፍ ያህክል እንኳን ቦታ የሌለው አየር ላይ የተንሳፈፈ ስብስብ መሆኑን የተረዳንበት፤ ህዝብ የጣለብንን ታሪካዊ አደራ እና ኃላፊነት ለመሸከም የበለጠ መደራጀት፤ የበለጠ መታገል እንደሚገባን የተገነዘብንበት ወቅትም ጭምር ነው። በ10 ቀናቱ የተሳካ ኦፕሬሽን በሁሉም ክፍለ ጦሮቻችን ስር ባሉ ግዛቶች በተደረጉ አውደ ውጊያወች በደፈጣ፣ በመደበኛ ውጊያ እና ከተማ ላይ በሚደረጉ የሰርጎ ገብ የቅጣት እርምጃወች ከ50 በላይ የቡድን መሳሪያወችን፣ ከ732 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያወችን እና በ10 ሺወች የሚቆጠሩ ተተኳሾችን ማርከናል።በጠላት ተሽከርካሪወች ላይም ከባድ ጉዳት አድርሰናል፤ የጠላት ሰራዊ ላይ በወሰድነው ተከታታይ እርምጃ ከ2340 በላይ የጠላት ኃይል ደምስሰናል። ወራሪው ሰራዊት ያቀደውን ስር ነቀል የሚመስል ዘመቻ መሉ በሙሉ ከማክሸፋችንም በላይ የጠላትን የኃይል ስምሪት በማዛባት ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ምስቅልቅል ውስጥ አስገብተነዋል። በሌላ በኩል ጠላት ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው በየአውደ ውጊያው የደረሰበትን ሽንፈት ለመበቀል እና ህዝብን ለማሸበር ታሳቢ አድርጎ ባህርዳርን ጨምሮ በብዙ ቦታወች ላይ የሃይማኖት አባቶችን፣ ጎዳና ተዳዳሪወችን እና የዩኒቨርሲቲ ተማሪወችን ጨምሮ ከ35 በላይ ንፁሃንን ጨፍጭፏል። ብልፅግና የሚባለው ቡድን ኃላፊነት የማይሰማቸው እብዶች ጥርቅም መሆኑን ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ የኢትዮጵያን ፖለቲካ የሚከታተሉ ዓለም አቀፍ ተዋንያንም ታዝበውታል። የፋኖ ኃይል እነኝህን እና መሰል እርምጃወችን ሲወስድ ሁልግዜም ህዝብ አብሮት አለ። ላለፉት አስር ቀናት የእንቅስቃሴ ገደቡን በመተግበር እና አብሮንም ዋጋ በመክፈል የተሳተፈውን ህዝብ ጥያቄ ሳንመልስ ለአፍታም ቢሆን የማናርፍ መሆኑን ለመላው የአማራ ህዝብ በድጋሚ እናረጋግጣለን። የከተማ ኦፕሬሽኖቻችን የተሳኩ ይሆኑ ዘንድ በውስጥ አርበኝነት የአንበሳውን ድርሻ ለተወጡት ጥቂት የብልፅግና የታችኛው የፀጥታ መዋቅር አመራር እና አባላት ላደረጉት ተጋድሎ ልዩ ክብር ያለን መሆኑን እናሳውቃለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ ላለፉት በርካታ ቀናት ራሱን ከማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴወች አቅቦ ትግላችንን ሲደግፍ እና መመሪያችንን ሲተገብር የቆየው ህዝብ ባቀረበልን ጥያቄ መሠረት እንዲሁም የመንገድ ክልከላው ዓላማም ግቡን የመታ በመሆኑ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ግዜ ሁሉ ተለዋጭ ትዕዛዝ እንደምንሰጥ ታውቆ  ከነገ ነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ገደቡ መነሳቱን እናስታውቃለን። ይሁን እንጅ የተጀመረው ዘመቻ ለአፍታም ቢሆን የማይቆም በመሆኑ መላው ሰራዊታችን በወትሮ ዝግጁነት እንዲጠብቅ እናሳስባለን። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ!

የድል ዜና❗️ የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር ሥር የየሚገኙት ንጉሥ ተክለሃይማኖት ብርጌድ እና ስናን አባጅሜ ብርጌድ፤;ዛሬ 16/12/2016 ዓ.ም ወደ ረቡዕ ገበያ ሬሸን ለመቀ
የድል ዜና❗️ የአማራ ፋኖ በጎጃም ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር ሥር የየሚገኙት ንጉሥ ተክለሃይማኖት ብርጌድ እና ስናን አባጅሜ ብርጌድ፤;ዛሬ 16/12/2016 ዓ.ም ወደ ረቡዕ ገበያ ሬሸን ለመቀባበል እና ለጥቃት የተንቀሳቀስን የጠላት ኃይል ሶስት ቦታ ላይ ደፈጣ በመጣል በልኩ አቅምሰውታል። ከሞት የተረፈው ጠላት አስከሬኑን ተሸክሞ፣ ድል ያደረገ ለመምሰል እና ሕዝባችን ላይ የሥነ ልቦና ጭና አደርጋለሁ በሚል ቂልነት ደብረ ማርቆስ ከተማ ሲገባ እየጨፈር ገብቷል።

የፈረንሳዩ APA በዘገባው ስለጎጃም ፋኖ ይሔን ብሏል! የአከባቢው ተዋጊዎች በኢትዮጵያ አማራ ክልል የትራንስፖርት እገዳ ጣሉ! በክልሉ ጎጃም አካባቢዎች ከሳምንት በፊት የጀመረው እገዳው ወደ ሌሎች የ
የፈረንሳዩ APA በዘገባው ስለጎጃም ፋኖ ይሔን ብሏል! የአከባቢው ተዋጊዎች በኢትዮጵያ አማራ ክልል የትራንስፖርት እገዳ ጣሉ! በክልሉ ጎጃም አካባቢዎች ከሳምንት በፊት የጀመረው እገዳው ወደ ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች በመዛመት በዋና ዋና ከተሞች እና ከተሞች መካከል የመንገድ ትራንስፖርት እንዲቆም መደረጉን ኤ.ፒ.ኤ. ርምጃው የፋኖ ሃይሎችን በቆራጥነት ለመምታት ከ30,000 በላይ አዳዲስ ሃይሎችን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በማሰማራት የመንግስትን ከፍተኛ ቅስቀሳ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የመጣ ነው። በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጊያ ተካሂዷል። በጎጃም የፋኖ ሃይሎች አብዛኞቹን አካባቢዎች ከመንግስት ሃይሎች ጠርገው የክልሉን ርዕሰ መዲና ባህርዳርን ለመቆጣጠር ሲጥሩ እንደነበር ተናግሯል። በከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴዎች ተዘግተው የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል። የስራ ማቆም አድማው በይፋ ያልተጠራ ሲሆን ርምጃው ለፋኖ ሃይሎች ግልፅ ድጋፍ ተደርጎ ይወሰዳል። የፌደራል መንግስት ባለፉት ወራት በክልሉ በሚገኙ ሚሊሻ ተዋጊዎች አንዳንድ ወረዳዎችን እና ከተሞችን እየተቆጣጠረ ነው። ሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ማለትም ጎንደር፣ ወሎ እና ሸዋ በመንግስት ታጣቂዎች እና ፋኖ መካከል እንደገና ኃይለኛ ውጊያ ታይቷል። የፋኖ ሃይሎችም በእነዚህ አካባቢዎች የጉዞ ገደቦችን ጥለዋል። የመከላከያ ሰራዊቱ በፋኖ ሃይሎች ላይ ድል እያስመዘገበ ይገኛል። በመስከረም ወር መጨረሻ የፋኖ ሃይሎችን ለማፅዳት አቅዶ ነበር። APA የፋኖ ሃይሎች ተጨማሪ አካባቢዎችን እየተቆጣጠሩ እና ተጨማሪ ወታደራዊ እመርታ እያስገኙ እንደሆነ ተረድቷል። © https://apanews.net/local-fighters-impose-transport-restrictions-in-ethiopias-amhara-region/

እሬት ነገር እኮ ዲማን ሊረገጥ ⁉️ ልዩ ዘመቻው እንደቀጠለ ነው። የጎጃም አፈር ማለስለሻ የሆነው የብርሃኑ ጁላ ጦር ዛሬም እንደወትሮው በአባ ኮስትር ልጆች ሲቀጠቀጥ ውሏል። ከቢቸና ከተማ እና ከደ/ወርቅ ከተማ ተነስቶ ወደ ዲማ ጊዮርጊስ መግባት አስቦ የተንቀሳቀሰው ሁለት ሬጅመንት ኃይል የጀግኖችን በትር መቋቋም አቅቶት ሊረገጣት የፈለጋትን ዲማ ጊዮርጊስን በከባድ መሳሪያ መነፅሮቻቸው ከርቀት አይተው አስከሬን እና ቁስለኛቸውን ሰብስበው ወደ ኋላ በመፈርጠጥ ጠልማ አካባቢ ምሽግ ቆፍሮ አድሯል። አንድ ዙ-23 እና ሞርተር ጨምሮ የመጣው የጠላት ሃይል ከጠዋቱ 1:30 ጀምሮ እስከ ቀኑ 8ሰዓት ድረስ በአባ ኮስትር ብርጌድ ልጆች ባደረጉት ከባድ ውጊያ ከ60 የብርሃኑ ጁላ ጦር ሲደመሰሱ እና 38 ቁስለኛ ሆነዋል። ዲማን ለመቆጣጠር ፈልጎ ያልተሳካለት ይሄው ኃይል ሙትና ቁስለኞችን ወደ ቢቸና እና ደብረወርቅ ከተማ ሸኝቶ በዲማ እና ጠልማ መካከል ላይ የሚገኘው ከፍታ ቦታ ላይ ምሽቱን ከባድ ምሽግ በመቆፈር ላይ ይገኛል። ልዩ ዘመቻውን ውጤታማ እንዲሆን የአማራ ፋኖ በጎጃም በላይ ዘለቀ ክ/ጦር አካል የሆኑት ደባይ ጮቄ ብርጌድ ናብራ ሻለቃ እና ሶማ ብርጌድ የተሳተፉ ሲሆን የአምበሳውን ድርሻ የተወጣው የአባ ኮስትር ብርጌድ 4ኛ ሻለቃ ፣5ኛ ሻለቃ እና ኢ/ር ተሾመ ሻለቃ ናቸው። በሌላ በኩል ሁለተኛ 2ኛ ሻለቃ ከለምጨን ፣ባንጃ እና ሸረር በመነሳት ቢቸና ከተማ የገባው የወገን ጦር ጠላትን ሲያስጨንቀው ውሏል። የአማራ ፋኖ በጎጃም ልዩ ዘመቻ ይቀጥላል ! ©ጥላሁን አበጀ

ለደብረ ማርቆስ ከተማ ንዋሪዎች በሙሉ:- የደብረማርቆስ ሕዝብ ከ13/12/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ዛሬ 15/12/2016 ዓ.ም ድረስ ከአማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈውን የእቀባ ትዕዛዝ ተከትሎ ትዕዛዙን ተቀብላችሁ፤ ጥርቅም አድርጋቹ በመዝጋት ከሕዝባዊ ትግሉ ጎን መሆናችሁን በሚገባ አሳይታችኋል። ለዚኽ የሚደንቅ ትብብርም ለደብረማርቆስ ሕዝብ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ነገር ግን በነገዉ እለት የሚከበረዉን በዓል ምክኒያት በማድረግ ለከተማዉ ዉስጥ እንቅስቃሴና ሥራ የተፈቀደ መሆኑን እናሳዉቃለን። በዚህ መሰረት የከተማዉ ታክሲዎች እና ባጃጆች ለእንቅስቃሴ ነፃ ናቸዉ። ሱቆች እና ሌሎች የአገልግሎት መስጫ ተቋማትም ክፍት ይሆናሉ። የባጃጅ ታርጋ የፈታችሁ እና ሆቴል እና ሱቅ ያሸጋችሁ የአማራን ህዝብ ጉዳት የማሰማችሁ አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ታርገውን የማትመልሱ እና ያሸጋችሁትን የማትለቁ ከሆነ በስም ለይተን ያወቅን በመሆኑ እርምጃ የምንወስድ መሆኑን እናሳውቃለን። በድርጅታችን ብ0አማራ ፋኖ በጎጃም የተላለፈዉ የእንቅስቃሴ ገደብ መመሪያ ግን እንደተጠበቀ ይሆናል። ማሳሰቢያ :- ከከተማ ውጪ የሚደረግ ምንም አይነት የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አልተፈቀደም። አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳስብ! አዲስ ተስፋ!!!! ©እስቲበል አለሙ፤ የአማራ ፋኖ በጎጃም፣ የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር ሰብሳቢ፤

መረጃ❗️ በደብረ ማርቆስ ከተማ 2ኛ ቀኑን ባስቆጠረው የሥራ ማቆም እቅባና ትዕዛዝ፤ ሰው በላው አገዛዝ ያሰማራው ተላለኪ ሚሊሻና አድማ ብተና የባጃጅ ታክሲዎችን ታርጋ እየፈተ እየወሰደ ሲሆን፤ በተጨማሪም ሥራ የማትጀምሩ ከሆነ ባጃጅችሁን እናጋየዋለ እያለ እያስፈራ ይገኛል። በተያየዘ መረጃ፥ ዛሬም ሥራ ለማጀመር እያኮበኮባችሁ የምትገኙ ግለስቦች እንዳላችሁ ታዘብናል። መዝግበን ይዘናል። እረፉ ብለናል፤ ብታርፉ ጥቅሙ ለራሳችሁ ነው❗️

ደማቅ ሰበር ዜና - ሞጣ ከተማ በሞጣ ከተማ የአገዛዙ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ማለትም የአካባቢው ዋናና ምክትል ወታደራዊ አዛዦች፣ የከተማው ዋና ኢንስፔክተርን ጨምሮ በአጠቃላይ 6 ከፍተኛ የአገዛዙ ወታደራዊና የፀጥታ አመራሮች በተጠና ኦፕሬሽን በድንች ናዳ (💣💣) ፍርፍር ሆነው መሰናበታቸውን ባህርዳር ዊክሊክስ ያገኘችው መረጃ ያስረዳል። ስማቸውን የተመለከተ መረጃ እየጠበቅን ቢሆንም፣ ከተሰናበቱት ውስጥ ግን የጄኔራል ማዕረግ ያለው ወታደራዊ አመራር እንዳለበት ለማወቅ ተችሏል። እነዚህ አራዊቶች የተሰናበቱት ውበት ሆቴል ውስጥ በፓትሮሎች ታጅበው እየተጠበቁ ባለበት ሁኔታ መሆኑን ይህንን ኦፕሬሽን የፈፀሙት ጀግና ልጃችንና ሽፋን ሰጭዎች በታሪክ ማህደር ስማቸው ደምቆ እንዲጻፍ ያደርገዋል። (ለሌሎች የአማራ አክቲቪስቶች የእኛ ልጆች ስም ለጊዜው እንዳይወጣ)

የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክፍለ ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ💪 https://youtu.be/qlmYLulGGPc?si=MNjZpk0_OlwnpGXI

📌ጥብቅ መረጃዎችና የጥንቃቄ መልዕክቶች የወገን ጦር ፋኖ ወርቃማውን የክረምት ወራት ስኬታማ በሆነ ማጥቃት ላይ ሆኖ እያሳለፈው ነው። ሆኖም ግን በአንዳንድ አውደ ውጊያ ቦታዎች ከጥንቃቄ ጉድለት ጋር ተያይዞ ውስንነቶች እንደታዩ የውስጥ አርበኞች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ያደረሱት መረጃ ያመለክታል። በመሆኑም ለሚዲያ የሚመጥነውን መረጃ መጥነን የሚከበሉን የጥንቃቄ መልዕክቶች ለወገን ጦር እናደርሳለን፦ መረጃ ፩ በውጊያ ወቅት ጠላት ጨርሶ ባልሸሸበት ሁኔታ አብሪ ኃይሎች ምልክት ባላሳዩበት ሁኔታ በፍጥነት ወደ ጠላት ቀጠና መጠጋት ወጥመዱ ውስጥ እንደመግባት ነው። የወገን ጦር ፋኖ ነጻ ቀጠናውን መቆጣጠሩን ሳያረጋግጥ ወደፊት ባይገሰግስ የሚል ምክር ከውስጥ አርበኞች የደረሰን መረጃ ያሳያል። መረጃ ፪ በምዕራባዊ ወሎና በሸዋ አዋሳኝ ቀጠናዎች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክትትል ያለ በመሆኑ ጠላት በሽፋን ማንነት (cover identity) በመስጠት የስለላ ስምሪት ሰጥቷል። ከገነቴ አቅጣጫ ወደሸዋ ቀጠናዎች ያሉ እንቅስቃሴዎች ክትትል ያስፈልጋቸዋል። ይህን ፋኖ ባለው ቀጠናዊ ትስስር መረጃዎችን በጥንቃቄ በመቀያየር የጠላትን ወታደራዊ የመረጃ ሥራ ማምከን ይጠበቃል። በተለይም በሸዋ ቀጠና በአለም ከተማ፣ ሬማ፣ መራኛ፣ ኮረማሽ፣ መሃል ሜዳ እና በረኸት ከተሞች የወገን ጦር ፋኖ የራሱን የደህንነት ኃይል በማሰማራት ከፍተኛ ንቃት ያለው የፀረ-ስለላ ስራ ሊኖር ይገባል። የፋኖ አደህንነቶች ከፋኖ ማዘዣ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባል። በተለይም መረጃ ከመቀያየር አኳያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባህላዊ መንገዶችን መጠቀም ይመከራል። በስልክ ላይ አሁንም እምነት የማሳደር ችግሮች ያሉ በመሆኑ ይህ መታረም አለበት። ታንክና ባንክ በእጁ የያዘ ኃይል፤ የቴክሎጂ ብልጫ የወሰደ ቴሌም፣ ኢንሳም በእጁ የሆነው ጠላት "ምንም አያመጣም" አይባልም። ጥንቃቄ ያስፈልጋል። መረጃ ፫ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ስር ያለው ኮሎኔል ጃዋር ዴኮ የሚመራውን የብልጽግና ሰራዊት ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም ወደክምር ድንጋይ ጋይንት ቀጠና አንድ የኦሕዴድ ጀነራል እንደሚጓዝ መረጃው ለኢትዮ 251 ደርሷል። የጉዞው ዓላማ አጠቃላይ ሁኔታውን ለመገምገም እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ስለሆነም ደብረታቦር፣ እስቴ፣ ስማዳና ጋይንት መስመር በዋናነት ጉና ቀጠና ያለው የወገን ጦር ይህን መረጃ ይዞ ክምር ድንጋይ ላይ ያለውን ጠላት ታርጌት ቢያደርግ ይመከራል። መረጃ ፬ የ ኦህዴድ/ብልጽግና ቁልፍ አመራሮች የራሳቸውን ስብሰባ ተቀምጠዋል። በዚህ ስብሰባ ከኦሕዴድ ድርጅታዊ ጥቅም ማስከበር ጋር በተያያዘ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እንደሚወሰኑ ነው የተሰማው። በቅርቡ የሚወገዱ ብዐዴኖች ይኖራሉ። ዋና መመቻው ካርድ ደግሞ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ትገናኛላችሁ በሚል ነው። የኦህዴድ ስብሰባ ሲያልቅ ወሳኝ የሚባሉ ውሳኔውዎች በአማራ እና ትግራይ ክልል ዙሪያ ይወስናሉ። ከኢኮኖሚ አኳያ፦ ➽ የኦሮሞ ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቢሊየን የሚቆጠር ብድር የወሰዱ "የተበላሸ ብድር" በሚል መሰረዝ ስለሚቻልበት ሁኔታ፣ ➽ ተጨማሪ ብድሮች ከፖሊሲ ባንኩ ስለመፍቀድ፣ ➽ አዳዲስ የማዕድን ፍቃዶችን ለኦሮሞ ባለሃብቶች ስለመስጠት፣ ➽ ብሔራዊ ባንክ በልዩ ሁኔታ በሚያወጣቸው የዶላር ሽያጭ ጨረታዎች ላይ ገዳ፣ ስንቄ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል፣ ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ፣ አዋሽ፣ … ያሉ መሠረታቸው የኦሕዴድ የሆኑ ባንኮች ቀጣይነት ባለው መልኩ ጨረታውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ፣ እና ➽ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችን ለመወሰን በግርማ ብሩ በኩል የውሳኔ ሃሳቦች እንደሚቀርቡ የኢትዮ 251 የመረጃ ምንጮች ያከረሱን መረጃ ያሳያል። በሌላ በኩል "ኢትዮጲያ ታምርት" በሚለው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንቅናቄ ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት ላይ በኦሮሞ ባለሃብቶች በሰፊው መጠቀም የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚገመገም መረጃዎች ያመለክታሉ። የወደብ ጉዳዩም ተመሳሳይ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል። ኦሕዴድ ዋና ፍላጎቱ ሶማሊላንድን ይዞ ቀጠናውን ማተራመስ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ስብሰባ በኋላ የብአዴን አመራሮች መካከል በተለይ በዞን ደረጃ ያሉትን ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል የመምታት ውሳኔ መወሰኑ ይጠበቃል። በአማራ ክልል ያለው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚወሰነው በኦሕዴድ ነው። ብአዴን እንደሕዳር አህያ የሚጭኑትን ከመቀበል ውጭ ምንም ድምፅ የለውም። በቅርቡ ዐቢይ አሕመድ ባለበት በተካሄደ አንድ ስብሰባ ላይ ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ብአዴንን በተመለከተ የተናገረው ንግግር አስቂኝ ነበር፦ "የክልሉ አመራር (ብአዴንን ማለቱ ነው) ያረጀ ጀኔረተር ማለት ነው። ያረጀ ጀኔረተር ነዳጅ ካልሰጡት ወይም ካልደበደቡት አይሰራም" ሲል ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ተሳልቆባቸዋል። እነሱ ያረጀ ጀኔረተራቸውን ይደብድቡ፤ የወገን ጦር ፋኖ ደግሞ የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላን ሰራዊት ወደአፈር መቀላቀሉን ይቀጥላል!! ኢትዮ 251 ሚዲያ

📌ጥብቅ መረጃዎችና የጥንቃቄ መልዕክቶች የወገን ጦር ፋኖ ወርቃማውን የክረምት ወራት ስኬታማ በሆነ ማጥቃት ላይ ሆኖ እያሳለፈው ነው። ሆኖም ግን በአንዳንድ አውደ ውጊያ ቦታዎች ከጥንቃቄ ጉድለት ጋር ተያይዞ ውስንነቶች እንደታዩ የውስጥ አርበኞች ለኢትዮ 251 ሚዲያ ያደረሱት መረጃ ያመለክታል። በመሆኑም ለሚዲያ የሚመጥነውን መረጃ መጥነን የሚከበሉን የጥንቃቄ መልዕክቶች ለወገን ጦር እናደርሳለን፦ መረጃ ፩ በውጊያ ወቅት ጠላት ጨርሶ ባልሸሸበት ሁኔታ አብሪ ኃይሎች ምልክት ባላሳዩበት ሁኔታ በፍጥነት ወደ ጠላት ቀጠና መጠጋት ወጥመዱ ውስጥ እንደመግባት ነው። የወገን ጦር ፋኖ ነጻ ቀጠናውን መቆጣጠሩን ሳያረጋግጥ ወደፊት ባይገሰግስ የሚል ምክር ከውስጥ አርበኞች የደረሰን መረጃ ያሳያል። መረጃ ፪ በምዕራባዊ ወሎና በሸዋ አዋሳኝ ቀጠናዎች ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክትትል ያለ በመሆኑ ጠላት በሽፋን ማንነት (cover identity) በመስጠት የስለላ ስምሪት ሰጥቷል። ከገነቴ አቅጣጫ ወደሸዋ ቀጠናዎች ያሉ እንቅስቃሴዎች ክትትል ያስፈልጋቸዋል። ይህን ፋኖ ባለው ቀጠናዊ ትስስር መረጃዎችን በጥንቃቄ በመቀያየር የጠላትን ወታደራዊ የመረጃ ሥራ ማምከን ይጠበቃል። በተለይም በሸዋ ቀጠና በአለም ከተማ፣ ሬማ፣ መራኛ፣ ኮረማሽ፣ መሃል ሜዳ እና በረኸት ከተሞች የወገን ጦር ፋኖ የራሱን የደህንነት ኃይል በማሰማራት ከፍተኛ ንቃት ያለው የፀረ-ስለላ ስራ ሊኖር ይገባል። የፋኖ አደህንነቶች ከፋኖ ማዘዣ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በጥንቃቄ ሊያዝ ይገባል። በተለይም መረጃ ከመቀያየር አኳያ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ባህላዊ መንገዶችን መጠቀም ይመከራል። በስልክ ላይ አሁንም እምነት የማሳደር ችግሮች ያሉ በመሆኑ ይህ መታረም አለበት። ታንክና ባንክ በእጁ የያዘ ኃይል፤ የቴክሎጂ ብልጫ የወሰደ ቴሌም፣ ኢንሳም በእጁ የሆነው ጠላት "ምንም አያመጣም" አይባልም። ጥንቃቄ ያስፈልጋል። መረጃ ፫ በሰሜን ምዕራብ ዕዝ ስር ያለው ኮሎኔል ጃዋር ዴኮ የሚመራውን የብልጽግና ሰራዊት ያለበትን ሁኔታ ለመገምገም ወደክምር ድንጋይ ጋይንት ቀጠና አንድ የኦሕዴድ ጀነራል እንደሚጓዝ መረጃው ለኢትዮ 251 ደርሷል። የጉዞው ዓላማ አጠቃላይ ሁኔታውን ለመገምገም እንደሆነ የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ስለሆነም ደብረታቦር፣ እስቴ፣ ስማዳና ጋይንት መስመር በዋናነት ጉና ቀጠና ያለው የወገን ጦር ይህን መረጃ ይዞ ክምር ድንጋይ ላይ ያለውን ጠላት ታርጌት ቢያደርግ ይመከራል። መረጃ ፬ የ ኦህዴድ/ብልጽግና ቁልፍ አመራሮች የራሳቸውን ስብሰባ ተቀምጠዋል። በዚህ ስብሰባ ከኦሕዴድ ድርጅታዊ ጥቅም ማስከበር ጋር በተያያዘ ወታደራዊና ፖለቲካዊ ውሳኔዎች እንደሚወሰኑ ነው የተሰማው። በቅርቡ የሚወገዱ ብዐዴኖች ይኖራሉ። ዋና መመቻው ካርድ ደግሞ ከገዱ አንዳርጋቸው ጋር ትገናኛላችሁ በሚል ነው። የኦህዴድ ስብሰባ ሲያልቅ ወሳኝ የሚባሉ ውሳኔውዎች በአማራ እና ትግራይ ክልል ዙሪያ ይወስናሉ። ከኢኮኖሚ አኳያ፦ ➽ የኦሮሞ ባለሃብቶች ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በቢሊየን የሚቆጠር ብድር የወሰዱ "የተበላሸ ብድር" በሚል መሰረዝ ስለሚቻልበት ሁኔታ፣ ➽ ተጨማሪ ብድሮች ከፖሊሲ ባንኩ ስለመፍቀድ፣ ➽ አዳዲስ የማዕድን ፍቃዶችን ለኦሮሞ ባለሃብቶች ስለመስጠት፣ ➽ ብሔራዊ ባንክ በልዩ ሁኔታ በሚያወጣቸው የዶላር ሽያጭ ጨረታዎች ላይ ገዳ፣ ስንቄ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል፣ ኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ባንክ፣ አዋሽ፣ … ያሉ መሠረታቸው የኦሕዴድ የሆኑ ባንኮች ቀጣይነት ባለው መልኩ ጨረታውን ስለሚያሸንፉበት ሁኔታ፣ እና ➽ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ውሳኔዎችን ለመወሰን በግርማ ብሩ በኩል የውሳኔ ሃሳቦች እንደሚቀርቡ የኢትዮ 251 የመረጃ ምንጮች ያከረሱን መረጃ ያሳያል። በሌላ በኩል "ኢትዮጲያ ታምርት" በሚለው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንቅናቄ ዕቅድ ማስፈፀሚያ በጀት ላይ በኦሮሞ ባለሃብቶች በሰፊው መጠቀም የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚገመገም መረጃዎች ያመለክታሉ። የወደብ ጉዳዩም ተመሳሳይ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል። ኦሕዴድ ዋና ፍላጎቱ ሶማሊላንድን ይዞ ቀጠናውን ማተራመስ እንደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ስብሰባ በኋላ የብአዴን አመራሮች መካከል በተለይ በዞን ደረጃ ያሉትን ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል የመምታት ውሳኔ መወሰኑ ይጠበቃል። በአማራ ክልል ያለው ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ የሚወሰነው በኦሕዴድ ነው። ብአዴን እንደሕዳር አህያ የሚጭኑትን ከመቀበል ውጭ ምንም ድምፅ የለውም። በቅርቡ ዐቢይ አሕመድ ባለበት በተካሄደ አንድ ስብሰባ ላይ ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ብአዴንን በተመለከተ የተናገረው ንግግር አስቂኝ ነበር፦ "የክልሉ አመራር (ብአዴንን ማለቱ ነው) ያረጀ ጀኔረተር ማለት ነው። ያረጀ ጀኔረተር ነዳጅ ካልሰጡት ወይም ካልደበደቡት አይሰራም" ሲል ምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ተሳልቆባቸዋል። እነሱ ያረጀ ጀኔረተራቸውን ይደብድቡ፤ የወገን ጦር ፋኖ ደግሞ የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላን ሰራዊት ወደአፈር መቀላቀሉን ይቀጥላል!! ኢትዮ 251 ሚዲያ የነጻነት አንደበት